gfyygy | Unsorted

Telegram-канал gfyygy - አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

883

ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot

Subscribe to a channel

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ከሰኞ እስከ ሰኞ  ተከታታይ ወርቃማ ቀናት ከፊታችን 👇
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖


✔️ ሰኞ ፦ የሙሐረም ዘጠነኛው ቀን ነው

✔️ ማክሰኞ ፦ ሙሐረም አስር (ዐሹራ ፆም)

✔️ እሮብ ፦ የዐሹራ ቀጣይ ቀን

✔️ ሐሙስ ፦ ስራዎችወደ አለህ
       የሚቀርቡበት ቀን

✔️ አርብ ፦ አያሙል ቢድ የመጀመሪያው
      ቀን (ሙሐረም 13 )

✔️ ቅዳሜ ፦ አያሙል ቢድ

✔️ እሁድ ፦ አያሙል ቢድ

✔️ ሰኞ ፦ ስራዎች ወደ አለህ የሚቀርቡበት ቀን



🥀 ምርጥ አጋጣሚ ነው እንኳን ሰበብ
       ኖሮት
      ይቅርና ምንም ሰበብ ሳይኖረው
  ሙሐረምን ሙሉውን መፆም ይወደዳል።


🥀 ውዶች ያቻልን እንፁም  ለሌሎችም
        ሼር ሼር በማድረግ እናመላክት ።
       ወደ ጥሩ ነገር ያመላከተ ልክ እንደ
      ሰሪው አጅር ያገኛል ስለተባለ
    ይሐው አሁን ጀምረን ለሌሎች ሰዎች
      እናስተላልፍ።


☑️ አያሙል ቢድ ማለት ፦ ከወሩ ውስጥ
      መፆማቸው የተወደዱ የሆኑ ቀናቶች
       ናቸው። ከወሩ 13ኛው ቀን፣ 14ኛው
         ቀን እና 15ኛው ቀን መፆም ነብዩ
        ያነሳሱበትና የተወደደ ተግባር ነው።

                           منقول

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

የሙሐረምን ወር አስረኛውን
ቀን መፆም ያለው ደረጃ

t.me/Achachir_mkroch

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩሕሩሕ እና በጣም አዛኝ በሆነው።

ለወላጅ ዱዓ ማድረግን አደራ ችላ አትበሉት

ወንድም እህቶችን አደራ ማለትን ፈለኩኝ

ወላጆች በሂዎትም ይኑሩ አይኑሩም ግን በመልካም ዱዓችን ሁሌም ልናስባቸው ግድ ይለናል ትልቅ የሆነ ሐቃቸው አለብን።ግን ለወላጆቻችን ያለ እኛ ማን አላቸው?ሌላውን ባንችል ከታላቁ ጌታችን ምህረትን መለመን እንዴት ይከብደናል?!!!!!!!

አላህ እነሱን አስመልክቶ "ለኔና ለወላጆች" ልብ በሉ!ከራሱ ጋር አያይዞ ነው "ለኔና ለወላጆች"ብሎ የተናገረበት አገጣሚ አለ በተከበረው ቃሉ።ሱብሐነላህ!

"በኔ ላይ ምንንም አታጋሩ ለወላጆቻችሁም መልካምን ስሩ።"ይላል በሌላ ቦታም።

እናም ጌታችንን  አላህ   ሆይ! ለወላጆቼ ማር፣እዘንላቸው  እነሱ ባለማወቅ ብዙውን ሐቅህን ሊያጓድሉ ይችላሉ አንተ ደሞ ከአዛኞች ሁሉ በላይ አዛኝ ነህ! እነሱ (ወላጆቻችን)እኛን በማሳደግ ብዙ ለፉ ያንተንንም ሐቅ አጓደሉ ።"እያልን እንማፀነው።

አላህዬ ደሞ በጣም አዛኝ ዱዓን ተቀባይ በሁሉም ነገር ቻይ እሱን መለመንን የሚያበዙትን የሚዮድ የሆነ ጌታ ነው።

አንተ ወይም አንቺ ባደረግሺው ዱዓ ለወላጆች ደረጃ ሲጨመርላቸው ወላጆችም "ጌታችን ይህ መልካም ስራ የኛ አይደለም ከየት መቶ ነው"?ብሎ ይጠይቃሉ። ከዚያም" ይህማ  ልጅህንም ያደረገልህ ዱዓ ነው"ይበላል።


