የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል
✞ ቅዱሳን ሐዋርያት ✞
አመ አመ ሰበክዎ(፪)
ቅዱሳን ሐዋርያት
ቅዱሳን ሐዋርያት - - - ሐዋርያት
የዓለም ብርሃን ናችሁ - - - ሐዋርያት
መጀመሪያ ጴጥሮስ - - - ሐዋርያት
ኋለኛው ጳውሎስ - - - ሐዋርያት
/አዝ=====
ብርሃናተ ዓለም - - - ሐዋርያት
ጴጥሮስ ወጳውሎስ- - - ሐዋርያት
በእውነት ተሰየፉ - - - ሐዋርያት
ስለ ክርስቶስ - - - ሐዋርያት
/አዝ=====
ሐዋርያት ዘርተው - - - ሐዋርያት
ሲለቅሙ በሻማ - - - ሐዋርያት
ሰዎች አትለዩ - - -ሐዋርያት
ከወንጌል አውድማ - - - ሐዋርያት
/አዝ=====
የዘላለም ሕይወት - - - ሐዋርያት
ማደስ ካማራችሁ - - - ሐዋርያት
የሐዋርያት ሥራ - - - ሐዋርያት
ይሁን አላማችሁ - - - ሐዋርያት
/አዝ=====
ውሆች ቀለም ሆነው - - - ሐዋርያት
እንጨቶች ብዕር - - - ሐዋርያት
ቢፅፉት አያልቅም - - - ሐዋርያት
የሐዋርያት ክብር - - - ሐዋርያት
/አዝ=====
ሐምሌ አምስት ቀን - - - ሐዋርያት
ማኅበራችን - - - ሐዋርያት
በክርስቶስ መስቀል - - - ሐዋርያት
ተባረከልን - - - ሐዋርያት
በጴጥሮስ ወ ጳውሎስ ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት ዘማርያን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
ታላቅ የንግሥ ጉዞ ወደ ተአምረኛው ስዕለት ሰሚ ቁልቢ ቅ/ገብርኤል ገዳም
በሐረርና ድሬዳዋ የሚገኙ ገዳማትና አድባራትን ጨምሮ
→ መነሻ ሐምሌ 17
→ መመለሻ ሐምሌ 20
→ የጉዞ ዋጋ፦ ማረፊያ ቤት እና መስተንግዶን ጨምሮ 2500
በጉዞአችን መምህራን እና ዘማርያን ተጋብዘዋል
በካህናት አባቶቻችን በመታገዝ ዘወትር ጸሎተ ኪዳን እና ምህላም ይኖረናል፡፡
ፈጥነው ይደውሉ የቀረን ጥቂት ቦታ ነው
ለበለጠ መረጃ 0922849489 ይደውሉ
ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌምም ምዝገባ ጀምረናል፡፡
✞ መጥምቁ ዮሀንስ ድንቅ ታምር ሰራ ✞
መጥምቁ ዮሀንስ ድንቅ ታምር ሰራ
ለምፃምን አነፃ እውራን አበራ
እንደ ወንጀለኛ ዮሀንስ
መታሰርህ አንሶ *
ሄሮድስ ለሰው ሰጠ *
አንገትህን ቀንጥሶ *
ተቆርጣ ብትወድቅም *
በአረማውያን ሴራ *
ወንጌል አስተማረች *
በአለም ተዘዋውራ *
/አዝ=====
ከገባው ቃል ኪዳን ዮሀንስ
አንተ ብትቀለው *
አንገትህን ቀልቶ *
በወጪት አኖረው *
አንገት ተለይቶ *
ከሌላ ሰውነት *
እንዴት ያስተምራል *
አስራ አምስት ዓመት *
/አዝ=====
እውነትን መስክረህ ዮሀንስ
መልካም ስራ ሰርተህ *
መጥምቁ ዮሀንስ *
በክብር አለፈ *
የማያወላውል *
የእምነትህ ፅናትህ *
ሆኖናል ምሳሌ *
ለአዳም ልጅ ህይወት *
የወንጌል ገበሬ የሀይማኖት አርበኛ
መጥምቁ ዬሀንስ ለምንልን ለእኛ
በወንጌልህ ትምህርት ዮሀንስ
እንዳስገነዘብከን *
ጎድጓዳውም ይሙላ *
ይቅና ጎባጣው *
ተራራውም ይናድ *
ከፍ ያለው ዝቅ ይበል *
ለክርስቶስ መንግስት *
ሁሉም ይስተካከል *
ሸንኮራ ዬሀንስ ድንቅ ታምር ሰራ
ለምጣምን አነፃ እውራን አበራ
እምነቱን አብሰን ዮሀንስ
ጠበሉን ጠጥተን *
ከስጋ ደዌያችን *
በአንተ ተፈውሰን *
ልናገር ዝናህን *
ልመስክርልህ *
የሚሰማ ሁሉ *
ይምጣ ከደጅህ *
ሸንኮራ ዬሀንስ ድንቅ ታምር ሰራ
ለምጣምን አነፃ እውራን አበራ
ዬሀንስ ታምሩን ዮሀንስ
ያደረገላችሁ *
እግዚአብሔር ይመስገን *
እንኳን ደስ አላችሁ *
እኔስ ምን ላርግለት *
ውለታው ደነቀኝ *
ለቅዱስ ዮሐንስ *
ከደዌ ለአነፃኝ *
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ሊቀ_ሰማዕት ✞
ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘልዳ
አውሬው ሳይበላኝ አዳንከኝ ሳልቀር ከሜዳ በነጩ ፈረስ አልፈህ አባቴ በበሬ
ድራጎን ጠፍቶል እኔም ቆሜያለው ከብሬ/×2
ሰማዕቱ ስልህ አፌን ሞልቼ
ስዘምርልህ ቤት ገብቼ
ያንተ ስለሆንኩ ደስ እሰኛለው
ከጠላት ዘንዶ ባንተ ድኛለው
/አዝ=====
መሞት መነሣት የድልህ ዝና
የእምነት ገበሬ ያስባለህ ጀግና
ያንተጋድሎህን ልጅህ አስቤ
ኩራት ተሰምቶት ዘለለች ልቤ
/አዝ=====
ለኔ ያደረከው ውለታህ በዛ
አይገለፅም እንዲ በዋዛ
የልቤ ደርሶ የተመኘሁት
ለቅሶና ሀዘንን ባንተ ሸኘውት
/አዝ=====
የአባቶቼ ድል አክሊላቸው
ጣርና ጋሻ ክብር ዝናቸው
ለኔም መከታ ጌጤ ኩራቴ
የተዋህዶ እንቁ ጊዮርጊስ አባቴ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ አባ ገሪማ ✞
አባ ገሪማ ፀሎትህ ትባርከኝ 2
ነፍሴ ስጋዬኔ ከሞት ታድነኝ 2
ኢያሱ እንዳቆመ በገባኦን ፀሀይ
አንተም አቁመሀል አይናችን እስክታይ
እስከምትፈፅም ወንጌሉን ፅፈህ
ፀሀይዋ አልጠለቀች ታዛ ለቃልህ
/አዝ=====
አባ በፀሎትህ ድንቅን አድርገሃል
በነግህ የዘራኸው በሰርክ ደርሶልሃል
ታምርህ ይነገር ይገለጥ ለዓለም
ባርከን ልጆችህን እስከ ዘላለም
/አዝ=====
ወንድሞችህ ሲያሙህ ሲዘብቱብህ
እጅግ ተደነቁ በፀሎትህ ሃይልህ
ድንጋይ መሰከረ እፅዋት ዘንባባ
ገረምከኒ ግሩም እያሉ ገሪማ
/አዝ=====
የጸሎት አንበሳ የቅዱሳን መሪ
ቁምልኝ ገሪማ በቅድመ ፈጣሪ
ደጅህን ልሳለም መጥቼ መደራ
ስለ ቃል ኪዳን ነፍሴን ግን አደራ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
💒 ገብርሔር ❤️
የተፈጥሮን ፀጋ ያለ ስጋት ለገዳማውያን
በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላል ብለው ሰውነታቸውን በፊቱ መከራውን ያስችሏታል!
