gfyygy | Unsorted

Telegram-канал gfyygy - አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

883

ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot

Subscribe to a channel

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ደስ እየላችሁ አንብቡት  ኢብኑል ቀይም ማለት የታላቁ ኡለማ የኢብኑ ተይሚያህ ደረሳ ናቸው።

ከኢማም ኢብኑል ቀይም፦رحمه الله
                                        ለእኛ፦ የተሰጠ የህይወት ምክር ፦
'እንደገና መነሳትና መቀጠል መቻል የራስ ሀላፊነት ነው።
በህይወት ክንውኖች ውስጥ ስብራት ያለ ነው። በምትሰበሩበት ጊዜ ግን ከራሳችሁ በቀር ማንም ያንተን ስብራት አይጠግንም። ከቁርጠኝነታችሁ በቀር ማንም ለናንተ ድል አይሰጥም።
ራሳችሁን ጠብቁ! ተንከባከቡ፣ አሳድጉ ፤ ለራሳችሁ ያላችሁ ራሳችሁ ብቻ ናችሁ።
ጓደኛ ፣ የምትወዱት ሰው የህይወታችሁን ውጣ ወረድ በትክክል አይጋራም ፤ ህመማችሁን በአካል አይወስድም። [ መደጋገፉ እና አብሮነቱ እንዳለ ሆኖ ]
ማንም ሰው በስማችሁ አያድርም።
ለራሳችሁ ያላችሁን ግምት በሰዎች ዓይን አትመልከቱ ፦ በህሊናችሁ ውስጥ ዋጋችሁን ፈልጉ። እውነተኛ ማንነታችሁን ካወቅችሁ ስለ እናንተ የተነገረው ነገር አይጎዳችሁም።
የዚህን ህይወት ጭንቀት አትሸከሙ፤፦ ምክንያቱም ይህ ለአላህ ነው። የሲሳይንም ጭንቀት አትሸከሙ፦ እርሱም ከአላህ ዘንድ ነው። ለነገ፦ ለወደፊቱም አይጭነቃችሁ እርሱም በአላህ እጅ ነው።
አንድ ነገር ግን ተሸከሙ፦ አላህን ማስደሰት።
አላህን ብታስደስቱት እርሱ ያስደስታችኋል፤ ህይወታችሁን በፀጋው ሞልቶ ሙሉ አድርጎ ያበለጽጋችኋል።
በህይወት ጉዳይ ላይ ልባችሁን አስጨንቃችሁ አታልቅሱ።
"አላህ ሆይ!  በቅርቢቱም ሆነ ፤ በመጨረሻው ዓለም በመልካም ነገር ክፈለኝ ።" በሉ!
ሀዘን በስግደት፣ በስጁድ ጊዜ ከውስጥ ተኖ ይወጣል ፤ ደስታ ከልባዊ ዱዓ ጋር ይመጣል።
አላህ፦ ለሌሎች ያደረጋችሁትን መልካሙን ነገር፤  የሰራችሁትን በጎ ተግባር አይረሳም።
አላህ ፦ ለናንተ ሳቅ፦ ፈገግታ እንጂ ስታነባ የነበረችዋንም ዓይን አይረሳትም።
አሁን፦ ህይወታችሁን በመርህ ኑሩ፦ ለመልካምነታችሁ ምላሽ ባታገኙም፤ የአላህን ውዴታ ለማገኝት ስትሉ መልካምን ፣ በጎን ተግባር አድርጉ።'
ምክንያቱም፦
           "አላህም በጎ አድራጊዎችን ይወዳል፡፡" ¹
               { Lencho Mohammed }
ምንጭ ፦ [ Quran፦ 3:148 ¹ ፣ Timeless Seeds Of Advice ¹⁰⁶ ]

ኮፒ ከአብድረሂም አህመድ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

«ከሁሉም ሠላቶቹ በኋላ አያተል ኩርሲይ የቀራ ሰው ከሞት በስተቀር ጀነት መግባት የሚከለክለው ነገር የለም።»
ረሱል (ሠለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:➛ሶሒሁል ጃሚዕ (6464)

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ከፌስቡክ መንደር የተገኘ የተመቸኝ መልዕክት፦

«…  መኪና ውስጥ ነበርን፤ (ፒዛ አዘን እየበላን) አስተናጋጁ ሲያልፍ በእጄ ቢል እንዲያመጣልኝ ነገርኩት።

ቢል ይዞ መጣ።

እያየኝ ከፊት ከኃላ ኪሴ አውጣጥቼ ሂሳብ ከፈልኩ ...
ሄደ።
መልስ መጠበቅ ጀመርኩ፤ አልመጣም። ጠበኩት፤አልመጣም። ተበሳጭቼ ክላክስ አስጮህኩ።

(ሱሰኛ ይመስላል ፣ የቀረውን ገንዘብ ለማስቀረት አስቦ ነው ፣ ጉርሻ በፍቃደኝነት የሚሰጥ እንጂ በብልጠት የሚዘገን አይደለም ፣ ሲቆይብን ሰልችቶን እንድንሄድ ነው።)

ያስጮኩትን ክላክስ ሰምቶ መጣ።

"መልስ ስጠን እንጂ ጌታው! "አልኩት።

"የሰጠኸኝ አራት መቶ ብር ነው፤ ሂሳቡ ደሞ አራት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ነው "አለኝ (ኪሴን ስበረብር ስላየኝ የለው ይሆናል በማለት ተሳቆ ነው እንዳልገረጣ ይጎላል ያላለው።)

ከሌለህ ብዬ ነው አይነት ፊት አሳየኝ ። አንዳንድ አድራጎት የሚያገዝፈው አደራረጉ ነው።

ይቅርታ ቢሉን በደንብ ስላላስተዋልኩት ነበር።
በጣም አመሰግናለሁ አልኩት።

እንደገና ኪሴን በርብሬ ድፍን ሁለት መቶ ብር ሰጠሁት፤ እንዲመጣልኝ እንዳልቸኮልኩ እንዲሄድልኝ ቸኮልኩ።
መልስ ሊያመጣልኝ ሄደ!

