የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን" መዝ 150÷6 " አሕዛብ ሁላችሁ፥ እጆቻችሁን አጨብጭቡ፥ በደስታ ቃልም ለእግዚአብሔር እልል በሉ።" (መዝሙረ ዳዊት 47:1) ለማንኛውም ሀሣብ, ጥቆማ, አስተያየት @Kidusyared_comment_bot ላይ ቢያስቀምጡልን ይደርሰናል
✞ እንባችን ደረቀ ✞
እንባችን ደረቀ ለካስ ያልቃል እንባ
ሃይል አጣን ለሀዘን ኧረ ወዴት እንግባ
ኤርምያስን እንጥራው ቢያስተምረን ሰቆቃ
'መቼ ነው ሚቆመው የምዕመናን ሴቃ/2/
አሐዱ አብ ቅዱስ ብሎ የቀደሰው
የካህኑ ደም ነው በግፍ የፈሰሰው
ማን ማንን ያፅናና በሁሉም ቤት ለቅሶ
መቼ ነው ምናየው ዕንባችን ታብሶ
/አዝ=====
ለምን ትተኛለህ ጌታችን ሆይ ንቃ
መገፋት ስቃዩን አልቻልነውም ይብቃ
የሰማዕታት ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ
የሰማነው ሁሉ በኛ ላይ ደረሰ
/አዝ=====
ኃጥያት በአንድ በኩል ከውስጥ ይወጋናል
ጠላትም ከውጪ ቀስት ያነሳብናል
ከማዕተባችን ጋር በፍቅርህ እሰረን
ከፈተና አታግባን ቢመጣም አስችለን
/አዝ=====
እኛን ከሞት ይልቅ መካድ ያስፈራናል
ከፈተናም ይልቅ መውደቅ ያሰጋናል
የሠለስቱ ደቂቅ የአርባዕ ሐራ ጌታ
አሁን ድረስልን በአለም አንረታ
/አዝ=====
ቅዱሳን ሰማዕታት ኢትዮጵያን ክበቡ
በእምነታችን አፅኑን ሳይሰጥም መርከቡ
ጊዮርጊስ ሆይ ድረስ ዛሬም እንደ ጥንቱ
ያንተን ፀሎት አምነን አንቀርም በከንቱ
👉ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሚፀጋ ዮሐንስ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ እግዚአብሔር ያጽናናሽ ✞
እግዚአብሔር ያጽናናሽ ዕንባሽን ያብሰው
ቤተክርስቲያን ሆይ እስከ መጨረሻው
ካህንሽ ከመቅደስ ከበጎቹ ጋራ ስለታረደብሽ
እንደ ራሔል ዕንባ እግዚአብሔር ያስብሽ
ስለ ጌታ ፍቅር ማኅተቧን ይዛ አክሊል ተቀዳጀች
በደሙ ከዋጃት ከክርስቶስ ጋራ እኖራለሁ አለች
የእውነት ሰማዕትነት ሲመጣ በገሃድ
ይሻሙ ነበረ ከእሳቱ ለመንደድ
/አዝ=====
በዚህ በእኛ ዘመን ቅዱሳን ተሻሙ
አክሊሉን ለመውሰድ ከሁሉ ሊቀድሙ
የተክለሃይማኖት የክርስቶስ ሠምራ ህፃናት ተነሱ
በመሞት ሕይወትን ከእግዚአብሔር ሊወርሱ
/አዝ=====
አሕዛብ አትድከም በመግደል አትጸድቅም
ነፍሰ ገዳይነት አሸንፎ አያውቅም
በበቀል ጭካኔ የሠው ልጅን ማረድ
እጅግ የወጣ ነው ከሃይማኖት መንገድ
/አዝ=====
ይህቺ ቤተክርስቲያን የተገነባችው በደም ስለሆነ
በሞት ሕይወት ሊያገኝ ክርስቲያን ታመነ
ምድሪቱ ለእግዚአብሔር የተቀደሰች ናት
ሕዝቧም ሊሆን ቀርቧል እንደ በግ መስዋዕት
👉 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ መከራው ክርስትናዬን አጣፈጠው ✞
መከራው ክርስትናዬን አጣፈጠው
ስደቱ ማህተቤን አጠበቀው
በሞት መንደር በሀዘን ውስጥ በመከራ
አየውት እግዚአብሔርን ከኔ ጋራ
ክርስትያን ተብለን በክርስቶስ ስም የተጠራነው
በጥልቁ ውስጥም በእግዚአብሔር እንድናምን ነው
ለጥቂት ግዜ ቢበረታብን ስደት ሀዘኑ
አምላክ ግን መውጫ ያዘጋጃል በዚህ ተፅናኑ
/አዝ=====
በስደት ሳለን ካፋችን ቢደርቅ የፅዮን ዜማ
ከወንዙ አጠገብ ቁጭ ብለን ሰለን ድምፁን ሳንሰማ
በእግዚአብሔር ጊዜ ከባቢሎን ምድር እንለቃለን
መሰንቆአችንን ከአርያም ዛፍ ላይ እናወርዳለን
/አዝ=====
ደካሞች ሲሉን በስሙ ያን ጊዜ እንበረታለን
ድሆች ስንባል ባለጠጎች እናደርጋለን
በምድር ቅዱስ ህዝብ አድርጎ ለእርሱ ለየን
ጨለማው አልፎ በቸርነቱ ብርሀን አሳየን
/አዝ=====
ከፀጋ በላይ እንዳንፈተን ይከልለናል
በቁስላችን ላይ የፈውስን ዘይት ያፈስልናል
በጊዜም ቢሆን ያለ ጊዜውም በእርሱ እንፅና
እንኳን ስደቱን ሞቱን ሊገታው ይችላልና
👉 ሊቀ-መዘምራን ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
ልታስበው የሚገባ በመሆኑ ከጾመ ነቢያት ጋር አያይዘን እንድንጾም ሐዋርያት ሰብአ ነነዌ የተነሳሕያን አብነት ናቸውና ሥርዓቱም ጾሙም አይቅር ብለው ቀኖና ሠርተውልናል፡፡ እኛም በጾምና በጸሎት ከፈጣሪያችን ምሕረትና በረከት ለማግኘት ስንል እንጾመዋለን፡፡
በተጨማሪም ይህ ጾም ለዐቢይ ጾም መዘጋጃ በመሆን ያገለግላል፡፡
የነነዌን ሕዝብ በእሳት ከመቃጠል ያዳናቸው አምላክ እኛንም ከገሃነም እሳት ያድነን፡፡ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ስንክሳር ዘታኅሣሥ 6 ፣ ሰባቱ አጽዋማት ፣ ጾምና ምጽዋት
@EwketBirhan
✞ ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን ✞
ይለፍ ይጠር ይሄ ዘመን(፪×)
በብዙ መከራ ያለንበት ታመን
ያች የቃየን ድንጋይ የሞት መልእክተኛ
ለማቁሰል ለመግደል ዛሬም አትተኛ
ንጹህ ደም አፍስሰህ አትሁን ቀበዝባዛ
አቤልን አትግደል ቃኤን ልብ ግዛ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
/አዝ=====
መተሳሰብ ጠፋ ክፋት ሰለጠነ
እግር ደም ለማፍሰስ አብዝቶ ፈጠነ
መልካም አይታይም መልካም አይሰማ
አምላክ አንተ ሁነን ማምለጫ ከተማ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
/አዝ=====
አልደራደርም ስላለ በርስቴ
በግፍ ደሙ ቢፈስስ ቢገደል ናቡቴ
አንድ ቀን አይቀርም ዳኛው ፍርድ ይሰጣል
የኤልዛቤልን ደም ውሾች ይልሱታል
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
/አዝ=====
ጥልና ክርክር በመስቀል ተገድሎ
ይኸው ዛሬ ታይቶአል በልባችን በቅሎ
በሥራና በእውነት መዋደድ አብዛልን
እግዚአብሔር አቅልለው የከበደብንን
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
/አዝ=====
ለራስ ወዳድነት እጅ የሰጠ ትውልድ
በእሾህ አጥሮበታል የወንድሙን መንገድ
ደግ ሰው አለቀ ፍቅራችን ቀዝቅዛ
እኛ ማለት ቀርቶ እኔን ማለት በዛ
አሳላፊው ቅዱስ አሻጋሪው ጌታ
ኢትዮጵያን አስባት አትይ በዝምታ
👉 ዘማሪ ቀሲስ ወንድወሰን በቀለ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞═══●◉❖◉●═══✞
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
╚✞═══●◉❖◉●═══✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
†✝† እንኳን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †✝†
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያዊ †††
††† ልደት †††
††† መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን
የወለዱት ደጋጉ: ጸጋ ዘአብ ካህኑና እግዚእ ኃረያ ናቸው::
እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ
እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::
በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው ቅዱስ
ሚካኤል: ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ
አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን
መወለድ አብስሯቸዋል::
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱት መጋቢት 24 ቀን
በ1206 ዓ/ም ሲሆን የተወለዱት ደግሞ ታኅሣሥ 24 ቀን
በ1207 ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት
ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::
††† ዕድገት †††
የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው "ፍሥሃ ጽዮን" ይሰኛል::
ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው
አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት:
ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ
እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁናም ከወቅቱ ጳጳስ አባ ጌርሎስ
ተቀብለዋል::
††† መጠራት †††
አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት
ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑት
በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::
የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:: "ከዛሬ
ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን::
ከዚህ በኋላ አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር
ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ
ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላ ሰዓትን አላጠፉም::
ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው
እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::
††† አገልግሎት †††
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከጳጳሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል
አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው
ሽዋ (ጽላልሽ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን
አሳምነው አጠመቁ:: ያን ጊዜ ኢትዮጵያ 2 መልክ ነበራት::
1ኛ. ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች
ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን
ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::
2ኛው ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ
ተነቃቅቶ ነበር::
ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት ሐዲስ ሐዋርያ
አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ
መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን:
መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን
(ጠንቋዮችን) አጥፍተዋል::
††† ገዳማዊ ሕይወት †††
††† ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮጵያን
ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል::
እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት
አገልግለዋል::
እነዚህም በአቡነ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት:
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ
ዳሞ ከአቡነ ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26
ዓመታት አገልግለዋል::
በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ
(ዞረሬ) ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት
ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን
በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::
††† ስድስት ክንፍ †††
ኢትዮጵያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት
ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት
ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ
መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::
ከወቅቱ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው
ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ
ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ
ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም
ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::
ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት
የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
*በቤተ መቅደስ ብስራቱን
*በቤተ ልሔም ልደቱን
*በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
*በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
*በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::
የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ
ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት
ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና
ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል
ማርያም ፈጥና ደርሳ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ወደ ሰማይ
አሳረገቻቸው::
††† በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*6 ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ
ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::
††† ተአምራት †††
የቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት
የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::
ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን
መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ
ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን
ታሥሯልና::
††† ዕረፍት †††
††† ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን
ሆነው: መከራን በብዙ ተቀብለው: እልፍ አእላፍ ፍሬን
አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው
ነሐሴ 24 ቀን በ1306 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል
ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10
ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::
††† በዚህ ዕለት አባታችን ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት
የቆሙበት ቀኝ እግራቸው መሠበሩንና በአንድ እግራቸው
ለ7 ዓመታት ቆመው መጸለያቸውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
ታስባለች::
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
✞ በስባረ አጽምህ ✞
