የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል
💧የበዓሉ አከባበር በኢትዮጵያ
በሀገራችን ኢትዮጵያ ይህ ታላቅ በዓል በየዓመቱ በሚከበርበት ጊዜ ዋዜማው ማለትም ጥር 10 ቀን ‹‹ከተራ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ‹‹ከተራ›› የሚለው ቃል ከተረ፣ ከበበ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም የተከተረ፣ የተከበበ ወይም የተገደበ ማለት ነው፡፡ ይህም ለበዓለ ጥምቀቱ ማክበሪያ የሚሆን ምንጭ ወይም ወንዝ በሚገኝበት ቦታ የሚገደበውን ወይም የሚከተረውን ውኃ የሚያመለክት ቃል ነው፡፡ በዚህም ዕለት የቃል ኪዳኑ ታቦት ከየአብያተ ክርስቲያናቱ ተነስተው በሊቃውንት፣ በካህናት፣ በመዘምራንና በምእመናን ታጅበው ባሕረ ጥምቀቱ ወደ ተዘጋጀበት ስፍራ ሔደው ያርፋሉ፤ ይህም የሚሆነው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መሔዱን ለማሰብ ነው፡፡ ከዚያም የቃል ኪዳኑ ታቦታት ከአደሩበት ቦታ ስብሐተ እግዚአብሔር ሲደርስ ያድርና በማግስቱ ጥር 11 ቀን ጠዋት ባሕረ ጥምቀቱ ጸበል ከተረጨ በኋላ የቃል ኪዳኑ ታቦታት ከቦታው ተነስተው በዝማሬ በምስጋና ታጅበው ወደየመጡበት ቤተ ክርስቲያን በክብር ይመለሳሉ፡፡ ከበዓለ ጥምቀቱ በረከት እንድንሳተፍ አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር በቸርነቱ ይርዳን፡፡ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ስንክሳር ዘጥር 11
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 2015 ብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል
@enamsgn @mezmuredawit
✞ በዛሬው_ጥምቀቱ ✞
በዛሬው ጥምቀቱ እሰይ እሰይ
ተነግሮ አዋጅ እሰይ እሰይ
ነጻነት አገኘን እሰይ እሰይ
በእግዚአብሔር አብ ልጅ እሰይ እሰይ
እሰይ እሰይ ተወለደ
እሰይ እሰይ ተተመቀ/2/
ከሰማየ ሰማይ ወረደ/2/
ከድንግል ማርያም ተወለደ
አብም መሰከረ እሰይ እሰይ
ቃሉን አላበየም እሰይ እሰይ
የምወደው ልጄ እሰይ እሰይ
ይሄ ነው እያለ እሰይ እሰይ
/አዝ=====
ጌታ በዮሐንስ እሰይ እሰይ
ሊጠመቅ ሲል ገና እሰይ እሰይ
ወደ ኋላ ሸሸ እሰይ እሰይ
ዮርዳኖስ ፈራና እሰይ እሰይ
/አዝ=====
ተራሮች ዘለሉ እሰይ እሰይ
እንደ ጊደር ሁሉ እሰይ እሰይ
እፁብ ነው ድንቅ ነው እሰይ እሰይ
ምን ይገርም እያሉ እሰይ እሰይ
/አዝ=====
ውኃን ወይን አረገ እሰይ እሰይ
በተጠራበት ቤት እሰይ እሰይ
የብርሃናት ጌታ እሰይ እሰይ
የዓለም መድኃኒት እሰይ እሰይ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ትህትናሽ ግሩም ነው ✞
ትህትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም /2/
እናቱ ሆነሻል ለመድኃኔአለም /2/
ንጽህይት ስለሆንሽ እመቤቴ እመቤቴ
እንከን ሌለብሽ •••••••• °° ••••••
የፍጥረታት ጌታ •••••••• °° ••••••••
በአንቺ አደረብሽ ••••••• °° •••••••••
የድንግል መመረጥ ••••••• °° ••••••
ዜናው አስገረመኝ •••••••• °° ••••••
እሳቱን ታቀፈች •••••••• °° ••••••••
የማይቻለውን •••••••• °° •••••••••
/አዝ=====
ምርኩዜ ልበልሽ እመቤቴ እመቤቴ
ጥላ ከለላዬ •••••••• °° ••••••••
ጋሻዬ ነሽ አንቺ •••••• °° •••••••••
ለእኔስ መመኪያዬ •••••••• °° •••••••
በአለም እንዳልጠፋ ••••••• °° •••••••
ህይወቴ መሮብኝ •••••••• °° •••••••
እንደ ወይን አጣፍጪው •••• °° •••••••
ድንግል ድረሺልኝ •••••••• °° •••••••
/አዝ=====
የምስራቅ ደጃፍ ነሽ እመቤቴ እመቤቴ
የሁላችን ተስፋ •••••••• °° •••••••••
እሙለ ፀሃይ ጽድቅ •••••••• °° •••••••••
የሁሉ ጠበቃ ••••••••• °° ••••••••••
ድንግል የድል አክሊል ••••••••• °° ••••••
ድንግል የጽድቅ ስራ ••••••• °° •••••••
ድንግል መሰላል ነሽ ••••••• °° •••••••
ለተዋህዶ ተስፋ •••••••• °° ••••••••
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ የአለም ቤዛ ✞
የአለም ቤዛ መድሃኒአለም ነው
በመስቀል የተሰቀለው
ቀድሞ የነበረ መድሃኒአለም
ከአባቱ ጋራ መድሃኒአለም
ሁሉን የፈጠረ መድሃኒአለም
ሁሉንም የሠራ መድሃኒአለም
ስጋችንን ሊለብስ መድሃኒአለም
መጣ ከሰማይ መድሃኒአለም
ሞታችንን ሞተ መድሃኒአለም
ሲኦል እንዳናይ መድሃኒአለም
ድንግል ማርያም የጌታ አናት
ሞገሴ አክሊሌ ናት
በሄድኩበት ሁሉ ድንግል ማርያም
መንገዴን አቅንታ ድንግል ማርያም
ኑሮዬን አስተካክላ ድንግል ማርያም
