ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot
ዩሱፍ አልዐይደሩስ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
ኡስታዝ ሳዳት ከማል
በዒባዳችን ጣዕም
ያጣነው ለምንድን ንው?
t.me/NABAWITUBE
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
ሁሉም ነብስ ሞትን ቀማሽ ናት!
ለሞት መዘጋጀት
t.me/NABAWITUBE
ሶላት የረሳ ሰው ሲያስታውስ ይሰግዳል። የመጀመሪያውን በማስቀደም ቅደም ተከተሉን ይጠብቃል። ለምሳሌ ዙህርን ረስቶ የዐስር ወቅት ከገባ በኋላ ቢያስታውስ መጀመሪያ ዙህርን ይሰግዳል። ከዚያ ዐስርን ያስከትላል።
ዐስርን መስገድ ከጀመረ በኋላ ካስታወሰ ግን የጀመረውን ያጠናቅና ከዚያ ዙህርን ይሰግዳል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
ሸይኽ ዐብዱልከሪም አልኹዶይር እንዲህ ይላሉ፦
"ልብ ሳይገነዘብ እንዲሁ በምላስ ጫፍ የሚፈፀሙ ዚክሮች ይጠቅማሉ። ነገር ግን ምላስ ከልብ ጋር የተዋሀዱባቸው ዚክሮች የሚኖራቸውን ያክል ውጤትና ምንዳ አይኖራቸውም።" [አተዕሊቃቱ ሰኒያህ፡ 116]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።
በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።
የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።
ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።
ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።
እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።
እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።
እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።
እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።
ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
ተጠንቀቅ! ደካማ አያልቅስብህ
~
በጉልበትህ፣ በስልጣንህ፣ በወገንህ፣ በሃብትህ፣ ... ተማምነህ ሰዎችን አትግፋ። "ጌታዬ! እኔ አቅም የለኝም፣ አንተ ፍረደኝ!" ብሎ ሰው ካለቀሰብህ ወላሂ ወዮልህ! ያኔ እርቃንህን ብቻህን ከአላህ ፊት ለምርመራ ስትቀርብ ምን ይውጥሀል?! ያኔ ዛሬ የተመካህበት ጉልበት ይከዳሀል። ያኔ ዛሬ የጠገብክበት ስልጣን ያዋርድሃል። "ምነው በቀረብኝ?!" ትላለህ። ያኔ ዛሬ የተመካህበት ዘመድና ወገን ጥሎህ ይሸሻል።
{ فَإِذَا جَاۤءَتِ ٱلصَّاۤخَّةُ (33) یَوۡمَ یَفِرُّ ٱلۡمَرۡءُ مِنۡ أَخِیهِ (34) وَأُمِّهِۦ وَأَبِیهِ (35) وَصَـٰحِبَتِهِۦ وَبَنِیهِ (36) لِكُلِّ ٱمۡرِئࣲ مِّنۡهُمۡ یَوۡمَىِٕذࣲ شَأۡنࣱ یُغۡنِیهِ (37) }
"አደንቋሪይቱም (መከራ) በመጣች ጊዜ፤ ሰው ከወንድሙ በሚሸሽበት ቀን፤ ከእናቱም ከአባቱም፤ ከሚስቱም ከልጁም እንዲሁ። ከእነርሱ ለየሰው ሁሉ በዚያ ቀን (ከሌላው) የሚያብቃቃው ሁነታ አልለው።" [0በሰ፡ 33-37]
=
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
ከሶላት በኋላ የተስቢሕ አፈፃፀም
~
1- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ። 100ኛ "ላ ኢላሀ ኢለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ማለት። [ቡኻሪይ እና ሙስሊም]
2- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 34 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [ሙስሊም]
3- ሱብሓነላህ 33 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 33 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 33 ጊዜ ማለት። ድምሩ 99 ይሆናል። [ሙስሊም]
4. ሱብሓነላህ 10 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 10 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 10 ጊዜ ማለት። ድምሩ 30 ይሆናል። [ቡኻሪይ]
5. ሱብሓነላህ 11 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 11 ጊዜ፣ እና አሏሁ አክበር 11 ጊዜ ማለት። ድምሩ 33 ይሆናል። [ሙስሊም]
6. ሱብሓነላህ 25 ጊዜ፣ አልሐምዱሊላህ 25 ጊዜ፣ ላ ኢላሀ ኢለላህ 25 ጊዜ እና አሏሁ አክበር 25 ጊዜ ማለት። ድምሩ 100 ይሆናል። [አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
አፋልጉኝ!
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ከስር በፎቶ የምትመለከቷቸው አባት ስማቸው ጀማል አህመድ ይባላሉ።
በመስከረም 23/2017 ከወራቤ ወደ ሻሸመኔ ጉዞ ጀምረው በመሀል ድምፃቸው ጠፍቷል። ስልክ ሳይዙ ሰለወጡ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙበት መንገድ የላቸውም። ልጆቻቸው በከባድ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ። ምናልባት ያገኛቸው ካለ 0916692699 በመደወል ይተባበሩን።
ሼር አድርጉት።
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ከመግቢያ ሰዓቱ የሚዘገይ ወይም ቀድሞ የሚወጣ ሰራተኛ አላህ በቅጣት ከዛተባቸው አታላዮች ውስጥ ነው።"
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
ሙስሊም መሆን መታደል ነው!
ሙስሊም ስቶን ስትሰግድ ለአንድ ፈጣሪ ብቻ ስትፆም ለአንድ ፈጣሪ ብቻ ስለት ብትገባ ለአንድ ፈጣሪ ብቻ
https://youtube.com/shorts/qt-JNVa3_hU?si=aHQrX6kQAuML0Uu8
Читать полностью…ኑ ከነብዩ ﷺ ማእድ ተቋደሱ!