በገጠሪቷ ኢትዮጵያ ፣ በምድረበዳ ፣ በተራራ ፣ በዋሻ እና ጉድጓድ የሚኖሩ ገዳማውያን እናቶች የተፈጥሮን ሂደት ወይም የወርአበባ እንዴት ያስተናግዱት ይሆን?
ብዙ ሴት መነኮሳይት እናቶች እና እህቶች የተፈጥሮ ሂደት ፈተናቸው ነው!
በዓታቸውን ዘግተው ስለሀገር ሰላም ሌትተቀን ለሚጸልዩ ሴት መነኮሳያት ከሰኔ 5 እስከ ሐምሌ 5 የሚቆይ ልዩ የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ተዘጋጅቷል!
ይህ ብቻ አይደለም በዚህ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘመቻ በየገዳማቱ ላሉ በአልጋ ላይ ለቀሩ አረጋውያን መነኮሳት የንፅህና መጠበቅያ ከ1000 በላይ ዳይፐር እና ለ2000 ሴት መነኮሳት የ6ወር የንፅህና መጠበቅያ ፓድ እንዲሁም ከ40 በላይ የጤና ባለሙያዎች ለእነዚሁ ገዳማውያን ነፃ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅታችንን አጠናቀናል።
ለዚህ የበረከት ጥሪ እኔ ፣ አንቺ ፣ አንተ ሁላችንም ተጋብዘናል።
በአይነት ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ ሾላ የካ ፖሊስ ጣብያ ፊትለፊት እልፍ ፀጋ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ መተው ያበርክቱ።
የህክምና ባለሞያዎች ሙያዊ እገዛችሁ ያስፈልገናል እና ኑ አብረን ገዳማውያንን እናክም።
ይህንን በጎ አላማ በገንዘብ መርዳት የምትፈልጉ
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት
1000480421209
ወይም
በአቢሲኒያ ባንክ
95999328
ደብረ ቁስቋም በማለት በመለገስ ለገዳማውያን እናቶች እህቶች እንድረስላቸው!
ለበለጠ መረጃ፡-0912920992 ፣ 0923289169 ወይም 0986348964
የተፈጥሮን ፀጋ ያለ ስጋት ለገዳማውያን
በምችሉት ቻናል ያላችሁ ሁላችሁም በአምላከ ቅዱሳን ስም እጠይቃለው ለሁሉም አድርሱልኝ
ያሬድ ፈልፈለ ማህሌት ወቅኔያተ ወጠነ
ኅብስተ መላእክቲሁ ወበውእቱ በላዕነ
አሠርገዋ በድርሰቱ ለአቅሌስያ እምነ
ያሬድ መሠረት ወጥነ ዘኢትዮጵያ ብርሃነ
ይስሐቅ ክርስቲና ፀሐይ ወልደው አክሱም
የስብሐቱ ጮራ ፈንጥቆለት ሁሉም
ጋይንትና ጸለምት ቂርቆስ ወዙርአንባ
መችቀረ ሃሌታው በዓለም አስተጋባ
አዝ ========
ዋይ ዜማ ዋይ ዜማ ዘሰማዕኩ እም ሰማይ
ዘአምጽአ ያሬድ ግዕዝ ዕዝል አራራይ
ድጓ ፆመ ድጓ ምዕራፍ መዋሥዕት
ምልክት ቀማሪ ነዋያት የእርሱ ምርት
አዝ ========
በመጀመሪያ ቃል ንባብ ብቻ ነበር
ያ ቃል ዜማ ባይሆን ያሬድ ሳይወርድ ቢቀር
ቁመቱ ባልነበር ቅዳሴ ኪዳን
ይኼን አገልግሎት ይሄን ውበት ባጣን
አዝ ===========
እንዳለ ትንቢቱም ከዓለም ተመርጠህ
የኢትዮጵያ ሰው ሆይ ያው ምግብህ ተሰጠህ
የምድሩን ዘፈን ተው በል የአርያም ዜማ
ስብሐተ ያሬድ ልበስ እንደሸማ
✞ ፃድቃኔ ማርያም ✞
ፃድቃኔ ማርያም ገዳም አምሳለ ኢየሩሳሌም/2/
ገዳም ኢየሩሳሌም/3/
/አዝ=====
የእንጦጦ ኪዳነ ምህረት
ፀበልሽ እሳት ለአጋንንት/2/
ፀበልሽ እሳት ነው ለአጋንንት/3/
/አዝ=====
ደብረ ሊባኖስ ተክልዬ
ሠላም ልበልህ ሀብትዬ/2/
ሠላም ልበልህ ሀብትዬ/3/
/አዝ=====
የሲሪንቃዋ አርሴማ
ዝናሽ በዓለም ተሠማ/2/
ዝናሽ በዓለም ተሠማ/3/
/አዝ=====
ዋልድባ ገዳም ያላችው/2/
አደራ ሳልሞት ልያችው/2/
አደራ ሳልሞት ልያችው/3/
/አዝ=====
የወይን አበባ ነው ደጅሽ
የማር ዘለላ ነው ቅጥርሽ/2/
ከማር ይጣፍጣል ለጠራው ስምሽ
ሚዛንን ይደፋል እናቴ ምለጃሽ
እኔም እልሻለው እምነ ፅዮን
በአንቺ ስለበላው የሕይወት ምግብን
/አዝ=====
የወይን አበባ ነው ደጃቸው
የማርዘለላ ነው ደጃቸው/2/
ኢትዮጵያዊው መምህር ትጉህ ወንጌላዊ
ፀጋህ ከሠማይ ነው አይደለም ምድራዊ
የተጋድሎህ ፅናት አርአያ ነው ለኛ
አባ ተክለሃይማኖት የእምነት አርበኛ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ አንድ አድርገን ✞
አንድ አድርገን ጌታ ሆይ አንድ አድርገን
ሰላምህን ፍቅርህን ለግሰን/2/
ቤተክርስቲያን ሆይ ምነው ተረበሽ
አንድነትሽ ጠፍቶ ሰላምን አጣሽ
አንደኛዉ ሲጠቅምሽ ሌላኛው ሲጎዳሽ
ብዙ ልጆች ወልደሽ የወላድ መካን ሆንሽ
/አዝ=====
በዘርና ጎሳ ስንከፋፈል
ቅጥራችን ፈረሰ በጠላታችን
መሳለቂያ ሆንን በየ አደባባዩ
ልዩነትን አይተው ብዙዎች ተለዩ
/አዝ=====
ላያችን የሚያምር ልስን መቃብሮች
አስመስለን ያለን የሐሰት አማኞች
በመካከላችን ፍቅርን አስወጥተን
እንደ ርብቃ ልጆች እንገፋፋለን
/አዝ=====
ለእምነት ያልቆመው በውሸት ሲከሰን
አንድነት ሳይኖረን ዘመንን አስቆጠርን
ያ ጥቅም ፈላጊው ስምን እያጠፋ
ለሥጋው የሚሆን ርስትን አሰፋ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ዕርገት
ዕርገት ‹‹ዐርገ›› ወጣ፣ ከፍ ከፍ አለ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ቃል ሲሆን ወደ ላይ መውጣትን ያመለክታል፡፡ የተነገረው ትንቢት የተቆጠረው ሱባኤ እና የተመሰለው ምሳሌ ይፈጸም ዘንድ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተቀበረ በሦስተኛው ቀን በሰንበተ ክርስቲያን መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል ሙስና መቃብርን ድል ነሥቶ ተነሥቷል፡፡ ከዚያም ለሐዋርት እየተገለጠ መጽሐፈ ኪዳንን አስተምሯቸዋል፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጉባኤ ሠርቶ ያስተማራቸው ሦስት ጊዜ ነው፤ እነዚህም በትንሣኤ (ዮሐ 20፥19)፣ በአግብኦተ ግብር/በዳግማይ ትንሣኤ (ዮሐ 20፥26) እና በጥብርያዶስ ወንዝ (ዮሐ 21፥1) ናቸው፡፡