በበረከት ሞልታ ድንግል ማርያም
የራሴ ላይ አክሊል ድንግል ማርያም
እንዳይወድቅበኝ ድንግል ማርያም
ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም
ጎኔ ቁሚልኝ ድንግል ማርያም
ተክለሃይማኖት አባታችን
መመኪያ ጥላ ጋሻችን
በቅዱስ ወንጌሉ ተክለሃይማኖት
ጣኦት የሰበረ ተክለሃይማኖት
በሰዎች ልቦና ተክለሃይማኖት
እምነትን ያኖረ ተክለሃይማኖት
ለእኛ የተሰጠ ተክለሃይማኖት
ከእግዚአብሄር ተክለሃይማኖት
ተክለሃይማኖት ነው ተክለሃይማኖት
ሰባኪ ወንጌል ተክለሃይማኖት
ሀብተማርያም ስንልህ
አድነን አውጣን ፈጥነህ
መከራና ችግር ሀብተማርያም
ሲበዛ ፈተና ሀብተማርያም
ለሰዎች ከብጄ ሀብተማርያም
ስኖር ያለ ምግባር ሀብተማርያም
ስዕሉ ፊት ቆሜ ሀብተማርያም
ስሜን አከበረ ሀብተማርያም
በሀብተማርያም ሀብተማርያም
ታሪክ ተቀየረ ሀብተማርያም
ሀብተማርያም ስንልህ
አድነን አውጣን ፈጥነህ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ጾመ_ገሀድ
ገሀድ ማለት ‹‹ገሀደ›› ግልጥ ኾነ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ግልጥ፣ ገሀድ ማለት ነው፡፡ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ሲሆን በገሀድ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ደንግጓል፡፡ የገሀድ ጾም ዋናው ምሥጢር የረቡዕ እና የዓርብ ምትክ መሆኑ ነው፤ ጥምቀት ረቡዕ እና ዓርብ ሲውል ጥሉላት ምግቦች (ሥጋ፣ ቅቤ፣ ወተት ወዘተ) ስለሚበሉ ነው፡፡ በጥምቀት ዋዜማ እንድንጾም በተደነገገው መሠረት በጾም ጀምረን በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታ እናከብረዋለን፡፡ ገሀድ በዕለተ እሑድና በቀዳሚት ሰንበት ቢውል ዐርብ እስከ ምሽት ይጾማል፤እሑድና ቅዳሜ ግን የጥሉላት (የፍስክ) ምግቦችን ከመብላት መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡
ጥምቀት የሚውለው ሰኞ ከሆነ በሰንበት ቀን ጾም ስለሌለ ከጥሉላት ምግቦች ብቻ ይጾማል፤ ሌሎች የጾም ምግቦችን ከቅዳሴ በኋላ መብላት ይቻላል፡፡ ጥምቀት የሚውለው ማክሰኞ ከሆነ ሰኞ እስከ ምሽት (እንደየአቅማችን) ሰዓት ድረስ ይጾማል፡፡ ጥምቀት የሚውለው ሐሙስ ከሆነ ረቡዕ ይጾማል፤ ወትሮም ጾም ነውና፡፡ ሌሎቹንም ቀናት ከላይ እንደተገለጸው በመጾም የጥምቀት ቀን የጥሉላት ምግቦችን መመገብ ይቻላል፡፡
ጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት ዕድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሢሕ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኋላ በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ‹‹ይወርዳል፣ ይወለዳል፣ ይሰቀላል፣ ይሞታል፣ ይነሳል›› ብለው የተናገሩለት መሢሕ እርሱ መሆኑ ተገልጧልና እንዲሁም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምሥጢረ ሥላሴ የተገለጠበት በመሆኑ ገሀድ ይባላል፤ (ማቴ 3፥13-17)፡፡ ይህን በማሰብ ጥር 10 ቀን የምንጾመው ጾም የገሀድ ጾም ይባላል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ ጾምና ምጽዋት
✞ ዮርዳኖስ ደስ ይበልሽ ✞
ዮርዳኖስ ደስ ይበልሽ
አምላክ መረጠሽ ተጠመቀብሽ(፪)
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ አድያመ ዮርዳኖስ ✞
አድያመ ዮርዳኖስ
ዖደ ዐቢይ ነቢይ(፪)
ትርጉም፡ ዐቢይ ነቢይ ዮሐንስ የዮርዳኖስን አውራጃ ዞረ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ተናገራ እዝራ ተናገራ ✞
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /4/
ተናገራ ከእናቱ ጋር ታየ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ በበረት ተወልዶ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ የአብ ልጅ እየሱስ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ ከሰማያት ወርዶ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ እጅ መሻ ያዙ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ ግቡ ከግርግሙ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ ጎንበስ ቀና በሉ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ ከደጀ ሰላሙ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /4/
ተናገራ እመቤተ ማርያም ዳዊት ዘመራ
