mezmuredawit | Unsorted

Telegram-канал mezmuredawit - ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

28629

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Subscribe to a channel

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ የሐና ልጅ ነሽ ✞

የሐና ልጅ ነሽ የኢያቄም በረከት /2/
ድንግል ድንግል ወለዲተ ቃል

የሐና ልጅ ነሽ    የፀሐይእናቱ
የሐና ልጅ ነሽ   ድንግል የምሥራቅ ደጅ
የሐና ልጅ ነሽ   ቅድስተ ቅዱሳን
የሐና ልጅ ነሽ   የፍጥረት አማላጅ
የሐና ልጅ ነሽ   ለእናቷ አንዲት ናት
የሐና ልጅ ነሽ   ለወለደቻት
የሐና ልጅ ነሽ   የኢያቄም ስጦታ
የሐና ልጅ ነሽ    ምሣሌ የሌላት

          /አዝ=====

የሐና ልጅ ነሽ   የጾም ጸሎት ፍሬ
የሐና ልጅ ነሽ   የቅድስና ሀብት
የሐና ልጅ ነሽ   ከአምላክ የተሰጠች
የሐና ልጅ ነሽ   ንጽሕት እመቤት
የሐና ልጅ ነሽ   ደመና በመሆን
የሐና ልጅ ነሽ   ሕዝብን የጋረደች
የሐና ልጅ ነሽ   የኢያቄም በረከት
የሐና ልጅ ነሽ   ድንግል ማርያም ነች

          /አዝ=====

የሐና ልጅ ነሽ   በሊባኖስ አድባር
የሐና ልጅ ነሽ   ዛሬ ደስታ ሆነ
የሐና ልጅ ነሽ   መላእክት ዘመሩ
የሐና ልጅ ነሽ   እርቅም ተወጠነ
የሐና ልጅ ነሽ   እኛም ደስ ይበለን
የሐና ልጅ ነሽ   መዳናችን ቀርቧል
የሐና ልጅ ነሽ    ከሐና ከኢያቄም
የሐና ልጅ ነሽ    ንጹሕ ዘር ተገኝቷል

          /አዝ=====

የሐና ልጅ ነሽ   የሰላምብሥራት ነሽ 
የሐና ልጅ ነሽ   የፍጥረታት ተስፋ
የሐና ልጅ ነሽ   ምክንያት አንቺ ሆነሽ
የሐና ልጅ ነሽ   መርገማችን ጠፋ
የሐና ልጅ ነሽ   እግዚአብሔር ታረቀን
የሐና ልጅ ነሽ   ዓለም ሁሉ ዳነ
የሐና ልጅ ነሽ   ሞት ተሸነፈና
የሐና ልጅ ነሽ   ህይወት ለኛ ሆነ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit   ❖
❖   @mezmuredawit   ❖
❖   @mezmuredawit   ❖
✥   ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተወለደችልን ✞

ተወለደችልን ድንግል ማርያም
ነቢያት ትንቢት ሕይወተ አዳም(፪)

ሐና እና ኢያቄም በጸሎት ሲተጉ
የአምላክን ስጦታ ፀንተው ሲፈልጉ
በሕግ በሥርዓት ሆነው ሲማልዱ
የጸሐይን እናት ሰማይን ወለዱ

            /አዝ=====

አባቶች ነቢያት ያደረጓት ተስፋ
ምልክት የሆነች በሞት እንዳንጠፋ
የቀረችልን ዘር የአምላክ መገኛ
የሕይወት ውሃ ምንጭ ተወለደች ለእኛ

