የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል
✞ ጌታ_ሆይ ✞
ጌታ ሆይ አይሁድ አማጽያን
ሰቀሉህ ወይ
የዓለም መድኃኒት የዓለም ሲሳይ
ሰቀሉህ ወይ /2/
የአዳም በደል አደረሰህ
አንተን ለመሰቀል
የሔዋን ስህተት አበቃህ ለሞት
ቸሩ አባት/2/
ንጹሕ ክርስቶስ ሆንክ ወንጀለኛ
ብለህ ስለእኛ
መሰቀል አሸክመው
አስረው ገፈፉህ እያዳፉህ/2/
ግብዞች እንደራሳቸው መስሏቸው
ምራቅ እየተፉ በፊትህ ቀለዱ
አንተን ሊጎዱ/2/
እጅና እግርህን በብረት ተመታ
የዓለም ጌታ
የሾህ አክሊል ደፍተህ
ጎንህን ተወጋህ አልፋ ኦሜጋ/2/
በመሰቀል ላይ ተጠማሁ ስትል
ታላቅ በደል
ሀሞትና ከርቤ ሰጡህ ቀላቅለው
ጠጣ ብለው/2/
ይቅር ባይ ግልጽ በደላችንን ሁሉ ሳታይ
አንተ ይቅር በለን
በእኛ ሳትከፋ እንዳንጠፋ /2/
#እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞
#እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞
#አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞
#ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በፍሥሓ_ወበሰላም። ✞✞✞
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
✥ ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ተፈጸመ አለ ✞
ተፈጸመ አለ ጌታ ነፍሱን ሰጠ
ስለኔ ኃጢአት በመከራ አለፈ
በግፍ ተሰቃየ ፍዳን ተቀበለ
ተገርፎ ተወግሮ በእንጨት ተሰቀለ
ደፋ ቀና እያለ ሲወድቅ ሲንገላታ
የብርሃን ፊቱን በጥፊ ተመታ
/አዝ=====
በሐሰት ተከሶ በሐሰት ተገደለ
በፍርድ ሸንጎ ፊት በአደባባይ ዋለ
በውሃ ጥም ዛለ በርሃብ ተቀጣ
ስለ ሰው ልጆች ሲል የሞት ጽዋ ጠጣ
/አዝ=====
አንቺ ዕለተ አርብ እንዴት ያለሽው ነሽ
ሰማያዊው አባት የተሰቀለብሽ
ከኋላ ከፊቱ በጠላት ተከቦ
ማንን ማ ነበረ የሚያጽናናው ከቶ
/አዝ=====
ሩኅሩኅ ጌታዬ ስለኔ ብለህ ነው
ያን ሁሉ መከራ በትዕግስት ያለፍከው(2)
#እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞
#እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞
#አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞
#ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በፍሥሓ_ወበሰላም። ✞✞✞
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#ሠሉስ(ማክሰኞ)
የሰሙነ ህማማት ሠሉስ(ማክሰኞ) "የጥያቄ ቀን" በመባል ይታወቃል ምክንያቱም ሹመትን ወይም ስልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰኞ ባደረገው አንጾሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ስልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበረ።
ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኃለው የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም? ይለናል ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል እንደ መምህርም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸው ሁሉ በራሱ ስልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ ነው እንጂ
ከዚህ የምንማረው የእነሱን ክፉ ጠባይና ግብር መከተል እንደማይገባን ነው በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምረን ነው።
#እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞
#እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞
#አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞
#ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በሰላም። ✞✞✞
✞ ሆሳዕና ✞
ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና
ሆሳዕና ብለን እናቅርብ ምስጋና
ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና
ለወልደ አምላክ - - - ሆሳዕና
ትህትናን አሳየን - - - ሆሳዕና
ስሙ ይባረክ - - - ሆሳዕና
/አዝ=====
ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና
ለሰማይ ንጉስ - - - ሆሳዕና
ግርማ ለብሶ መጣ - - - ሆሳዕና
እኛን ሊቀድስ - - - ሆሳዕና
/አዝ=====
ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና
ለወልደ ዳዊት - - - ሆሳዕና
ነብያት በትንቢት - - - ሆሳዕና
ለተናገሩለት - - - ሆሳዕና
ሐዋርያት በወንጌል - - - ሆሳዕና
ለሰበኩለት - - - ሆሳዕና
/አዝ=====
ሆሳዕና በሉ - - - ሆሳዕና
ለአምላከ ምህረት - - - ሆሳዕና
ተወልዶ ከድንግል - - - ሆሳዕና
እንደ ህጻናት - - - ሆሳዕና
እረኞች በዋሻ - - - ሆሳዕና
የሰገዱለት - - - ሆሳዕና
የአዳም ልጆች ሁሉ - - - ሆሳዕና
ደግሞም መላእክት - - - ሆሳዕና
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#ሆሳዕና_በአርያም
ሆሳዕና(2) በአርያም
ሆሳዕና በአርያም
ቅድስት ሀገር ሆይ ኢየሩስአሌም
ክብርሽ የሆነው በመላው ዓለም
በአህያ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ የገባው
ኢየሱስ ክርስቶስ የዓለም መድኀኒት ነው
ኀይልና ስልጣን በአንድ ላይ ስላለው
ጠላቶችም ፈሩ ህዝብሽም ደስ አለው
እናውቃለን ባዮች ግብዞች ሲጠሩ
ወጣት ሽማግሌ ህፃናትም ሆነው በአንድነት ዘመሩ
ሰውማ ቢዘምር ምን ያስደንቀናል
ሆሳዕና ሰው ቀርቶ ድንጋይ ያናግራል
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ሆሳእና_ዕምርት ✞
ሆሳእና ዕምርት
እንተ አቡነዳዊት
ቡርክት እንተ ትመጽእ መንግስት/2/ ትርጉም፦የታወቀች የድኅነት ቀን
የምትመጣይቱ የአባታችን
የዳዊት መንግስት ቡሩክት ናት
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
7. ኒቆዲሞስ