ተናገራ የወርቅ መሰላል ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ ጌታችን ሰው ሆነ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ ካንቺ ከድንግል ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ ማርያምን ለመውሰድ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ አትፍሩ ሁላችሁ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ እናት አድርጓታል ዳዊት ዘመራ
ተናገራ ቅዱስ አምላካችሁ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /4/
ተናገራ በእዝራ መሰንቆ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ በዳዊት በገና ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ ይከብራል ጌታችን ዳዊት ዘመራ
ተናገራ ይወደሳል ገና ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ አለምን ያዳነ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ በበጎ ፍቃዱ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
ተናገራ ጽድቅና ሰላም ነው ዳዊት ዘመራ
ተናገራ የጌታ መንገዱ ዳዊት ዘመራ
ተናገራ እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /2/
እዝራ ተናገራ ዳዊት ዘመራ /4/
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ክርስቶስ_ተወልደ_ወተጠምቀ ✞
ክርስቶስ ተወልደ ወተጠምቀ
አስተርእዮቱ አማን አስተርእዮቱ(፪)
#ትርጉም
ክርስቶስ ተወለደ ተጠመቀ
መገለጡም እውነት ነው
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ አጥመቆ_በማይ ✞
አጥመቆ በማይ(፫)
ዮሐንስ(፪)አጥመቆ በማይ
#ትርጉም
ዮሐንስ በውሃ አጠመቀው።
(ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስን)
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ መጽአ_ቃል ✞
መጽአ ቃል እምደመና /ዘይብል/(፪)
ዝንቱ ውእቱ ወልድየ ዘአፈቅር (፪)
መጣ ቃል ከደመና እንዲህ የሚል(፪)
የምወደው የማፈቅረው ልጄ ይህ ነው(፪)
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯ቅድስት_ሥላሴ (ጥር 7)
ሥላሴ የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ›› ሦስት አደረገ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ነው፡፡ ይህም በምሥጢረ ሥላሴ ስለ ነገረ ሃይማኖት የሚያስረዳ ሲሆን አንድም ሦስትም ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን አንድም ሦስትም ብለን ማመናችንን የምንገልፅበት የሃይማኖት ዶግማ ነው፡፡ የሥላሴ አንድነታቸው በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በስልጣን፤ (ኢሳ 66፥1) ሲሆን በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ቢባሉም አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አማልክት አይባሉም፤ (2ቆሮ 13፥14 ፣ ኤፌ 4፥5)።
✞ ሥላሴ መታመኛዬ ✞
ሥላሴ መታመኛዬ(፪)
አምላኬ መጠለያዬ(፪)
ጉልበቴ ነህ ማሸነፊያዬ
ሥላሴ መታመኛዬ
ጠፈሩም እርሱ መሠረቱም እርሱ
ፍጥረታት በሙሉ ስሙን አወድሱ
ሱራፌልን ልክህ ከንፈሮቼን ዳሰኝ
ለምፄን ተመልክተህ አምላክ አትጣለኝ
ለምፄን ተመልክተህ ጌታዬ አትጣለኝ
/አዝ=====
እንዴት ያለ አንደበት ስምህን ይጠራል
ግርማህን አይቼ ልቤ ተሸብሯል
ኦዝያን አለፈ ክፋቱ እጅግ በዝቶ
አምላኬን አየሁት በዙፋኑ ጸንቶ(፪)
/አዝ=====
አልአዛር የአንተ ነው መንገድ የወደቀው
ከእጅ ያላመለጠ ነዌ ባለፀጋው
ነግሥታትም የአንተ በሥልጣን ያሉት
ለስምህ ይንበርክከ ይህ ሁሉ ፍጥረረት(፪)
/አዝ=====
በድቅድቅ ጨለማ ተስፋ በሌለበት
ብርሃን ሆኖ አየሁት የጌታዬን ምሕረት
ኃይልን ማሸነፍን ጽናትንም ስጠኝ
ጠላት እንዳይጥለኝ ጸጋህን አልብሰኝ(፪)
👉ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ዮሐንስኒ_ሀሎ ✞
ዮሐንስኒ ሀሎ ያጠምቅ
በሄኖን በቅሩበ ሳሌም(፪)
#ትርጉም
ዮሐንስ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዮርዳኖስ ማዶ ያጠምቅ ነበር።
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እንኳን ለበዓለ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!