            /አዝ=====

የጥል ምክንያት ብትሆን ሔዋን
በድንግል መወለድ እርቅ ሆነልን
ለአዳም ዘር ሁሉ መድኃኒት ናትና
እናቱን የሰጠን ይድረሰው ምስጋና


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
        #ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ
   ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት ነው፡፡ አባቱ ዞሮንቶስ (አንስጣስዮስ) የቀጰዶቅያ ሀገር መስፍን ሲሆን እናቱ ቴዎብስታ (አቅልሲያ) ደግሞ ከፍልስጤም ሀገር ናት፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሀገሩ ልዳ ሲሆን ማርታ እና እስያ የሚባሉ ሁለት እህቶች ነበሩት፡፡ ዐሥር ዓመት ሲሆነው አባቱ  ስላረፈ ሌላ መስፍን ተሾመ፤ ይህ የተሾመው መስፍን ደግ ክርስቲያናዊ ነበርና ከቤቱ ወስዶ እያስተማረ አሳደገው፡፡ እርሱም ፈረስ መጋለብ ቀስት መወርወር ለመደ፤ ጦር ሜዳ ወጥቶ ከጠላቶቹ መሀል ገብቶ እኔ የክርስቶስ ወታደር መጣሁባችሁ ሲላቸው ደንግጠው ይሸሹ ነበር፡፡
   ሃያ ዓመት ሲመላው መስፍኑ የ15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እርሷን አግብቶ ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ጌታ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ኀዘኑን ጨርሶ ቤሩት ኼደ፡፡ ቤሩት በኢያሪኮ ዳርቻ ያለች ጽኑ ሀገር ስትሆን ሰዎቿ እግዚአብሔርን የማያውቁ ደራጎንን የሚያመልኩ ሴት ሴት ልጆቻቸውንም እየገበሩለት የሚኖሩ ነበሩ፡፡ ልጆቻቸውን ሰጥተው ቢጨርሱ ሹሙን ልጆቻችንን ሰጥተን ጨረስን፤ ሚስቶቻችንን እንዳንሰጥ ያለእነርሱ መኖር አይቻለንም፤ ካልሰጠነው ደግሞ ይፈጀናል ስለዚህ ወደ ሌላ ሀገር እንኼዳለን ባሉት ጊዜ እኔም ልጄን እሰጣለሁ ሀገራችሁን ትታችሁ አትኺዱ አላቸው፡፡ ጊዜውም ሲደርስ የሹሙን ልጅ ወስደው ከግንድ አሰሩለት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዚያ ሲያልፍ  የልቅሶዋን ድምጽ ሰምቶ ‹‹ምን ሆነሻል?›› ብሎ በጠየቃት ጊዜ ‹‹ለአምላካችን ለደራጎን ተሰጥቼ ነው›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹አምላካችሁ ወዴት አለ?›› አላት፡፡ ምግቡን ሊፈልግ ኼዷል፤ ሲመጣ ይተናኮልሀልና ፈጥነህ ኺድ ባለችው ጊዜ ‹‹እኔማ ምን ኃይል አለኝ?! ከእኔ ጋር ያለው ግን እርሱ ያሸንፈዋል›› አላት፡፡ ይህን ሲነጋገሩ ደራጎን ምድሪቱን እያነዋወጠ መጣ፤ ሊበላው ሲቀርብ ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ ሲያማትብበት በላዩ ያደረ ሰይጣን እንደ ጉም ተኖ እንደ ትቢያ በኖ ጠፋ፤ ኃይሉ ደከመ፡፡ አንገቱን ልጅቷ በታሠረችበት ገመድ አሥሮ እሷ እየጎተተች እርሱ በፈረስ ሆኖ ከተማ ሲደርሱ ሕዝቡ ሊያስፈጀን ነው ብለው ሲሸሹ አጽናንቶ መለሳቸው፡፡ አምላካችንን ለምን አመጣህብን ባሉት ጊዜ ‹‹ይህ ራሱን እንኳ ማዳን አልተቻለውም እንደምን አምላካችሁ ይሆናል?›› አላቸው፡፡ እነርሱም አምላካችንን አንተውም አሉ፤ እንዲህ ካላችሁማ ለቅቄ አስፈጃችኋለሁ ሲላቸው ይህስ አይሁን፤ ባይሆን ከገደልከው በአምላክህ እናምናለን አሉት፡፡ ከዚያም ከከተማ አውጥቶ በጦር ወግቶ ገደለው፤ ይህንንም አይተው በእግዚአብሔር ስም አምነው ተጠምቀዋል፡፡ እነርሱም አውሬውን ከገደለበትና ከመሀል ከተማ ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ሠርተዋል፡፡
   በዚህ ጊዜ የፋርሱ ንጉሥ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ይሰግድ ያሰግድ ነበረ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የአባቴን ምስፍና ተቀብዬ ልምጣ ብሎ እጅ መንሻ ይዞ ብላቴኖች አስከትሎ ቢኼድ ሃይማኖታችሁን ካዱ ለጣዖት ስገዱ ብሎ አውጆ ሕዝቡም ለጣዖት ሲሰግዱ አገኘ፡፡ ለአምልኮተ እግዚአብሔር ቀናዒ ነበርና አዘነ፤ ወርቅ ብሩን ለነዳያን መጽውቶ ብላቴኖቹን አሰናብቶ ነገሥታቱ ከተሰበሰቡበት ገብቶ ‹‹አነ ውእቱ ክርስቲያናዊ ወአአምን በእግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ›› ትርጓሜውም ‹‹እኔ ክርስቲያን ነኝ፤ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስም አምናለሁ›› አለ፡፡ ዱድያኖስ ‹‹ሦስት ዓመት ሙሉ ሃይማኖታችሁን ካዱ ለጣዖት ስገዱ ስል እንዲህ ያለኝ አንድ እንኳ የለም፤ ለመሆኑ የማን ልጅ ነህ? ሀገርህስ ወዴት ነው?›› አለው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ‹‹ከእኔ ጋር ምን ኅብረት አለህና አባቴን ሀገሬን ትጠይቀኛለህ?›› አለው፡፡ ሌሎች ያወቁት ነበሩና የዞሮንቶስ መስፍነ ልዳ ልጅ ነው አሉት፡፡ አንተማ የእኛ ወገን ነህ፤ በዐሥር አህጉር ላይ እሾምሃለው የእኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ ሲለው ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክድም አለው፡፡ ተቆጥቶ በእንጨት አሰቅሎ ሥጋውን በመቃጥን አስተፈተፈው፤ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶ ኺድ አለው፡፡ ችንካሮቹ እግሮቹን በሳስተው ወጡ፣ ደሙ እንደ ውኃ ፈሰሰ፣ አጥንቱ ደቀቀ፤ መኼድ አቅቶትም አጎንብሶ ኼዷል፡፡ መከራው ቢፀናበት ‹‹ይህን ከሀዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ›› ብሎ ወደ ጌታው አመለከተ፡፡ በዚህም እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤልን ልኮ ፈውሶታል፡፡  ከዚያም ኼዶ አንተ ከሀዲ እፈር ባለው ጊዜ በሰባ ችንካር አስቸንክሮ፣ በእሳት አስተኩሶ፤ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡ እርሱም የማይሞት ሆነ፤ ሥጋውን በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነሰነሰሰበት ተቆራርጦም ወደቀ፡፡ ከዚያም ከዝግ ቤት አስገብተው ትተውት ኼዱ፤ በመንፈቀ ሌሊት ጌታ በእጁ ዳስሶ አስነስቶ ‹‹ገና ስድስት ዓመት ስለ ስሜ ትጋደላለህ ሦስት ጊዜ ትሞታለህ በአራተኛው ታርፋለህ›› አለው፡፡ ሲነጋም ከንጉሡ ዘንድ ኼዶ ‹‹አንተ ከሀዲ እፈር አምላኬ አዳነኝ›› አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሥ ዱድያኖስ ‹‹በሥራይ የሚያሸንፍልኝ ባገኝ ቤቱን በወርቅ እመላለታለሁ›› አለ፡፡ አትናስዮስ የተባለ መሠርይ መጥቶ ‹‹ንጉሥ ሺህ ዓመት ንገሥ ጠላትህ ይደምሰስ›› ሲለው በምን አውቀዋለሁ? አለው፡፡ መሠርይውም የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው፡፡ እርሱም ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኘ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንቋዩ ማረኝ ብሎ ከእግሩ ወድቆ መመለሱን አይቶ የቆመባትን መሬት በእግሩ ረግጦ ውኃ አፍልቆ ወደ ጌታ ቢያመለክት ሐዋርያው ቶማስ በአካለ ነፍስ መጥቶ አጥምቆት ጥር 23 ቀን አንገቱን ለሰይፍ ሰጥቶ በሰማዕትነት ዐርፏል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስን ግን በመንኮራኩር አስፈጭቶ ከጥልቅ ጉድጓድ ጥለውት ደንጊያ አትመውበት ተመልሰዋል፡፡ ጌታ የተፈጨ ሥጋውን በእጁ ዳስሶ መንፈሱን መልሶ አንስቶታል፡፡
   ከዚያም አሕዛብን እያስተማረ ከንጉሥ ቀርቦ ‹‹አንተ መስህት እፈር አምላኬ ከሞት አነሳኝ›› አለው፡፡ ንጉሡም ተበሳጭቶ በብረት አልጋ አስቸንክሮ ከበታቹ እሳት አንድዶበታል፤ እሳቱም ደሙ ቢነጥብበት ድርግም ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ‹‹ክርስቶስ አምላክ ነው ትላለህ ምን አድርገህ ታሳየናለህ?›› አሉት፡፡ የለመለሙትን ዕፅዋት አድርቆ የደረቁትን አለምልሞ ከሞቱ 430 ዘመን የሆናቸውን ሙታንን አሥነስቶ አሳይቷቸዋል፡፡ በረሃብ በጥም ይሙት ብሎ የሚላስ የሚቀመስ ከሌላት ድኃ መበለት ቤት እንዲታሠር አዘዘ ከምሶሶው ጋርም አሠሩት፡፡ ራበኝ አብይኝ ባላት ጊዜ የምትሰጠው ብታጣ ወደ ደጅ ወጣች፡፡ ስትመለስ የታሠረበት ምሶሶ ለምልሞ 15 ክንድ ያህል ከጣራው አልፎ፣ ካጠገቡ እንጀራ የተመላ መሶብ ተቀምጦ እህሉ ዘይቱ በየዕቃው መልቶ አገኘች፡፡ እርሷም ‹‹የገሊላውያን አምላክ ሰው መስሎ ከሰማይ ወርዶ ከቤቴ ገብቷል›› አለች፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም አገልጋዩ እንጂ እርሱን (አምላክ) አይደለሁም አላት፡፡ መበለቲቷ ጆሮው የማይሰማ፣ ዓይኑ የማያይ፣ አፉ የማይናገር ሐንካሳ ልጅ ነበራት፤ ሰው እንዳያየውም ሸሽጋ ታኖረው ነበር፡፡ አምጥታ የቅዱስ ጊዮርጊስን አካል ብታስነካው ዓይኑ በርቶለታል፤ ጌታዬ ጆሮውንም፣ አፉንም ፈውሰው አለችው፡፡

