የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል
✞ ነአምን_ክርስቶስሃ ✞
ነአምን(፪) ክርስቶስሃ ነአምን መድኅነ
ዘዮሐንስ አጥመቆ በዮርዳኖስ
ዘዮሐንስ አጥመቆ አጥመቆ በዮርዳኖስ
እናምናለን መድኅን ክርስቶስን
እናምናለን ክርስቶስን
ዮሐንስ ያጠመቀውን በዮርዳኖስ
ዮሐንስ ያጠመቀውን በዮርዳኖስ ያጠመቀውን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በቃልና በኑሮ ✟
በቃልና በኑሮ ሆነሀል ምስክር
እንደፀሀይ ያበራል በእግዚአብሔር ሀገር
ሰማያዊ ነህ እንጂ አይደለህም ምድራዊ
ገብረመንፈስቅዱስ እርእሰ ባህታዊ
በስሙ ለሚያምኑት አማላጅ ሆነሀል
በፀሎትህም ሀይል ተማምነንብሀል
የክብር ኮከብ ነህ የገዳም መብራት
አስተምህረኛል ምግባር ሐይማኖት
/አዝ=====
የሚያልፈውን ዓለም የምድሩን ንቀሀል
የታመንከው አምላክ ህያው አድርጎሀል
በስጋህ በነብስህ እግዚአብሔር ከበረ
የማስታረቅን ቃል ባንተላይ አኖረ
/አዝ=====
በተጋድሎ ብዛት በፆም በፀሎት
ትተጋ ነበረ በፀናች እምነት
ስለቃልኪዳንህ በረከት ይወርዳል
ያንተስም ሲጠራ አጋንንት ይርዳል
/አዝ=====
ገብረመንፈስቅዱስ የእምነት አባት
አናብስ አናብርት የታዘዙለት
ከንሂሳ ተነስቶ የኢትዮጵያ ደረሰ
ፀጋው በረከቱ በኛላይ ፈሰሰ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ዮሐንስ ✞
ጌታ አብልጦ ይወድሃል
ከሁሉ በላይ አክብሮሃል
ዮሐንስ ባለ ራእይ ደቀ መዝሙር
ለአንተ አለኝ ልዩ መውደድ ልዩ ፍቅር(፪)
በመጀመሪያ ቃል ነበረ
ሁሉ በእርሱ ተፈጠረ
ብለህ ጽፈሃል ያ ቃል ሥጋ ሆነ
ቅዱስ ዮሐንስ ጸጋህ የገነነ
/አዝ=====
ሐዋርያ ነህ ላይከ ሐዲስ
ወንጌላዊ ነህ ለክርስቶስ
ስለ ብርሃን ምስክር የሆንከው
ወልደ ነጎድጓድ ምስጉን ነህ እላለሁ
/አዝ=====
በፍጥሞ ደሴት ብትታሰር
መለኮት ታየህ በእሳት መንበር
ሞትን እንዳታይ ወደ ላይ ነጥቆሃል
ልቤ ተማርኮ አንተን አንተን ይላል
/አዝ=====
መስቀለ ሞቱን በመሸከም
ዞረህ ሰብከሃል በጽናፈ ዓለም
እኔም እንዳልቀር በጥብርያዶስ ባሕር
ከእግርህ ልከተል በደጅህ ልኑር
👉ዘማሪት ሰላማዊት በርታ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ
ዮሐንስ ማለት ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ ወሣህል ማለት ነው፡፡ ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል የሆነው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ አባቱ ዘብዴዎስ እናቱ ማርያም ባውፍልያ (ሰሎሜ) ይባላሉ፡፡ ለአገልግሎት የተጠራው ከአባቱና ከወንድሙ ያዕቆብ ጋራ በገሊላ ባሕር ዓሣ ሲያጠምዱ እንደሆነ ወንጌላዊው ማቴዎስ ገልጾታል፤ (ማቴ 4÷21-22)፡፡
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የሚጠራባቸው ሌሎች ስሞች፦
#ፍቁረ_እግዚእ፦ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ያዕቆብ ፣ ዮሐንስና ጴጥሮስ) ቀዳሚው ነው፤ በኑሮው ጌታን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታ የሚወደው (ፍቁረ እግዚእ) ተባለ፤ (ዮሐ 20÷2 ፣ ዮሐ 13÷23)፡፡ በዚህም ምክንያት ምሥጢረ መንግሥትን በታቦር ተራራ፣ ምሥጢረ ጸሎት በጌቴሴማኒ፣ ምሥጢረ ቁርባንን በምሴተ ሐሙስ ከጌታ ጎን ተቀምጦ አይቷል፡፡ በተጨማሪም ጌታችን በጸሎተ ሐሙስ ለደቀ መዛሙርቱ ትህትናን ሊያስተምር እግራቸውን ሲያጥብ በድር የተሠራች የወገብ መታጠቂያ አድርጎ ነበር፤(ዮሐ 13፥4-5)፡፡ ይህችንም የወገብ መታጠቂያ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰጥቶታል፡፡ እርሱም ጌታ በታጠቀበት መታጠቂያ ቢታጠቅ ሕገ ሥጋ ጠፍቶለታል፤ ይህም ፍቁረ እግዚእ አሰኝቶታል፡፡