በስባረ አጽምህ በፈሰሰው ደምህ
በፈጸምከው ገድልህ በአማላጅነትህ
ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ
እርዳን በጸሎትህ
የጨለማው ገዢ ሳጥናኤል ይፈር
በጸሎትህ እሳት ተቃጥሎ ይረር
አጥር ቅጥር ሆነህ በዙሪያችን ኑር
ጠላታችን ጠፍቶ እንድናገኝ ክብር
/አዝ=====
እጆችህ ይዘርጉ በመስቀሉ ባርከን
ክህነት አለህና ጠብቅ ልጆችህን
በችግር ላይ ስንወድቅ አውጣን ከመከራ
በተሰጠህ ኪዳን ሰውረን አደራ
/አዝ=====
ጻድቁ አማልደን በነፍስም በሥጋ
ከኢየሱስ ክርስቶስ እንድናገኝ ዋጋ
በክንፎችህ ጋርደን በቆላም በደጋ
አባት አትለየን ጠብቀን ከአደጋ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ሞትማ_ለመዋቲ_ይገባል ✞
ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪)
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(፪)
ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(፪)
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ(፪)
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(፪)
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያመልአከ ሞት፪)
/አዝ=====
ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(፪)
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(፪)
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(፪)
/አዝ=====
ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(፪)
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(፪)
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(፪)
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(፪)
ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት:
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #የእመቤታችን_በዓለ_ዕረፍት
(አስተርእዮ ማርያም)
‹‹ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ›› (ነግስ ዘቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ)
ማርያም ማለት ልዕልት ማለት ነው፤ ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች ናትና፡፡ አንድም የብዙኃን እናት፣ ጸጋ ወሀብት ማለት ነው፤ ለጊዜው ለእናት አባቷ ተሰጥታለች፤ ፍጻሜው ለዓለም ተሰጥታለችና ፍጽምት ማለት ነው፡፡ አንድም ለጊዜው መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተገኝታለችና ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ንጽሐ ነፍስ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ ይዛ ተገኝታለችና፡፡ አንድም መርሕ ለመንግሥተ ሰማያት ማለት ነው፤ በአማላጅነቷ ምእመናንን መርታ መንግሥተ ሰማት ታስገባለችና፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕረፍት (የአስተርእዮ ማርያም በዓል) ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት መካከል አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በ64 ዓመቷ ጥር 21 ቀን ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከመከራና ከሐዘን ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ታላቅ ዕለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ታላቁ የቤተ ክርቲያናችን አባት ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ሞት ለማናቸውም ሥጋን ለለበሰ ሰው ሁሉ የተገባ ነው የቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሞት ግን ሁሉን እጅግ ያስደንቃል ያስገርማል›› በማለት ያደነቀው።
ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ላይ የኖረችባቸው 64 ዓመታት እንደሚከተለው ተገልጸዋል።
❖ ከእናት ከአባቷ ጋር 3 ዓመት
❖ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት
❖ ጌታን በጸነሰች ጊዜ በአረጋዊው ዮሴፍ ቤት 9 ወር ከ 5 ቀን
❖ ከልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር 33 ዓመት ከ3 ወር
❖ ከጌታ ዕርገት በኋላ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር 15 ዓመት በድምሩ 64 ዓመት በዚህ በኃላፊው ዓለም ኖራ ጥር 21 ቀን በ49 ዓ.ም በክብር ዐርፋለች።
ይህንንም አበው ‹‹ሞትኪሰ ማርያም ይመስል ከብካበ›› ‹‹ማርያም ሆይ ሞትሽስ ሰርግ /ከብካብ/ ይመስላል›› በማለት ይናገራሉ፤ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ‹‹ጊዜ ዕረፍታ ለማርያም ወረደ ወልድ እምዲበ ልዕልና በልሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና›› በማለት በዜማ ድርሰቱ ተናግሯል፡፡ የእመቤታችን ዕረፍት እንባ መራጨት፣ ጠጉር መንጨት፣ ደረት መድቃት እንዳለበት የሰነፍ ሰው ሞት አልነበረም፤ ይልቁንም እንደ ሠርግ ቤት መላእክት በውዳሴ፣ በማኅሌት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና ወደ ሰማይ ሸኟት እንጂ፡፡ ይህንን ታላቅ ምሥጢር ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ ታቦት›› (መዝ 131፥8) ፣ ‹‹በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች›› (መዝ 44፥9) ሲል የተናገረው ቃለ ትንቢት በንጽሐ ሥጋ፣ በንጽሐ ነፍስ፣ በንጽሐ ልቡና የጸናች የእመቤታችንን ዕረፍት፣ ትንሣኤ፣ ፍልሰት/ዕርገት/ የሚያስገነዝብ የትንቢት ቃል ነው፤ (ራእ 11፥19)፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ ‹‹የሰማይ ንግሥት›› (ራእ 12፥1) በማለት እንደገለጻት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንም የእመቤታችንን ክብርና ልዕልና አምልተውና አስፍተው ገልጸውታል፡፡ ‹‹…በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዐን ናቸው፤ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል›› ራእ 14፥13) እንዲል እመቤታችን ከዕረፍቷና ዕርገቷ በኋላ የመጨረሻ ወደ ሆነው ክብር መሸጋገሯን ያስረዳል።
#የዕረፍቷ_ነገር
64 ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 ቀን ጌታ እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሎ መጥቶ ‹‹እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ›› ባላት ጊዜ ‹‹ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህን አንተን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማሕፀኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን?›› አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ ‹‹እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል›› አላት፤ አነኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፤ በዚህ ጊዜ ቅድስት ሥጋዋ ከቅድስት ነፍሷ ተለይቷል፡፡ ዕረፍቷ ጥር 21 ሲሆን የሥጋዋ በክብር ማረፍና ዕርገቷ በወርሃ ነሐሴ ነው፡፡ በዚህም ብዙ ተአምራትና አስደናቂ ምሥጢር የተገለጠበት በመሆኑ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› ተባለ።