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ጉባኤ አቅሌስያ

    የእግዚአብሔር ፍቅር የበዛላችሁ የሊቀ መላእክቱ የቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ሆይ እነሆ በጎ ስራ በመስራት እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኝበት ጊዜ ደረሰ።

    በማዕከላዊ ጎንደር በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው የሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከፍተኛ የሆነ የህልውና ችግር አጋጥሞታል።
    
      ስለክርስቶስ ስም ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ ገዳማውያን አበው መነኮሳት እና መነኮሳይት ከማይታየው ፣ ከማይዳሰሰውና ከማይጨበጠው ጠላታችን ጋር በፆም በፀሎት  ሲዋጉልን በአለም ከሚገጥማቸው ችግር ደግሞ ልናግዛቸው የመንፈስ ልጆቻችሁ አለን ልንላቸው ይገባናል።

     ስለሆነም ገዳሙ ከቁስቋም ቅድስት ማርያም መንፈሳዊ ማህበር ጋር በመተባበር ግንቦት 6 ቀን  2015 ዓ.ም ታላቅ የሆነ ጉባኤ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዮኒቨርስቲ አራተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ አዘጋጅቷል።
   

    በዕለቱም ትምህርተ ወንጌል

    1- መምህር ጳውሎስ መልከዐ-ሥላሴ
    2- መጋቢ ሀዲስ እሸቱ አለማየዉ
    3-መምህር አንተነ አበበ እና ሌሎች መምህራን

    እንዲሁም  በዝማሬ
      1- ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
      2- ዘማሪት ሲስተር ሊድያ ታደሰ እና ሌሎችም የሚቀርብ ሲሆን

የተለያዩ የኪነጥበብ ስራዎችም በተለያዩ አርቲስቶች
    1-አርቲስት ቸርነት ፍቃዱ እና ሌሎችም ይቀርባል


ኑ የወንጌል ማዕድ እየተቋደስን ስለኛ የተራቡ ገዳማውያንን አለን እንበላቸው።

ለበለጠ መረጃ:-0986348964 ወይም 0912779749

ገዳሙን ድጋፍ ማረግ ለምትፈልጉ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ 1000442598391 ሙት አንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል ገዳም 

ወዳጄ ሆይ የቅዱሳን ገዳማውያን ገድልና የህወታቸው ኑሮ ለሁሉም መልካም ምሳሌና አርአያ ሊሆን ይችላል ።

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ስምሽን ስጠራው ✞

ስምሽን ስጠራው ድንግል
ስምሽን ስጠራው ማርያም
ለአንደበቴ ማር ነው ለልቤ ሰላም
ስምሽን ስጠራው ድንግል


ትውልድ ነኝና ልጅሽ የፈጠረኝ
ድንግል እመቤቴ ላንቺ ምስጋና አለኝ
በፈቃደ እግዚአብሄር በአባቶችሽ ጸጋ
ሰአሊለነ እላለሁ ሲመሽም ሲነጋ

           /አዝ=====

በጠየክሽው ጊዜ ወይኑን እንዲሞላ
አክብሮሻልና በቃና ገሊላ
የሰላም እናቴ ሰላም ልበልሽ
ዘመኔ ይፈጸም ሳመሰግንሽ

           /አዝ=====

በሠላምታ ድምጽሽ መንፈስ ተመልቼ
አደግድጌ ልቁም እጆቼን ዘርግቼ
በሀይል ቃል ጮኬ ልመስክር በጎቹን
ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሄር እናቱ

           /አዝ=====

ከስሏ ስር ቆመን አንቺን ማወደሱ
ሲገለጽ ሲፈቀድ ከመንፈስቅዱስ
ማርያም እናቴ ምክንያት ለመዳኔ
ብዙ ነው ሚስጥሩ አንቺን ማመስገኑ

👉ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ኪዳነ ምሕረት የረፍቴ እናት ✞

ኪድነ ምሕረት የእ ረፍቴ እናት
ሠላም ሆነ በ አንቺ አማላጅነት
ንጽሕት ድንኳን በ ዕምነት የአጌጥሁብሽ
ሠላም ሆነ በ አማኑኤል ልጅሽ
ሠላም ሆነ በ አማኑኤል ልጅሽ/፪/

የ ብርሐን ዝናር በአይኖረኝም
በ ንጉሥ ፊት ተሸልሜ ብቆም
በ ልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ
በ ምልጃሽ ነው ሥሜ መቀየሩ
        በ ልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ
        አዎ ሥሜ ተጠርቷል በ ልጅሽ
        ከ ታች በ ምድር እስከ ሠማያት ድረስ
        ድርሻዬ ነው ሥምሽን ማወደስ
        ድርሻዬ ነው ሥምሽን ማወደስ

             /አዝ=====

የ ከበረ ሆነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለ ክብርሽ ዘምሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብዬ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በ ሠማይ ጸሐይ
        ሥለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሠሠ
        አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሠ
        ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
        በ ልጅሽ ነው የ ነፍሴ ጽናቱ
        በ ልጅሽ ነው የ ነፍሴ ጽናቱ

             /አዝ=====

ከ ኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያለ አንቺ እናቴ
ተዋብሁብሽ ነፍሴ በ አንቺ አበራ
አንደበቴ ሥምሽን ሲጠራ
        እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
        ማምለጫዬ ከ ፈርዖን ቀንበር
        ከ እንግዲኽማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
        አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ
        አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ

  👉 ዘማሪ ዲያቆን_አቤል_መክብብ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ የትንሣኤው ጌታ ✞

በአምላክነቱ ነውና ገናና
በኃይል ተነሣልን በክብር በምስጋና
ጥበቃ ቢያኖርም የአይሁድ ጉባኤ
ከቶ መቼ ቀረ የጌታ ትንሣኤ

መላእክት ነጭ ለብሰው ለአምልኮ ወርደዋል
ትንሣኤውን አይተው እርሱን አድንቀዋል
የአዳምን ዘር ወዶ እራሱን የሰጠ
በትንሣኤው ብርሃን ጨለማን ለወጠ

