gfyygy | Unsorted

Telegram-канал gfyygy - አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

883

ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot

Subscribe to a channel

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ጥብቅ ማሳሰቢያ ለአሽከርካሪዎች
~
1- መኪና ይዘህ ጎዳና ላይ ከመውጣትህ በፊት እጅህን አጥራ። በቂ ችሎታ ይኑርህ። ያለበለዚያ የምታደርሳቸው አደጋዎች ከአላህ ፊት ተጠያቂ ያደርጉሃል።
2- የትራፊክ ህጎችን አክብር። አስረግጬ እነግርሃለሁ! ህግ እየጣስክ በምታደርሰው አደጋ ተጠያቂ ነህ። በትራፊክ ወይም በፍርድ ቤት እያልኩህ አይደለም። ይሄ ተራ ነገር ነው።
3- መኪናህ የጎደለው ወይም አደጋ እንዳያደርስ የምትሰጋው ችግር ካለበት በቸልተኝነት ወጥተህ ህዝብ ጋር እየተጋፋህ አትዋል። አንድ ነፍስ ብታጠፋ በሸሪዐችን የሚከተልህ መዘዝ ከምታስበው በላይ ነው።
ከነዚህ ሶስት ሰበቦች በአንዱ ወይም በሌላ ያንተ በሆነ ጥፋት የተነሳ፡

[1ኛ]፦ ነፍስ ብታጠፋ

በኢትዮጵያ ህግ የተቀመጠውን 40 ሺ (?) ስለከፈልክ የአላህን ቅጣት የምትገላገል እንዳይመስልህ። በሸሪዐ የተቀመጠው የነፍስ ካሳ ወይም ጉማ 100 ግመል ወይም 1,000 ዲናር ወርቅ ነው። ወደ ግራም ሲቀየር 4,250 ግራም ማለት ነው። ርቀቱን ለማወቅ በወቅታዊ የወርቅ ዋጋ አባዛው። አንድ ግራም 4 ሺ ብር ከሆነ 4,250 ግ. x 4,ዐዐዐ =17,000,000 (አስራ ሰባት ሚሊዮን) ብር ማለት ነው።

[2ኛ]:- አካል ብታጎድልስ?

[2.1] ጥንድ የሆኑ የውጭም ይሁን የውስጥ የአካል ክፍሎች ለምሳሌ ሁለት አይኖች ቢጠፉ፣ ሁለት እጆች፣ ሁለት እግሮች፣ ሁለት ጆሮዎች ቢቆረጡ፣ ልክ በተራ ቁጥር አንድ ላይ እንደሰፈረው ሙሉ የነፍስ ጉማ ዋጋ አላቸው። የጎደለው ከነዚህ ጥንድ ክፍሎች ውስጥ አንድ ከሆነ የሙሉው ጉማ ግማሽ ይከፈላል።
[2.2] ሙሉ አፍንጫ ከጥቅም ውጭ ቢሆን፣ ምላስ ወይም ብልት ቢቆረጥ፣ ጀርባ በማያንቀሳቅስ መልኩ ቢጎዳ በተመሳሳይ ነፍስ ባጠፋ ላይ ያለው ሙሉ ጉማ አለበት።
እንግዲህ የተጎዱት ሰዎች ሲበዙ ጉዳዩ ምን ያህል እንደሚከብድ አስቡት።

