ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot
የማይረቡ የቲክ ቶክ ቀልዶችን በመመልከት ፤በጅንጀና ጫት በመቃም በቀልድና በጫወታ የእንቅልፍ ጊዜያችንን በማሳለፍ ሱብሒ ሶላት ላይ የምንቀልድ ሰዎች እንጠንቀቅ!!!እላለሁኝ
Читать полностью…•ወዱእ ያለው መስሎት ያለ ውዱእ የሰገደ ሰው ሶላቱን እንደገና መስገድ አለበት። ያለ ውዱእ ሶላት የለምና። ያስታወሰው ወቅት ካለፈ ቢሆን እንኳ ሶላቱን መመለስ አለበት።
ኢማሙ ረስቶ ያለ ውዱእ ካሰገደስ? የተከታዮቹ ሶላት ይበላሻል?
* ሶላቱ ሳይጠናቅቅ ካስታወሰ መቀጠል የለበትም። ይልቁንም ሌላ ሰው ተክቶ ይወጣል። የተተካው ሰው ከመጀመሪያ መጀመር ሳይጠበቅበት የቀረውን ያሰግዳል።
* ኢማሙ ውዱእ እንዳልነበረው ያስታወሰው ሶላቱን ካጠናቀቀ በኋላ ከሆነ ግን የተከታዮቹ ሶላት ትክክል ስለሆነ መመለስ (ዳግም መስገድ) አይጠበቅባቸውም። ይህንን የኢብኑ ዑሠይሚን ፈትዋ ማየት ትችላላችሁ። https://binothaimeen.net/content/7883
•ኹፍ ወይም ካልሲ በጦሀራ የለበሰ መስሎት አብሶ የሰገደ ሰው ኋላ ላይ በጦሀራ ሆኖ እንዳልለበሰው ካስታወሰ ውዱኡንም ሶላቱንም መመለስ አለበት። ማለትም እንደገና ውዱእ አድርጎ መስገድ ይኖርበታል።
እንዴት - በአላህ ለመካድ እንኳን አደረሳችሁ - ይባላል?!
—————
አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ እያለ:-
قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ ۞ اللَّهُ الصَّمَدُ ۞ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ ۞ وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ
«በል፣ እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፤ አልተወለደምም። ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም፡፡» አል-ኢኽላስ 1-4
➣ በዓለማቱ ጌታ በብቸኛው አምላክ አላህ ክዶ። "አልወለድኩም አልተወለድኩምም" እያለ፣ እርሱም በብቸኝነት እንዲመለክ ጥሪ የሚያደርጉ መልእክተኞችን ልኮ፣ ከመልእክተኞችም ውስጥ የላከውን መልእክተኛ ነቢዩ ዒሳን (ዐለይሂ ሰላም) "አምላክ ነው፣ ጌታ ነው፣ ለእኛ ብሎ ተሰቀለ…" ብለው የሚያመልኩ አካላትን አዕምሮ ያለው ስለ እስልምናው የሚያውቅ ሙስሊም እንዴት ለዚህ ክህደታቸው "እንኳን አደረሳችሁ" ይላል?!።
📩 የደረሰው ላልደረሰው ያድርስ!! ለየትኛውም የከሀዲዎች በዓላቶቻቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት በእስልምና ሀይማኖት የማይፈቀድ በጥብቅ የተከለከለ (ሀራም) የሆነ ከባድ ወንጀል ነው!!
➣ ልብ በሉ! ለምሳሌ:- አንድ የሰውን ህይወት ያጠፋ ሰው "እንኳን ለዚህ አበቃህ (አደረሰህ)" ተብሎ የደስታ መግለጫ እማይደረግለት ከሆነ፣ ከዚህ የከፋውን ተግባር በመፈፀም በአለማቱ ጌታ በብቸኛው አምላክ አላህ ክዶ እንኳን በፈጣሪህ ክደህ ያሻህን ልታመልክ፣ ለጣዖት፣ ለፍጡራን ልታጎበደድና ልትሳል፣ ያሻህን እርም የተደረጉ ተግባራትን ሁሉ ልትሰራ፣ ልትሰክርና ልትጠጣ፣ ልታመነዝር፣ አደረሰህ ይባላልን?! በፍፁም!! እስልምና አጥብቆ ያወገዘው ተግባር ነው!!
➣ በበዓላቸው ልጆች እንዳይቦዝኑብኝ ብሎ ማረድም ሆነ ሌሎችን ከነሱ የሚያመሳስል ነገር መስራት አይፈቀድም!! የሙስሊም ልጆችን የራሳችን የሙስሊም በዓል አለን ብሎ ማስተማር ነው!!
➣ እነሱ ለበዓላቸው የሰሩትን ቅመሱ ብለው አምጥተው ቢሰጡ ተቀብሎ መብላትም አይፈቀደም!!
➣ እነሱ ለራሳቸው ጊዜ ጥግ የደረሱ አክራሪዎች ሆነው የነሱን እምነትና ባህል የኛም እምነትና ባህል እንዲሆን ይተጋሉ!። እነሱ "የእኛ እምነትና በእምነታቸው የተመሰረተ ባህላቸውን ለምን የበላይ አልሆነ" ብለው ነው ሀገር የሚበጠብጡት። እኛን ደግሞ የራሳችን በሁሉ ነገር ላይ የእራሱ መለኮታዊ ህገ-ደንብ ያለው ድንቅ ሀይማኖት አለን ብለን ቆፍጠን ስንል "አክራሪ፣ ፀረ አንድነት፣ ፀረ ሰላም፣ ፀረ መቻቻል… ፀረ ፀረ ፀረ…" ይሉናል።
➣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሀይማኖቱን እሴት አክብሮ ሊኖር ይገበዋል። ከከሀዲዎች ጋር የጋራ በዓልም ሆነ እምነት የለንም!!። ለኛ የራሳችን እምነትና በዓል አለን!!። የምናደምቀው የራሳችን እምነትና በዓል ነው። በነሱ በዓል ጊዜ ሙስሊሙ አብሮ ግርግር እንዲፈጥር የሚያደርገው ነገር የለም።
አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-
قُلْ يَا أَيُّهَا الْكَافِرُونَ لَا أَعْبُدُ مَا تَعْبُدُونَ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ وَلَا أَنَا عَابِدٌ مَّا عَبَدتُّمْ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ لَكُمْ دِينُكُمْ وَلِيَ دِينِ
«በላቸው፣ እናንተ ከሓዲዎች ሆይ! "ያንን የምትግገዙትን አልግገዛም፡፡ እናንተም እኔ የምግገዛውን ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡ እኔም ያንን የተገዛችሁትን ተገዢ አይደለሁም፡፡ እናንተም እኔ የምግገዛውን (አሁን) ተገዢዎች አይደላችሁም፡፡ ለእናንተ ሃይማኖታችሁ አልላችሁ፡፡ ለእኔም ሃይማኖቴ አለኝ!፡፡» አል-ካፊሩን 1-6
➣ ይሄው ነው! እስልምናችን መጨመላለቅንና አጎብዳጅነትን አላስተማረንም!! ሀይማኖትህን ለማስከበር ቀድመህ አንተው መርሆዎቹን አክብር!!።
👉 በተለያዩ ቃላት ሊያጃጅልህ ሲሞክር መጃጃልህን ትተህ አትተሻሽ "አይ! እምነቴ አይፈቅድልኝም!።" በለው።
ይህን ጉዳይ የሚመለከቱ የቁርኣንና የሀዲስ ማስረጃዎችን እንዲሁም የታላላቅ ሊቃውንቶችን ንግግር በርካታ ከመሆናቸውም ጋር ከጊዜ ጥበትና ፅሁፉ እንዳይረዝም፣ ብዙዎች ዘንድ በከፊሉም ቢሆን የሚታወቅ ከመሆኑም አኳያ አልጠቀስኩም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
/channel/IbnShifa
/channel/IbnShifa
قال شيخ الإسلام ابن تيمية – رحمه الله – :
" القلب إذا ذاق طعم عبادة الله والإخلاص له لم يكن عنده شيء قط أحلى من ذلك ولا ألذ ولا أمتع ولا أطيب "
العبودية صـ ( ٩٠ )
🔷 ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላል : –
" ልብ አላህን የመገዛትና የኢኽላስን ጥፍጥና ከቀመሰ እሱ ዘንድ በጭራሽ ከሱ የበለጠ ጣፋጭ, በጥፍጥናው የሚረኩበት, እርካታ የሚያገኙበትና የተሻለ ነገር የለም " ።
/channel/bahruteka
⇛ በአሁኑ ሰዓት ስለ ዲኑ ጠንቅቆ የሚያውቀው በጣም አናሳ ነው፣ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ አብዘሃኛው ማለት በሚያስችል መልኩ ትንሽ ያውቃል ተብሎ ተስፋ የሚደረግበትም አላህ ያዘነለት ሲቀር የስሜቱ ተከታይ ነው። በስሜት ተከታይነት ሀራሙ እንደ ሀላል ተቆጥሯል። በስሜት ተከታይነት ሱንና ቢድዓ ይደረጋል፣ ቢድዓ ደግሞ በተቃራኒው እንደ ሱንና ይታያል። በስሜት ተከታይነት ሺርክ እንደ ተውሂድ የሚቆጠርበት ቦታም አለ… ሌላም ሌላም።
ይህንኑ የሚያበረታቱና ባለ በሌላ ሀይላቸው የሚያስፋፉ የሸይጧን ወዳጆች ደግሞ በዚያው ልክ በዝተዋል።
⇛ ልብ በይ እህቴ አንቺ የሕብረተ-ሰቡ መሰረት ነሽ፣ አንቺ ከተበላሸሽ ይህ ህብረተሰብ ይበላሻል፣ አንቺ ከተስተካከልሽ ህበረተሰቡም ይስተካከላል። አንቺን ለማጥመምና ከእምነትሽ ትእዛዝ እንድታፈነግጪ፣ ከተፈጥሮሽ ለማውጣት፣ ከሂጃብሽ ለማላቀቅ ከአላህና ከመልእክተኛው ﷺ ተከታይነት አስወጥተው የሸይጧንና የስሜትሽ ተከታይ ሆነሽ የጀሀነምን ገደል ገብተሽ ህብረተሰቡንም ወደ ጀሀነም ገደል እንድታስገቢ ሸይጧንና የሸይጧን ወዳጆች የሚያደርጉትን ጥረት አውቀሽ ለእነሱ አላማ የሚመቻቸውን አካሄድ እርግፍ አድርሽ ትተሽ፣ ወደ አላህ ተመልሰሽ ሒጃብሽን ጠብቀሽ፣ ስለ ዲንሽ ተምረሽ አውቀሽ፣ ተግብረሽ ምርጥ ትውልዶችን የጀነት ሙሹሮችን አፍሪ።
ይህቺ አለም እያየሻት ነው አጭርናትና ለዘላለማዊ አለም ጥሩ ስንቅ ሰንቂ። እህቴ ሆይ! ነገ ወደ ቀብርሽ ተሸፋፍነሽ ከመሄድሽ በፊት ስሜትሽን ትተሽ ሸሪዓው እንዳዘዘሽ አሁኑኑ ተሸፋፋኚ!!።
አላህ ከጀነት ሙሹሮች ያድርገንም ያድርግሽም!!
