gfyygy | Unsorted

Telegram-канал gfyygy - አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

883

ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot

Subscribe to a channel

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የሰለፎች ሁኔታ በረመዷን

«ክፍል» 01-

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

t.me/Binit_Seid_Al_kelaliya

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ቆየት ካሉ የጁሙዐ ኹጥባ

↶⊱ احْذَرْ الشِّرْكَ قَبْلَ رَمَضَانَ

⊰ከረመዷን በፊት ሺርክን ተጠንቀቅ !!

🕌 ደሴ አል አዝሓር መስጂድ

[شعبان/٢٠ /١٤٤٢]

🎙በአቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም

=
t.me/abu_reyyis_arreyyis/9172
t.me/abu_reyyis_arreyyis/9172

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የፍቅረኛሞች ወይስ የዝሙተኞች ቀን?!
፧??፧          ፧??፧          ፧??፧
"መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ" እንደሚባለው ዝሙትን አሰማምረው ስሙን ቀይረው ያበረታታሉ። ነጭ ነጩን ስናወራ ቅር አይበላችሁ!። ሺርኩን ሺርክ ነው፣ ቢድዓውን ቢድዓ ነው፣ ሀራሙ ስሙን ቀያይሮ ሲመጣም ሀራም ነው ስንል ቅር ሊላችሁ አይገባም!፣ እውነታውን መቀበል ነው። የዝሙተኞችን ቀን ስሙን ቀያይረው የፍቅረኛሞች ቀን ቢሉ ያው በኒካህ ያልተሳሰሩ ተቃራኒ ፆታዎች  “ያለ ኒካህ የተፋቀርንበትን ቀን ታሳቢ አድርገን አብረን እንዝናና አብረን እንደር” ተብሎ ዚና የሚሰራበት በዚህ አመለካከት ለተዘፈቁ ሰዎች የዝሙተኞች ቀን እንጂ የተለየ ነገር የለውም።

ምናልባትም አንዳንድ ሰዎች “የዚና ቀን ለማለት ይከብዳል” በማለት ድክም ያለች ምክንያት ያነሳሉ፣ ምክንያታቸውም "ተፋቅረው ወደ ኒካህ የሚሄዱ አሉ፣ ስለዚህ ያንን ቀን ቢያከብሩት ምንችግር አለው?!" የሚሉና ሌሎችንም መሰል ምክንያቶች የሚያነሱ አይጠፉም። ሲጀመር ከኒካህ በፊት መፋቀር ሚባል ነገር የለም!። እስቲ የሚከተሉትን ነጥቦችን እንመልከት:-

①, ቀኑ ስያሜውን ያገኘውና መከበር የጀመረው በማን እና መቼ ነው? ካልን፣ ያው በከሀዲ ፈረንጆችና በዝሙተኞች ከሚል መልስ የተለየ ነገር አናገኝለትም። ሌሎችም በነሱ ቀንተው ነው “ፍቅረኛዬ” ወይም ሴትና ወንድ ሆነው እያለ “ጓደኛዬ” በሚል ስም በዝሙት ሲንዘላዘሉ ቆይተው መጀመሪያ የተገናኙበት ቀን ታሳቢ በማድረግ ይህን ቀን የሚያከብሩት። ይህ ታዲያ የዝሙተኞች ቀን ለመሆኑ ዋና ማሳያ ነው።

②, በእለቱ በተለየ መልኩ ወጣቱን ለዝሙት ይበልጥ የሚያነሳሱ ተግባሮች ይከናወኑበታል። በማህበራዊና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን እያነሱ ወጣቱን ትዳር ከሚባለው ነገር አርቀው “ፍቅረኛሞች” በሚል የዝሙት ህይወት እንዲኖር ያበረታቱታል።

③, በስርኣቱ ሸሪዓ እንደሚያዘው ኒካህ አድርገው ቢሆን ኖሮ የኒካህ ቀን ብለው ነበር የሚሰይሙት እንጂ የፍቅር ቀን ብለው አይሰይሙትም ነበር፣ ምክንያቱም በእስልምና መፋቀር ከኒካህ በኋላ ነው። ይህም ቢሆን እስልምና እውቅና ያልሰጠው ሌላኛው የቢድዐ ተግባር ሆኖ ሀራም ይሆናል።

④, ሌላው የጀመሩት አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ናቸው። በአይሁድና ክርስቲያን መመሳሰል ደግሞ ወንጀሉ የከፋ ነው። ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) "በሰዎች የተመሳሰለ ሰው እርሱ ከነርሱ ነው" ብለዋል። ሰዎች ማለት አይሁድና ክርስቲያኖች ማለት ነው።

⑤, ሰዎች ከትዳር ርቀው "ፍቅረኛዬ፣ ወንዱ ሴት ጓደኛዬ፣ ሴቷም ወንድ ጓደኛዬ" እየተባባሉ በዝሙት እንዲቆዩ ለዝሙትና ለዚህ ሸሪዓን ለጣሰ ግንኙነት እውቅና መሰጠትም ነው። በሸሪዓችን ያለ ኒካህ የተቃራኒ ፆታ ጓደኝነት የሚባል ነገር ሀራም (ክልክል) ነው!!