🕯 #በዓለ_ጥምቀት
‹‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ›› (ማቴ 3÷13) ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ በብሔራዊ ደረጃ በዐደባባይ ከምታከብራቸው ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ የጥምቀት በዓል ነው፡፡ ‹‹ጥምቀት›› የሚለው ቃል አጥመቀ፣ አጠመቀ ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም መነከር፣ መዘፈቅ፣ ሙሉ አካልን በውኃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው፡፡ ይህ በዓል በፅርዕ (በዮናኒ) ቋንቋ ኤጲፋኒ (Epiphany) ፣ በግእዝ ደግሞ አስተርእዮ ይባላል፡፡ አስተርእዮ ማለት መገለጥ ማለት ነው፡፡
የበዓሉ ስያሜ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ መጠመቅና ለዓለም መገለጥ የሚያበሥር ነው፡፡ ይህም ታላቅ በዓል መጽሐፍ ቅዱሳዊ በዓል ነው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ሌሎቹም ወንጌላውያን እንደጻፉልን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 30 ዓመት ሲሞላው በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ በመጣ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?›› ብሎ በትሕትና ተናግሮ ነበር፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ‹‹ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና…›› ብሎ ከአስተማረው በኋላ በደቀ መዝሙሩ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ ሰማያት ተከፈቱ (ምሥጢር ተገለጠ)፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ ታየ፤ እግዚአብሔር አብም ከሰማይ ሆኖ ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው›› ሲል ተሰማ፤ (ማቴ 3÷13-17 ፣ ማር 1÷9-12 ፣ ሉቃ 3÷21-23)፡፡
በዚህ የጥምቀት በዓል የምንማራቸውና የምንረዳቸው ቁም ነገሮች፦
💧 #ኢየሱስ_ክርስቶስ_ለምን_ተጠመቀ?
እርሱ ጸጋን የሚሰጥ እንጂ የሚቀበል ባለመሆኑ በመጠመቁ የሚያገኘው ጸጋ የለም፤ ስለሆነም የተጠመቀበት ምክንያት፦
ሀ. #ለእኛ_አርዓያ_ለመሆን፦ እርሱን አብነት አድርገን እኛ እንድንጠመቅና በጸጋ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን ነው፡፡
ለ. #ለቀድሶተ_ማያት፦ የምንጠመቅበትን ውኃ ለመባረክና ለመቀደስ ነው፡፡
ሐ. #የሥላሴን_አንድነትና_ሦስትነት_ለማስረዳት፦ እርሱ በተጠመቀ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ተቀምጧል፤ አብም በደመና ሆኖ ‹‹በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው›› ብሎ መስክሮአልና ምሥጢረ ሥላሴ በኋላ በተረዳ ነገር ተገልጧል፤ ‹‹ሰማያት ተከፈቱ›› ተብሎ የተነገረውም ይህን የሥላሴ ምሥጢር የአብ፣ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን መገለጥ ለማስረዳት ነው፡፡
💧ለምን በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ?
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሎች ብዙ ወንዞች እያሉ የዮርዳኖስን ወንዝ የመረጠበት ምክንት የተነገረው ትንቢትና የተመሰለው ምሳሌ እንዲፈጸም ነው፡፡
#ትንቢቱ፦ ‹‹ባሕር አየች፤ ሸሸችም፤ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ››፤ (መዝ 113÷3) ተብሎ የተነገረው ነው፡፡
#ምሳሌው፦ የዮርዳኖስ ወንዝ ምንጩ አንድ ሲሆን ዝቅ ብሎ በደሴት ይከፈላል፤ ከዚያም በወደብ ይገናኛል፡፡ የዮርዳኖስ ወንዝ ምንጩ አንድ እንደሆነ የሰው ሁሉ ዘር መገኛም አንድ አዳም ነው፡፡ ዝቅ ብሎ በደሴት እንዲከፈል እስራኤል በግዝረት አሕዛብ በቁልፈት (ባለመገረዝ) ተለያይተዋል፡፡ ከታች ወርዶ በወደብ እንዲገናኝ ሕዝብና አሕዛብም በክርስቶስ አምነው ተጠምቀው አንድ ሆነዋል፡፡ እስራኤልም ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ምድረ ርስት ገብተዋል፤ (ኢያ 3÷17)፡፡ ኤልያስም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ብሔረ ሕያዋን ገብቷል፤ (2ነገ 2÷8)፡፡ ንዕማንም በዚሁ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠምቆ ከለምጹ ድኖአል፤ (2ነገ 5÷14)፡፡ የዚህ ሁሉ ምሳሌ ማጠቃለያም ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን ላይ የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ ስቃይ አጸናባቸው፤ ከዚያም ስመ ግብርናቸውን (የእርሱ ባሪያ) መሆናቸውን ‹‹ጽፋችሁ ብትሰጡኝ ስቃዩን አቀልላችሁ ነበር›› አላቸው፤ እነርሱም ጽፈው ሰጡት፤ (ይሁንብን አሉ)፡፡ እርሱም ያንን የሰጡትን የዕዳ ደብዳቤ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል ጥሎት ነበርና በዮርዳኖስ የጣለውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደ ሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ አጥፍቶላቸዋል፤ በሲኦል የጣለውንም በዕለተ ዓርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ አጥፍቶላቸዋልና በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀበት ምክንያት ይህ ነው፡፡
💧ለምን በውኃ ተጠመቀ?
ለጥምቀት ውኃን የመረጠበት ምክንያት ትንቢቱ እንዲፈጸም ነው፤ አስቀድሞ በነቢዩ ሕዝቅኤል ‹‹ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ፤ እናንተም ትጠራላችሁ››፤ (ሕዝ 36÷25) ተብሎ ተነግሮ ነበርና ያ የትንቢት ቃል እንዲፈጸም ነው፡፡ ሌላው ምክንያት ውኃ የተሰጠው ለሁሉም ነው፤ ጻድቁም ኃጥኡም፣ ትንሹም ትልቁም፣ ድኃውም ሀብታሙም እኩል ያገኘዋል፡፡ ጥምቀትም የተሰራው ለሁሉ ነው፤ ውኃ ከሥጋዊ እድፍ ያነፃል ጥምቀትም ከነፍስ እድፍ ከኃጢአት ያነፃል፡፡
💧ለምን ወደ ዮሐንስ ሔዶ ተጠመቀ?