አስቀድመው 12ቱ ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ ይህም የሆነው እንዲህ ነው፡- እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍቷ ሲቀርብ በጸሎቷ ሐዋርያትን እንዲያመጣላት ወደ ጌታ በመጸለይዋ ነው፡፡ ጌታም ዮሐንስን ከኤፌሶን፣ የሞቱትን አስነስቶ ያሉትን በደመና ጭኖ አመጣላት፡፡ እነርሱም መጥተው ሰገዱላት፤ በደብረ ዘይት ያሉ ደናግልም ተሰበሰቡ፤ ጌታም እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሎ መጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ዕውራን በሩ፤ ለምጻሞች ነጹ፤ አጋንንት ከሰዎች ወጡ፤ የተለያዩ በሽታ ያለባቸው ሁሉ ተፈወሱ፡፡ ከዚህ በኋላ በዝማሬ መላእክት በቃለ አቅርንት መልአከ ሞት ሳይቀርባት ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ ሥጋዋን ቅበሩ ብሎ አሳረጋት።
ቅዱሳን ሐዋርያት የእመቤታችንን የከበረ ሥጋዋን ገንዘውና ከፍነው ለማሳረፍ ወደ ጌቴሴማኒ መካነ ዕረፍት (የመቃብር ቦታ) ይዘው ሲሔዱ አይሁድ በቅንአት መንፈስ ተነሳስተው ‹‹ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሳ፤ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ፤ አሁን ደግሞ እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች፣ ዐረገች እያሉ ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን? ኑ ተሰብሰቡና ሥጋዋን በእሳት እናቃጥል›› ብለው ተማክረው መጡ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊም የከበረ ሥጋዋን የተሸከሙበትን የአልጋ ሸንኮር በድፍረት ሲይዝ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁለት እጆቹን ቆረጣቸው፡፡ እጆቹ ተንጠልጥለው ከቆዩ በኋላ ‹‹በእውነት የአምላክ እናት ናት›› በማለት ስለ አመነ እጆቹ ተመልሰው እንደነበሩ ሆነውለታል፡፡ ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ በገነት መኖሩን ለቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፤ ሐዋርያትም የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ በገነት አግኝተው ለመቅበር በነበራቸው ምኞትና ጉጉት የተነሣ ‹‹እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን ብንጠየቅስ ምን እንመልሳለን?›› በማለት በነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ጀምረው ሲጾሙና ሲጸልዩ ሰንብተው በሁለተኛው ሱባኤ መጨረሻ ነሐሴ 14 ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ የከበረ ሥጋ አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬና ውዳሴ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀላት መካነ ዕረፍት በጌቴሴማኒ ቀበሩዋት፡፡ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር›› የተባለበት ዐቢይ ምክንያትም ይህ ነው፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነስታለች፤ ትንሣኤዋም ‹‹ከመ ትንሣኤ ወልዳ ፥ እንደ ልጇ ትንሣኤ›› ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታና ምሥጢር ነው፡፡
✞ ይህ አይገባትም ✞
ይህ አይገባትም አገር ለሰራችው
አገር ላቆመችው
ድምጿን ስትቀንስ /ዝም ያለች መስሏችሁ፪×/
የነኳት አልፈዋል እርሷ ግን ጸንታለች
ይህንንም አልፋ ገና ትኖራለች
ከአምላኳ ተምራ ብዙ ብትታገስ
ጽኑ ናት ተዋህዶ ዘላለም የማትፈርስ
የማታውቁ እንደሆን መዝገቧን ግለጡ
መቻል ልማዷ ነው በዓይኗ ግን አትምጡ
/አዝ=====
አርዮስ ንስጥሮስ መች አነቃነቋት
ግራኝ እና ዮዲት መች ቻሉ ሊያጠፏት
ስድባችሁን ችላ ብትመርቃችሁ
በመንገዷ ላይ ግን አትቁሙ ገብታችሁ
/አዝ=====
ወደኋላ አታይም እርፍን ጨብጣለች
በሥጋ ደም ጥበብ መቼ ትመካለች
ከእርሷ ላይ ውረዱ እጃችሁን አንሱ
እሳትን ለማጥፋት እሳት አትለኩሱ
/አዝ=====
ነፍስን የሚታደግ ጉዞዋ ረጅም ነው
ከምድር ተጀምሮ ሰማይ ነው የሚያልቀው
ስለማትችሉ ይህን ልታስቆሙ
ተዋህዶን ለማጥፋት በብዙ አትድከሙ
👉 ዘማሪ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
#አንዲት ቤተ ክርስቲያን
#አንድ ሲኖዶስ
#አንድ ፓትርያርክ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ቂርቆስ ለወዳጁ ✞
ለወዳጁ ቂርቆስ ለወዳጁ
ያነሳዋል ላደገ ከደጁ
በብርቱ ሰልፍ ሆኖ ለእኔ ብርቱ
ሰው አርጎኛል በምልጃው ሰማዕቱ
እንደ ቤተልሔም ቤቱ ነው ልደቴ
ማረፊያዬም እርሱ ናዝሬት ሰገነቴ
አንዳች ያልነበራት ቤቴ ተጎብኝታ
አወጀች ለክብሩ የድሉን እልልታ
ውበት ማዕረጌ
ቆምኩኝ አደግድጌ
ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
ታብሷል እንባዬ
/አዝ=====
ግሩም ቃልኪዳኑ በውስጤ እየሰራ
ሜዳ ያረግ ነበር ግዙፉን መከራ
አበባ ነው ስሙ ዕፍራን የተባለ
ስንቱን አልፎ አየው ቂርቆስ ቂርቆስ ያለ
ውበት ማዕረጌ
ቆምኩኝ አደግድጌ
ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
ታብሷል እንባዬ
/አዝ=====
በወዳጅ ንከሻ ሲዛነፍ ሰላሜ
ገድሉን እየሰማሁ ቀለለ ሸክሜ
በናቀኝ ዓለም ፊት አርጎኝ ባለዋጋ
ጨለማውን ይኸው ሰማዕቱ አነጋ
ውበት ማዕረጌ
ቆምኩኝ አደግድጌ
ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
ታብሷል እንባዬ
/አዝ=====
ከማውጀው ቃላት ንግግር በላይ ነው
በመውጣት መውረዴ ቂርቆስ ያደረገው
ዛሬን ለመዋጀት መሠረት ሆነና
መጽሐፈ ዜናውን ቃኘው እንደገና
ውበት ማዕረጌ
ቆምኩኝ አደግድጌ
ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
ታብሷል እንባዬ
/አዝ=====
ውለታውን ሳስብ እንባ ካይኔ ይፈሳል
ስለ እርሱም ስከትብ ብዕሬ ኅይል ያጣል
ከመቅደሱ ጽድቅን ታጥቄ በረከት
አጉራሹ ሰማዕቱ ይታያል በኔ ፊት
ውበት ማዕረጌ
ቆምኩኝ አደግድጌ
ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
ታብሷል እንባዬ
👉 ዘማሪ ዲያቆን ገዛኸኝ ኤርባ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔✞══●◉❖◉●══✞
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit ❖
╚✞══●◉❖◉●══✞
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ቃና_ዘገሊላ