#ቦአኔርጌስ፦ ቅዱስ ዮሐንስ እና ታላቅ ወንድሙ ያዕቆብ ከቤተ ክህነትና ከቤተ መንግሥት (በአባታቸው ከነገደ ይሁዳ በእናታቸው ከነገደ ሌዊ) ተወልደዋል፤ እነዚህ ሁለቱ ወንድማማቾች የሰማርያ ሰዎች በእሳት እንዲጠፉ ተመኝተው ነበርና በዚህ የችኩልነት ስሜታቸው ጌታ ‹‹ቦአኔርጌስ›› (የነጎድጓድ ልጆች) ብሏቸዋል፤ (ማር 3÷17 ፣ ሉቃ 9÷54 ፣ 2ነገ 1፥10-12)፡፡
#ታኦጎሎስ (ነባቤ መለኮት)፦ ቅዱስ ዮሐንስ ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ነፍስ፣ ንጽሐ ልቡና ተሰጥቶት በትምህርቱ ጥልቀትና ኃይል የኢየሱስን አምላክነት በመግለጡ ከሌሎች አልቆና አምጥቆ ምሥጢረ ሥላሴን የቃልን ቀዳማዊነትና አምላክነት ‹‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ያም ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ›› እያለ በማመሥጠሩ ነባቤ መለኮት (ታኦጎሎስ) ተብሎ ተጠርቷል፤ (ዮሐ 1÷1-2)፡፡
#አቡቀለምሲስ፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጓሜውም ባለራእይ ማለት ነው፤ በፍጥሞ ደሴት ራእይን አይቷልና (የራእይ መጽሐፍን ጽፏልና) አቡቀለምሲስ ተባለ፡፡
#ቁጽረ_ገጽ፦ ከሌሎች ሐዋርያት ተለይቶ በዕለተ ዐርብ ከመስቀል ሥር የዋለ ብቸኛ ሐዋርያ በመሆኑ የጌታን መከራ መስቀል በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ያማረ ሳይለብስ ፊቱ በሐዘን እንደተቋጠረ ስለ ኖረ ቁጽረ ገጽ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በመስቀል ሥር በመገኘቱም የመስቀል ሥር ስጦታችንን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናት አድርጎ ሰጥቶታል፤ (ዮሐ 19÷25-27)፤ እመቤታችንም በዮሐንስ ቤት ለ15 ዓመት ኖራለች፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስን አዕማድ ብሎ ይጠራዋል፤ (ገላ 2÷9)፡፡
በቅድስት ሥላሴ ሥዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳት አንዱ ንስር ነው፤ ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡ ንስር በእግሩ እንደሚሽከረከር ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡ ንስር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላውያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏልና በንስር ተመስሏል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ አምስት ቅዱሳት መጽሐፍትን የጻፈ ሲሆን እነዚህም ወንጌለ ዮሐንስ፣ ሦስት መልእክታት እና ራእይ ናቸው፡፡ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ብሎ መጻፍ ሲጀምር መልአኩ ከትልቅ ሐይቅ ዳር ቁጭ ብሎ የሐይቁን ውኃ በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ መሬት ሲያፈስ አየው፤ ቅዱስ ዮሐንስ ምን እየሰራህ ነው ብሎ ሲጠይቀው የሐይቁን ውኃ ወደ መሬት አፍስሼ ለመጨረስ ነው ይለዋል፡፡ ዮሐንስም በእንቁላል ቅርፊት ይህ እንዴት ይሆናል አለው፤ ያም መልአክ ይህ ሐይቅ ፍጡር ነው ከረጅም ዘመን በኋላ ያልቃል አንተ ግን ቢቀዱት የማያልቀውን ቢጀምሩት የማይጨርሱትን የመለኮት ነገር የምትመራመር አለው፡፡ በዚህ ጊዜ የጀመረውን አቁሞ ‹‹ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ›› በማለት ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መጻፍ ጀመረ፤ ከዚያ ቃልም ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ ብሎ ወደ ምሥጢረ ሥጋዌ ገባ፡፡
ወንጌላዊው ዮሐንስ መልኩ ጌታችንን ስለሚመስል ይሁዳ ጌታን በመሳም ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠው መልካቸው ስለሚመሳሰል ተሳስተው ዮሐንስን እንዳይዙት ነው፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ ሀገረ ስብከቱ እስያ ሲሆን በዚያ እየተዘዋወረ ለብዙዎች የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከ ፣ ድውያንን እየፈወሰ፣ ሙታንን እያስነሳ ብዙ ገቢረ ተአምራትን እያደረገ በክርስቶስ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል፡፡
ሞትን ያልቀመሰ በሕይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ፣ እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነው፤ ጌታችን ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ?›› (ዮሐ 21፥20-23)፤ ይህ የሚያሳየው እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነው፡፡ ‹‹እውነት እላችኋለሁ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ አስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ›› (ማቴ 16፥28) ተብሎ የተጠቀሰው ቃል ለቅዱስ ዮሐንስ እና መሰሎቹ የተነገረ ነው፡፡ በፍጥሞ ደሴት የተሰወረበት መታሰቢያ ጥር 4 ቀን ይከበራል፡፡ ከወንጌላዊው በረከት ያሳትፈን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ መድበለ ታሪክ ፣ ስንክሳር ዘጥር 4
✞ አምላክ ሰው ሆነ ✞
አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ(፪)
በድንግል ማርያም ተከናወነ
የአብ ሙሽራ የወልድ እናቱ
የመንፈስቅዱስ ጽርሐ ቤቱ
በሰማይ ሆኖ አብ አጸናሽ
ወልድም ለራሱ ቤት አረገሽ
መንፈስቅዱስ ነው(፪)የጸለለሽ
/አዝ=====
ከሦስቱ አካል ወልድ አንዱ አካል
መጣ ወረደ በገባው ቃል
ተጸንሶ ሳለ ወልድ ከእናቱ
አልተነጠለም ከሦስትነቱ
ተአምራት አርጓል ድውይ ፈውሷል በአምላክነቱ
/አዝ=====
ይህንን ድንቅ ምስጢር በሉ ግሩም
ምስጋና አቅርቡ ለዘለዓለም
በስነ ፍጥረት ይታወቃል
የዓለም ፈጣሪ የእግዚአብሔር ቃል
ደስ ይበላችሁ ደስ ይበለን በሉ እልል
/አዝ=====
የአብ ሙሽራ የወልድ እናቱ