እናም በሂዎት ካሉ  በዱዓ በደዕዋና በቻልነው መጠን በእንክብካቤ አደራ


ለመተወዎስ ያክል ነው መተዋዎስና አደራ መበባል ለአማኞች ጠቃሚ ስለሆና

ወሰላሙ  ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ



/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

~ የአደም አፈጣጠር

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

t.me/Achachir_mkroch

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ወጣቱና ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም

«እጂግ በደለኛ ፍጡር ሰው»

❶የአማና ክብደት፣
❷የሰው ልጅ በደለኝነት፣
❸የወጣቱና የጠቢቡ ምክር


አድምጡት ይጠቅማችኋል

በኑረዲን አል አረብ

http://t.me/nuredinal_arebi

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

"ቤቴ ከፈረሰብኝ በላይ አደጋ ደርሶብኛል"

አብሽሩ ስለ ችግርና መከራ ላወራ አይደለም

አንድ  ጎረቤቴ ቁርስ ቤት የሚሰራ ጴንጤ አለ።እኔና እሱ በጣም እንቀረረባለን ።የፈለገውን ይጠይቀኛል እሰጠዋለሁኝ እኔ ግን የፈለኩትን አልጠይቀውም ደሞ ከጴንጤ ልጠይቅ¿¿

ከወር በፊት የሱ ዘመዶች"ለዛላላም የሚቆይ እውነተኛ አምላክ እያሱስ ብቻ ነው ......"እያሉ መንገድ ላይ ሲዋሹ የሰማ አንድ ወንድሜ " ለዘላላም የሚቆይ እውነተኛ አምላክ አላህ ብቻ ነው"!  በማለት ሲናገር የሰማው

እንከፉ ጎረቤቴ  ለአንድ ክርስቲያን ጓደኛችን በጆሮው "እነዚህኮ አንድሺህ ሚስት ማግባትን የሚፈቅድ ሰው ተከታይ ናቸው "።ብሎ ድብን ያለ ውሸት  ያው ቀጣፊነት አመላቸው በህሪያቸው  ልዩ መተወቂያቸውም አይደል?! ብሎ በተናገረ በነገራችን ላይ ይህ ንግግር ብዙ ዋጋ አስከፍሎታል።አልሐምዱሊላህ።

አሁን በቅርቡ ደሞ  ቤቱ ፈርሶበት  የሱን ሀዘን ሳይጨርስ  እህቱ ሰለመችና በሀዘን ላይ ሀዘን ደረበችለት ።

አላህ  ለእህቱ በኢስላም በተውሒድ ላይ ፅናቱን  ይስጣት።

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የቀጠለ አስገራሚውና አስተማሪው ድንቅ ታሪክ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

እነዚያ ያመኑት ልባቸው አላህን በማስታወስ ትረካለች (አዋጅ )ንቁ አላህን በማስታወስ ልቦች ይረካሉ።

አላህን እያስተወስን ሶላት እየሰገድን ቁርኣንን እየቀራን ሶዳቃ እየሰጠን ዝምድናን እየቀጠልን(በስልክም ቢሆን) እንርካ።አላህ በችሎታው ያግራልን

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የዑለማዎች ምክር በአማርኛ በአፕልኬሽን

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የነብያት ታሪክ በአማርኛ በአፕልኬሽን አውርዳችሁ አነብቡ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

በከተማዎች አብዛኛው ቤቱ እየፈረሰበት ያለው ሙስሊሙ ነው። አላህ ይድረስላቸው ወገኖቻችንን።
አይዟችሁ! ተስፋ አትቁረጡ። አላህ በጀነት ቤት ይተካችሁ። ዱንያ ብትደላም ያው ዱንያ ናት። ሶብር አድርጉ። ነገሮች ነገ ይቀየሩ ይሆናል። ዱንያ እንደሆነች ተለዋዋጭ ናት። ከችግር በኋላ መልካም ነገር አለ። ስንት አያልፍም የተባለ ነገር አልፏል። ይህም ያልፋል ኢንሻአላህ።
=
ቴሌግራም፡
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ይህች እህታችን #ፋጡማ ወይም ዳቦ ትባላለች!! የሁለት ልጆች እናት ነች :: ትንሽ የአዕምሮ ህመም ያለባት ሲሆን ሚያዝያ 16 ቀን እሩፋኤል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከቤት እንደወጣች እስካሁን አልተመለሰችም ! ያለችበትን የሚያውቅ ወይም ያየ በ 0930288906 እና 0922430226  ደውሎ ቢያሳወቀን ወረታ እንከፍላለን ::
#ሼር በማድረግ አፋልጉን

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

"""""""""""""'"""""""""""ይነባብ"""""""""""
"""""""አባት ለሴት ልጁ ያለው ፍቅርና ክብር """""
አንዲት እህት እንዲህ ትላለች
ከወንድሜ ጋር በሀይለኛው ተጣላን አስለቀሰኝ
ለአባቴ እንደምናገር አስፈራራሁት....!