ኒቆዲሞስ ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃና መምህር ነበር፡፡ ኒቆዲሞስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምናገኘው መምህር መሆኑን የሚከተለው ጽሑፍ ያስገነዝበናል፡፡ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ መምህር ሆይ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን›› አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም›› አለው፡፡ ኒቆዲሞስም ‹‹ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል?›› አለው፡፡ ኢየሱስም ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካለተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም፤ ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፤ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁ አታድንቅ፤ ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፤ ድምፁንም ትሰማለህ ነገር ግን ከወዴት እንደመጣ ወዴትም እንዲሔድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው›› አለው፤ (ዮሐ 3፥1-8)፡፡ ከውኃና ከመንፈስ ዳግም መወለድ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑት ልዩ መገለጫ ነው፡፡
ኒቆዲሞስ በሌሊት እየመጣ ከኢየሱስ ክርስቶስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ወንጌልን ይማር ነበር፡፡ ሰንበቱ በእርሱ ስም የተሰየመው ሥራውን ለመዘከር ነው፡፡ በሌሊት መጣ የሚለው በምሥጢር ሲተረጎም አንደኛ ወደፊት በቀን ይመጣልና ከዚያ አስቀድሞ መጣ ለማለት ነው፤ አንድም በኋላ በዕለተ ዓርብ የጌታን ሥጋ ከመስቀሉ አውርዶ ገንዞ ለመቅበር ይመጣልና ከዚያ አስቀድሞ ለመማር መጣ ለማለት ነው፡፡ አንድም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስን ሳያምን በፊት በኦሪት ጨለማ እያለ መጣ ለማለት በሌሊት መምጣቱን ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አመሥጥረው ያስተምራሉ፡፡
ኒቆዲሞስ ከመዓልት ይልቅ በሌሊት መማር የመረጠበት ምክንያቶች
ሀ. ውዳሴ ከንቱ ሽቶ፦ እርሱ ራሱ የአይሁድ አለቃና መምህር ስለነበር ከሌላ መምህር (ከኢየሱስ ክርስቶስ) እግር ሥር ተቀምጦ ሲማር አይሁድ ቢያዩት ሳይገባው ነው መምህር ያልነው ብለው ይነቅፉት ነበር፡፡ በሌላ አገላለጽ ኒቆዲሞስ መማርን ይፈልጋል ደቀ መዝሙር መባልን ግን አይፈልግም፡፡ በአንጻሩም ምሁረ ኦሪት ነበረና መምህር መባልን ይፈልጋል፡፡
ለ. የአይሁድን ዛቻና ማስጠንቀቂያ ፈርቶ፦ አይሁድ በክርስቶስ የሚያምንና ትምህርቱንም የሚሰማ ቢገኝ ከማኅበራችን ይለይ ቤቱም የጉድፍ መጣያ ይሁን ብለው ተስማምተው ሕግ አውጥተው ነበርና ቅጣቱን ፈርቶ ላለመታየት ሌሊት መማርን መርጧል፡፡
ሐ. አእምሮ ልቡናውን ሰብስቦ ለመማር ፈልጎ፦ መዓልት ዓይንን፣ ጆሮንና አእምሮን የሚሰርቅ ነገር ብዙ ነውና ከቀን ይልቅ ሌሊትን መረጠ፡፡ አንድም አለቃ እንደመሆኑ ቀን ቀን የራሱ ሥራ ይበዛበት ነበረና ሌሊትን መረጠ፡፡
በዚህ ሳምንት ቤተ ክርስቲያን ስለ ምሥጢረ ጥምቀት ታስተምራለች፡፡ ጥምቀት ሰው ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግመኛ ተወልዶ የክርስቶስ አካል የማኅበረ ምእመናንም አባል የሚሆንበት ምሥጢር ነው፡፡ በጥምቀት ኃጢአት ይሰረያል፤ የእግዚአብሔር ልጅነት ይሰጣል፤ ልጅ ለሆነው ሁሉ ርስት ገነትና መንግሥተ ሰማያትም ይወረሳል፡፡
በዚህ ሰንበት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጎበኘኸኝ ፈተንኸኝ ምንም አላገኘኽብኝም፤ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው››፤ (መዝ 16፥3-4) የሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ነው፡፡
ዛሬ ብዙዎቻችን ባለሥልጣን ስለሆንን በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውስጥ ባለው መሬት ላይ ቁጭ ብለን መማር ያሳፍረናል፤ ሌሎቻችንም ባለሀብት ስለሆንን ለገንዘባችን እንጂ ለእግዚአብሔር የሚሆን ጊዜ አጥተናል፤ ሌሎች ደግሞ መምህር ነኝ አለቃ ነኝ በቅቻለሁ ነቅቻለሁ ትምህርት አያስፈልገኝም በማለት ከቤቱ ርቀናል፡፡ ቀሪዎቻችን ደግሞ የየራሳችን ምክንያት አበጅተናል፡፡ ኒቆዲሞስ ግን ከጌታ እግር ሥር ቁጭ ብሎ ለመማር እነዚህ ሁሉ ምክንያቶች አልከለከሉትም፡፡ እነዚህን ሁሉ ተጋፍጦ በመማሩ ከዮሴፍ ጋር የክርስቶስን ሥጋ ገንዞ ለመቅበርና በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ በታሪክ ለመዘከር በቅቷል፤ (ዮሐ 19፥38-42)፡፡ የእኛንም ሕይወት መቃኘት እንደሚገባን ቤተ ክርስቲያን በዚህ ሳምንት ከኒቆዲሞስ ሕይወት ጋር በማነጻጸር ታስተምረናለች፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ጾምና ምጽዋት፣ ሰባቱ አጽዋማት
✞ ድንግል የዚያን ጊዜ ✞
ድንግል የዚያን ጊዜ(2) ሐዘንሽ በረታ
በመስቀል ላይ ሆኖ ልጅሽ ሲንገላታ(2)
የግፍ ግፍ ደርሶበት የዚያን ጊዜ ተጠማሁ ሲልሽ
ለውሻ ያጠጣሽ በወርቅ ጫማሽ(2)
ሴቶች ሲያባርሩት የዚያን ጊዜ
ራርቶ ሆድሽ
ለፍጡር በማዘን ውሀ ያጠጣሽ (2)
ተጠማሁ እያለ የዚያን ጊዜ
ሲናገር ልጅሽ
ታድያ እንደምን ቻለው ወላድ አንጀትሽ(2)
እንደዚያ ስታለቅሽ የዚያን ጊዜ
ሐዘን ሲውጥሽ
እነማን ነበሩ ቀርበው ያፅናኑሽ(2)
ስታለቅሽ በማየት የዚያን ጊዜ
ራርቶ ልጅሽ
ዮሐንስን አፅናኝ አንድ ልጅ ሰጠሽ (2)
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ የሚጸልይ ሰው አሸናፊ ነው ✞
የሚጸልይ ሰው አሸናፊ ነው ይሰማል ጸሎቱ
ለጸሎት የሚቆም አሸናፊ ነው ይሰማል ጸሎቱ
አምላኩን ሲጣራ ይጠፋል እሳቱ
ጌታው ከእርሱ ጋር ነው ይሰምራል ስለቱ
ድል የሚያደርግበት ኃይልን ይታጠቃል
ውኃ እየገደበ በጸሎት ያቆማል
ሰባት እጥፍ እሳት በፊቱ ቢነድም
በረዶ ነው ለእግሩ ረግጦት ሲሄድ
/አዝ=====
ሺህ ጠላት ቢሰለፍ ቢጋረድ በፊቱ
የብርቱዎችን ቀስት ይሰብራል ጸሎቱ
አምኖ ለለመነ ሁሉ ይቻለዋል
ተራራውን ነቅሎ ባህር ላይ ይተክላል
/አዝ=====
ኃይሉ እያደረገ የጸሎትን ጉልበት
ወህኒውን ይሰብራል ይቆርጣል ሰንሰለት
በእሳት ሰረገላ በሰማይ ይበራል
ፀሀይ እያቆመ ዝናብን ያዘንባል
/አዝ=====
ተራራ ያከለው የችግራችን ቀን
ደልዳላ ይሆናል ፊቱ ከወደቅን
ለጸሎት ተነሱ ሰልፉን እንሰለፍ
እንቁም በእንባ መከራችን ይለፍ
👉 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
6. #ገብርኄር
ገብርኄር ማለት ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አገልጋዮችና አገልግሎታቸው በምሳሌ ያስተማረው ትምህርት የሚነገርበት ሳምንት ነው፡፡