[2.3] ሌሎች የአካል ክፍሎችና የጉዳት አይነቶችም የራሳቸው ተመን ይኖራቸዋል።

[3ኛ] የንብረት ውድመት

የደረሰው ጉዳት የንብረት ከሆነ ሙሉ ለሙሉ መክፈል ግዴታህ ይሆናል።

ማሳሰቢያ፦
~
ነፍስ ያጠፋ ሰው ከጉማው በተጨማሪ ስልሳ ቀን በተከታታይ መፆም አለበት። ያለ ሸሪዐዊ ምክንያት መሀል ላይ ካፈጠረ እንደገና አንድ ብሎ ይጀምራል።
በዚህ መልኩ ሆን ብሎ ለመግደል አስቦ ሳይሆን በእንዝላልነት ነፍስ ያጠፋ ሰው ሲኖር ጉማ መክፈል ያለበት ማነው? ቅደም ተከተሉ እንደሚከተለው ነው:-
1ኛ- በአባት በኩል ያሉ የገዳዩ ሰው ወንድ ቤተሰቦች ወይም ቤተዘመዶች (العاقلة)። እነሱ ከሌሉ ወይም ካልቻሉ
2ኛ- ከሙስሊሞች ግምጃ ቤት (بيت المال)። ይህም ከሌለ
3ኛ- እራሱን ገዳዩን ይመለከታል።

አደጋ የደረሰው:-
1- ከአቅም በላይ ወይም ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ከሆነ፣
2- ወይም በራሱ በተጎጂው ጥፋት ከሆነ፣
3- ወይም በሌላ ሶስተኛ ወገን ጥፋት ከሆነ (ለምሳሌ ከኋላ የመጣ መኪና የሱን መኪና ሲመታበት ተንደርድሮ ነፍስ ቢያጠፋ)
በዚህን ጊዜ ተጠያቂ አይሆንም። ጉዳዩ አጥፊውን ይመለከታል።

ልብ በሉ፦
1ኛ፦ ይሄ ጉዳይ የአሽከርካሪ አደጋ ላይ የተገደበ አይደለም። ይልቁንም በየዘርፉ የሚገባ ነው። ለምሳሌ አንድ ሐኪም በማይችለው ጉዳይ ላይ ገብቶ ወይም በእንዝላልነት ነፍስ ቢያጠፋ ተመሳሳይ ህግ ይከተለዋል። ለምሳሌ መቆረጥ ያለበት እግር ቢኖር የታመመውን ጥሎ ያልታመመውን በስህተት ቢቆርጥ ግማሽ የነፍስ ጉማ አለበት። በስህተት አንድ ጤነኛ ጥርስ ቢነቅል አምስት ግመል ይከፍላል።
2ኛ፦ ለጥንቃቄና ለግንዛቤ መነሻ እንዲሆን ያክል እንጂ ያቀረብኩት መረጃ የተሟላ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewo

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

https://vm.tiktok.com/ZMhJS7tf2/

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

👉👉👉👉መንዙማ👈👈 👈👈

ለብዙዎች ሺርክ ላይ መውደቅ ሰበብ ሲሆን የሚታየው የቢድዐ አይነት በሀገራችን መንዙማ እየተባለ የሚጠራው ነው ።በስፋት እንደሚስተዋለው ብዙ የመንዙማ ግጥሞች ግልፅ የሆነ ሽርክና ድንበር ማለፍ የሚንሰበረቅባቸው ናቸው ። እንነዚህ መንዙማዎች እንደ ሃይማኖት ማስተማሪያ መንገድ ሰለሚታሰቡ በውስጣቸው ያለውን መልእክት ያለምንም ማመንታት እንዳለ የሚቀበለው ቀላል አይደለም ። በዚህም ሳቢያ በውስጣቸው ያለው መርዛመ አመለካከት በቀላሉ ከህዝብ ዘንድ ይሰርፃል ። በሀገራችን በስፋት ከሚደመጡ ሺርክ ከተሰገሰገባቸው መንዙማዎች ጥቂት ስንኞችን ለምሳሌ ያክል እንመልከት ።

"ቅመን ተቃቅመን ታመጣው ከዳቱን
ስኒና ጀበና ይብላው ዳኝነቱን ።"
ሱብሐነላህ!ስኒና ጀበና ምን ዳኝነት አለው?አንድ የማይረባ ግኡዝ ሸኽላ ቀርቶ ነብይም ፣ወልይም ፣ጂንም ፤ መልአክም ከአላህ ውጭ ሊጠቅም ሊጎዳ የሚችል አንድም የለም ።
"በዘመን የላችሁ ሳዳቶች አኽያር
ቀኝ እጄን ጨምጡኝ ወድቄ እንዳልቀር
ሸሊላ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር
መቼም ያለናንተ ሁሉም አያምር
በናንተየሸሸ ምንግዜም አያፍር!"
ሀያሉ ጌታችን ግን ምን እንደሚል እንመልከት ፦