~
ከአቡ ሁረይራ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ የሆኑ ሰዎች፡ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በቂያማ ቀን ጌታችንን እናየዋለን?” በማለት ለአላህ መልእክተኛ ﷺ ጥያቄ አቀረቡ። የአላህ መልእክተኛም ﷺ፡ “ጨረቃ ሙሉ በሚሆንበት በወሩ 14ኛው ቀን ላይ ጨረቃን ከማየት ትቸገራላችሁን?” ብለው ጠየቁ። “በጭራሽ! የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አሉ። ፀሐይንስ ከስሯ ዳመና ሳይኖር (ለማየት) ትቸገራላችሁን?” ሲሏቸው “በጭራሽ! የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አሉ። በዚህ ጊዜ (ነብዩ ﷺ) እንዲህ አሉ፡-
“እንግዲያው በርግጥም ልክ እንደዚሁ አላህንም ታዩታላችሁ! የቂያማህ ቀን አላህ ሰዎችን ይሰበስብና ‘የሆነን ነገር ሲያመልክ የነበረ እሱኑ ይከተል’ ይላል። ከዚያም ፀሀይን ሲያመልክ የነበረ ፀሀይን ይከተላል። ጨረቃን ሲያመልክ የነበረ ጨረቃን ይከተላል። ጣኦታትን ሲያመልክ የነበረ ጣኦታትን ይከተላል። ይህቺ ህዝብ ግን ከነ ሙና .ፊቋ ትቀራለች። ቀድመው ያውቁት በነበረው ሳይሆን በሌላ ቅርፅ (ሱራ) የላቀው አላህ ይመጣቸውና ‘እኔ ጌታችሁ ነኝ’ ይላቸዋል። እነሱም ‘ኧረ ካንተ በአላህ እንጠበቃለን! እኛ ጌታችን እስከሚመጣን ድረስ ይሄው ነው ቦታችን። ሲመጣን ደግሞ እናውቀዋለን’ ይላሉ። ይህኔ የላቀው አላህ ቀድመው በሚያውቁት ቅርፁ ይመጣቸውና፡ ‘እኔ ጌታችሁ ነኝ’ ይላል። እነሱም ‘አንተ ጌታችን ነህ’ ይላሉ። ከዚያም ይከተሉታል።
በጀሀነም ጀርባዎች ላይ ድልድይ (ሲራጥ) ይዘረጋል። እኔና ህዝቦቼ መጀመሪያ የሚያቋርጡት እንሆናለን። በዚያን ቀን መልእክተኞች እንጂ ማንም ሌላ አይናገርም። የመልእክተኞችም ንግግር ያኔ፡ ‘ጌታዬ ሆይ ሰላም አርገው! ሰላም አርገው!’ የሚል ነው። ጀሀነም ላይ ልክ እንደ ቀንጠልፋ እሾህ ያሉ መንጠቆዎች አሉ። ቀንጠልፋ አይታችኋል?’
‘አዎ’ አሉ።
ከዚያም እንዲህ አሉ፡- ‘እነሱ ልክ እንደ ቀንጠፋ እሾህ ናቸው። ባይሆን የግዝፈት መጠናቸው ምን እንደሚያክል አላህ እንጂ ማንም አያውቅም። ሰዎችን በስራዎቻቸው ይጠልፋሉ። ከነሱ በስራው የሚተርፍ አማኝ አለ። ከነሱ ነፃ እስከሚወጣ ድረስ የስራውን የሚያገኝ አለ።
ከዚያም በባሪያዎቹ መካከል ያለውን ፍርድ ሲጨርስ ከእሳት ጓዶችም በእዝነቱ ሊያወጣ የፈለገውን በፈለገ ጊዜ፣ ‘ላኢላሀ ኢለላህ’ ከሚሉት በአላህ ምንም ያላጋራውን፣ የላቀው አላህ ሊያዝንለት የፈለገውን እንዲያወጡ መላእክትን ያዛል። በእሳት ውስጥም ያውቋቸዋል። የሚያውቋቸው በሱጁድ ምልክቶቻቸው ነው። የኣደምን ልጅ የሱጁድ ቦታዎቹ ሲቀር እሳቷ ትበላዋለች። የሱጁድ ቦታን እንዳትበላ በጀሀነም እሳት ላይ ክልክል አድርጎባታል። ሰዎቹ በርግጥም ተቃጥለዋል። የህይወት ውሃ በላያቸው ላይ ይፈሰስባቸዋል። ከሱም ቦይ ተሸክሞት የመጣው ደለል ጋር እንደምትበቅል ቡቃያ ይበቅላሉ።
ከዚያም የላቀው አላህ በባሪያዎቹ መካከል ያለውን ፍርዱን ሲጨርስ ፊቱ ወደ እሳት የዞረ ሰው ይቀራል። ሰውየው መጨረሻ ጀነት የሚገባው የጀነት ሰው ነው። እናም፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ፊቴን ከእሳቷ አዙርልኝ? ሽታዋ አሰቃየኝ! ወላፈኗም አቃጠለኝ!’ እያለ አላህ የፈቀደውን ያክል አላህን ይለምናል። ከዚያም የላቀውና ከፍ ያለው አላህ፡ ‘ይህን ካደረግኩልህ ሌላ ላትጠይቅ ቃል ትገባለህ?’ ይለዋል። ‘ከዚህ ውጭ አልጠይቅም’ ይላል። አላህ የፈለገውን ያክል (ሌላ ላይጠይቅ) ለጌታው ቃል ይገባል። ማጠናከሪያም ያስቀምጣል። ከዚያም አላህ ፊቱን ከእሳቷ ያዞርለታል።