በተነሣ በአርባኛው ቀን አስቀድሞ በምሴተ ሐሙስ (ሐሙስ ምሽት) እንደነገራቸው የመንፈስ ቅዱስን መምጣት አስረድቶ ባረካቸው፡፡ ከዚያም ‹‹አንትሙሰ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም እስከ ትለብሱ ኃይለ እም-አርያም›› ትርጓሜውም ‹‹እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ›› ብሏቸው እስከ ቢታንያ አውጥቶ ክህነትን በአንብሮተ እድ ሾሟቸው ዐርጓል፤ (ሉቃ 24፥50-53)፡፡ በአርባኛው ቀን ያረገበት ምክንያት አዳም በ40 ቀን አግኝቶ ያጣትን ልጅነት እንደመለሰ ለማጠየቅ ሲሆን ያረገውም ከእመቤታችን በነሣው ሥጋ ነው፡፡ ያረገበት ምክንያት ደግሞ ተለየ ተለወጠ ላሉት እንዳይመቻቸው አንድም ቅዱሳን ማረጋቸውን ገነት መንግሥተ ሰማያት መግባታቸውን ለማጠየቅ ነው፡፡
✞ ተዋህዶ ሃይማኖቴ ✞
ተዋህዶ ሃይማኖቴ
የጥንት ነሽ የእናትና አባቴ
ማህተቤን አልበጥስም
ትኖራለች ለዘላለም
የግብፅን ከተሞች በደም ገንብተናል
በመግደል ፅድቅ የለም ሞተን ግን ኖረናል
ማተብሽን ፍች በጥሽው ቢሉኝ
እኔስ ከነ አንገቴ ውሰዱት አልኩኝ
/አዝ=====
ጴጥሮስ ተሰቀለ ጳውሎስ ተሰየፈ
ተዋህዶ እያለ አረ ስንቱ አለፈ
ሌሎችም ለእሳት በስቃይ አልፈዋል
ዘመን የማይሽረው ታሪክን ፅፈዋል
/አዝ=====
ፊተኛ ነንና አንዳንሆን ኋለኛ
ህዝቤ ተነቃቃ ተነስ አትተኛ
ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን ጩኽት
የተዋህዶ ልጆች አሁንነው ሰዓቱ
/አዝ=====
አይተን እንዳላየን ስንቱን አሳልፈናል
የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል
አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር
ይገለጥ ይታወጅ የተዋህዶ ምስጢር
👉ዘማሪት_አዜብ_ከበደ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ያሬድ ካህኑ ዘመረ ✞
ያሬድ ካህኑ ዘመረ/2/
ዘመረ ያሬድ ዘመረ
አምላኩን አመሰገነ /2/
አርያም በማለት።።።።።።።፡ያሬድ ዘመረ
ማኅሌት ጀመረ።።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
ዜማውን ከመልእክት እያስተባበረ
ምስጋና አቀረበ።።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
በዜማ መሣሪያ።።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
ጸናጽል አነሳ ከበሮ መቋሚያ
/አዝ=====
በግዕዝ በዕዝል።።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
በአራራይ ዜማ።።።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
ከብሉይ ከሐዲስ ምስጢር እያስማማ
በዜማው ምልክት።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
የአምላክን መከራ።።።።።።።፡ያሬድ ዘመረ
የመስቀሉን ነገር የማዳኑን ስራ
/አዝ=====
ደሙ እየፈለቀ።።።።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
በጦር ተወግቶ።።።።።።።።።፡ያሬድ ዘመረ
ሊቁ ማኅሌታይ በመንፈስ ተቃኝቶ
በጥዑም ልሳኑ።።።።።።።።።፡ያሬድ ዘመረ
በተሰጠው ጸጋ።።።።።።።።።፡ያሬድ ዘመረ
ለንጉሥ እግዚአብሔር ለአልፋ ኦሜጋ
/አዝ=====
ድጓ ጾመድጓ።።።።።።።።።።።፡ያሬድ ዘመረ
ምዕራፍ መዋሲት።።።።።።።።፡ያሬድ ዘመረ
ምሥጢር ተገልጦለት በሰማይ መላእክት
የዜማ መሠረት።።።።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
ተንበለ ዝማሬ።።።።።።።።።።።ያሬድ ዘመረ
የኢትዮጲያ ኩራት የተዋህዶ ፍሬ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ አቤቱ እባክህ አሁን አድን ✞
አቤቱ እባክህ አሁን አድን አቤቱ እባክህ አሁን አቅና
ከጸሐይ መውጫ እስከ መግቢያው ድረስ
ምድር ትከደን በምስጋና
የተሰበረው እንዲጠገን
ደዌው እንዲርቅ ተፈውሶ
አንተን እንዲያመልክ በህይወቱ
ከኃጢአት ከበደል ተመልሶ
የባዘነውን ሰበሰብከው
የጠፋውንስ መቼ ተውከው
በቀል የማታውቅ ቅዱስ ጌታ
አንተ ብቻ ነህ ያከበርከው
/አዝ=====
በጎች ቢሞሉም በበረቱ ውስጥ
ዘጠና ዘጠኝ ቢኖሩህም
አንዱ እንደወጣ ይቅር ብለህ
እኔን መፈለግ ቸል አላልክም
ለእጆቼ አንባር ለእግሬ ጫማ
ለአካሌ አዲስ ልብስ አለበስከኝ
እድፌን አንጽተህ እንዳመሰግን አደረከኝ
/አዝ=====
ህፃን አዋቂው ያመልክሃል
ከቤቱ ነቅሎ ደጅህ መጥቶ
ቅኔ መወድስ ተቀኘልህ
ይኧው ለስምህ ክብርን ሰጥቶ
መሻቱን ብቻ ተመልክተህ
ልቡን አንቅተህ ብትፈውሰው
ጅማሬው ቢሆን ፍፃሜውም
ሁሉን አንተ ነህ ያደረከው
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ኢያቄም_ወለዳ ✞
ኢያቄም ወለዳ ኢያቄም
ዳዊት ዘመዳ ኢያቄም ወለዳ
#ትርጉም
ኢያቄም ወለዳት ዳዊት ዘመዷ ነው
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ አዕይንታ_ዘርግብ ✞
አዕይንታ /ዘርግብ/(፪) ኢያቄም ወለዳ
ኢያቄም ወለዳ (፭) ዘርግብ ኢያቄም ወለዳ (፪) እኸ (፫)
#ትርጉም:-
አይኖቿ የርግብ የመሰሉ/የሆኑ/ልጅን ኢያቄም ወለደ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ቅዱስ_ጴጥሮስ
ጴጥሮስ ማለት በግእዙ ዐለት፣ ኰኲሐ ሃይማኖት ማለት ነው፤ (ማቴ 16፥18-19
)፡፡ በአረማይክ ኬፋ ሲባል የመጀመሪያ ስሙ በእናቱ ነገድ ስም ስምዖን ተብሏል፤ ስምዖን ማለት ሰምዐኒ (ሰማኝ) ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ አባቱ ዮና ይባላል፤ ትውልዱ ከነገደ ሮቤል ሲሆን የተወለደው በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ለሐዋርያነት የተጠራው ከወንድሙ እንድርያስ ጋር ዓሣ ሲያጠምድ ነበር፤ (ማቴ 4፥18-22)፡፡
የቅዱስ ጴጥሮስ መገለጫዎች፡-
የዋህ ነበር፡- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ‹‹ጌታ ሆይ አንተስ ከሆንክ ወዳንተ እንድመጣ ፍቀድልኝ›› ብሎ በባሕር ላይ ሊሄድ ሞክሯልና፤ (ማቴ 14፥22-33)
ፈጣን ነበር፡- ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነሐሴ ሰባት ቀን ደቀ መዛሙርቱን በቂሣርያ ‹‹ሰዎች ማን ይሉኛል?›› ብሎ ጠይቋቸው ‹‹ሙሴ ነው፣ ኤልያስ ነው፣ ከነቢያት አንዱ ነው›› ይሉሃል ባሉትና እርሱም መልሶ ‹‹እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?›› ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ሐዋርያው ጴጥሮስ ፈጥኖ ‹‹የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ›› ብሎ መልሷልና፤ (ማቴ 16፥13-19)