እንዲህ ያሉ ከባባድ ወንጀሎችን ምንም ያህል ስማቸውን እየቀያየሩ የተፈቀዱ በማስመሰል ሙስሊሙ ዘንድ ቢያቀርቧቸውም፣ ያው ወንጀል ከመሆናቸውና ሀራም ከመሆናቸው የሚቀየሩ ነገር የለም።

የአላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ አስካሪ መጠጥ ሲናገሩ "ያለ ስሙ ይጠሩታል…" ብለው ነበር፣ እንዳሉትም አስካሪ መጠጦች ስማቸው እየተቀያየረ ብቅ ሲሉ ዓሊሞች ደግሞ "ስሙ ቢቀያየርም እውነታውን አይቀይርም" እያሉ ሀራምነቱን ለአማኙ ማህበረሰብ ግልፅ እያደረጉ ሙስሊሙም እየተጠነቀቀ ቀጥሏል። ልክ እንደ አስካሪ መጠጡ ሌሎች ከባባድ ወንጀሎችንም ስማቸውን እየቀያየሩ ያለ ስማቸው ቢጠሯቸውም ልንሸነገል አይገባም።

የእስልምና እና የሙስሊሙ ጠላቶች ሙስሊሙ ማህበረሰብ ፈፅሞ የማይደራደርባቸውና እውቅና ሊሰጣቸው የማይችልባቸውን ከባባድ ወንጀሎችን ስማቸውን ቀያይረው እያመጡ በእስልምና ዘንድም እንደ ሀላል (የተፈቀዱ) ለማስመሰል ይሞክራሉ። ይህን ጊዜ ሙስሊሙ ነቅቶ "የስም መቀያየር እውነታን ሊቀይር አይችልምና" ሀራሙን ሀራም ነው እምነታችን አይፈቅደውም ሊላቸው ይገባል።

በምንም አቅጣጫ ከሀዲዎች ቆሻሻና የሸሪዓችን እሴቶችና ድንቅ የሆኑ ስነ-ምግባሮችን ሊንዱብን የሚችሉ ባህላቸውን እኛ ላይ እንዲጭኑብን ልንፈቅድ አይገባም!። በተቃራኒ ፆታዎች ግኑኙነት ዙሪያ የሙስሊሙ ትክክለኛው እምነት፣ ባህልና እሴት ሴትን ልጅ ፍቃደኝነቷ ከተረጋገጠ በኋላ በኒካህ ከሀላፊዎቿ ወስዶ በማግባት በትክክለኛ ውዴታ ተንከባክቦ እያኖሩ ጥሩ ትውልድን ማፍራት ነው።

አላህ ዝሙትን ከሌሎች ከባባድ ወንጀሎች በተለየ መልኩ "ዝሙትን አትቅረቡት!!" ብሎ በሩቁ ነው ያስጠነቀቀው። ይህ ማለት ወደ ዝሙት መጓዝ ይቅርና ጭራሹኑ ወደ ዝሙት መዳረሻ የሆኑ ነገሮች በጠቅላላ የተከለከሉ (ሀራም) ናቸው ማለት ነው።

የዝሙተኞችን (የፍቅረኛሞችን) ቀን እንጠየፍ‼
ሙስሊም የዝሙተኞችን ቀን አያከብርም‼
ለዝሙተኞች ቀንም እውቅና አይሰጥም‼።
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join ያድርጉና ይቀላቀሉ
/channel/IbnShifa
/channel/IbnShifa

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የሻዕባን ወር ሙሉ ወሩን መፆም እንዴት ይታያል?? መልስ የሻዕባን ወሩን ሙሉ አይፆምም የሚፆመዉ የወሩ አብዘሀኛዉ ቀናት ነዉ ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንደነበሩት በሻዕባን ወር ፆም ያበዙ ነበር ነገር ግን ሙሉ ወሩን አይፆሙም ነበር ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ወሩን ሙሉ አልፆሙም ረመضاን ቢሆን እንጅ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّاسُ ٱتَّقُوا۟ رَبَّكُمۡۚ إِنَّ زَلۡزَلَةَ ٱلسَّاعَةِ شَیۡءٌ عَظِیمࣱ }

እናንተ ሰዎች ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ የሰዓቲቱ እንቅጥቃጤ በጣም ከባድ ነገር ነውና፡፡

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ጌታችን ከአርሹ በላይ እንደሆነ አንድሺህ ማስረጃዎችን ከቁርኣን ከሐዲስ ከሰለፎች አግኘተን ስናበቀ እኛም በማስረጃው መሰረት "አዛኙ ጌታች ከዐርሹ በላይ ነው"ስንል " ቆሞ ነው? ተቀምጦ ነው? ተኝቶ ነው? "የሚል በፍልስፍና የታወረ የደነዘዘ መሀይም ተንኮ ጠንሳሽ ከቁርኣንና ከሐዲስ ከሰለፎች ማስረጃ ይልቅ የራሱን ከንቱ ጭንቀላት የሚያስቀድም ወይም የአጥማሚውን ሸይኽ የጥመት መንገድን መርጦ ህዝብ ለማጥመም እንደፀሃይ ፍንትው ብሎ የተገለፀን ሐቅ ለመሸፈን የሚሞክሩ ቦቅባቃዎች እያሉ መች ሰላም እንሆናለን?!!

👉ጥርት ባለው ሰማይ ሙሉ ጨረቃ እየበራ

👉እይታህን እክል ገጥሞት አይንህ ስራውን ባይሰራ

👉"ጨረቃ የለም" እያልክ በከንቱ አትገላገል
👉አለም እያዬው ነውና እውነቱን ከዩ ተቀበል

👉እውነት መቀበል ከሆነብህ ኩራት

👉ተወ! ወንድሜ አትሁን የሐቅ ጠላት

👉መንገድ ለይ ቆመህ በሐቁ ጎዳነ

👉ሰዎችን አትስበክ ወደ ባጢል ወደ ጥመት ጎዳነ


👉ሀዳሁመሏ አጅመዒን!!