               /አዝ=====

ምድር ያልቻለችው ጌታን የወደድሽ
መግደላዊት ማርያም ምንኛ ታደልሽ
ዙሪ ተመልከቺ ጌታ ቀኝሽ ቆሟል
በታላቅ ስልጣኑ ከሙታን ተነስቷል

               /አዝ=====

መምህርሽ ነውና ስገጂ ለጌታ
አዳኝሽ ክርስቶስ እስርሽን የፈታ
ሄደሽ ንገሪያቸው ለሐዋርያቱ
ተነሥቷል ጌታችን ሳይል መግነዝ ፍቱ

               /አዝ=====

በሞት ላይ ኃይል ያለው ነውና አምላክሽ
ተነሥቷል በስልጣን ሐሴት ይሙላው ልብሽ
በሌሊት ጨለማ የፈለግሽው ጌታን
መግደላዊት ማርያም አታፍስሺ እንባን

               /አዝ=====

መከራው ቢያይልም ቢከብድ ፈተናችን
እስከ ሞት አይወልቅም ከእኛ ማዕተባችን
የጨለማው ዘመን ይሻራል በጌታ
ትንሣኤ እስክናገኝ ወገኖች እንበርታ

👉ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ እና
👉ዘማሪ ሊቀ ዲያቆን ተመስገን ይባቤ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ረቡዕ (አልዓዛር)
አልዓዛር ጌታችን በጥንተ ስብከት መጋቢት 17 ቀን ከሞት ያስነሳው ሲሆን ታሪኩ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቧል (ዮሐ 11፥11-46)። አበው የውኃ በዓል ከውኃ በዓል ጋር ይሁን ብለው ቃና ዘገሊላን ከጥምቀት ማግስት እንዳዋሉ የአልዓዛርም ትንሣኤ ከጌታ ትንሣኤ ጋር እንዲውል አደረጉ። በዚህም ይህች ዕለት አልዓዛር በማለት ተሰይማለች፡፡ 

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ በእኩለ ለሊት ✞

በእኩለ ለሊት(፬)ጌታችን /ተነስቷል(፫)
በእርግጥ ከመቃብር

ማርያም መቅደላዊት እንደተለመደው
ማለዳ ተነስታ ሽቶውን ልትቀባው
ነገር ግን ድንጋዩ ተከፉፍቶ ነበር
ጌታችንም የለም በርግጥ ከመቃብር

              /አዝ=====

ብርሀን የለበሱ መላዕክትም መተው
ህያውን ከሙታን የምትሽው ለምነው
አስቀድሞ በግልፅ እንደተናገረው
ተነስቷል ከሙታን ግሩማን ሀያል ነው

               /አዝ=====

ጌታን ባየች ጊዜ ስላላወቀችው
የአትክልት ጠባቂ መስሏት ጠየቀችው
ማርያም ባላት ጊዜ ጌታዋን ለየችው
ረብሁኒ ብላ በደስታ ጠራችው

             /አዝ=====

በአበው በትንቢት እንደተናገረው
እግዛብሄር እንደ ሀይል ተነስቷል ልክ ነው
በመዝሙር መፀሀፍ ትንቢቱ ታውጇል
የእግዛብሄር ክብሩ በእርግጥ ተነስቷል


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ክርስቶስ_ተንስዓ_እሙታን
#በዓብይ_ሀይል_ወስልጣን
#አሠሮ_ለሠይጣን
#አግዐዞ_ለአዳም
#ሠላም_እምይእዜሠ
#ኮነ_ፍሠሀ_ወሠላም  


🖋❣ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ”

እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው በሰላምና በጤና አደረሰን

#መልካም_በዓል

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ዓርብ /የስቅለት ዓርብ/፦
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጥንተ ተፈጥሮ አዳምን በዕለተ ዓርብ ፈጥሮታል፤ ዳግመኛም በዕለተ ዓርብ ሊያድነው መሥዋዕት ሆኖለታል። ከዕለተ ሐሙስ ምሽቱ ሦስት ሰዓት እስከ ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ማኅበረ አይሁድ በጌታ ላይ መከራን አብዝተውበታል፡፡ ይህን አብነት በማድረግ አንድ ቆራቢ (የጌታን ሥጋና ደም ለመቀበል የተዘጋጀ) ሰው 18 ሰዓታት መጾም እነደሚገባው ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሠርታለች፤ ምክንያቱም ከሐሙስ ምሽት ሦስት ሰዓት እስከ ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ 18 ሰዓት ነውና። ክርስቶስም ሥጋውን በበላን ጊዜ ደሙንም በጠጣን ሰዓት መከራውንና ሞቱን ልናስብ ይገባል።
   ከሐሙስ ምሽት ሦስት ሰዓት እስከ ዓርብ መዓልት ስድስት ሰዓት ብዙ መከራና እንግልት አፈራርቀውበታል፡፡ ከዚያም ዓርብ ከቀኑ ስድስት ሰዓት በመስቀል ላይ ሰቅለውታል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለበት ጊዜ ብዙ ገቢራትና ተአምራት ተፈጽመዋል፡፡ እነዚህም፦
#ፀሐይና ጨረቃ የፈጣሪቸውን ዕርቃን ላለማየት ብርሃናቸውን ከልክለው ደም ለብሰዋል።
#ከዋክብት ከሰማይ ረግፈዋል።
#የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለሁለት ተከፍሏል።
#መቃብራት ተከፍተው ሙታን ተነሥተዋል፤ (ማቴ 27፥45-52)።
   በመጨረሻም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ሁሉ እንደተፈጸመ ተመልክቶ እናቱ ድንግል ማርያምን ታጽናናን ዘንድ በወንጌላዊው ዮሐንስ አማካኝነት ለእኛ ሰጥቶናል። ከዚያም ‹‹ሁሉ ተፈጸመ›› (ዮሐ 19፥30) በማለት ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ሥጋው በገዛ ፈቃዱ ለይቷል።
(በዕለተ ዓርብ በጌታ ላይ የተደረገበትን ግፍና መከራ በስፋት በመጽሐፈ ግብረ ሕማማት ላይ ያንብቡ)።


#እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞
#እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞
#አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞
#ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በፍሥሓ_ወበሰላም። ✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ምስባክ
#በ9_ሰዓት_የሚሰበክ

መዝ 68÷21
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።
ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ።
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ምስባክ
#በ3_ሰዓት_የሚሰበክ

መዝ 27÷17
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።
ወአኀዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን።
ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

በዕለተ አርብ ስቅለት የሚሰበኩ ምስባኮች

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ሐዋርያቲሁ✞

ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሃጸበ
ኮኖሙ አበ ወእመ ወመሃሮሙ ጥበበ
ሃሌ ሉያ