የእርሱ መንገድ ጠራጊ ሆኖ የተላከውን ቅዱስ ዮሐንስን መጥተህ አጥምቀኝ ማለት ሲችል ወደ እርሱ ሔዶ የተጠመቀበት ምክንያት ትሕትና ለማስተማር እና ሥርዓት ለመሥራት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ መምህረ ትሕትና ነውና ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዳችሁ ከአባቶች ካህናት ዘንድ ተጠመቁ በማለት ትሕትናንም ሥርዓትንም ለማስተማር ነው፡፡
💧ለምን በሠላሳ ዘመኑ ተጠመቀ?
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅና ማስተማር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ እንደነበር ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ መዝግቦት እናገኘዋለን፤ (ሉቃ 3÷23)፡፡ ስለዚህ በሠላሳ ዘመኑ የተጠመቀበት ምክንያት፦
ሀ. በብሉይ ኪዳን ሥርዓት መሠረት ለቤተ እግዚአብሔር ተልዕኮና አገልግሎት የሚመረጡ ካህናት ሠላሳ ዓመት ሲሞላቸው፣ በዕድሜና በእውቀት የበሰሉ ሲሆኑና ተልዕኮአቸውን ለመወጣት የበቁ ሲሆኑ ስለነበር ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ነው፡፡
ለ. የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በዐርባኛው ቀን ተሰጥቶት የነበረውን የእግዚአብሔር ልጅ የመሆን ጸጋ ትእዛዘ እግዚአብሔርን በማፍረሱ አጥቶት ነበርና ያንን የልጅነት ጸጋ ለመመለስ ነው፡፡
✞ ግነዩ ለእግዚአብሔር ✞
ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር
እስመ ለዓለም ምሕረቱ እስመ ለዓለም(፪)
እናመስግንሽ የአምላክ እናት በዝማሬ
የዓለም ቤዛ ነውና የማኅፀንሽ ፍሬ (፪)
ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከአንቺ ተወልዶ
መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ(፪)
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ ዕዳችንን ፋቀ
በቸርነቱ አወቀን ከበደል አራቀን (፪)
በድንግልና የወለድሽው ያንቺው ጽንስ
የድኩማኖች ብርታት ነው የሕሙማን ፈውስ(፪)
ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም ያዘከረ
በመንግስተ ሰማይ ይኖራል እንደተከበረ (፪)
ብርሃነ መለኮት ያደረብሽ አዳራሽ
ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ (፪)
እመቤታችን እናታችን ማርያም
የተማፀነሽ ይኖራል ለዘለዓለም(፪)
መዝሙር
በማኅበረ ቅዱሳን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በዕደ ዮሐንስ ✞
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቀ
ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
ሠማያዊ/4/ሠማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/
አዳም ያጠፋውን ልጅነት ሊያስመልስ
በሠላሳ ዘመን ተጠመቀ ኢየሱስ
እርሱ አምላክ ሢሆን ፈጥሮ የሚገዛ
ወረደ ወደምድር እንዲሆነን ቤዛ
አዝ-----ኧኸ ሠማያዊ-----
ሊያጠፋው አቅልጦ እንደ አምላክነቱ
እረግጦ ሊሠርዝ እንደ ሠውነቱ
የፍጥረቱ ጌታ በዮርዳኖስ ቆሟል
የእዳውን ፅህፈት በስልጣኑ ሽሯል
አዝ-----ኧኸ ሠማያዊ-----
የአንድነት ሶስትነት ተገልጧል ምስጢሩ
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቆ መምህሩ
አብም በደመና ለልጁ መስክሯል
በአምሳለ ርግብ መንፈስ ቅዱስ ወርዷል
አዝ-----ኧኸ ሠማያዊ-----
ሲነገር እንዲኖር የእርሱ ትህትና
ለዓለም እንዲገለጥ የባሪያው ልዕልና
ተጠማቂው ሄደ ወደ አጥማቂው
አምላክ የሠራልን ስርዓቱ ይህ ነው
በዕደ ዮሐንስ ተጠምቀ ኢየሱስ ናዝራዊ/2/ ሠማያዊ/4/ሠማያዊ ኢየሱስ ናዝራዊ/
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በቀራንዮ የሞተው ✞
በቀራንዮ የሞተው ቤዛችን ነው/2/
የሞተው/2/ ቤዛችን ነው
አዲሱ በፍታ ጸአዳው ኢየሱስ ነው/2/
ጸአዳው/2/ ኢየሱስ ነው
አንጻኝ እጠበኝ ከሃጥያቴ ቸር መድሃኒቴ/2/
ከሃጥያቴ /2/ ቸር መድሃኒቴ
በስጋው ጥልን ያፈረሰ ጌታ ነገሰ/2/
ያፈረሰ/2/ ጌታ ነገሰ
የህይወት እራስ ጉልላቴ የምህረት ቤቴ/2/
ጉልላቴ/2/ የምህረት ቤቴ
የሞት አበጋዝ ተሸነፈ ቀስቱ ታጠፈ/2/
ተሸነፈ/2/ ቀስቱ ታጠፈ
ልዩ ስጦታ ልዩ ጸጋ የድንግል ልጅ ጋር/2/
ልዩ ጸጋ/2/ የድንግል ልጅ ጋር
በውድ ልጁ ስላየን አጸደቀን/2/
ስላየን/2/ አጸደቀን
ህዝቡ ምስጋና ተቀኙለት ተመስገን በሉት/2/
ተቀኙለት/2/ ተመስገን በሉት
በፍቅር ስቦ አከበረን ከፍ አደረገን/2/
አከበረን/2/ ከፍ አደረገን
አዲሱን ምራፍ የከፈተው ጌታ ሞተህ ነው/2/
የከፈተው/2/ ጌታ ሞተህ ነው
የሞት መድሃኒት ሰላማዊ ደጉ ሳምራዊ/2/
ሰላማዊ/2/ ደጉ ሳምራዊ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ እዩት ሎሌው ሲያምር ✞
እዩት ሎሌው ሲያምር ሎሌው ሲያምር/2/
ሎሌው................
