mezmuredawit | Unsorted

Telegram-канал mezmuredawit - ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

28629

የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል

Subscribe to a channel

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

        🕯  #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አባቱ ስምዖን እናቱ አቅሌስያ ይባላሉ። በላዕላይ ግብፅ ንሂሳ በተባለች ቦታ ለ30 ዘመን ሲኖሩ ልጅ አልነበራቸውም። ከዚህ በኋላ አቅሌስያ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዳ ከሥሉስ ቅዱስ ሥዕል ብትማጸን ክብሩ ከሚካኤልና ከገብርኤል፣ ከመጥምቁ ዮሐንስና ከነቢዩ ኤልያስ የሚተካከል ልጅ ተቀበይ አልዋት፤ በዚህም አናብስትን የሚገዛ በአምላኩ ኀይልም አበሳን የሚያስተሰርይ ልጅ መጋቢት 29 ቀን ተፀነሰና በታኅሣሥ 29 ቀን ተወለደ፡፡
ሲወለድም ስሙን ኒኮላዎስ አሉት፡፡ በተወለደም ጊዜ ከእናቱ ዕቅፍ ወርዶ ስብሐት ለአብ፣ ስብሐት ለወልድ፣ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ እያለ ሦስት ጊዜ አመስግኗል።
ሦስት ዓመት ሲሞላው ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ ከእናቱ ዕቅፍ አንስቶ ወደ እግዚአብሔር ወሰደው፤ ከዚያም ወደ እናቴ ውሰደውና ትባርከው አለው፡፡ ከዚያም ከአዳም ጀምረው አበው ቅዱሳን ባርከውታል፤ ከተባረከ በኋላ ብዙ ባሕታውያን ወደ አሉበት ወስዶ አባ ዘመደ ብርሃን ለሚባል አበ ምኔት እንዲያስተምረው ሰጠው፡፡ እርሱም አንሥቶ አቅፎ ስሞ ወደ በዓቱ በማስገባት በፍቅርና በሥነ ሥርዓት ብሉይና ሐዲስን እያስተማረ አሳደገው፡፡ ከዚያም ዲቁናን ይሰጠው ዘንድ አብርሃም ወደ ሚባል ጳጳስ ወስዶ በማዕርገ ዲቁና ተሾመ፤ እርሱም እንደ ቀዳሜ ሰማዕት እስጢፋኖስ ጸጋና ሞገስን የተሞላ ሆነ።  በኋላም ማዕርገ ቅስና ተቀብሎ በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደትና በብዙ ትጋት እየተጋደለ ብቻውን በበረሃ መኖር ጀመረ፡፡ ‹‹ነፍስ ሆይ ዕወቂ በእግዚአብሔር ፊት ዕራቁትሽን ትቆሚ ዘንድ አለሽና ታገሺ በርቺ›› ይላት ነበር፡፡