✍🏻 ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
/channel/IbnShifa
/channel/IbnShifa
እጅግ ድንቅ እና ብርቅ ፕሮግራም
╭─••°─═•°•═─••─╮
📩 ክ ፍ ል ❶ 📩 ╰─••°─═•°•═─••─╯
🎞 ፕሮግራሙ ስለ ውዱ ነብያችን ﷺ የህይወት ታሪክ ነው።
➲ አጠር ባለ አቀራረብ ማወቅ ያለብንን ጉዳይ ለማብራራት ተሞክሯል። ነብያችንን ﷺ መውደድ ግዴታችን ነው። ታሪካቸውን ማወቅ ደግሞ ከመውደድ ይቆጠራል።
የትምህርቱ አቅራቢ ⬇️
🎙 لفضيلة الشيخ عبدالحميد بن يس اللتمي -حفظه الله-
🎙 በሸይኽ ዓብዱልሐሚድ ያሲን አለ‐ለተሚይ አላህ ይጠብቃቸው!
♻️ አስፈላጊ በመሆኑ ለሌሎችም ያካፍሉ!!!
/channel/abdulham/1821
/channel/abdulham/1821
🎙የምሽት ምርጥ ቲላዋ…
🏷ግን እስኪ ስሙን ካወቃችሁት ንገሩኝማ በዚህች ክተቡልኝ⇙
@Abu_Sufiyan1_bot
"የመሲሕ ባሮች ሆይ 1 ጥያቄ አለን?
የ ኢማም ኢብኑል ቀይም መካሪ ግጥም"
የግጥሙ አማርኛ ትርጉም
✍ሙሐመድ አህመድ(ኢብኑ ሙነወር)
🎬ቅንብር ጦለሃ አህመድ
/channel/tolehaahmed
/channel/tolehaahmed
አሰላም አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ ። የተከበራችሁ ወንድም እና እህቶች እንዴት ናችሁ በያላችሁበት ሰላማችሁን አላህ ያብዛዉ ወላሂ ጤንነት ትልቅ የአላህ ፀጋ ነዉ። ረሱል (ሰዐወ) እንዲህ ብለዋል "ሁለት ፀጋዎችን ብዙ ሰዎች በአግባቡ አይጠቀሙባቸዉም።እነሱም ፦ጤንነትና ትርፍ ጊዜ" (ቡኻሪ ዘግበዉታል) ቶፊቅ ናስር እባላለሁ የምኖረው እዚሁ አዲስ አበባ ነው እናቴ በማህፀን ጫፍ ካንሰር (Cervical Cancer Stage 2) ታማብኝ እየተሰቃየች ትገኛለች በአሁኑ ሰዓት የበሽታው ተፅዕኖ ኩላሊቷን እያመማት ነው ለመንቀሳቀስ እንኳን አስቸግሯታል ስለዚህ ዉድ ወንድምና እህቶች እናቴን ማሳከሚያ ገንዘብ የአቅማችሁን ከታች ባለዉ አካዉንት ቁጥሬ ባማስገባት እንድትረዱኝ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ የከይር ጀዛችሁን አላህ ይክፈላችሁ። በተጨማሪ ከታች የህክምና ማስረጃ አያይዣለሁ ቶፊቅ ናስር ሙሳ 1000176587068 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ።
Читать полностью…ቀልብ ሲሞት
~
ጤነኛ አካል ሲቆስል ህመም አለው። ስቃይ አለው። የህመም ስሜቱ ደግሞ ጥቅም አለው። አፋጣኝ ምላሽ እንድትሰጥ ያደርግሃል። ባላሰብከው በኩል አካልህ እየነደደ ምንም ስሜት ባይኖርህ ተቃጥለህ ታልቅ ነበር። ባላየኸው አቅጣጫ ስለት እየወጋህ ስቃዩ ባይሰማህ ለሞት ይዳርግህ ነበር። ስለዚህ ህመም በራሱ ኒዕማ ነው። የህመም የስቃይ ስሜት ለደረሰብህ ጉዳት ህክምና እንድትፈልግም ያነሳሳሀል። ባይሆንማ "ቀላል ነው" እያልክ ትዘናጋ ነበር። ይህ የሚሆነው ታዲያ አካል ህያው ሲሆን ነው። አካላችን በድን ቢሆን ለሚደርስበት ጉዳት ምላሽ አይሰጥም። ህመም ስቃይ አይሰማውም። ሞቷላ! የሞተ አካል ምን ይሰማዋል?!
በርግጥ ማውራት የፈለግኩት ስለ አካላዊ ህመም አይደለም። ሰው ኒዕማነቱን ቢዘነጋም ስሜቱን አያጣውም። ይልቅ "ወንጀል በቀልባችን ላይ የሚያደርሰው ቁስለት ይሰማናል ወይ?" ማለት ነው የፈለግኩት። ወንጀል፣ በደል፣ ግፍ፣ ፈፅመን የሚሰማን የህመም ስሜት አለ? ወንጀልኮ ያቆስላል ወንድሞች! ታዲያስ! ያውም ቀልብን ነዋ! እና ቀልባችን በወንጀል ሲቆስል ይሰማናል ወይ? ያመናል ወይ? ስሜቱ፣ ህመሙ ከሌለ ቀልባችን ሞቷል ማለት ነው፤ አላህ ይድረስልንና። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"የቀልብ ሞት ምልክቱ በፀያፍ ወንጀሎች እየቆሰለ ህመሙ የማይሰማው መሆኑ ነው።"
[ኢጋሠቱ ለህፋን: 1/113]
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
☑️ አዲስ ምክር ለወጣቶች
👉ሞክሮ ያየው ሰው ምክር!!
🎙በአቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
/channel/Sadik_Ibnu_Heyru
🟢 የወስዋስ ፈውስ
🟢የፈትዋ ቁጥር 1⃣4⃣9⃣
🟢 ሁለት ወሳኝ ፈውሶች
👉በአላህ መጠበቅ
👉ለውስወሳው ቦታ አለመስጠት
🟢 ሸይጣን በወስዋስና ማስፈራሪያ ይረብሻል
መልስ
🔊አሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሳሊህ አልኡሰይሚን
በዚህ የፈታዋ ብቻ ቻናል⤵️
/channel/FATTAWAS
የፈትዋ ጥያቄ ለመጠየቅ⤵️
https://forms.gle/1iDs6V7JPMHREx4GA
እጅግ ድንቅ እና ብርቅ ፕሮግራም
╭─••°─═•°•═─••─╮
📩 ክ ፍ ል ❹ 📩 ╰─••°─═•°•═─••─╯
🎞 ፕሮግራሙ ስለ ውዱ ነብያችን ﷺ የህይወት ታሪክ ነው።
➲ አጠር ባለ አቀራረብ ማወቅ ያለብንን ጉዳይ ለማብራራት ተሞክሯል። ነብያችንን ﷺ መውደድ ግዴታችን ነው። ታሪካቸውን ማወቅ ደግሞ ከመውደድ ይቆጠራል።
የትምህርቱ አቅራቢ ⬇️
🎙 لفضيلة الشيخ عبدالحميد بن يس اللتمي -حفظه الله-
🎙 በሸይኽ ዓብዱልሐሚድ ያሲን አለ‐ለተሚይ አላህ ይጠብቃቸው!
♻️ አስፈላጊ በመሆኑ ለሌሎችም ያካፍሉ!!!
✅ ይ ቀ ጥ ላ ል
👇👇👇 ጆይን ብለው ይከታተሉ
https://t.me/joinchat/Sn62xstw8Nvq1swV
ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ
➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ
⚙ 📝 أَبُــو عَــمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕞❩
/channel/AbuImranAselefy
#ባል_ከሚስቱ_ጋር ስሜታዊ ጣዕምን ለመጠቃቀም ሲል ጡቷን በአፉ አስገብቶ ለአራት የተለያዩ ግዜያት ቢጠባው ሚስቱ ሃራም ትሆንበታለችን?
በሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ)
አንዲት እንስት የራሷ ያልሆነን ህፃን ልጅ በደንቡ መሰረት ካጠባች እናት እንደምትሆነው ይታወቃል። ባልስ የሚስቱን ጡት መላሱ ብሎም መጥባቱ እንዴት ይታያል? እንደሚታወቀው ሰዎች እርስ በርሳቸው በጥብቅ ከሚዛመዱባቸው ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው መዋለድ መሆኑን ኢስላም የሚያስተምር ሲሆን ቀጣዩ የዝምድና መንገድ ደግሞ ወላጅ እናት ያልሆነችን እንስት ጡቷን በመጥባት የሚገኝ ዝምድና መሆኑን አስምሮበታል። ይህም በህፃንነት የጡት መጥቢያ እድሜ ወቅት ከአምስትና ከዚያ በላይ ለሆነ የተለያዩ ግዜያት ወተት ያለው ጡቷን መጥባቱ መሆኑን ኢስላም በግልፅ ያሰፈረው ጉዳይ ነው። በዚህም ሰበብ ጡቷን ያጠባችው እንስት ለህፃኑ እናት ስለምትሆን ልጆቿም ወንድሞችና እህቶች ይሆኑታል። ሌላውም ዝምድና እንደየ ደረጃው ይቀጥላል። በውልደት ተዛምደው እንዳይጋቡ እንደሚከለከሉ ሁሉ ጡት በመጥባት የተዛመዱትም አንዳቸው አንዳቸውን እንዳያገቡ ይታገዳሉ።
ሌላው ርእስ በባልና ሚስት መሃል የሚፈጠረው እርካታ ሲሆን ከታላላቆቹ የጋብቻ ፋኢዳዎች አንዱና ዋነኛውም ይኸው አንዳቸው ባንዳቸው መርካታቸው፣ መደሰታቸውና ማረፋቸው ነው። ከዚያም ልጅ ማፍራትና ሌሎቹ ተከታይ ጥቅሞች ይሆናሉ። ይህንን የህይወት ማጣፈጫ እርካታ በተፈለገው መልኩ እንድንቋደስ ምንም ጉድለት የሌለበቱ ሸሪዓችን እንዳሻችን እንድንጠቃቀም መንገዱን ጠቁሞናል። ስርኣቱንም አስተምሮናል። በዚህም ዙርያ ከተወረዱት መረጃዎች አንፃር አንዳንድ ሊፈጠሩ የሚችሉ ብዥታዎችንም አስወግዷል።
ለምሳሌነትም ባዕድ የሆኑ ግለሰቦች ሸሪዓዊ ጋብቻን ከመሰረቱ በኋላ የራሱን ወይም የሚስቱን ወይም ለጋራ ስሜት ሲል ባል የሚስቱን ጡት ቢልስ ቢጠባ የሚከሰት ዝምድና ይኖራልን በሚል አንዳንድ ተማሪዎች ምሁራንን መጠየቃቸው አልቀረም። ከተጠያቂ ምሁራን መካከልም አል አል'ላማ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን የሚባሉ ታላቁ የክፍለ ዘመኑ ፈቂህ አንዱ ናቸው።(ረሂመሁላሁ ተዓላ) ለዚህም ቀጣዩ ጥያቄ ቀረበላቸውና ጥበባዊ ምላሻቸውን ለግሰዋል። “ባል ከሚስቱ ጋር ስሜታዊ ጣዕምን ለመጠቃቀም ሲል ጡቷን በኣፉ አስገብቶ ለአራት የተለያዩ ግዜያት ቢጠባው ሚስቱ ሃራም ትሆንበታለችን? ”
ምላሽ:- "ለአላህ ምስጋና ይገባውና ሃያሉ አምላካችን አላህ … ስሜታቸውን ለማርካት ሲል ባል በሚስቱ እንዳሻው እንዲጠቃቀም የተፈቀደ አድርጎላቸዋል። በምን መልኩ ሊገናኛት እንደሚገባው በተመለከተም ከእንከን ሁሉ ፅዱ የሆነው አምላካችን አላህ “ ሴቶቻችሁ ለናንተ እርሻዎቻችሁ ናቸውና እርሻዎቻችሁን እንዳሻችሁ እረሱት። ” ብሏል። ይሁንና “ እርሻዎቻችሁን እረሱት…።” የሚለውን ቃል ጠንቅቀህ ልትረዳው ይገባል። "እርሻ" የሚለው ቃል የቡቃያ መውጫና ዘር ማፍሪያ ቦታ ማለት ነው። እሱም የሴቷ ብልት ማለት ነው።
ለዚህም ባል ሚስቱን በብልቷ ብቻ በመገናኘት ሊያጣጥሙት ይገባል። በዚህም ሂደት ከፊት ለፊት በኩል ቢገናኛት፣ ከኋላዋ በኩል ቢገናኛት ወይም ቆማም ቢገናኛት እንዲሁም ተጋድማ ቢገናኛት ባጠቃላይ በየትኛውም አኳኋን ቢገናኛት መስፈርቱ በብልቷ በኩል መገናኘቱ ነው። እንዲሁም እንዳሻው ቢያቅፋት፣ ቢስማት፣ ቢተሻሻት ምንም የተገደበ ነገር የለውም። ነገር ግን በየወር አበባዋ ግዜ የሩካቤ ሥጋ ሊፈፅምባት አይገባውም። ልክ እንደዚያው በመቀመጫዋ በኩልም ሊገናኛት ሙሉ በሙሉ አይፈቀድለትም። መልእክተኛው(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሴቶቻችሁ እርሻዎቻችሁ ናቸውና እርሻዎቻችሁን እንዳሻችሁ እረሱት።” የሚለው የፈጣሪያችን የአላህ አዝዘ ወጀልለ መመሪያ ሲወርድና ለሰሃቦቹ ሲያብራሩት በቡኻሪ [8/154] ና በሙስሊም [4/156] ዘገባ “ብልት ውስጥ እስከ ሆነ ድረስ ከፊትለፊት ሆነ ከኋላ በኩል ተገናኟቸው።” ባሉት መሰረት እንዲሁም ኢብኑ ዐዲይ [1/211] ዘግበውት አል አልባኒይ በአዳቡ-ዝዚፋፍ [105] ላይ ሰሂህ ባሉት መሰረት “ሴቶቹን በመቀመጫዎቻቸው የሚገናኛቸው ሰው እርጉም ነው።” ብለዋልና በየትኛውም አቅጣጫና አኳሃን የዘር መግቢያና የልጅ መውጫ የሆነውን መንገድ (ብልትን) መገናኘት የተፈቀደ ነው። ይህ የትዳር መዘውርና በትዳር ውስጥ የሚከሰቱትን በርካታ ጉድለቶች በመሸፈን የሚያቻችለው የእርካታ ጥበብ ከዚህ ውጪ መንገድ የለውም። እርካታውም የጋራ መሆኑን ልብ ካልነው ከላይ የተነሳው ርእስ ለማረሻውም ሆነ ለእርሻው ግቡን መምታት ምን ያህል አጋዥና አስፈላጊ እንደሆነም በዚሁ አጋጣሚ እንገነዘባለን።
በዚህም መሰረት ይህ አጠቃላይ የሆነ መርህ ነውና አንድ ግለሰብ የሚስቱን ጡት በመላስ፣ በመጥባት ስሜቱን ቢያጣጥመው ምንም ችግር የለበትም። በዚህም ሰበብ (ልክ እንደ ህፃንነቱ ዘመን ሁኔታ) እርም አትሆንበትም። ጡቷን ሲጠባው (ፈሳሽ ኖሮት ቢስበው) እንኳ እርም አትሆንበትም። ይህ አንግዲህ የአብዛኞቹ ሊቃውንት (ጁምሁር አህሉል ዒልም) አቋም ነው።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጡት መጥባት ሰበብ አንዷ በአንዱ ላይ እርም የምትሆንበት መስፈርቱ ከጡት መጣያ ወቅት በፊት (እድሜው ሁለት አመት ከመሙላቱ በፊት) የሆነ እንደሆን ነው። ከጡት መጣል (ከጡት መጥቢያ ዘመን) በኋላ ከሆነ እርም አያደራርግም። ምንም አይነት ተፅዕኖም አይፈጥርም። ስለዚህም ጡት የመጥባት ደንቡ ህፃኑ አምስቴ እና ከዚያ በላይ ለሆነ ግዜ መጥባት ሲኖርበት ከአምስት ግዜ በታች ከሆነ በፍፁም ምንም አይነት ተፅዕኖ አይኖረውም። ይህ ክስተት ያለ ወተት የማይወስድ ህፃን ልጅ ሆኖ እንኳን ከአንዲት ሴት ለአራት ግዜያት ያህል ብቻ ቢጠባ በዚህ ሰበብ ልጇ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም አንዱን ባንዷ ላይ እርም የሚያደራርገው (ወንድምና እህት አደራርጎ ጋብቻ የሚያከላክለው) ለአምስት ግዜያት በመጥባት እንጂ ከዚያ በታች ከሆነ አይደለምና።»
የሸይኽ ሷሊህን መልእክት በቀጣዩ ማስፈንጠርያ ያድምጡት
↪ https://m.youtube.com/watch?v=pCzIaiqGoH0 2:40 min
Abufewzan
ሱጁድ-አስ'ሰህው መቼና እንዴት ይደረጋል?
🔅ሰላት ላይ ረስቶ ግዴታን ወይም መሰረትን የመተው፣ የመጨመር ወይም የመቀነስ ክፍተት ሲፈጠር መስተካከል ያለበትን -የፊቅህ ትምህርቶች ላይ በተብራራው መሰረት- ካስተካከሉ በኋላ ሱጁድ-አስ'ሰህው ማድረግ ዋጅብ/ ግዴታ ነው።
ነገር ግን የተረሳው የሰላት ክፍል የቃልም ይሁን የተግባር ሱንናህ ከሆነ ሱጁድ-አስ'ሰህው መውረዱ ግዴታ አይሆንም።
🔅በመሰረቱ ሱጁዱን ከማሰላመት በፊትም ይሁን ካሰላመቱ በኋላ ማድረግ እንደሚቻል ብዙሃኑ የፊቅህ ሊቃውንት ይስማማሉ።
ከማሰላመት በፊት ቢሆን ይሻላል፣ አይ ካሰላመቱ በኋላ ቢሆን ይመረጣል ወዘተ የሚባለው ሱንናህ እና በላጩን ከመግለጽ አንጻር ነው።
በዚህ መሰረት ብዙሃኑ የሐዲሥ ሊቃውንት ዘንድ ተመራጩ ሱጁድ-አስ'ሰህው የሚደረገው- ሰላቴ ላይ ጨምሬአለሁ ተብሎ ከሆነ ካሰላመቱ በኋላ፣ አጉድያለሁ ተብሎ ከሆነ ከማሰላመት በፊት፣ በመጠራጠር ከሆነ ጥርጣሬውን አስወግዶ እርግጠኛ የሆኑበትን አድርጎ ከሆነ ከማሰላመት በፊት፣ አመዛኙን ግምት በመከተል ከሆነ ካሰላመቱ በኋላ ማድረጉ ይመረጣል።
🔅ዋናው ቁም ነገር ተሸሁድ ከጨረሱ በኋላ የሰላት መረጨሻ ላይ ከማሰላመት በፊትም ይሁን በኋላ ተክቢር በማድረግ ክፍተት መሙያ፣ ጥርጣሬ ማስወገጃና ሸይጣንን ማናደጃ 2 ሱጁዶችን አድርጎ ማሰላመቱ ነው።
🔅እነዚህ ሱጁዶች ያለ ውዱእ አይሆኑም። ውዱእ የፈታ ሰው አድርጎ ተመልሶ ሱጁድ ማድረግ ይጠበቅበታል።
🔅ለየት ያለ ዚክርም የላቸውም፤ በየትኛውም ሱጁድ ላይ የሚባለው ዚክር ነው የሚደረገው።
🔅ሰላት ውስጥ የሚደረገው ሱጁድ ላይ የሚወደዱ ነገሮች ሁሉ ይህ ሱጁድ ላይም ይወደዳሉ/ይፈለጋሉ።