ይኽውም አንድ ባለጸጋ ሰው ወደ ሌላ ሀገር ከመሔዱ አስቀድሞ ለሦስት አገልጋዮቹ እንደየአቅማቸው አንድ፣ ሁለት እና አምስት መክሊት እንደሰጣቸውና ከሔደበትም በተመለሰ ጊዜ ሁሉንም ጠርቶ ከነትርፉ መክሊቱን እንዲመልሱለት እንደጠየቃቸው ያስተማረበት ነው፡፡ ሁለቱ አገልጋዮች በእጥፍ አትርፈው ባለአምስቱ ዐሥር አድርጎ፣ ባለሁለቱም አራት አድረጎ መልሰውለታል፡፡ ባለአንዱ መክሊት ደግሞ መክሊቱን መሬት ቆፍሮ ቀብሮት ነበርና ሳያተርፍበት ያንኑ መልሶለታል፡፡ የቀበረበትንም ምክንያት ሲናገር ‹‹ጌታ ሆይ አንተ እኮ ካልዘራህበት የምታጭድ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ስለዚህ ፈራሁ ሔጄም መክሊትህን በምድር ቀበርኩት›› ብሏል፡፡ ባለጸጋውም አትርፈው የመለሱለትን ‹‹እናንተ ታማኝ አገልጋዮች በጥቂቱ ታምናችኋልና በብዙ እሾማችኋለሁ ወደ ጌታ ደስታ ግቡ›› ብሎ ሾሟቸዋል፡፡ ቀብሮ የመለሰውን ግን ‹‹አንተ ክፉና ሀኬተኛ ባሪያ…አትርፈህ ብትመልስ በተሸለምክ ነበር፤ ስለዚህ ያለውን ውሰዱበትና ዐሥር ላለውም ጨምሩለት ላለው ይጨመርለታል ከሌለው ግን ያንኑ ይወስዱበታል፤ እርሱን ግን ወደ ውጭ አውጥታችሁ ጣሉት›› ብሎ ፈረደበት፤ (ማቴ 25፥14-30)፡፡
በምሰሌያዊ ትምህርት ባለጸጋ የተባለው የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ አገልጋዮች የተባሉት ምእመናን ናቸው፤ መክሊት የተባለው ደግሞ ለምእመናን የተሰጣቸው መንፈሳዊ ጸጋዎች ናቸው፡፡ አትርፈው የመጡት በተሰጣቸው ጸጋ ለራሳቸው ተጠቅመው ለሌላውም ተርፈው መልካም አርአያና ምሳሌ ሆነው የሚኖሩ አገልጋዮች ምሳሌ ሲሆኑ የተሰጠውን መክሊት ቀብሮ ሰንብቶ ያንኑ የመለሰው ደግሞ የተሰጠውን ጸጋና ዕድሜን በከንቱና በዋዛ ነገር ሲያባክን የሚኖር ምእመን ምሳሌ ነው፡፡ አትርፈው የመጡት የተሸለሙት መንግሥተ ሰማያትን ሲሆን ቀብሮ የመጣው ደግሞ የተፈረደበት ትሉ ወደማያንቀላፋ እሳቱ ወደማይጠፋ ገሃነመ እሳት ነው፡፡ የተማረውን በልቡ ይዞ የኖረ ሰው፣ ሃይማኖት በልብ ነው፤ መናገር አያስፈልግም፤ የልቤን እግዚአብሔር ያውቀዋል፤ የእንጀራ ጉዳይ ነው ምን ላድርግ? እያሉ ራሳቸውን የሚያታልሉ ባለሥልጣናት የባለአንድ መክሊቱ አገልጋይ ምሳሌ ናቸው፡፡ ሳምንቱ ገብርኄር ተብሎ የተሰየመው በታማኞቹ አገልጋዮችና በታማኝነታቸው ነው፡፡
በዚህ ሰንበት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹አምላኬ ሆይ ፈቃድህን ለማድረግ ወደድሁ ሕግህም በልቤ ውስጥ ነው፤ በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አወራሁ እነሆ ከንፈሮቼን አልከለክልም አቤቱ አንተ ጽድቄን ታውቃለህ›› (መዝ 39፥8-9) የሚለው ነው፡፡ እኛም ሳምንቱን ስንዘክር ከእግዚአብሔር የተሰጠንን ጸጋ መጠቀም እንጂ መቅበር እንደሌለብን ራሳችንን እየጠየቅን መሆን አለበት፡፡ ቀሪ ዘመናችንንም ስላለፈው ዘመን ኃጢአት ንስሐ ለመግባት መወሰን ይገባናል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ሰባቱ አጽዋማት
━━━━━✦📖 ❖ 📖✦━━━━━
#የበገና_መዝሙር
#በከመ_ምህረትከ
#ዘማሪ_አቤል_ተስፋዬ
@enamsgn @enamsgn
@enamsgn @enamsgn
#ሰበር_ዜና
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) አረፉ።
ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ የሆኑት በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ (ዶ/ር) በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪ እና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል።
በረከታቸው ይደርብን!!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #እግዚአብሔር_ቅዱስ_ሚካኤልን_ወደ_በለዓም_እንደላከው
በለዓም በባላቅ ዘመን የነበረ ሀብተ መርገምና ቡራኬ የተሰጠው ሰው ነበር፡፡ እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በኋላ ዐርባ ዘመን በበረሃ ተጉዘው ሞዓብ ሲደርሱ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ‹‹ከግብጽ የወጣ ሕዝብ ምድርን በብዛቱ አለበሳት፤ ከእኔ ይበረታሉና እነሱን ለመውጋት አልችልም መጥተህ ርገምልኝ›› ብሎ እጅ መንሻ አስይዞ ወደ በለዓም ላከበት ላከበት፡፡ በለዓምም መልእክተኞችን ‹‹ዋሉ እደሩ አላቸው››፤ ሌሊቱንም እግዚአብሔር ወደ እርሱ መጥቶ ‹‹አትሒድ›› አለው፡፡ ከዚያም መልእክተኞቹን ‹‹አልሆነም ሒዱ›› አላቸውና ሔዱ፡፡ ንጉሥ ባላቅም እጅ መንሻ ቢያንስበት የተላኩት ተራ ሰዎች ቢሆኑ ነው ብሎ ከፊተኞቹ የበዙና የከበሩ ሰዎችን ላከ፡፡ እነዚህ የተላኩት ሰዎችም ባላቅ ‹‹ክብርህን ከፍ ከፍ አደርጋለሁ ያልኸኝንም አደርግልሃለሁና እኝህን ወገኖች መጥተህ ርገምልኝ›› ይልሃል ብለው ለበለዓም ነገሩት፡፡ እርሱም ‹‹ዋሉ እደሩ ወርቅና ብር ቢሰጠኝ በትልቁም ይሁን በትንሹ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ቸል አልልም፤ እግዚአብሔር የሚለኝን ልወቅ›› አላቸው፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ተነሥ ከእነርሱ ጋር ሒድ፤ ነገር ግን የምነግርህን ብቻ ትናገራለህ አለው፡፡
አህያይቱን ጭኖ ‹‹ከሔድኩማ እንዴት አልረግምም ኑ›› እያለ ሲጓዝ በመንገድ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፉን መዝዞ ለአህያይቱ ታያት፡፡ ፈርታ ቆመችና ወደ ምድረ በዳ ሔደች፤ በለዓምም ለመመለስ መታት፡፡ እንደገና ቅዱስ ሚካኤል በቀኝና በግራ የወይን አጥር ባለበት ቦታ ቆመ፤ አህያይቱም ወደ ቅጥሩ ተጠግታ የበለዓምን እግር መለጠችው (ላጠችው)፡፡ ዳግመኛ የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ቀኝም ወደ ግራም የሚሉበት በሌለ በጠባብ ቦታ ቆመ፡፡ ያችም አህያ መልአኩን ባየችው ጊዜ ከበለዓም እግር በታች ሰገደች፤ እርሱም አህያይቱን ይመታት ጀመር፡፡ አንደበቷን እግዚአብሔር ከፍቶላት ‹‹ይህ ሦስተኛ ነው፤ የምትመታኝ ምን አደረግሁህ?›› አለችው፡፡ እርሱም ‹‹ዘብተሸብኛልና ሰይፍ (ሾተል) በያዝሁ በቀላሁሽ በወጋሁሽ ነበር›› አለ፡፡ ያን ጊዜ በሰው አንደበት ‹‹ከታናሽነትህ ጀምረህ ተራራውን ውጪ ሜዳውን ሩጪ ብለህ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? ለምን ሦስት ጊዜ መታኸኝ? ምን አድርጌ ነው?›› አለችው፡፡ በዚህን ጊዜ ዓይኑ ተከፍቶ መልአኩ ተገለጠለት፤ ከአህያዋም ወርዶ ሰገደለት፡፡ መልአኩም ‹‹አህያህን ለምን ሦስት ጊዜ መታህ? ከፊቴ ባትሸሽ ኑሮ አንተን በገደልኩህ ነበር›› አለው፡፡ በለዓምም ‹‹በድያለሁ ፈቃድህ ካልሆነ ልመለስ›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹ሒድና የምነግርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ›› አለው፡፡
ንጉሡ ባላቅም በለዓም መምጣቱን ሰምቶ በደስታ ወደ አርኖን ዳርቻ ወጣ፡፡ እርሱም ‹‹ስለመጣሁ ደስ አይበልህ፤ እግዚአብሔር የገለጸልኝን ብቻ እናገራለሁ›› አለውና ወደ ምሥራቅ ተዟዙሮ ከተመለከተ በኋላ ‹‹እግዚአብሔር ያልረገመውን እንዴት እረግማለሁ እግዚአብሔርስ ያልነቀፈውን እንዴት እነቅፋለሁ›› ብሎ መለሰለት፡፡ ይሁን እንጂ ባላቅ ‹‹ርገምልኝ ብልህ ትመርቃቸዋለህን?›› ቢለው ‹‹የገለጸልኝን ብቻ እናገራለሁ አላልኩህምን›› በማለት በለዓም መለሰለት፡፡