ቁጡ ነበር፡- አይሁድ ጌታን በያዙት ጊዜ ተቆጥቶ የማልኮስን ጆሮ በሰይፍ ቆርጧልና፤ (ዮሐ 18፥10)
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ባለጸጋ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል›› ብሎ ሲያስተምር ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ ዋጋችን ምንድን ነው?›› ብሎ ጠየቀ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹እውነት እላችኋለሁ እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ›› ብሎ ከወንድሞቹ ጋር የሚያገኘውን ክብር ነግሯቸዋል፤ (ማቴ 19፥23-28)።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹ጌታዬ አትተኛምን?›› ብሎ በጠየቀው ጊዜ የዕንቁ ጽዋ ውኃ ሞልቶ ሰጠው፤ ጴጥሮስም ሳይጠጣው እንቅልፍ ያዘውና ጽዋው ከእጁ ወድቆ ተሰበረ፡፡ ሲነቃ ጽዋው ተሰብሮ ውኃው ፈሶ ቢያገኘው ደነገጠ፡፡ በዚህን ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹እኔም ይህን ዓለም የያዝሁት በእጄ ነው፤ መተኛት ማንቀላፋት ቢኖርብኝ ዓለሙ እንዲህ ተሰብሮ በጠፋ ነበር›› ብሎ መለሰለት፡፡ ዳግመኛም ‹‹እንዴት አድርገህ ትይዘዋለህ?›› ብሎ ጠየቀው፤ ከዚያም ዓለምን በመሀል እጁ ይዞ እርሱን (ጴጥሮስን) ከመሀል አድርጎ ‹‹ስምዖን ወዴት አለህ?›› ሲለው ‹‹ያለሁበትን አላውቀውም›› ብሎ መልሶለታል፤ (ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ)።
ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታን ከሁሉ አስቀድሞ ቢከተለውም በሕማሙ ጊዜ ከሁሉ አስቀድሞ ክዶት ነበር፤ በኋላ ግን በንስሐ ተመልሷል፤ (ማቴ 26፥69-75)፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዕርገቱ አስቀድሞ ‹‹በጎቼን ጠቦቶቼን ጠብቅ›› ብሎ እንደ አባት ሆኖ እንዲንከባከባቸው አደራ ሰጥቶታል፤ (ዮሐ 21፥15-19)፡፡ ከዐረገም በኋላ በ10ኛው ቀን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ የሚያውቀው ጸንቶለት የማያውቀው ተገልጾለት በአንድ ቀን ስብከት 3000 ሕዝብ አስተምሮ አሳምኗል፤ (ሐዋ 2፥41)፡፡ አንድ ቀን ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለጸሎት ወደ ምኩራብ ሲገቡ እግሩ አንካሳ ሆኖ የተወለደ ሰው ስመ እግዚአብሔር ሲጠራባቸው ‹‹ወርቅና ብር የለኝም ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ›› ብሎት ‹‹በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥና ተመላለስ›› ብሎ ፈውሶታል፤ (ሐዋ 3፥1-8)።
ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ መዲናቸው ኢሩሳሌምን አንድ ዓመት በኅብረት ካስተማሩ በኋላ ወንጌል ካልደረሰበት ለማድረስ ዓለምን በዕጣ በተከፋፈሉ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ርእሰ ሐዋርያት በመሆኑ ሮምን ደርበው ሰጥተውታል፡፡ ለሁሉ አባት በመሆኑም ሐዋርያትን ሁሉ ከሀገረ ስብከታቸው አድርሶ አለማምዶ ይመለስ ነበር፡፡ በሮም ለ25 ዓመት ከማስተማሩ አስቀድሞ በሰማርያ፣ በልዳ፣ በኢዮጴ፣ በአንጾኪያ፣ በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያና በቢታንያ አስተምሯል፡፡ በኢዮጴ ስምዖን ጫማ ሰፊውን አስተምሯል፤ ጣቢታን ከሞት አስነሥቷል፤ (ሐዋ 9፥32-42) ፣ ቆርኔሌዎስን አሳምኖታል (ሐዋ 10፥1-31)።
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በሰማርያ ሲያስተምር ሲሞን የሚባል መሠርይ ብዙ ወርቅና ብር አምጥቶ ‹‹እኔም እጄን በጫንኩበት ላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድ ተአምር እንዲደረግ አድርጉልኝ›› አለ፡፡ በዚህን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ጸጋ እግዚአብሔርን በወርቅ ትገዛለህን? ለጥፋትህ ይሁንልህ፤ በዚህ ከእኛ ጋራ ዕድል ፈንታ የለህም በጽኑ ክህደት ተይዘህ አይሃለሁና›› አለው፤ (ሐዋ 8፥9-25)፡፡ በኋላም የሲሞን ተከታዮች ትንሣኤ ሙታን የለም፣ ጌታ ነፍስ አልነሳም፣ ሕድረት እያሉ ባወኩ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ዐሥራ አንዱን ሐዋርያት፣ ሰባ ሁለቱን አርድዕት ቅዱስ ጳውሎስንና ያዕቆብን በኢየሩሳሌም ሰብስቦ (በ50ዓ.ም) በያዕቆብ ሊቀ-መንበርነት 43 አንቀጽ ያሉትን መጽሐፈ ዲድስቅልያ እንዲወስኑ አድርጓል፡፡ ከዚህም ሌላ ያስተማራቸው ምእመናን ከሃይማኖት ከምግባር እንዳይወጡ ሁለት መልእክታትን ጽፎላቸዋል፤ የመጀመሪያውን በ54 ዓ.ም በባቢሎን ሁለተኛውን ደግሞ በ60 ዓ.ም በሮም ጽፎታል፡፡
በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ኔሮን ቄሣር ጣዖት አምላኪ ስለነበር ቅዱስ ጴጥሮስን አስሮት ነበር፡፡ በመጨረሻም ኔሮን ቄሣር እንዲሰቅሉት በአዘዘ ጊዜ ሰማዕትነትን ሲቀበል ‹‹እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ›› ብሏቸው ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ ሰማዕትነት የተቀበለውም ሐምሌ 5 ቀን ሲሆን ይህ ዕለት የጾመ ሐዋርያት መጨረሻ ቀንም ሆኖ በድምቀት ይከበራል፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስ በረከት በሁላችን ላይ ይደር አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ገድለ ሐዋርያት ፣ ስንክሳር ዘሐምሌ 5
- ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ ፣ መዝገበ ታሪክ
✞ በደስታ በሀሴት ✞
በደስታ በሀሴት ዘለለ
መጥምቀ መለኮት በማህፀን ሳለ
በደስታ በሀሌት ዘለለ
የድንግል ሰላምታዋን በእናቱ ሆድ ሰምቶ
በደስታ ዘለለ ፍስሀ ተሞልቶ
ምን ያለ ድምጽ ነው እንዴት ቢያስደስተው
ዮሐንስ ማህፀን ውስጥ ደስታ ያዘለለው /2/
/አዝ=====
በመንፈስ ቅዱስ ሙላት ኤልሳቤጥ ደስ አላት
ሰላምታ አቀረበች ሰግዳ ለአምላክ እናት
የስድስት ወር ፅንሷ ድንግልን ሲሰማ
በሆዷ አወደሰ በቅኔ በዜማ /2/
/አዝ=====
ፅንሱ በማህን ሳለ የስድስት ወር
አንደበት ሆነችው እናቱ ስትዘምር
የወንጌል ሰባኪ የጌታ ምስክር
ደስታ አዘለው ለእምላክ እናት ክብር /2/
👉ዘማሪት ትንቢት ቦጋለ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ይሁዳ (የአረጋዊው ዮሴፍ ልጅ)
ይሁዳ ማለት ታማኝ ማለት ሲኾን የአረጋዊው ዮሴፍ ልጅ የያዕቆብ ወንድም ነው፤ (ማቴ 13፥55 ፣ ይሁዳ 1፥1)፡፡ ቁጥሩም ከሰባ ሁለቱ አርድዕት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ኺዱና ወንጌልን ለዓለም ሁሉ ስበኩ›› ብሎ ሐዋርያትን ያዘዛቸውን አስቦ እርሱም ልክ እንደ ሐዋርያቱ ዞሮ በማስተማር ብዙዎችን ወደ ክርስቲያንነት መልሷል፡፡ በመጨረሻም ዓላውያን ተመቅኝተው ከዝግ ቤት ጥለውት ሳለ ያስተማራቸው ምእመናን ከሃይማኖት እንዳይፋለሱ በኃጢአት እንዳይረክሱ የተግሣጽ መልእክት ጽፎ ልኮላቸዋል፤ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አንድ ምዕራፍ ያለው የያዕቆብ ወንድም የይሁዳ መልእክት የሚለው ነው፡፡ ሰኔ 25 ቀን በመስቀል ተሰቅሎ በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ በረከቱ ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ስንክሳር ዘሰኔ 25 ፣ መዝገበ ታሪክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ሕንጸተ_ቤታ_ለእግዝእትነ_ማርያም (ሰኔ 20)
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዐረገ በስምንተኛው ዓመት ቅዱስ ጳውሎስ በደማስቆ ጎዳና ኢየሱስ ክርስቶስ በብርሃን ነጸብራቅ አስደንግጦ ‹‹ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ?›› ሲል ካነጋገረው በኋላ በክርስቶስ አምኖና ምርጥ ዕቃ በመሆን የክርስትና ሃይማኖት አስተማሪ ሆኗል፤ (ሐዋ 9፥1-27)፡፡ ከዚህም በኋላ በአመነ በዐሥራ አንድ ዓመቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዐረገች በአራት ዓመት (በ53 ዓ.ም) በሁለተኛው ሐዋርያዊ ጉዞው ከበርናባስ ጋራ የኬልቄዶን ዕጣ በምትሆን በቂሳርያ ወደ ፊልጵስዬስ ገብተው በማስተማር ምእመናንን አጥምቀው ዳግመኛ ወደ ቤተ ጣዖት እንዳይሄዱ አዘዟቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ምእመናኑ ‹‹የለመድነውን ከከለከላችሁን የጸሎት ቦታ ስጡን›› ብለው ቅዱስ ጳውሎስንና በርናባስን ጠየቋቸው፡፡ እነርሱም በጥያቄአቸው ደስ ተሰኝተው ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ከወንጌላዊው ዮሐንስ ጋራ ነበርና ‹‹ያለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ በቀር ምንም የምታደርጉት የለም፤ ስለዚህ ያመኑትን ይዛችሁ አንድ ሱባዔ ጹሙ፤ እኛም እንጾማለን›› ብለው ላኩባቸው፡፡ በሱባዔው ማለቂያ ጌታ ሐዋርያትንና የሞቱትን አስንሥቶ ያሉትን ጠርቶ በሕይወተ ሥጋ በፊልጵስዬስ ሰበሰባቸው፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ ጴጥሮስን ‹‹ለምን እንደሰበሰበን ጠይቀህ ንገረን›› ብሎ ሲጠይቀው ጴጥሮስም ‹‹በምሴተ ሐሙስ የጠየቅኸው አንተ ነህና ጠይቀው›› አለው፤ ከዚያም ሲጠይቅ ‹‹በእናቴ ስም ቤተ ክርስቲያን እስከ ዓለም ዳርቻ እንዲሠራ ፈቃዴ ነውና አሠራሩን ላሳያችሁ ሥርዓት ላስተምራችሁ ነው›› አላቸው፡፡
ይህንን ብሎ ወደ ምሥራቅ ወሰዳቸውና ተራርቀው የነበሩ ሦስት ደንጊያዎችን በተአምራት አቀራርቦ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ቤተ ክርስቲያን ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውኃ በሦስት ደንጊያዎች ልጇ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እያሳያቸው ሠርተውታል፡፡ ሥራውን ሲሠሩ እንደሰም በእጃቸው ላይ እየተሳበ ቁመቱ 24 ወርዱ 12 ክንድ አድርገው በሦስት ክፍል ሠርተውታል፡፡ በማግሥቱም (ሰኔ 21 ) ኅብስት ሰማዊና ጽዋዕ ሰማያዊ ወርዶላቸው ኢየሱስ ክርስቶስ ካህን፣ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ተራዳኢ ካህን፣ እስጢፋኖስን ደግሞ ሠራኢ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸዋል፡፡ ከዚህም በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንዲህ አድርጉ›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስን እጁን ጭኖ ፓትርያርክ አድርጎ ሾሞት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ በዚህም ጊዜ መላእክትና ሐዋርያት አንድ ሆነው አመስግነዋል፡፡ ሰኔ 21 ቀን ‹‹ቅዳሴ ቤታ ለማርያም›› ተብሎ ይከበራል፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ጸሎት አይለየን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መዝገበ ታሪክ ፣ መድበለ ታሪክ
#ሊቀ_መዘምራን_ይልማ_ሀይሉ
#አልበም
ሼር_ማድረጎን_አይርሱ
👇👇👇👇👇👇
@enamsgn @mezmuredawit
@enamsgn @mezmuredawit