🔅ከሱጁድ-አስ'ሰህው በኋላ ተሸሁድ መቅራት አይጠበቅብንም፤ ይህም የብዙሃኑ የፊቅህ ሊቃውንት አቋም ነው፤ ጥቂቶች ማድረግ ይገባል የሚል አቋም ቢኖራቸውም ትክክለኛ የሐዲሥ ማስረጃ የለውም።
🔅ኢማም ሱጁድ ሲወርድ አብሮ መውረድ ግዴታ ነው፤ ነገርግን መእሙም ከኢማሙ ጋር እየሰገደ ውስጡ ላይ ለተፈጠረበት ጥርጣሬ ብሎ ሱጁድ-አስ'ሰህው ማድረግ አይችልም። መስቡቅ ከሆነ ግን በግሉ (ከኢማም ከተለየ በኋላ) ላጠፋው ጥፋት ሱጁድ ማድረግ ይችላል።
🔅ኢማሙ/አሰጋጁ ጥፋት አጥፍቶ ተከታዮች ሲጠቁሙት አስተካክሎ ግዴታ የሆነን ሱጁድ ማድረግ ከተወ ማእሙም/ተከታይ ሱጁድ የማድረግ ግዴታ ይኖርበታል።
🔅በአንድ ሰላት ውስጥ ተደጋጋሚና የተለያየ ክፍተት ቢፈጠር እንኳ መጨረሻ ላይ አንድ ሱጁድ-አስ'ሰውህ ብቻ ነው የሚደረገው።
🔅ከፍተኛና ተደጋጋሚ የመርሳት (የወስዋስ) ችግር ያለበት ሰው እርግጠኛ ላልሆነበት ክፍተትና መርሳት ሱጁድ አስ'ሰህው ማድረግ አይፈቀድለትም!።
ይህ ካልሆነ ሁሌም ሱጁድ አስ'ሰህው እያደረገና ሰላት ላይ እየጨመረ ነው የሚኖረው!።
🔅ሱጁድ አስ'ሰውህን የረሳ ሰው ባስታወሰበት ጊዜና ሰዓት መስፈርቱን አሟልቶ ማድረግ ይቻላል።
ከመስጂድ ከወጡ፣ ጊዜው ከረዘመ... አይሆንም የሚሉ አስተታየቶች በቂ ማስረጃ የላቸውም።
ሌላ ሰላት ውስጥ ከገባ በኋላ ከፊት ለሰገደው ሰላት ሱጁድ አስ-ሰህው ማድረግ አንደነበረበት ያስታወሰ ሰው የያዘውን ሰላት እንደጨረሰ ሱጁዱን ማድረግ ይችላል፤ ይህም ከአነስ ኢብኑ ማሊክ رضي الله عنه ተዘግቧል።
🔅ጊዜው/ ክፍተቱ በጣም ከረዘም ሰላቱ ሙሉ ቢደገም ይሻላል የሚል አቋም ያላቸው ሊቃውንት ስላሉ ይህን ማድረጉም የተሻለ ይሆናል።
🔅ለሱጁድ-አስ'ሰህው (ሲረሳ) ሌላ ተጨማሪ ሱጁድ አስ'ስህው አያስፈልግም።
📖📚 አል-አውሰጥ፣ አል-መጅሙዕ ሊን'ነወዊ፣ መጅሙዕ አል-ፈታዋ፣ አሽ'ሸርሑል ሙምቲዕ፣ ተስሂሉል-ፊቅህ።
ኮፒ
🟢 ከዒሻእ በኋላ መቆየት
አላህ ልቅና የተገባው አምላክ ፍጥረተ ዐለሙን ሙሉ በሆነ ጥበቡ ሲያስተናብር ለሁሉም የሚስማማውን ክንውን በመስጠት ነው ። ቀንን ፈጥሮ ለባሮቹ መከሰቢያና መንቀሳቀሻ አደረገው ። ለሊትን ፈጥሮ ለባሮቹ ቀን ሲተጋና ሲለፋ የዋለው አካልና አእምሯቸወ ማረፊያ አደረገው ። ይህን አስመልክቶ መለኮታዊ በሆነው ህያው ቃሉ እንዲህ ይላል : –
« وَهُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ اللَّيْلَ لِبَاسًا وَالنَّوْمَ سُبَاتًا وَجَعَلَ النَّهَارَ نُشُورًا »
الفرقان ( 47 )
« እርሱም ያ ለእናንተ ሌሊትን ልብስ እንቅልፍንም ማረፊያ ያደረገ ፤ ቀንንም መበተኛ ያደረገላችሁ ነው ፡፡
وَجَعَلْنَا اللَّيْلَ لِبَاسًا
النبأ ( 10)
ሌሊቱንም ልባስ አደረግን ፡፡
وَجَعَلْنَا النَّهَارَ مَعَاشًا
النبأ (11)
ቀኑንም (ለኑሮ) መስሪያ አደረግን ፡፡
ኢማሙ ቁርጡቢይ – ራሕመቱላሂ ዓለይሂ – ይህን የቁርኣን አንቀፅ አስመልክቶ እንዲህ ይላል :–
قال القرطبي – رحمه الله – :
" وقد قيل: إن الحكمة في كراهية الحديث بعدها أن الله تعالى جعل الليل سكناً ، أي يُسكن فيه ، فإذا تحدث الإنسان فيه فقد جعله كالنهار الذي هو متصرف المعاش ، فكأنه قصد إلى مخالفة حكمة الله تعالى التي أجرى عليها وجوده ".
تفسير القرطبي (12 / 138)
" ከዒሻእ በኋላ ንግግር የተጠላበት ምክንያት አላህ ለሊትን ማረፊያ ስላደረገው ሰው በሚናገርበት ጊዜ ልክ ለመኖር እንደሚቀሳቀስበት ቀን ስሊሚያደርገው ነው ። በዚህም የአላህን ያ ፍጥረተዐለሙን ያስገኘበትን ጥበብ እንደተቃረነ ይቆጠራል " ።
የአላህ መልእክተኛ ከዒሻህ በኋላ የነበራቸው ፈለግ ምን ይመስል እንደነበረ እናታችን ዓኢሻ ስትነግረን እንዲህ ትላለች : –
عن عَائِشَةَ – رضي الله عنها – قَالَتْ :
( مَا نَامَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَبْلَ الْعِشَاءِ ، وَلَا سَمَرَ بَعْدَهَا ) ·
رواه ابن ماجه (702) وصححه الألباني
" የአላህ መልእክተኛ ከዒሻእ በፊት ተኝተው አያዉቁም ። ከዒሻእ በኋላም አምሽተዉ አያውቁም "።
እንዲሁም አቡ በርዛህ የተባለ ሶሀብይ ባወራው ሐዲስ እንዲህ ይላል : –
عَنْ أَبِي بَرْزَةَ – رضي الله عنه – أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ – صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ –
" كَانَ يَكْرَهُ النَّوْمَ قَبْلَ الْعِشَاءِ ، وَالْحَدِيثَ بَعْدَهَا "
متفق عليه
" የአላህ መልእክተኛ ከዒሻእ በፊት እንቅልፍና ከዒሻእ በኋላ ንግግርን ይጠሉ ነበር "
እነዚህ መረጃዎችና በዚህ ዙሪያ የመጡ በርካታ ኑሱሶችን አስመልክቶ የኢስላም ሊቃውንቶች ለተለያዩ ሸሪዓዊ ጉዳዮችና ግዴታ ለሆኑ ነገርች ከዒሻእ በኋላ ንግግር ይፈቀዳል ያሉ ሲሆን ወሰን ባለፈና ሱና በሚመስል መልኩ ማዘውተሩ በምንም ሚዛን የማይደገፍ መሆኑ አያጠራጥርም ።
ምክንያቱም ከዒሻእ በኋላ ከሚገባው በላይ ማርፈድን ተከትሎ የሚመጡ በርካታ ጉዳቶች ስላሉ ።
ለምሳሌ :– የፍጅር ሶላትን አለመስገድ ወይም በእንቅልፍ ልብ በድብርት ላይ ሆኖ ምን እንደሚል ሳይውቅ መስገድ ። የእለት ከእለት ተግባሩ በትክክል እንዳያከናውንና የጠዋቱን ክ/ ጊዜ በእንቅልፍ ማሳለፍና የመሳሰሉ ኢማሙ ቁርጡብይ የጠቀሱት የአላህን ጥበብ የሚቃረኑ ነገሮች ላይ መውደቅን ይመስል ።
ከዚህ በመነሳት በአሁኑ ጊዜ እያየን ያለነው ለመስጂዶች ገቢ ማሰባሰቢያ እየተባለ በየጊዜው እየጨመረ የሚሄደው ግሩፕ ከፍቶ ሙሓደራ ከተደረገ በኋላ የገቢማሰባሰቢያ ቀጥሎ እስከ ፈጅር ድረስ መቆየት አግባብነት የሌለውና በተለይም ሱናን ተግባራዊ በማድረግ ግንባር ቀደም መሆን ካለባቸው ሰለፍዮች የማይጠበቅ ስለሆነ ከተቻለ ወደ ቀን መቀየር ካልሆነ በተወሰነ ጊዜ ርቀት ላጭር ጊዜ በማድረግና ቶሎ ዘግቶ ሰዎች ወደ እረፍታቸው እንዲሄዱና የለይል ሶላታቸውን እንዲሁም ፈጅርን በጀማዓ ሰግደው ስራቸውን በአግባቡ እንዲያከናውኑ እድል መስጠት አስፈላጊ ነው ።
በዚህ ፕሮግራም ላይ የምትሳተፉ መሻኢኾችና ኡስታዞች ይህ ነገር በጣም አየበዛና ሱና በሚመስል መልኩ እየተዛመተ ስለሆነ መስመር በማስያዝ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ አደራ እላለሁ ።
አላህ ሁላችንንም ሱና ላይ ኖረን በሱና ላይ የምንሞት ያድርገን ።
/channel/bahruteka
ቁርአንን በማስተንተን ማንበብ ፣
አይኖችን ካልተፈቀዱ ነገሮች ማቀብ ፣ የሌሊትን ሰላት መስገድ ፣
ምላስን ከሃሜትና ከረከሱ ርእሶች መጠበቅ ፣
የመቃብርን ቦታ መጎብኘት
እና
አኺራን ማስታወስ የልብን ድርቅና ለማከም ፍቱን መድሃኒቶች እንደሆኑ ዑለማእ ያወሳሉ
/channel/Muhammedsirage
لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ يُحْيِيْ وَيُمِيْتُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرُ. (10× بعد صلاة المغرب والصبح)
Читать полностью…قال الشيخ العلامة صالح الفوزان - حفظه الله -
إذا ضاعت المرأة ضاع البيت ،
وإذا ضاع البيت ضاع الأولاد ،
وإذا ضاعت البيوت ضاع المجتمع .
محاضرات في العقيدة والدعوة صـ ( 162 )
✅ ሸይኽ ፈውዛን – ሐፊዘሁሏሁ – እንዲህ ይላሉ : –
" ሴት ከተበላሸች ቤት ይበላሻል ,
ቤት ከተበላሸ ልጆች ይበላሻሉ,
ቤቶች ሲበላሹ ማህበረሰቡ ይበላሻል "።
/channel/bahruteka
እህቴ ሒጃቡን አንቺ እንደምትፈልጊው ሳይሆን ሸሪዓው እንደሚፈልገው ልበሺው!!
—————
⇛ ሒጃብ ለአላህና ለመልእክተኛው መታዘዝ እንጂ የሆነ ሀገር ባህል ተከታይነት አይደለም። አዎ! ይህን ርዕስ ልብ በይው አንዳንድ ሰዎች ልክ እንደ ከሀዲዎች ሚዲያን ሽፋን አድርገው በቦዲ ተወጣጥረው አለያም ካባ ለብሰው ጥምጣም ጠቅልለው አዋቂ መስለው "ይሄማ የእንዲህ ያለ ሀገር ባህል ነው" እያሉ የሚናገሩትን ሰምተሽ አትታለይ!። እነሱን በጭፍን መከተል አደጋው የከፋ ነውና ተጠንቅቀሽ ስለ ሒጃብሽ ጠንካራ ከሆኑ አስተማሪዎች ትክክለኛውን ሒጃብ አውቀሽ ሸሪዓው በሚፈልገው መልኩ ልበሺ!!።
ከላይ ስለ ሰዎች ሁለት አይነት ባህሪ ማስቀመጤንም ልብ በይው!፣ በሁለቱም መልክ ስላሉ ነውና ነቃ በይ!፣ ማንኛውም ሰው በአለባበሱና በአፈ ቀላጤነቱ እውነተኛ ሊባል አይችልም!!። እውነተኛነቱ በቁርኣንና በሀዲስ በሶሃቦች ግንዛቤ ተፈትሾ ሲያልፍ ብቻ ነው።
⇛ ሒጃብ ጥብቅነትና ንፅህና ነው። ሒጃብን የማትለብስና ከሂጃብ የተራቆተች እንስት ሁለት ነገሩዋ ቆሿል፣ አንዱ ንፁህ ቢሆን እንኳን አንዱ ንፁህ አይሆንም፣ አንደኛ ልቧ ቆሿል ሁለተኛ ሰውነቷን በተለያየ ወንጀል አቆሽሸዋለች፣ በተለያየ ሸሪዓው እርም ባደረጋቸው ነገሮች ሰውነቷን አጨማልቃው ሊሆን ይመቻል፣ የሚፀዳው ሒጃቧን ሸሪዓው በሚያዛት መልኩ ለብሳ፣ ክብሩዋን ጠብቃ ጥንቁቅ ሆና ወደ ጌታዋ ቁርጥ ያለን መመለስ ስትመለስ ነው!።
ልቧ ባይቆሽሽ አትራቆትም ነበር፣ ከሂጃብ መራቆቷ ራሱ የወንጀል መብዛት አንዱ ምልክት ነው። ሸይጧን ሴትን ልጅ ወንጀል እንድታበዛና እንድትሰራ ይገፋፋታል፣ ከዛ በኋላ ግን ከሂጃቧ እንድትገፈፍና ክብር እንዳይኖራት፣ በባለጌዎች እንድትደፈርና እንደ ቀላል እንድትታይ በማድረግ ለዝሙት ፈላጊ ባለጌዎች ምቹ ያደርጋታል። ሒጃቧን በአግባቡ የምትለብስ ሴት ግን ሁሉም ዘንድ ክብር አላት፣ ባለጌዎች ዘንድም ክብር አላት፣ እሷን ቀና ብለው እንኳን አያዩዋትም፣ መልካም ሰዎች ዘንድም ልዩ ክብር አላት።
⇛ ሒጃብ ኢማን ነው ኢማን ማለት:- በልብ ማመን በምላስ መናገር በአካል መተግበር ነው። አማኝ የሆነችዋ ሴት በሒጃብ ግዴታነት በልቧ ካመነች በአካሏም ትተገብረዋለች።
አንዳንዶች ካሉበት ሸሪዓን የሚቃረን ተግባር እንዲመለሱ ሲነገራቸው "ኢማን በልብ ነው ልቤን ከፍተህ አይተሃል?" እያሉ በውሸት ሲያስመስሉ ይስተዋላሉ።
ጥያቄ አለኝ ልባቹ ካመነበት ተግባራቹ ሊመሰክር ምን ከለከላችሁ?! ለአላህ ግን መዋሸት አይቻልም!፣ ለማንኛውም ኢማን ሶስት ክፍሎች አሉት ከነዛ ውስጥ ምንም ማጉደል አይቻልም፣ ታዲያ 3ኛው በአካል መተግበር ነውና ተግብሪ!፣ ሒጃብሽን ጠብቂ!! አንቺ ሒጃብ ብለሽ የምትጠሪውን አናትሽ ላይ የምትጠቀልይውን ብጣሽ ሻሽ ብጤ ጨርቅ ሳይሆን ኢስላም (ሸሪዓ) ሒጃብ ብሎ ያስቀመጠልሽን ሒጃብ ነው የምልሽ። አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ በማለት ያዘዘሽን ሒጃብ:-
يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ
«አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡» አህዛብ 59
⇛ ሒጃብ የሀፍረተ-ገላ መደበቂያ ነው። ሴት ልጅ ደግሞ መላ ሰውነቷ ሀፍረተ-ገላ ነውና መላ ሰውነቷን ልትሸፍነው ይገባታል!! የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሶሂህ ሀዲስ እንዲህ ብለዋል:- “ሴት ልጅ ሀፈረተገላ ናት፣ ከቤቷ በወጣች ጊዜ ሸይጧን (አሸላልሞ) ብቅ ብቅ ያደርጋታል።”
አንዳንድ (ፈቂህ መስለው ሙተፈቂሆች) ስለ ዲኑ ሳይገነዘቡ የተገነዘቡ የሚመስሉ በአንዳንድ ዑለማዎች ንግግር በማምታታት የግል ስሜታቸውን ለማሰራጨት የሚፈልጉ ሰዎች "አይ እጅና ፊት እንኳን ሱና ነው፣ ኪላፍ አለበት ምናምን…" የሚሉትን ተረታቸውን ትተሽ አንቺ ለአላህ ብለሽ ተቃራኒ ፆታዎችን ላለ መፈተንና ራስሽም ፈተናው ላይ እንዳትወድቂ ብለሽ መላ ሰውነትሽን ልትሸፍኚው ይገባል። ልብስሽን ጉልበትሽ ድረስ አሳጥረሽ ሀፍረተገላሽን ከፍተሽ ለሚወጣ ለሚወርደው አታሳይ!! ልብሱን እንዲያሳጥር የታዘዘው ወንዱ እንጂ አንቺ አይደለሽም!! አንቺማ ክንድ ሚያክል አስረዝመሽ ከመሬት እንድትጎትቺው ነው የታዘዝሺው።
⇛ ሒጃብ የአይናፋርነት (ሀያእ) ምልክት ነው። የሴት ልጅ ተፈጥሮ አይናፋርነት ነውና ተፈጥሮን ጥለሽ ሌላን ለመሆን መሞከር አደጋው የከፋ ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ "ሴት ሆና በወንድ የምትመሳሰልና ወንድ ሆኖ በሴት የሚመሳሰልን አላህ ረግሟዋቸዋል።" ብለዋል። ልብ በይ! እህቴ የአላህ እርግማን አለበት!፣ አንዳንድ ሴቶች አላህ ይምራቸውና ከአይናፋርነት አልፈው እንደ ወንድ ሱሪ ለብሰው የሚሄዱ አሉ። እነዚህ እጃቸው ላይ የነበረውን ብርቅዬ ኢስላማዊ የሴት ልጅ ስርኣትን አሽቀንጥረው በመጣል የባለጌዎችን ከተመሳሳይ ፆታ ጋር ጋብቻን መስራቾችን የምእራባዊያንን ስርኣት ናፋቂ ናቸው።
⇛ ሒጃብ መልካም የሆነች አማኝ ሴት ባህሪ ነው። አላህ ይጠብቅሽና እህቴ የዚህ ተቃራኒ መሆንሽ ምንኛ የከፋ ነው? መልሱን ቆም ብለሽ እንድትመልሺው ለአንቺው ተውኩት።
⇛ ሒጃብ ተፈጥሮ ነው መገላለጥ ስሜታዊነት ነው። ተፈጥሮሽን አላህንና መልእክተኛውን ትተሽ ስሜትሽን በመከተል የስሜትሽ አምላኪ መሆን የለብሽም!።
አላህ በተቀደሰው ቃሉ ስለ ሰሜት ተከታዮች እንዲህ በማለት ተናግሯል:-
أَفَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَٰهَهُ هَوَاهُ وَأَضَلَّهُ اللَّهُ عَلَىٰ عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمْعِهِ وَقَلْبِهِ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِ غِشَاوَةً فَمَن يَهْدِيهِ مِن بَعْدِ اللَّهِ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ
«ዝንባሌውን (ስሜቱን) አምላክ አድርጎ የያዘውን፣ አላህ ከእውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን በአይኑም ላይ ሽፋን ያደረገበትን ሰው አየሀን?! ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቃናው ማነው?። አትገሰፁምን?!።» አል-ጃሲያ 23
⇛ ልብ በይ! እህቴ፣ ስሜት ተከታይነት ምን ያህል የከፋ ተግባር እንደሆነ ቆም ብለሽ አስተውይ!!
ስለ እውነቱ እናውራ ከተባለ በአሁን ጊዜ ስለ ሒጃብ ከሚነገራቸው በላይ የሚያውቁ ሴቶች በዝተዋል። ምክንያቱም ⇛ ከተለያዩ ዳዒዎች የሰበሰቡት እውቀት አለ፣ ነገር ግን አላህ ያዘነላቸው እንጂ ከተግባሩ የሉበትም፣ ምን ከለከላቸው? መልሱም ቀላል ነው፣ ስሜት ተከታይነት ነዋ።
ከአንድ ሰው ጋር ከተገናኘን ቆይቶ በቅርቡ ተገናኝተን በአንዳድ የዲን ጉዳዮች ስናወራ ስለ አክፍሮት ሀይላት እንቅስቃሴ ማውራት ጀመርን እሱም እንዲህ አለኝ:- "እኔ ግን የሚያሳስበኝ ሙስሊሙ ማሐበረሰብ በሌሎች ስብከቶች ሌላ ሃይማኖት ይከተላል የሚለው ጉዳይ ሳይሆን በስሜት ተከታይነት ይጠፋል የሚለው ጉዳይ ነው የሚያሳስበኝ።" አለኝ፣ አዎን! በትክክል ተጨባጩም የሚያስገነዝበው ይህን ነው።
መሠረት እና ፍሬ
∬√√√√√√√√∬
قال الإمام الشافعي - رحِمَهُ اللّٰه:-
أصل العلم التثبيت، وثمرته السّلامة،
وأصل الورع القناعة، وثمرته الراحة،
وأصل الصّبر الحزم، وثمرته الظفر،
وأصل العمل التوفيق، وثمرته النجاح،
وغاية كل أمر الصدق.