ከዚያም ወደ ጀነት ሲዞርና ሲመለከታት ጊዜ አላህ የፈቀደውን ያክል ዝም ይላል። ከዚያ ግን፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ወደ ጀነት በር አቅርበኝ?’ ይላል። አላህም፡ ‘ከሰጠሁህ ውጭ ላትጠይቅ ቃልኪዳንና ማጠናከሪያዎችን አልሰጠህም ነበር? ወዮልክ የኣደም ልጅ! ምንኛ ቃል አፍራሽ ነህ?!’ ይለዋል። ሰውየውም፡ ‘ጌታዬ ሆይ!’ እያለ አላህን ይለምናል። ከዚያም ‘ይህን ካደረግኩልህ ሌላ ላትጠይቅ ቃል ትገባለህ?’ ይለዋል አላህ። ‘በክብርህ ይሁንብኝ! ሌላ አልጠይቅም’ ይላል። አላህ የፈለገውን ያክል ለጌታው ቃል ይገባል። ማጠናከሪያም ያስቀምጣል። ወደ ጀነት በርም ያቀርበዋል። ጀነት በር ላይ ሲቆም ጊዜ ጀነት ትከፈትለታለች! በውስጧ ያሉትን መልካም ነገሮችንና ደስታዎችን ያያል። አላህ የፈቀደውን ያክልም ዝም ይላል። ከዚያም፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ጀነት አስገባኝ?’ ይላል። አላህም፡ ‘ከሰጠሁህ ውጭ ላትጠይቅ ቃልኪዳንና ማጠናከሪያዎችን አልሰጠህም ነበር? ወዮልህ የኣደም ልጅ! ምንኛ ቃል አፍራሽ ነህ?!’ ይለዋል። ሰውየውም፡ ‘ጌታዬ ሆይ! ከፍጡሮችህ የመጨረሻ እድለ-ቢሱ አልሁን!’ እያለ የላቀውና ከፍ ያለው አላህ በሱ እስከሚስቅ ድረስ ይለምናል። አላህ በሱ ከሳቀ በኋላ፡ ‘ጀነትን ግባ’ ይለዋል። ከገባ በኋላ ደግሞ አላህ፡ ‘(ያሻህን) ተመኝ’ ይለዋል። ከዚያም (ምኞቱ አልቆበት) አላህ፡ ‘ይህም አለ’፣ ‘ይህም አለ’ እያለ እስከሚያስታውሰው ድረስ ጌታውን ይለምናል። ይመኛልም! ምኞቶቹ ሲያልቁበት ጊዜ አላህ፡ ‘ያን (የተመኘኸውን) እና አምሳያውን (ተሰጥቶሀል)’ ይለዋል።”
አቡ ሁረይራ ይህን ሲተርኩ አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ አብረው ነበሩ። ነገር ግን ምንም አይመልሱም ነበር። አቡ ሁረይራ አላህ ለሰውየው፡ “ያን (የተመኘኸውን) እና አምሳያውን (ተሰጥቶሀል)” እንደሚለው ሲናገሩ ግን (አቡ ሰዒድ)፡ “ ‘ከሱው ጋር #አስር አምሳያውን’ ነው የተባለው” አሉ። አቡ ሁረይራ፡ “እኔ ግን ‘ያን (የተመኘኸውን) እና አምሳያውን’ የሚለውን ብቻ ነው የያዝኩት” ሲሉ። አቡ ሰዒድ ደግሞ፡ “እኔ ግን ‘ከሱው ጋር አስር አምሳያውን’ የሚለውን ከአላህ መልእክተኛ ﷺ እንደያዝኩኝ እመሰክራለሁ” አሉ። አቡ ሁረይራ፡ “ይሄ ሰውየ ነው ከጀነት ሰዎች መጨረሻ ጀነትን የሚገባው” አሉ። [አልቡኻሪይ፡ 806] [ሙስሊም፡ 469]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
ሱረቱል ከህፍ ቂረአት ሙሉውን
〰〰〰〰〰〰〰〰
🎙አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን
የሞኝ ቀልድ አትቀልድ!
~
በጩቤ፣ በዱላ፣ በመጥረቢያ፣ በመኪና፣ በጦር፣ በጠመንጃ፣ በሰይፍ፣ … ሰዎች ለማስደንገጥ ከመቀለድ፣ ከመቃጣት ተጠንቀቅ። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
من أشار إلى أخيه بحديدة فإن الملائكة تلعنه حتى ينتهي.
"ወደ ወንድሙ በመሳሪያ የጠቆመ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።" [ሙስሊም]
በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል:–
لا يحل لمسلم أن يروع مسلماً.
"ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።"
አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል።
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:– "አንድ ሰው የምሩንም ይሁን በቀልድ ወደ ወንድሙ ጠመንጃ ሊያዞር አይፈቀድለትም። መኪናም እንዲሁ (አይፈቀድም)። የከፋ ነውና።" [ሸርሑ ሶሒሒል ቡኻሪ: 9/ 502]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 30/2010)
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
2ኛ ከለርድ እትም
ከተወሰነ ጭማሪጋ
የተዳሰሱ ርዕሶች
👉 ሕይወቴ በጴንጤ ዓለም ሳለሁ
👉 ሐይማኖት አልባነት
👉 እንዲህ ነበር የሰለምኩት
👉 ከሰለምኩ ኋላ
👉 ያቺ ጉደኛ ምሽት
👉 መንግስተ ሰማይና ገሀነም ደርሰን መጣን ያሉ ትናንሽ ደጃሎችና ወዘተ
/channel/Abuenqurarit
ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