ለሁለተኛ ጊዜ ባላቅ መሠዊያውን ከፍ አድርጎ ሠርቶ መሥዋዕቱን ጨምሮ ሠውቶ ‹‹እንደገና ርገምልኝ›› አለው፡፡ በለዓም ግን ክብራቸውን ተረድቶ ‹‹ከተራሮች ራስ አየዋለሁ ከኮረብቶችም አስተውለዋለሁ እነሆ ብቻውን የሚኖር ሕዝብ ከአህዛብም ጋር አይቆጠርም›› ብሎ ተናገረ፤ ባላቅም ‹‹ርገምልኝ ስልህ ክብራቸውን ትናገራለህ›› ብሎ አዘነ፤ (ዘኁ 23፥9)፡፡ ሦስተኛም መሥዋዕት ሠውቶ ‹‹ርገምልኝ›› አለው፡፡ በለዓምም ‹‹ያዕቆብ ከተማህ ምን ያምር እስራኤል ቤቶችህ ምን ያምሩ›› ብሎ አድንቆ አሞገሰ፡፡ አያይዞም ‹‹ኮከብ ከያዕቆብ ይወጣል›› እያለ ምሥጢረ ሥጋዌ ተገልጾለት ተናገረ፡፡ ‹‹ርገምልኝ ብልህ ትመርቃቸዋለህ?›› ሲለው ‹‹እግዚአብሔር የገልጸልኝን ብቻ እንደምናገር አላስታወቅሁህምን? የምትሻው ጥፋታቸውን ከሆነ ረግሜ ባላጠፋልህም መክሬ አጠፋልሃለሁ›› አለው፡፡ ከዚያም ‹‹ደናግሉን ጣዖት አሳዝለህ መሥዋዕተ እሪያ አስይዘህ ላካቸውና እንድረስባችሁ ሲሏቸው ለጣዖት ስገዱ ከመሥዋዕተ እሪያው ብሉ ይበሏቸው፤ መሥዋዕተ እሪያ ይበላሉ ለጣዖት ይሰግዳሉ፤ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ተቆጥቶ ያጠፋቸዋል›› አለው፡፡
ንጉሥ ባላቅም እንደ መከረው አደረገ፡፡ እስራኤልም ዐርባ ዘመን በበረሃ ሲዞሩ የኖሩ ናቸውና ተሻሟቸው፡፡ የይሁዳ የቤት አለቃ ዘምሪ ከባላቅ ቤት አለቃ ልጅ ከክስቢ ጋር ተጣቅሰው ወደ ድንኳን ገብተው ተኙ፡፡ አንድ ብላቴና አይቶ ለፊንሐስ ሲነግረው ፊንሐስ ከደብተራ ኦሪት ዘገር ነጥቆ በአጭር ታጥቆ ሁለቱን በጦር ከመሬት አጣበቃቸው፡፡ ወዲያው ጌታ ተገልጾ ‹‹የአሮን ልጅ ፊንሐስ ልቤን ደስ አሰኘሃት›› ብሎ መዓቱን በምሕረት መልሶላቸዋል፡፡ ለፊንሐስም ዘር ለሦሰት መቶ ዓመት ያህል መዋዕለ ክህነት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ፊንሐስን ‹‹የአሮን ልጅ›› ያለው አሮን አልዓዛርን አልዓዛር ፊንሐስን ስለወለደ ነው፤ (ሙሉ ታሪኩን ዘኁልቁ ምዕ 22 እና 24 ያንብቡ)፡፡ ይህ ታሪክ የተፈጸመው በ1280 ዓ.ዓ ሲሆን የበዓሉ መታሰቢያ መጋቢት 12 ቀን ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ስንክሳር ዘመጋቢት 12፣ መድበለ ታሪክ
✞ ለፍርድ ይመጣል አምላካችን ✞
ለፍርድ ይመጣል አምላካችን
ለፍርድ ይመጣል አምላካችን
ዋጋ ሊከፍል እንደ ስራችን
በኃይል በስልጣን ይገለጣል
የወጉት ሁሉም ያዩታል
ለፍርድ ይመጣል .. .. .. ..
አንደበትን ሁሉ ዝም ይላል
የተከፈተ አፍ ድዳ ይሆናል
መጽሐፍት ሁሉ ተዘርግተው
ይገለጣል የሁሉም ስራው
ለፍርድ ይመጣል .. .. .. ..
ዓለም በኃጢአቱ ይቀጣል
የትዕቢት ኩራት ይሻራል
ይዋረዳሉ ጨካኞቹ
ይከበራሉ ትሑቶቹ
ለፍርድ ይመጣል .. .. .. ..
ለአህዛብ ሊሆን ምስክር
የመንግስቱ ወንጌል ሲነገር
ቅዱስ ወንጌል ይህን ብሏል
ፍጻሜ ዘመን ያኔ ይሆናል
ለፍርድ ይመጣል .. .. .. ..
እንዲወጣ መብረቅ ከምስራቅ
እስከ ምዕራብ እንዲዘልቅ
የጌታ መምጣት እንደዚህ ነው
መንግስትና ፍርዱ በእጁ ነው
ለፍርድ ይመጣል .. .. .. ..
እንጠብቀው ተዘጋጅተን
ልባሞች ሆነን መብራት ይዘን
አናውቀውምና ቀኒቱን
የሙሽራውን መምጫውን(፪×)
👉 ዘማሪ ዲ/ን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #የመስቀል_መገለጥ (መገኘት)
ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ ሆኗል፡፡
የመጀመሪያው አይሁዳውያን ቀብረውት በላዩም ላይ ቆሻሻ እየጣሉ ከ200 ዓመታት በላይ ቆይቶ ነበር፡፡ የንጉሥ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት ዕሌኒ ልጇ ወደ ክርስትና ሃይማኖት ቢገባ ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን እስካገኘችው ድረስ ልትፈልገው፣ በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ልታንፃቸው ለእግዚአብሔር ተስላ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅዋ ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን አምኖ በተጠመቀ ጊዜ ዕሌኒ ቅድስት ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ ስለ ከበረ መስቀል በመረመረች ጊዜ ስለቦታው የሚያስረዳት አላገኘችም፡፡ ቤቱን የሚጠርግ ሰው ሁሉ ጥራጊውን በውስጡ የከበረ መስቀል ባለበት ላይ እንዲጥል አይሁድ አስቀድመው አዝዘው ነበርና ንግሥት ዕሌኒ እስከ ደረሰችበት ጊዜ ድረስ ጥራጊያቸውን ሲጥሉበት ስለኖሩ ኮረብታ ሆኖ ነበርና፡፡ በኋላም የአይሁድ ወገን የሆነ ኪራኮስ የሚባል ሽማግሌ ሰው አግኝታ ብትጠይቀው ምንም አልነገራትም፤ እርሷም ምግብና መጠጥ ከልክላው በተጨነቀ ጊዜ ዕጣን በማጤስ ከዚያም የዕጣኑ ጢስ የሚያርፍበት የጎልጎታን ኮረብታ አስጠርጊ ብሎ ነገራት፡፡ በዚያ አካባቢ ሦስት ተራራዎች ስለነበሩ ለምልክት ይሆን ዘንድ ነው የዕጣኑን ጢስ እንድታጤስ ምልክት የነገራት፤ ጢሱም የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በተቀበረበት ተራራ ላይ ሔዶ ሰገደ፡፡ ይህንም ያስደረገችው መስከረም ዐሥራ ስድስት ቀን (በአሁኑ ዘመን ደመራ በመባል የሚከበረው) ሲሆን መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን ቁፋሮውንና ጥርጊያውን ይጀምሩ ዘንድ አይሁዳውንን አዘዘቻቸው፡፡
አይሁዳውያንም ሥራውን መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን ጀምረው መጋቢት ዐሥር ቀን ሦስት መስቀሎች የተገኙ ቢሆንም የትኛው ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል እንደሆነ ግን አላወቁም ነበር፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል የትኛው እንደሆነ ለመለየት በተቸገሩ ጊዜ የሞተ ሰው አግኝተው አመጡና አንዱን መስቀል በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አልተነሣም፡፡ ደግሞ ሌላውን መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አኖሩት አሁንም አልተነሣም፡፡ ከዚህም በኋላ ሦስተኛውን መስቀል አምጥተው በሞተው ሰው ላይ አደረጉት ያን ጊዜ የሞተው ሰው ተነሣ፡፡ ዕሌኒም የክርስቶስ መስቀል መሆኑን አውቃ ሰገደችለት፤ የክርስቲያን ወገኖችም ሁሉ ሰገዱለት፡፡ ይህን መስቀል ከቅንዋቱ ጋር ወደ ልጅዋ ቆስጠንጢኖስ ልካዋለች፡፡ ከዚህም በኋላ አብያተ ክርስቲያናትንና የከበሩ ቦታዎችን አሳንፃለች፡፡
ሁለተኛው በኋላ ዘመን የፋርስ ሰዎች ኢየሩሳሌምን ወርረው የከበረ የክርስቶስ መስቀልን፣ ብዙ ሰዎችንም ማርከው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፤ በዚያም የፋርስ ንጉሥ ጉድጓድ አስቆፍሮ የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አስቀበረው፡፡ ንጉሥ ሕርቃል በሮም በነገሠ ዘመን ወደ ፋርስ ዘምቶ ይህን የተቀበረውን መስቀል አውጥቶ ወደ ቁስጥንጥንያ ወሰደው፡፡ ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን አስቆፍራ ያገኘችበት እና ንጉሥ ሕርቃልም ለሁለተኛ ጊዜ የተቀበረውን መስቀል ያገኘበት መጋቢት ዐሥር ቀን ነው፡፡ የመስቀሉ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ ስንክሳር ዘመጋቢት 10