/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

☑️ ይቅርታን እንልመድ
〰〰〰〰〰〰〰

በትንሽ ቅራኔ በትንሽ ችግር አንዳንዴም ባልተረጋገጠ ወሬ ምርጥ ጓደኛችን ከነፍሱ በላይ የሚሳሳልን ወዳጃች እንርቃለን። ተቆራረጣለን ቁጭ እንላለን። አንደኛችን ዝቅ ብሎ ይቅርታ ከመጠየቅ ይልቅ የነፍስያ ጣጣና የሸይጧን ግፊት ውስጣችን ሞልቶ ለብዙ ጊዜያት በአይነ ቁራኛ እንተያያለን። ወዳጄ ከሁሉ ነገር የፀዳ ንፁህ ጓደኛ አታገኝም። ከጓደኛህ በኩል የሚከሰት ትንሽዬ ስህተት ከማጉላትና በዛ ላይ ጎሜ ከመያዝ ይልቅ ባላየ እያለፍክ ገፍቶ ከመጣም ይቅር እያልክ ካልሆነ በቀር ከማንም ጋር አብሮ መዝለቅ አትችልም። ለጓደኝነት ከሚከፈል መስዋእትነት አንፃር ዝቅ ብለህ ይቅርታ ብትለው ውርደት ሳይሆን ክብር ነው።

እስቲ ዛሬ በይቅርታና በእዝነት በእኛና በወዳጆቻችን መካከል ያለውን የክፋትና የጥላቻ ድልድይ በመስበር ያስቀየምናቸው አልያም ከመሬት ተነስተው የራቁንን ሰዎች ይቅርታ በመጠየቅና በማቅረብ ፍቅራችንና ወዳጅነታችን እናድስ።

ከይቅርታ በላይ ምንም የለም። ተራርቆ በናፍቆት ከመቃጠል ይቅር ተባብሎ አብሮ መዝለቅ።

ለብዙ ጊዜ የራቀህን ወዳጅህ ሲታረቅህ ያለው ፍቅርና ደስታ አትጠይቀኝ።

↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

እስልምና የሰው ልጅ የነብያት ሁሉ ሀይማኖት እንጂ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የጀመሩት ወይም ለዚህ ኡማ ብቻ የተደነገገ ሀይማኖት አይደለም!!
//

ከእስላም ወጭ የትኛውም ሀይማኖት ተቀባይነት የለውም!! የትኛውም ጂንም ይሁን ሰው አላህን በብቸኝነት ሊያመልክ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነብይነት ሊያምን ከሳቸው ቦኃለ ምንም አይነት መልእክተኛ እንደማይላክ እስላም ትክክለኛና ከእስላም ውጭ ያለ ሀይማኖት ተቀባይነት እንደሌለው የማመን ግዴታ አለበት!!


*ተውሒድ*

ተውሒድ የነብየት ሁሉ የመጀሚሪያ ጥሪ ነው ። ብዙውን ሂይወታቸውን የፈጁትም ተውሒድን በማስተማር መሆኑን የማይካድ ሐቅ ነው።

*ተውሒድ *

ተውሒድ ማለት የሽርክ ተቃራኒ ነው።አንድ ሰው ተውሒድን ጠንቅቆ ካለወቀ ሽርክ የጠቀዋል ።

*ሽርክ*

ሽርክ ማለት የተውሒድ ተቃራኒ ነው ።አንድ ሰው ተውሒድን ከወቀ ተቃራኒውን ሽርክንም ማወቅ የግድ ያስፈልገዋል ።

*ሽርክ *

ሽርክ የዘላለም የጀሀነም ኢሳትን ያስወረሳል ።ሽርክ በዱንያ ላይ እያለ አንድ ሰው ተውበት ካላደረገ በአኼራ በሸፈአም ይሁን በሌሎች ዒበዳዎች ብዛት አይማርም ።በል እንዲያውም ሌሎች ተራራ የሚያክል ዒባዳ ቢሆንም እንኳን ያወድማል ።ሽርክ ስራን በሙሉ የወድማል !!

*ተውሒድ*

ተውሒድ ዘላላማዊ የሆነውን ጀነትን ያስወርሳል ።ተውሒድ የተጣሪዎች የመጀመራ ጥሪም ናት።አንድ ዱዓት የመጀመራ ጥሪውን ተውሒድ ካላደረገ የነብያት መንገድ በግልፅ ተቃርኖዋል።

✍በጥቅልሉ ሁሉም ሰው እስልምናውን የሚኒድበትን (የሚያፈርስበትን)ሽርክን ጠንቅቆ ሊያውቅ ይገባል!! ዲኑን ከበአድ አምልኮ ሊጠብቅ ትንሹንም ትልቁንም የሽርክ አይነት ሊጠነቀቅ ይገበዋል ።

አላህ ከትንሹም ከትልቁም ሽርክ እኛንም ይጠብቀን። ቤተሰቦቻችንንም ዘመዶቻችንንም ጓደኞቻችንንም ይጠብቅልን ።አልሐምዱሊላሂ አለኒዒመቲል እስላም ።!!!!!