የአብዛኞቻችን ልብ ሞቷል
t.me/NABAWITUBE
ጣፋጭ ቲላዋ ከኡለማዎች አንደበት
🎙 በሸይኽ ሱለይማን አል-ሩሓይሊ ሓፊዘሁላህ
~ t.me/Darutewhide
አስቸኳይ ማስታወቂያ
መረከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዓሪ ለአዳሪ የቁርአን ሒፍዝ ፕሮግራም ኡስታዞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል ።
ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1, ቁርአንን መርከዝ ዉስጥ በጥሩ ተጅዊድ እና ሙራጅዓ የሀፈዘ ::
2, የቁርአን ሽሀዳ ያለውና መርከዝ ዉስጥ አስተምሮ የሚያዉቅ ::
3, መሰረታዊ የተጅዊድ ህግጋቶች ላይ ግንዛቤ ኖሮት ማስተማር የሚችል ።
4, የስለፊያን ዳዕዋ የተረዳ, ኪታቦችን የቀራና የ ማስተማር ልምድ ያለው ።
5, ለተማሪዎች በሁለንተናው ጥሩ አርአያ መሆን የሚችል እና የማስተማር ልምድ ያለው
6, እድሜው ከ 23 ዓመት በላይ የሆነ ::
7, ብዛት : 2
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ከታች ባለው ዩዘር ኔም ያናግረን ።⤵️⤵️⤵️
📞 0930547776
@AbulAbasNasirMuhammed
ምንኛ ደስ የሚያሰኝ ርብርብ ነው! ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ የሚችለውን እያደረገ ነው። በዚህ የመስጂድ ግንባታ ላይ የሶደቀቱን ጃሪያ ድርሻ እንዲኖረው የሚሻ ያቅሙን በማገዝ ለኣኺራው ስንቅ ያስቀምጥ።
መስጅደል ፉርቃን በወረባቦ ወረዳ ዋና ከተማ ቢስቲማ ላይ እየተሰራ ያለ መስጂድ ነው። መስጂዱ ለከተማው ድምቀት ነው። ከዚያ በላይ ግን ለከተማውም በዙሪያው ላሉ ቀበሌዎችም ጥሩ የደዕዋ መነቃቃት ይፈጥራል ተብሎ ይጠበቃል፣ ኢንሻአላህ።
መርዳት ለምትፈልጉ ከታች በተለጠፈው አካውንት ገቢ ማድረግ ትችላላችሁ።
#ወረባቦ ፉርቃን መስጂድ
ንግድ ባንክ - 1000401221957
አቢሲኒያ - 64828638
ዳሽን - 2935824167011
መልእክቱን በማሰራጨት ተባበሩን። ምናልባት በናንተ በኩል ተሳትፎ የሚያደርግ ቢኖር ከአጅሩ ተካፋይ ትሆናላችሁ።
{ مَنْ دَلَّ عَلَى خَيْرٍ فَلَهُ مِثْلُ أَجْرِ فَاعِلِهِ }
"ሌሎችን ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የተገበረውን ሰው አምሳያ ምንዳ ይኖረዋል።"
=
ቴሌግራም ቻናል:-
/channel/IbnuMunewor
ሁድሁድ የተሰኘው የአዕዋፍ ዝርያ ዜና ሲያስተላልፍ ዲሲፕሊን በተሞላበት መልኩ ነበር። «ሰማሁኝ ወይም ይላሉ» የሚሉ ገለጻዎችን በጭራሽ አይጠቀምም። ለነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) (وَجِئْتُكَ مِن سَبَإٍۭ بِنَبَإٍۢ يَقِينٍ) «ከሰበእም እርግጠኛ የሆነን መረጃ አመጣሁልህ» አላቸው።
ግና ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) ሁድሁድ በእርሳቸው ላይ ለመዋሸት ቅንጣት እንደማይደፍር እርግጠኛ ቢሆኑም እንኳ እንደኛ መረጃን በንፋስ ፍጥነት ኮፒ ፔስት ለማድረግ አልቸኮሉም። ይልቅ ምላሽ የሰጡት
(سَنَنظُرُ أَصَدَقْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْكَٰذِبِينَ)
« ያልከው እውነት መሆኑን ወይም ከዋሾዎች መሆንህን በቅርቡ እናያለን» በማለት ነበር።
መረጃን ግራ ቀኝ ተመልክቶ ማረጋገጥ ሸሪዓዊ መስፈርት እና ነብያዊ ስልት ነው። እርግጠኛ ያልሆንክበትን ነገር ከማሰራጨት መቆጠብ ትርፍ ባታገኝበት እንኳ አትከስርም።
t.me/IbnuHashm
የሰዎች ትንኮሳ መቼ ነው የሚጎዳህ?
~
ሰዎች በንግግር፣ በፅሁፍ፣ በሃሜት፣ በየትኛውም አይነት ክፉ ቃል ሲፈትኑህ እየተብከነከኑ ጤናንም፣ ሰላምንም፣ እንቅልፍንም ማጣት አይገባም። ቢቻል አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ነው። ካልሆነ ግን የሚፈትሉትን ክፋት እዚያው እነሱው እንዲጠመዱበት መተው ነው። በመርሳት ሰላምህን ጠብቅ። ካልሆነ ግን ክፋታቸው ሳይሆን ማብሰልሰልህ ይጎዳሀል። ሰዕዲይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦
"የሰዎች ትንኮሳ አይጎዳህም። ይልቁንም እነሱኑ ነው የሚጎዳቸው። ትኩረት በመስጠት ራስህን ካልጠመድክ በስተቀር። ያኔ እንደሚጎዳቸው አንተንም ይጎዳሀል። ቦታ ካልሰጠኸው ግን ምንም አይጎዳህም።"
[አልወሳኢሉል ሙፈደህ ሊልሐያቲ ሰዒደህ፡ 30]
=
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
ሐበሻ በአልዑመሪ እይታ
~
የፀሐፊው ሙሉ መጠሪያ አቡል ዐባስ ሺሃቡዲን አሕመድ ብኑ ፈድሊላህ ብኒ የሕያ አልዑመሪ ይባላል። ባጭሩ ኢብኑ ፈድሊላህ አልዑመሪ ወይም አልዑመሪ በመባል ይታወቃል። በሂጅራ አቆጣጠር ከ 700 እስከ 749 ባለው ነው የኖረው። በአውሮፓው አቆጣጠር ሲታይ በ1349 ነው የሞተው። ታዋቂ የታሪክ፣ የጂኦግራፊ እና የ'ኢትኖግራፊ' ምሁር ነው። ከበርካታ ኪታቦቹ ውስጥ مسالك الأبصار في ممالك الأمصار ስራው በሰፊው ይታወቃል። የሙስሊሙን ዓለም እና አጎራባች ህዝቦችን ባህል፣ ልማድ፣ ቋንቋ፣ ጂኦግራፊ፣ የአየር ንብረት፣ ... በ 27 ቅፅ (ሙጀለድ) የዳሰሰ ስራ ነው። ይሄ ትልቅ ስራ ስለ ሃገራችን ኢትዮጵያ በሃገር ውስጥ ምንጮች ውስጥ የማይገኙ በርካታ መረጃዎችን ይዟል። በተደጋጋሚ በዚህ ስራ ውስጥ ያሉ መልእክቶችን ጨምቄ ማቅረብ እየፈለግኩኝ ሳይሆንልኝ ቀርቶ ነበር። ዛሬ ባጭሩ ነካ ማድረግ እፈልጋለሁ።
በቀደምት ምንጮች ላይ እንደሚታወቀው ሐበሻ በሚል ነው የሚገልፃት። በዚህ ስያሜ የሚታውቀው ግዛት ዛሬ ካለችው ኢትዮጵያ በእጅጉ የሰፋ ነው። በምስራቅና ሰሜን ምስራቅ በኩል የሃገሪቱ ድንበር ህንድ ውቅያኖስና የመን ነው። ቀይ ባህርንም የሐበሻ ባህር በሚል ነው የሚጠራው።
ሐበሻ ቀደም ባለው ዘመን መናገሻ ከተማዋ አክሱም እንደነበረች የምትገኘውም በሰሐርት ግዛት ውስጥ እንደሆነ፣ ሰሐርት ቀደም ብሎ ቲክራይ (ትግራይ?) በመባል ትታወቅ እንደነበር ይገልፃል። በፀሀፊው ዘመን የመንግስቱ ዋና ከተማ በአምሐራ ግዛት ውስጥ እንዳለ ሲገልፅ መርዐዲ በመባል ትታወቃለች ይላል። ከአምሐራ ቀጥሎ ሸዋ፣ ዳሞት፣ ላምናን፣ ሲሁ፣ ዘንጅ፣ ዐድሉል ኡመራእ ( ፍትሐ ነገስት?) ፣ ሐማሳ፣ ባሪያ፣ ሰባቱ ኢስላማዊ ሱልጧኔቶች እንዳሉ ሲጠቅስ እነዚህ ሁሉም የየራሳቸው ንጉስና ሰራዊት አላቸው። ትልቁ መሪያቸው በቋንቋቸው አፄ በመባል ይጠራል። በዘመኑ ያለው ንጉስ አፄ አምደ ፅዮን ነው ይላል።
የአባይን ወንዝ ሲሁን ብሎ ነው የሚጠራው፣ ግዮን የሚለው ይመስለኛል። የህዝቡ አለባበስ በክረምትም በበጋም አንድ አይነት ነው። ከጥጥ የሚሰራ ያልተሰፋ ልብስ ሲሆን እያንዳንዱ ሰው ሁለት ልብሶች አሉት፤ ከላይ የሚለበስ አንድ ከስር የሚታጠቁት ሌላ። ቁምጣና ቦላሌው ብዙም አልነበረም ማለት ይሆን?
አብዛኛው ግብይታቸው እቃ ለእቃ ልውውጥ ነው። ከሰባቱ የኢስላማዊ ሱልጧኔቶች ውስጥ በአምስቱ የነበረው ግን ከዚህ ይለያል። የኢፋት ሱልጧኔት ዋና ከተማ ላይ የወርቅና የብር ሳንቲሞችን ይጠቀማሉ። ደዋሮ፣ አሪቢኒ (አርባቢኒ?)፣ ሸርኻ እና ሀዲያ ሱልጧኒቶች ሐከና ብለው የሚጠሩት በትልልቅ መርፌ ቅርፅ የሆነ መገበያያ ይጠቀማሉ።
የሐበሻ ህዝቦች በአመት ሁለት ጊዜ ዝናብ ተጠቅመው ያመርታሉ። በሁለቱ ወቅቶች የሚገኘውን ዝናብ በል (በልግ?) እና ክረም (ክረምት) ብሎ ጠቅሷል። ስንዴ፣ ገብስ፣ በቆሎ፣ ጤፍ እና ሌሎችም የእህልና የጥራጥሬ አይነቶች፣ ፍራፍሬዎች እንዳሉ ያወሳል። በኢስላማዊ ሱልጧኔቶቹ ውስጥ በተለይም በኢፋት ሸንኮራ አገዳ እንዳለ ይጠቅሳል።
በሐበሻ ምድር የሚገኙ የሙስሊም ሱልጧኔቶችን በተመለከተ በቁጥር ሰባት እንደሆኑ ሲጠቅስ ከነዚህ ውስጥ ሰፊው ኢፋት (እሱ አውፋት እያለ ነው የሚጠቅሰው) ሲሆን በሰራዊት ብዛት ጠንካራው ደግሞ ሀዲያ እንደሆነ ይጠቅሳል። እነዚህ ሱልጧኔቶች አቅማቸው ደካማ፣ ሀብታቸው አነስተኛ፣ በመካከላቸው መጣጣም የሌላቸው የተለያዩ እንደሆኑ ያነሳል። አብዛኞቹ ስፋታቸው በጣም አነስተኛ ነው። ከአምሐራው ገዢ በኩል ጫና እንዳለባቸውና በመካከላቸው ያለውን ፉክክር ትተው ቢግባቡ ኖሮ መጋፈጥ ይችሉ እንደነበር የነስቡ ራያን ኪታብ አዘጋጀ ታዋቂውን ዘይለዒይን ያጣቅሳል።