ሥጋው ከአጥንቱ እስከሚጣበቅ ድረስ ያለ መብልና መጠጥ በገድል ተጠምዶ ኖረ፤ ከእንጨት ሥርና ፍሬ ቅጠል ምንም ምን አልተመገበም ለሥጋውም የሚጠቅም ምክንያት አላደረገም፡፡ ‹‹ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም›› ሉቃ. 4፥4 እንዲል።
ከብዙ ዘመን በኋላ ጌታችን ተገልጦ ወዳጄ ሆይ ከዛሬ ጀምሮ ሰው እንዲያውቅህ አደረግሁ፤ መላእክት ይጎበኙሃል፤ ወደ ምትፈልገው እንድትበር የብርሃን ሠረገላ ይሁንልህ በፈለግህ ጊዜ በሦስትነቴ ታየኛለህ አለው፡፡ ቀጥሎም ‹‹ወይእዜኒ ሑር ምድረ ኢትዮጵያ በህየኒ ሀለውከ ነፍሳት›› ትርጓሜውም ‹‹አሁንም ወደ ኢትዮጵያ ሒድ በዚያ ከመከራ የምታወጣቸው ነፍሳት አሉህ›› አለው፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በገዳመ ንሂሳ መንኩሶ በግብፅ 300 ዓመት ከኖረ በኋላ በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ወደ ኢትዮጵያ በታላቁ ጻድቅ በንጉሥ ላሊበላ ዘመን መጣ፡፡ ጌታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስን የሚያገለግሉ ስልሳ አናብስትንና ስልሳ አናምርትን በድምሩ በ120 ቤተሠብ ልክ 120 አድርጎ እንዲከተሉት ሰጠው፤ በዚህም ጊዜ እነዚህን ምን ላብላቸው ብሎ ፈጣሪውን ጠየቀ፤ አንተ የረገጥከውን አቧራ ይልሳሉ ብሎ ጌታ ነገረው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በላሊበላ ቤተ መንግሥት ሮሃ ገባ፤ ላሊበላም የገብረ መንፈስ ቅዱስን መልክ፣ ፀጉርና የአንበሶቹን ጽዳት ቅልጥፍና አይቶ አደነቀ፡፡ አብረው በቤተ መንግሥት ትንሽ ቀን ከቆዩ በኋላ ቅዱስ ገብርኤል በብርሃን ሠረገላ እየመራ አምጥቶ ምድረ ከብድ አደረሳቸው፡፡ ቅዱስ ላሊበላም አብሮ እስከ ምድረ ከብድ ሸኝቶ ተሰናብቶ ሲመለስ አዳዲ ማርያምን አንጾ እንደተመለሰ ተጽፎ ይገኛል፤(ገድለ ቅዱስ ላሊበላ)።
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስም አሻግሮ ሲመለከት ምዕራፈ ቅዱሳን በኩረ ገዳማት ዝቋላ ታየው፤ ይህች ቦታ ለእኔ ማረፊያዬ ናት ብሎ ተነስቶ ሔደ፤ ከተራራው ስር ሲደርስ የሀገሩን ሰዎች አገኛቸው፤ እነሱም የአንበሶቹን ሥልጣን እና የገላውን ማማር ሲያዩ እርስ በእርሳቸው ምንድን ነው ይህ ሰው ወይስ መልአክ ነው እያሉ ኦቦ አሉት፤ ጻድቁም ቋንቋቸው ተገልጾለት ለምን ኦቦ (አንተ) ትለኛለህ ሲሉ ታዲያ ማን ልበልህ ሲል ጠየቃቸው ስሜ ኒቆላዎስ ነው አሏቸው፡፡ በዚያ የሰዎችን ኀጢአት ተመልክቶ ወደ ባሕር ገባ፤ ይህን ሕዝብ ካልማርክ ከዚህ ባሕር አልወጣም እያለ 40 ቀንና 40 ሌሊት እንዲህ ሆኖ ኖረ፤ በዚህም ጌታችን መጥቶ ተነስ ውጣ ከባሕሩ አለው፤ ጻድቁም መላውን የኢትዮጵያ ሰዎች ካልማርክልኝ አልወጣም ብሎ በባሕሩ ውስጥ 100 ዓመት ኖረ፡፡ ደሙ ፈስሶ አጥንቱ እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፤ አእላፍ አጋንንትም በየቀኑ ከአራቱም ማዕዘን እየመጡ በቀስት ይነድፉታል፣ በሻፎ (ሱፋጭ) ድንጋይም ይፍቁታል፤ እንዲህ እየሆነ ታግሦ ኖረ።
ከዚህ በኋላ ጌታ መጥቶ ሁሉን እምርልሃለሁ ተነስ ብሎ ዳሰሰውና ጤነኛ አደረገው፤ በዚህም ጊዜ ጻድቁ ከተዘቀዘቀበት ባሕር በጥር 5 ቀን ወጥቶአል። ከዚህም በኋላ በተሰጣቸው ሀብተ መብረቅ ከሰይጣን ጋር ሲዋጉ ኑረዋል፡፡ ቦታው ከዋዕዩና ከቆላማነቱ የተነሳ ዝ-ቆላ ‹‹ይህ ቆላማ ቦታ›› በሚል ዝቆላ እየተባለ 260 ዓመት ሙሉ ሲጠራ ከቆየ በኋላ በአሁን ጊዜ ዝቋላ በሚለው ፀንቷል፡፡ ከዚያም ወደ ምድረ ከብድ ተላከ፡፡ በዚያም እንደ ተተከለ ዐምድ ሆኖ ዓይኖቹን ሳይከድን ወደ ሰማይ እየተመለከተ ሰባት ዓመት ሲጸልይ ሰይጣን በቁራ ተመስሎ መጣ፤ ዐይኖቹም ወደ ሰማይ ተንጋጠው አገኘ፤ በራሱም ላይ ተቀምጦ ሁለት ዓይኑን አንቁሮ አሳወረው፡፡ በዚህ ጊዜ ሚካኤልና ገብርኤል መጥተው በፊቱ እፍ ብለው ዓይኑን አበሩለትና ጠላቶችህን እንድትበቀል ኀይል ተሰጥቶሃልና ወደ ዝቋላ ሒድ አሉት፡፡ ከዚያ ወደ ዝቋላ ሲሔድ በመንገድ ሦስት አረጋውያንን አይቶ ልደበቃቸው ብሎ በልቡ ሲያስብ በጀርባህ እያዘልህ አንድ አንድ ምዕራፍ ሸኘን እያሉ ጠሩት። ከዚያም አንዱን አዝሎ አንድ ምዕራፍ አደረሰው፤ ከዚያም ሁለቱን እንዲሁ አደረገ። በዚያ ጊዜ በአንድነትና በሦስትነት እንደ አብርሃም ሥላሴ ተገልጠውለት ፊታቸው እንደ መብረቅ ተንቦገቦገ፤ ጻድቁም በምስጢር ጎርፍ ተዋጠና ደነገጠ፡፡ ከዚያም በባሕር ሳለ ያሰቃዩት አጋንንት ወደ አሉበት በመብረቅ እየበረረ ሔደ፤ ቅዱሳን መላእክትም አጋንንቱን መተሯቸውና አመድ ሆነው ተበተኑ።
አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አባ አንበስ ዘአዘሎ እና አባ ብንያም ዘምድረ ግብፅ የተባሉት ቅዱሳን ተነስተው በአንበሳ ተጭነው ከገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘንድ ዝቋላ ሔዱ፤ እንደደረሱም የገብረ መንፈስ ቅዱስ አናብስት የሦስቱንም ቅዱሳን አናብስት ዋጡአቸው፡፡ በዚህ አዝነው ሳሉ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በሚያስፈራ ግርማው ከበዓቱ ወጣ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱሳኑ የሆነውን ነገሩት፤ እጁን ሲፀፋ ስልሳውም አናብስት መጡ፤ በሉ ትፉ ለምን የሰውን አናብስት በላችሁ አሏቸው። አናብስቱም አናብስቱን ተፉአቸው፤ ይህ የሆነው በጥቅምት 5 ቀን ነው፡፡ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ62 ዓመት ተዘዋውሮ ሰብኳል፤ ጌታችንም ወዳጄ ገብረ አብ፣ ገብረ ወልድ፣ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፍቁርዬ ይለዋል።
በዚያችም ጎዳና አንድ ንጉሥ አየውና አንተ ጠጉር ለባሽ ምንድን ነህ? አለው፤ እርሱም የክርስቶስ ባሪያ ነኝ አለው፤ ንጉሡም አይሁድ በሰቀሉት ታምናለህ? አለው፤ አምንበታለሁ ስለ እኔ ብቻ የተሰቀለ አይምሰልህ ለአንተና ከአንተ ጋራ ላሉት ሁሉ ነው፤ እመንበት አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተቆጥቶ እሳት አንድደው ጻድቁን እንዲጨምሩት አዘዘ፡፡ ጻድቁም እያዩት በፈቃዱ ከእሳቱ ውስጥ ገባ፤ አሳቱም ውሃ ሆነ፡፡ ሰራዊቱም ተደንቀው እኩሌቶቹ አመኑ፤ ንጉሡ ግን ተቆጥቶ ያመኑትን በሰይፍ አሰይፏቸው በሰማዕትነት ሞቱ፡፡ ከዚያም ሰይፉን መዞ ሊመታው ተወርውሮ ሲሔድ መብረቅና ነጎድጓድ መጥቶ እስከ ሠራዊቱ አጠፋው፡፡ ጻድቁም የሞቱትን ሰዎች ነፍሳቸውን መላእክተ ጽልመት

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተማምኜ አላውቅም በሰው ✞

ተማምኜ አላውቅም በሰው
ተደግፌ አላውቅም በሰው
ታሪኬ ኢየሱስ ነው

እርሱን አመስግኜ እርሱን አወድሼ
ይኸው እኖራልሁ ዕንባዬን አብሼ
ማን ደርሶልኝ ያውቃል ስተክዝ ሲከፋኝ
ክብር ለማርያም ልጅ ታሪኬ ለሆነኝ

             /አዝ=====

ጥልቁን ያሻገረኝ እጄን በፍቅር ይዞ
ማዕበል ሞገዱን ጸጥ ያረገው አዞ
እርሱ ነው ወዳጄ የቆጠረኝ ከሰው
የሕይወቴ ታሪክ ስሙም ኢየሱስ ነው

             /አዝ=====

ምስጋናን የሞላኝ ቅኔን ያስተማረኝ
ምግብና መጠጤ ደስታዬ የሆነኝ
ኧረ እሱስ ፍቅር ነው እንደ ሰው አይደለም
ስሙን አልሸሽግም እገልጣልሁ ለዓለም

             /አዝ=====

ከሚያስተማምነው አረፍኩ ከመዳፋ
ጸጥታ ከሞላው ሰላም ነው እቅፋ
ከሰው አልጠብቅም ከሰው ምን አለና
እርሱ አያልቅበትም ቸር አባት ነውና