"ወይስ ያ ችግረኛ በጠራው ጊዜ መልስ የሚሰጥ ፣ክፉንም የሚያስወግድ ፣በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት ?) (ይህን የሚያደርግ )ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን?!ጥቂትንም አትገሰፁም !"[አንነምል 62] ሌላው ደሞ እንዲህ ይላል ፦

"ያ ቀመረል መካ ልቤ ባንቱ በርሶ ተመካ "

አላህ ግን ምን እንደሚል እንመልከት።

"አማኞችም ከሆናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ ።"[አልማኢዳህ 23]
"በአላህ ላይ የሚመካ እሱ በቂው ነው። "

ሌላው ደግሞ "ወልይ"ብሎ ሲለሚያስበው ሙት አካል "ገድል "ሲተርክ እንዲህ ይላል ፦

"የቸገረው ሄዶ የለውም ማፈር
ከሐያቱ በልጧል ውለታው በቀብር"
ሞቶ ቀርቶ በህወይት እያለም ፉጡራን እርስ በርስ ሲያደርጉት ከሚችሉት ባለፈ ማለፈ ማንም ለተቸገረው መድረስ ፣ለጨነቀው ግልግልን ማምጣት አይችልም ።ይሄ ፍጥጥ ባለ መልኩ ወደ ቀብር አምልኮ ወደ ሽርክ መጠራት ነው ።ጌታችን ለመልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ በሏቸዋል " 'እናንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላ እንዳመልክ ታዙኛላችሁን ?' በላቸው"።[{አዝዙመር 64----66]}
//
ወገኔ ሆይ!እራስህን አትርፍ ።ሙተኖችን ጥለህ ወደ ማይሞተው ሂያው አምላክ ፊትህን አዙር ።

"አቤት ጠራኃችሁ ጌቶቼ ዱስቱር
እረዳቴ ማንነው ከናንተ በቀር "
ረዳታች ደካመ ፉጡራን ሳይሆኑ ሀያሉ ጌታችን ብቻና ብቻ ነው ።ጌታችንም እንዲህ ይላል ፦

"አላህ ለባሪያው በቂ አይደለምን?በነዚያ ከሱ ሌላ ባሉት (በሚያመልኳቸው )ያስፈራሩሀል።አላህ የሚያጠመውንም ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም ።"[{አዝዙመር 36 ]}
//
እነዚህን የመሳሰሉ ህዝባችን በገንዘቡ ሸምቶ የገዛ እምነቱን የሚያፈርስባቸው ዱንያ አኼራውን የሚያጠፋባቸው መሪን የለቀቁ መንዙማዎች በርካታና በየግዜው እየጨመሩ ያሉ ናቸው ።እረሳችንን ወገኖቻችንን ከነዚህ ዘላለማዊ ክስረትን ከሚያወርሱ ጥፋቶች ልንርቅና ሊናስጠነቅቅ ይገባል ።

የተወሰደው 👉ተውሒድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ መፅሐፍ [{ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ]}አላህ ይጠብቀው

🌹አላህ ሆይ!ሐቅን በሐቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርግልን አላሁመ ኣሚንንን🌹

/channel/gfyygy

ሌሎችም ጠቃሚ ትምህርቶችን ያገኛሉ አሁኑኑ ጆይን ይበሉ ይከታተሉ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

abdrahim.sani?_t=8pRx1ILJqGU&_r=1" rel="nofollow">https://www.tiktok.com/@abdrahim.sani?_t=8pRx1ILJqGU&_r=1