የነዚህ ሰባት ግዛቶች ነዋሪዎች እምነታቸውን የሚተገብሩና የሚጠብቁ ናቸው። መድረሳዎችና የሱፍያ ዛውያዎች እንደሌሉም አውስቷል።
የኢፋት ሱልጧኔት ግዛት ከመሀል ሃገር እስከ ዘይላ (ሶማሊያ ጠረፍ) እንደሚዘረጋ ይገልፃል። የአብዛኛው ነዋሪ አለባበስ ሽርጥና ኮፍያ እንደሆነ ፉቀሃኦቹ ዘንድ ደግሞ ቀሚስና ጥምጣም እንደሚለበስ ይጠቅሳል። ይሄ እንግዲህ እነዚህ ልብሶች በቅርብ ከዐረቢያ የመጡ ለሚመስላቸው አካላት የሚሰጠው ጥቆማ አለው። ሱሪ መልበሱም ቢሆን ጦሩ አካባቢ እንዳለ አንስቷል።
የኢፋት ህዝቦች ቋንቋቸው ሐበሽኛ እና ዐረብኛ ነው። ዐረብኛ በሰፊው እንደነበር አስተውሉ። ኋላ በምን ምክንያት ጠፋ ታዲያ? ሐበሽኛ የሚለው ሌሎች ቦታዎች ላይ ከተጠቀሱ ነጥቦች ጋር ስናዛምደው አማርኛውን ነው የሚመስለው።
ኢፋት ውስጥ የሚገኙ የእህል፣ ጥራጥሬ፣ ፍራፍሬና የአትክልት አይነቶችን ሲዘረዝር አንዱ የጠቀሰው ጫት ነው። ፍሬ እንደሌለው፣ የሚበላው ቅጠሉ እንደሆነ፣ ማስተዋልን እንደሚጨምር፣ የሽምደዳ (ሒፍዝ) ችሎታን ለማዳበር እንደሚያግዝ፣ የረሳን እንደሚያስታውስ፣ ደስታን (ምርቃና?) እንደሚሰጥ፣ የምግብ፣ የእንቅልፍና የግንኙነት ፍላጎትን እንደሚቀንስ፣ ሁሉም እንደሚበሉትና እንደሚጓጉለት ይገልፃል። ስለዚህ የጫት ወረራው የጥንት ነው ማለት ነው። አፄዎቹ አሰራጭተውብን ነው የሚለው የአንዳንዶች ክስ እዚህ ላይ ጥያቄ ውስጥ ይገባል። በተለይ ደግሞ ዒልም ፈላጊ ደረሶች፣ በስራ እና በሌሊት ጉዞ ምክንያት ሌሊቱን ነቅተው ማሳለፍ የሚሹ ሰዎች ይጠቀሙታል። እዚህ ላይ ከጫት ጋር ተያይዞ የየመኑ ጫት ራሱ መነሻው ሐበሻ እንደሆነ ጥቆማ የሚሰጥ አስገራሚ ታሪክ ጠቅሷል። ስለ ኢፋት ህዝብ አመጋገብ ሲያነሳ ብዙም ዶሮ መብላትን አይፈልጉም፤ ቆሻሻ ስለምትበላ ይፀየፋሉ ይላል።
የደዋሮ ሱልጧኔትን በተመለከተ የኢፋት ጎረቤት እንደሆነና ስፋቱ ትንሽ ቢሆንም ከኢፋት ጋር የሚቀራረብ ጠንካራ ሰራዊት እንደነበረው ይገልፃል።
የሀዲያ ሱልጧኔት ስፋቱ ትንሽ ቢሆንም ከሰባቱ ሱልጧኔቶች ሁሉ ጠንካራ ሰራዊት ያለው ነበር። የደዋሮ፣ የሀዲያ፣ የአራቢኒ፣ የሸርኻ፣ የዳራ እና የባሊ ሱልጧኔቶች ሁለ ነገራቸው አንዱ ከሌላው ጋር ተመሳሳይ ነው። ከኢፋት በተለየ ሁሉም የሐነፊያ መዝሀብ ተከታይ ናቸው። በኢፋት ግን የሻፍዒያ መዝሀብ ነበር በሰፊው የነበረው። እነዚህ ሱልጧኔቶች ሁላቸውም ለኢፋት ሱልጧኔት አክብሮት አላቸው። በአንዳንድ ጊዜም ከጎኑ ይቆማሉ።
የሐበሻ ህዝብ ብዛት አለው፡፡ ሃይለኞች እና ጦረኞች ስለሆኑ ከነሱ ውጭ ያለ አካል ገዝቷቸው አያውቅም። ከጀግንነታቸው ባሻገር ይቅር ባዮች ነበሩ። በጦርነት ላይ መሳሪያውን የጣለን ሰው አይነኩም። እንግዳ አክባሪዎች ናቸው። ለዚህም የነጃሺን ቁረይሽን መቀበሉን ማጣቀሻ ያደርጋል። ማስመሰል የላቸውም። በእውነተኝነትና በታማኝነት ይታወቃሉ። ግን እነዚህ መልካም ስብእናዎች ዛሬ የሐበሻ ህዝብ ላይ ምን ያህል አሉ?
ሌላ ያነሳው ነገር ዘራቸው አይነቱ አንድ ቢሆንም ከ50 የሚበልጡ ቋንቋዎች እንዳሉ የሁሉም መፃፊያ ፊደል አንድ እንደሆነ እሱም ሐበሽኛ (አማርኛ?) እንደሆነ ነው። የሚፃፈውም ከቀኝ ወደ ግራ ነው፣ ልክ እንደ ዐረብኛው ማለት ነው። መቼ ይሆን ታዲያ ዛሬ ያለው የአማርኛ አፃፃፍ ከግራ ወደ ቀኝ ወደ መፅፃፍ የዞረው? የፊደል ገበታው 16 ፊደሎችን የያዘ እንደሆነና እያንዳንዱ ሰባት ሆሄያት እንዳለው ጠቅሷል። እንደሚታወቀው በየጊዜው እየተጨመረ ነው ዛሬ የደረሰበት የደረሰው።
መረጃዎቹን ጨምቄ ነው ያመጣኋቸው። የፈለገ ሰው የተጠቀሰውን ኪታብ 4ኛ ቅፅ ከገፅ 31 እስከ 44 መመልከት ይችላል። ተጨማሪ መረጃዎችን የፈለገ አልመቅሪዚይ እና አሰኻዊይ የፃፉትን ማየት ይችላል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 25/2017)
/channel/IbnuMunewor
ጥያቄ፦ በአውሮፕላን እጓዛለሁ። አንዳንዴ የጉዞው ቆይታ ረጅም ይሆናል። በዚህን ጊዜ ሶላትን በወቅቱ ብሰግድ ነው ወይስ መሬት ስወርድ እሰግድ ዘንድ መጠበቅ ነው በላጩ?