አባቴ ሲመጣ ሳልናገር ቀረሁ
እናቴ ግን የተፈጠረውን ነገረቺው ለአባቴ...

ሳላስበው አባቴ ክፍላችን ገብቶ
ወንድሜን እንዲህ ሲል ተናገረው ....

እህትህ ጋር ለምንድነው የተጣላችሁት..?
ወንድሜም እየተነጫነጨ እሷ ነች የጀመረቺው አባቴ..!

አባቴም እጁን ይዞ ከክፍሉ ወጣ
የምትናገረውን ልብ ብለሀል ታውቆሀል ወይ አለው..? እሷ ነች የጀመረቺው ማለት ምን ማለት ነው!

ይህ እኮ ቤተመንግስቶ ነው
እዚህ ከተዋረደች የት ነው የምትከበረው!
አንተ እኮ ከኔ ቀጥሎ መከታዋ ነህ.. ምርኩዛ ነህ..አንተ ከሰበርካት ወደየት ትጠጋለች!

ልጄ እህት አለህ ማለት እኮ
የዱንያን ጀነት ከነ ፀጋው አገኘህ ማለት ነው!

አደራህን ልጄ
'ባንተ ልቧ እንዲሰበር አታድርግ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

#ጓደኛ አለኝ
.
ቆየት ብሏል፡፡ የሆነ ቀን በአፍሪካ ቲቪ የፈትዋ ፕሮግራም እያዳመጥኩ ነበር፡፡ ሸይኽ ሰዒድ ነበሩ፡፡ አንዷ ዘና ብላ ገባች፡፡ ‹ጓደኛ ነበረኝ› ብላ ጀመረች፡፡ ዝም አሏት፡፡ ‹ጓደኛዬ … እያለች ቀጠለች፡፡ ሰቀጠጣቸው መሠለኝ አስቆሟት ‹በቃ እሱን ቃል አታንሺ፣ አትደጋግሚ ሰምተናል፡፡ እኛ የምናውቀው ወንድ ለወንድ፣ ሴት ለሴት ጓደኛ ሲሆን እንጂ ወንድ ለሴት፣ ለሴት ለወንድ ብሎ ጓደኛ በሸሪዓችን የለም … › አሏት።
.
እውነትም የለም፡፡ የምሬን ነው የምላችሁ የለም፡፡ ዛሬ ግን ይኀው በሙሉ ልብ በአደባባይ ይነገራል፡፡ የሆነ ቀን በሆነ ቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ የፕሮግራም መሪው ሒጃቧን ጥስቅ አድርጋ ያሠረች አንዷን ሙስሊም ያወራታል ‹ አግብተሻል ወይ?›፣ ‹አላገባሁም›፣ ‹ጓደኛ አለሽ?› ‹ አዎን አለኝ› አለች አየተፍለቀለቀች፡፡ … ምናልባት እኮ ላይኖራትም ይችላል፣ ግን ለምን ከሰው ልቅር ዓይነት ሆኗል ነገሩ … በሐራም ፉክክር ተጧጡፏል፡፡ ጓደኛ መያዝ ብርቅ ይመስል፣ ማወቅ፣ መማር፣ መመራመርና መሠልጠንና ጽድቅ ነገር ይመስል፡፡ ‹ የነርሱን ዱካ በሁሉም ነገር ውስጥ ትከተላላችሁ› ብለዋል ነቢዩ፡፡ … ረበና ይስቱር፡፡
.
Its normal አለኝ፣ አንዱ የሥራ ባልደረባዬ ። ‹ኖት ኖርማል› አልኩት እኔም በተራዬ፡፡ በክብር ታጭቻለሁ፣ ኒካሕ አስሬያለሁ፣ ጎጆ ልወጣ ነው … አንድ ነገር ነው፡፡ ‹ጓደኛ አለኝ › ማለት ግን ትርጉሙ ምንድነው? … ‹ጓደኛ አለኝ› ሲባል የሚገባኝ እንዲህ ነው ‹ ልጃገረድ አይደለሁም፣ ሐራም እየፈፀምኩ ነው፣ ዝሙት እየሠራሁ ነው፤ ገላዬን እያራከስኩ ነው፣ ይህንንም በኩራት እናገራለሁ …. › ሌላም፡፡ ወገን! ሰው እኮ አላህ የሠተረው ሆኖ ሳለ ዝሙት እየሠራ መሆኑን በአደባባይ የሚናገርበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ በሐራም መመፃደቅ ተራ ነገር ሆኗል፡፡ ኤሌመንተሪ ሂዱ፣ ሃይስኩል እና ዩኒቨርስቲ ሂዱ፡፡ ወሬው ሁሉ ጓደኛ አለው አላት? ሆኗል። ስንት ጉድ ታያላችሁ!፡፡ ከ12 እና ከ13 ዓመት ጀምሮ ንፅህና ተጠልቷል፡፡ ስንቷ ናት ጓደኛ ባለመያዟ ምክንያት የተገለለችው! የተተረበችውና የተናቀችው፡፡ አላህ ፅናቱን ይስጥሽ እህቴ