የቁልቢው ደብር ሎሌው ሲያምር
ስለታችን ሲሰምር ሎሌው ሲያምር
ማልዶ ህዝቡን ሲያስምር ሎሌው ሲያምር
ቅዱስ ገብርኤል ሲከብር ሎሌው ሲያምር
ሎሌው..............
እዩት ሎሌው ሲያበራ ሎሌው ሲያበራ/2/
ሎሌው...............
በቁልቢው ተራራ ሎሌው ሲያበራ
ሞገስ ክብሩ ሲያስፈራ ሎሌው ሲያበራ
ለለመነው ሲራራ ሎሌው ሲያበራ
ህዝቡን ጠቅሶ ሲመራ ሎሌው ሲያበራ
ሎሌው..................
ቅኔው መዝሙር ሲዘራ ሎሌው ሲያበራ
ማእደቱን ሲመራ ሎሌው ሲያበራ
የገብርኤል ደብተራ ሎሌው ሲያበራ
ሎሌው.................
እዩት ሎሌው ሲያገሳ ሎሌው ሲያገሳ/2/
ሎሌው.................
ባለግርማው ሲነሳ ሎሌው ሲያገሳ
ባለ ሰይፉ ሲነሳ ሎሌው ሲያገሳ
ደጉ መልአክ ሲነሳ ሎሌው ሲያገሳ
ቅዱስ ገብርኤል ሲነሳ ሎሌው ሲያገሳ
ሎሌው...............
እዩት ሎሌው ሲያምር ሎሌው ሲያምር/2/
ሎሌው................
የቁልቢው ደብር ሎሌው ሲያምር
ጥሩት በአዲስ መዝሙር ሎሌው ሲያምር
የረዳችሁ በፍቅር ሎሌው ሲያምር
እልል በሉ እልል ሎሌው ሲያምር
ቅዱስ ገብርኤል ሲከብር ሎሌው ሲያምር
ሎሌው..............
እዩት ሲያበራ እንደጀንበር/2/
እንደ ጀንበር ኧኸ/2/
የገብርኤል ኧኸ
የልብሱ ዘርፍ ኧኸ
እሳት ገብተው ኧኸ
ህጻናቱ ኧኸ
ሲሳለሙ በታቦቱ ኧኸ
መጣ ከላይ ኧኸ
ገብርኤል ኧኸ
ውሃ ሆነ ኧኸ
ነበልባሉ ኧኸ
እዩት ሲያበራ እንደ ጀንበር/2/
እንደ ጀንበር ኧኸ/2/
እየሉጣ ኧኸ
ትመስክር ኧኸ
እንደሚያድን ኧኸ
እግዚአብሄር ኧኸ
ቂርቆስ ይግባ ኧኸ
በደመና ኧኸ
ከፈላ ውሃ ኧኸ
ገብቷልና ኧኸ
እዩት ሲያበራ ተመልከቱ/2/
ተመልከቱ ኧኸ/2/
የሚካኤል ኧኸ
መቀነቱ ኧኸ
የሚካኤል ኧኸ
ስራ ቤቱ ኧኸ
ካመኑበት ኧኸ
በጸሎቱ ኧኸ
መከታ ነው ኧኸ
ለጠላቱ ኧኸ
ክፉን ጋርዶ ኧኸ
ያድነዋል ኧኸ
ክፉን ቀስት ኧኸ
ይሰብረዋል ኧኸ
እዩት ሲያበራ ተመልከቱ/2/
ተመልከቱ ኧኸ/2/
የባህራንን ሞት ኧኸ
የቀየረ ኧኸ
ሚካኤል ነው ኧኸ
የከበረ ኧኸ
የረዳችሁ ኧኸ
እልል በሉ ኧኸ
ለመልአኩ ኧኸ
ለሃያሉ ኧኸ
እዩት ሲያበራ ተመልከቱ/2/
ተመልከቱ ኧኸ/2/
ሚካኤል ነው ኧኸ
ተዋጊው ኧኸ
ለእግዘአብሄር ርስት ኧኸ
የቆመው ኧኸ
ዘመኑ ሲያልቅ ኧኸ
ራስ ይሆናል ኧኸ
ካመኑበት ኧኸ
ይማልዳል ኧኸ
እዩት ሲያበራ በሰማይ/2/
በሰማይ ኧኸ/2/
የሰራዊት ኧኸ
አለቃ ነው ኧኸ
ታማኝ ሆኖ ኧኸ
የተሾመው ኧኸ
መብረቅ እሳት ኧኸ
ሰገነቱ ኧኸ
እንደ ርግብ ነው ኧኸ
ደግነቱ ኧኸ
እዩት ሲያበራ ተመልከቱ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ጌታ ተጠመቀ ✞
ጌታ ተጠመቀ(፫)
ተጠመቀ(፫)ጌታ ተጠመቀ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ክርስቶስ ትንቢቱ ሲደርስ ✞
ክርስቶስ ትንቢቱ ሲደርስ
መጣ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ
ይጥል ዘንድ የበደልን ደጅ
ገብቶ ተጠመቀ በዮሐንስ እጅ
ወዲያውኑ ተጠምቆ ሲወጣ
አዋጅ ከደመና እንዲህ የሚል መጣ
ይህ ነው የምወደው ልጄ
ወደዓለም የላኩት እንዲሞት ወድጄ
መንፈስ ቅዱስ በአምሳለ ርግብ
በራሱ ላይ አርፎ መሰከረለት
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ የኛ ነው ✞
የኛ ነው ዋሻው እምነቱ ፀበሉ
አናፍርም ትምከታችን ነው መስቀሉ (፪)
የኛ ነው የኛ ......(.፪)