ጌታ መሃላቸው ተገኝቷል
የሐዋርያትን እግር አጥቧል
አባትና እናት ሆናቸው
ጥበብንም አስተማራቸው     
ሃሌ ሉያ    
                             
የወደዳቸውን እነሱን ወደዳቸው
በትህትና ሆኖ ይኸው አጠባቸው
ሰጣቸው ለሕይወት ሥጋውና ደሙን
እንዲመሰክሩ እስከሞት ስሙን
  
ሥላሴን በቤቱ አስተናግዶ ነበር
እግራቸውን አጥቦ አብርሃም በፍቅር
ዛሬ መለሰለት ይህንን ውለታ
ዝቅ ብሎ አጠበ አማኑኤል ጌታ
       አዝ= = = = =
ይሁዳም ታጠበ ሳይከራከረው
አካሉ ከጌታ ልቡ ከአይሁድ ነው
አሳልፎ ሰጠ ደግ መምህሩን
ታሪኩን ቀይሮ ሰው ያረገውን
   ሥላሴን በቤቱ...
   .....
       አዝ= = = = =
ራሱን ዝቅ አረገ አምላካቸው ሲሆን
ምሳሌውን ተወ እንዲመስሉ እርሱን
ከእናንተ የሚሻ ታላቅ መሆንን
በመካከላችሁ ታናሽ ሰው ይሁን
  ሥላሴን በቤቱ...
  ...
       አዝ= = = = =
ዓለምን የያዘ ፍጥረቱን የፈጠረ
አሳልፎ የሚኖር ያለ የነበረ
ተገልጦ አየነው ልዑሉ ትሁት
ረቂቁ ገዘፈ ሊያድነን ከሞት
    ሥላሴን...
    .....

          ሊቀ ልሳናት
ቀሲስ አብርሃም ዲበኩሉ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮ /channel/mezmuredawit
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተወልዳለችና ✞

ተወልዳለችና የጌታ እናት የእኛ መድኃኒት/2/
እናመስግናት እናወድሳት እንውደዳት/2/
የአዳምን ሕይወት
       
አዳም ሲሰደድ ከጥንት ርስቱ
ፊቱን ሸፈነው ጭንቀት ፍርሃቱ
እያለቀሰ ገነትን ሲያጣ
ተስፋ አንቺ ሆንሽው የመዳኑ ዕጣ

       /አዝ=====

ሊባኖስ ተራራ ተሰማ ዜና
ምሥራቅ ወለዱ እያቄም ወሐና   
ዳግማዊት ሄዋን ምክንያተ ድህነት
ልደቷን ሰማን በቅድስት ዕለት
       
       /አዝ=====

የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው
በአንቺ ነውና ልጅ የተባልነው
ፋራን የተባልሽ ቅድስት ተራራ
በአንቺ መወለድ ዓለሙ በራ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ይህ ጊዜው ገና ነው አላት፡፡ እርሱንም ቅዱስ ሚካኤል ከእሥር ፈቶት መበለቲቱን ከነልጇ አጥምቆ እያስተማረ ወደ ንጉሥ ተመልሷል፡፡
   ንጉሥ ዱድያኖስ በተመለከተው ጊዜ የሚያደርገው ጠፍቶት ‹‹በመንኮራኩር ፈጭታችሁ ደብረ ይድራስ ወስዳችሁ ንዙት›› አለ፡፡ ፈጭተው ወስደው ቢነዙት ሥጋው ያረፈበት ሣር ቅጠሉ ደንጊያው እንጨቱ ሁሉ ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር እያሉ አመስግነዋል፡፡ ጌታም ሦስተኛ ከሞት አንሥቶት ጭፍሮቹን ተከትሎ አምላኬ ከሞት አስነሳኝ ሲላቸው ደንግጠው ከእግሩ ሥር ወደቁ፤ መሬቱን በእግሩ መትቶ ውኃ አመንጭቶ ቅዱስ ዮሐንስ አጥምቋቸዋል፡፡
  
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ልሹምህ ልሸልምህ ለአጵሎን ስገድ አለው፤ ከሾምከኝማ ሌላ ምን እሻለሁ እሺ እሰግዳለሁ አለው፡፡ እንኪያስ እስከዛሬ ባስከፋሁህ ይቅር በለኝ ብሎ ከእልፍኝ አስገብቶት ወጣ፡፡ ንግሥቲቱ እለእስክንድርያ ስመ እግዚአብሔር ጠርቶ ሲያመሰግን ሰምታ ‹‹ምን ማለት ነው?›› ብላ ጠየቀችው፡፡ ይህን ምክንያት አድርጎ አስተምሮ አሳምኗታል፡፡
   ሲነጋ ንጉሡ ዱድያኖስ ‹‹ጊዮርጊስ ለአጵሎን ሊሰግድ ነውና ከአደባባይ ተሰብሰቡ›› ብሎ አዋጅ አስነገረ፡፡ ያች መበለት ልጇን አቅፋ ‹‹ሐሰት ይሁን ጊዮርጊስ ለአጵሎን አይሰግድም›› እያለች ታለቅስ ነበር፡፡ ልጅሽን ከዚህ አኑሪው ብሏት በዚያ አስቀመጠቸው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ተነስተህ መልእክቴን አድርስ ሲለው ተነስቶ ቆሟል፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹ከቤተ ጣዖት ገብተህ አጵሎንን የክርስቶስ አገልጋይ ጊዮርጊስ ይጠራሀል በለው›› አለው፡፡ ኼዶ ቢጠራው በዚያ ያደረ ሰይጣን እየጮኸ ሕፃኑን ተከትሎ መጥቶ ከፊቱ ቆመ፡፡ ሕፃኑ በዚህ አጋጣሚ ጆሮውን አፉን ተፈውሷል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ‹‹በውኑ አንተ አምላክ ነህን?›› አለው፤ ቢሰውልኝ ቢሰግዱልኝ እንጂ አምላክ አይደለሁም አለ፡፡ እንኪያስ ዳታንንና አቤሮንን የዋጠች ምድር ትዋጥህ ሲለው ምድር አፏን ከፍታ ውጣዋለች፡፡
   ንጉሡ እንዲያደንቁለት የሰበሰባቸው ሁሉ አለማድነቃቸውን ሲመለከት ልብሱን ቀዶ ከእልፍኙ ገባ፡፡ ንግሥቲቱም ‹‹ምን ሆንክ?›› ብላ ስትጠይቀው የሆነውን ሁሉ ነገራት፡፡ እርሷም ‹‹ነግሬህ አልነበረምን? ጊዮርጊስን እስከዛሬ ያሰቃየኸው አይበቃህምን? ትምህርቱን ሰምተህ፣ ተአምራቱን አይተህ ከክፋትህ አትመለስምን?›› አለችው፡፡ ከዚያም ፀጉሯን ይዞ እየጎተተ ወስዶ ከነገሥቱ ፊት አቁሞ ፍረዱኝ አላቸው፤ እነርሱም ትቀጣ አሉት፡፡ ዕርቃኗን አሰቅሎ በሰይፍ አስመተራት፤ ደሟም ጥምቀት ሆኗት አስተማሪዋ ቅዱስ ጊዮርጊስን ቀድማ በሰማዕትነት ዐርፋለች፡፡ በተጨማሪም ትምህርቱን ሰምተው ተአምራቱን አይተው ያመኑትን ብዙ ሺህ ሰዎች አሰይፏቸዋል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስንም በሰይፍ ሊቀጡት ይዘውት ሲኼዱ መከራዬን ስቃዬን ተቀብለህስ ከሆነ በኤልያስ ቃል ከሰማይ ወርዳ ጠላቶቹን የበላች እሳት እንዚህን ሀሳውን ትብላቸው ብሎ ወደ ፈጣሪው ቢያመለክት ወዲያው ንጉሥ ግብር አግብቶ ከአዳራሽ ተገኝቶ ሲበላ ሲጠጣ እሳት ከሰማይ ወርዳ በልታቸዋለች፡፡ ከዚያም ቃልኪዳንን ከፈጣሪው ተቀበለ፤ እንዲሁም ከማኅበረ ሰማዕታት የሚመስልህ የሚተካከልህ የለም ብሎ ነግሮታል፡፡ ጭፍሮቹ ግን ይህን ሊያዩ ሊሰሙ አልታደሉምና ከወደቁበት ተኝተው ነበር፤ እርሱም ቀስቅሶ የታዘዛችሁትን ፈጽሙ አላቸው፡፡ ከዚያም በዘጠኝ ሰዓት በሰይፍ በመቱት ጊዜ ከአንገቱ ደም፣ ውኃና ወተት ፈሷል፡፡
   ጌታም ስለ ሰባት ዓመት ተጋድሎው ሰባት አክሊላት አቀዳጅቶታል፡፡ በሰማዕትነት ያረፈው ሚያዝያ 23 ቀን በ27 ዓመቱ ነው፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፀጋና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!
          ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ምንጭ፦ መዝገበ ታሪክ፣ ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ስንክሳር ዘሚያዝያ 23፣ መድበለ ታሪክ
  