             /አዝ=====

ጸጋውን ሳይሰስት ሰጥቶኝ በቸርነት
ይኸው አውጃለሁ የገባኝን እውነት
አንተ ባትሞትልኝ ስለእኔ ባትደማ
ከየት አገኝ ነበር የክብርህን ዜማ

👉 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ተሰድጄም አገር አለኝ ✞

ተሰድጄም አገር አለኝ
በሄድኩበት የሚያሳርፈኝ
ዛሬም ነገም መመኪያዬ
እግዚአብሔር ነው አለኝታዬ
(፪×)


በዚያ በበረሀ እኔን እየመራ
ደጋፊዬ ነበር ልቤ እንዳይፈራ
ጥሜን ቆረጠልኝ አፍልቆ ከአለቱ
አቤት የኔ ጌታ ግሩም ደግነቱ

          /አዝ=====

በማላውቀው ምድር በባዕዱ ሰፈር
አለህ የምታውቀኝ የኔ ጌታ እግዚአብሔር
እስኪያልፍ እኔ አልልም ማለፍ በስምህ ነው
ልቡ ያለቀሰበት አንተን ይዞ ማነው

          /አዝ=====

አባት ካሉት በላይ ወገን ካሉት በላይ
ይብዛልኝ መታመን በፈዋሽህ ፀሀይ
የኔ መሰማራት ሆኖአል በለምለሙ
ነፍሴን አሳርፏት ኢየሱስ ሰላሙ

👉 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
         
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ዘለሰኛ
#እጅግ ብዙ ነው ቸርነቱ
#ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

3. #ምኩራብ
   ምኩራብ የአይሁድ ቤተ ጸሎት ናት፡፡ በብሉይ ኪዳን የአይሁድ አምልኮ በኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ ላይ ብቻ የሚፈጸም ነበር፡፡ በኋላ ንጉሥ ናቡከደነፆር ቤተ መቅደሳቸውን አፍርሶ ሕዝቡንም ማርኮ ወደ ባቢሎን አፈለሳቸው፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለጸሎትና ለማኅበርተኝነት ልዩ ቤት በመሥራት ስሙን ምኩራብ አሉት፤ (ሕዝ 11፥16)፡፡ በዚህ ምኩራብ ይጸልያሉ፣ ይማራሉ፣ ያስተምራሉም፤ በአጠቃላይ ከመሥዋዕተ ኦሪት ውጭ የቀረውን ሥርዓተ አምልኮ ሁሉ ይፈጽሙበት ነበር፤ መሥዋዕት ለማቅረብ ደግሞ ወደ ኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ይሄዱ ነበር፡፡
  ኢየሱስ ክርስቶስ በዚያ ምኩራብ ለማስተማር በገባ ጊዜ ከግብሯ በተቃራኒ መሸጫና መለወጫ ሆና ርግብና በሬ ሲነግዱባት አገኛት፡፡ ጌታም ይህን በተመለከተ ጊዜ ‹‹ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት›› (ማቴ 21፥13 ፣ ኢሳ 56፥7 ፣ ኤር 7፥11) በማለት ለጸሎት ሳይሆን ለንግድ የገቡትን ከምኩራብ እንዲወጡ በጅራፍ እየገረፈ አባሯቸዋል፡፡ ጌታ ይህን ያደረገበት ሳምንት መታሰቢያ በመሆኑ ሳምንቱ ምኩራብ ይባላል፡፡
   በዚህ ሳምንት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹የቤትህ ቅናት በልታኛለችና የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቋልና፤ ነፍሴን በጾም አስመረርኳት ለስድብም ሆነብኝ›› (መዝ 68፥9) የሚለው ሲሆን የዕለቱ ወንጌል ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተ መቅደስ ርግቦችን፣ በሬዎችን፣ በጎችን ወዘተ ይሸጡና ይለውጡ የነበሩትን ከቤተ መቅደሱ ማባረሩንና ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ‹‹የቤትህ ቅናት ይበላኛል›› የሚለው ትንቢት መፈጸሙን እንዳስታወሱ ይነገራል፤ (ዮሐ 2፥12-25)፡፡ ጌታ በዕለቱ በሬ፣ በግ፣ ርግብ ወዘተ ይሸጡ የነበሩትን ከምኩራብ አስወጥቶ በእነዚህ እንስሳት ይፈጸም የነበረውን መሥዋዕተ ኦሪት አልፎ የክርስቶስ ሥጋና ደም ብቻ የሚሠዋበት ጊዜ መድረሱን አስተምሯል፡፡
   ቤት የተባለው በምሥጢሩ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነው የሰው ሰውነት ነው፡፡ ስለሆነም ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሳምንት ሸቀጥ ከተባለው ኃጢአት በንስሐ ታጥበን ለመቅደሱ ሥርዓት የምንመች ሆነን እንድንኖር ትሰብካለች፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ›› (ሮሜ 12፥2) ብሎ እንዳስተማረን በንሥሐ እየታደስን ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያነት ሰውነታችንን ማዘጋጀት ይገባናል፡፡
              ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣  ሰባቱ አጽዋማት
    

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ማረን አምላካችን ✞

አንተ የሰላም ንጉሥ መልካሙ እረኛ
እግዚአብሔር ብቻ ነህ እውነተኛ ዳኛ
እንባችንን አብስ ይብቃ ኅዘናችን
እጃችንን ሰጠን ማረን አምላካችን

የኢትዮጵያን ትንሣኤ ዘመናት ናፍቆናል
ክንዳችንን ሳይሆን ስምህን አምነናል
በወደድከው ጊዜ ሰላም እንደሚሆን
የቀደመው እባብ(፪×) ይቀጥቀጥልን

              /አዝ=====

እውነት ነው ጌታችን በዝቷል በደላችን
አክሊላችን ወድቋል ተገፏል ፀጋችን
በርኩሰት ስንጠፋ ተላልፈን ሕግህን
በአባታዊ ፍቅርህ ማረን ልጆችህን

              /አዝ=====

አንድስ እንኳን የለም ጽድቅን የሚያወራ
የገዛ ክንድህ ነው ተዓምር የሚሰራ
እንዳንጠፋፋ እንዳንነካከስ
የእጅህ ስራ ሁሉ(፪×) በስምህ ይፈወስ

              /አዝ=====

የኢትዮጵያን ትንሣኤ ዘመናት ናፍቆናል
ክንዳችንን ሳይሆን ስምህን አምነናል
በወደድከው ጊዜ ሰላም እንደሚሆን
የቀደመው እባብ(፪×) ይቀጥቀጥል


👉 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ዘለሰኛ
#ይሄ_ነው_ቃሉ
# @enamsgn @enamsgn

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ዘለሰኛ
#አቤቱ
# @enamsgn @enamsgn

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ ✞

በጾም ትትፌውስ ቁስለ ነፍስ
'ወበጸሎት ትትኃሰይ መንፈስ/2/

መዓልትና ሌሊት በጾም ፀሎት ተግቶ
አሳይቷል ጌታ ስርዓትን ሰርቶ
አይቀርም ፈተናው ትጋት ከሌለበት
ስጋ ካልደከመ ች በጾምና ፀሎት