ወንድማች አብዱረሒም

ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

✍ቀን 4/2/2012 ላይ የተፃፈ

/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አስ-ሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ አሕሉሱንና

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ጀነት ውስጥ ትልቁ ፀጋ ምንድነው? (አላህ ይህን ከሚጎናፀፉት ያድርገን)

ኢብኑል ቀዪም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል።

"አብዛኛው ሰው ለጀነት ያለው አመለካከት የተሳሳተ ነው፣
ጀነት ማለት ዛፎች ያሉባት፣የተለያዩ ፍራፍሬዎች፣ምግብ፣መጠጥ፣ሑረልዒን፣ወንዞችና ህንፃዎች ለነዚህ ለዛዎች ብቻ የዋለ ስም አይደለም።
ጀነት ማለት ሙሉና ልቅ የሆነች የመጠቃቀሚያ አገር ናት፣
ከመጠቃቀሚያዎች በሙሉ በላጩ ፀጋ፦
የቸሩ አላህን ፊት መመልከት ፣ንግግሩን መስማት፣የጀነት ሰዎች የአይን ማረፊያቸው ከርሱ መቅረብና ውዴታው መሆኑ።
የዚህ ፀጋ (ለዛ)ከመብላት ከመጠጣት ከመልበስ ለዛ ጋር ፈፅሞ ሊነፃፀር አይገባም።"

【መዳሪጁ ሳሊኪን፤2/80】

አላህ ሆይ በራህመትህ ጀነትን ከሚገቡና ፊትህን ከሚያዩ ሰዎች አድርገን!።

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

╭「• አለ ቃል ኪዳንሽ •」
│ ❏ በልቤ ተከትቦ
│ 🏝🔎 ደስ የሚል ግጥም
├───────────
├📲 📝 ኡሙ ፈውዛን
╰——————————
⏸↘️⤵️↙️
#ሰለፍያ____!!!
✍️✍️✍️✍️✍️✍️
አለ ቃል ኪዳንሽ በልቤ ተከትቦ
በመከራ መሀል ደምቆና ተውቦ
ሙሀባሽ እንደ ነርቭ አካሌን ተብትቦ
ብዙውን አለፍኩት ፍቅርሽ ተደራርቦ
አሻግሬ አይቼ የእውነትሽን ልቀት
ከጨለማ ወጣሁ ገዝቶኝ ያንች ድምቀት
☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅
#ሰለፍያ___!!!
ሁሌ በእየለቱ ፍቅርሽ ይጨምራል
ተውሒድና ሱናሽ እጂግ በጣም ያምራል
ሙሉ ማንነትሽ እውነት ይናገራል
ብርሀንሽ በርቀት ጨለማን ያበራል
ሰው ጂን እንስሳትን ህግሽ ያስከብራል
ይሔ ሚስጥርሽ ነው የኔነቴ ሞራል
#ሰለፍያ___!!!
✅⭕️☑️✅⭕️☑️
የኔ መታወቂያ ንፁህ የደም ስሬ
የመንፈሴ እርካታ የእውነት መምህሬ
የጀነት ትኬቴ የሰውነት ክብሬ
ሀዘን ማስወገጃ የደስታ ጂምሬ
ሀቅን ያየሁብሽ ማጉያ መነፀሬ
የالله ስጦታ አንችኮ ነሽ ፍቅሬ
☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️
#ሰለፍያ___!!!
ፍቅሬ ከልቤ ነው ማስመሰል አይደለም
ካንች ተለይቼ ከምኖር ዘላለም
ያንች ሆኘ ልሙት ይድረቅብኝ ቀለም
አስተማማኝ መርከብ በሁለቱም አለም
ሰለፍያ አንች ነሽ ካንች ሌላ የለም
✍️⭕️✅📱☑️↪️📝↩️
#ሰለፍያ__!!!
ሰንት ነገር ገጥሞኝ ባንች ተፅናንቼ
አንች አለሽኝ ብዬ ወደ አንች ገብቼ
ያንች አገልጋይ መሆን ልቤን አስመኝቼ
ምርኮኛሽ ሆኛለሁ እጅ እግሬን ሰጥቼ
ከሽርክ ከቢዲዐ ወደ አንች ቶብቼ
ምንም ብዘገይም እንቅልፌን ተኝቼ
ባለ ማወቅ አለም ብቆይም ዘግይቼ
ሳውቅሽ ገሰገስኩኝ እጂግ ተፀፅቼ
አሁን ግን ያንች ነኝ ፅናት ተመኝቼ
➘➴➘➷➴
#ሰለፍያ___!!!
አካሌ ከርፍቶኝ በወንጀል ጨቅይቼ
የአመፅን ቁልቁለት ዳገቱን ወጥቼ
ጭንቅንቅ ብዬ ሰውነቴን ስቼ
ከሀሳብ ስመለስ ራሴን አንፅቼ
ሀዘኔ ይጠፋል አንችን ተመልክቼ
☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅
#ሰለፍያ___!!!
መጥፎ ነሽ እያሉ ሰወች ሲፀየፉኝ
በጎን እየገፉ በማስመሰል ሲያቅፉኝ
ሀቅን እንዳልሰማ እያደናቀፉኝ
እውነትን ደብቀው ውሸትን ሲያቀብሉኝ
አብሽር በርቺ ጠንክሪ ግፊበት እያሉኝ
በሆነ ባጋጣሚ በሆነ ክስተት
እውነትን ፍለጋ ሁሌም ስንከራተት
ድንገት ቀና ብዬ ሀቅን ስመለከት
አንችን አገኘሁሽ በالله በረከት
✅☑️✅☑️✅☑️✅☑️✅
#ሰለፍያ___!!!
በወንጀል ጨቅይቼ ምን ብሸማቀቅም
አንችን በመምረጤ እኔ አልሳቀቅም
ከቶ ይስጠኝ እንጂ የእውነት ያድለኝ
ፍቅርሽን ዘምሬ ማንም ምንም ቢለኝ
ህዝብ ፊት መንገድ ዳር ቀጥቅጦ ቢገድለኝ
በالله ይሁንብኝ ምንምኮ አይመስለኝ
♻️☑️✅⭕️♻️☑️✅⭕️
#ሰለፍያ__!!!
እውነተኛ ሚዛን የሌለሽ አምሳያ
የስኬትን ሚስጥር አብራርቶ ማሳያ
ጥፍጥናሽ የሚገዝፍ ከማር ከቡቃያ
መታወቂያዬ ነሽ ጥምጣምም ኮፍያ
ከህይወት በላይ ነሽ ደዕዋ ሰለፍያ!!!