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ደምቆ እያበራ ✞

ደምቆ እያበራ ነጭ ልብሱ
ጊዮርጊስ መጣ በፈረሱ
እኔን ከክፉ ሊያወጣኝ
እስሬን ፈቶ ሊያቆመኝ

ታግሎ ሲያሸንፍ ዓለምን
እስከ ሞት ድረስ ሲታመን
የክብር አክሊል ተቀዳጀ
ጊዮርጊስ ከአምላኩ ተወዳጀ

         /አዝ=====

ግብር ሰተውኝ ለጠላቴ
ተስፋ ቢስ ስሆን ቀርቦ ሞቴ
አስጣለኝ ጊዮርጊስ ከሞት አፍ
ከአስፈሪው ጥፋት እንድተርፍ

         /አዝ=====

ኃይሉ ደከመኝ የጠላቴ
ጊዮርጊስ ሲመጣ እረዳቴ
የጸሎቱ ኃይል ትሩፋት
ቤቴን ሞላልኝ በረከት

         /አዝ=====

ዘንዶውን ጥሎ ገሎልኝ
አምላኬን ገልጦ አሳየኝ
አሁን አዳኜን አውቂያለሁ
ለጊዮርጊስ አምላክ እዘምራለሁ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ቅድስት ሆይ የምንልሽ ✞

ቅድስት ሆይ የምንልሽ
ለምኝልን የምንልሽ
የወለድሽው ሰላም ፍቅር
በእጅሽ ላይ ነው ይላል ይቅር

አሸናፊው እግዚአብሔር
በዙፋኑ ነግሦ የሚኖር
ከአንቺ ጋር ነው በኩር ልጅሽ
አሳስቢልን በኪዳንሽ

           /አዝ=====

የአብን ቃል የወለድሺው
መልካሟ ርግብ የተባልሺው
ከእሴይ ስር የተገኘሽ
ድንቅ አበባ አንቺ እኮ ነሽ

           /አዝ=====

በእምነት ያጽናን በሃይማኖት
ክብር ይስጠን ጸጋ ምሕረት
እንዲሰረዝ በደላችን
ለምኚልን እናታችን

           /አዝ=====

ፍህም ያለብሽ ማዕጠንተ ወርቅ
መገኛ ነሽ ለፀሐየ ጽድቅ
አዘክሪ አሳስቢልን
የእሳቱን ባህር አያሳየነ

           /አዝ=====

ፍሬሽ ጥዑም የሚፈውስ
የወልድ እናት የክርስቶስ
ፍቀጂልኝ ማርያም ድንግል
ሥጋ ደሙን እንድቀበል

👉ሊቀ_መዘምራን_ቴዎድሮስ_ዮሴፍ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ምክንያት_ስላለኝ_ነው ✞

ምክንያት ስላለኝ ነው የምዘምርልሽ
ምክንያት ስላለኝ ነው ቅኔ የምቀኝልሽ
አሁንም ይብዛልኝ ፍቅርሽ(፪)
ከዚህ በላይ እንዳመሰግንሽ

አውቃለሁ ከደጅሽ ምን እንዳገኘሁኝ
አስታውሰዋለሁ ሸክሜን እንደጣልኩኝ
የለመንኩሽ ሁሉ መቼ ከንቱ ቀረ
ሰይጣን ተመለሰ እያቀረቀረ
   ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ/2/
   አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ/2/
      
            /አዝ=====

ልቤ አርፏል በአንቺ በእናቴ አማላጄ
እንቅፋት እሾሁ አይበቅልም በደጄ
በሚጣፍጥ ዜማ በኤፍሬም ውዳሴ
ሳሸበሽብልሽ ትረካለች ነፍሴ
   ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ/2/
   አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ/2/

            /አዝ=====

ውለታ ያለበት የማይከፈል
ሲመሽም ሲነጋም ያመሰግናል
ማርያም ማርያም ይላል ምድርና ሰማዩ
በልጅሽ መከራ አልፎለት ገዳዩ
   ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ/2/
   አደገድጋለሁ ደግሜ ደግሜ/2/