ሳይነግሩን ለዋሉልን እየነገርን መዋል ነውር ነው አይደል ?
ሳይመጣብኝ ሄድኩኝ ።»

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

Umma Life ምንድነው? ማነው የሰራው? ዓላማውስ ምንድነው?

ይህ Umma Life(ኡማ ላይፍ) የተሰኘው አፕልኬሽን ልክ እንደ ፌስቡክ አካውንት ከፍተን የራሳችንን ፅሁፎች፣ ምስሎች እና ቪድዮዎች ጭምር ማጋራት የምንችልበት ፕላትፎርም ሲሆን ከፌስቡክ የሚለየው እያንዳንዱ የምንለቃቸው ነገሮች ከሸሪዐ አስተምህሮ ጋር የሚጋጭ መሆን የለበትም።

የዚህ ፕላትፎርም መስራችና ስራ አስኪያጅ "ዒሳ ዳገስታኒ(Isa Dagestani) ሲባል በዜግነት ቱርካዊ ነው።

ይህን ፕላትፎርም ለማዘጋጀት እንደምክንያት ሆኖ ያነሳሳቸው በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሀሳቡን ሲያንፀባርቅ ሀሳቡን/ፅሁፉን ከማገድ አልፈው አካውንቱን እስከመዝጋት በመድረሳቸው ነው።

Non-ሙስሊም የሆኑ ሰዎች የፕላትፎርሙን ህገ_ደንብ ካከበሩ መቀላቀል እንደሚችሉ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።

እኔ ያየሁዋቸው መስተካከል ያለባቸው የተወሰኑ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ የኮሜንት ሴክሽኑ ክፍት ቢሆንም ሀሳብ ማስፈር አንችልም። በተጨማሪ አንድ ጊዜ ፖስት ካደረግን በኋላ Edit ማድረግ አንችልም።

አሁን ቨርዥን 2.4.15 ላይ ደርሷል።

አፕልኬሽኑን ለማግኘት ተቸግረናል ላላችሁኝ በሚከተለው የቴሌግራም ሊንክ ገብታችሁ ማውረድ ትችላላችሁ።
👇👇👇👇👇
/channel/AmmarAli75/623

ተጠቀሙበት! ለሌሎችም አድርሱት!

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ሒጃብ እከለክላለሁ ብላ ዝግጅቷን ጨርሳ የነበረችው ፈረንሳይ ሒጃብ በግዴታ የሚያስለብስ የትኋን ወረርሽኝ ለቆባታል።

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

እጅግ አንገብጋቢ ምክር ከሸይኽ ዐብዱሰላም አሹወይዒር
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

https://youtu.be/1Hr7azdaQ44?si=1D08JQF9kUSrX0a0

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች
~
① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ።
"አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።"
"ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።"

② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚገድላቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የሃንዳውት፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ።

③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። የማንም ሙገሳ ከፍ እንደማያደርግህ ሁሉ የማንም ትችትም ዝቅ አያደግህም። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው።
"ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።"

④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። አስቀራ። ኪታብ ተማር። አስተምር። ደዕዋ ሞክር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው።
"ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።"

⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ እራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ እንዳለው ተረዳ።
"Education is a better safeguard of liberty than a standing army."

⑥ እራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ እንጂ። አንተ'ኮ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም።
"እራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።"

⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም ። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሐብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።
እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮች ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።
"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ እራስህ እያለፍክ ነው።"

⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ እራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።"

⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ።
ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ። "መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ።
"ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።"

(10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ እንደ ቴኳንዶ ያሉ ራስን መከላከያ ሥልጠና፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ።
"ራስን ብቁ ዜጋ ማድረግ ለሀገርም ለወገንም እሴት መጨመር ነው።"

(11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን።
"ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።"
"ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"

(12) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነቱ ዋጋ የሚሰጥ ሰው በተልካሻ ቆሻሻ ነገሮች አይታሰርም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ኣ? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። እራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም።
"እራስን በሱስ በመጉዳትና እራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"

(13) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል" ይባላል።
"የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።"

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ወንድማዊ ምክር ለሙስሊሟ እህቴ!

በጥሩ ንያ አንብቡት በአላህ ፍቃድ አንድ ቀን ይጠቅማችሁ ይሆናል!

✍ጌታችን አላህ ለትልቅ አለማ እኛን ፈጥሮናል።በምን አይነት መንገድ እሱን(አላህን)መገዛት(ማምለክ)እንዳለብንም ነብይ ልኮ፣መፅሐፍት አውርዶ ነግሮናል። ባወረደውም ቁርኣን እንዲህ ብሎናል "ጂንንም ሆነ ሰውን እኔን እንዲገዙ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም"‼️

ወደ 👉ወነው አርስቴ ስገባ ሴቶችዬ ከወንዶች ጋር (በተለይም ከ* ካ* ፊ* ር ወንዶች ጋር መቀራረብን የምናበዘ እህቶች ረሳችንን ለምን አይነት ከባድ አደጋ አሳልፈን እንደምንሰጥ እንወቅ!

በየ ሶሻል ሚድያውና በየሰፈራችን የምንሰማው ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ታሪክ ማስተዋል ለቻለ ትልቅ ትምህርት አለው። ለምሳሌ ያክል ከዚህ በታች ባለው ቻናል የተወሰኑትን አስቀምጣለሁ ።

እህቴ ሆይ! ራስሽን ጠብቂ ! ከሁሉም ወንድ ካልተጀናጀንኩ፣ከሁሉም ወንድ ካላወራሁ፣ከሁሉም ወንድ ካልተለፋሁ አትበይ በአላህ እህቴ ክብርሽን ጠብቂ!

ሶሃባው ኡመር ያለውን አልሰማሽምንዴ?!! "በጣም አስጠሊተሟ ሴት ማለት በወንዶች ላይ በጣም ደፋር የሆነቿ ናት"ስለዚህ እህቴ ሀያሽን ጠብቂ! ጌታችን አላህ አንቺንኮ አልቆሻል።

ጌታችን አላህ አልቆሽ ሲያበቃ እሱን ለማምለክ ፈጥሮሽ ሲያበቃ አንቺ ግን ይህንን ችላ ብለሽ ከ* ካ* ፊ* ሩ* ም ፣ከሙስሊሙም ፣ከቦዘኔውም ከሁሉም እየተጨማለቅሽ ከሆነ የምትኖሪው በትልቁ ቀይ መስመር ላይ ነሽ እህቴ ሆይ!ተመለሺ ግዴለም ተመለሺ መመለሱ ይጠቅምሻል እንጂ አይጎዳሽም!!