የመንፈስቅዱስ ጽርሐ ቤቱ
በሰማይ ሆኖ አብ አጸናሽ
ወልድም ለራሱ ቤት አረገሽ
መንፈስቅዱስ ነው(፪)የጸለለሽ
👉ዘማሪ ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
"መልአኩም እንዲህ አላቸው። እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤"
(የሉቃስ ወንጌል 2:10)
➦" ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።"
(የሉቃስ ወንጌል 2:11)
🙏እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
መልካም የገና በአል ይሁንላችሁ 👏❤⛪❤
✞ በበረት ተመሰገነ ✞
በበረት ተመሰገነ
በአርያም ክብሩ ገነነ
በሠማይ በምልዐት ያለ
በምድርም እኛን መሠለ(፪)
በኪሩቤል ጀርባ የሚቀመጥ ጌታ
ዘወትር የሚሠማ የመላዕክት ዕልልታ
እንግዳችን ሆኖ የመጣ ወደ እኛ
ነጻነት ሆነልን ለታሠርነው ለእኛ
/አዝ=====
ትንቢት ተፈጽሞ እውነት ተገለጠ
የእግዚአብሔር ልጅ ለእኛ ሊያድነን ተሠጠ
በጎል ቤተልሔም በበረት ተኝቶ
ሠላም ታወጀልን ልደቱ ተሠምቶ
/አዝ=====
ከአዳራሹ ወጣ ታላቁ ሙሽራ
ሰውን ወደ እውነት ወደ ጽድቅ ሊመራ
የእሴይ ቁጥቋጦ ወይን አፍርቶልናል
ይኸው ተወለደ በታላቅ ምሥጋና
/አዝ=====
ሠባት መጋረጃ ከፊቱ ሲኖር
እንደ ሕጻን ተወልዶ ታየ በክብር
ቤዛችን የሆነ የሕይወት ራስ
ከእናቱ ጋር ታየ ንጉሥ ክርስቶስ
/አዝ=====
በጎል ቤተልሔም በበረት ተኝቶ
ሠላም ታወጀልን ልደቱ ተሠምቶ
ትንቢት ተፈጽሞ እውነት ተገለጠ
የእግዚአብሔር ልጅ ለእኛ ሊያድነን ተሠጠ
ዘማሪ ፋንቱ ወልዴ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
"በጻድቁ ልደት መታሰቢያ ልዮ ስጦታ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጥር 5 የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የልደት መታሰቢያ በዓል ዕለት የመዝሙር ሲዲ የምንለቅ መሆኑን በታላቅ ደስታ እንገልፃለን። "
✢ @mezmuredawit ✢
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ኖሎት_ርእይዎ ✞
ኖሎት ርእይዎ መላእክት አእኩትዎ
ዮም ሰማያዊ(፪) ሰከበ በጎል
#ትርጉም
እረኞች አዩት መላእክት አመሰገኑት
ዛሬ ሰማያዊው በበረት ተገለጸ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ እሰይ ተወለደ ✞
እሰይ ተወለደ [የዓለምመድኃኒት (3)]
ይኸውተወለደ [የዓለምመድኃኒት (3)
ትንቢት ተናገሩ [ነብያትበሙሉ (3)]
አምላክቀዳማዊ [ይወርዳልእያሉ (3)]
/አዝ=====
ሰብዓ ሰገል መጡ [ሊሰግዱበሙሉ (3)]
የእስራኤልንጉስ [ተወልዷልእያሉ (3)]
/አዝ=====
ሰብዓ ሰገል መጡ [ይዘውእጅ መንሻ (3)]
ወርቅዕጣኑን ከርቤ [ለማርያምእጅ መንሻ (3)]
/አዝ=====
በሶርያ ታየ [ፈጣሪእንደ እንግዳ (3)]
ብስራተልደቱን [ለሁሉምሊያስረዳ (3)]
/አዝ=====
ሕጻናት እንሂድ [ልደቱቤት (3)]
ውሃሆኗልና [ማርናወተት (3)]
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ የዓለም መድኃኒት ✞
የዓለም መድኃኒት የተወለደብሽ
አንቺ ቤተልሔም የተቀደስሽ ነሽ
የአማልክት አምላክ ንጉሠ ነገሥት
ኃያላን በሙሉ የሚሰግዱለት
በጨርቅ ተጠቅልሎ ተኛ በበረት
/አዝ=====
አዋቂዎች ሁሉ በቅን ሀሳባቸው
ወደ አንቺ ተጓዙ ኮከብ ሲመራቸው(፪)