📚 سير أعلام النبلاء (٤١/١٠)
👉 ኢማሙ ሻፍዕይ – ረሒመሁላሁ – እንዲህ ይላሉ፦
"የእውቀት መሰረቱ ማጣራት ነው። ፍሬው ሰላም መሆን ነው።
የወረዕ (የማይገባ ቦታ አለመገኘት) መሰረቱ መብቃቃት ነው። ፍሬው የልብ እረፍት ማግኘት ነው።
የትእግስት መሰረቱ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ነው። ፍሬው ድል መቀዳጀት ነው።
የስራ መሰረቱ መገጠም ነው። ፍሬው ወደ ሚፈልጉት ነገር ማለፍ ነው።
የነገሮች ሁሉ ግባቸው እውነተኝነት ነው።"
/channel/bahruteka
አሏህ የአዛኞች አዛኝ አምላክ ነው።
አሏህ ዝሙትን ይምራል።
አሏህ ወደ ሀራም ማየትን ይምራል።
አሏህ የሽርክንም ወንጀል
የተውበት በር ሳይዘጋ፤
ሩሁ ከጉሮሮው ሳትጠጋ፤ ከቶበተ ይምራል።
ስለዚህ መቼም ተስፋ አትቁረጥ አሏህ መሀሪና አዛኝ አምላክ ነው።
/channel/nuredinal_arebi
/channel/nuredinal_arebi
ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት የስሜት መለዋወጥ
==========================
ከ80 እስከ 90 ከመቶ ሴቶች የወር አበባ ከመምጣቱ በፊት ያለው ሳምንት ላይ ምቾት አለመሰማት ያጋጥማቸዋል። መጠነኛ ራስ ምታት፣ የጡት መወጣጠር፣ ሆድ መነፋት ሊያግጥማቸው ይችላል። ልክ እንደ አካላዊ ለውጦች የስሜት ለውጦችም ይኖራሉ። መነጫነጭ፣ መከፋት፣ ከማህበራዊ ነገሮች ራስን ማግለል ...ወዘተ። እነዚህ ምልክቶች ብዙ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አያደርሱም። ይሁን እንጂ ከ20-30 አመቶ የሚሆኑት ላይ በስራቸው ወይም በትምህርታቸው ላይ ተፅእኖ ሊያመጣ ይችላል።
ይህ ህመም የሚያጋጥማት አንዲት ሴት የወር አበባ ከ15 አመቷ እስከ 50 አመቷ ብታይ በህይወቷ ይሄ ህመም 420 ጊዜ ያጋጥማታል ማለት ነው። ስለዚህ መፍትሄው ምንድነው?
1) ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ህመምና የስሜት መለዋወጥ በህክምና የሚስተካከል ስለሆነ በዝምታ ከመሰቀያት ሀኪምን ማማከር።
2) ራስን መንከባከብ፣ እረፍት ማድረግ።
3) የወር አበባን ተከትሎ አንዳንድ ሴቶች ላይ የምግብ ፍላጎት ሊጨመር ወይም አንዳንድ ምግቦች ሊያምራቸው ይችላል። ሀይል ሰጪ (ካርሀይድሬት) የምግብ አይነቶች የድብርት ስሜትንና ጭንቀትን ስለሚያባብሱ በተቻለ አቅም መቀነስ።
4) ቫይታሚኖችን መውሰድ። አንዳንድ ቫይታሚኖችና ሚኒራሎች በተለይ ቫይታሚን ዲ እና ካልሺየም ከወር አበባ ጋር ተያይዞ የሚመጡ አካላዊና አእምሮዊ ምልክቶችን ለመቀነስ ያግዛሉ። ከሀኪም ጋር ተማክሮ መውሰዱ ጥሩ ነው።
ዶ/ር ዮናስ ላቀው
☑️ ሱጁድ ላይ የሚባል ዱአ
❀•°
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أنَّ رَسولَ اللهِ صَلَّىٰ اللَّهُ عليه وسلَّمَ كانَ يقولُ:
في سُجُودِهِ اللَّهُمَّ اغْفِرْ لي ذَنْبِي كُلَّهُ دِقَّهُ، وجِلَّهُ، وأَوَّلَهُ وآخِرَهُ وعَلانِيَتَهُ وسِرَّهُ.
📕[ صحيح مسلم ٤٨٣ ]
‘አላህ ሆይ! ሁሉንም ወንጀሌን ማረኝ፡፡ ትንሹንም ትልቁንም፡፡ የመጀመሪያውንም የኋለኛውንም፡፡ ይፋ የሆነውንም ምስጢራዊ የሆነውንም፡፡’
በተወኩል ፣በዚክር ፣በዱዓ ፣ያልተገነባች ልብ በነፍስያና በሸይጧን ተንኮል ትሽበባለች ።
ለጭንቀትና ለሀሳብ ትጋለጣለች።
==
/channel/https_Asselfya
⇛ስለ «ቀልቡ» ሁኔታ የሚጨነቅ ሁሉ ሊከታተለው የሚገባ እጁግ የምወደውን ቻናል ልጋብዛችሁ!
📢 ፕሮግራሙ ስለ ቀልብ፣ ኢማን ላይ ብቻ የሚያጠነጥን ነው… ትምህርቱንም የሚሰጡት ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ዓብዱ ረዛቅ አል በድር ናቸው።
📚በቻናሉ ውስጥም የሚሰጡትም እየተሰጡ ያሉትም ደርሶች፦
📚منظومة السير إلى الله.
📚أدب النفوس للآجري.
📚القصيدة الهائية في الزهد.
📚رسالة ابن القيم لاحد إخوانه.
📚أحاديث أعمال القلوب.
📚الداء والدواء لابن القيم.NB_አረብኛ ለምትችሉ ነው!
⇙
t.me/aemal_alqulub
t.me/aemal_alqulub
✏️ #ከባዱ_በሽታ_ምቀኝነት_!!
/
- ምቀኝነት ሰይጣን አባታችንን አደምን ሲመቀኘው በመጀመሪያ ሰማይ ላይ አላህ ሊታመጽበት የቻለ ወንጀል ነው።
ምቀኝነት
- ከአባታችን አደም የተወለዱት የአንድ ሰው ልጆች ሀቢልና ቃቢል አንዱ አንዱን እስከሚገድል ድረስ ጠላትነት መነሻ ምቀኝነት ነው።
- አይሁዳዎች ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) አዲስ ነገር አገኘ ወይም ተሰጠው ብለው መመመቀኘታቸው ምክንያት ይሄው ለሙሐመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)ና እሳቸውን ለተከተሉ ሙስሊሞች ባጠቃላይ ያላቸው ጥላቻ የከፋው። አላህ ግን ለሙሐመድ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ብቻ ሳይሆን ለኢብሯሂምና ለኢብሯሂም ቤተሰቦችም ትልቅ ንግስናን ሰጥቶ እንደነበረ ተናግሯል
أَمْ يَحْسُدُونَ النَّاسَ عَلَىٰ مَا آتَاهُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ ۖ فَقَدْ آتَيْنَا آلَ إِبْرَاهِيمَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَآتَيْنَاهُم مُّلْكًا عَظِيمًا
{{ይልቁንም ሰዎችን (ሙሐመድን) አላህ ከችሮታው በሰጣቸው ነገር ላይ ይመቀኛሉን ለኢብራሂምም ቤተሰቦች መጽሐፍንና ጥበብን በእርግጥ ሰጠን ታላቅንም ንግሥና ሰጠናቸው፡፡}} [ ሱረቱ አል-ኒሳእ - 54 ]
- ኩፋሩል ቁረይሽ የተለያዩ ተዓምራቶች በግልጽ እየመጡላቸው፣ እውነት እንደ ረፋድ ፀሀይ ፍንትው ብሎ እየታያቸው። ከመቀበል አይናቸውን ያሳወራቸው ምቀኝነት ነው።
ምቀኝነት ወንድም ከወንድም፣ ጎደኛ ከጓደኛ፣ ከቤተሰብ፣ ከጎረቤት በዲንያም ይሁን በዲን ጉዳይ በመልካም ተሰባስበው የነበሩትን ሳይቀር ያፋጃል።
قال:النبي صلى الله عليه وسلم (لا تباغضوا ولا تحاسدوا ولا تدابروا وكونوا عباد الله إخوانا). متفق عليه.
ነብያችን ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ እንዲህ ይላሉ፦
{{አትጠላሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባ አትሰጣጡ፣ (ትክክለኛ) የአላህ ባሪዎች በመሆን ወንድማማቾች ሁኑ}}
አላህ ይጠብቀንና አንድ አማኝ ሰዎችን በመመቅኘት በሽታ ከተወረፈ የራሱ ኢማን እየመነመነ፣ መልካም ሥራው እየቀለለ፣ ከናካቲውውም ዲኑንም ሊያጣ ይችላል
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ﷺ: إِيَّاكُمْ وَالْحَسَدَ، فَإِنَّ الْحَسَدَ يَأْكُلُ الْحَسَنَاتِ كَمَا تَأْكُلُ النَّارُ الْحَطَبَ.
📚 أَخْرَجَهُ أَبُو دَاوُدَ.
{{ከአቡ ሁረይራ በተወራ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል አደራችሁን ምቀኝኘትን ተጠንቀቁ እነሆ ምቀኝነት ልክ እሳት እንጨትን እንደምትበላው ሁሉ መልካም ሥራን ይበላል}}
(አቡ ዳውድ ዘግቦታል)
قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله :-
"القلب لا يدخله حقائق الإيمان إذا كان فيه ما ينجّسه من الكِبْرِ والحسد".
مجموع الفتاوى (١٣ / ٢٤٢)
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያህ እንዲህ ይላሉ፦ ልብ ውስጥ ትክክለኛ እምነት አይገባበትም፣ ከሱ ውስጥ (እሱን) የሚነጅሰው ኩራትና ምቀኝነት ካለ
(መጅሙዑል ፈታዋ: 242/13 )
ምቀኝነት እንደት እንደተስፋፋ ተመልከት ሁሉም ሰው ምቀኛ አያጣውም።
قال عمر بن الخطاب رضي الله عنه: (ما من أحد عنده من الله نعمة إلا وجدتَ له حاسداً)رواه ابن حبان في روضة العقلاء(٤١٣)
አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና ታላቁ ጀግና ዑመር ኢብኑል ኸጧብ እንዲህ ይላል
አንድም ሰው የለም ከአላህ ዘንድ ፀጋ ተሰጥቶት ምቀኛ ያላገኘሁለት
(ኢብኑ ሂባን ረውዶቱል ዑቀላ:413)
ምቀኛ ምቀኝነቱን እንዲተው ብለን የሚያስደስተው ሥጦታ እንሰጠዋልን??