#ዕለተ_ረቡዕ
፩ኛ)#ምክረ_አይሁድ ይባላል።
★ የአይሁድ ሊቀ ካህናት ጌታን እንዴት መያዝ እደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ጭንቀት ነበር፤ ምክንያቱም ወቅቱ አይሁድ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ፳፥ ፮)
👉 የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ እለት በቤተክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ፣ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በሐዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻህፍትን በማንበብ በጾም፣ በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
፪ኛ)#የመልካም_መዓዛ_ቀን ይባላል።
★ ጌታችን በዚህ ዕለት ስምኦን ቤት ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ህይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቶዋ ማርያም)፤‹‹ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ›› ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦሰት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሄድ በጠጉሩ(በራሱ)ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ተብሎ ይጠራል፡፡
፫ኛ)#የዕንባ_ቀን ይባላል።
★ ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር አንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሰዋለችና፡፡ (ማቴ፳፮፥ ፮፣ ማር ፲፬፥ ፱፣ ዮሐ ፲፪፥ ፰)
#እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞
#እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞
#አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞
#ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በፍሥሓ_ወበሰላም። ✞✞✞
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞ ኪራላይሶን ✞
ኪራላይሶን ኪራላይሶን/3/
ኪራላይሶን /2/ አማኑኤል ጌታ
ኪራላይንሶ /2/ በጥፊ ተመታ
ኪራላይሶ /2/ አለምን ሊታደግ
ኪራላይሶን /2/ ተነዳ እንደበግ
ኪራላይሶን /2/ አዳምን ሊፈውስ
ኪራላይሶን /2/ ቆመ ከጵላጦስ
ኪራላይሶን ኪራላይሶን ኪራላይሶን
ኪራላይሶን/3/
ኪራላይንሶ /2/ እጁን ቸነከሩት
ኪራላይሶን /2/ አጥንቱን ቆጠሩት
ኪራላይሶን /2/ የእሾህ አክሊል ደፍቶ
ኪራላይሶን /2/ ገዳዩን እረቶ
ኪራላይሶን /2/ የሁላችን በደል
ኪራላይሶን /2/ ተሻረ በእርሱ ቁስል
ኪራላይሶን ኪራላይሶን ኪራላይሶን
ኪራላይሶን/3/
ኪራላይሶን /2/ እጣ ተጣጣሉ
ኪራላይሶን /2/ ልብሱን ተካፈሉ
ኪራላይሶን /2/ ለፍርድ ተወሰደ
ኪራላይሶን /2/ እንደበግ ታረደ
ኪራላይሶን /2/ ለብሶ ከደም ሜዳ
ኪራላይሶን /2/ ተከፈለ እዳ
ኪራላይሶን ኪራላይሶን ኪራላይሶ
ኪራላይንሶ /3/
ኪራላይንሶ /2/ ሆምጣጤ አጠጡት
ኪራላይሶን /2/ በገመድ ጎተቱት
ኪራላይሶን /2/ በወንበዴው ፈንታ
ኪራላይሶን /2/ ተሰቀለ ጌታ
ኪራላይሶን /2/ ሁሉም ዘበቱበተ
ኪራላይሶን /2/ በዘላለም ህይወት
ኪራላይሶን ኪራላይሶን ኪራላይሶን
#እምበለደዌ_ወሕማም፤ ✞✞✞
#እምበለ_ጻማ_ወድካም ✞✞✞
#አመ_ከመ_ዮመ_ያብጸሐነ፤ ✞✞✞
#ያብጸሐክሙ_እግዚአብሔር_በፍሥሓ_ወበሰላም። ✞✞✞
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#አዘነች_ድንግል_አለቀሰች
አዘነች ድንግል አለቀሰች ፍጹም አምርራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ
በአንድ ልጇ ምክንያት ደርሶባት መከራ/፪/
#አዝ
በመንጻቱ ወር በዓርባኛው ቀን
ሥምዖን አረጋዊ ታቀፈ እና ጌታን
ትንቢት ተናገረ ተገልጾለት ሞቱ
በነፍስሽ ሠይፍ ያልፋል አንቺም እናቲቱ
ይኽንን መከራ ሲሠማ ጆሮዋ
አምርራ አለቀሰች አልቆም አለ ዕንባዋ
#አዝ
በአሥራ ሁለት ዓመቱ ለማክበር በዓል
በኢየሩሳሌም ቢገኝ አማኑኤል
ሲጠይቅ ሲሠማ በቤተ መቅደሱ
የኦሪት ካኅናት ሲደነቁ በእርሱ
እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈልጋ
ልቧ ተሠበረ በሐዘን አለንጋ
#አዝ
ጠዋት በማለዳ በጲላጦስ ደጅ
ሲጸናበት አይታ የጨካኞች እጅ
ርቃኑን አድርገው ያለ አንዳች ጥፋት
ከግንድ ጋር አስረው ጀርባውን ሲገርፉት
እንዴትስ አታለቅስ እንዴት አታነባ
ሲገርፉት ሲያዳፉት ልጇን እንደ ሌባ
#አዝ
የዓለሙን ፈጣሪ የዓለሙን ዳኛ
ንጹሑን ጌታ መሥሏቸው ቀማኛ
እጁን እና እግሮቹን በችንካር ወጥረው
በወንበዴ መሐል ሠቅለውን ብታየው
ድንግል አለቀሰች አልቻለች መጽናናት
ዕንባዋ ወረደ እንደ ክረምት ጅረት
#አዝ
ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በአንድ ሲማከሩ
ቅዱሥ ሐያል ብለው ገንዘው ሊቀብሩ
በአዲስ መቃብር በአሥራ አንደኛው ሠዓት
ሥጋውን አኑረው በድንጋይ ቢዘጉት
እያለች ዐነባች አንድ ልጄ እኮ ነው
ከእርሱ የሚቀድም ተከታይ የሌለው።
/channel/mezmuredawit
/channel/mezmuredawit
✞ ቃልሽ ተቀየረ ✞
ቃልሽ ተቀየረ አንቺ እየሩሳሌም
ሆሳዕና እንዳላልሽ ክብር በአርያም
ስቀለው ስቀለው ብለሽ መጮህሽ
ያልሰጠሽ ምን አለ ያጎደለብሽ
ደም ግባቱ ጠፍቶ የአብ አንድ ልጅ
ሲገርፉት አመሹ በቀያፋ ደጅ
አፉን አልከፈተም መልስንም ለመስጠት
የውኃውን አምላክ ሃሞት ሲያጠጡት
/አዝ=====
መቆም እስኪያቅተው ሰውነቱ ዝሎ
መከራውን አየ ስለኛ ኃጢያት ብሎ
የአማልክት አምላክ ተንገላታ እንደሰው
የጠፋው አዳምን ቤቱ ሊመልሰው
/አዝ=====
በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል በግ
ዝምታን መረጠ መልካምን ለማድረግ
ለሰው ያለው ፍቅር ወሰን አልነበረው
እርሱ እየሸሸው በፍቅር ተከተለው
👉 ዘማሪት ለምለም ከበደ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#የዘመን_ፍፃሜ
የዘመን ፍፃሜ እስከዚህ የሌለህ
ዘላለም የምትኖር /3/ ፍጹም አምላክነህ
ሆሳዕና /3/ በአርያም
ቡሩክ ሆሳዕና አምላከ እስራኤል
ተቀምጦ መጣ /3/ በአህያ ግልገል
ትንሹም ትልቁም በአንድነት ዘመሩ
አመሰገኑት /3/ ሆሳዕና እያሉ
በጣም ደስ ይበልሽ እልል በይጽዮን
ንጉስሽ መጣልሽ /3/ ሊሆንሽ መድኅን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
ኒቆዲሞስኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ ክቡር
በጨለማው ግርማ ኮከብ የደመቀ