📝 በኡሙ ፈውዛን

/channel/AbuImranAselefy
/channel/AbuImranAselefy
/channel/AbuImranAselefy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ሡፍያን አስ–ሰውሪይ እንዲህ ይላሉ፦

“ሁሉን ቻይ የሆነውን አላህን በመፍራት ላይ አደራህን! ከሰዎች መገለልን አጥበቀህ ያዝ፣ በራስህ ላይ ተጠመድ፣ የአላህን መፅሐፍ (ቁርኣን) መጽናኛ አድርግ።”

📚አልጀርህ ወት–ተዕዲል (1/87)

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

እንጊዲ ይህንን አይቶ ልብካላዘነ ከባድ ነው ።እስኪ በአላህ የምንችለው ለነሱ ዱዓ ማድረግ ነው በደንብ በዱዓ እናስታውሳቸው

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🍁ሁሉ ፀጋ ተወጋጅ ነው፡ የጀነት ሰዎች ፀጋ ሲቀር🌴

🍁ሁሉ ጭንቀት ተወጋጅ ነው፡ የጀሀነም ሰዎች ጭንቀት ሲቀር🌴

✨ #ሀሰነል_በስሪይ✨ 

🍁ጠፊና ተወጋጅ በሆነው በዱንያ ብልጭልጭ ሳንሸወድ፡ ዘውታሪ የሆነውን አኼራን ሁሌም እናስታውስ፡ ለሱም እንዘጋጅ🌴

قال الحسن البصري :
‏" كلُّ نعيمٍ زائل ، 
‏إلا نعيمُ أهلِ الجنَّة ،
‏وكلُّ غـمٍّ زائل ،
‏إلا غـمُّ أهـلِ النار ".

‌‏📚 المجالسة وجواهر العلم/١٥٩١

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አንብቡ ሼር አድርጉ
☞መፍትሄዉ ምንድን ነዉ ?

#ጥያቄ ፦

☞ወጣት ነዉ ፡ ሱብሂ ሶላት መስጂድ ሄዶ በጀመዐ ለመስገድ ይሞክራል ፡

ችግሩ ፦ ከእንቅልፉ ይነሳና ነገር ግን መቆም ይከብደዋል

☞መፍትሄው ምንድን ነዉ ።

#መልስ ፦

☞ለዚህ ለጠያቂው ወንድሜም ይሁን እንደሱ አይነት ላሉ ሰዎች ምክሬ ፡ በጊዜ እንዲተኛ ነዉ ፡ ከዛ በሇላ በሚነሳ ጊዜ በፍጠነት [ከአልጋዉ] ላይ ይቁም

☞ምክንያቱም ፦ኢማም ሙስሊም በሶሂሀቸዉ ላይ በዘገቡት ሀዲስ
አዒሻ [ረዲየሏሁ አንሀ] ስለ ረሱል [ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም] የእንቅልፍ አነሳስ ስትናገር እንዲህ አለች ፦ [#በፍጥነት ይቆማሉ]

ይህን የአዒሻን ንግግር የዘገበዉ ሰዉ ሲናገር እንዲህ ይላል ፦ [ወላሂ አዒሻ #ይቆማሉ አይደለም ያለችዉ ፡ እሷ ያለችዉ #በፍጥነት_ይቆማሉ]

☞አንተም ከእንቅልፍ የሚያነሳህን [አላርምህን] ስትሰማ በፍጥነት ቁም ፡ አንተ በአሏህ ታግዘህ በፍጥነት ከቆምክ አሏህም ያግዝሀል ።

☞ሸይኽ ኢብን ኡሰይሚን [አሏህ ይዘንላቸዉ]

ምንጭ ☞አሊቃዑ አሻህሪይ [3]