             /አዝ=====

ሙሴ የተባው ያ የእግዚብሔር ሰው
የበራለት አርባ ቀን ፆሞ ነው
በሲና ተራራተቀብሎ ህግ
እርሙን እንድንተው አሳየን መንገድ

             /አዝ=====

የፀሎት ናቷ ስለሆነች ጾም
ትህትናን ይዘን ደግሞም ንድ ሆነን
ተጋ በፀሎት ንሰሐ ጋራ
ታደርሰናለች ከጽዮን ተራራ

             /አዝ=====

አንደበትም ይጹም አይም ይረጋጋ
ጆሮም ክፉ ሰምቶ ነፍሱን እንዳይወጋ
ድሃን ከመበደል ልብም ተመልሶ
መጾምስ እንዲ ነው የበደለን ክሶ


👉 ዘማሪ አቤል ተስፋዬ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ በእርሷ ፀልዩ ✞

በፍቅሩ በከበረች
በደሙ በታነፀች
ባለመ መላእክት በነበረች
በሰማዕታት ደም በፀናች

ፀልዩ በሐበ ዛቲ ቤተክርስቲን ቅድስት
ወማኅበረነ ውስቴታ

ሐዋርያት በሰበኳት
ድል ነሽዎች በሞቱላት
ደናግላን በመነኑላት
ስለእርሷ በኖሩላት

ፀልዩ በሐበ ዛቲ ቤተክርስቲን ቅድስት
ወማኅበረነ ውስቴታ

የሰማይ ደጅ በሆነች
ከጽንፍ እስከጽንፍ በተሰራች
የምስጋና ዥረት በሚፈስባት
ፀልዩ በእርሷ በእውነት

ፀልዩ በሐበ ዛቲ ቤተክርስቲን ቅድስት
ወማኅበረነ ውስቴታ

ስጋውና ደሙ በሚሰዋባት
መላዕክቱ በሚረቡባት
ከፍ ብላ በተሠራች
በመስቀሉ ድል ባደረገች

👉 ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አምላክ አደራ ተለመነን ✞

አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ ድንግል ማርያም ማረን ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስላዛኝት ብለህ ማረን ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ እማአምላክ ብለህ ማረን ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/

አፍላጋቷን ሙላ ወንዞቿን ባርክላት
ምድሪቷን አሳርፍ ኢትዮጵያን ቀድሳ
የሰዶምን እሾህ አምላክ ንቀልላት
አምላክ አደራ ተለመነን/2/

ስለ መላእክቱ ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለሚካኤልም ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ ቅዱስ ገብርኤል ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ እሩፋኤልም ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ ዑራኤልም ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ እራጉኤልም ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/

ስምህን ስጠራ እጆቿን ዘርግታ
እንደወጣ አይቅር አይርገፍ ወጣቷ
በናትህ ሀገር ላይ አይሰልጥን ጠላቷ
አምላክ አደራ ተለመነን/2/

ስለሰማዕታት ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለህፅን-ቂርቆስ ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለአርሴማ ቅዱስት ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለእስጢፋኖስ ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለቅዱስ ጊዮርጊስ ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/

ከነአን ኢትዮጵያ ይስመርላት ሰብሉ
በፊትህ ይደጉ ልጆቿ በሙሉ
ዘንባባውን ይዘው ሆሳዕና እንዲሉ
አምላክ አደራ ተለመነን/2/

ስለ ቅዱሳኑ ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ ተክለሀይማኖት ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለሀራ-ድንግል ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ አቡነ አሮን ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/
ስለ ሐብተማርያም ብለህ ይቅር በለን
አምላክ አደራ ተለመነን/2/

አሳደጊ አይጡ ህፅናት ተወልደው
አዛውንት ይጦሩ እድሜ ካንተ ጠግበው
እንዲያገለግሉ እንደ ካሌብ ሆነው
አምላክ አደራ ተለመነን/2/

አምላክ አደራ ተለመነን/4/


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ሰበር ዜና

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ሕገወጡ ቡድን በፈጠረው ቀኖናዊ ጥሰት እና ህገ ወጥ እንቅስቃሴ ከሁለት ቀናት በፊት ሰላም መቋጨቱ መታወጁ ይታወሳል። አሁን ግን የምንሰማቸው  ነገሮች ነገሮች  ሁሉ እንደገና ጆሮን ጭው የሚያደርጉ ቤተ ክርስቲያንን የሚከፋፍል አባቶችን ከልጆች ልጆችን ከአባቶች የሚያሻክሩ ነገሮችን ሆነዋል።

በዛሬው እለት ወደ ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ "አዲሱ ሲኖዶስ" በሚል አዲስ ስም እስካሁን ከሚጠቀሙበትም ለየት ባለ ስም የተሰጠ መግለጫ በሚል በሰጡት ባስተላለፉት

ሁሉም በአንድነት ጵጵስናው የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸውም የኤጲስ ቆጶስነቱ ደረጃም በስምምነቱም በጋራ የጠፋ ወይም የተሻረ የተደመሰሰ መሆኑን እያወቁም የቅድስናውን ልብስ በመልበስና ሌሎችም የስምምነቱ አካል ሆነው ስምምነቱን ያነበቡት ሳይቀሩ በአንድ ላይ ስምምነቱን ጥሰውታል ቀኖናውን እንደገና ደግመው ጥሰውታል።

ሹመታቸው ሕጋዊ እንደሆነና በምንም ይሁን በምን የማይሻር መሆኑንም መልእክት አስተላልፈዋል።ይህ ከዕለት ወደ ዕለት የሚታይ የሚሰማ ከንቱ ክስ ሆኗል። ከሃይማኖታዊ ይልቅ ፖለቲካዊ ይዘትን ተጎናጽፏል። በሃይማኖታዊ መንገድ በሰላምና በፍቅር በክርስቶስ ደም የተመሠረተችውን ቤተ ክርስቲያን ከመጠበቅ በክርስቶስ ደም የተዋጁትን ምእመናን ከማስተማር ይልቅ በኃይልና በጉልበት ሁሉንም በነገረ ሰሪነት ግጭት በመፍጠር ሁሉንም ለመቆጣጠር ከዕለት ወደ ዕለት ደፋ ቀና ሲሉ ታይተዋል።

ወደ ተዋህዶ ማንም ቢመጣ ተጠቃሚው ራሱ ግለሰቡ ነው ከሄደም ተጎጂው ራሱ ነው!!
ስለዚህ አይናችን ወደ ቤተክርስቲያን ጆሯችን ወደ ቅዱስ ሲኖዶሳችን እናድርግ


✞ @enamsgn @enamsgn
✞ @enamsgn @enamsgn

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ ሰበር መግለጫ!!!
የካቲት 8 ቀን 2015 ዓ.ም