‹ ዝሙት በይፋ ይሠራል› ይላሉ ነቢያችን ከቂያማ ምልክቶች መካከል አንዱን ሲናገሩ፡፡
.
ወዳጆቼ በኢስላም ጋብቻ እንጂ ጓደኝነት የለም፣ ትዳር እንጂ ዝሙት የለም፡፡ ከትዳር በፊት መቀማመስ መዳራት የለም፡፡ ማቆያና መክሰስ የለም። ተሞካክሮ መተው የለም፡፡ በአልጋ እንጠናና፣ እንተያይ፣ እንፈታተሸ፣ እንጣጣም የለም፡፡ ይህ የእስልምና ብቻ ሳይሆን የትክክለኛ ህሊና ፍርድም ነው፡፡ ማን ተሞክሮ ሊግገፋ! ማን ተፈትሾ ሊትተው! ማን ተመጦ ሊጥጣል፣ ማን ተቀምሶ ሊትተፋ...
ከትዳር በፊት ወሲብ ዝሙት ነው፡፡ ከኒካሕ በፊት ግንኙነት አመፅ ነው፡፡ ያለ ቦታ መቆም ነው። ያለ ጊዜ መድረስ ነው። ክብር ማጣት ነው።
ወሲብ ከአካል ንክኪ በላይ ነው። ከብልቶች መገናኘት በላይ ትርጉም አለው፡፡ አላህ ንፁህ እና ያልቆሸሸ ገላ ሠጠህ/ሠጠሸ፡፡ ገላህ/ሽ ወደፊት ለሚያገባህ/ሽ ሰው አማና ነው፡፡ ብትጠብቂው/ ቀው ለህሊናህ/ሽ ዕረፍት ነው፡፡ ለሚያገባህ/ሽም ክብር ነው፡፡ ለውስጥህ/ሽም ሠላም ነው፡፡ አላህ ይጠብቀን።
.
የሚገርመኝ ከዓመታት የጓደኝነት ቆይታ በኋላ ሴቷ ጓደኛዬ የትዳር ጥያቄ አቀረበልኝ፣ ቀለበት ሊያሥርልኝ፣ ኒካሕ ሊያደርግልኝ ነው ብላ መደሰቷ። ስንት ዓመት ሊተወኝ ይችላል ብላ በመሸማቀቅ ኖራ ይሆን!
ከረጅም ጉዞ በኋላ ጋብቻ በር ላይ ደረሱ፡፡ ይህ በርግጥ ለነርሱ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ የጥሪ ወረቀቱ እንደ አዲስ መሽራ ‹የልጃችን የወጣት እገሌ እና የወይዘሪት ...የጋብቻ ሥነሥርዓት የሚፈፀመው.. .እያለ ይቀጥላል።
የዚህ ዓይነቱ ጋብቻ ምንም ስሜት አይሠጥም፣ ሞገስም የለውም፡፡ ድሮ ጋብቻ ሲባል አብሮ የቆየ ሳይሆን አዳዲስ ፊቶችን ነበር የምናየው፡፡ አቤት ሙሽራና ሙሽሪትን ለማየት የነበረው ጉጉት !.. አሁን ግን ትዳር እራሱ ጣዕሙ ጠፋ፡፡ ቀድመው የተጋቡ ሰዎች ስለሚጋቡ፡፡ የተፈጨን ዱቄት መልሶ መፍጨት፡፡
.
ለሁሉም ግን የዚህ ፅሑፍ ጭብጥ ‹ ከትዳር በፊት … ኖ ጓደኝነት!› የሚል ነውና አትርሱብኝ ለማለት ወደድኩ፡፡
"ከኒካ በፊት አትንካ" ብለዋል,,,,,,,,,,,,,,,,,, ልጆች
አንችም አትንኪ አደራ.. .
ክብርሽ ያለው በእጅሽ ነው
.
በተለይ እህቶቼ አላህ ከማይቋረጡና ተከታትለው ከሚመጡ ከጊዜው ፈተናዎች አላህ ይጠብቃችሁ...አሚን

ምክሩ ለኔም ነው 👌

#share_አድርገህ_የአጅሩ_ተካፋይ_ሁን

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አዲስ ወቅታዊ ሙሃደራ
➖➖➖➖➖➖➖➖

የሙሳ መዳን እና የፊርአዉን መስመጥ ታሪክ!