ቃና በሰሜናዊ እስራኤል ከናዝሬት ከተማ ሰባት ምዕራፍ ወጣ ብላ በገሊላ አውራጃ የምትገኝ ሲሆን ጌታ ገቢረ ተአምር አድርጎባታል። ይህም ‹‹ወአመ ሣልስት ዕለት ከብካብ ኮነ በቃና ዘገሊላ›› ትርጓሜውም ‹‹በሦስተኛው ቀን የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና ሰርግ ሆነ›› እንዲል (ዮሐ 2፥1)። ሰርጉ የተደረገው ጌታ ከገዳመ ቆሮንጦስ እሑድ የካቲት 20 ቀን ወጥቶ ማክሰኞ የካቲት 23 ቀን በሙሽራው በነዶኪማስ ቤት ነው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ጌታችንና ደቀ መዛሙርቱ የዚህ ሰርግ ታዳሚ ነበሩ፡፡ ሆኖም ግን ሰርጉ ሳያልቅ እንግዳው ሳይመለስ ወይን አለቀባቸው፤ እመቤታችንም ሲጨነቁ አይታ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ትርጓሜውም ‹‹ወይን እኮ አልቆባቸዋል›› ብላ ለልጇ ለኢየሱስ ክርስቶስ ነገረችው። እርሱ የማያውቀው ሁኖ አይደለም፤ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ለማለት ነው እንጂ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ እነርሱ መጨነቋንና መማለዷን ዐውቆ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋራ ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት ፤ ይህም ውኃውን ጠጅ አድርግላቸው ብትይኝ አይሆንም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋራ ምን ጠብ አለኝ ሲላት ነው፡፡ አንድም ውኃውን ጠጅ አድርግላቸው ብትይኝ አይሆንም እልሽ ዘንድ ውኃውን ጠጅ ላላደርግላቸው ከሰርግ ቤት ተጠርቼ መጥቻለሁን? ሲል ነው።
ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር እንዲል ‹‹ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜዬ›› ነገር ግን ጊዜዬ አልደረሰም አለ። ሥራውን የሚሠራበት ጊዜ አለውና በቀትር የሚሠራውን በሠለስት አይሠራውምና በሠለስት የሚሠራውን በነግህ አይሠራውምና፤ አንድም ጠጁ ፈጽሞ አላለቀም ነበር። ያለውን አበረክተ እንጂ ድንቅ ተአምር አልሠራም ብለው አይሁዳውያን ለሚያነሱት ኑፋቄ ምክንያት ለማሳጣት ነው፡፡ አንድም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሁዳ ወደ ውጭ ወጥቶ ነበርና እስኪመለስ ነው፤ ምክንያቱም ከተአምራቱ ቢለየኝ በሞቱ ገባሁበት እንዳይል ምክንያት ለማሳጣት ነው። ምሥጢሩ ግን በወይን ተመስሎ የሚሰጠው ደሜ የሚፈስበት ዕለተ ዐርብ አልደረሰምና ጊዜዬ ገና ነው ሲላት ነው፡፡ ለጊዜው ግን ስላለቀው የወይን ጠጅ ነበርና እመቤታችን ፈቃዷን እንደሚፈጽምላት ዐውቃ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው። በዚያም ሥፍራ የነበሩትን 6 ጋኖች ውኃ እንዲሞሏቸው ጌታ አሳላፊዎቹን በአዘዛቸው ጊዜ እስከ አፋቸው ድረስ ሞሏቸው፤ ወዲያው ውኃው ተለውጦ የወይን ጠጅ ሆነ። ለሊቀ ምርፋቁም (ለአሳዳሪው) እንዲቀምስ ሰጡት፤ ምክንያቱም ሁሉ ጠጥቶ ሰክሯል ጣዕም አያውቅም እርሱ ግን አልጠጣምና ጣዕም ያውቃል ብለው። በቀመሰውም ጊዜ ከቀድሞው ይልቅ ጥሞ ቢያገኘው ሙሽራው ዶኪማስን ጠርቶ ‹‹ሰው ሁሉ ያማረውን መጀመሪያ ያጠጣል ፤ በኋላ መናኛውን ይሰጣል፤ አንተ ግን ጥሩውን እስከ አሁን አዘገየኽ›› ብሎ አድንቋል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ 33 ዓመት ሲያስተምር ለሚያደርጋቸው ደጋግ ተአምራት የመጀመሪያው ምልክት ይህ ነው፡፡ በዚህም የጌታ አምላክነት የድንግል ማርያም አማላጅነት ተገለጸበት፤ (ስለ ቃና ዘገሊላ ዮሐ 2፥1-11 ያንብቡ)።
ይህ ተአምር የሆነው የካቲት 23 ሲሆን ‹‹በዓለ ማይ ምስለ ማይ›› ትርጓሜውም የውኃን በዓል ከውኃ ጋር በሚል ጥር 12 ቀን ከበዓለ ጥምቀት ቀጥሎ ይከበራል። በዓሉ አማናዊ ወይን (ደመ መለኮት) የሚፈስበት የስቅለት ምሳሌ ሲሆን መታሰቢያው ጥር 12 ቀን ይከበራል። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የዮሐንስ ወንጌል አንድምታ
✞ ደመቀ አበራልን ✞
ደመቀ አበራልን የአማኑኤል ሥራ/2/
ሙሽሮች ሆኑ አብርሃምናሣራ
በቤተክርስቲያን ጥላ ተጠልለው
ተክሊል አድርገዋል ሙሽሪት ሙሽራው
ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ስለተሰጣቸው
ሙሽሪት ሙሽራው አበራፊታቸው
/አዝ=====
የተራራቀ አካል አንድ ሆነ በተክሊል
እግዚአብሔር ይመስገን እልልእልል እንበል
አጥንትሽ ከአጥንቴ ሥጋሽ ከሥጋዬ
አዳም ያሰበከው ይኸው ዛሬታዬ
/አዝ=====
የተክሊል ብርህኗ በኛ መሃል በርቶ
ረቂቅ አንድነት ታየ በሷ ጎልቶ
ይህን ድንቅ ነገር ለማየት ያበቃን
ምሥጢሩን የሚገልጽ እግዚአብሔር ይመስገን
/አዝ=====
ነጭ መጎናጸፍያ በአንድነት ተጐናጽፈው
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል አረፉ በጥላው
ሙሽሪት ሙሽራው ለፍቅር ተሸነፉ
ለቁርባን መቁረቢያ ነጭ ልብስ አሰፉ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ መጥተዋል ጌታ ወደ አንተ ✞
መጥተዋል ጌታ ወደ አንተ(፪)
ሙሽሮቹ ጌታ ወደ አንተ(፪)
የቅዱሳን ክብር የእኛ ተስፋችን
የማትጠየፈን በኃጢአት ብንወድቅም
ለጎረቤታችን ምሳሌ እንድንሆን
መዋደድ መፋቀር ሰላሙን አድለን
/አዝ=====
ሁሉን እንድንችል ኃይልን የምትሰጠን
መጽናኛ ደጋፊ አባት የምትሆነን
ብናጣም ብናገኝ አንተ ሃብታችን ነህ
እንዳንደክም እንዳንዝል ጽናት የምትሆነን
/አዝ=====
መጥተዋል ድንግል ወደ አንቺ(፪)
ሙሽሮቹ ድንግል ወደ አንቺ(፪)
ቃና ዘገሊላ በዚያ በዚያ በሠርግ ቤት
አማላጅነትሽ በተገለጠበት
ለልጅሽ ነግረሽው ጋኑን ያስሞላሽው
ዛሬም ለሚጠሩሽ ለሚማጸኑሽ
ፈጥነሽ ድረሽና ባርኪው ጎጆውን
/አዝ=====
ወላዲተ አምላክ ቅድስተ ቅዱሳን በጭንቀት ደራሽ ነሽ ሩኅሩኅ እናታችን
ወደ አንቺ ስንመጣ ወደ ደጃፍሽ
እቅፍ ድግፍ አርጊን እንዳንጠፋብሽ
👉 ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ኧኸ ቃና ዘገሊላ ✞
ኧኸ ቃና ዘገሊላ(፪)
በእመብርሃን ምልጃ በረከት ተመላ
በክርስቶስ ተአምር በረከት ተመላ
ኧኸ ቃና ዘገሊላ
የዶኪማስ እልፍኝ ያልተስተካከለው
ሁሉን ለመሸኘት ብዙ የጎደለው
ጥቂት ብቻ ነበር የጓዳው ዝግጅት
ሞልቶ ተራረፈ ጌታ ሲገኝበት
/አዝ=====
አልባሌውም ወይን ፈጽሞ እንዳለቀ
ኋላም በምትኩ አዲስ ተጠመቀ
ለስካር አይደለም ለእምነት ሆነላቸው
የእመብርሃን ምልጃ እጅግ ደነቃቸው
/አዝ=====
የቃናው ሰርግ ቤት ትንሽ የምትመስለው
ዝናዋ ገነነ ዓለም ሁሉ ሰማው
ዛሬም ይህች ድንኳን ትንሽ አይደለችም
ስለታደመባት ጌታ መድኃኒዓለም
/አዝ=====
ጋኖቻችሁ ሁሉ የጎደለባቸው
ወይን ስላለቀ እጅግ ያፈራችሁ
የጌቶቹን ጌታ ጥሩት ከእናቱ ጋር
ባርኮ ከሰጣችሁ ይዳረሳል ለአገር
/አዝ=====
አልባሌውን ወይን ፈጽሞ እንዳለቀ
ኋላም በምትኩ አዲስ ተጠመቀ
ለስካር አይደለም ለእምነት ሆነላቸው
የክርስቶስ ተአምር ስለበዛላቸው
መዝሙር
በማህበረ ሰላም
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ተዋሕዶ ሰማያዊት ✞
ተዋሕዶ(2)ሰማያዊት
የፀናች እምነት(2)ሃሌ ሉያ
ተዋሕዶ(2)መንፈሳዊት
የመንፈስ መብራት(2)ሃሌ ሉያ
ተዋሕዶ(2)መለኮት
ንጽህት እምነት(2)ሃሌ ሉያ
በአንቺ ቢያምኑ(2)ቅዱሳን
ድልነሱ ሰይጣንን(2)ሃሌ ሉያ
በአንቺ ቢያምኑ(2)ሰማዕታት
ተፈተኑ በእሳት(2)ሃሌ ሉያ
እንደ ወርቅ(2)ተፈትለው
አበራ ገድላቸው(2)ሃሌ ሉያ
እንኑር (2) በእመነታችን
በተዋህዶ መክበሪያችን(2)ሀሌሉያ
👉 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ አቤቱ_የሆነብንን ✞
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
ቅኔ ማህሌቱ በደምህ ረሰረሰ
መቅደስ ተቃጥሎ መሰውያዉ ፈረሰ
ጮሁ ደናግላን ደም እንባ አለቀሱ
በቅድሱ ስፍራ ታርዷልና ቄሱ
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
ሰላም መስሎን ነበር መዉጣት መግባታችን
ለካስ በሾህ ታጥሯል ዙርያው ጎዳናችን
የፅዮን መንገዶች በዕንባ ተሞልተዋል
የሚያምሩት ግንቦችዋ በሌሊት ፈርሰዋል
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