وقال معاوية بن أبي سفيان رضي الله عنهما: (كلُّ الناس أستطيع أن أرضيه إلا حاسد نعمة، فإنه لا يرضيه إلا زوالها)رواه ابن عساكر في تاريخ دمشق(٥٩/٢٠٠)
ሁለቱንም አላህ መልካም ሥራቸውን ይወደድላቸውና የአቡ ሱፍያን ልጅ ሙዓውያ እንዲህ ይላል፦
{{ሁሉንም ሰው ማስደሰት እችላቸሁ በሰዎች ፀጋ ላይ የሚመቀኝ ምቀኛን ሲቀር (ምክንያቱም) እሱ ያቺ ፀጋ ሥትወገድ ሥትጠፋ ነው የሚደሰተው}}
(ታሪኹ ድመሽቅ 59/200)
ይልቅ ምቀኛ አካል ከምቀኝኘነት በሽታው የሚላቀቅበት መድሀኒቱ ምንድን ነው።
قَالَ حَاتِم الْأَصَمّ رحمه الله :
«رَأَيْتُ النَّاسَ يَتَحَاسَدُونَ فَنَظَرْتُ فِيٰ قَوْلِهِ تَعَالَىٰ:
«نَحْنُ قَسَمْنَا بَيْنَهُم مَعِيشَتَهُمْ
فَتَرَكْتُ الْحَسَدَ، لِأَنَّهُ إِعْتِرَاضٌ عَلَىٰ قِسْمَةِ اللهِ»
📚 [ مختصر مِنْهَاج الْقَاصِدِين ٢٨ ]
(ታላቁ የቀደምት ሊቅ) ሀቲም አል አሶም እንዲህ ይላል፦
ሰዎች ሲመቀኛኙ ተመለከትኩና (ከዛ የምቀኝነትን ምንነት) በአላህ ቃል በቁርአን ውስጥ ሥመለከት፦ {{እኛ ኑሯቸውን በመካከላቸው አከፋፍለናል፡፡}}[ ሱረቱ አል-ዙኽሩፍ - 32 ] የሚለውን አገኘሁ ከዛ በኋላ ምቀኝነት የሚባል ነገር ተውኩኝ አለ
(ምንጭ፦ ሙኽተሶር ሚንሀጁል ቃሲድን: 28)
#እናስተውል፦ በተመቀኝን ጊዜ ዓይን የሚባለውን በሽታ በሰዎች ላይ እየላክንባቸውና ሰዎችን እየጎዳን እንደሆነም ልናውቅ ይገባል፦
ما رواه مسلم عن ابن عباس رضي الله عنهما عن النبي صلى الله عليه وسلم: "الْعَيْنُ حَقٌّ، ولو كانَ شيءٌ سابَقَ القَدَرَ سَبَقَتْهُ العَيْن
ኢማሙ ሙስሊም ከታላቁ ሰሀብይ ከአብደላህ ኢብኑ አባስ ባዎሩት ሀዲስ ነብያችን እንዲህ ብለዋል {{ ቀደርን (የአላህ ወሳኔን) የሚቀድም ነገር የለም እንጅ ቢኖር (ሰዎችን በማጥፋትም ሆነ አደጋ በማደረስ) የሰው ዓይን ይቀድም ነበር }}ُ ብለዋል
ሆን ብለው ሰዎችን ለመጉዳት የሚመቀኙ አካላቶች ደግሞ አላህ ፈቅዶት በዚች ርካሽ ዱንያ ላይ ቢሳካላቸው እንኳ አላህ የነርሱን መጨረሻ አበላሽቶ ለነዚህኞቹ የተሻለውንና ዘለአለማዊ ደስታ እንደሚሰጣቸው ከአሁኑ ሊያውቁት ይገባል
وللآخرة خير لك من الأولى وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ
መጨረሻይቱም (ዓለም) ከመጀመሪያይቱ ይልቅ ላንተ በላጭ ናት፡፡ ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡ [ ሱረቱ አል ዱሃ - 4 ]
#እኔም_አልኩኝ፦ በዚች ርካሽ ዱንያ ሰዎችን ከመመቅኘት ይልቅ የተሻለውን ሀገር ደስታ ከአላህ በመከጀል ከደጋግ የአላህ ባሮች ጋር መቋደስ ይቻላልና እሱን መመኘት ይሻላል።
ንፁሃኖች ደግሞ ከምቀኛ አደጋ የሚጠበቁባቸውንም ሳይቀር አላህ ተናግሯል
وَمِن شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ
«ከምቀኛም ክፋት በተመቀኘ ጊዜ፤ (በአላህ እጠበቃለሁ በል)፡፡» [ ሱረቱ አል-ፈለቅ - 5 ]
ኮፒ
👉 ኢልያስ አሕመድና ዶክተር ጀይላን
ኢልያስ አሕመድ ዶክተር ጀይላንን ከሰለፍዮች ውግዘትና ተሕዚር ውርጅብኝ ለመከላከል በሚመስል መልኩ ኪታቦቹን ሲያስተዋውቅና አንብቡዋቸው እያለ ሰለፍዮችን ሲገፋፋ እራሱ ላይ ውግዘት ገጥሞት በጥያቄ ሲያጨናንቁት አቋሙን በማጠናከር አሁንም እላለሁ ብሎ የቀረበለትንና የሚያውቀውን የዶክተሩን ኢንሒራፍ የማይቀበል መሆኑን አረጋግጧል ።
ኢልያስ አሕመድ ሰለፍይ ነው የሚለውና ተነጋግረን እናውቃለን መስለሐና መፍሰዳ በማየት ተወሱዕ ታደርጋላችሁ ብለነዋል አብረን እንሰራለን ከፊላችን ከፊሉን ይሞላል ።
የሚለውን ዶክተር ጀይላን ማንነት የተመጠነ ማረጋገጫ ከሚለው የወንድማችን አቡ ዐ/ራሕማን ፅሑፍ በጥቂቱ እንመልክት ።
ወንድማችን አራተኛ ብሎ የዶክተር ጀይላንን ኢንሒራፋቶች ( የሰለፍያ መንገድ የኻለፈባቸውን ነጥቦች ሲዘረዝር እንዲህ ይላል : –
– " ወጣቶች እንዴት ሙፍቲን እንዲቀበሉ እናድርግ "
እሱ ( ሙፍቲ ) ማለት ዑመር ኢድሪስ አል ሐበሺ ( የአሕባሽ ዐቂዳ አራማጅ ) ሙወሒዶችን የሚያከፍር ፣ የኮሚቴው ሀላፊ ፣ ተቀዳሚ ሙፍቲ ( የሚሉት ሲሆን ) አላህ ከዐርሽ በላይ አይደለም የሚል ፣ አላህ ከላይም ከታችም አይደለም , ከዐለም ውጪም ውስጥም አይደለም , ከላይም ከታችም አይደለም, በቀኝም በግራም አይደለም የሚል ሲሆን አላህ ከዐርሹ በላይ ነው የሚልን ሰው የሚያከፍር ወሀብዮች ካፊሮች ናቸው የሚል ነው !!!!!! ።
ከዚህም በተጨማሪ ሙፍቲነት ትልቅ በእውቀት የሚገኝ ደረጃ ነው ሸይኻችን ሸይኽ ሙፍቲ ዑመር ኢድሪስ ታጋሹ ፣ ምንዳ ከአላህ ፈላጊው በጥንካሬ ፣ በትግል ፣ በእውቀት ያገኘው ነው ‼። ይላል
ይህን ደረጃ ከዚህ በፊት ከነበረው በበለጠ አላህ አረጋግጦለታል ። እሱ ማለት በጣም አዛ የተደረገ ነው እያለ ይቀጥላል ። ተመልከት ሱሩርዩ ጀይላኒ የሚያልቀውንና የሚያተልቀውን ሙፍቲ እንዴት እንደሚያሞግስና በመገረም የተመልካቾች እጅ በጭብጨባ ( ድምፃቸው ) በተክቢር እንዴት እንዳደመቀው ።
– " ሐሰን ታጁን እንዴት ወደ ህብረተሰቡ እንመልሰው " ማለቱ
ሐሰን ታጁ ማለት ከመንገድ የወጣ ኢራንን ( ራፊዳዎችን) የሚያደንቅ በተቃራኒው የሱና ዑለሞችን እንደ ሸይኹል ኢስላምና የሌሎችንም ክብር ዝቅ የሚያደርግና አላዋቂ ናቸው የሚል ነው ።
– " ወጣቶችን እንዴት አድርገን ከሸይኽ ጣሃ ( የአንዋር ኢማም ) ኋላ እንዲሰግዱና ማክፈራቸውንም እንዲተዉ እናድርጋቸው " ማለቱ
እሱ ( ጣሃ )ማለት ቲጃኒ የአሕባሽ ዐቂዳን የሚያራምድ ጫፍ የወጣ ሱፍይ ነው
– " ዛሬ ሌሊት የአል ጀዚራን ጣቤያ ተመልክቻለሁ ከዛም ኢራን ባለንበት ዘመን ከሁሉም የምትበልጥ ሀገር መሆኗን አውቄያለሁ ‼ ። ለዚህ ነው ሳውዲ የምትጠላት በተቃራኒዋም ጦር ታሰልፋለች ።
– " በዚህ ዘመን በዐቂዳ አዋቂው ታላቁ ዓሊም ሰፈረል ሀዋሊ ነው " ። ማለቱ
– የሳውዲ መሪዎች ስልጣናቸውን ለማቆየት ወደ ጠንቋዮች ይጠጋሉ" … ‼ ።
– ሰይድ ቁጥብ ለመመፃደቅ ሸሂድ ሆኖ መገደሉ ይበቃዋል " ማለቱ
– " ፖለቲካ ባይሆን ኖሮ ደፋር ሰው ማለት ኦሳማ ቢላድን ነው እል ነበር " ። ማለቱ
– የተብሊጝ ጀማዓዎች የዳዕዋ ጀማዓዎች ናቸው እስልምናን ኻድመዋል እንወዳቸዋለን ።
ዳዒሾች የሱና ወጣቶች ናቸው ዒራቅ ላይ ለሱናና ለሱና ሰዎች ለመከላከል የቆሙ ድፍረታቸውማ አንድ ሰው የሚገረምበት ጉዳይ ነው ። ማለቱ
– የሱና ዑለሞችን መዋጋቱና በእነርሱ ላይ መቅጠፉ ለዚህ ማሳያ በታለቁ ሸይኽ አማን አልጃሚ ላይ (ረሂመሁላህ) የተናገረውን እንመልከት
" አላህ ምላሱን በካንሰር ይዞ ፈተነው ይህ የሆነው ዑለማዎችን በማነወሩ ነው " ይላል
– " ወጣቶች እንዲቀበሉ ( የመጅሊሱ ስምምነት ላይ) ሱፍያ ማለት ነፍስን ማጥራት ማለት ነው ብለን አሻዒራ ማለት ደግሞ አህሉ ሱናዎች ናቸው ብለን እናስገባለን ምክንያቱም አህሉ ሱና ስለሆኑ ‼ ።
– " እነዚያ ከተብሊጝና ኢኽዋን የሚያስጠነቅቁ ከሸይጧን ናቸው " ሁለቱም ሰለፍዮች ናቸው ማለቱ
እነዚህ ወንድማችን በመረጃ ካቀረባቸው ጥቂቶቹ ናቸው ሙሉዉን የተመጠነ ማረጋገጫ በሚለው pdf ማግኘት ይቻላል ።
/channel/bahruteka
ቤተሰቦቻችንኮ ኮፊያ የለበሰ ጀላቢያ የለበሰ ጥምጣም የለበሰ ሁሉ ሐዲስን ያወረ ሁሉ አረብኛን የተናገራ ሁሉ እውነተኛ የእስላም ተጣሪ ነው የሚመስላቸው ።ምክንያቱም መሰረታዊ የዲን እውቀት አብዘሀኛዎች ጋር የለም አልተማሩምና ወደ ቀብር አምልኮ የሚጠራውን አካል እንኳን አይለይም በምልጃ (በሸፈዐ)አሳቦ ወደ ቀብር አምልኮ የሚጣሩ ብዙዎች ናቸው ።እናም ከዚህ የአሕባሽ የጥበት ቲቢቤተሰቦቻችን ጎረቤቶቻችን ዘመዶቻችን እንዲሁም ጓደኞቻችን እናስጠንቅቅ
አላህ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን!