/አዝ=====
ለተከታይ ትውልድ ምሳሌ በመሆን
ሰግደው ገበሩለት ወርቅ እጣን ከርቤን(፪)
/አዝ=====
የሚያድለው ጌታ እውቀት ለሕጻናት
የሚመሰገነው በአፈ መላእክት
ከእንሰሳት ጋራ አደረ በበረት
/አዝ=====
በሥጋ ተገልጦ ረቂቅ ምሥጢሩ
ሰውና መላእክት በአንድ ላይ ዘመሩ(፪)
የኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
መዝሙር
በዲያቆን ፍጹም ሻምበል
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ድንግል በድንግልና ✞
ድንግል በድንግልና ጸንሳ
በድንግልና ትወልዳለች
ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች/2/
ገና ሳይጸነስ ዘመኑ ሳይገባ
ገረድ መሆን ሻተች ትንቢቱን አንብባ
ልታያት ናፈቀች ያችን ቅድስት እናት
ለክብርዋ ተገዝታ ውሃ ልትቀዳለት
ባርያ ልሁን አለች ዝቅ አድርጋ ራሷን
መች አወቀችና እናቱ መሆኗን
ጥቂት ለሚሻ ሰው ያውቃል ብዙ መስጠት
በማህጸኗ መቅደስ ሲቀድስ ኖረበት
/አዝ=====
ሐር ወርቁን ስትፈትል በቤተ መቅደሱ
ማደርያው እንድትሆን መረጣት ንጉሱ
በህሊናው ተስላ የነበረች ምናብ
መሰላል ሆነችው ለአዳም ድህነት ርካብ
በጎ መዓዛዋን ውበቷን ወደደ
በማህፀኗ ሊያድር እግዚአብሔር ወረደ
ከኪሩቤል ይልቅ ጀርባዋ ተመቸው
ንጽህይት ናትና የማትቆረቁረው
/አዝ=====
የተዘጋች መቅደስ ከቶ ማትከፈት
ታትማ የኖረች የክብሩ ሰገነት
ማንም አይከፍታትም ጥበብ አላትና
የእስራኤል ቅዱስ ገብቶባታልና
በረቀቀ ጥበብ ድንግል ተደነቀች
በሆዷ ቅዳሴን እያስተናገደች
ጎንበስ አለች ማርያም ውዳሴ ልትሰማ
ከቅኔያት ሀገር ከሆዷ ከተማ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ተወለደ ሕጻን ሆነ ✞
ተወለደ ሕጻን ሆነ በቤተልሔም ተመሰገነ
ቤዛ ኲሉ ዓለም ተወለደ ከማርያም
ሕጻናት እንሂድ(፪) ወደ በረቱ
ተኝቷልና በግርግም ታቅፎ በእናቱ
/አዝ=====
ሰማያዊ ነው(፪) ወላጅ አባቱ
የአዳም ልጅ ናት የዳዊት ልጅ ናት ድንግል እናቱ
/አዝ=====
ሰላም ሰፈነ (፪) በምድራችን
ተወልዷልና ሕጻን ኢየሱስ ለሁላችን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በበረት_የተኛው ✞
በበረት የተኛው ቅዱሱ ህፃን
ለዓለሙ ሁሉ ሆነለት መድኅን
ምሥክር ሊሆኑ ለፍፁም መንግስቱ
ትንፋሽ ገበሩለት ከበው እንስሳቱ
እሰይ የምሥራች ሃሌ ሃሌ ሉያ
ጌታ ተወለደ ከድንግል ማርያም
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ እልል_እልል_ደስ_ይበለን ✞
እልልል እልልል ደስ ይበልን
እልል እልል ደስ ይበለን
አጀበን መጣን ታቦተ ህጉን
እልል ብላችሁ ተቀበሉን
የቃልኪዳን ታቦት እልልል የክብሩ ዙፋን
ከመንበሩ ወርዶ እልልል እየባረከን እልልል
ቅዱሱ መጽሐፍ እልልል እንደነገረን እልልል
ወጣን ከሰፈሩ እልል እልል እየተከተልን እልል
/አዝ=====
የሰማዩ መቅደስ እልልል እላይ ሲከፈት
ተገልጦ አየነው እልልል የክብሩ ታቦት
እልልታ ዝማሬ እልልል እናቅርብ ምስጋና እልልል
ታቦቱ ልጆቹን እልልል ሊባርክ ነውና እልል
/አዝ=====
በውስጥና በውጭ እልልል በወርቅ ተለብጦ እልልል
የእግዚአብሔር ቸርነት እልል በእርሱ ላይ ተገልጦ እል
እስራኤል በምህረት እልልል ከሞት ተከለለእልል
ታቦቱ ሲነካው እልልል ባህር ተከፈለ እልል
/አዝ=====
በእግዚብሔር ጣቶች እልል ተቀርጾ ትእዛዙ እልል
ካህናቱ ይዘው እልል በስርአት ሲጓዙ እልል