ብዙዎች ፍቅር ምን እንደሆነና ለከባድ አደጋ እንደሚጥል ሳይረዱ እንደ ቀልድ ከካ* ፊ*ሩ ጋር ልቅ በሆነ ቅርርባቸው የተነሳ በፍቅር ዮድቃሉ። ያው እንደሚባለውም ፍቅር አይነስውር ነው አይደል? ግን ፍቅር ያለ ምንም ቅርርብ አይዝምና እህቴ "ፍቅር ነው ጉድ ያደረገኝ"ከማለተሽ በፊት ጠንቀቅ በይ!

እናስተውል!

"ሙስሊም የሆነች ሴት ካ***ፊር ወንድን ማግባት አይፈቀድላትም ካደረገችውም እሷ የምትኖረው ያለ ኒካሕ ነው"

ደሞ ከተጋቡ በኋለ መክፈርም አለ፣

ወላሂ! ተወዳዳሪ የሌላት ቂል ማለት ለዚህች ጠፊ ዱንያ ብላ ዘውታሪ የምትሆንበትን አገር አፍርሳ ለወንድ ብላ የምትከፍር ሴት ናት!ከዚህች ሴት የሚወዳደር ቂል ቢኖር በተለያየ ዱንኒያዊ ጥቅም እስልምናን የሚሸጥ ለጠፊዋ ዱንያ የሚከ*ፍር ናው።

እናም በብዛት እህቶችን ለዚህ እጅግ ከባድ አደገ ለመውደቅ ሰበብ የሚሆንባቸው

👉የመጀመራውና ትልቁ ልቅ የሆነ ከወንዶች ጋር መቀራረብ
👉መጥፎ የሆኑ ዘመናዊ የፍቅር ፊልሞች
👉ዲናቸውን በሚገባ አለመረዳትና ግዜያቸውን እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንዳለባቸው ካለ መረዳት
👉መጥፎ የሆኑ ስለ ፍቅር የሚዘፍኑ ዘፋኞችን ዘፈን ማዳመጥ
👉በቀልድ የተጀመራ ጅንጀና ምክርን አለመስማት የመሳሰሉት ተደማምሮ ወደ መጥፎ ነገር ውስጥ ይከታል

ስለዚህ ሙስሊሟ እህቴ ፀፀት ውስጥ ከመውደቅሽ በፊት ፀፀት ውስጥ ከሚጥልሽ ነገር ታቀቢ እላለሁ።

👌ሳጠቃልል

መሞታችን አይቀርምና ይህን ሞት የሚባለውን ነገር በሚገባ እንረዳው።ጓደኞቻችን፣ቤተሰቦቻችን፣

ዘመዶቻችን የወሰደው ሞት ለኛም ቀጠሮ ይዞ እየጠበቀን ነው።ለምንድነው ሞትን እሩሩሩሩሩሩሩሩቅ አድርገን የምንመለከተው?!!
//
እስኪ እናንተም በሰፈራችሁ የገጠማችሁን ታሪክ በወንድም ይሁን በሴት ለወንድ ብላ የከ*ፈረች ፣ለሴት ብሎ የከ*ፈረ ካለ በኮሜንት ወይም በቻናሉ በቦት (በአስተየት መስጫ)ላኩልኝ ባረከላሁ ፊኩም።

ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

✍ወንድማችሁ Abdurhim Sane አቡ ኡካሻ ነኝ ከአዳማ

/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/7385

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

⁌ 📲 ❏ አዲስ አፕ ተለቀቀ ❐  ⁍

ሸርሑ ሱና ⍿ شرح السنة للبربهاري | ሙሉ ደርስ Offline ያለኔት

➩🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

➩📚 ከክፍል 01-37 ሙሉ ደርስ

➩📥 ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ! #share በማደረግ ለብዙሃን ይደረሰ ዘንድ የበኩሉን አሰተዋጽኦ ያድርጉ!

📮 መሰል ጠቃሚ 📲አፖችን ማሰራት የምትፈልጉ ከስር ባለው አድራሻችን ይነግሩን!

❑በቴሌግራም-@Yusufapp_developer

▢App developer:- Yusuf App
ኢስላማዊ እውቀት ከሁሉም በፊት!

http://t.me/Yusuf_App1

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ከኮሜንት የተገኛ
ኡስታዞች በታሰሩበት ወቅት እኔ ያኔ የእሥልምና አማኝ ባልሆንም ግን ሙሥሊሞች ምን ያህል እንደታገሉ እና እንደተጎዱ ድምጽ እንደሆኑ አውቃለው ። ዛሬ ላይ ግን ሴት ልጅ ኒቃቤን እና ሒጃቤን አክብሩልኝ ብላ ድምጿን ስታሰማ በካሐዲያን ሴራ እንግልት ሲደርስባት ራቁታቸውን ለሚሃዱት ነጻነት ተሰጥተው በሙሥሊሟ እንእስት ላይ በደል ሲደርስ በሚዲያ ላይ ጭራሽ የካሐዳያንን ሴራ ድጋፍ እና ሽፋን ለመስጠት ኒቃብን ማጣጣል ከአንድ አስተማሪ መስማት የእውነት ይገርማል። ዲኑንም ሆነ ትክክለኛ አማኝ ባሪያዎቹን የሚጠብቀው አሏህ ነው ። ነገር ግን የዲንን ጉዳይ እንደ ቀላል ለስልጣን መግቢያ እና ለዱኒያ ክብር ተብሎ ስትጫወቱበት ማየት ያሳፍራል ።

የሆኖም ኢሥላምን ሕግጋትን እና ትእዛዝ ኢሥላም ስላዘዘ ብቻ እንተገብራለን ማንም ምን ቢል ወደ ኋላ አንልም ። በኢሥላም ያሾፈ ራሱን እንጅ ማንንም አይጎዳል ። በኒቃባችን አንደራደርም በዲናችን አናፍርም በኢሥላም ላይ ተፈጥረናል በኢሥላምም ውስጥ እንኖራለን በኢሥላምም ነስርን እናገኛለን ለእርሱም ስንል እንሞታለን ። የተፈጠርንበት ዓላማም ይህ ስለሆነ ።