√ የሙሀረም 10ኛዉ ቀን ክስተት !


🎙አቡ ረይስ ሙሐመድ ኢብኑ ኢማም

=
t.me/abu_reyyis_arreyyis/9817

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

.
⚠️ ማስታወሻ!

🔘 ዓሹራን ለመፆም ያቀዳችሁ!

🗓 መጪው #ሰኞ ሙሐረም 9ኛው እና #ማክሰኞ ደግሞ ሙሐረም 10ኛው [ዓሹራ] ነው።

የዓሹራ ቀን ፆም በሐዲስ እንደመጣው ያለፈውን አንድ ዓመት ወንጀል ያሰርዛል።  አሏህ ይወፍቀን።

📨 ሌሎችን በማስታወስ በአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

وقفة مؤثِّرة:
«ماذا يعني أن ترى الله؟»

🎙لفضيلة الشيخ:
أ.د. صالح سندي -حفظه الله-

ሸይኹ በጣም ከመመሰጣቸው እያለቀሱ ሲያወሩ سبحن الله

#በዩትዩብ ለማየት 👇👇👇
🔗 https://youtu.be/3KT3KsCM3n0?si=jM-jusaD8qeZODJs

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

መውሊድን ማን ጀመረው?
ሺዓዎች ወይስ መሊክ አል-ሙዘፈር

🔊ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔗 t.me/Achachir_mkroch

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

~ ኒፋቅ

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር


t.me/Achachir_mkroch

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ከታሪክ አምባ
(ክፍል አራት)
——————
ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪ ረሒመሁላ፞ህ እንዲህ ይላሉ:—
"በሐጅ ወቅት መካ ውስጥ ነበርኩ። አንድ ከኹራሳን የሆነ ሰው ‘እናንተ ሑጃጆች ሆይ! እናንተ የመካ ሰዎች ሆይ! ነዋሪዎች! መጤዎች! አንድ ሺህ ዲናር የያዘ ከረጢት ጠፍቶብኛል። የመለሰልኝ ሰው አላህ ምንዳውን ይክፈለው። ከእሳትም ነፃ ያድርገው። በምርመራው ቀንም ምንዳና ሽልማት ይኖረዋል’ ሲል ሰማሁት።

በዚህን ጊዜ ከመካ ነዋሪዎች ውስጥ አንድ ትልቅ አዛውንት ተነሳና ‘አንተ ኹራሳናዊ ሆይ! ሃገራችን ሁኔታዋ የከፋ ነው። የሐጅ ቀናት ጥቂት ናቸው። ክብረ በአላቱም ውስን ናቸው። የስራ በሮች ተዘግተዋል። ምናልባትም ይሄ ገንዘብ ከድሃ አማኝ፣ ከትልቅ አዛውንት እጅ ወድቆ ወሮታውን እንድትሰጠው ቃል እንድትገባለት ሊከጅል ይችላልና ገንዘቡን ቢመልስ ትንሽ ሐላል ገንዘብ ትቸረዋለህ ወይ?’ አለ።

ኹራሳኒው:— ስንት ነው ወሮታው? ስንት ይፈልጋል?
አዛውንቱ:— አንድ አስረኛ ይፈልጋል። መቶ ዲናር። የአንድ ሺው 10%።
ኹራሳኒው:— አልተስማማም። ‘አላደርገውም። ይልቅ የዚህን ሰውዬ ጉዳይ ወደ አላህ አስጠጋለሁ። በምናገኘውም (የቂያማ) ቀን ወደሱው እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን፣ ያማረ የሆነ መመኪያ’ አለ።"

ኢብኑ ጀሪር አጦ፞በሪ ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ድሃ ሰው የተባለው ይሄ ሽማግሌ መሰለኝ። ምናልባትም የዲናሮቹን ከረጢት አግኝቶት ከሱ ትንሽ ፈልጎ ነው። ተከተልኩት። ወደቤቱ ተመለሰ። እንደጠረጠርኩት ነበር።