ስሙ በርሱ ላይ ነው
ታላቅ ስልጣን ያለው
እስራኤልን የረዳ ቅዱስ ሚካኤል ነው (2)
የሲናን ግለት ፀሐዩን ጋርዶ
ሌቱን በብርሀን መናን አውርዶ
ወደ ከነአን መራው ለረፍት
የጌታ መልዐክ ቆሞ ከፊት
ስሙ በርሱ ላይ ነው
ታላቅ ስልጣን ያለው
ድንግልን ያበሰረ ቅዱስ ገብርኤል ነው (2)
በቤተ መቅደስ ሐር ወርቅ ስትፈትል
ትንቢቱን ሰምታ ባየኋት ስትል
እግዚአብሔር ስለመረጣት
በገብርኤል ብስራት ቃል ተዋኃዳት
ስሙ በርሱ ላይ ነው
ታላቅ ስልጣን ያለው
ፈታሄ ማህፀን ቅዱስ ሩፋኤል ነው (2)
የጦቢትን ዓይን ደርሶ ያበራ
ከሞት አስጥሎ በጽድቅ የመራ
የሚቀድምልን በመንገዳችን
ሩፋኤል መልዐክ አማላጃችን
ስሙ በርሱ ላይ ነው
ታላቅ ስልጣን ያለው
የእውቀት ፅዋን ያጠጣ ቅዱስ ዑራኤል ነው(2)
በዙሪያችን ነው መሽቶ እስኪነጋ
ጭንቀታችንን እያረጋጋ
ከጠላት ወጥመድ ይታደገናል
ቅዱስ ዑራኤል ይጠብቀናል
ስሙ በርሱ ላይ ነው
ታላቅ ስልጣን ያለው
እስራኤልን የረዳ ቅዱስ ሚካኤል ነው (2)
እኔም ልበልህ ጊዮርጊስ
ፈጥነህ የምትደርስ በፈረስ
ስምክን ጠርቼ አላፍርም
ኪዳንህ ፀንቷል ዘለዓለም
የጌታ ወዳጅ ጊዎርጊስ
የአምላክ አገልጋይ ጊዎርጊስ
ሊቀ ሰማዕታት ጊዎርጊስ የፅድቅ ተዋናይ
ተጋድሎ ፍቅርህ ከአዕምሮ ረቋል
በፅኑ ዕምነትህ ደራጎን ወድቋል
አዝ =========
የልቤ ውበት ጊዎርጊስ
መዓዛ ሽታዬ ጊዎርጊስ
የከንፈሬ ጣዕም ጊዎርጊስ ዋሴ አለኝታዬ
ባለ ፈረሱ ብሩህ እውነቴ
አባቴ አንተነህ የልጅነቴ
አዝ ==========
ሀዘን መከራ ጊዎርጊስ
ህማም ቢያከሳን ጊዎርጊስ
አድገን በቤቱ ጊዎርጊስ ስንቱን እረሳን
ምንም ብንጎድፍ በኃጢያት ብንወድቅም
ከስምህ ሌላ ትምክህት አናውቅም
አዝ ============
አብሪ ኮከብ ነህ ጊዎርጊስ
የልዳ ፀሐይ ጊዎርጊስ
ዘመን ቢጨልም ጊዎርጊስ ፈክተህ የምትታይ
የጠራ ፀሐይ እንቁ ጨረቃ
ምልጃህ ጸሎትህ ለዓለም ይበቃል
አዝ ===========
ማነው በችግር ጊዎርጊስ
ያልደረስክለት ጊዎርጊስ
ቤቱን ጓዳውን ጊዎርጊስ ያልባረክለት
እንኳን ተማፅነን አርግልን ተብለህ
ዝምታን መስማት ታውቅበታለህ
አዝ ============
ለኢትዮጵያ ሀገሬ ጊዎርጊስ
ዋልታ ገበዟ ጊዎርጊስ
ሲጨንቃት እረፍት ጊዎርጊስ ብትር ምርኩዟ
ተዋጊ አባቴ ኃያል ጦረኛ
ኢትዮጵያ ሀገሬን ሁናት መዳኛ
✞ ፃድቃኔ ማርያም ✞
ፃድቃኔ ማርያም የፍቅር እናት
ከእናትም በላይ ለኔ ልዩናት
ከደጇ ሄጄ ሁሉን ሰጠችኝ
እንባዬን በእጇ አበሰችልኝ
ፃድቃኔ ማርያም የእግሬ ሰንሰለት
ፃድቃኔ ማርያም ባንቺ ተቆረጠ
ፃድቃኔ ማርያም በምልጃሽ ያመነ ከሞት አመለጠ
ፃድቃኔ ማርያም አሳርፈሽኛል
ፃድቃኔ ማርያም ከጠላት ፉከራ
ፃድቃኔ ማርያም የአማኑኤል እናት ሆነሽ ከኔ ጋራ
/አዝ=====
ፃድቃኔ ማርያም ጤናዬን አገኘሁ
ፃድቃኔ ማርያም ከደድሽ መጥቼ
ፃድቃኔ ማርያም ሰላሜ በዛልኝ አንቺን ተጠግቼ
ፃድቃኔ ማርያም አላፈርኩም እኔ
ፃድቃኔ ማርያምበምልጃሽ አምኜ
ፃድቃኔ ማርያም ይኸው እዘምራለሁ ከህመሜ ድኜ
/አዝ=====
ፃድቃኔ ማርያምበፀበል እምነትሽ
ፃድቃኔ ማርያምበሽታዬ ዳነ
ፃድቃኔ ማርያምምን ይጎልበታል ከአንቺ የታመነ
ፃድቃኔ ማርያም አልፏል መከራዬ
ፃድቃኔ ማርያም ስምሽን ስጠራ
ፃድቃኔ ማርያም ባንቺ በእናቴ ወጣው ከመከራ
/አዝ=====
ፃድቃኔ ማርያም ወደኔ አዘንብለሽ
ፃድቃኔ ማርያም ጨኸቴን ሰምተሻል
ፃድቃኔ ማርያም እመቤቴ ማርያም ፀጋ አልብሰሺኛል
ፃድቃኔ ማርያም የጠላቴ መረብ
ፃድቃኔ ማርያም ወድቋል ተበጣጥሶ
ፃድቃኔ ማርያም ገባሁ ወደቤቴ እንባዬ ታብሶ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
ሐዋርያትም ለጌታችን አምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰግደው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰዋል፤ (ሉቃ 24፥52 ፣ ሐዋ 1፥8-9)፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለከት ድምፅና በመላእክት ምስጋና ዐርጓል፤ ‹‹ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ ወእግዚእነ በቃለ ቀርን›› እንዲል (መዝ 46፥5)፡፡ ከዚያም በአብ ቀኝ በኪሩቤል ጀርባ ተቀምጧል፤ (1ጴጥ 3፥22)፡፡ ጥንተ ዕርገቱ ግንቦት 8 ቀን ሲኾን ከዚያ በኋላ ቅዱስ ድሜጥሮስ በሠራው የበዓላት ቀመር መሠረት የትንሣኤን በዓል ተከትሎ ከሐሙስ ሳይወጣ በአርባኛው ቀን አስበን እናከብረዋለን፡፡ ከጌታችን ከአምላካችንና ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት ረድኤት በረከት ያሳትፈን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፤ መድበለ ታሪክ ፣ መዝገበ ታሪክ
#አዲስ_ዝማሬ_የእኔ_አለመታመን_ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ
✞ የእኔ አለመታመን ✞
የእኔ አለመታመን ታማኝነትህን
ከቶ አያስቀረውም ፍቅር መሆንህን
ለእኔ ነው ጉድለቱ ድፍረትን ማብዛቴ
ተመልሰህ ማረኝ ሩህሩህ አባቴ
አልሻረውምና ሞትህ ንግሥናህን
በአባትህ ቀኝ አለህ ፈጽመህ ስራህን
በጽድቅ እንድኖር ነው የሞትክልኝ ለእኔ
እኔ ግን ሆኛለሁ የኃጢአት ሸማኔ
/አዝ=====
በበደል ላይ በደል ስደራርብ አይተህ
አላጠፋኸኝም ታግሰህ ታግሰህ
እኔን መጠበቅህ እስክመለስ ድረስ
ናፍቀህ ነው ወድደህ ነው መዳንን እንድወርስ
/አዝ=====
ለርኩሰት ብሰለፍ ከሰው ተደብቄ
አለህ በዙፋንህ ታየኛለህ ጽድቄ
አንተ እንደምታየኝ እኔም ወደ አንተ ልይ
አስገባኝ ከእልፍኝህ በይቅርታ ድልድይ
/አዝ=====
በበደል ላይ በደል ስደራርብ አይተህ
አላጠፋኸኝም ታግሰህ ታግሰህ
እኔን መጠበቅህ እስክመለስ ድረስ
ናፍቀህ ነው ወድደህ ነው መዳንን እንድወርስ
👉ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ያሬድ እናስታውስህ ✞
ያሬድ እናስታውስህ እናስታውስህ
እንዘክር ስምህን /2/
የተዋህዶ ልጆች ህያው ታሪክህን /4/
የኢትዮጵያ አለኝታ።።።።።እንዘክር ስምህን
ልዩ ስጦታዋ።።።።።።።።፡እንዘክር ስምህን
የተዋህዶ ዜማ ።።።።።።፡እንዘክር ስምህን
መሰረት ጣሪያዋ።።።።።።እንዘክር ስምህን
መፃሕፍትን ሁሉ።።።።።።እንዘክር ስምህን