ከጉንችሬ ኒቃቢስት ተማሪዎች መካከል አንድ እህታችን የተናገረችው ንግግርስ እንዴት ይረሳል ? ትምህርትን ጠልተን ሳይሆን በኢሥላም መከበረን ስለምንፈልግ ነው ። ዋ ሙእተሲም ብለን የምንጠራው አካል አጥተናል ነስሩን ግን ከአሏህ እናገኛለን ።

ካሚል ሸምሱ የእህቶቻችንን ክብር በመርገጥ ኃይለ ቃል ተጠቅሞ ለዲኑም ክብር ሳይሰማው እንደ ቀላል የተናገራቸውን አይባሌ ንግግሮች ማስተካከል እና ለሙሥሊሙ ዑማ ይቅርታንም መጠየቅ አለበት ።

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ስንፈጠር ውሃብያ ለምንመስላችሁ በሙሉ ፦

መውሊድ ረሱልን ﷺ መውደድ መስሎን አክብረንው፣ዲን መስሎን ጠብቀንው እናውቃለን። በግሌ ቁርኣን ቤት ስንቀራ የመውሊድ እንጀራ ሰብስቡ ተብለን የ«ብሔር ብሔረሰቦችን» እንጀራ እየዞርን ሰብስበናል። የወጡን ሽታ ፣ የመረቁን ጥፍጥና ቀምሰናል። የአድሩሱን ጭስና የቡና ስርአቱን ድባብ ከቅርብ ተከታትለናል። የፍትፍቱን ጣዕም እየተጎራረስን አጣጥመናል።

እንደውም ያኔ አደብ ያለው ነበር። አሁን ላይ በግልፅ ከሚታዩ ነውሮች የፀዳ ሆኖ ነው የምናውቀው ማለት ይቻላል። ሴቶች ከመጋረጃ ጀርባ ምግብ ያዘጋጃሉ እኛ ትናንሾቹ እየተቀበልን እናመጣለን። ደረሶች ተሰብስበው ይበላሉ። ቡና ይሽከረከራል። ዱዐ ይደረጋል።

ጫት የዚያን ጊዜ ለዱዐ ብቻ ለዚያውም በፌስታል ደበቅ ተደርጎ የሚገዛ ነበር። የሆነ የመውሊድ ኪታብ ቁርኣን የሚያቀሩን ሱፍያ ሸሀችን ያነበንባሉ። ሰለዋት ይወረዳል። ተመራርቀው ይለያይሉ። በአላህ እምላለሁ አሁን እንደምናዬው ልቅ ጋጠወጥነት የተሞላበት ዝላይና የወንድና የሴት ቅልቀል ፣ፉጭትና ጩኸት አልነበረም!

ሴቶች በተለዬ መልኩ አስበውት እንደ ዒድ «ማች» እየለበሱና የከንፈር ቀለም እየተለቀለቁ አይመጡም። እንደውም ሴቶች ከምግብና ከቡና ማዘጋጀት እንዲሁም እዚያው እርስ በራሳቸው ዱዐ አድርገው ከመለያየት ውጭ የሚያደርጉት ነገር አልነበረም ብል ውሸት እይሆንብኝም። ወጣት ሴቶችም ስለመሳተፋቸው ሁሉ እርግጠኛ አይደለሁም።

ከጊዜ በኃላ አላህ በናንተ አጠራር « ዉሃብያ» ዳዒዎችን አስነሳልን። ወደ ሐቁ ጠሩን። ቢድዐነቱን አስተማሩን ዲን ብለን ስናደርገው የነበረውን ነገር ዲን እንዳልሆነ አስረዱን ። የአላህ ትሩፋቱ ሆኖ ሂዳያን አገኘን።ምንም ልጅ ሆነን ቢሆንም ያከበርነው በዚያው ቀጥለን ብንሆን አሁን ላይ ጥመት ላይ ነበርን። አልሐምዱሊላህ ሂዳያ ለሰጠን ጌታ! በዚህ መንገድ ላይ ከእስር እስከ ግድያ ሙከራ ዳዒዎቻችን አስተናግደዋል።ሸይኽ አብዱለጢፍ ፣ዳዒ አብዱልፈታሕ ሐጂ፣ ዳዒ አብዱ ሚግራ፣ ዳዒ ጀማል ሀሰን የአንበሳውን ድርሻ ወስደዋል።

ዛሬ ላይ በመውሊድ ቀን የተለዬ እንቅስቃሴ የማይታይባት ከሚሴን ለመፍጠር የነዚህ ሰዎች ጂሃድ ቀላል አልነበረም። አላህ ጀዛቸውን በእጥፍ ይክፈላቸው!

መውሊድ ከነሽርክ ስንኞቹ አይደለም ሰደቃ አድርጎ ብቻ በመለያየት ታስቦ የሚውል ቢሆን እንኳን ቢድዐነቱ አይፋቅም። አሁንም ቢሆን ሌላ ዱንያዊ አላማ ለሌለው ሰውና ለዲን ብሎ እያደረገው ላለ ሰው ቢድዐነቱን መረዳት ቀላል ነበር። ግን ዱንያዊ ጥቅም ከገባበት ሰው ሐቅን እያወቀም ቢሆን አያደርገውም!

ስለዚህ ለዲን ብላችሁ ከሆነ አሁንም ጊዜው አልረፈደም! ወደ ዲንና ወደ መልእክተኛው ﷺ ትእዛዝ ተመለሱ! በነፍስያ የሚነዷችሁ ሰዎች ከአላህ ቁጣ ሊያድኗችሁ አይችሉም! ይህን የቁርኣን አንቀፅ ብታስተነትኑት መልሱ በውስጡ አለላችሁ፦

አላህ ﷻ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፦
«በቤቱ ዘንድም (በካዕባ) ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ (ይባላሉ)፡፡»
(አል አንፋል 35)

ከሙሽሪኮች ጋር የምትመሳሰሉበት ማፏጨትና ማጨብጨብ የአላህና የመልእክተኛው ﷺዲን ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?!?!