የቁጣህን በትር ማን ይቋቋመዋል
የኃይልህን ጽናት ማንስ ይችለዋል
የሽማግሌው ፊት አልታፈረምና
ከፊት ቀና እንበል እንዴት እንፅናና
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
እንደ ዘካርያስ እንደ እግዚአብሔር ወዳጅ
ወደቁ ብዙዎች ገቡና ካንተ ደጅ
ህፃን አዛዎንቶች ጎበዦቹ ሁሉ
ተሰዉ ለፍቅር አንክድም እያሉ
አቤቱ የሆነብንን አስብ እግዚአብሔር(2)
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ጾመ_ሰብአ_ነነዌ
ይህ ጾም የነነዌ ሰዎች የጾሙት ሦስቱ ዕለታት ማለትም ሰኞ፣ ማክሰኞና ረቡዕ በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት የሚጾም ጾም ነው፡፡ በመባቻ ሐመር የጾሙ ወቅት ከፍና ዝቅ ይላል፤ ማለትም አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል፡፡
የነነዌ ከተማ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የተመሠረተችና ከጥንት ጀምሮ ጣዖት ይመለክባት የነበረች ጥንታዊት የአሶራውያን ዋና ከተማቸው ነች፡፡ በተጨማሪም በከተማዋ ጣዖት የሚያመልኩና እግዚአብሔርን የሚዘባበቱ ሕዝብና ነገሥታት ነበሩባት፡፡ (ለምሳሌ የንጉሥ ሰናክሬምና የእስራኤል ንጉሥ ሕዝቅያስን ታሪክ 2ኛ ነገ ምዕ 19 ያንብቡ)፡፡
ይህች ከተማ በዚህ ሁኔታ ቀጥላ በ770 ቅ/ል/ክ የሕዝቡ ኃጢአት ከፈጣሪ ሲደርስ እግዚአብሔር ‹‹ነነዌ በዚህ ሦስት ቀን ትገለበጣለች ብለህ ንገራቸው›› ብሎ ነቢዩ ዮናስን ላከው፡፡ ዮናስ ግን የዋህ ስለነበረ ‹‹አንተ መሐሪ አምላክ ነህና እኔ እናገራለሁ አንተም ትምራቸዋለህ በመጨረሻም እኔ ውሸተኛ እባላለሁና ስለዚህ ወደ ነነዌ ሔጄ አልሰብክም›› በማለት ወደ ተርሴስ ለመሔድ በመርከብ ተሳፈረ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በአውሎና በወጀብ መካከል መንገድ ያለው ፍጥረታቱም ሁሉ የሚታዘዙለት አምላክ መሆኑ ይታወቅ ዘንድ በባሕሩ ላይ ወጀብ አስነሳ፡፡ ዮናስ የተሳፈረበት መርከብም ታወከች፤ በመርከቢቱ የተሳፈሩ ሌሎች ተሳፋሪዎችም ‹‹ከእኛ መካከል በደለኛ ማን ነው?›› ሲባባሉ ዮናስ ግን በመርከቡ አንደኛው ክፍል ገብቶ ተኝቶ ነበር፡፡ እነርሱም ቀስቅሰው ማንነቱን ሲጠይቁት ‹‹እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን የማመልክ ሰው ነኝ፤ በእርሱ ላይ በማመጼ ይህ ሁሉ መከራ በእኔ ምክንያት አግኝቷችኋል፤ ስለዚህ እኔን ወደ ባሕር ጣሉኝ›› አላቸው፡፡ መርከበኞቹም እውነቱን ለማረጋገጥ እጣ ቢጣጣሉ በተከታታይ ሦስት ጊዜ በዮናስ ላይ ስለወጣ ዮናስን ከመርከባቸው አውጥተው በባሕር ላይ ጣሉት፡፡ ፍጥረታቱ ሁሉ ለእግዚአብሔር ይታዘዙለታልና ትልቅ ዓሣ ዮናስን ውጦ በባሕር ላይ እየተጓዘ በሦስተኛ ቀኑ በባሕር ወደብ ላይ በነበረች በነነዌ ከተማ ተፋው፡፡ ዮናስም ከዓሣው ሆድ ከወጣ በኋላ ስለከተማዋ በጠየቀ ጊዜ ነነዌ መሆኗን ነገሩት፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር በል እንዳለው ‹‹ይህች ከተማ በሦስት ቀን ትገለበጣለች›› ብሎ ሰበከ፤ (ሙሉ ታሪኩን ትንንቢተ ዮናስ አራቱንም ምዕራፎች ያንብቡ)፡፡
የነነዌ ሰዎች አስቀድሞ በሰናክሬምና በወታደሮቹ ላይ የደረሰውን ጥፋት እና ‹‹ኃይሌ ጉልበቴ አንተ ነህ›› ያለውን ሕዝቅያስን ከነሕዝቡ የመዳኑን ታሪክ ሰምተዋልና እግዚአብሔር ይቅርባይ መሐሪ መሆኑን አምነው ወደ እርሱ ተጠግተው ከአዋቂ እስከ ልጅ ከንጉሥ እስከ አገልጋይ ተስማምተው ጾምን አወጁ፤ በአንድ ልብ በአንድ መንፈስ ሆነውም አለቀሱ፡፡ እግዚአብሔርም መመለሳቸውን ተመልክቶ ይቅር አላቸው፡፡ ዮናስ ግን መደሰት ሲገባው በየዋህነቱ አዘነ፤ ቀድሞውኑ እኔ የተናገርኩት ሳይሆን ቢቀር ውሸተኛ እባላለሁ ብሎ ነበርና፤ (ዮና 4፥1)፡፡
ይህን ጾም የምንጾምበት ዐቢይ ምክንያት አብርሃም ሶርያዊ ሊቀ ጳጳስ የሠራው ሥርዓት በመሆኑ ነው፡፡ አብርሃም ሶርያዊ ከክርስቲያን ወገን የተወለደና አስቀድሞ ገንዘብ ያለው ነጋዴ ነበር፡፡ እየነገደም ምስር (ግብፅ) አገር ደርሶ በዚያው መኖር ጀመረ፡፡ ለድኆችና ለችግረኞች ርኅራኄን የሚያደርግ በመሆኑና በዚህም ብዙ ትሩፋቶቹ በመገለጣቸው የእስክንድርያ ኤጲስ-ቆጶሳት በፈቃደ እግዚአብሔር በእስክንድርያ ሊቀ-ጵጵስና ሾሙት፡፡ ከዚህ በኋላ ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች መጽውቶ የሊቀ-ጵጵስናውን ሥራ መሥራት ጀመረ፡፡ በሹመቱም ወራት ክፉ ልማድን ሁሉ አስወገደ፤ ኤጲስ-ቆጶሳቱንም ስለ ክህነት ሹመት መማለጃ እንዳይቀበሉ አወገዛቸው፤ ውግዘቱንም በሰሙ ጊዜ ሁሉም ፈርተው ክፉ ልማዳቸውን በመተው በደላቸውን ያስተሰርይላቸው ዘንድ ለመኑት፡፡
እግዚአብሔርን ከማይፈራ አንድ የንጉሥ ጸሐፊ ከሆነ ሰው በስተቀር ሁሉም ግዝቱን አክብረውታል፡፡ አብርሃም ግን ያን ክፉ ሰው ስለ ራሱ ድኅነት ብዙ ጊዜ ቢለምነውም ከክፋቱ አልተመለሰም፡፡ ጻድቁ አብርሃም ማስተማሩንና መገሠጹን ሳይሰለች ለሌሎች ዕንቅፋት እንዳይሆን ወደዚያ ክፉ ሰው ቤት ሄደ፤ ሆኖም ግን ይህ ክፉ ሰው የሊቀ-ጳጳሱን መምጣት በሰማ ጊዜ ደጁን ቢዘጋበትም አብርሃም ደጁን እያንኳኳ ለተወሰነ ሰዓት ቆመ፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹የዚህ ሰው ደም በራሱ ላይ ነው፤ እኔ ከደሙ ንጹሕ ነኝ›› ብሎ የእግሩን ትቢያ አራግፎ ተመለሰ፡፡ ያም ክፉ ሰው በክፉ አሟሟት ሞተ፡፡ ይህን የተመለከቱ ብዙዎችም ንስሐ ገብተዋል፤ (ስንክሳር ዘታኅሣሥ 6)፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በአብርሃም ሶርያዊ የሊቀ-ጵጵስና ዘመን ለምስር (ግብፅ) ንጉሥ የጭፍራ አለቃ የሆነ አንድ አይሁዳዊ ሰው ነበር፡፡ ለዚህም የጭፍራ አለቃ አብሮት ወደ ንጉሥ የሚገባ ሌላ አይሁዳዊ ወዳጅ ነበረው፡፡ ይህ አይሁዳዊ ከጭፍራ አለቃው ጋር ወዳጅ በመሆኑ ከንጉሥ ጋር ይነጋገራል፤ ከንጉሥ ዘንድ ባለሟልነትን ባገኘ ጊዜም ንጉሡን ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ ሊቀ-ጳጳሳት አባ አብርሃምን እንድታስመጣውና በፊትህ እንድከራከረው ተመኝቻለሁ›› አለው፡፡ ንጉሡም ልኮ አባ አብርሃምን አስመጣው፤ ከርሱም ጋር የእስሙናይን ኤጲስ-ቆጶስ አባ ሳዊሮስ ነበረ፡፡ ይህ አይሁዳዊም ከሊቀ-ጳጳሳቱ ጋር ተከራክሮ በመረታቱ ንጉሡ ሊቀ-ጳጳሳቱን አክብሮ በሰላም ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡ የጭፍራ አለቃውና አይሁዳዊ ወዳጁም አፈሩ፡፡ ሆኖም ግን ሊቀ-ጳጳሳቱንና የክርስቲያን ወገኖችን የሚያሸንፉበት ሌላ ነገር መሥራት ጀመሩ፡፡ በአንዲትም ቀን የጭፍራ አለቃው ወደ ንጉሡ ገብቶ ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ የማስረዳህ ነገር አለ፤ እነዚህ ክርስቲያኖች ሃይማኖት የላቸውም፤ ወንጌላቸው፡- የሰናፍጭ ቅንጣት ታህል ሃይማኖት ካላችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ተነቅለህ ወደዚያ ሂድ ብትሉት ይሄዳል የሚሳናችሁ የለም›› ይላልና አለው፡፡ ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ መጠየቅ ሽቶ ሊቀ ጳጳሱን ሲያገኘው ነገሩን ያጣዋል፤ ነገሩ ትዝ ሲለው ሊቀ ጳጳሱን ያጣዋል፡፡ ከዕለታት በአንዱ ግን እርሱ ባለበት ነገሩ ትዝ ይለውና ‹‹አባቴ የምጠይቅህ ኑሮኝ አንተን ሳገኝህ ነገሩን እየዘነጋሁት ነገሩ ትዝ ሲለኝ አንተን እያጣሁህ ቆየሁ፤ አሁን ግን ነገሩም ትዝ ብሎኛል አንተም መጥተሃል›› አለው፡፡ ከዚያም በወንጌል ‹‹የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህንን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም›› (ማቴ 17፥20 ፣ ማቴ 21፥21 ፣ ሉቃ 17፥6) ተብሎ ተጽፏል፤ ወንጌል እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃል ነው ብለህ የምታምን ከሆንህ ይህን ፈጽመህ አሳየን አሉት፡፡ አብርሃም ሶርያዊም ሦስት ቀን እንዲሰጡት ጠይቆ ሦስቱን ቀን በጾምና በጸሎት ወደ እግዚአብሔር ተማጸነ፤ ከዚያም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጣለት ጫማ ሰፊ ተብሎ የሚታወቀው ስምዖን ግብጻዊ ጋር እንዲሄድና ከእርሱ ጋር ሆነው አይሁድ ላቀረቡት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኙ ነገረችው፡፡ በመጨረሻም በሊቀ ጳጳሱ አስተባባሪነት፣ በስምዖን መሪነት፣ በምእመናን ጸሎትና በእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ 41 ኪራላይሶን አድርሰው ሰግደው ሲነሡ ተራራው ተነሣ፤ በውስጡም ተያዩ፡፡ ተራራውንም አፍልሰው በኢ-አማንያን ፊት ድንቅ ተአምር አሳይተዋል፡፡ ይህ ተአምር የተደረገበት ወቅት ደግሞ ጾመ ነቢያት ከመግባቱ በፊት ስለነበር የተደረገውም ተአምር ቤተ ክርስቲያን ዘወትር