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ እመኑ በእርሱ ✞

እመኑ በእርሱ ድንቅ ያደረጋል ጌታ
በረዶ አዝንቦ ጠላት እየመታ
ውቅያኖስ ጥልቁን ፈጥኖ እያተነነ
ነገር ለወጠ ሁሉ በእርሱ ሆነ

እመኑ በእርሱ ተራራው ነደደ
*** ሸለቆው ታወከ
*** ዝግባው ተሰባብሮ
*** አለቱ ደቀቀ
*** የአህዛብ ጣዖታት
*** በፊቱ ረገፉ
*** በስሙ የታመኑ
*** ወጀቡን ቀዘፉ

/አዝ=====

እመኑ በእርሱ የማይነጋ ለሊት
*** የማያልፍ ቀን የለም
*** ሁሉ ይቻለዋል
*** ጌታ መድኃኔዓለም
*** ፍቅር ነው ዘለዓለም
*** ደግ አባት ለልጁ
*** ሁሌ ተዘርግታ
*** ትኖራለች እጁ

/አዝ=====

እመኑ በእርሱ ሞገድ የማይሰብረው
*** ፅኑ መርከብ አለን
*** አንፈራም አንሰጋም
*** ከእርሱ ጋር እያለን
*** ጠላት ተሸንፏል
*** ሰይጣን አፍሯል ዛሬ
*** ወህኒው ይነዋወጥ
*** በታላቅ ዝማሬ

/አዝ=====

እመኑ በእርሱ ባዶ ነው አይሰራም
** የጠላት ፉከራ
*** የማይተወን ጌታ
*** አለ ከእኛ ጋራ
*** እጅግ አትረፍርፎ
*** ፀጋ ከበዛለት
*** በሞት ጀርባ ቆመን
*** ገና እንዘምራለን

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ሰበር_ዜና

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የቤተክርስቲያን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ አቀረቡ !!
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

( የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም
     አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ)
   
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት የተስጠ አስቸኳይ ሰበር መግለጫ

የኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት መንግሥት ቤተ ክርስቲያኒቱ መግለጫውን ባወጣች ፵፰ ሰዓታት ውስጥ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖት፣ ቀኖና እና አስተዳደራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግሥት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያዬት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በመግለጽ ጥሪ ማስተላለፏ ይታወሳል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይህንን የቤተ ክርስቲያናችንን ጥሪ መሠረት በማድረግ ለውይይት ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሆኖም ግን ውይይቱ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ ሊሆን የሚገባ ነው በሚል በተነሳው ሐሳብ በጉዳዩ ላይ ከሽማግሌዎች ጋር ጥልቅ ውይይት በማድረግ የደህንነት ተሽከርካሪዎች እና የጸጥታ አካላት ብዛት ሲታይ ምእመናንን ስጋት ላይ እንዳይወድቁ እና ላልተጋባ ጉዳት እንዳይዳረጉ በማሰብ የሰላም ጥሪውን መንግሥት ከተቀበለ እና በቤተ መንግሥት መገኘቱ ሰሕዝባችን የሚያመጣው መፍትሒ የሚኖር እንደሆነ በማሰብ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችንን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በቤተ መንግሥት የሚገኝ መሆኑን እያሣወቅን ሕዝበ ክርስቲያኑም አባቶች የደረሱበትን ውጤት እስኪያሳውቁ ድረስ በትእግስት ትጠባበቁ ዘንድ እናሳስባለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
የካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ርግብና ዋኔን ✞

ርግብና ዋኔን
አብረዉ ዘመቱና ዋኔን
ርግብ ደህና ገባች >> /2/
ዋኔን ገደሉና >> /2/

በዘርና ጎሳ ዋኔን
ሠዉ ሁሉ ተከፍሎ >>
ሰይፍንም ጨበጠ >>
ልቦናዉ ቂም አዝሎ>>
ሰላምን የሚያወርድ >>
እንድ የሚያረገንን >>
እባክህን አምላክ >>
ሙሴን አድለን >>
ሠላምህን አብዛ ምድሪቷን አሳርፍ
የቅዱሳን አምላክ በጭንቃችን ድርስ /2/

             /አዝ=====

በወገን ላይ ወገን ዋኔን
ይብቃ መነሳቱ >>
ይስፈን በምድር ላይ >>
የእግዚአብሔር መንግስቱ >>
ጦራችን ይሰቀል >>
እንያዝ በገና >>
ሠላምን እናዚም >>
በፍቅር እንፅና >>
ምድሪቷን አሳርፍ ሰላምህም ይብዛ
በአንድነት አኑረን የአለሙ ቤዛ /2/

             /አዝ=====

የመርገም ጨርቅ ሆነ ዋኔን
ፅድቃችን በሙሉ >>
አንተን ያልበደለ >>
ማነዉ በዘመኑ>>
አማነዉ በማታ >>
ቀን ያከበርነዉን >>
የኛ ስራ ሆኗል >>
መክሰስ የበቃው >>
ፍቅር ባትሆን ኖሮ ባያቅትህ መጥላት
አይታይም ነበር የሰዉ ልጅ በህይወት


👉 ሊቀ ዲያቆናት ነብዩ ሳሙኤል

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

4. #መጻጉዕ
   መጻጉዕ ማለት ድውይ፣ በሽተኛ ማለት ነው፡፡ ሳምንቱ በዚህ ስም የተሰየመበት ምክንያት ለ38 ዓመታት በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ ተይዞ ይኖር የነበረውን ሰው ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተአምር የፈወሰበት ሰንበት መታሰቢያ ስለሆነ ነው፤ (ዮሐ 5፥5-6)፡፡
   ታሪኩም እንዲህ ነው፡- በኢሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ (ቤተ ሣህል/ ምሕረት) የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት፡፡ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች፣ ዕውሮች፣ አንካሶችና ሰውነታቸው የሰለለ ብዙ ሕዝብ በእነዚህ አምስቱ መመላለሻዎች ውስጥ ይተኙ ነበር፡፡ በሳምንት አንድ ቀን (የዮሐንስ ወንጌል አንድምታ ዮሐ 5፥4 ቀኑ ቅዳሜ መሆኑን ይገልጻል) የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ ውኃውን ያናውጠዋል፤ ከውኃው መናወጥ በኋላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ድኖ ጤናማ ይሆን ነበር፡፡ በዚያም ለ38 ዓመታት የታመመ አንድ ሰው ነበረ፤ ኢየሱስ ይህን ሰው ተኝቶ ባየው ጊዜ እስከ አሁን ብዙ ዘመን እንዲሁ እንደ ሆነ አውቆ ‹‹ልትድን ትወዳለህን?›› አለው፡፡ ድውይውም ‹‹ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም፤ ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለሁ ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል›› ብሎ መለሰለት፡፡ ኢየሱስም ‹‹ተነሣና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› አለው፡፡ ወዲያውም ድኖ አልጋውን ተሸክሞ ሔደ፤ (ዮሐ 5፥2-9)፡፡ በተለያዩ ደዌያት የተያዙ ሰዎች የመልአኩን መውረድ የውኃውንም መናወጥ እየተጠባበቁ መጠመቃቸውና መፈወሳቸው በዘመነ ብሉይ በጸበል የመጠመቅ ትውፊት መኖሩን ያመለክታል፡፡ መልአኩ የሚወርድበት ምክንያት ደግሞ ለቀድሶተ ማያት (ውኃውን ለመባረክ)፣ ለአዕርጎተ መሥዋዕት (መሥዋዕትን ለማሳረግ) ነው፡፡ መጀመሪያ የገባ ሰው ብቻ መዳኑ በብሉይ ኪዳን ዘመን ፍጹም የሚባል ድኅነተ ሥጋም ሆን ድኅነተ ነፍስ አለመኖሩን ሲያመለክት አንዳንድ ሰው መዳኑ ደግሞ የእግዚአብሔር ምሕረት ፈጽሞ እንዳልራቀ ያስገነዝባል፡፡ አምስቱ መመላለሻዎች የተባሉት የአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት፣ መልአኩ የቀሳውስት፣ ውኃው የጥምቀት ምሳሌ ናቸው፡፡
   በዚህ ዕለት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋልና፤ እግዚአብሔር በደዌ አልጋ ሳለ ይረዳዋል መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል›› (መዝ 40፥1-3) የሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ነው፡፡
              ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣  ሰባቱ አጽዋማት
               