✍አቡል ቡኻሪ ኡመር ባህረዲን

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🔃አድስ ተከታታይ ሙሃደራ
  ➖➖➖➖➖➖➖➖

📚ርዕስ፦ተውሂድ የስኬት ምንጭ ነው

🕌ወረባቦ ቀበሌ 18 ታች ሚሽንጋ

🎙Abu reyyis Ibnu imam

➲/channel/abu_reyyis_arreyyis/7212

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

«መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ነው።» እያልክ ልትናገር ድፍረቱ ይኖርሃልን ከፊታቸው ብትሆን??
~~~~

ውዱ ወንድማችን Ibnu Munewor ሐፊዘሁላህ «ተቅዋ» በተሰኘው ሙሃደራው ላይ ከተናገው ንግግር ለሁላችንም አንድ ጥያቄ ጠይቆን ነበር ...

እንዲህ ብሎ: –

«..... ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ቢድዓ ገና ከፊታቸው በሌለበት ነበር ጠዋት ማታ (ስለቢድዓ አስከፊነት) የሚቀጠቅጡት።
فيما رواه جابر ابن عبد الله رضي الله عنه ....
”كان رسول الله صلى الله عليه وسلم اذا خطب احمرت ايناه ....

(ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳወራው) :–
« መልእክተኛው صلى الله عليه وسلم ኹጥባ ሲያደርጉ ..... (ምንድን ነበሩ?)
‘احمرت ايناه’
አይኖቻቸው ይቀሉ ነበር።
‘وعلا صوته‘
ድምፃቸው ከፍ ይል ነበር።
‘واشتدت غدبه‘
ቁጣቸው ይከፋ፣ ይበረታ ነበር። አለ።

ሱብሓነላህ! (....)

’كانه منذر جيش‘
ልክ ሰራዊት እንደሚያስጠነቅቁ
’صبحكم ومساكم‘
ማታ መጣባችሁ፣ ጠዋት መጣባችሁ።
ግዙፍ ሰራዊት የሚጨርስ፣ የሚያጭድ እየመጣ ነው ያለው። ጠዋት ነው የሚደርሰው። ነገ ጠዋት። ነገ ማታ። እያሉ የሚያስፈራሩ (የሆነ) አስፈሪ የሆነ አቀራረብ ነበር የነበራቸው።

ተመልከቱ! እንዲህ አይነት አስፈሪ የሆነ አቀራረብ ይዘው ግን የሚያስፈራሩት ስለምንድን ነበር? ...
የተለመደውን ኹጥባ ‘ኢነል ሐምደ ሊላህ ..’ ብለው ከጨረሱ በኋላ ...

وخير الهدى هدى محمد (صلى الله عليه وسلم) ...
#وشر_الاُمور_محدثاتها ،

ከነገር ሁሉ ክፉ ማለት መጤዎች ናቸው። አሉ (በዲን ውስጥ) ። በዲን ውስጥ ክፉ ማለት መጤዎች ናቸው።
ልብ ይበሉ! እንደዛ እየተቆጡ፣ እንደዛ አይናቸው ቀልቶ፣ ድምፃቸው በርትቶ፣ ቁጣቸው ከፍቶ እየተናገሩ እያለ ...
«መውሊድ ጥሩ ቢድዓ ነው።» እያልክ ልትናገር ድፍረቱ ይኖርሃልን ከፊታቸው ብትሆን???

ይኖርሃል እንደዚህ አይነት (ድፍረት)??

ፍፁም ሊሆን አይችልም!! ....»

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

😥😥😥

"ውሀ ላምጣ ብሎ ሀይላንድ ይዞ ነው የሄደው" #እናት
" እማዬ እማዬ እያለ እያለቀሰ አይተነዋል" #ልጆች

አንዲት ጎዳና ላይ ሶፍት የምትሸጥ ምስኪን እናት የልጇን ፎቶ ይዛ እያለቀሰች "ልጄን አይታችሁታል?ጠፋብኝ...6ቀን ሆነው" እያለች ጣፎ መንገድ ላይ ያገኘችውን ሰውሁሉ እየጠየቀች ያየቻት ልበመልካም ወደኛ ልካታለች!!

ህፃኑ #በረከት_ሰለሞን ይባላል!ሀሙስ ጥር30 የሚጠጡትን ውሀ በሀይላንድ "ቀድቼ ልምጣ" ብሎ ከአጠገቧ ተነስቶ ሄዶ ሳይመለስ ቀርቷል!!

ታማሚ ታናሽ እህቱን ጨምራ እየታመመች በስቃይ ብቻዋን የምታሳድጋቸው እናት "ልጄ ምን ሆነ"ብላ ጭንቅ ላይ ናት!እባካችሁን #ሼር በማድረግ እናፋልጋት🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#ባይሽ_ኮልፌ_በጎ_አድራጎት
0927320571-ዝናሽ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ኡኽታ!!

ሒጃባሽ አላህ ባዘዘሺይ ኡንጋ በለበሺ
ጌሳ በአኼራ ሰብነታሽ ጅራ ላይነቺ እትክላከልንሻን
ኮፒ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አንተ ያመጣኸውን ቢድዓ አርክሶ ሱናውን የሚያነግስከንቱ አስተሳሰብህን ገርስሶ ሸሪዓን የሚያልቅ፤ ለጥቅም ብለህ በዲን ስታጭበረብር ጉሮሮህ ላይ ቆሞ የዲኑን አስተምህሮት የሚያስቀድም ጀግና አይጠፋም።

እናም ተስፋ ቁረጥ!!!

⚙ 📝 أَبُـــو عِـمْــرَان ❨𝕒𝕓𝕦 𝕚𝕞𝕣𝕒𝕟❩

🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣ 
╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
/channel/AbuImranAselefy
/channel/AbuImranAselefy
/channel/AbuImranAselefy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🌹 አል-ሐሰን እንዲህ ብለዋል፡-