‘ሉባባ ሆይ!’ ብሎ ሚስቱን ሲጣራ ሰማሁት።
‘አቤት የጊያሥ አባት!’ አለች።
‘የገንዘቡን ባለቤት እያፈላለገ ሲጣራ አገኘሁትኮ። ላገኘለት ሰው ምንም ሊሰጥ አይፈልግም። ከሱ ላይ መቶ ዲናር ስጠን ብየው ነበር። እምቢ ብሎ ጉዳዩን ወደ አላህ አስጠጋ። ምን ባደርግ ይሻላል ሉባባ? የግድ መመለስ አለብኝ። እኔ ጌታዬን እፈራለሁ። ወንጀሌ እንዳይደራረብ እሰጋለሁ’ አለ።
በዚህን ጊዜ ሚስቱ እንዲህ አለች:— ‘ሰውየ! እኛኮ ካንተ ጋር ከአምሳ አመት ጀምሮ በድህነት እየማቀቅን ነው። አራት ሴት ልጆች፣ ሁለት እህቶች፣ እኔ፣ እናቴ አለን። አንተ ዘጠነኛችን ነህ። ፍየል የለን፣ የግጦሽ ቦታ የለን። ገንዘቡን ሁሉንም ውሰድ። ተርበናል አጥግበን። ያለንበትን ታውቃለህ አልብሰን። ምናልባትም አላህ — ዐዘ ወጀለ— ከዚያ በኋላ ያብቃቃህ ይሆናል። ያኔ ቤተሰብህን ካበላህ በኋላ ገንዘቡን ትሰጠዋለህ። ወይ ደግሞ በትንሳኤ ቀን እዳህን አላህ ይከፍልልሃል’ አለች።

ሰውየው:— ሉባባ ሆይ! እድሜዬ 86 አመት ከደረሰ በኋላ ሐራም ልበላ ነው? ድህነቴን ይህን ያክል ከታገስኩ በኋላ አካሌን በእሳት ላቃጥል? ለቀብሬ ከቀረብኩ በኋላ የኃያሉን ቁጣ በራሴ ላይ ላስወስን? በፍፁም አላደርገውም ወላ፞ህ!’ አለ።"

ኢብኑ ጀሪር እዚህ ላይ እንዲህ ይላሉ:— "የዚህ ሰውዬና የሚስቱ ነገር እያስደነቀኝ ተመለስኩኝ። በነጋታው ያ የዲናሮቹ ባለቤት ልክ እንደ ትላንቱ ሲጣራ ሰማሁት። ያ አዛውንት ተነሳና
‘አንተ ኹራሳናዊ! ትላንት ያልኩትን ብዬህ መክሬህ ነበር። ሃገራችን ወላ፞ሂ አዝመራውና እላቢው የቀለለ ነው። ገንዘቡን ያገኘው ሰው ሸሪዐን እንዳይፃረር ትንሽ ገንዘብ ብትሰጠው፤ ላገኘው ሰው መቶ ዲናሮችን ስጠው ብልህ እምቢ ብለሃል። ገንዘብህ አላህን — ዐዘ ወጀለ— ከሚፈራ ሰው እጅ ላይ ቢወድቅ በመቶው ፋንታ አስር ዲናሮችን ብቻ ብትሰጠው ምናለበት? እነሱንም ይሰትራቸዋል፣ ይሸፍናቸዋል፣ ቀለብም ይሆናቸዋል’ አለ።
ኹራሳናዊው:— ‘አላደርገውም። ገንዘቤን ከጌታዬ ዘንድ እተሳሰበዋለሁ። በትንሳኤ ቀንም ወደሱ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው’ አለ።"

"በቀጣዩም ቀን የዲናሮቹ ባለቤት እንደቀደሙት ቀናት ጥሪውን አስተጋባ። አሁንም ያ ሽማግሌ ተነሳና እንዲህ አለ:—
‘አንተ ኹራሳናዊ! የመጀመሪያ ቀን ላይ ገንዘቡን ላገኘው ሰው መቶ ዲናር ስጠው ብዬህ እምቢ ብለሃል። ከዚያ አስር አልኩህ እምቢ አልክ። እሺ አንድ ዲናር ብትሰጠውና በግማሿ የሚፈልጋትን ነገር ቢሸምት፣ በግማሿ ደግሞ የሚያልባት ፍየል ቢገዛና ሰዎችን እያጠጣ ገቢ ቢያገኝ፣ ልጆቹን እያጠጣም ምንዳውን ቢያስብ ምናለበት?’
ኹራሳናዊው:— ‘አላደርገውም። ለአላህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በቂያማ ቀንም ከጌታዬ ዘንድ እከሰዋለሁ። እሱ ነው በቂያችን ምን ያማረ የሆነ መመኪያ ነው።’
ሽማግሌው:— ሰውየውን ልብሱን ጎተተውና ‘ና ተከተለኝ። ዲናሮችህን ውሰድና ሌሊቱን እንድተኛ ተወኝ። ይህንን ገንዘብ ካገኘሁበት እለት ጀምሮ ሰላም አላገኘሁም’ አለ።