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ይበላሃላ ✞

ይበላሃላ(፮×)
አንተንም አፈር ይበላሃላ
እንደ ሞኝ ሰው እንደተላላ

ሞኜ ተላሌ(፬×)
ይደላህ መስሎህ ነገ እንደ ዛሬ
ንስሃን ትተህ ተበላህ አውሬ
ሞኜ ተላሌ(፪×)

በላው አፈር(፬×)
ያንን ወታደር ያንን ምሁር
በላው አፈር(፪×)

ንስሃ ግባ የእናቴ ልጅ(፪×)
የክተት ጥሪ ሳይታወጅ
ስራና ሰሪው ሳይቀናጅ
ንስሃ ግባ የእናቴ ልጅ

ንስሃን ትተህ የት ትሄዳለህ(፪×)
ሲመለከቱህ ታሳዝናለህ
ንስሃን ትተህ የት ትሄዳለህ

በላው አፈር(፬×)
ያንን ገበሬ ያንን ወታደር
በላው አፈር(፪×)

ተሰብሰብ ዛሬ ወደ አምላክህ(፪×)
እንድታመልጠው ሰይጣንን ፈጥነህ
ተሰብሰብ ዛሬ ወደ አምላክህ

የሰላም አምላክ ሲጠራህ ስማ(፪×)
በጠላት ነፍስህ እንዳትቀማ
የሰላም አምላክ ሲጠራህ ስማ

ፆምና ጸሎት ምጽዋት ሆነህ(፪×)
መድኃኒት ሆኑህ ዓለም ያዳነህ
ፆምና ጸሎት ምጽዋት ሆነህ

👉 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ እጅግ ብዙ ነው ቸርነቱ ✞

ኧ...................ኸ
እጅግ ብዙ ነው ቸርነቱ

እጅግ ጥልቅ ነው ቸርነቱ
ጌታ ስጦታህ ማስደሰቱ
ለጋሽ አምላክ ነው አያልቅበት
ለሚታመኑት በሃይማኖት

ኧ...................ኸ
ለጋሽ አምላክ ነው አያልቅበት

ወዛዝርት ሁሉ በጎዳና
ይሯሯጣሉ ያለ ጤና
የልኳንዳ ቤት ተበራክቷል
ሥጋ በይፋ ይሸመታል

ኧ...................ኸ
እጅግ ድንቅ ነው ቸርነቱ

ሻጭ ቢቸግራት ቢርባት
ሥጋዋን ሸጠች ያለ እፍረት
ገዢው ይገርማል ቅምጥሉ
እ'ቱን ይበላል ለአመሉ

ኧ...................ኸ
ለጋሽ አምላክ ነው አያልቅበት

አስነሱት አሉ ደሃውን
ዓለምን ጠልቶ ቢመንን
አንድ ከስንዝር መሬቱን
ይነሱት ይሆን ርስቱን

ኧ...................ኸ
እጅግ ድንቅ ነው ቸርነቱ

እፍረት የሚሏት የሰው ነዋይ
ተለወጠች ወይ በአባይ ሚዛን
ሰውን ቢንቀው ባያፍር
ተደፈረ ወይ እግዚአብሔር

ኧ...................ኸ
ለጋሽ አምላክ ነው አያልቅበት

መግረፊያው ብዙ የእግዚአብሔር
ምንም ከፍታ ብንኖር
ጤናው በእጁ ነው አርጩሜው
ግፈኛን አስሮ መግረፊያው

ኧ...................ኸ
እጅግ ጥልቅ ነው ቸርነቱ

ብቻዬን ሆኜ ሳስበው
አስደነገጠኝ የመጪው
እያጣቀሰ ግፍ የጠራው
ያባራ አይመስልም ከነአካቴው

ኧ...................ኸ
ለጋሽ አምላክ ነው አያልቅበት

አፋ እስኪቀደድ የጎረሰው
አይጠረቃም ወይ ወየው ወየው
ትርጉም ለሌለው ለዚህ ዓለም
ለማይኖርበት እንዲህ መድከም

ኧ...................ኸ
ለጋሽ አምላክ ነው አያልቅበት

ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


      ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ የጴጥሮስን ዕንባ ✞

የጴጥሮስን እንባ ስጠኝ እልሃለሁ
ኃጢአቴን ልናዘዝ ፍቅርህን እያየሁ
በሞት ጥላ ውስጥ እንኳን ብሄድ ጌታሆይ(፪)
ልቤን በፍቅር ውሃ እጠበው እባክህ

ቸርነትህ በዝቶ ምህረት ቢያሰጠኝ
እጀቼን ዘርግቼ እማጸናለሁኝ
ደምህ የፈሰሰው ለኔ ስለሆነ(፪)
በኃጢአት ልተወኝ ልብክ አልጨከነም
      
           /አዝ=====

ዓለማዊ ምግባር ልቤ ቢከተልም
ከዚህ ሁሉ ማዳን ጌታ አይሳንህም
ኃጢአት እየሰራሁኝ ባስቀይምህም(፪)
በሄሶጵ እርጨኝ ጌታ እጠበኝ እባክህ
       
           /አዝ=====

ዲያቢሎስ ያመጣው ጸጸት የውድቀት ነው
የይሁዳ ምሬት የሞት ነው ፍፃሜው
ይህንን መማረር እኔ አልፈልግም(፪)
የውድቀት ጉዞ እንጂ ትንሳኤ የለውም

           /አዝ=====

ጴጥሮስ አባብሎ የተማጸነበት
ፍቅሩን በንስሐ ስቦ ያመጣበት
ፍፃሜው የሚያምር ንስሐ ስጠኝ(፪)
የለቅሶ  አምሀ የእንባን ይወት ስጠኝ