ለአንድ ሙእሚን የሚወደውን ሰው አላህን ሲታዘዝ ከማየት በላይ ለአይኑ መርግያ(አስደሳች) የሆነ ነገር የለም።

📖صحيح البخاري(١٧٨٣/٤)

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

እስልምና  የሰው ልጅ  የነብያት  ሁሉ  ሀይማኖት እንጂ  ነብዩ  ሶለላሁ  ዐለይሂ  ወሰለም  የጀመሩት  ወይም    ለዚህ  ኡማ  ብቻ  የተደነገገ  ሀይማኖት  አይደለም!!
//

ከኢስላም   ወጭ  የትኛውም  ሀይማኖት  ተቀባይነት   የለውም!!  የትኛውም  ጂንም  ይሁን ሰው   አላህን  በብቸኝነት  ሊያመልክ  በነብዩ  ሶለላሁ  ዐለይሂ  ወሰለም  ነብይነት  ሊያምን  ከሳቸው  ቦኃለ  ምንም  አይነት መልእክተኛ   እንደማይላክ  እስላም  ትክክለኛና  ከኢስላም  ውጭ  ያለ  ሀይማኖት  ተቀባይነት  እንደሌለው  የማመን  ግዴታ  አለበት!!


*ተውሒድ*

ተውሒድ  የነብየት ሁሉ  የመጀሚሪያ ጥሪ  ነው ።  ብዙውን  ሂይወታቸውን  የፈጁትም  ተውሒድን  በማስተማር  መሆኑን  የማይካድ  ሐቅ ነው።

*ተውሒድ *

ተውሒድ   ማለት  የሽርክ  ተቃራኒ  ነው።አንድ  ሰው   ተውሒድን  ጠንቅቆ  ካለወቀ    ሽርክ  ያጠቀዋል ።

*ሽርክ*

ሽርክ  ማለት  የተውሒድ  ተቃራኒ  ነው ።አንድ  ሰው ተውሒድን  ከወቀ  ተቃራኒውን  ሽርክንም  ማወቅ  የግድ  ያስፈልገዋል ።

*ሽርክ *

ሽርክ  የዘላለም  የጀሀነም   ኢሳትን  ያስወርሳል ።ሽርክ  በዱንያ  ላይ እያለ  አንድ  ሰው  ተውበት  ካላደረገ  በአኼራ   በሸፈአም  ይሁን በሌሎች  ዒበዳዎች  ብዛት  አይማርም ።በል  እንዲያውም  ሌሎች  ተራራ  የሚያክል  ዒባዳ ቢሆንም  እንኳን  ያወድማል ።ሽርክ  ስራን  በሙሉ  የወድማል !!

*ተውሒድ*

ተውሒድ  ዘላላማዊ   የሆነውን  ጀነትን  ያስወርሳል ።ተውሒድ  የተጣሪዎች  የመጀመራ  ጥሪም  ናት።አንድ  ዱዓት   የመጀመራ  ጥሪውን  ተውሒድ  ካላደረገ  የነብያት  መንገድ  በግልፅ  ተቃርኖዋል።

✍በጥቅልሉ    ሁሉም  ሰው  እስልምናውን  የሚንድበትን (የሚያፈርስበትን)ሽርክን  ጠንቅቆ  ሊያውቅ  ይገባዋል!! ዲኑን ከበአድ  አምልኮ   ሊጠብቅ  ትንሹንም  ትልቁንም  የሽርክ  አይነት  ሊጠነቀቅ  ይገበዋል ።

አላህ  ከትንሹም ከትልቁም  ሽርክ እኛንም ይጠብቀን።  ቤተሰቦቻችንንም  ዘመዶቻችንንም  ጓደኞቻችንንም  ይጠብቅልን ።አልሐምዱሊላሂ  አለኒዕመቲል   ኢስላም ።!!!!!

ወንድማችሁ  አብዱረሒም  ሳኒ አቡ ኡካሻ ነኝ ከውቢቷ አዳማ

ወሰላሙ  ዐለይኩም  ወረሕመቱላሂ  ወበረካቱሁ

✍ቀን 4/2/2012  ላይ  የተፃፈ

/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🔖ኢስላማዊ የወር አቆጣጠር ቅደም ተከተል፡-
➀ ኛ ወር- ሙሐረም
⓶ኛ ወር- ሰፈር
➂ኛ ወር- ረቢዑል-አወል
⓸ኛ ወር- ረቢዑ-ሣኒ
➄ኛ ወር- ጀማዱል-አወል
➅ኛ ወር- ጀማዱ-ሣኒ
➆ኛ ወር- ረጀብ
⓼ኛ ወር- ሻዕባን
➈ኛ ወር- ረመዷን
➀⓪ኛ ወር- ሸዋል
➀➀ኛ ወር- ዙል-ቀዒዳህ
➀⓶ኛ ወር- ዙል-ሒጃህ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

'ቤቲንግ'
~
ቁማር በኢስላም የተከለከለ ነው። በሐራም ስራ ላይ መሰመራትም መተባበርም አይፈቀድም። ስለዚህ የቁማር (betting) ቤት መክፈት፣ ቁማሩ ላይ መሳተፍ፣ ለአቋማሪዎች ቤትን ማከራየት፣ ከነሱ ዘንድ ተቀጥሮ መስራት፣ በየትኛውም መልኩ ለቁማሩ ስራ /ቤት ድጋፍ መስጠት አይፈቀድም።
{وَتَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلۡبِرِّ وَٱلتَّقۡوَىٰۖ وَلَا تَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلۡإِثۡمِ وَٱلۡعُدۡوَ ٰ⁠نِۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِیدُ ٱلۡعِقَابِ }
"በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ። ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ። አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።" [አልማኢዳህ፡ 2]

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ለዱዓህ ምላሽ ቶሎ ባታገኝ ራሱ
ዱዓእ ትልቅ ዒባዳ መሆኑን እወቅ ለዒባዳኮ አላህ ወፍቆሃል ማለት ነውኮ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ያ የቁጭት ቀን ከመምጣቱ በፊት ዛሬን እንጠቀምበት
~