ሌቱን በብርሃን የሚማር መምህር (፪)
በመከራው ፅናት ይህን ዓለም ናቀ
መምሕር ሆኖ ሳለ ከመማር ያልራቀ
የትዕቢትን ጅረት በትሕትና ተዋርዶ አደረቀ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
ፍርሃትን በሚጥል ፍፁም ፍቅር ያደረ
ከመስቀል አውርዶ ጌታውን ቀበረ
የመግነዙን በፍታ በሽቱ ያከበረ
ከመቅደሱ አንቀጽ ላይረሳ አምድ ሆኖ ታጠረ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ነገረች
ህጉን ለሚያስበው ምክር አለኝ እያለች
ከጨለማው ኃጢአት ነቅታ ብርሃን ካየች
እንደ ኒቆዲሞስ ነፍስህም ተምራ ተመለሰች
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
አኮኑ አጽባዕት እምነ አጽባዕት የአቢ
ረቢ ሰገደ በመንፈቀ ሌሊት ለረቢ
/channel/mezmuredawit
/channel/mezmuredawit
✞ የምትወዱት ሰዎች አልቅሱለት ✞
ብክይዎ ወላሕውዎ
እለ ታፈቅርዎ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ኤልማስ
ዘበ እደ አይሁድ ተአስረ
አመ ጸምአ ማይ ይሰቲ
ሀሞተ ወከርቤ መሪረ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ
ጌታዬ አምላኬ በደል ሳይኖርበት ተገፋ
የአዳምን መርገም ሊያጠፋ
በአይሁድ እጅ ታሰረ
እንደ ወንጀለኛ ተቆጠረ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ስለኔ
አልቅሱለት ስለ መከራው የምትወዱት
አዕንቃዕደ ወሰማየ
ኀበ አቡሁ ነጸረ
ሶበመንፈሱ ትወጽዕ
በላዕለ መስቀሉ ገአረ
ወይቤ ወይቤ ተፈጸመ ኲሉ
ውሃን የፈጠረ ተጠማ
ሀሞትን አጠጡት እየደማ
የሾህ አክሊል ደፍቶ ቀና አለ
መራራውን ጽዋ ተቀበለ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ስለኔ
አልቅሱለት ስለ መከራው የምትወዱት
በእናቱ ፊት ሰቀሉት
በጥፊ እየመቱ ዘበቱበት
ሐዘኑንስ እንዴት ትቻለው
መተኪያ የሌለው ልጇ እኮ ነው
እውነት ወደ ምድር ቢመጣ
በሀሰት ዳኝነት ተመታ
በጀርባው ላይ ጅራፍ አረፈ
ደሙ እንደ ውሃ ጎረፈ
ጌታዬ አምላኬ ሞተልኝ ሰለኔ
ወይቤ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ
ወይቤ ኤሎሄ ተፈጸመ ኲሉ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ መዘንጋት በአለበት ✞
መዘንጋት በአለበት በታናሽ ህሊና
መዘመር ልጀምር ለድንግል ምስጋና
እኔስ በውዳሴሽ ባሕር እዋኛለሁ
ገናንነትሽን ክብርሽን እያሰብኩ
የትህትናሽ ነገር ቢወሳ አያልቅም
ታነቢያለሽ እና ለዚህ ክፉ ዓለም
ድንግል ሆይ ለኃጥአን ታስቢያለሽና
ልቦናዬ በአንቺ በምልጃሽ ተፅናና
/አዝ=====
ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን
አንቺን ተማጽነናል እንድታማልጂን
ዘወትር እጆችሽ ተዘርግተዋልና
ስለ በደለኞች ሊያቀርቡ ልመና
/አዝ=====
እሳታውያኑ ሱራፌል ኪሩቤል
ሊነኩት ያልቻሉት የእሳቱን ነበልባል
አንቺ ግን ታቀፍሽው ሳምሽው በከንፈርሽ
ከፍጥረት ለይቶ ፍፁም ስላፀናሽ
/አዝ=====
ማርያም ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን
አንቺን ተማጽነናል እንድታማልጂን
ዘወትር እጆችሽ ተዘርግተዋልና
ስለ በደለኞች ሊያቀርቡ ልመና
👉ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞ ቸር አገልጋይ ማነው ✞
ቸር አገልጋይ ማነው ለንጉሥ የታመነ
መክሊቱን ያልቀበረ አትርፎ የከበረ (፪)
ባለ አምስቱ መክሊት መልካም ያደረገው
በመውጣት በመውረድ አትርፎ መጥቶ ነው
በጥቂቱ ታምኖ በብዙ የተሾመው
ባለ አምስቱ መክሊት ሊቀ ጳጳሱ ነው
/አዝ=====
ሳይሰለች የተጋ ባለሁለት መክሊት
የታመነ እረኛ በፍቅርና በእምነት
ግባ የተባለው ወደ ጌታው ደስታ
አጥምቆ ያቆርባል ካህኑ የጌታ
/አዝ=====
ለሚበልጠው ጸጋ ተጠርቶ የነበረ
መክሊቱን ደብቆ ቆፍሮ የቀበረ
ሰነፍ ባርያ ተብሎ ወደ ፍርድ ተጣለ
ማኔ ቴቄል ፋሬስ በአምላክ ፊት ቀለለ
/አዝ=====
ፈቃድህን ማድረግ ነፍሱ ለምትወደው
ወንጌልህን መግለፅ የየዕለት ግብሩ ነው
ህግህ ለዘለላም ተጽፎ ይኖራል
በታላቅ ጉባኤ ጽድቅህ ይነገራል
👉 ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞ ይቅር ስላልከኝ ✞
ይቅር ስላልከኝ ነው የእኔ መቆም
ደግሞ እንዳልፈርድ እርዳኝ(፪×)
በሰዎች ድካም
ለዛሬ መድረሴ አይደል በጽድቄ
እያነሳኸኝ ነው አይተህ ወድቄ
በፈረድኩበት ፍርድ እንዳይፈረድ
አልሁን ፈሪሳዊ ወንድሜን ልውደድ
ጉዱፉን አልይ የወንድሜን በደል
አለ በኔ ላይ ምሰሶን የሚያህል(፪×)
ባታለብሰኝ ኖሮ ነውሬን ሸፍነህ
ባታቆመኝ ኖሮ በደሌን ከድነህ
በጠፋ ነበር ስም አጠራሬ
ድካሜ ብዙ ነው እንደ ራስ ፀጉሬ
ጉዱፉን አልይ የወንድሜን በደል
አለ በኔ ላይ ምሰሶን የሚያህል(፪×)
በምሕረትህ ብዛት ከቤትህ ልግባ
ዘወትር ላቅርብልህ የእንባዬን መባ
የውስጤን ማንነት ላንተ ልግለጥ
ለሰው አሳልፈህ ለማትሰጥ
ጉዱፉን አልይ የወንድሜን በደል
አለ በኔ ላይ ምሰሶን የሚያህል(፪×)
ዕለት ዕለት ግብሬ ኃጢአት መስራት ነው
አንተም ዕለት ዕለት እኔን መማር ነው
የበደለን መተው ያንተ ነውና
በወንድሜ መማር ቆሜ አልቅና
👉 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በከመ ምህረትከ ✞
ከአስሩ አንዱ ድንገት ቢጠፋባት
ድሪሟን ፍለጋ ሴቲቱ ተነሳች
ቤቷን ስታፀዳ አብርታ መብራቷን
ከቆሻሻ መሃል አየችው ድሪሟን
ያ ድሪም እኔ ነኝ በቃልህ ማልገኝ
በቤትህ ውስጥ ሆኜ በቤትህ ማታውቀኝ
ከቆሻሻ መሃል ከምታገኛቸው
አገልጋዮች መሃል እኔነኝ ዋነኛው
በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
የሰበከውን ቃል በህይወቱ ነዋሪ
የጠፋው ርሱ ነው ሞልቷል ተናጋሪ
በክፉ ስራዬ በኔ ተነቅፈሃል
የስም ብቻ አገልጋይ መች ያስደስትሃል
ቅርብ ነው አንደበቴ ልቤ ግን የሸሸ
ማንነቴ ባዶ በቃልህ ያልታሸ
ዛሬ አስተካክለኝ ልታነፅ በቃልህ
በእኔ አይሰደቡ ቅን አገልጋዮችህ
በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
ሀገሪቱ ረስታ መጎብኘቷ ወራት
እንባህን አፍስሰህ ለሷ አለቀስክላት
ዛሬ ብትመጣ በልቤ ከተማ
አዝነህ ታለቅሳለህ በእኔ ምግባርማ
በመቅደስህ መሃል ድፍረቴ የበዛ
ልቤ ለአለም እንጂ ለአንተ ያልተገዛ
የስም ብቻ አገልጋይ መሆኔን ታውቃለህ
ድሮስ ከእኔ አይነቱ ምንስ ታገኛለህ
በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
የቃኤል መሠዋዕት ከመቅደስህ ገብቶ አንድነት ተረስቶ ሁሉ ተለያይቶ
እንክርዳዱን መሠዋዕት ቁራ በትኖታል
ፍቅር አልባ መሠዋዕት መች ያስደስተሃል
ይቁም በመቅደስህ መሸጥ መለወጡ
አፊንና ፊንሃስ ከመቅደስህ ይውጡ
ሳሙኤልን መሠል ቅን አገልጋዮችህ
በመቅደስህ ይብዙ ተናገር ይበሉህ
በከመ ምህረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ
አምላካችን ሆይ እንደቸርነትህ ነው እንጂ እንደበደላችን አይሁን/3/
👉 ዘማሪ አቤል ተስፋዬ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
ልዩ መረጃ!
በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉት ቀሪ 23 ግለሰቦች የይቅርታ ደብዳቤያቸውን ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ለብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እያቀረቡ ይገኛሉ።
ዝርዝር መረጃ ከደቂቃዎች በኋላ የምናደርስ ይሆናል!
✞ ኃዘንተኛዋ ሙሽራ ✞
ኀዘንተኛዋ ሙሽራ ቤተክርስቲያን ሆይ
ይመጣል ንጉሥሽ ከላይ ከሰማይ
ይታበሳል እንባሽ መች ይቀራል ፈስሶ
ኀዘንሽ ይቆማል በደስታሽ ተክሶ
ቢኖርም ሺህ ታንኳ ገሊላ ባህር ላይ
አይሏል ወጀቡ ጌታ ባለበት ላይ
ንውጽውጽታው ሲያይል ጭንቀቱ እንዳይንጠን
ቅዱስ ጴጥሮስ አለ ይጣራል ጌታሽን
ያብሳል እንባሽን ያብሳል
ሙሽራሽ ክርስቶስ ይነሳል
/አዝ=====
በሰፊው ድንኳንሽ በብዙ የገባው
ከድግስሽ ሊቀምስ ማልዶ የታደመው
የሠርግሽ ተጋባዥ ታውኳል መንፈሱ
አይመጣም ወይ ይላል አይደርስም ንጉሡ
ይደርሳል ንጉሥሽ ይደርሳል
ታዳሚሽ ከጽዋው ይቀምሳል
/አዝ=====
በዘመናት ሁሉ ቢያይልም ፈተናሽ
ፈታኞችሽ ጠፍተው አንቺ ግን ሕያው ነሽ
አጥብቆሽ ነው የሚያልፈው ጊዜያዊው ፈተና
ኃይልና ጉልበትሽ ክርስቶስ ነውና
ይመጣል ይደርሳል ሙሽራሽ
ወደ ደስታሽ ሊጠቀልልሽ
አዝ=====
አይደንቀንም ከቶ የማዕበሉ ብዛት
ፅኑ መሠረት ነው የቆምሽበት አለት
ሙሽራይቱ ሆይ ከቶም አትዘኚ
እንባን በሚያብሰው በአምላክሽ ታመኚ
ብትደክሚም በእንባ በኀዘን
አይቀርም የደስታሽም ቀን
👉ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
5. #ደብረ_ዘይት
ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ በዚህ ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኢየሩሳሌም መፍረስና ስለ ዓለም መጨረሻ አስተምሯል፤ (ማር 13፥3)፡፡ በሆሣዕና ዕለትም ወደ ኢየሩሳሌም የገባው ከዚህ ተራራ ተነስቶ ነው፤ (ማር 11፥1)፡፡ በዕለተ ሐሙስ ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ ለአይሁድ ራሱን አሳልፎ የሰጠውም ከዚህ ተራራ ግርጌ በምትገኘው በጌቴሴማኒ ነበር፤ (ማቴ 26፥30)፡፡ በመጨረሻም ወደ ሰማይ ያረገው በዚሁ ተራራ ነው፤ (ሉቃ 24፥51 ፣ ሐዋ 1፥12)፡፡ በዚህ ተራራ ሐዋርያት የዓለም ፍጻሜና ዳግም ምጽአት መቼና እንዴት እንደሆነ ጠይቀውታል፤ ጌታም የዘመኑ ፍጻሜ ሲቃረብ የሚታዩትን ምልክቶች ዘርዝሮ ነግሯቸዋል (ማቴ 24፥1-8)፡፡ ይህ ሰንበት የዐቢይ ጾም እኩሌታ /ደብረ ዘይት ተብሎ መሰየሙ ጌታ በደብረ ዘይት ተራራ ስለ ዓለም መጨረሻ ምልክቶች ለደቀ መዛሙርቱ የነገረው የሚታሰብበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡
የደብረ ዘይት ዕለት የሚሰበከው ምስባክ ‹‹እግዚአብሔር ከክብሩ ውበት ከጸዮን ግልጥ ሆኖ ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይነዳል፤ (መዝ 49፥2-3) የሚለው የቅዱስ ዳዊት መዝሙር ነው፡፡ ‹‹ግልጥ ሆኖ ይመጣል›› ያለው ከዚህ ቀደም ሰው ሆኖ እንደተገለጠ ያይደለ በግርማ መለኮት በክበበ ትስብእት ይገለጣል ማለቱ ነው፡፡ ‹‹ዝምም አይልም›› ማለቱ ደግሞ አመጣጡን ሲለየው ነው፤ ከዚህ ቀደም አይሁድ በጥፊ ሲመቱት፣ ምራቅ ሲተፉበት፣ በመስቀል ሰቅለው አምላክ ከሆንክ ና ውረድ እያሉ ሲሳለቁበት፣ የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ነው፣ በአጋንንት አለቃ ስም በብኤልዜቡል አጋንንትን ያወጣል ብለው ሲዘልፉት አንዳችም ሳይመልስ ዝም እንዳለ አሁን ዝም አይልም ኃጢአተኛውን ወደ ገሃነም ጻድቁን ወደ መንግሥተ ሰማያት ግባ ብሎ ይፈርዳል እንጂ፡፡
ሐዋርያት በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ስለ ዳግም ምጽአት ስለ ዓለም ፍጻሜ እንዲያስረዳቸው ኢየሱስ ክርስቶስን በጠየቁት ጊዜ ዘመኑንና ቀኑን ከሥለሴ በስተቀር ማንም አንደማያውቅ ነገር ግን ዘመኑ ሲደርስ የተለያዩ ምልክቶች እንደሚታዩ ከነገራቸው በኋላ ‹‹ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ›› (ማቴ 24፥20) ብሏቸዋል፡፡
ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት አይሁን ለምን አለ?