   👉 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

ዜና ዕረፍት

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቀሌ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
በረከታቸው ይደርብን

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ዘለሰኛ
✞ ይሄ ነው ቃሉ ✞

ኧኸ........ኸኧ.........ኧኸ.............ኸኧ

ህዝቡን በይፋ ሲያሳምኑ
ሂዱ ቢላቸው ደርሶ ቀኑ
የተናገረው #ይህ_ነው_ቃሉ
ልጆች በወላጆች ይነሳሉ

ኢየሩሳሌም ያደነቀው
ጌታን በውሃ ያጠመቀው
በስራው ሁሌ የሚረካ
መንገድ ጠራጊ ሆኗል ለካ

ኧኸ.......ኸኧ........ኧኸ.............ኸኧ

የኢየሱስ ደቀመዛሙርት
በእለተ ሰንበት በጠዋት
እሸት ቢቀምሱ እርቧቸው
ቀጠፋ ብለው ወቀሷቸው

ኢየሱስ አለ ከጎናቸው
ፈሪሳውያን ቢከሷቸው
እርሱም ፈረደ የሚበጅ
ለሰንበት ጌታ ለሰው ልጅ

✞ እኔን እኔን እኔን ✞

ጌታን ለመውቀስ ቢያጡ መላ
ከሀጢያተኞች ጋር አሉት በላ
ሠምቶ መለሠ በጽሞና
ለጻድቃን መቼ መጣሁና

አንስቶ ድጏስ የሱን አንባር
መቼም ላይራብ ላይጠማ
በእምነት በጥምቀት የተሠራ
ጌታ ለህይወት ነው እንጀራ

በምድር ላይ ለስጋው እየባጀ
የሰማይ ቤቱን ያላበጀ
ነፍሱን ሲነጥቃት ክፉ ሞት
እሳት ነው ስሙ በአምላክ ፊት


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

#ዘለሰኛ
✞ አቤቱ ✞

ኧኸ........................አቤቱ


ከማያውቁት ሃገር ጊዜ መሽቶበት/2/
ብቻውን አደረ ከመቃብር ቤት አቤቱ

አቤቱ

ከትንሳኤው ሳንደርስ ከዕለተ ምፅዓት/2/
አሁኑኑ አለቀ ገና በህማማት አቤቱ

አቤቱ

ወርውረው ቢጥሉት ሸክላ መች ይድናል/2/
ለካስ ይሰበራል ገል አፈር ይሆናል አቤቱ

አቤቱ

ዕዝራ በመሰንቆ ዳዊት በበገና/2/
ሙሴ ቀድሞ አለፈ ተሸክሞ መና አቤቱ

አቤቱ

እመቤቴ ወልዳ የጌታዬ እናት/2/
ምን ልሂድ አልሂድ የተጠራሁ እለት አቤቱ

አቤቱ

አሁን ምን ያጣላል የመሬት ጉዳይ/2/
እንዲህ ዘር ሲጠፋ ይቀር የለወይ አቤቱ

አቤቱ

ታላቅ ታናሽ ስጋ ሞልቶ በገበታ/2/
ልብን መርጦ አየነው በህይወት የኛ ጌታ አቤቱ

አቤቱ

ሁለት ወር ሁዳዴ ፆሞ እያነባ/2/
ለምን ይርበዋል ህማማት እየገባ አቤቱ ጌታዬ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ኢትዮጵያ እጅሽን ዘርጊ ✞

ኢትዮጵያ እጅሽን ዘርጊ
ወደ አምላክ ወደ አዶናይ
ህዝብሽን ከሞት የሚያድን
ይዉጣልሽ የምህረት ፀሐይ


ህጻናት ወላጆች አጥተው በሜዳ ሲበታተኑ
ንስሮችሽ ወጣቶች አልቀው የአፈር ሲሳይ ሲሆኑ
የሞት መልአክ ተልኮብሽ መሬትሽ አጥታ ጸጥታ
ቁጣዉን እንዲመልሰው ለምኚ የሰማይ ጌታ

              /አዝ=====

ታማሚው እያጣጣረ ጤነኛው ቆሞ ሲፈራ
አምላክሽ ይቅር ይበልሽ ይለፍሽ ይሄ መከራ
አበዉን ይዘሽ ተነሺ ጸሎትሽን ቆመሽ አድርሰሽ
ያብርደው እሳት ንዳዱን በምልጃሽ በልመናሽ

              /አዝ=====

ልጆችሽ ቅጣት ገብቷቸው እንዲያዩ  ወደ አምላካቸው
መከራው ትምህርት ሆኗቸው ይመለስ ታካች ልባቸው
የበደልነውን ታግሶ ቁጣውን እርሱ መልሶ
ይማረን ይቅር ይበለን ጽኑ ምህረቱን አስታውሶ

              /አዝ=====

አህዛብ ተነጋገሩ አምላክሽ እረሳሽ ብለው
ልጆችሽ ሞት ሲፈጃቸው እያዩ እጅግ ተገርመው
ጉልበትሽ እንዳይሰበር ምርኩዝሽ እርሱ ነውና
ደዌ ቸነፈሩን ያርቅ አቅርቢ ፅኑ ልመና

👉 ዘማሪ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ኪዳነ ምህረት እናቴ ✞

ኪዳነ ምህረት እናቴ አማልጂኝ እኔን ከልጅሽ 
የፍቅር እናት ነሽና አማልጅኝ እኔን ከልጅሽ 
የሰላም እናት ነሽና አስታርቂኝ እኔን ከልጅሽ 

የተገለጠው ብርሀን በምስራቅ የተወለደው 
በፍቅር ሰንሰለት ታስሮ ይህንን ዓለም አዳነው (፪) 

               /አዝ=====

በረሀውን ባሰብኩት ጊዜ የግብፅን የአሸዋ ግለት 
አንቺ ትንሽ ብላቴና ኧረ እንዴት ቻልሽው በእውነት(፪) 

               /አዝ=====

ዝም ብዬ ይደንቀኛል የአምላክን ሥራ ሳስበው
ምክንያት አንቺን አድርጎ ዓለምን ሁሉ አዳነው(፪)


👉 ሊቀ መዘምራን ይልማ ሃይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ 
      ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ቀኑን በሙሉ እንከፋለን ✞

ቀኑን በሙሉ እንከፋለን
የሚረግሙንን እንመርቃለን
ልምዳችን ሆኗል ስደት በማታ
ያልሆነው የለም ባንተማ ጌታ ባንተማ ጌታ


እጅግ ብዙ ነገር ባንተ ደርሶብናል
እየተገፈተርን ከሙክራብ ወተናል
ባያቁት ነው እንጂ ባያስተውሉት
እየሱስ ፍቅር ነው ያለም መዳኒት

            /አዝ=====

እብዶች አይደለን እናስተውላለን
ለዘመን የማይቆም የፀና ቃል አለን
አይዟችሁ አትፍሩ ተፅናኑ በጌታ
ይፍታ ሲል ይፈታል የሲኦል ጅማቷ