መልስ፦
ርቀቱ የሶላት ወቅት የሚወጣበት ነው ወይስ አይደለም በሚለው መሰረት ነገሩና ብይኑ ይለያያል።
* ማዘግየቱ ሶላትን ከወቅቱ የሚያስወጣ ከሆነ፤ ለምሳሌ የፈጅር ሶላት ወቅት ፀሐይ የምትወጣ በመሆኑ የሚያልፍበት ከሆነ ባለበት ሁኔታ አውሮፕላኑ ላይ ይሰግዳል።
* ጉዞው ሲጠናቀቅ ወቅት የሚያገኝ ሆኖ መሬት ላይ ሙሉ ሶላትን መስገድ የሚችል ከሆነ በዚህ ላይ ማዘግየቱ በላጭ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፣ ልክ ነብዩ - ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም - በመፈፀሟት መልኩ ይፈፅማት ዘንድ ማለት ነው።
ሸይኽ ዐብዱልከሪም አልኹዶይር
=
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/IbnuMunewor
ክርስቲያኖች ግን ፈጣሪ አንድ ነው ይላሉ ግን በተግባር ሲታዩ የሚያመልኩት ብዛቱ!!
Читать полностью…ጥሪ ለአስተዋይ ክርስቲያኖች
~
ክርስትና ውስጥ ከሚመለኩ ነገሮች ውስጥ አንዱ መስቀል ነው። በገሃድ የምናየው ከመሆኑ ጋር መፅሀፍ መጥቀሱ አይከፋም፡፡ ይሄውና :-
- “ዓለምን ለማዳን ሲል እየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀልም እሰግዳለሁ፡፡ መስቀል ሀይላችን ነው፡፡ ሃይላችን መስቀል ነው፡፡ የሚያፀናን መስቀል ነው፡፡ መስቀል ቤዛችን ነው፡፡ አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን፡፡ ያመነውም እኛም በመስቀሉ እንድናለን፡፡ ድነናልም።” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 8]
- “… ለእየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል፡፡” [ውዳሴ ማርያም፤ የዘወትር ፀሎት፡ 9]
ህሊናችሁን ጠይቁ እስኪ። እንዴት ነው "ጌታችን በግፍ ተገ ደለበት" ለምትሉት መስቀል የምትሰግዱት? በቢላዋ ቢታ ረድ ቢላዋ ልታመልኩ ነበር? በድንጋይ ተወግሮ ቢገ ደል ድንጋይ ልታመልኩ ነበር?
አምላክ ይቅርና ሰው ወንድሙ ወይም አባቱ የተገ ደለበትን ጩቤ የቤቱን ግድግዳ አሸብርቆበት ብታዩት ምን ትላላችሁ? በኪሱ ይዞት ቢዞርስ? አንገቱ ላይ ቢያስረውስ? ቢስመውስ? ቢሳለመውስ? ቢሰግድለትስ? በእምነት ስም ስለቀረበ እንጂ አዕምሮው እያለ ሰው ይህን ያደርጋል ተብሎ ይታሰባል ግን? ዘወትር ስለምናየው ለምደነው እንጂ ይሄ እኮ እጅግ በጣም የሚደንቅ ነገር ነው፡፡ ሰው በራሱ ጊዜ በዚህ መጠን በህሊናው ላይ ይሸፍታል? ግዴላችሁም አስተውሉ። በአባት በአያት ውርስ ሳትሸነፉ ለእውነት እጅ ስጡ። ትርፉ ለራሳችሁ ነው።
* ምስሉ ከፌስቡክ የተወሰደ ነው።
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
https://youtube.com/shorts/Qp7ZUK3QJlg?si=zq7TWH_RiPYzo8Td
Читать полностью…የተዋሉልን ፀጋዎች እና የኛ አያያዝ
~
አላህ ለኛ የዋለልን ፀጋዎች ምን ያህል በሚገባ መልኩ አስተንትነናቸው እናውቃለን? ከዒልም፣ ከሃብት፣ ከጤና፣ ከሰላም፣ ከትዳር፣ ከልጅ፣ ከጓደኛ፣ ከጎረቤት፣ ከብዙ አቅጣጫ ብንመለከት ስንትና ስንት የአላህ ፀጋዎች አሉ?! ሌላው ሁሉ ይቅር። አላህ ኢስላምን ስለሰጠን ብቻ የዋለልንን ውለታ በምን መመለስ ይቻላል?
በህይወታችን ከባድ ፈተና ላይ ወድቀን ከጭንቅ የወጣንባቸውን ጊዜዎች አሉ? እነሱ የአላህ ፀጋዎች ናቸው። ህመም ራሱ የአላህ ፀጋ ነው። በህመም ወንጀል ይረግፋል። ትእቢት ይተነፍሳል። ኣኺራን ማስታወስ ይኖራል። ለተውበት ያዘጋጃል።
መርሳት የአላህ ፀጋ ነው። በህይወታችን ስንት የሚያሸማቅቁ፣ የሚያሳቅቁ፣ የሚያስጨንቁ ነገሮች ይገጥሙናል። ባንረሳቸው ኖሮ ሰላም ይነሱን ነበርኮ። የምንመገበው ምግብ፣ የምንጠጣው ውሃ፣ የምንስበው አየር የአላህ ፀጋዎች አይደሉ? ሰላም ትልቅ የአላህ ፀጋ ነው። ሰላም ሲጠፋ የሰላም ኒዕማ ጎልቶ እየታየ ነው። አካላችን ሁሉ የአላህ ፀጋ ነው። እስኪ ህይወትን ያለ ዐቅላችን፣ ያለ ምላሳችን፣ ያለ አይኖቻችን፣ ያለ ጆሮዎቻችን፣ ያለ እጆቻችን፣ ያለ እግሮቻችን፣ ... እናስበው። ምን ያህል ፈታኝ ነበር?