የሶስት ሺ አመት .....የኛ
ታሪክ ያላት.. ...የኛ
ታቦተ ፂወን.. ...የኛ
ያለችበት ..........የኛ
የፀሎት ሰፍራ.. ..የኛ
የኪዳን ሀገር ......የኛ
ኢትዮጵያ እናቴ.. ...የኛ
ሀገር እግዚአብሔር.. .የኛ
የኛ ነው የኛ
/አዝ=====
የኛ ነው የኛ.. .....የኛ (፪)
ከአንዲት ድንጋይ.. ....የኛ
የተወቀረው.. ....የኛ
የላሊበላ.. ........የኛ
ድንቅ ስራ ነው .....የኛ
ጣራው ክፍት ሆኖ......የኛ
ዝናብ ማይገባው.......የኛ
አቡነ አሮን.. ....የኛ
ምንኛ ውብ ነው ......የኛ
የኛነው የኛ
/አዝ=====
የኛ ነው የኛ.....የኛ (፫)
ኢትዮጵያ ሀገር ....የኛ
ልጅሽ ባኮስ.. .......የኛ
ተጠምቆልሻል.. .....የኛ
በፊልጾስ.. .....የኛ
የአምላክ ስው መሆን .....የኛ
ሚስጥርን አውቆ.. ......የኛ
በእየሱስ አምኖ ......የኛ
መጣ ተጠምቆ.. ......የኛ
የኛ ነው የኛ
/አዝ=====
የኛነው የኛ.. .....የኛ (፪)
ትምከታችን ነው .....የኛ
የጌታ መስቀል ......የኛ
አምነን ድነናል.......የኛ
በእምነት በፀበል.. ...የኛ
መለያችን ነው .........የኛ
ማተባችን .......የኛ
ተዋህዶ ናት ......የኛ
እምነታችንን.. ....የኛ
የኛ ነው የኛ
/አዝ=====
የኛ ነው የኛ .......የኛ (፪)
ፃርቃኔ ሂዱ.. .....የኛ
ሽንኮራ ሂዱ.......የኛ
ግሽንም ውጡ.. ..የኛ
አክሱምም ወረዱ.. ..የኛ
ሽባው ተፈቶ.. ..የኛ
እውሩ በረቶ.....የኛ
ጎባጣው ቀንቶ.....የኛ
ደንቆሮው ሰምቶ...የኛ
ፍፁም አምነናል ..የኛ
አይናችን አይቶ....የኛ
ፀንተን ቆመናል.. .የኛ
ጀሮአችን ስምቶ.. ..የኛ
የኛ ነው
👉 ዘማሪ_አሸናፊ_አበበ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ከክርስቶስ ፍቅር ✞
ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ ማነው
መከራ ችግር ስቃይ ወይስ መራቆት ነው/4/
አንፈራም አንሰጋም አንጠራጠርም /2/
እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ይኖራል ለዘለዓለም/4/
የሰማይ ቤታችን አማኑኤል የሰራው
የሰማይ ቤታችን እየሱስ የሰራው
ግንቡ ንጹህ ውሃ መሰረቱ ደም ነው/4/
ሳይነጋ ተራምደን እንግባ በጧት/2/
በደሙ መስርቶ ከሰራልን ቤት/4/
ከቶ የት ይገኛል እንዲህ ያለ ቤት/2/
የውሃ ግድግዳ የደም መሰረት/4/
የውሃ ግድግዳ የደም መሠረት/2/
ይኸው እዚህ አለ የአማኑኤል ቤት/4/
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ እግዚኡ_መርሐ ✞
እግዚኡ መርሐ ዮርዳኖስ አብጽሐ
ወበህየ ዮሐንስ ወበህየ ፍጹመ ተፈሥሐ
ጌታውን መራና ዮርዳኖስ አደረሰው
በዚያችም ለት ዮሐንስ በዚያችም ለት በፍጹም ደስ አለው
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ አንሶሰወ ✞
አንሶሰወ(፪)ወአስተርአየ
በዮርዳኖስ ኧኸ ተጠምቀ በዮሐንስ(፪)
#ትርጉም:-
ተመላላሰ ታየ በዮርዳኖስ ወንዝ
በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ።