የማትፈቀድለትን ሴት እጅ ጨብጦ የማያውቀው ነብይ ሴትና ወንድ ተቀላቅሎ የሚደረግን ዒባዳ እውቅና ይሰጠዋል ብላችሁ ታስባላችሁ!?! ﷺ

አሁን ባላችሁበት አሕዋል ረሱል በህይወት ኖረው የአላህ ቤት ውስጥ ጫት ስትቅሙ ቢያገኟችሁ ፍቃድ ይሰጡናል ብላችሁ ታስባላችሁ? እንደዚያ የምታስቧቸው ከሆናችሁ ወላሂ ረሱልን ﷺ አታውቋቸውምና ሲራቸውን ተማሩ?!

ልብ ግዙ! እልክና ስሜት አላህ ፊት ዑዝር አይሆኑም! ከግብግቡ ወጣ ብላችሁ አስቡ!

አላህ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል፦
« በላቸው፡- «አላህን የምትወዱ እንደኾናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና፡፡ ኀጢኣቶቻችሁንም ለናንተ ይምራልና፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»

እውነት ወደ አላህ መቃረብን ፈልጋችሁ ከሆነ ረሱልን ተከተሉ!
አላህ ይምራን!! ይምራችሁ ! !

Ismaiil Nuru

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የአሕባሽ መሪና  አብደላህ አልሐረሪንና የሸይኽ ፈውዛንን የመውሊድ ማስረጃን ያነፃፅሩ አጭር ቪድዮ  ጉድ መውሊድ አክባሪያን ሁሉ እንዳይበርር ፈራን

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ውድ የሱንና/የኢስላም/ወንድም እህቶች

ወድ የሆኑትን  የሱንና ወንድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ከአላህ ሚንዳን በመፈለግ ተፈላለጉ።እሩቅ ቢሆኑ ፣ከሀገር ወጪም ቢሆኑ እንኳን  በስልካችሁ  ተደዋወሉ ተዘያየሩ።

እውነተኛ ለአላህ ብቻ ብለው ከተዋደዱ የአላህ ባሮች ነገም በአኼራ አብረው በጀነት ጓደኛ ከሚሆኑት ያድርገን ያረብ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

#ፈጅር ሶላት የፈጣሪህን ትእዛዝ ለመተግበር #በሸይጧን ላይ ድል አድርገህ የቀን ውሎህን በደስታ የምትጀምርበት ትልቅ ፀጋ ነዉ::

“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም”
“አሰላቱ ኸይሩን ሚነ ነውም”
ሶላት ከእንቅልፍ ይበልጣል
ሶላት ከእንቅልፍ ይበልጣል።

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የባህሪ ለውጦች
~
አንዳንዴ ለዘመናት በመልካምነት የምናውቃቸው ሰዎች የማናውቃቸው እስከሚመስለን ድረስ ባህሪያቸው ተቀይሮ ለመሸከም የሚከብዱ ይሆናሉ። ምክንያቱ ምን ይሆን? የችግሮቹን መንስኤዎች ማወቅ ለማስታመም፣ ለማለፍ፣ ለመረዳት፣ ...  ያግዘናል። የሰዎችን ባህሪ ከሚቀይሩ ነገሮች ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው።

1- ስልጣን፦
ስልጣንና ኃላፊነት ሲያገኙ የሚቀየሩ ብዙ ሰዎች አሉ። የሚያውቁትን እንደማያውቁት ይሆናሉ። ንቀትን ንቃት ያደርጋሉ። ውለታ ይረሳሉ።
2- ስልጣን ማጣት፦
ከስልጣንና ኃላፊነት ሲነሱ በብስጭት፣ በቁጭት እየተብከነከኑ ለሩቁ ቀርቶ ለቅርብ ሰዋቸው ጭምር ባህሪያቸው የሚፈትኑ ይኖራሉ።
3- ሃብት፦
ትሁትና ደግ የነበሩ ሰዎች ሃብት ካገኙ በኋላ ትእቢት፣ ንቀትና ኩራት የሚባሉ ነውሮችን ጌጥ የሚያደረጉ የዋሆች አሉ።
4- ድህነት፦
አግኝቶ ማጣት ትልቅ ህመም አለው። ድህነት ሲዳብሳቸው መልካም ባህሪያቸው ከገንዘባቸው ጋር ጥሏቸው የሚጠፋ ሰዎች አሉ። መቼም አመላችን እንደ መልካችን ብዙ አይነት ነው።
5- ሱስ፦
በሱስ በመጎዳታቸው የተነሳ ከጊዜ ጊዜ ትእግስት እንደ ቁምጣ እያጠራቸው የሚሄድ፣ ይሉኝታ የማያውቁ፣ "ሰው ምን ይለኛል?" የማይገዳቸው ሰዎች ቁጥራቸው ከብዙም የበዛ ነው።
6- ሃሳብ፦
የሰው ልጅ በህይወቱ ለተለያዩ ሃሳቦች መጋለጡ የሚጠበቅ ነው። የሃሳብ መደራረብ፣ የአእምሮ መወጠር ደግሞ የሰው ባህሪ ላይ ግልፅ ተፅእኖ ያሳድርበታል።
7- ህመም፦
ህመም ባህሪን ይቀይራል። ያነጫንጫል። ከሰው ቀርቶ ከእንስሳ፣ ከግድግዳ ጋር ሁሉ ያጋጫል።
8- እርጅና፦
እርጅና እንደ ልጅ ያደርጋል። እንዲያውም ሊብስ ይችላል። ልጅን ተቆጥተህ ታስደነግጠዋለህ። ከእርጅና ጋር የሚመጣ ክፉ ባህሪ ግን ለገላጋይ አይመችም። እርጅና ላይ ሌሎች ገፊ ችግሮች ሲደረቡበት ደግሞ በቡሃ ላይ ቆረቆር ይሆናል።