            /አዝ=====

ፈተናና ስቃይ መከራ ቢበዛ
ሰለቸኝ አያቅም በደም የተገዛ
ሁሉም ለበጎ ነው ሁሉም ለክብራችን
እስካለም ዳርቻ ተሰምቷል ድምፃችን

            /አዝ=====

የቀደሙት ሁሉ ባንተ ተሰደዋል
በሠንሠለት ታስረው ሸንጎ ፊት ቆመዋል
በቀስትና በጦር በፊትህ እረገፉ
ወጡ ከዚች አለም ታሪክ እየፃፉ


👉 ዘማሪ ዲ/ን እንዳልካቸው ዳኘው

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢    ✥
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
          ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
                                    ✥   ✢   
   ╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ ድል አለ በስምህ ✞

ድል አለ በስምህ ድል አለ በቃልህ(፪×)
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኔአለም ስልህ

ቃዴስን ታላቁን በረሃ
አለፍነው ሳንጠማ ውሃ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የጸና ስምህ ነው
አምላኬ የጸና ስምህ ነው

/አዝ=====

በእልልታ ቢፈርስ ኢያሪኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢ ሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ካንተ ነው(፪×)

/አዝ=====

ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማራ ውሃ ቢጣፍጥ
ብንበላ መናን ከሰማይ
ስለሆንክ ነው አዶናይ
ስለሆንክ ነው ሁሉን ቻይ

/አዝ=====

የቆምነው ዛሬ በሕይወት
ስምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ከተርጠን ብንነግሥ
ሆነህ ነው ክብርና ሞገሥ(፪×)

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

​​✞ ምስጋናው ይቀጥል ✞

ምስጋናው ይቀጥል ዝማሬው ይቀጥል
እግዚአብሔር ስላለ ከያዘ የማይጥል
በምናየው ነገር በምንሰማው ወሬ
እንዳይቆም ምስጋና እንዳይቆም ዝማሬ

የሰማእታቱ ደም የፈሰሰው በምድር
አይተናል ሲያስቀጥል የክርስትናን ዘር
እንድናምን ብቻ መች ተጠራን እና
በእሳቱም መካከል ቅኔ አለን ምስጋና

/አዝ=====

መች ማጥፋት ይቻላል እሳትን በእሳት
አይቆምም ማህሌት ቅዳሴ ሰዓታት
ከሰማዩም በላይ ከሰማዩም በታች
ቤተ ክርስቲያን ዛሬም ነገም አለች

/አዝ=====

የዓለም ጨው ሆነን በዓለም የበዛነው
እየተደበደብን እየተገፋን ነው
በገደሉን ጊዜ ቁጥራችን ይበዛል
ከሞትም በኃላ ሂወት ይቀጥላል

/አዝ=====

የተስፋይቱን ምድር ተነሱ እንወርሳለን
በመዝሙር በእልልታ ቅጥሩን እያፈረስን
የሰላዮቹን ቃል ሰምታችሁ አትፍሩ
በሃይማኖት ጽኑ በእምነታችሁ ኑሩ


#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።


        ✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖  
❖ @enamsgn @enamsgn ❖         ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ✞

በሰው ዘንድ ቢሟጠጥ ተስፋ እና ደስታ
እኛስ ፈጣሪ አለን ሁሉን የሚረታ
ተስፋ እንደ ሌላቸው አንሆንም ከቶ
ክርስቶስ አለልን የሚያሳይ አብርቶ

ያለቀሱ ሁሉ ይስቃሉ አይቀርም
ይለዋውጠዋል ጌታ መድኃኔዓለም
ማንም ያላሰበው ያልጠበቀውን ድል
ለእኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል
ማንም ያልጠበቀው ያልገመተውን ድል
ለእኛ ለምስኪኖች ጌታ ይሰጠናል

/አዝ=====

ሰዎች ቢጠበቡ ገንዘብ ለመሰብሰብ
ይጠላለፋሉ ባልጠበቁት መረብ
እግዚአብሔርን ይዘው በቅን ካልተጓዙ
ክፋት እና ተንኮል ብዙ ነው መዘዙ
እግዚአብሔርን ይዘው በቅን ካልተጓዙ
ክፋት እና ተንኮል ብዙ ነው መዘዙ

/አዝ=====

ድሆች አስለቅሶ ግፍ የሚሰበስብ
ምን ይመልስ ይሆን በጌታ ፊት ሲቀርብ
ለዝች አጭር ዘመን የሚስገበገቡ
አይረኩም አይጠግቡም ድሆች እያስራቡ
ለዝች አጭር ዘመን የሚስገበገቡ
አይረኩም አይጠግቡም ድሆች እያስራቡ

/አዝ=====

የእህል ሽታ ጠፍቶ መሶቡም ቢራቆት
ተስፋችን ሙሉ ነው እኛስ በጌታ ፊት
ይህን ክፉ ዘመን ያሻግራል ጌታ
ከሰራን በኋላ በፀሎት እንበርታ
ይህን ክፉ ዘመን ያሻግራል ጌታ
ከሰራን በኋላ በፀሎት እንበርታ

👉 ሊቀ-መዘምራን ይልማ ሀይሉ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…

ዜማ ዘቅዱስ ያሬድ

✞ አትፈርስም ✞

አትፈርስም አትጠፋም በጠላት (2)
ኢየሱስ ነው በደሙ የመሰረታት
ኢየሱስ ነው ተዋህዶን ያነፃት

የሚደክሙ በከንቱም የሚለፉ
የሚታትሩ ተዋህዶን ሊያጠፉ
አይሳካም ምኞታቸው አይሰምርም
ቃል ስላላት በጠላት እጅ አትወድቅም

/አዝ=====

ከሰማይ ነው አይደለም ከምድር
ጠባቂዋ ለዘላለም በፍቅር
የማይፈርስ የጸና ስም ስላላት
ምን ብትለፉ አትችሉም ልታጠፏት

/አዝ=====

የሶስት ሺ ዓመት ታሪክ ያላት
የቀደሙት የተጋደሉላት
ቀን ከሌሊት ለፀሎት የምትተጋ
ስሙ አይኖርም ከእርሷ ጋር የሚዋጋ

/አዝ=====

የእውቀት እና የጥበባት መፍሰሻ
የከበረች አዲስ ክብር የማትሻ
ጠላት ቢጮህ እንዳሻው ቢፎክር
ሙሽራዋ ሞሽሯታል በክብር

/አዝ=====

እንኳን ዛሬ ትናንት ያልፈረሰች
በቀለማት አብርታ የታየች
ብዙ ብዙ እጅግ ብዙ ብትለፉ
ተዋህዶን በጭራሽ አታጠፉ

👉 ዘማሪ ዲ/ን ሙሉቀን ከበደ

#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።

╔ ​✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit
❖ @mezmuredawit @enamsgn
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════​✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ

Читать полностью…
Subscribe to a channel