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

በኢሞ ደርስ መጀመር የሚፈልግ በዚህ መመዝግብ ይችላል አንድ የሱንና ኡስተዛችን ከሚሺቱ ሶስት ሰአት ተኩል ቦኃለ ሊጀምር ስለሆነ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ስለ ክብርህ ስትል ተዋቸው
~
የሰው ልጅ አመል እንደ መልኩ ብዙ አይነት ነው። ብዙ ደግ የመኖሩን ያህል በየትኛውም ሁኔታ መጥፎህን ብቻ ለማውራት ያሰፈሰፈ አለ። ልቡ በክፋት የተሞላ። በጎህን ሲያይ ይከፋዋል። ሰዎች በመልካም ቢያነሱህ ያመዋል። ያለ ስምህ ስም ይሰጥሃል። ያለ ግብርህ ያሸክምሃል። በሌለህበት ያውልሃል። ያለህን መልካም ይገፍሃል። ክፉህን ቢያይ ይቦርቃል። ሰዎች ቢያወግዙህ አታሞ ይመታል። ይቅርታህ አይዋጠውም። ዝምታህ አይጥመውም። ምላሽህም አይመቸውም። የቱንም ብታደርግ አታስደስተውም። ስህተት ቢያገኝ ጭራና ቀንድ አውጥቶለት ቆርጦ፣ ቀጣጥሎ ጭራቅ ያደርግሃል። ንግግርህን ፈፅሞ ባላሰብከው መልኩ ተርጉሞ ራሱ አጣሞ በተረዳው ላይ ተመርኩዞ ነብር ግስላ ሆኖ ይነሳብሃል።

በቃ! አንዳንዱ ባህሪው የውሻ አይነት ነው። ባለፍክ ባገደምክ ቁጥር ይጮሃል። "ዋው!" ማለትን የመተንፈስ ያህል ኖርማል አድርጎታል። ብትነካውም ይጮሃል። ብትተውም ይጮሃል። እንዲያውም ውሻ ሲያይህ ነው የሚጮኸው። ይሄኛው ሳያይህም ይጮሃል። "አትርሱኝ" ባይ ነገር ነው። በሌለህበትም፣ ሳታስታውሰውም ይጮሃል። በየትኛውም ሁኔታ ሊነድፍህ ስለተዘጋጀ ተያያዥ ጉዳይ እስከሚያገኝ አይታገስም። ይበላዋል። ያሳከዋል። ስለ ጦሃራ ስታወራ "ዋው!" ስለ ተውሒድ ስትናገር "ዋው!" ስለ ራስህ ብታነሳ "ዋው!" ራሱ የሚደግፈውን ሃሳብ ብታነሳም "ዋው!" ከማለት አይመለስም። ብትመልስለት አገር በጩኸት ያቀጣጥላል። ዝም ስትለውም ወይ አጀንዳ ፈጥሮ፣ ወይ "አሸነፍኩ" ብሎ ይጮሃል።
እና ምን ይሻላል? ጩኸቱን ላታስቆመው ነገር አትጨነቅ። እርሳው። ሰላምህ ያለው እሱን ከመርሳት ነው። ሊፈትንህ ይችላል። ከዚህ ውጭ ያለው ምርጫ ግን የበለጠ ፈታኝ ነው። አሕመድ ሻኪር - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦

"የማያውቅ ሁሉ ይወቅ! ምድር ላይ ሞኞች ብዙ ናቸው። እና አንድ ሰው ከሞኝ ለሚንፀባረቅ ሞኝነት ሁሉ የሚበሳጭ ከሆነ በብስጭቱ ሰበብ ብሶት መከፋቱ ይራዘማል። ሞኞችን ያሻቸውን ይበሉ ተዋቸው። ለክብርህ ስስት ይኑርህ። ክብርህ ለሞኞች ምላስ ተብሎ የሚመነዘር ከመሆን በላይ ውድ ነውና።"
[መጅሙዑል መቃላት፡ 1/579]
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