✞ አንዲት ናት ✞
አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት(፪)
ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት
ቤተክርስቲያን አንዲት ናት
አዲስ አይደለንም ለመከራው ጉዞ
የወደቀ አናውቅም መስቀል ተመርኩዞ
አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ነውና
በርቱ ክርስቲያኖች በእውነት ጎዳና(፪)
/አዝ=====
የአበውን እምነት በአላውያን ፊት
ሰምተን ስላደግን ከገድላት አንደበት
መስዋዕትም ቀርቧል ከፊታችን
እውነት ስትገፋ አይችልም ልባችን(፪)
/አዝ=====
አልጠፋችምና በእሳት ተፈትና
ይህን እናውቃለን በገሀድ ነውና
መሰደድ መቃጠል ሁሉም ከጊዜው ነው
ለእውነት ከሆነ ሞትም ክብራችን ነው(፪)
/አዝ=====
ከተዋሕዶ ጋር ስላለ መንፈሱ
እውነትን ለማጥፋት መቅደስ አታፍርሱ
በግፍ ቢገደሉም ክርስቲያኖች ሁሉ
ኦርቶዶክስ አትጠፋም ተነግሯል በቃሉ(፪)
/አዝ=====
ታሪክን ያኖረች ፊደላትን ቀርጻ
ቅርስን ያወረሰች ገዳማት አንጻ
እንግዳ ተቀባይ መንፈሳዊት እናት
ይህንን አትዘንጉ ኦርቶዶስ አገር ናት
ይህንን አትዘንጉ ተዋሕዶ አገር ናት
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
❖ @enamsgn @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✞ የተክለሃይማኖት ፍቅሩ ✞
የተክለሃይማኖት ፍቅሩ አደረብኝ /2/
ገድሉ ታምራቱን እያሳየኝ
አባ ተክለሃይማኖት ስምህ ገናና ነው
አባ ተክለሃይማኖት በገድል በትሩፋት
አባ ተክለሃይማኖት አጋንንት ይርዳል
አባ ተክለሃይማኖት በተጠራህበት
አባ ተክለሃይማኖት መመኪያ ሆነሃል
አባ ተክለሃይማኖት የእኛ አማላጅ
አባ ተክለሃይማኖት እናከብርሃለን
አባ ተክለሃይማኖት ልጆችህ በአዋጅ
/አዝ=====
አባ ተክለሃይማኖት መብረቅም ፀሐይም
አባ ተክለሃይማኖት ቢሆኑ አይመስሉህም
አባ ተክለሃይማኖት ክብርህን ከፍ አድርጓል
አባ ተክለሃይማኖት ጌታ መድኃኔዓለም
አባ ተክለሃይማኖት እኔስ አባት አለኝ
አባ ተክለሃይማኖት ተክለሃይማኖት
አባ ተክለሃይማኖት ብደክም የሚያነሳኝ
አባ ተክለሃይማኖት ከወደኩበት
/አዝ=====
አባ ተክለሃይማኖት እጨጌ ፊሊጶስ
አባ ተክለሃይማኖት መንበርህን ተክቶ
አባ ተክለሃይማኖት ከአንተ የተማረውን
አባ ተክለሃይማኖት አይተናል አስፋፍቶ
አባ ተክለሃይማኖት ድንቅ ነገር አየው
አባ ተክለሃይማኖት ደብረ ሊባኖስ
አባ ተክለሃይማኖት እርጥብ እንጨት ነዶ
አባ ተክለሃይማኖት ደዌ ሲፈውስ
👉 ዘማሪት አዜብ ከበደ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ከንቱ_ነኝ ✞
ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱነኝ
ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ
ተስፋ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ
አምላኬ ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ
እኔ ንጉሥ ነበርኩ በክብር ያጌጥኩኝ
ሁሉን በምድር ላይ በጥበብ ፈጸምኩኝ
የዚህ ዓለም ደስታ ምንም አላዋጣኝ
በመጨረሻውም በሞት ተወሰድኩኝ (2)
/አዝ=====
ከጣይቱ በታች አዲስ ነገር የለም
ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም
ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ
ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ (2)
/አዝ=====
ከኔ አስቀድመው የከበሩ ሁሉ
አፈር ተጭኗቸው በመቃብር አሉ
እብደትና እውቀት ሁሉን አወኳቸው
ምንም ቋሚ የለም ሁሉም ከንቱ ናቸው (2)
/አዝ=====
ልቤን የጣልኩበት ተስፋ ያደረኩት
አልጨበጥ ብሎኝ አለሁኝ ስታክት
የጥበብም ብዛት ለትካዜ ሰጠኝ
እኔ በዚህ ምድር ጐስቋላ ፍጥረት ነኝ (2)
/አዝ=====
ልቤንም ፈተንኩት በደስታ ብዛት
የዚህን ዓለም ለውጥ ጣሙን አቀመስኩት
ሳቅም በልቤ ውስጥ ይፍለቀለቅ ነበር
ሁሉም ከንቱ ሆነ ገብቶ ከመቃብር (2)
👉 ሊቀ_መዘምራን_ይልማ_ኃይሉ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#ለምን_አስተርእዮ_ማርያም_ተባለ?
በዓለ አስተርእዮ (አስተርእዮ ማርያም) የተባለበት ዐቢይ ምክንያት እግዚአብሔር ወልድ በተነገረው ትንቢት በተቆጠረው ሱባኤ መሠረት ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ፣ ረቂቁ ገዝፎ፣ የማይታየው ታይቶ፣ የማይዳሰሰው ተዳስሶና በዮርዳኖስ ወንዝ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ተጠምቆ የሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ኅቡዕ ምሥጢር በተገለጠበትና በታየበት ዘመን ዘመነ አስተርእዮ ውስጥ የእናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዕረፍትዋ በዓል ስለሚከበር ነው፡፡
የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ እናትነት፣ በረከትና ቃል ኪዳን አይለየን፡፡ አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ ስንክሳር ዘጥር 21 ፣ ነገረ ማርያም
✞ አማላጅ የምትሆኚ ✞
አማላጅ የምትሆኚ በእውነት ለሰው ወገን
ንጽሕት ድንግል ማርያም የወለድሽው አምላክን
አስታራቂያችን ሆነሽ እኛን ታስቢን ዘንድ
በእግዚአብሔር ዘንድ ቁሚልን ስላለሽ መወደድ
ፈጣን ነው ያንቺ ምልጃ ግዳጅን የሚፈጽም
አንገትን አያስቀልስ ፊትን አያስመልስም
የባሕሪያችን መመኪያ ወደ አንቺ እንጮሃለን
ኦ ምለዕተጸጋ ሰላም ለኪ ብለን
/አዝ=====
በእውነት ያስገኘሽው የጽድቁን ብርሃን
እርሱም እናት አድርጎ ለኛ ሰጠን አንቺን
የመመኪያችን ዘውድ የድኀንነት መሰረት
የሀጥአን ተስፋችን ድንግል ምዕራገ ጸሎት
/አዝ=====
ንግስት የምትሆኚ የአምላክ እናት ማርያም
የተዘጋችው ደጃፍ ህትምት ለዘለዓለም
በግንባራችን ወድቀን ማለልን ካንቺ ፊት
ያስተሰርይልን ዘንድ የእኛን ሀጢአት
/አዝ=====
ዘወትር የምንለምንሽ ደኀንነትና ክብር
መማፀኛ ከተማ ሀገረ እግዚአብሔር
በንጽሕና የተጻፍሽ የእርቃችን ሰነድ ነሽ
ከአፋችን የማትጠፊ በልባችን የታተምሽ
👉 ዘማሪ ዲያቆን ሄኖክ ሞገስ
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
🕯 #ሕፃኑ_ቅዱስ_ቂርቆስ