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተመዘገበው ከጥፋት ውኃ በኋላ የኖኅ ልጆች ወልደው ተዋልደው ብዙዎች ሆኑ፤ (ዘፍ 9፥1 ፣ ዘፍ 10፥1)፡፡ በባቢሎን የነበሩት በሰናዖር ሰፊ ሜዳ አግኝተው ‹‹በምድር ላይ ሳንበተን ስም ማስጠሪያ ግንብ እንገንባ›› ብለው መክረው ታላቅ ግንብ ገነቡ፡፡ የኩሽ ልጅ ናምሩድ በምድር ላይ ኃያል መሆንን በጀመረ ጊዜ ግዛቱም በሰናዖር ባቢሎን ነበር፡፡ በናምሩድ ኃያልነት እና መሪነት ከዚያ ሆነው ጦር እየሰበቁ ይወረውሩ ጀመር፤ ሰይጣንም ከደመና በምትሀት ደም እየቀባ ይልክላቸዋል፤ እነርሱም ደሙን እያዩ ‹‹አሁን አብን ወጋነው፣ አሁን ወልድን ወጋነው፣ አሁን መንፈስ ቅዱስን ወጋነው›› ይሉ ጀመር፡፡ በሕዝቡ ላይ ዲያብሎስ ስለ ሰለጠነባቸው እና ለሌሎች ከሀድያን ትምህርት ይሆን ዘንድ ‹‹ንዑ ንረድ ወንክዐው ነገሮሙ›› በማለት እግዚአብሔር ቋንቋቸውን ለያየባቸው፤ እነርሱም የማይግባቡ የማይደማመጡ ሆነው በምድር ላይ ሁሉ ተበታትነዋል፡፡ከተማይቱም ስምዋ ባቢሎን ተባለ፡፡ ባለማስተዋል የሠሩትንም ሕንፃ ዓመጻ ነፋስ ጠራርጎ አጥፍቶታል፡፡ ይህን ያደረጉበት የቅድስት ሥላሴ በዓል ጥር 7 ቀን ይከበራል፡፡
ይህም ቅድስት ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ቀን ነው፤ (ዘፍ 11÷1-9)፡፡ እግዚአብሔርም አለ ‹‹ኑ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው››)፡፡ ‹‹እግዚአብሔርም አለ›› አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹ኑ እንውረድ›› ሦስትነታቸውን ያጠይቃል፡፡ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ
✞ ሥላሴ በሉ ✞
ሥላሴ ሥላሴ በሉ
መስክሩ ፍጥረት በሙሉ
በሰማይ በምድርም ያለው
እግዚአብሔር አንድም ሦስትም ነው
በመለኮት በስልጣን በአገዛዛቸው
በባህሪይ ሥላሴ አንድ ናቸው
በስም በአካል በግብር ሶስትነት
ይኖራሉ ዘላለም ፀንተው በእውነት(፪)
/አዝ=====
የላከው አብ አባት ነው በህላዌው
የተላከ ወልድ አምላክ አቻ ነው
ማህየዊ መንፈስ ቅዱስ
ህይወት አፅናኝ እስትንፋስ ነው ንጉስ
/አዝ=====
እንደ አብርሃም እንደ ይስሀቅ
እንደ ያእቆብ
መበላለጥ በነሱ አይታሰብ
ይመክራሉ ይፈፅማሉ
ቸርነትን ለአለም ያደርጋሉ(፪)
/አዝ=====
መጉደልና መከፈል ለሌለበት
ለሥላሴ ይገባል መገዛት
ባለማወቅ እንዳንናገር
ይህን ጥበብ አንችልም ልንመረምር(፪)
👉ዘማሪ ሮቤል ማትያስ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ምስጋና አምልኮ ✞
ምስጋና አምልኮ ስግደት ውዳሴ
ይገባል በሉ ሰዎች ለቅድስት ስላሴ
ዘላለም አለም ቅዱስ ነህ
አምሳያም ወደር የሌለህ
መተማመኛም ሆነኸኛል
ሥላሴ ባንተ ደስ ይለኛል
/አዝ=====
የታመነ ነው የተፈራ
የጽድቅን ፀሐይ የሚያበራ
ዓለሙ ፀንታል በሥላሴ
ትዘምርለት ለእርሱ ነፍሴ
/አዝ=====
ዘመናት በእጁ በመዳፉ
ሁሌም የእርሱ ነው ድሉ ሰልፉ
የእሳት መድረኮች ያሉት ጌታ
የማያልፍ ነው የማይረታ
/አዝ=====
አብርሃም አምኖ ተሰደደ
በእርጅናው ወራት ልጅ ወለደ
የተስፋውን ቃል ፈፀመለት
ሥላሴ በሉ በቀን በለሊት
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በዮርዳኖስ_ተጠምቀ ✞
በዮርዳኖስ ተጠምቀ በሠላሳ ክረምት
ከመ ይስዐር መርገማ ለሔዋን ዲበ ዕፀ መስቀል ተሰቅለ
#ትርጉም
በሠላሳ ዓመቱ በዮርዳኖስ ተጠመቀ
የሔዋንን እርግማን ይሽር ዘንድ በዕፀ መስቀል ተሰቀለ።
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