👉ዘማሪት_ምርትነሽ_ጥላሁን
 
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
             #ዳግማይ_ትንሣኤ (ፈጸምነ)
    በዓለ ትንሣኤ የበዓላት ሁሉ ርዕስ ነው፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እስከ በዓለ ዕርገት ድረስ ያለውን ዘመነ ትንሣኤ ብላ ሰይማለች፡፡ የዳግም ትንሣኤ ዕለት የሚደርሰው ምስጋና ከዕለተ ትንሣኤ ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ ዕለት ደቀ መዛሙርቱን ከተዘጋ ቤት ገብቶ ‹‹ሰላም ለእናንተ ይሁን›› ባላቸው ጊዜ ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት አንዱ ቶማስ የተባለው ዲዲሞስ ከእነርሱ ጋር አልነበረም፤ እርሱም ከአገልግሎት ሲመጣ ‹‹ጌታን አየነው›› አሉት፡፡ ኺዱና አስተምሩ እንደሚላቸው ያውቃልና እነርሱ አየን ብለው ሲያስተምሩ እኔ ሰማሁ ልል ነውን? ብሎ በችንካር የተቸነከሩ እጆቹን ካላየሁ፣ በችንካር የተቸነከሩ እግሮቹን፣ በጦር የተወጋ ጎኑን ካልዳሰስኩ አላምንም አለ፤ (ዮሐ 20 ፥19-25)
   ከስምንት ቀን በኋላም ደቀ መዛሙርቱ ደግመው በውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡ ደጆች ተዘግተው ሳሉ ኢየሱስ መጣ፤ በመካከላቸውም ቁሞ ‹‹ሰላም ለእናንተ ይሁን›› አላቸው፡፡  ቶማስ ጎኑን ካልዳሰስኩ ብሎ ነበርና ከዚያም በኋላ ቶማስን ‹‹ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው ያመንህ ሁን እንጂ ያላመንህ እትሁን›› አለው፤ (ዮሐ 20 ፥27)፡፡ ቶማስም ቢዳስሰው እጁ ከእሳት እንደ ገባ ጅማት ኩምትርትር አለች፤ እርሱም ጌታዬ አምላኬ ሆይ አለ፡፡ ኢየሱስም ‹‹ስላየኸኝ አምነሃል፤ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው›› ብሎ ፈውሶታል፡፡ ጎኑን የዳሰሰችው እጁ ዛሬም በሕያውነት በሕንድ ከታቦቱ ጋር ትኖራለች፤ በዓመት በዓመቱ  በእመቤታችን በዓል (በአስተርእዮ) ሊያጥኑ ሲገቡ ቀድሳ ታቆርባለች፤ የሚሾመውን ወጥታ ቀኝ እጁን ትይዘዋለች፡፡ እንዲህ እያለች እስከ ምጽአት ድረስ ትኖራለች፤ (አንድምታ ዘዮሐንስ ወንጌል 20፥28)፡፡
            ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የዮሐንስ ወንጌል አንድምታ ምዕ 20
   

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ሐሙስ (አዳም ሐሙስ)
የአዳም ምሉዕ ተስፋ የተፈጸመበትን ምሥጢር የምናስታውስበትና የምንዘክርበት ዕለት ነው። ምክንያቱም ለክርስቶስ ሰው መሆን ዋና ምክንያቱ ጸሎተ አዳም ወሔዋን ስለሆነ ርደተ ሲዖልን በጽአተ ሲዖል፣ ርደተ መቃብርን በሙስና መቃብር፣ ጽልመተ ሲዖልን በብርሃነ መለኮት ለውጦ ሞተ ሥጋ ወነፍስ ተፈርዶባቸው የነበረው ሁሉ አልፎ “ኃጢአት ከበዛችበት ዘንድ ጸጋ እግዚአብሔር ትበዛለች” ብለው ያመሰገኑበት መታሰቢያ ነው፡፡ አዳምና ሔዋን ከሲዖል የወጡት ዓርብ ሲሆን ሐሙስ መከበሩ ለምንድ ነው ቢሉ ዓርብ ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት መታሰቢያ ስለሆነ በዚህ ዕለት ይከበራል። ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ አለመከበሩ ሐሙስ መከበሩ ለምንድ ነው ቢሉ ከእሑድ እስከ ሐሙስ አምስት ቀን ይሆናል። አምስት ቀን ተኩል ሲፈጸም አድንሃለሁ ብሎት ነበርና ያ እንደተፈጸመ ለማጠየቅ ነው።

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ከትንሣኤ እሁድ በኃላ ያሉት እለታት ስያሜዎች

#ሰኞ (ማዕዶት)፦
ማዕዶት ማለት (መሻገሪያ፣ መሻገር) ማለት ነው። ቀድሞ እስራኤላውያን ባሕረ ኤርትራን ተሻግረው ምድረ ርስት ገብተዋል። ምሳሌነቱም ፈርዖን የዲያብሎስ፣ ሠራዊቱ የሠራዊተ ዲያብሎስ፣ ግብፅ የሲዖል፣ ባሕረ ኤርትራ የባሕረ ሲዖል፣ እስራኤል የምእመናን፣ ሙሴ የወልደ እግዚአብሔር፣ በትረ ሙሴ የመስቀል ምሳሌ ሲሆን እስራኤላውያን በሙሴ መሪነት ተሻግረው ምድረ ርስት እንደገቡ ነፍሳትም በክርስቶስ መሪነት ባሕረ ሲዖልን ተሻግረው ገነት የመግባታቸው ምሳሌ ነው። ስለዚህ ትንቢቱ ምሳሌው መድረሱን ለማጠየቅ ዕለቷ ማዕዶት ተብላለች።

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

​​✞ የሕያዋን አምላክ ✞

የሕያዋን አምላክ ሙታንን ሊያስነሳ
በእኩለ ለሊት ክርስቶስ ተነሣ(፪)

ሙታን አይደለንም - - - ክርስቶስ ተነሣ
ሕያዋን ነን እኛ - - - ክርስቶስ ተነሣ
በመስቀሉ የዳንን - - - ክርስቶስ ተነሣ
ከኃጢአት ቁራኛ - - - ክርስቶስ ተነሣ
የተዋረድነውን - - - ክርስቶስ ተነሣ
ሊያከብረን ዳግመኛ - - - ክርስቶስ ተነሣ
ሞትን አሸንፎ  - - - ክርስቶስ ተነሣ
ተነሣልን ለእኛ - - - ክርስቶስ ተነሣ
      
               /አዝ=====

እናንተስ አትፍሩ - - - ክርስቶስ ተነሣ
እነግራችኋለሁ - - - ክርስቶስ ተነሣ
የተሰቀለውን - - - ክርስቶስ ተነሣ
እንድሹ አውቃለሁ - - - ክርስቶስ ተነሣ
ሕያውን ከሙታን - - - ክርስቶስ ተነሣ
ለምን ትሻላችሁ - - - ክርስቶስ ተነሣ
እንደተናገረው - - - ክርስቶስ ተነሣ
ተነሥቷል ጌታችሁ - - - ክርስቶስ ተነሣ

               /አዝ=====

ሞትን ድል አድርጎ - - - ክርስቶስ ተነሣ
በእኩለ ለሊት - - - ክርስቶስ ተነሣ
አስቀድሞ ታየ - - - ክርስቶስ ተነሣ
ለመግደላዊት - - - ክርስቶስ ተነሣ
አርሷም ትንሣኤውን - - - ክርስቶስ ተነሣ
ለአለም አበሰረች - - - ክርስቶስ ተነሣ
ጌታዬን አየሁት - - - ክርስቶስ ተነሣ
ተነሥቷል እያለች - - - ክርስቶስ ተነሣ