ኢብኑ ጀሪር ቀጥለው እንዲህ ይላሉ:— "ባለ ዲናሩ ሰውየ ከሽማግሌው ጋር ሄደ። ተከተልኳቸው። ሽማግሌው ከቤቱ ገባ። መሬት ቆፍሮ ዲናሮቹን አወጣና ‘ገንዘብህን ውሰድ። አላህን ይቅር እንዲለኝና ከትሩፋቱ እንዲለግሰኝ እለምነዋለሁ’ አለ።”
ኹራሳናዊው:— ተቀበለና መውጣት አሰበ። በሩ ጋር ሲደርስ እንዲህ አለ:— ‘አንተ አዛውንት ሆይ! እኔ አባቴ ሶስት ሺህ ዲናር ትቶ ሞቷል፣ አላህ ይዘንለትና። እና ‘ሲሶውን አንተ ይበልጥ ይገባዋል ለምትለው ስጥ’ ብሎኝ ነበር። በዚህ ከረጢት ውስጥ ያስቀመጥኩት ለሚገባው ለመስጠት ነው። በአላህ ይሁንብኝ! ከኹራሳን ከወጣሁ ጀምሮ እዚህ እስከምደርስ ድረስ ካንተ የበለጠ የሚገባው ሰው አላየሁም። ስለዚህ ውሰደው አላህ ይባርክልህና። አማናህን ስለተወጣህ፣ በድህነትህ ላይ ስለታገስክ አላህ በመልካም ይመንዳህ’ አለና ገንዘቡን ትቶ ሄደ። ሽማግሌው ተነስቶ አላህን እየተማፀነ ማልቀስ ያዘ። እንዲህም አለ:— ‘የዚህን ገንዘብ ባለቤት (ሟቹን) በቀብሩ ውስጥ አላህ ይዘንለት። በልጁም ይባርክለት።’

ምንጭ:— ጀምሀረቱል አጅዛኢል ሐዲሢያ፞ህ: 251]

ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል:—
{ذَلِكُمْ يُوعَظُ بِهِ مَنْ كَانَ يُؤْمِنُ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ وَمَنْ يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَلْ لَهُ مَخْرَجًا (٢) وَيَرْزُقْهُ مِنْ حَيْثُ لَا يَحْتَسِبُ وَمَنْ يَتَوَكَّلْ عَلَى اللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُ إِنَّ اللَّهَ بَالِغُ أَمْرِهِ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لِكُلِّ شَيْءٍ قَدْرًا} [الطلاق: ٢، ٣].
"ይህ በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምን የሆነ ሰው ሁሉ በእርሱ ይገሰፅበታል። አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል። ከማያስበውም በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል። በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው። አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው። አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አድርጓል።" [አጦ፞ላቅ: 2–3]

/channel/IbnuMunewor
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ዱኒያ እንደ ህልም ናት፣ የምንወደውን ህልም ስናይ ከእንቅልፋችን መንቃት ባንፈልግም እንኳ ድንገት ልንነቃ እንችላለን

ከነቃን በኃላ የጀመርነውን ህልም ዳግም ተኝተን መቀጠል አንችልም በዱኒያም ስንኖር ፀጋዋ የቱንም ያህል ቢያረካም ወደ አኼራ የምንሄድበት ቀን ስለማናውቀው ከህልም የተለየ ስሜት የላትም።
ይሉናል
   ኢማሙ ገዛሊ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አስገራሚ አስተማሪ ድንቅ ታሪክ ተቆራርጦ ነው ቀሪው ከታች ተለቆዋል

በወንድም ሱልጣን (🌷ሀፊዘሁላህ)🌹

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

📖 ከሱረቱል ኢስራእ የተወሰኑ አንቀፆች፤ 1 - 17።

🎙በአቡ ረይስ ሙሐመድ ብኑ ኢማም

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ስለድግምትና ቡዳ የመሳሰሉትን አስመልክቶ ምርጥ ትምህርት