ምንጭ፦ አብዛኛው ሃሳብ ከሸይኽ ዐብደላህ አልፈውዛን (ሚንሐቱል ዐላም፡ 10/295 - 296) የተወሰደ ነው።

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

https://fb.watch/o0MPE31Y4I/?mibextid=Nif5oz

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ስለ ሶላቱል ጀናዛህ አሰጋገድ  በተመለከተ በፈጅር ቲዩብ የተዘጋጀ አጭር ሞሽን ግራፊክስ
ጆይን፡‐/channel/fejir_tube

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የአፋልጉኝ ማስታወቂያ

ሙሉ ስም አብዱል አዚዝ ሽኩር ሙሐመድ
የትውልድቦታ ደላንታ ወገልጤና ከተማ
ለቂርአት ብሎ በደሴና በኮቦልቻ አካባቢ የዛሬ ሳምንት እሁድ መስከረም 20/2016 እንደወጣ አልተመለሰም። እባካችሑ ወገኖቸ ልጀን አፋልጉኝ ይላሉ እናቱ
የሰማችሁም ያያችሁም ጠቁሙን

0927352384 ዘይነባ አሊ እናት ካልሰራላችሁ
0933519871 አፋላጊ ጀማል እንድሮ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አላሁ አክበር ድንቅ የሆነ ቲላዋ የጠዋት ግብዣዬ ነው

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

(14) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ።
"የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።"

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011)
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

በኦሮምኛ የጤና መረጃ ምትፈልጉ ይህንን ተከታተሉ!

Namoonni Afaan Oromoo Dandeeysan Odeeffannoo waa'ee fayyaa argachuuf Telegrama kana hordofaa, gaafis gaafadhaa barnoota fayyaa baay'ee irraa argattu jennee yaadna.
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
/channel/Pharmacist_Elias/76
⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️⬆️

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

https://www.facebook.com/100016829829342/posts/pfbid0CrP3gnJVErZTf8HCz1WZBeYWoLHa4c2hQ4b4SYkPRx2PxSdc65sJrzjGTq9eCjo4l/?app=fbl

እሬቻ ላይ የሚፈፀመውን ሽርክ በማስረጃ ተመልከቱ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ለክርስቲያን ወገኖቻችን
~
እባካችሁን ቆም ብላችሁ አስቡ። መቼም ከሞት በኋላ ሕይወት እንዳለ ታምናላችሁ። ህይወት ሁለት ሶስት እድል የላትምና ዛሬን ቁርጠኛ ውሳኔ ወስኑ። ከንዲህ ዓይነት ለፈጣሪ ቀርቶ ፍጡርን የሚያሸማቅቅ ታሪክ ቁም ነገር አድርጎ ከሚሰብክ ሃይማኖት ውጡ፡፡ እልህ ምንም አይሰራም። ብልጥ ማለት ለነገ ህይወቱ ዛሬ ሰከን ብሎ የሚያስብ ነው።
ከፍጡር አምልኮ ውጡ። ጥሪዬ ወደ ጋራ እውነት ነው። መጽሐፍችሁ እንዲህ የሚል አለ፦
"ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። #ከትእዛዛቱ_ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ #ጌታ_አምላካችን #አንድ_ጌታ ነው፥" (የማርቆስ ወንጌል 12:29)
የኢስላም ጥሪም ወደ የትኛውም ፍጡር አምልኮ ሳይሆን ወደዚህ እውነት ጥሪ የተደረገው። ይሄውና፦
{ قُلۡ یَـٰۤأَهۡلَ ٱلۡكِتَـٰبِ تَعَالَوۡا۟ إِلَىٰ كَلِمَةࣲ سَوَاۤءِۭ بَیۡنَنَا وَبَیۡنَكُمۡ أَلَّا نَعۡبُدَ إِلَّا ٱللَّهَ وَلَا نُشۡرِكَ بِهِۦ شَیۡـࣰٔا وَلَا یَتَّخِذَ بَعۡضُنَا بَعۡضًا أَرۡبَابࣰا مِّن دُونِ ٱللَّهِۚ فَإِن تَوَلَّوۡا۟ فَقُولُوا۟ ٱشۡهَدُوا۟ بِأَنَّا مُسۡلِمُونَ }
"የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ሆነች ቃል ኑ። (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው። እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መሆናችንን መስክሩ በሏቸው።" [ኣሊ ዒምራን፡ 64]

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

⁌ 📲 ❏ አዲስ አፕ ተለቀቀ ❐  ⁍

ሸርሑ ሱና شرح السنة للبربهاري | ሙሉ ደርስ Offline ያለኔት

➩🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🏷በምርጥ ጥርት

➩📥 ዳውንሎድ አድርገው ይጠቀሙ!
/channel/yusuf_app1/412

☎️ መሰል ጠቃሚ 📲አፖችን ማሰራት የምትፈልጉ ከስር ባለው አድራሻችን ይነግሩን!

🔘በቴሌግራም-@Yusufapp_developer

App developer:- Yusuf App
ኢስላማዊ እውቀት ከሁሉም በፊት!

http://t.me/Yusuf_App1

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ለምታስተውሉ ብቻ!
~
ሱ ፊያ ማለት እጅግ ያፈነገጠ ቡድን ነው። ከቁርኣንና ከሐዲሥ ብቻ ሳይሆን ከግብረ ገብነትና ከሐያእም የተኳረፈ ነው። እስኪ አሁን በዚህ መልኩ ዐቅሉን ስቶ የሚዘለው የመስጂድ ሙአዚን ነው ቢባል ማን ያምናል? ነብያችን ﷺ መስጂድ ውስጥ ግብይት እንኳ እንዳይፈፀም ከልክለዋል። እነዚህ ግን በተከበረው የአላህ ቤት ውስጥ ቅልጥ ያለ ጭፈራ ይፈፅማሉ። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! በዚህ መጠን መስጂድ መቀለጃ ሲሆን በጣም ያሳዝናል።
በነገራችን ላይ ይሄ ጭፈራና ፉጨት የመካ ሙሽሪኮች ከዕባ ዘንድ ሲፈፅሙት የነበረ ነውረኛ ተግባር ነው። አላህ እንዲህ ብሏል:-
وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ
{በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አንፋል፡ 35]
ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር በአራቱም መዝሀብ የተወገዘ እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው። ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው። ዑለማዎች ይህንን ነውረኛ ተግባር እጅግ በጠነከሩ ቃላት ኮንነውታል። ጥቂት ምሳሌ ልጥቀስ።
.
1. አቡል ወፋእ ኢብኑ ዐቂል (513 ሂ.)፡-
"በዜማና የመሳሪያ ድምፅ እየተከተለ የሚደንስና የሚጨፍር ባለ ፂም ማየት ምንኛ አስቀያሚ ነው? ባለ ሽበት ሲሆን ደግሞ የባሰ ነው! በተለይ ደግሞ በወጣቶችና በሴቶች ድምፅ ሲታጀብ። ከፊቱ ሞት፣ ጥያቄ፣ መቀስቀስና ሲራጥ ያለበት፣ ከዚያም ከሁለቱ አገሮች ወደ አንዱ የሚሆን ሰው እንደ እንስሳት ዝላይ ሊዘል፣ እንደ ሴቶች ማጨብጨብ ሊያጨበጭብ እንዴት ይዋጥለታል?!" [ተፍሲሩል ቁርጡቢ: 10/263]