እግዚአብሔር ገልፆልክ።፡እንዘክር ስምህን
ብሉይና ሃዲስን።።።።።።።እንዘክር ስምህን
አስተባብረክ ቃኘክ።።።።።እንዘክር ስምህን
/አዝ=====
በኤዶም ገነት ውስጥ።።፡እንዘክር ስምህን
ወፎች ተልከው።።።።።።።እንዘክር ስምህን
በስላሴ አምሳል።።።።።።።እንዘክር ስምህን
ሶስት ሆነው መጥተው።።እንዘክር ስምህን
በሰዎች አንደበት።።።።።።እንዘክር ስምህን
እያናገሩህ።።።።።።።።።።።እንዘክር ስምህን
የመላዕክት ዜማ።።።።።።፡እንዘክር ስምህን
ላንተ አቀበሉህ።።።።።።።።እንዘክር ስምህን
/አዝ=====
የመስቀል ምሳሌ።።።።።።።እንዘክር ስምህን
መቋሚያህን ይዘህ።።።።።፡እንዘክር ስምህን
ፅናፅል ከበሮ።።።።።።።።።።እንዘክር ስምህን
በአንድነት አስማምተህ።።።እንዘክር ስምህን
ወረብ ስትወርብ።።።።።።።።እንዘክር ስምህን
በሽብሸባ ደምቀህ።።።።።።፡እንዘክር ስምህን
ያሬድ አባታችን።።።።።።።።።እንዘክር ስምህን
ልዩ ነው ዝማሬህ።።።።።።።፡እንዘክር ስምህን
/አዝ=====
እንደ መላዕክቱ።።።።።።።።፡እንዘክር ስምህን
ስትዘምር አይተው።።።።።።።እንዘክር ስምህን
አፄ ገብረመስቀል።።።።።።።፡እንዘክር ስምህን
በተመስጦ ሆነው።።።።፡።።።እንዘክር ስምህን
ባንድ እግርህ መሃል ላይ።።።እንዘክር ስምህን
ሲወጉህ በጦር ።።።።።።።።።እንዘክር ስምህን
ደምህ እየፈሰሰ።።።።።።።።።እንዘክር ስምህን
ትዘምር ነበር።።።።።።።።።።።እንዘክር ስምህን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ቅዱስ_ያሬድ
የቅዱስ ያሬድ ሐገረ ትውልድ ከካሕናተ አክሱም ወገን ነው፤ አባቱ አብዩድ ወይም ይስሐቅ ይባላል፤ እናቱም ክርስቲና ወይም ታውክልያ ትባላለች። ቅዱስ ያሬድ በ 505 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ተወለደ። እግዚአብሔር ሥራውን ሊሠራበት የመረጠው ቅዱስ ሰው ነውና ለወደፊት በእርሱ አማካይነት የሚሰራውን ሥራ ለመግለጽ ስለፈለገ በወላጆቹ አድሮ ከአዳም ስድስተኛ ትውልድ በሆነው በስድስተኛው ሰው በመላልኤል ልጅ በያሬድ ስም “ያሬድ” ተብሎ እንዲጠራ አደረገ። (ዘፍ 5፥15)
ያሬድ ማለት ርደት፣ ወሪድ ማለትም መውረድ ማለት ነው፤ በቀዳማዊው ያሬድ ጊዜ ደቂቀ ሴት ከደብር ቅዱስ ወደ ደቂቀ ቃየል ወደ ምድረ ፍዳ ስለወረዱ ያንን ለማስታወስ አባቱ መላልኤል ያሬድ ብሎታል፤ “ወጸውዐ ስሞ ያሬድሃ እስመ በመዋዕሊሁ ወረዱ መላእክተ እግዚአብሔር ውስተ ምድር እለ ተሰምዩ ትጉሃነ” መጽ. ኩፋሌ 5፥21፤ ትርጓሜውም ስሙን ያሬድ ብሎ ጠራው በእርሱ ዘመን ትጉሃን ተብለው የሚጠሩ የእግዚአብሔር መላእክት (ደቂቀ ሴት)ከደብር ቅዱስ ወደ ምድረ ፍዳ ወርደዋልና ማለት ነው።
በኢትዮጵያም ዳግማዊ ያሬድ በስድስትኛው መቶ ክፍለ ዘመን ተነሥቶ ሰማያዊውን ልዩ ጣዕመ ዜማ ወደ ኢትዮጵያ የሚያወርድ ነውና ይህንን ለመግለጽ እግዚአብሔር በአባቱና በእናቱ አድሮ ያሬድ እንዲባል አድርጎአል፤ ምስጢሩ ልዩ ጣዕመ ዜማን ከሰማይ የሚያወርድ መሆኑን ያሳያል።
ቅዱስ ያሬድ አባቱ አብዩድ በሕጻንነቱ ስለሞተበት እናቱ ታውክልያ በሃይማኖት ኰትኩታ በፈሪሃ እግዚአብሔር አሳደገችው፤ ሕጻኑ ያሬድ በሰባት ዓመቱ ትምህርት እንዲማር የአክሱም ቤተ ጉባኤ (ቤተ ቀጢን)መምህር ወደ ነበረው ወደ ጌዴዎን ወሰደችውና ትምህርት መማሩን ቀጠለ፤ ጌዴዎን የታውክልያ ወንድም ስለነበረ የሕጻኑ ያሬድ አጎት ነበረና በቅርብ እየተከታተለ ያስተምረው ነበረ። ሆኖም ትምህርት አልገባ ብሎት 7 ዓመት ተጉላላ፤ በዚህም ምክንያት ከዕለታት በአንድ ቀን አጎቱ (መምህሩ) ጌዴዎን ተናዶ ክፉኛ ገረፈው፤ ሕጻኑ ያሬድም ተበሳጭቶና ተስፋ ቆርጦ ከአክሱም ከተማ ወጥቶ ወደ እናቱ መንደር ወደ መደባይ ወለል(ከአክሱም ወደ ሰሜን አቅጣጫ) ሲጓዝ ማይ ክሬዋሕ “ማይ ኪራሕ” ከምትባል የውኃ ምንጭ ዳር ተቀምጦ ሲያዝንና ሲያለቅስ እግዚአብሔር አንድ የሚያጽናና ምልክት አሳየው።
ይህም ክሬዋሕ (በትግርኛ ክራውሕ) ከሚባል ዛፍ ሥር በውኃው ምንጭ ዳር ተቀምጦ ወደ ዛፍዋ ሲመለከት አንድ ትል የዛፍዋን ፍሬ ለመመገብ ሽቶ ወደላይ እየወጣና እየወደቀ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በሰባተኛው ጊዜ ወጥቶ ፍሬዋን ሲመገብ ተመለከተ፤ ተመራማሪው ተማሪ ያሬድ ከዚህ ትል ጥረትና ስኬት ትምህርት ወስዶ እኔም እኮ ተስፋ ሳልቆርጥ ብዙ ጥረት ካደረግሁ እንደዚህ ሊሳካልኝ ይችላል ብሎ በተስፋ ተጽናንቶ እንደገና ወደ መምህሩ በመመለስ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ። ከዚህ በኋላ ወደ መደባይ ወለል የነበረውን ጉዞ ሠርዞ መልስ ወደ አክሱም ከተማ ወደ መምህር ጌዴዎን ጉባኤ ቤት ሆነ፤ መምህሩ ጌዴዎንም ተቀብሎ ማስተምሩን ቀጠለ። በዚህ ጊዜ ሕጻኑ ያሬድ ለብዙ ጊዜ አልገባ ያለውን ትምህርት በአጭር ጊዜ የግብረ ዲቁና ትምህርቱን አጠናቆ የታላቋ የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ጥሩ አገልጋይ ዲያቆን ሆነ፤ ትምህርቱንም በስፋት ስለቀጠለበት የመጻሕፍተ ብሉያትና የመጻሕፍተ ሐዲሳት ተርጓሚና ሊቅ ሆነ።
እግዚአብሔር አንድ ትልቅ የሆነ ሥራን ለመሥራት በፈልገ ጊዜ ለሥራው መገለጫ በሆኑ ሰዎች ላይ መጠነኛ ፈተና ማሳየት ልማዱ ነው። ለሣራ፣ ለኤልሳቤጥና ለቅድስት ሀና እንዲሁም ዕውር ሆኖ ለተወለደው ሰው ያደረገው ሁኔታ ይህንን ያረጋግጣል። ይኸውም ለሣራ ይስሐቅን ያህል ልጅ፣ ለኤልሳቤጥ ዮሐንስን ያህ ልጅ፣ ለሀናም ድንግል ማርያምን ታህል ልጅ ለመስጠት በፈልገ ጊዜ በመጀመሪያ በመካንነት ለብዙ ጊዜ እንዲቆዩ አድርጓል፤ የኋላ ኋላ ግን ሙቀት፣ ልምላሜና አበባ ቢለያቸው በከሃሊነቱ ልጆችን ወልደው እንዲታቀፉ አድርጓቸዋል። ዘፍ 18፥10_14፣ ሳሙ.ቀዳ 1፥2¬_8፣ ሉቃ 1፥9። ዕውር ሆኖ የተወለደው ሰውም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ካደረገ በኋላ በከሃሊነቱ የዓይን ብርሃንን ሰጥቶታል፤ ይህም ለምን ዕውር ሆኖ እንደተወለደ በደቀ መዛሙርቱ ለቀረበለት ጥያቄ ጌታችን ሲመልስ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው ሲል ገልጾአል። ዮሐ 9፥1_9