ወድቀን እንሰግዳለን እልል ለቅዱስ ታቦት እልል
የእግዚአብሔር ስም እልልል ለተጻፈበት እልል
አጀበን መጣን እልል ብላችሁ ተቀበሉን፤
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ የአምላክ ዐቃቤ ሕግ ✞
ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው
ገብረ መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ
ፀሐይ(2)የምድራችን ፀሐይ
በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ
የመላዕክት ወዳጅ(2)ገብረሕይወት ሰማይ
/አዝ=====
መብረቅ(2)ሰረገላው መብረቅ
የቃልኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ
የፍጥረቱ ደስታ(2)ገብረሕይወት ፃድቅ
/አዝ=====
ኮከብ(2)ክብረገድላን ኮከብ
ዓለምን የሚያስንቅ መዐዛው የሚስብ
አርከ ሥሉስ ቅዱስ(2)ገብረሕይወት ኪሩብ
/አዝ=====
ስኂን(2)ፄና ልብሱ ስኂን
የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን
የሚነበብ መፃፍ(2)ገብረሕይወት ድርሳን
/አዝ=====
መቅረዝ(2)የማኅቶት መቅረዝ
ምድረከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ
የዝጊቲው ፈዋሽ(2)ገብረሕይወት ምርኩዝ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ እንባዬን አብሰው ✞
እንባዬን አብሰው [ግባ ወደ ቤቴ]/2/
ወልደ ነጎድጓድ [ዮሐንስ አባቴ]/2/
ፈጥነህ ድረስልኝ ሁነኝ እረዳቴ
ቅዱስ ዮሐንስ ነው ታላቅ ሐዋርያ
መልኩ ደም ግባቱ የጌታ አምሳያ
የስሙ ትርጓሜ እግዚአብሔር ፀጋ
ምራኝ በብርሃንህ መሽቶ እስኪ ነጋ
/አዝ=====
እርዳኝ ብዬ ስለው አምላከ ዮሐንስ
አስከትል ምልጃህን ለእኔ ፈጥነህ ድረስ
ተለመነኝ እርዳኝ ነባቤ መለኮት
እንባዬን ሳነባ ስለ ኃጢያቴ ብዛት
/አዝ=====
ከእግረ መስቀሉ ስር እንደ አንተ እንድገኝ
አንተ ፍቅር አባት ጽናትን አድለኝ
እንደ ድንግል ማርያም ወደ ቤትህ ጥራኝ
የድንግል ባለሟል ዮሐንስ አማልደኝ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ልዑለ ስብከት ✞
ልዑለ ስብከት አቡቀለምሲስ
ወልደ ነጎድጓድ ልዩ ነው ዮሐንስ (2)
በህይወት በኑሮ ጌታን የመሰለ
ከሐዋርያት መኃል ቀራንዮ ያለ
ነባቤ መለኮት ታላቅ ሐዋርያ
ቁፅረገፅ ነው የፊቱ መለያ
ወልደ ዘብዴዎስ ዮሐንስ
ወንጌለ ጥዑም ታኦሎጎስ (2)
/አዝ=====
የፋሲካን እራት ተልዕኮ ያዘጋጀ
በቱርክ በአንፆኪያ ወንጌልን ያወጀ
ርዕሰ ደናግል ምድራዊ መልዐክ
በቃል በኑሮ ህይወቱ ሚሰብክ
ወልደ ዘብዴዎስ ዮሐንስ
ምስጢርን ያየ ታኦሎጎስ
ምስጢርን ገላጭ ታኦሎጎስ
/አዝ=====
በፍጥሞ ደሴት ላይ ራዕይን አይቶ
ታላቁን ምስጢር ፃፈልን አጉልቶ
ምልክቱ ንስር የጌታ ወዳጅ
ዛሬም ብርሃን ነው የዓለም አማላጅ
ወልደ ዘብዴዎስ ዮሐንስ
ኮከበ ከዋክብት ታኦሎጎስ(2)
/አዝ=====
በእያርዮስ ቤት እና በደብረ ታቦር
ዓይኖቹ ያዩ የጌታን ክብር
በህይወተ ስጋ የተነጠቀ
በአምላኩ እጅግ የተደነቀ
ወልደ ዘብዴዎስ ዮሐንስ
ምስጢርን ያየ ታኦሎጎስ
ምስጢርን ገላጭ ታኦሎጎስ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ተወለደ ሩኅሩኅ ጌታ ✞
ተወለደ ሩኅሩኀ ጌታ(፪)
መድኃኔዓለም የዓለም መከታ
አማኑኤል የኛ መከታ
ተወለደ - - - የዓለም ፈጣሪ