2. ኢብኑል ጀውዚይ (597 ሂ.)፡-
የሱፍያ ክፍሎችን ተግባር አንስተው ባወገዙበት እንዲህ ብለዋል:– “በየምግቡ ላይ ይቀመጣሉ፡፡ ሲጠግቡ ጊዜ ይደንሳሉ፡፡ … ከመዐቶቻቸው ሁሉ የከፋው መዐት ግን ይህንን (ጭፈራ) መቃረቢያ (ዒባዳ) አድርገው መሞገታቸው ነው፡፡ ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው ከኢስላም እንደሚወጣ በርግጥም የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጥሯል፡፡” [ሶይዱል ኻጢር፡ 168]

3. አልቁርጡቢይ (671 ሂ.)፡-
“ሱፍዮች የፈጠሩትን (ዜማ) በተመለከተ በክልክልነቱ ላይ ውዝግብ ከማይነሳበት ነገሮች ነው። ነገር ግን ብዙ በመልካም የሚታሰቡ ሰዎችን ስሜት አሸንፏቸዋል። ብዙዎቹ ላይ የእብዶችና የህፃናት ስራዎች እስከሚታዩባቸውና በተጠና መልኩ እስከሚደንሱ ደርሰዋል። ከዚያም ከፊል ሰዎች መቃረቢያና መልካም ስራ እስከማድረግ ደረሱ።…” [ተፍሲሩል ቁርጡቢ፡ 14/54]

4. ሲዩጢይ (911 ሂ.)፡-

"ከነዚህም (ቢድዐዎች) ውስጥ የሆነው በመስጂድ ውስጥ የሚፈፀም ጭፈራ፣ ዘፈን፣ ድቤ መምታት፣ ማሲንቆና ሌሎችም የሙዚቃ መሳሪያዎች ናቸው። ይህንን ከመስጂድ ውስጥ የፈፀመ ሊባረርና ሊደበደብ የሚገባው ጠማማ ሙብ - ተዲዕ ነው፡፡ ምክንያቱም አላህ እንዲላ፞ቅ ያዘዘውን ነገር እያቃለለ ነውና፡፡ … (ከመስጂድ ውስጥ) የዘፈነ ወይም የጨፈረ ቅጣት የሚገባው የሆነ ጠሞ አጥማሚ ሙብተዲዕ ነው፡፡” [ሐቂቀቱ ሱና፞ ወልቢድዐ፡ 191]

5. አልኢማም አሶ፞ንዓኒይ (1182 ሂ.):–

"ጭፈራና ጭብጨባ የአመፅና የብልግና ሰዎች ስራ ነው። አላህን የሚወድና የሚፈራ ሰው ተግባር አይደለም።" [ሱቡሉ ሰ፞ላም: 3/130–131]

Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

መውሊድን የማንም ጩኸትና ጋጋታ ፍቁድ አያደርገውም። ለነብዩ ﷺ ያለን ውዴታ መግለጫ አድርጎ ማቅረብም የለየለት ማምታታት ነው። ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ሱፊያዊ ውርስ ከማስቀጠል ያለፈ መረጃም አላማም የለውም። ከነብዩ ﷺ ሞት ከመቶዎች አመታት በኋላ የመጣ ቢድዐ ሳይፈፀም ነብዩን ﷺ መውደድ አይቻልም ብሎ ከማሰብ በላይ ድንቁ * ርና የለም። የመውሊድ ቢድዐን ተቃወማችሁ ብሎ ነብዩን ﷺ ትጠላላችሁ የሚል አካል ስሜትና ድንቁ * ርና ቤት የሰራበት ከንቱ ፍጡር ነው። ሰለፎቹ መውሊድን ያላከበሩት ነብዩን ﷺ ስለማይወዱ ነው?

Ibnu Munewor

=
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

اسلام عليكم ورحمةالله وبركاته

✍ሰለምቴ ለሆኑ ወንድም እህቶች!!

  ሼር  አድርጉ  ሼር ማድረግ ማንን ገደለ!

       የአላህ ፍቃድ ሆኖ ከጨለማ ወደ ብርሃን የመጣችሁ ወንድም  እህቶች ሆይ! ዛሬ በአላህ ፍቃድ  አጠር ያለች ምክር  በጌታዬ ፍቃድ ላደርስላችሁ ወደድኩኝ !