ሶደቃ የብዙ በላእ መመከቻ ሰበብ ነው። ለዱንያም፣ ለአኺራም፣ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ... የሚሻገር ብዙ ፋይዳዎች አሉት። መታከሚያ ያጡ ህመምተኞች፣ ዱንያ ጨልማባቸው ጎዳና ላይ የወደቁ ጎስቋሎች፣ የሚላስ የሚቀመስ ያጡ ሞት ሸሽተው ሜዳ ላይ የፈሰሱ ተፈናቃዮች፣ ተዘርፈው አገራቸው መግቢያ ያጡ መንገደኞች፣ ገቢ የሚያስገኝ ስራ አጥተው ሃሳብና ጭንቀት የወረሳቸው ምስኪኖች፣ ለያዙት ጨቅላ ጡት የሚሆን ነገር ያጡ አራሶች፣... በየጥጋጥጉ አሉ። በመሰል ቦታዎች ላይ ትንሽም ብትሆን የሶደቃ ድርሻ ይኑረን።
* ይህ ሲሆን ለወገን የመቆርቆር ስሜት እናዳብራለን። ይህንን ስሜትኮ ብዙዎቻችን አጥተነዋል።
* የአእምሮ ሰላም እናገኛለን። ይህንን አላህ ያደለው ብቻ ነው የሚያውቀው።
* የመስጠትን ባህሪ እያዳበርን እንሄዳለን። ሰውነት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚጎለብተው ልብም ኸይር ስራን በማዘወተር ይጎለብታል። መስጠትን ስናዘወትር መስጠት ባህሪያችን ይሆናል። ስንርቅ ከልባችን ይርቃል። ልባችንም ይደርቃል። ስለዚህ በሶደቃ ልባችንን እናክም።
* ከነገ ፀፀት ለመትረፍ ሶደቃ እናብዛ። ሰዎች በፀፀት እሳት ከሚቃጠሉባቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ "ምነው ጥቂት እድሜ አግኝቼ ሶደቃ ባደረግኩ?!" የሚል ነው። ሁሉን አዋቂው ጌታ እንዲህ ይላል፦
{ وَأَنفِقُوا۟ مِن مَّا رَزَقۡنَـٰكُم مِّن قَبۡلِ أَن یَأۡتِیَ أَحَدَكُمُ ٱلۡمَوۡتُ فَیَقُولَ رَبِّ لَوۡلَاۤ أَخَّرۡتَنِیۤ إِلَىٰۤ أَجَلࣲ قَرِیبࣲ فَأَصَّدَّقَ وَأَكُن مِّنَ ٱلصَّـٰلِحِینَ }
"አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና 'ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድሆን ዘንድ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ' ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።" [አልሙናፊቁን፡ 10]

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🔖ኢስላማዊ የወር አቆጣጠር ቅደም ተከተል፡-
➀ ኛ ወር- ሙሐረም
⓶ኛ ወር- ሰፈር
➂ኛ ወር- ረቢዑል-አወል
⓸ኛ ወር- ረቢዑ-ሣኒ
➄ኛ ወር- ጀማዱል-አወል
➅ኛ ወር- ጀማዱ-ሣኒ
➆ኛ ወር- ረጀብ
⓼ኛ ወር- ሻዕባን
➈ኛ ወር- ረመዷን
➀⓪ኛ ወር- ሸዋል
➀➀ኛ ወር- ዙል-ቀዒዳህ
➀⓶ኛ ወር- ዙል-ሒጃህ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

3 ነገሮች
~
1ኛ፦ ወገን ልጆቻችሁን እየጠበቃችሁ። የሚስሰማው ሁሉ ሰቅጣጭ ነው። ጥንቃቄ አድርጉ። አላህ ክፉን ይያዝላችሁና የሚገጥመው ስለማይታወቅ ወቅታዊ ፎቶዎችን ያዙ።
2ኛ፦ ዛሬም የባንክ ዝርፊያዎችን መስማታችንን ቀጥለናል። ባለፈው ነካ ባደርግ ጥንቃቄ እንዳደርግ የነገራችሁኝ ወንድሞች ስጋታችሁን የሚያረጋግጥ ነገር ሰምቻለሁ። እና በደፈናው እናገራለሁ። ዝም እንዳይባል የሚቻል ነገር አይደለም። ለማንኛውም ጥንቃቄ ማድረጋችሁን አትዘንጉ። እንኳን ሙሉ ገንዘብ ላይ ስጋት ደቅኖ ቀርቶ የአገልግሎት እያለ የሚቆርጠውን እንዲያቆም መንቀሳቀስ ይገባ ነበር።
3ኛ፦ Ethio telecom የጥሪ ማሳመሪያ የምትሉት ነገር በጣም ነው የሚረብሸው። ለምን አትተውንም? ሰው ያለ ምርጫው በስህተት መልእክታችሁን እንዲቀበል አመቻችቶ መላክ ፣ ከዚያም እሱን ሰበብ በማድረግ በየወሩ ብር መቁረጥ ምንድነው ስሙ? ቴሌን የሚያክል ትልቅ ድርጅት እንዴት እንዲህ ያለ የአጭበርባሪ ነጋዴ ስራ ይሰራል? እየታፈረ እንጂ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ምክር ለተገሳፆች ከዑለሞቻችን አንደበት~8
♣②②•ሸይኽ_ፈውዛን ሐፊዞሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«አቂዳው የተበላሸ ሰው በዱንያም በአሔራ ከሳሪ ይሆናል። ግልፅ ክስረት የሚባለውም ይህ ነው። አቂዳው የተስተካከለ ሰው ግን በዱንያም በአሔራ ደስተኛው እሱ ነው።»
📚 ۞ المنتقى【1/193】۞

♣②④•ኢብኑ_ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«እንስሳቶች እየበሉ፣ እየጠጡና እየተኙ ብቻ እንደሚኖሩት ልንኖር አይደለም ወደ ዱንያ የመጣነው። ይልቁንም ለአኺራህ ስንቅ እንድናዘጋጅ እንጂ!»
📚 ۞ الكــفايــة الشـــافـــيــة【4/279】۞

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ሀሉም ጥሎህ ሲሄድ ቀከብርህ ስፍራ
ካንተዉጋ ይቀራል የሰራኸዉ ስራ
ለዛ ለጭንቁ ቀን መልካምን የሰራ
በእርግጥ ይድናል ከጅሀነብ  ስፍራ
በሽርኩ ታጭቆ በጌታዉ ሲያጋራ
ሳይቶብት  ከሄደ  እሱን ሳያጠራ
ነፍሱንም በደላት  መልካምም ሳይሰራ

Читать полностью…
Subscribe to a channel