👉ዘማሪ ቀሲስ ወንደሰን በቀለ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
❖   @mezmuredawit     ❖
                                    ✥   ✢   
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ቅዳሜ /ቀዳም ስዑር/፦
   ቅዳሜ የተሻረ የሚባለው ስለሚጾምበት እንጂ በዓልነቱ ተሽሮ አይደለም፡፡ ዕለተ ቅዳሜ በሥነፍጥረት ታሪክ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ በመጨረስ ያረፈበት ቀን ነው፡፡ በዚህም የተነሣ በዓል እንድናደርግ (እንድንበላና እንድንጠጣ) እንደሰትበትም ዘንድ የተፈቀደ ቀን ነው፡፡ በሰሙነ ሕማማት የምትውለው ቅዳሜ ግን  ኢየሱስ ክርስቶስ በመቃብር የዋለባት ቀን ስለሆነች ይጾምባታልና ቀዳም ስዑር (የተሸረ ቅዳሜ) ተብላለች፡፡ በዚህ ዕለት ካህናት ቄጤማ ለምእመናን ያድላሉ፡፡ አባታችን ኖህ የጥፋት ውኃ ከምድር መድረቁን ለማወቅ የላካት ርግብ የጥፋት ውኃ መጉደሉን ለመናገር ለኖህ የሰላምና የተስፋ ተምሳሌት የሆነውን ለምለም ቅጠል ይዛለት ሔዳለች፡፡ አባቶቻችንም ከአዳም በዘር ይተላለፍ የነበረውን ጥንተ አብሶ መጥፋቱን በክርስቶስ መከራም የመከራችን ምንጭ መድረቁን ለምእመናን ሲያበስሩ በመስቀሉ ሰላም ሆነ እያሉ ለምለም ቄጤማ ያድላሉ፡፡ ከዚህም የተነሣ ዕለቱ ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡፡

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ።
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ።
አምንስቲቲ ሙዐግያ አንቲ ፋሲልያሱ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ምስባክ
#በ6_ሰዓት_የሚሰበክ

መዝ 21÷16
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ።
ወኋለቁ ኵሎ አዕፅምትየ።
ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ምስባክ
#በ1 ሰዓት የሚሰበክ

መዝ 34÷11
ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።
ወዘኢየአምር ነበቡ ላዕሌየ።
ተንሥኡ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ።

        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ በሚፈርደው ፈረዱበት ✞

በሚፈርደው ፈረዱበት
በሚምረው ጨከኑበት
በቁጣ ጎተቱት ቀይ ግምጃ አለበሱት
     
አዳምን የፈጠረ እጅ በመስቀል ቀኖት ተቸነከረ
ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ከወንበዴ ጋር ተቆጠረ
ህይወት እፍ ያለውን አፍ ጨክነው ሀሞት አጠጡት
በሞቱ ሞትን ይሽር ዘንድ ጌታን በመስቀል ሰቀሉት

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት
         አዝ= = = = =
በመፍራትና በመራድ መላዕክት ፊቱ ለሚሰግዱለት
የአለሙን ሁሉ ጌታ በአደባባይ ላይ አቆሙት
ለሱራፌል የክብር ዘውድ ያቀዳጃቸውን ጌታ
ፍቅር ያነበብንበት ፊቱን በክፉ ባርያ ተመታ

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት
         አዝ= = = = =
ፅድቅና የፀና ሰላም የሀጥያት ስርየት በሰጠን
እንደ ክፉ ሰው ተቆጥሮ በእሾህ አክሊል አጌጠ
ለኪሩቤል የግርማን ልብስ የሚያለብሳቸውን እርሱን
እርቃኑን ይሰቀል ብለው እጣ ተጣጣሉበት ልብሱን

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት
         አዝ= = = = =
በኢየሱስ መንገላታት አለም እንዲድን ከፍዳ
ቅዱሱ ደምና ውሀ ከአምላካችን ጎን ተቀዳ
ሰላም ለእናንተ ሲለን እጅና እግሩን አየን
ሙስና መቃብር ጠፋ ይኸው በአዲሱ ኪዳን

ይህን ያህል ትህትና ይህን ያህል ትዕግስት
ይህን ያህል ሰው ማፍቀር ይህን ያህል ምህረት
ዝም አለ አማኑኤል በግፍ ለሚሰቅሉት

                  ዘማሪ
      ገብረዮሐንስ ገብረ ጻድቅ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|:══╮
 /channel/mezmuredawit
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ሐሙስ /ጸሎተ ሐሙስ/፡-
   ይህ ዕለት ቅድመ ዓለም ለፍጥረታት ሁሉ ምግበ ሥጋን የፈጠረ ጌታ ለሰው ልጆች ምግበ ነፍስ ሆኖ ራሱን ማዕድ አድርጎ ያቀረበበትና ቅድሚያ መደረግ ያለበት ሥርዓተ ጸሎትን ያስተማረበት ነው፤ (ማቴ 26፥36)፡፡
ይህ ቀን ጌታችን ካደረጋቸው ሥራዎች አንፃር የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ እነዚህም፡-
1. ጸሎተ ሐሙስ፡- ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ በገጠመን ጊዜ ተግተን መጸለይ እንደሚገባን ለማስተማር፣ ኅብስቱን ለመባረክ ስለጸለየ እና ለሐዋርያት ሥርዓተ ጸሎትን ስላስተማራቸው ጸሎተ ሐሙስ ተብሎ ይጠራል፡፡
2. የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፡- ‹‹ይህ የሐዲስ ኪዳን አዲሱ ሥርዓት ነው›› ብሎ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት ስለሰጠ አንድም በእንስሳት ደም ይፈጸም የነበረውን መሥዋዕተ ኦሪትን ስለሻረ ነው፡፡
3. አረንጓዴ ሐሙስ፡- ኢየሱስ ክርስቶስ የጸለየው በአረንጓዴው የአትክልት ሥፍራ በጌቴሴማኒ በመሆኑ ነው፡፡
4. ትዕዛዘ ሐሙስ፡- ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ›› (ማቴ 26፥41) በማለት ትዕዛዝ በመስጠት እግራቸውን አጥቦ ‹‹እናንተም እንዲሁ አድርጉ›› ብሏቸዋል፤ (ዮሐ 13፥12-15) ፣ ሥጋውንና ደሙን ከሰጣቸውም በኋላ ‹‹ይህንን በበላችሁ ጊዜ ሞቴን አስቡ›› ሲል ስላዘዛቸው ነው፡፡ (ማቴ 26፥26-29)፡፡

#እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞
#እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞
#አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞
#ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በፍሥሓ_ወበሰላም። ✞✞✞

Читать полностью…
Subscribe to a channel