ሽሽት በክረምት፦ በዚህ ወቅት ቤተ ክርስቲያን ስለ መግቦተ እግዚአብሔር በሰፊው ታስተምራለች፤ ዳግም ምጽአቱንም ትዘክራለች፡፡ ‹‹ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፤ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም፤ ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጩቶች ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል›› (መዝ 146፥7-9) እንዲል ዳዊት በመዝሙሩ፡፡ ወርኃ ክረምት ገበሬው በቤቱ ያለውን እህል አውጥቶ የሚዘራበትና ፍሬውን ለማየት ወርኃ ጸደይን በተስፋ የሚጠብቅበት ነው፡፡ እስከዛ ድረስ ግን የሚበላ አጥቶ ይራባል፤ በዚህ ጊዜ ሽሽት ቢመጣ ለመንገድ የሚሆን ስንቅ የለውምና ከባድ ይሆንበታል፡፡
ቡቃያና ቅጠል እንጂ ፍሬ በማይገኝበት ክረምት ስደት አስቸጋሪ እንደሆነ ሁሉ መንፈሳዊ ፍሬ ሳናፈራ፣ የጽድቅ ሥራ ሳንሠራ ጌታ ለፍርድ መጥቶ የት ነበራችሁ? ምንስ ሠራችሁ? ባለን ጊዜ ምክንያትና ምላሽ እንዳናጣ በሃይማኖት ቆመን ትሩፋት እንድንሠራና መጨረሻዬን አሳምርልኝ፤ ፍሬ ሳላፈራ ቀኑ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ እያልን በጸሎት እንድንተጋ ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡ (ቅዳሜ የሚጸለየውን ውዳሴ አምላክ ይመልከቱ)፡፡
ሌላው የወርኃ ክረምት ከሰማይ በሚወርድ ዝናብ፣ ከምድር በሚፈልቅ ምንጭ የተነሳ ምድር የምትጨቀይበትና ወንዞች የሚሞሉበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ሽሽትና ስደት አስቸጋሪ ነው፤ ምክንያቱም ሽሽት ባለበት በፍጥነት መጓዝና አቋራጭ መንገዶችን መጠቀም ያስፈልጋልና፡፡ ይህ ከእኛ መንፈሳዊ ሕይወት ጋር ሲገናኝ ሕይወታችን በኃጢአት ጨቅይቶ መንገዳችን በክፋት ተሞልቶ ሳለ ጌታ እንዳይመጣ መጸለይ እንደሚገባን በተጨማሪም ድካምና መሰላቸት ሳይኖር በወቅትና በሁኔታ ሳንገደብ ሁል ጊዜ ተዘጋጅተን መኖር እንደሚገባን ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች፡፡
ሽሽት በሰንበት፦ በዕብራይስጥ ሰንበት ማለት ማቆም፣ መተው፣ ማረፍ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በስድስት ቀናት ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን አርፏልና ሰባተኛው ቀን ሰንበት መባሉም ከዚህ የመጣ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ድካምና ዕረፍት አይስማማውም፤ ዐረፈ ማለታችን ከዕለተ ዓርብ በኋላ አዲስ ፍጥረት እንዳልፈጠረ ለመግለጽ ነው፡፡ ከሰው አንፃር ግን ሰንበት ለምድራዊ ሕይወት ከመውጣት ከመውረድ ዐርፈን ለሰማዊት ርስት የሚያበቃንን መንፈሳዊ ሥራ የምንሠራበት ዕለት ነው፡፡
በኦሪት ሕግ ለእስራኤል ከተሰጡት ትእዛዛት አንዱ ‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ›› (ዘጸ 20፥8-11) የሚል ነው፡፡ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ይህን ሕግ እየጠቀሱ ጌታን ከሰውታል፤ ምክንያቱም ሕጉ ምንም ሥራ አትሥሩ ይላል፤ ጌታ ደግሞ ‹‹ኦሪትን አልሽራትም ግን ፍጹም አደርጋታለሁ›› (ማቴ 5፥17) እንዳለው በሰንበት ዕለት ድውያነ ነፍስን በትምህርት ድውያነ ሥጋን በተአምራት ይፈውሳቸው ነበር፡፡ አይሁድ ይህን አይተው ‹‹በሰንበት መፈወስ ተፈቅዷልን?›› ብለው በጠየቁት ጊዜ ‹‹ከእናንተ አንድ በግ ያለው በሰንበት በጉድጓድ ቢወድቅበት ይዞ የማያወጣው ሰው ማነው? እንግዲህ ሰው ከበግ ይልቅ እንደምን አይበልጥም?! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዷል›› ብሏቸዋል፤ (ማቴ 12፥1-12)፡፡
‹‹ሽሽታችሁ በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ›› መባሉ ሰባተኛውን ቀን ዐርፍበታለሁ ብሎ ስድስቱን ቀን ይተጋል፤ ቀኑም ሲደርስ ለማረፍ ወስኗልና ይተኛል፤ ያንቀላፋል፡፡ ከተኙበት ነቅተው የፈቱትን ታጥቀው መሸሽ ደግሞ ጊዜ ይጠይቃል፡፡ ልልበስ፣ ልታጠቅ እያለ ሌሎች ጥለውት ይሔዳሉ፤ በመጨረሻም በሩ ይዘጋበታል፡፡ ከዚያ በኋላ ለሚመጣ መልስ የሚሰጥ አይኖርም፡፡ ጌታችን ይህንን በምሳሌ ስለ አምስቱ ልባሞች እና አምስቱ ሰነፎች አስተምሯል፤ (ማቴ 25፥1-13 ያንብቡ)፡፡ ጽድቅን ከመሥራት፣ በጾምና በጸሎት ከመትጋት በደከምን ጊዜ በጎ ሥራችን ተሟጦ አልቆ የመንፈስ ዝለት ይዞን ጥሪው እንዳይደርሰን፣ የት ነበራችሁ? ምንስ ሠራችሁ? በተባልን ጊዜ ምላሽ እንዳናጣ ሽሽታችሁ በሰንበት አይሁን ብሎ በምሳሌ አስተማረ፡፡
ሽሽታችን በሰንበትና በክረምት እንዳይሆን ‹‹ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና›› (ማቴ 24፥44) ብሎ ያስተማረውን በመተግበር ወደ ልባችን ተመልሰን፣ ኃጢአታችንን ተናዘን፣ ካህኑ የሚሰጠንን ቀኖና በሚገባ ፈጽመን ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን ወገባችንን ታጥቀን መብራታችንን አብርተን ልንጠብቅ ይገባናል፡፡ ‹‹ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን›› (ሉቃ 12፥35) እንዲል፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ሰባቱ አጽዋማት
ወደ ሲኦል ሲወስዷቸው አይቶ በእኔ ምክንያት ነው ብሎ ወደ ገደል ሔዶ እግሩን በገመድ አስሮ ተዘቅዝቆ ሲጸልይ ሰይጣን ገመዱን ቆረጠው። ያን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ደርሶ በእግርህ ላቁምህ በራስህ ሲለው በራሴ አለው፤ ከዚያም በራሱ ቁሞ በድንጋይ ላይ ለሰላሳ ዓመት ቆየ፤ ከዚያ በኋላ ጌታ ሦስት ጊዜ ጠርቶ ምሬልሃለሁ አለው፡፡ ከማርክልኝ አስነሳቸውና ተጠምቀው ክርስቲያን ይሁኑ ቢለው ሥልጣን ሰጥቼሃለሁ ሒድና አስነስተህ አጥምቀህ ክርስቲያን አድርጋቸው ብሎ ላከውና አንስቶ ክርስቲያን አደረጋቸው። ከዚህም ዓለም የሚሰናበትበት የዕረፍቱ ቀን ሲደርስ ጌታችን ተገልጦ መታሰቢያውን ለሚያደርግ እስከ 15 ትውልድ እንደሚምርለት ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡ የግብፅና የኢትዮጵያንም ሰዎች ዐሥራት ተቀብሎ በብዙ ገድልና ትሩፋት ኖሮ ብዙ ባሕታውያን በተገኙበት መጋቢት 5 ቀን በዕለተ እሑድ በተወለደ በ562 ዕድሜው በሰላም ዐረፈ፡፡ የዕረፍቱ መታሰቢያ መጋቢት 5 ቀን ሲሆን በዓለ ዕረፍቱን ከጾም ለይቶ ለማክበር በአበው ትውፊት ጥቅምት 5 ቀን በጎላ ሁኔታ ይከበራል።
ጸሎቱ በረከቱ በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን!!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መድበለ ታሪክ ፣ ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፣ የቅዱሳን ታሪክ ቁጥር 5