ተወለደ - - - ቸሩ አባት
ተወለደ - - - እኛን ሊያድነን
ተወለደ - - - ከኃጢያት ሞት
ተወለደ - - - እርሱም እንደኛ
ተወለደ - - - እንደ ህፃን
ተወለደ - - - ድንቅ ነው ፍቅሩ
ተወለደ - - - መድኃኔዓለም
/አዝ=====
ተወለደ - - - ፍቅር ቢስበው
ተወለደ - - - የሠው ልጆች
ተወለደ - - - መጣ ከሠማይ
ተወለደ - - - ወልደ እግዚአብሔር
ተወለደ - - - ከእመቤታችን
ተወለደ - - - ተወለደልን
ተወለደ - - - በቤተልሔም
ተወለደ - - - በከብቶች ግርግም
/አዝ=====
ተወለደ - - - የምስራቅ ሠዎች
ተወለደ - - - መጡ ሊሠግዱ
ተወለደ - - - ስጦታን ይዘው
ተወለደ - - - እንደ ሥርዓቱ
ተወለደ - - - ወርቅ አመጡለት
ተወለደ - - - ስለ መንግስቱ
ተወለደ - - - ዕጣን ለክብሩ
ተወለደ - - - ከርቤን ለሞቱ
👉ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በኤፍራታ_በጎል ✞
በኤፍራታ በጎል በኤፍራታ ሆ
የዓለም መድኃኒት ተወለደ ጌታ ተወለደ ጌታ (፪)
ብርሃን ተገለጠ ጨለማ ተዋጠ
በራ በምድር ላይ የናዝሬቱ ፀሃይ የናዝሬቱ ፀሃይ
ሠራዊት ሳያዘምት ተኝቶ በበረት
በታላቅ ማዳኑ ማረከን ህፃኑ (፪)
/አዝ=====
ዓለምን በእፍኙ ጨብጦ አዳኙ
በከብቶቹ ግርግም አቀፈችው ማርያም (፪)
መጡ ሰብዐ ሠገል ሊሠግዱ ለልዑል
ዕጣን ለክህነቱ ወርቁን ለመንግስቱ (፪)
/አዝ=====
የመቅደሡ ናፍቆት በክንዱ መዘርጋት
ቤንሆር ተዋረደ መሲህ ተወለደ (፪)
የጥሉ መንጦላይት ለይቶን ከገነት
ሕይወትን አገኘን ልደቱ አስታረቀን (፪)
/አዝ=====
ምድር ተፈወሠች አዳኟን ስላየች
ሠውና መላዕክት ተቀኙ በአንድነት ዘመሩ በአንድነት
በሠላም አለቃ ኩነኔው ሊያበቃ
ስቃይ ሊመነገል ወለደችው ድንግል (፪)
/አዝ=====
ብርሃን ተገለጠ ጨለማ ተዋጠ
በራ በምድር ላይ የናዝሬቱ ፀሃይ የናዝሬቱ ፀሃይ
ሠራዊት ሣያዘምት ተኝቶ በበረት
በታላቅ ማዳኑ ማረከን ህፃኑ(፪)
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#ጌታ_ስለተወለደባት_ምሽት_ቅዱስ_ኤፍሬም_አንዲህ_አለ፦
"ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡
ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን፤ ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!
ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም!
ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡
ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን።
ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው
እንዳይታበይባት።
ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን
አንበቀልባት።
የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!
ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው።
ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡
ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!
የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት!
ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ።
✞ አማኑኤል ተወለደ ✞
አማኑኤል ተወለደ (፪)
ዓለም ነጻ ወጣ ጠላት ተዋረደ
ምድር ነፃ ወጣች ጠላት ተዋረደ
ከራድዮን ጌታ ስሙ ድንቅ መካር
በከብቶቹ ስፍራ ታይቶናል በፍቅር
ዓለምን ማረከ በበረት ተኝቶ
ድንገት በበብርሃን የሰውን ልጅ ሞልቶ
/አዝ=====
በጨርቅ ተጠቅልሎ እንስሳት ሲያሞቁት
ተገኝቷል ኢየሱስ በከብቶቹ በረት
እንደ ተርሴስ ንጉሥ ይዘናል አመሃ
ስላየን ተወልዶ የሕይወታችን ውሃ
/አዝ=====
ከዋክብትን የሚቆጥረው አማኑኤል ሊቆጠር
ወርዷል ቤተልሔም ከእናቱ ጋር ሊያድር
ያ ደገኛ ትንቢት ታይቶናል ማዳኑ
የመጎብኘት ዕለት መጥቶልናል ቀኑ
/አዝ=====
እስከ ቤተልሔም መርቶናል ኮከቡ
ዛሬም እንዲሰበክ የፈውስ ረሃቡ
ታዖስ ተገለፀ አዳኙ ማስያስ
በርስታቸን ቆመን ልንል ሥሉስ ቅዱስ
/አዝ=====
ማያት አፍላጋቱን በእፍኙ የሰፈረ
የሰው ሥጋ ለብሶ በማርያም አደረ
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሆነ
ሰላምም ለሰው ልጅ በምድር ተወሰነ
👉 ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በጎል_ሰከበ ✞
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ
ቤዛ ከሉ ዓለም(፪)ዮም ተወልደ
በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ
የዓለም መድኀኒት(፪) ዛሬ ተወለደ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ተወልደ_ኢየሱስ ✞
ተወልደ ኢየሱስ /በቤተልሔም/(፪)ዘይሁዳ በቤተልሔም
አዋልደ ጢሮስ /አሜሃ ይሰግዳ/(፪) በቤተልሔም
#ትርጉም
የይሁዳ ቦታ በሆነችው በቤተልሔም ኢየሱስ ተወለደ
ያን ጊዜም የጢሮስ ቆነጃጅቶ/ልጆች/ሰግደዋል
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ እሰይ እሰይ ተወለደ ✞
እሰይ እሰይ ተወለደ እሰይ እሰይ ተወለደ (፪) ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪) ከድንግል ማርያም ተወለደ
እሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸሩ አባታችን "
መች ትገኝ ነበረ "
ገነት ምድራችን "
/አዝ=====
ብርሃን ወጣላቸው እሰይእሰይ
ለመላ ሕዝቦቹ "
በጨለማው ጉዞ "
እንዲያሲሰላቹ "
/አዝ=====
እንደ ጠል ወረደ እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደ እኛ "
ወገኖቹን ሊያድን "
ከኃጢአት ቁራኛ "
/አዝ=====
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን "
እርሱ ወዷልና "
እንዲሁ ዓለሙን "
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ ⛪
✞ አንቺ አንቺ ቤተልሔም ✞
አንቺ አንቺ ቤተልሔም የይሁዳ መሬት
ባንቺ ተወለደ የአለም መድኃኒት/2/
ለአዳም ክብር ሲሻ ቤተልሔም
ለሁሉ ሠላም " "
ዛሬ ተወለደ " "
ከድንግል ማርያም " "
/አዝ=====
እጅ መንሻ አቀረቡ ቤተልሔም
የምስራቅ ነገስታት " "
በከብቶቹ በረት " "
ተኝቶ አገኙት " "
/አዝ=====
እስራኤል ህዝቤን ቤተልሔም
የሚጠብቃቸው " "
ካንቺ ይወጣል ብሎ " "
እንደነገራቸው " "
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በበረት_የተኛው ✞
በበረት የተኛው ቅዱሱ ሕፃን
ልብስም አለበሰ ነበረ እርቃኑን
የምታለብሰው ልብስ ባታገኝ እናቱ
ትንፋሽ አለበሱት ከበው እንስሳቱ
እሰይ የምሥራች ሃሌ ሃሌ ሉያ
ጌታ ተወለደ ሊሆነን አርዓያ/2/
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
ስብሐት ለእግዚአብሔር በሠማያት በሉ/2/
በምድርም እርቅ ሆነ ተፈፀመ ቃሉ/2/
በይሁዳ ምድር በዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ምስራች ተሠማ
ሰብዐ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ ዕጣን ከርቤውን ለእርሱ ለመገበር
/አዝ=====
በኤፍራታ ሠማን የጌታን ልደት
ንጉስ መወለዱን የዓለም መድኃኒት
የጌቶቹ ጌታ የነገስታት ንጉስ
በዳዊት ከተማ ተዐልዷል ኢየሱስ
/አዝ=====
ሠውና መላዕክት በአንድነት ዘመሩ
እንስሳት በግርግም እስትንፋስ ገበሩ
ክብርና ውዳሴ ምስጋናና እልልታ
በበረት ለተኛው ለሠራዊት ጌታ
👉 ዘማሪ ዮናስ ግዛው
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