እንደዚህም ሁሉ የቅዱስ ያሬድ ትምህርት አልገባ ብሎት ለብዙ ጊዜ መጉላላት ነሽም፣ ገላጭም፣ ሰጭም እርሱ መሆኑን ለመግለጽ የተጠቀመበት ሁኔታ ነው። ይህ ብቻም አይደለም ቅዱስ ያሬድ ከመጀመሪያ ጀምሮ ዐዋቂና ትምህርት ተቀባይ ተማሪ ቢሆን ኖሮ ሰዎች የተገለጸለት ዜማንም ካለው የቆየ ዕውቀት እንደተገኘ አድርገው ይገምቱ ነበር፤ ነገር ግን የፊደል ቆጠራን ብዙ ዓመታት የወሰደበት ቅዱስ ያሬድ እንደገና እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ ከፍተኛ ሊቅና የዜማ ደራሲ ሆኖ መገኘት የእግዚአብሔር ከሃሊነትና ሰጭነት በተጨባጭ የሚያስረዳና የቅዱስ ያሬድ ዜማም በሥጋዊ ዕውቀት የተገኘ ሳይሆን በእግዚአብሔር ገላጭነት የተገኘ መሆኑን የሚገልጽ ነው። እግዚአብሔርም መታሰቢያ ሊያቆምለት በወደደ ጊዜ ከገነት ሦስት ወፎችን ልኮለት በሰው ቋንቋ ተነጋገሩትና ወደ ኢየሩሳሌም ሰማዊት አወጡት፡፡ በዚያም የ24ቱን ካህናተ ሰማይ ማኅሌት ተማረ፤ ተመልሶም ኅዳር ሦስት ቀን በአክሱም ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሃሌ ሉያ ለአብ፣ ሃሌ ሉያ ለወልድ ፣ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ›› ብሎ አመሰገነ፡፡
ቅዱስ ያሬድ በግእዝ፣ በዕዝልና በአራራይ ዜማ የደረሳቸው ድርሰቶች አምስት ሲሆኑ እነዚህም፡-
#ሀ. ድጓ #ለ. ጾመ ድጓ #ሐ. ምዕራፍ #መ. ዝማሬ #ሠ. መዋሥዕት ናቸው፡፡
በተጨማሪም 13ቱንም ቅዳሴያት በዜማ፣ አንቀጸ ብርሃን፣ አእጋረ ፀሐይ፣ መጽሐፈ ብርሃንና ሌሎችንም ድርሰቶች ደርሷል፡፡
የቅዱስ ያሬድ የዜማ ምልክቶች ስምንት ናቸው፤ እነዚህም፡- ድፋት፣ ኺደት፣ ቅናት፣ ይዘት፣ ቁርጥ፣ ጭረት፣ ርክርክ እና ደረት ሲሆኑ ሁለቱ የዜማ ምልክቶች ማለትም ድርስ እና አንብር በኋላ በተነሡ ሊቃውንት የተጨመሩ ናቸው፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን ቅዱስ ያሬድ በጾመ አርብዓ በምኩራብ ሰሞን ስለምናኔው እያሰበ ሲዘምር ዐፄ ገብረ መስቀል ዜማውን እያዳመጠ እንደርሱ አዜማለሁ ብሎ በትረ መንግሥቱ በቅዱስ ያሬድ እግር ላይ ተተክሎበታል፡፡ ከእግሩ ስለፈሰሰው ደም ዋጋ የምትፈልገውን ለምነኝ ባለው ጊዜ ‹‹ወደ ገዳም ኼጄ እንድመነኩስ አሰናብተኝ›› አለው፡፡ ይህን በሰማ ጊዜ ንጉሡ ቢያዝንም እንዳይከለክለው መሐላውን ፈርቶ አሰናበተው፡፡
ከዚያም ወደ ብዙ ገዳማት በመኼድ በጾም በጸሎት ተወስኖ ሥጋወን እያደከመ ኖረ፡፡ በዚህ ሁኔታ በምናኔ ሰሜን ውስጥ ደብረ ሐዊ ከተባለው ተራራና ጫካ ብዙ ዓመታትን ካሳለፈ በኋላ ግንቦት 11 ቀን ከዚህ ዓለም ተለየ ወይም ተሠወረ። በዚህ ዓለም የኖረበት ጠቅላላ ዕድሜው 71 ዓመት ነው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ታሪክ ከልደተ ክርስቶስ እስከ 2000ዓ.ም ፣ መድበለ ታሪክ
✞ በንጹ ደሙ ✞
በንጹ ደሙ ያዳነን
ከወደቅንበት ያነሳን/2/
ብዙ ነው የርሱ ውለታ
እንዘምራለን ለጌታ
ቀና ብለናል በክብር
አንገቱን ደፍቶ በፍቅር
ስለእኛ ብዙ ሆነልን
የብርሀን አክሊል ደፋልን
"የአለም መድኃኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው/2/
/አዝ=====
እርቃኑን ሆኖ ሸለመን
እየደከመው አቆመን
እርሱ በመስቀል ሲሞት
እኛ ተጻፍን በህይወት
"የአለም መድኃኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው/2/
/አዝ=====
እስከ ሺ ትውልድ ይምራል
ፍቅር ነውና ይራራል
አይዝልም የርሱ ትከሻ
መጨረሻ ነው መድረሻ
"የአለም መድኃኒት ጌታ ነው
ጠላታችንን ያሰረው/2/
/አዝ=====
በደም ያጌጠ ልብስ አለን
ከአማልክት ማንም ማይመስለን
ትውልዱ ማዳኑን ይስማ
ነግሷል በጽዮን ከተማ
"የአለም መድኃኒት ጌታነው
ጠላታችንን ያሰረው/2/
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ የምሥራች ✞
የምሥራች ተወለደች እሰይ እሰይ
የአምላክ እናት(፪)የመድኃኔአለም(፪)
ተወለደች ድንግል ማርያም
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ዮም ፍስሐ ኮነ ✞
ዮም /ፍስሐ ኮነ/(፪)
በእንተ ልደታ ለማርያም
በባርነት ሳለን - - - ፍስሐ ኮነ
ኃጢአት በአለም ነግሳ - - - ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ - - - ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ - - - ፍስሐ ኮነ
እግዚአብሔር መረጠሸ - - - ፍስሐ ኮነ
ልትሆኚው እናቱ - - - ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ - - - ፍስሐ ኮነ
የዳዊት ትንቢቱ - - - ፍስሐ ኮነ
/አዝ=====
የሔዋን ተስፋዋ - - - ፍስሐ ኮነ
የአዳም ዘር ህይወት - - - ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሐና - - - ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት - - - ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድኂን - - - ፍስሐ ኮነ
ኪዳነምህረት - - - ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች - - - ፍስሐ ኮነ
የጌታዬ እናት - - - ፍስሐ ኮነ
/አዝ=====
በሔዋን ምክንያት - - - ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም - - - ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው - - - ፍስሐ ኮነ
በድንግል ማርያም - - - ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል - - - ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ - - - ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለችና - - - ፍስሐ ኮነ
የአለም ሁሉ ተስፋ - - - ፍስሐ ኮነ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