ጊዜ የአላህ ፀጋ ነው። እንዴት እያሳለፍነው ነው? ወጣትነት የአላህ ፀጋ ነው። ምን ተሰራበት? እድሜ ፀጋ ነው። ምን ተሸመተበት? ሃብት ፀጋ ነው። ሃብታችን ከኣኺራ አንፃር እዳ ነው ወይስ ምንዳ?
ዝናቡ፣ ፀሐዩ፣ ነፋሱ፣ ቀኑ፣ ሌቱ፣ ብርሃኑ፣ ጨለማው፣ እንስሳቱ፣ እፅዋቱ፣ እሳቱ፣ የትኛው ፀጋ ተወስቶ የቱ ይቀራል? እስኪ ህይወትን ያለነዚህ ኒዕማዎች አስቧት። ሱብሓነሏህ! ያለ ምክንያት አይደለም ጌታችን አላህ እንዲህ ማለቱ፦
{وَإِن تَعُدُّوا۟ نِعۡمَةَ ٱللَّهِ لَا تُحۡصُوهَاۤۗ إِنَّ ٱللَّهَ لَغَفُورࣱ رَّحِیمࣱ}
"የአላህንም ፀጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም። አላህ በእርግጥ መሃሪ አዛኝ ነውና።" [አነሕል፡ 18]
ስለዚህ የጎደለን ላይ ብቻ እያሰብን አናማር። የተሰጠንን እያስተዋልን እናመስግን። ጀሊሉ እንዲህ ብሏል፦
{لَئن شَكَرۡتُمۡ لَأَزِیدَنَّكُمۡۖ وَلَىِٕن كَفَرۡتُمۡ إِنَّ عَذَابِی لَشَدِیدࣱ}
"ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ። ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና።" [ኢብራሂም፡ 7]
ደግሞም ምስጋና ከቃልም ባለፈ በተግባር ይገለፃል። "ምስጋና (ሹክር) ማለት ወንጀልን መራቅ ነው" ይላሉ መኽለድ ብኑ ሑሰይን። ውለታ ቢስ ልንሆን አይገባም። የተሰጡንን ፀጋዎች አላህን ለማመፅ ካዋልናቸው ይሄ ከባድ ውለታ ቢስነት ነው። ስለዚህ የአላህን ፀጋዎች ወደ አላህ መቃረቢያ እንጂ ከሱ ጋር የምንጣላባቸው እንዳይሆኑ እንጠንቀቅ። ሰለማህ ብኑ ዲናር እንዲህ ይላሉ፦
"كل نعمة لا تقرّب من اللَّه فهي بلية"
"ወደ አላህ የማያቃርብ ፀጋ ሁሉ ፈተና ነው።" [አልሒልያ፡ 3/230]
የተሰጠን ፀጋ፣ የተዋለልን ኒዕማ ፈተና እንዳይሆንብን አላህ ይጠብቀን። ኣሚን።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
መፅሐፍ ቅዱስ ላይ ምን አለ መሰላችሁ
መልካም ንባብ👉። በርግጥ ለድሀዎች ስካሩም የተፈቀደ መሰለኝ።
(ለጥፋት ለቀረበው ሰው ብርቱ መጠጥ ስጡት፤ ነፍሱ ለመረረውም የወይን ጠጅ ስጡት ይጠጣ ድሕነቱንም ይርሳ ጉስቁልናውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያስብ፡፡) (መጽሐፈ ምሳሌ 31፡6)
ለሃብታምስ? ህጉ ይለያል።
(ለነገሥታትና ለሀብታምና ለመሳፍንትም፦ አስካሪ መጠጥ በፍፁም አይገባም፥ ልሙኤል ሆይ፥ ነገሥታት የወይን ጠጅ_ይጠጡ_ዘንድ_አይገባም።) (መጽሐፈ ምሳሌ 31፥4)
ለምን? ለድሃው የተፈቀደው ድህነቱን እንዲረሳ ነው። ሃብታሙ ከዚህ ችግር ነፃ ነው። እና ሃብታሞች ለምን ጤናችሁን አትጠብቁም?
ግራ የሚገባው መጽሀፉ ነብያት ሰክረው ወንጀል ፈፀሙ ሲል ነው። ለምሳሌ፦
* የፈጣሪ ነቢይ ኖህ #ሰክሮ ራቁቱን ሆነ‼ (ዘፍጥረት 9:20-21)
* በአስካሪ የወይን ጠጅ ስካር ምክንያት ውዱ የእግዚአብሄር ነቢይ ሎጥ ከወለዳቸው ከሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ጋር ሰክሮ ልጆቹ ከአባታቸው ከነቢዩ ሎጥ ዲቃ .ላ ጸነሱ። (ዘፍጥረት 19፡30-36)
* አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ። አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው። (መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 13፥28)
እንደ ኢስላም ነብያት ከእንዲህ ዓይነት ሃጢአት የተጠበቁ ናቸው።
እሺ መጠጣት ከተፈቀደ መጠኑ ምን ያህል ነው? ቄሱ እንዳለው 2 መለኪያ አይመስለኝም። ይልቁንም ጉዳዩ ለጠጪው የተተወ ይመስላል።
(ወዳጄ ሆይ ጠጪ እስክትረኪ ድርስ ጠጪ፡፡) (መኀልዬ መኀልዬ ዘሰለሞን 5፡1)
ጉድኮ ነው !
ወንድማችን ፉአድ ሙሐመድ ገቢሳ።
የምሽት ግብዣዬ