👉 የመጀመሪያው ምክሬ   በመታገስ ላይ አደራ።ትግስት ከሚባለው በላይ ወሳኝና አስፈላጊ መሆኑን አትዘንጉ ።ፈተና መከራው ብዙ ነው ከጓተኛ ከቤተሰብ ከዘመድ ብዙ ትችቶች መገለል ወዘተ ይከሰታል ሌላው ቀርቶ መጀመራ   ያስጠጉ ሙስሊሞች  ራሱ በሆነ አገጣሚ ሊበድሏቹ ይችላሉ። ግን  "ለኸይር ነው" በሉና በያዛችሁት ሐቅ ላይ ፅኑ።  ማንም  ቢበድልህ   አላህ ያደለህን ኢስላምን ለመልቀቅና ወደ ነበርክበት ጨለማ  ለመግባት መወሰን የለብህም ።ከሐቅ ቦኃለ ጥመት እንጂ ሌላ የለም እና  አጭር ለሆነቿ የዱንያ ፈተና ብለክ  ዘላቂና ዘውታሪ  ከሆነቿ ጀነት  አታፈገፍግ።

ኢስላምን በሙስሊሞች በደል ወይም በነሱ ምክንያት ለቀህ ብቶጣ ራስህን ነፍሲያህን ነው የምትጎዳው ።ያንተ መሄድም ይሁን መምጣት ለኢስላምና ለሙስሊሞች የምትጨምረው የምትቀንሰው ነገር የለም ።

ወደ ሐቅ የመራህ የሆነው  አላህ  "ሰዎች አሰቡን  አመንን ስላሉ ብቻ ሳይፈተኑ የሚተው መሰላቸውን ከነሱ በፊት ያለፉ ሂዝቦች እንደተፈተኑ ይፈተናሉ"። ይላልኮ ፈተና እንደሚከሰት እርግጠኛ መሆን ከዚያ እርግጠኛ የሆንክበት ጉዳይ  ሲከሰት መታገስ ከአላህ የተሻለ ሚንደ በመፈለግ  ዱዓ  እያደረጉ የተሻለው ጊዜ እስኪመጣ መታገስ መቻል ግድ ይላል።

ደሞ ከማንም ምንም አትጠብቅ ።ካደረጉልህ  ያድርጉልህ። ወደ ሐቅ በመራህ ጌታህ  ተመክተህ ዱዓ እያደረክ ሰበቡን አድርስ።ሁሉም ነገር ለምን በፍጥነት አልተስተካከለልኝም አትበል ትግስት ነው ብዙን ነገር የሚቀይረውና እስከመች ነው የምታገሰው አትበል ዱንያ በሙሉ ላንተ ብቻ ሳቶን ለመላው ሙስሊሞች ፈተና ናት ስለዚህ  በዱንያ እስካለህ ድረስ  ሁሌም  ታጋሽ መሆን አለብህ ሁላችንም ታጋሽ መሆን አለብን

ሰይጣን ስላመለጥከው ሰበብ አስባቡን እየፈለገ ወደ ነበርክበት ጨለማ ሊመልስህ እንደሚታገልህ አስተውላህ በር አትክፈትለት።  ሰይጣን ሰዎችን ሰዒር የምትባል ጀሀነም ውስጥ ጓዶች እንዲሆኑት  እንደሚጠራ አላህ ነግሮናል።

እናም አላህ ወደ ቅን መንገድ መርቶክ "ፈተና ለምን አገኘችኝ"ብለህ ወደ ኋለ የምትል /የምትይ/ከሆነ  አላህን ሳይሆን ረሳችሁን ነውና አደጋ ላይ የምትጥሉት አስቡበት ።

አማኝ ማለት ከኩፍር /ከክህደት/ከተመለሰ ቦኃለ ወደ  ክህደት መመለስን ሊጠላ ነው ኢሳት ውስጥ መጣልን  እንደሚጠላው።

ስለዚህ ወንድም እህቶች ዛሬ ነገ አይደለም ነገ ሌላ ቀን ነውና ከችግር ቦኃለ  በርግጥም ምቾት አለ ነውና ቃሉ  ከምንም በላይ በመታገስ በመረጋጋትና ኢስላምን በመማር ላይ በርቱ አላህ  ሁሉንም ነገር ለናንም ለኛም ያግራላችሁ ያግራልን ጨርሻለሁኝ


/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮምሽን አብቹ ነጋሳን በአፋጣኝ ለህግ አቅርቡ! የማታቀርቡ ከሆነ እርምጃ መዉሰድ ኀይማኖታዊ ግዴታችን ነዉ!
••••••••••••••••••••••••••••••
Mujib Amino

Abbichuu Nagaasaa (አቢቹ ነጋሳ ) የፌስቡክ ስሙ ነው። ሌት ተቀን Lelloo Nagaa (ሌሎ ነጋ ) ከምትባል ባለቤቱ ጋር በመሆን ኢስላምንና ሙስሊሙን ህብረተሰብ ስም ሲያጠለሹ ነዉ የሚታወቁት።

ታላቁን ነብይ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ክብርን ለማዋረድ፣ ስድብና ዘለፋ ፈጽሟል። እንዲህ ያለ ነዉር በማስተባበል፣ በይቅርታ፣ ...በየትኛዉም አይነት መንገድ አይቀልም፣ አይፈታም።

አድራሻው በአዲሱ ሸገር ሲቲ ሱሉልታ ተብሎ በሚታወቀዉ ልዩ ቦታው ኸጅማ ነዉ። ከዳሽን ባንክ በስተጀርባ አንድ ሱቱዲዮ እንዳለዉ ይነገራል። ስልክ ቁጥሩም 📲0913270202 ይህ ነው።

ይህ ነዉረኛ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ለማንጓጠጥ በልቡ የፈራዉን የጥላቻ ፍሬ ከበተነ ወዲህ ገጹ ላይ ያሰፈረዉን ልጥፍ ከቆይታዎች ቡኃላ አንስቶታል። ልጥፉን ካጠፋ ቡኃላም የፌስቡክ አካዉንቱን Deactive በማድረግ ከላይ የተገለጸዉንም ስልክ ቁጥር ዘግቷል።

ለጊዜዉ ስልኩን በማጥፋት ለመሰወር ቢሞክርም፣ በኦሮሚያ የምትኖሩ በተለይም በሸገር ሲቲ (ሱሉልታ) መግቢያ መዉጫዉን በመፈለግ ለሕግ እንድታቀርቡ እንገልጻለን።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮምሽን ይህን ነዉረኛ ግለሰብ በአፋጣኝ ለሕግ የማቅረብ ስራ ካልሰራ ማህበረሰባችን ለሚወስደዉ ማንኛዉም እርምጃ ኀላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እናሳዉቃለን።

N.B (ረሱል(ሰ.ዐ.ወ)ምን በቃላት ያነወረበትን አርፍተ ነገር ለክብራቸዉ ስል አለጠፍኩትም።)

Читать полностью…
Subscribe to a channel