አስ-ሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ
#Share_Share_Share_Share_Share_Share
==============================
ዛሬ ወደናንተ ላደርስ የወደድኩት በአላህ ፍቃድ " አላህ የት ነው "?ለሚለው ማስረጃ ከቁርኣን፣ከሐዲስ ፣ከሶሃባ ፣ከሶሃባ ታማሪ ፣ከሶሃባ ተማሪ ተማሪ ፣ከቁርኣን ሙፈሲር ፣ከመዝሀቡ መሪ ፣- - - - ።ከነዚህ(ከላይ ከጠቀስኳቸው )ከሁሉም አንዳንድ ማስረጃን ይዤ ብቅ ብያለሁ ።
ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ሁላችንንም ይህንን መልእክት በቻልነው አቅም መንገድ ለሳቱ ቡዱኖች ሁሉ ሼር እናድርገው ።
አላህ የት ነው ?ቁርኣናዊ ምላሽ!
ቁርኣን ለየትኛውም የልብ ህመም ፍቱን መድሃኒት ነው ።ቁርኣን ለምንወዛገብበት ጉዳይ ሁሉ አስተማማኝ ገላጋይ ነው ። አላህ እንዲህ ይላል ፦{መፅሐፍንም ለሁሉ ነገር አብራሪ መሪም እዝነትና ለሙስሊሞች ብስራትም ሆኖ ባንተ ላይ አወረድነው ።} [አንነሕል 89]
ስለዚህ አላህ ስለራሱ የትነት ምን እንደሚል እንኒይ
አላህ እንዲህ ይላል፦ {#አርረሕማን ከዐርሹ በላይ ሆነ።} [ጧሃ ፡5]
ይህንን ደሞ ከሰለፎች አረዳድ ምን ብሎ እንደተረዱት እንይ
አል ኢማም አል በገዊ በዚህች አንቀፅ እና ተመሳሳይ አገባብ ባላቸው ሌሎች አንቀፆች ላይ የተጠቀሰው "ኢስተዋ" የሚለው ቃል ፊቹ "👉ከላይ ሆነ"ማለት እንደሆነ ኢብኑ ዐባስን አጣቅሰው ዘግበዋል ።[ተፍሲሩልበገዊ 1/78]
አላህ የት ነው ?ሐዲሳዊ ምላሽ
❷ ሁለተኛው ማስረጃችን ከሐዲስ
ውዱ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሰማይ ያለው ጌታ ዘንድ ታማኝ ነበሩ ።ታዲያ ጌታቸው ከሰማይ በላይ እንደሆነ ሲነግሩንአናምናቸውምን?!
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ተይዞ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ ፦{አታምኑኝምን?እኔ በሰማይ ላለው ታማኝ ሆኜ ሳለ የሰማይ ወሬ ጧት ማታ እየመጣልኝ? [ቡኻሪ 435፣[ሙስሊም 2500]
አላህ የት ነው?ከሶሃባዎች ማስረጃ
❸ ሶስተኛ ማስረጃችን ያቀረብነው ከሶሃባ ነው ።
እናታችን ዓኢሻህ ረዲያላሁ ዐንሃ እንዲህ ትላለች "በአላህ ይሁንብኝ እኔ (ዑስማንን ረዲያላሁ ዐንሁ)መግደል ብወድ ኖሮ እገለው ነበር ብዬ እሰጋለሁ።ነገር ግን እኔ እሱን መግደልን እንደማልወድ አላህ 👉ከዐርሹ 👉በላይ ሆኖ አውቋል ።"[ሙኽተሰሩልዑሉው ፡104]
❹ አረተኛው ማስረጃችን ከታቢዒይ (ከሶሃባ ተማሪ)ነው
ረቢዐህ ኢብኑ አቢ አብዲረሕማን (62 ሂ.)አንድ ሰው "{አርረሕማን ከዐርሹ በላይ ከፍ አለ } ሲባል እንዴት ነው ?"ሲል ጠየቃቸው ።ይህኔ "👉ከላይ መሆኑ የማይታወቅ አይደለም ።እንዴትነቱ ግን አይታወቅም ።በዚህ ማመን ግዴታ ነው ።ስለዚህ መጠየቅ ቢድዐ ነው ።መልእክቱ የመጣው ከአላህ ነው ።በመልእክተኛው ላይ ያለው ማድረስ ነው ።በኛ ላይ ያለው አምኖ መቀበል ነው ።"አሉት ።[ሙኽተሶሩልዑሉውህ 132]
❺ተኛው ማስረጃችን ከአትባዑትታቢዒይ ነው ።
አውዛዒይ ረሒመሁላህ (157ሂ)እንዲህ ይላሉ "በርካታ ታቢዒዮች(የሶሃባ ተማሪዎች) እያሉ የላቀው አላህ 👉ከዐርሹ 👉በላይ ነው እንል ነበር" [ሙኽተሶሩልዑሉው 137]
❻ተኛው ማስረጃችን ከአትባኡትታቢዒይ ቦኃለ ከነበሩ አኢማዎች ነው ።
ሙሐመድ ኢብኑ ሙስዐብ አልዓቢድ (228 ሂ.)እንዲህ ይላል "ጌታዬ ሆይ! አንተ እንደማትናገር እና በአኼራም እንደማትታይ የሞገተ እሱ በፊትህ ክዷል ። አንተ ከሰባቱ ሰማያት 👉በላይ ከዐርሹ 👉በላይ እንደሆንክ እመሰክራለሁ። አፈንጋጭ የአላህ ጠላቶች እንደሚሉት አይደለም "[ሙኽተሶሩልዑሉው 183]
❼ተኛው ማስረጃችን ከእማም አሽሻፊዒይ ነው ።
አል ኢማም አሽሻፊዒይ ረሒመሁላህ (204 .ሂ) እንዲህ ይላሉ "እኔም ፣እንደ ሱፊያን ማሊክ እና ሌሎችም ያገኛኃቸው ሰዎች ያለንበት #የሱንና አቋም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌላ እና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ እንደሆኑ ፣ አላህ 👉በሰማይ ከዐርሹ 👉ላይ እንደሆነ ከፍጡሩ በፈለገው መልኩ እንደሚቀርብና በፈለገው መልኩ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ እንደሚወርድ ፣.... መመስከር ነው ። " "የአቡ በከር አስሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ኺላፈ የአላህ 👉በሰማዩ ሆኖ የወሰነው ፣የባሪያዎችን ልቦች በሰበሰበበት ነው ።" [አልጁዩሽ 180----109 ]
❽ተኛው ማስረጃችን ደሞ ከቁርኣን ሙፈስሲሮች ነው ።
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ረዲያላሁ ዐንሁ ፦"ዐርሹ ከውሃው በላይ ነው ።አላህ ደግሞ 👉ከዐርሹ 👉በላይ ነው ።ሆኖም ከስረዎቻቹችሁ ምኑም አይሰወረውም።" [ቡኻሪ ዘግበውታል ።[ኸልቁ አፍዓሊልዒባድ :43 ]ሙኽተሶሩልዑሉው 103 ----104]
እዚህ ጋር የፈለኩት ከሁሉም አንዳንድ ማስረጃ ስለሆነ እንጂ ማስረጃዎችማ ምናልባትም ከሁለት ሺህ በላይ ነው!!
አላህ ሆይ!ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን አላህ ሆይ!ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን አላሁማ አሚንን
/channel/gfyygy
ጀዛኩሙላህ ሼር በማድረግ ብቻ ተባበሩኝ ።
ወንድሜ ነው።ከድር ሳኒ ሙሳ ይበላል።ወላሂ ከተገናኘን ካዬሁት ከ12 አመት በላይ ነው።በጣም ናፍቆኛል ።በስልክ እንኳን አናገኘውም ።ስልኩ የለንም።የሚኖረውም ወደ ጋምቤላ መስመር ነው።እኛ ስናቀው የትዳር አጋር የለውም።ወላሂ በጣም ናፍቆኛል በጣምም ነበር የምወደው ። ምክንያቱም ደግ ሰው ነው።እኔ እስካ ማውቀው ድረስ ኑሮው ወደ ጋምቤላ መስመር ያደረገ ሲሆን የዛሬ 15 አመት አከባቢ ለአረፋ አገር ቤት ገብቶ ነበር።እኔ አዳማ የገባሁበት አመት ነበር ወላሁ አዕለም ከአንድ ወር በላይ አብረን ቆዬን ከዚያ ወደ ነበረበት ጋምቤላ ተመለሰ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ድምፁንም ሰምቼ አላቅም።
እናም ለአላህ ብላችሁ ከድር ሳኒ ሙሳን የምታቁ ይህንን መልእክት አድርሱልኝ "ወንድምህ አብድረሒም ሳኒ ሙሳ ነኝ ካስታወስክ "አብዲ ቆንጅ"እያልክ የምትጠራኝ ወንድምክ ነኝ ከአዳማ በጣም ስለናፈከውና ይፈልግካል ወንድሜ ከድር በአላህ ቢያንስ በስልክ ድምፅህን ልስማ !
ሼር አድርጉልኝ ምናልባት የአላህ ፍቃድ ሆኖ ከደረሰው
/channel/gfyygy