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ርብርብ ለጋራ ግብ
~
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

በዚህ የብዙ ሴቶች አለባበስ በተበላሸበት ዘመን ጂልባብ እና ኒቃብ መልበስ እየፈለጉ በችግር ምክንያት ያን ማድረግ ካቃታቸው እህቶች ጎን መቆም ድንቅ ስራ ነው።
ችግሩን ለመቅረፍ የበኩላችንን እንወጣ ዘንድ ይመለከተኛል የሚልን በሙሉ አካታች የሆነ ሰፊ ሀሳብ ይዘንላችሁ መጥተናል። ይህም የጂልባብ እና የኒቃብ ባንክ መክፈት ነው። ስራዉን በሚሰሩ ወይም በሚመለከታቸዉ እህቶች ስም የባንክ አካውንት የተከፈተ ሲሆን  
1. ገንዘብ በማሰባሰብ ኒቃብና ጅልባብ መግዛት፣
2. ቅያሪ ኒቃብና ጅልባብ ኖሯቸዉ መስጠት ለሚፈልጉ እህቶች ያሉበት ሰፈር ድረስ ሄዶ በመቀበል ለተቸገሩ እህቶቻችን ማድረስ ናቸው።

የድርሻችንን እንወጣ። በችግር ምክንያት መልበስ ላልቻሉ እህቶቻችን እንድረስላቸው።

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ➛ 1000588690486
Hikma and/or Ahlam and/or Muhiba

ለየትኛውም ሀሳብ፣ አስተያየት፣ ጥቆማና ጥያቄ እነዚህን አማራጮች መጠቀም ትችላላቹ።

እህቶች በዚህ👇
@AhluYeWereilua
@nikab_new_wbetea 

ወንድሞች በዚህ👇
@FuadBezu
@red_one1212

ስልክ 0913666695
         0903939033

የቴሌግራም  ቻናላችን👇
t.me/NikabJilbab

የቴሌግራም  ግሩፓችን 👇
t.me/nikab_jilbab_group

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ሙስሊሞ ወጣቶች ሆይ!

ተው ምክርን ተቀበሉ አለማ ይኑራችሁ ከሱስ ራቁ ፣ፊልም ድራማና ኳስ በመመልከት ላይ ጊዜያችሁን አትጭረሱ።

ወላሂ የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የመከሩንን ምክር ከልባችን ብንሰማና ቦታ ብንሰጠው እንዲህ እድሜያችን ላይ እንደቀለድን አንኖርም ነበር።

አላህዬ ይዘንልን።
አላህ ለኛ ብዙ ወለታ ውሎልን ስናበቀ ቼልሲ ማንችሲተር አርሴናል እያልን የነሱ አፍቃሪ ሆነን መዘውተራችን እጅግ ልብን ያደማል ።

በል ወንድሜ አሁን ንቃ ኢስልምናህን ተማር ቤተሰቦችህንም አስተምር ።

ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ወንድማችሁ አብዱረሒም ሳኒ ነኝ ከአዳማ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

/channel/Muhammedsaniy

የተወዳጁ ዳዒ ሙሐመድ ሳኒ ቻናል

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

{ ۞ أَلَمۡ یَأۡنِ لِلَّذِینَ ءَامَنُوۤا۟ أَن تَخۡشَعَ قُلُوبُهُمۡ لِذِكۡرِ ٱللَّهِ وَمَا نَزَلَ مِنَ ٱلۡحَقِّ وَلَا یَكُونُوا۟ كَٱلَّذِینَ أُوتُوا۟ ٱلۡكِتَـٰبَ مِن قَبۡلُ فَطَالَ عَلَیۡهِمُ ٱلۡأَمَدُ فَقَسَتۡ قُلُوبُهُمۡۖ وَكَثِیرࣱ مِّنۡهُمۡ فَـٰسِقُونَ }

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

"በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡" [ኑር: 24]
⑨ እራስህን በሐላል አብቃቃት (አግባ)። ለቻለ ሰው እንደ ትዳር ከዝሙት መጥጠበቂያ ሰበብ የለም።
(10) ማግባት ካልሆነልህ እስከዚያ ፆም አብዛ። አመጋገብህን አስተካክል። እራስህን ከቦዘኔነት አርቀህ በስራ ጥመድ።
(11) ስለዝሙት አደገኝነት፣ ከዝሙት መራቅ አላህ ዘንድ ስላለው ደረጃ አንብብ፣ አዳምጥ፣ አስታወስ።
~~~
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 19/2010)
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…
Subscribe to a channel