ቂርቆስ ማለት ቀለም ማለት ሲሆን አባቱ ቆዝሞስ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ፡፡ ኢየሉጣ ማለት ምልእተ ሃይማኖት ማለት ሲሆን ሀገሯ ሮም ነው፡፡ እለእስክንድሮስ በነገሠ ጊዜ በሃይማኖት ምክንያት በምእመናን ላይ ስደት ደረሰባቸው፤ ኢየሉጣም የሦስት ዓመት ሕፃኑን ቂርቆስን ይዛ ከሮም ወደ ጠርሴስ ተሰደደች፡፡ ንጉሡ ክርስቲያኖችን እያደነ ወደ ሸሹበት ሀገር ደርሶ አገኛቸው፤ ቅድስት ኢየሉጣንም ይዞ ‹‹ሀገርሽ የት ነው? ስምሽ ማን ይባላል? ወገንሽ ማን ነው?›› ብሎ ጠየቃት፡፡ እርሷም ‹‹ስሜ ክርስቲያን ሀገሬ ሮም ነው፤ ከአንተ ሸሽቼ ብመጣ አገኘኸኝን?›› አለችው፡፡ መኰንኑም መልሶ ‹‹ለጣዖት ስገጂ ስምሽን ግለጪ እንዳትሞቺ›› አላት፤ እርሷም ‹‹ሞት የሚሽረው ስሜ ኢየሉጣ ነው›› አለችው፡፡ ‹‹ለአማልክት መሥዋዕት አቅርቢ›› ብሎ ባዘዛት ጊዜ እርሷ ‹‹እውነትን ማወቅ ከፈለክ ወደ መንደር ልከህ የሦስት ዓመት ሕፃን አስመጣና የምናመልከውን እርሱ ይንገረን›› አለችው፡፡
ንጉሡም ወታደሮችን አስልኮ ቂርቆስን አመጡለት፤ ከዚያም ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስን ከሐዲው መኰንን ይዞ ‹‹ስምህ ማነው?›› ብሎ በጠየቀው ጊዜ ‹‹ከንጹሕ ምንጭ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው እናቴ የሰየመችኝ ሞክሼ ስም ቂርቆስ ነው›› በማለት መለሰለት፡፡ መኰንኑም ‹‹ስታድግ ሹመት ሽልማት እሰጥሀለሁ በወርቅ በብር አከብርሃለሁና ለአማልክት ስገድ ክርስቶስን ካድ›› ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን ‹‹የሰይጣን ወዳጅ ለእውነትም ጠላቷ የሆንክ ከእኔ ራቅ›› አለው፡፡ በዚህም መኰንኑ ተቆጥቶ መከራ አበዛበት፤እንደገናም በእናቱና በእርሱ አፍንጫ ጨውና ሰናፍጭ አስጨመረባቸው፡፡ ሕፃኑ ግን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ስለጠነከረ ‹‹ነገርኽ ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ሆነ፤ ከማርና ከስኳርም ለአፌ ጣመኝ›› እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡ መኰንኑ በዚህ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ የብረት ችንካሮችን እንዲሰኩባቸው አደረገ፤ ሆኖም ግን በጌታችን ፈቃድ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ጉዳት አላደረሰባቸውም፡፡
ከዚያም ወደ ወህኒ ቤት ወሰዷቸው፤ በኋላም በደረቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ስቃያቸውን አራቀላቸው፡፡ የሕፃኑ ምላስ እንዲቆረጥ አዝዞ ቢያስቆርጠውም ክብር ይግባውና ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ ከዚያም በታላቅ ጋን ውኃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውኃ ድምጽ የተነሳ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ አገኛት፤ ሕፃኑም ‹‹እናቴ ጨክኚ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል›› እያለ ወደ ፈጣሪው ጸልዮላት ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ ቅዱስ ገብርኤል ውኃውን አቀዝቅዞ አውጥቷቸዋል፤ ይህም የሆነው ሐምሌ 19 ቀን ነው፡፡
በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚቀዳጅበት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾለት ስሙን ለሚጠራ ሁሉ ቃል ኪዳን ሰጥቶት ጥር 15 ቀን ከእናቱ ጋራ አንገቱን ተቆርጦ የሰማዕትነትን ክብር ተቀዳጅተዋል፡፡ በዚህ ዕለትም ብዙ የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበርተኞች በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ የሰማዕታቱ በረከት ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፦ መድበለ ታሪክ ፣ ስንክሳር ዘጥር 15
እጅግ አሳዛኝ ዜና!
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የምስካየኅዙናን መድኃኒአለም ገዳም የበላይ ጠባቂ በዛሬው ዕለት እራሳቸውን ፓትሪያርክ በማድረግ 25 ኤጲስ ቆጶሳትን ሾመዋል!!!
በዛሬው ዕለት በወሊሶ መድኃኒአለም ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እራሳቸውን ፓትሪያርክ በማድረግ ለስልጣን ጥማት ያደረባቸውን 25 ኤጲስ ቆጶሳት አድርገው ሾመዋል።
ከአንድ የቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የማይጠበቅ እና ህገ ቤተክርስቲያንን የሚፃረር ድርጊት ይፈፅማሉ ብለን የማንጠብቃቸው አቡነ ሳዊሮስ ይሄንን አድርገዋል።
ቤተክርስቲያኒቷ በራሷ ስርዓት እና ህግ የምትገዛ ሆኖም ሲኖዶሳዊት የሆነችውን ይቺ ሀገር የሆነችውን ቤተክርስቲያን ብትንትኗን ለማውጣት ይሄን ያህል መንገድ መራመዳቸው እጅግ የሚያሳዝን ተግባር ነው።
በአስቸኳይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለምመናኗ መፍትሔ ሊሰጥ እንደሚገባ በታላቅ ትህትና እንጠይቃለን ።
✞ መርዓዊ ሰማያዊ ✞
መርዓዊ ሰማያዊ/2/
ለእመ ገብረበዓለ/2/እኸ/3/
ይኑሩ በሰላም/3/ጸንተው በዚህዓለም
ደናግል ተነሱ ያዙ መብራህቱን
ሙሽራው ደረሰ አጒል እንዳንሆን
/አዝ=====
ወንጌል ይዘዋል ጎዳናቸው ያምራል
አለማው መልካም ነው እርሱን እንምሰል
/አዝ=====
የድካም ዋጋቸው /2/
ብርሃኑ ያበራል ለተከታያቸው
/አዝ=====
የሙሽራው ሕይወት መልካም እንዲሆን
ካህኑ ይባርኩት ብሩክ ሰው ይሁን
/አዝ=====
የሙሽሪት ሕይወት መልካም እንዲሆን
ካህኑ ይባርኳት ብሩክት ትሁን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ ቃና ዘገሊላ ✞
ቃና ዘገሊላ (፪)
በዚያ በሠርግ ቤት ተገኝተሻል ድንግል
ከልጅሽ ጋራ ተገኝተሃል ጌታ ከእናትህ ጋራ
እድምተኞች ሞልተው የተጋበዙት
ሲበሉ ሲጠጡ ወይኑ አልቆበት
ድንግል እናታችን ቤዛዊተ ዓለም
አንች ደረስሽለት ሆንሽው አማላጅ
/አዝ=====
አንተ እያለህስ ማፈር የለባቸው
ሁሉ ይቻልሃል ወይኑን ሙላላቸው
ማድጋው ባዶ ነው ብለሽ የተናገርሽ
ጌታን ያሳሰብሽው እመቤታችን ነሽ
/አዝ=====
የጌታን አምላክነት የተገለፀበት
ምንኛ ታደለ የነዶኪማስ ቤት
ዛሬም ይሄው በሰርገኞቹቤት
በረከት ፈሰሰ በአምላክ ቸርነት
/አዝ=====
ውሃው ተለውጦ ወይን ጠጅ ሲሆን
በቃና ዘገሊላ ሁላችን አየን
እግዚአብሔር ከኖረ በመካከላችን
ሁሌ ይሰጠናል ይህን መሰል ወይን
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
✞ በቃና ዘገሊላ ✞
በቃና ዘገሊላ(፪)
ዘገሊላ ከብካብ ኮነ (፪)
ዘምስለ እሙ እግዚእ ክርስቶስ
ተአምረ ኮነ ቤተ ዶኪማስ
በውስተ ቃና ተጋብዑ ሕዝብ
አመ ተጸውዐ በውስተ ከብካብ
/አዝ=====
ጌታ ክርስቶስ ከእናቱ ጋራ
በቃና መንደር ሰርግ ተጠራ
እድምተኞቹ በሞሉበት
ተአምራት ሆነ ዶኪማስ ቤት
/አዝ=====
ርእያ ድንግል ተጽዕቆቱ
ወአእሚራ ኀዘነ ልቡ
ሰአለት ሎቱ ለፍቁር ወልዳ
እንተ ሐልቀ ወይን ምልዓ ብሂላ
/አዝ=====
የዶኪማስን ጭንቀቱን አይታ
የልቡን ኀዘን ድንግል ተረድታ
ማለደችለት ልጄ ሆይ ብላ
ያለቀው ወይን እንዲመላ
/አዝ=====
በድንግል ምልጃ እናትነት
ቤቱ ተመላ ፍጹም በረከት
የማያልቅበት በረከት ጸጋ
ንጉሥ ስላለ አልፋ ኦሜጋ
/አዝ=====
የጌታ ተአምር የታየበት
ያለቀው ወይን የመላበት
ቤተ ዶኪማስ መልካም ሰርግ ሆነ
በአምላክ ቸርነት ተከናወነ
መዝሙር
ርዕሰ አድባራት ቅድስተ ማርያም
የፍቅር ሕብረት ሰ/ት/ቤት
#Share and #join ያድርጉ፤ ያስደርጉ።
╔ ✞ ═════●◉❖◉●═════✞╗
✢ ✥
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @enamsgn @mezmuredawit ❖
❖ @mezmuredawit @enamsgn ❖
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
✥ ✢
╚✞ ═════●◉❖◉●═════✞╝
✍ ወድሰኒ
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