መውሊድ በማን ተጀመረ?
~
የመውሊድ ደጋፊዎች ከሚያነሷቸው ነጥቦች አንዱ መውሊድ “ታላቅ ዓሊም፣ ተቂይ፣ ሷሊሕና ጀግና በነበሩት” ንጉስ ሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚል ነው። ሙዞፈር የሞተው በ630 ሂጅሪያ ነው። ሰዎቹ ሙዞፈር ላይ ችክ የሚሉት እጅግ አፈንጋጭ በሆኑት “ፋጢሚያ” ሺዐዎች ነው የተጀመረው የሚለውን ለመሸሽ ነው። ነገር ግን በነዚህ ሺ0ዎች እንደተጀመረ ፍንትው አድርገው የሚያሳዩ ማስረጃዎች በጨባጭ አሉ። ለሐቅ እጅ ለሚሰጡ፣ ከመንጋዊ አስተሳሰብ አግልለው ህሊናቸውን ለሚያከብሩ ሰዎች ብቻ ማስረጃዎቹን አሰፍራለሁ።

1. ኢብኑል መእሙን (587 ሂ.):—

በታሪክ ድርሳናት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ መውሊድ ተጠቅሶ የተገኘው በኢብኑል መእሙን ስራ ነው። የኢብኑል መእሙን አባት የ“ፋጢሚያ” ንጉስ ከፍተኛ ባለሟል ነበር። የታሪክ ፀሐፊው አልመቅሪዚ (845 ሂ.) ኢብኑል መእሙንን በማጣቀስ በ517 ሂጅሪያ የተካሄደውን መውሊድ አስመልክተው እንዲህ የሚል መረጃ አስፍረዋል፡-
“የ‘ፊጢሚያ’ ገዢዎች በዓላትና ለተገዢዎቻቸው ነገሮችን ሰፋ የሚያደርጉባቸው እንዲሁም ችሮታ የሚበዘባቸው ዓውደ-አመታት” ካሉ በኋላ እንዲህ ይላሉ፡- ለፋጢሚያ ገዢዎች በአመቱ ውስጥ በዓላትና ዓውደ አመታት አሏቸው። እነሱም … የዓሹራእ ቀን፣ የነብዩ ﷺ ልደት (መውሊድ) ቀን፣ የዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ ልደት ቀን፣ የሐሰን የልደት ቀንና የሑሰይን የልደት ቀን (ሰላም በነሱ ላይ ይሁንና)፣ የፋጢመቱ ዘህራእ ዐለይሃ ሰላም ልደት ቀን፣ ስልጣን ላይ ያለው ገዢ የልደት ቀን፣ … የገዲር ዒድ (የሺዐዎች ነው)” እያሉ ይዘረዝራሉ። ከውስጣቸው የፋርስ መጁሳዎች፣ የሺዐና ከክርስትና ደግሞ እንደ ገና እና ትንሳኤ ያሉ በዓላት የተካተቱበት ሲሆን ባጠቃላይ 28 በዓላት ናቸው የተዘረዘሩት። [አልኺጦጥ፡ 1/436]
መውሊድ ከምን አይነት በዓላት ጋር እንደተጀመረ ተመልከቱ። በሌላ ኪታባቸው ላይም “በረቢዐል አወል ላይ (የ“ፋጢሚዮቹ” ንጉስ) ሌሊት ላይ በጎዳናዎችና መንገዶች ላይ ጧፎች እንዲበሩ ያስገድድ ነበር” ይላሉ። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 2/48] ሌላ ቦታ ደግሞ “ረቢዐል አወል ላይ የነብዩን ﷺ ክቡር ልደት መፈፀም ብሄራዊ ልምድ ሆኖ ቀጠለ” ይላል። [ኢቲዒዙል ሑነፋእ፡ 3/101] ልብ በሉ! ይህንን መረጃ የሰጠን ኢብኑል መእሙን የሞተው መውሊድን ጀመረ የሚባለው ንጉስ ሙዞፈር ገና በተሾመ በአመቱ ነው፡፡ እያስተዋላችሁ!!

2. ኢብኑ ጡወይር (617 ሂ.):—

ሌላኛው መውሊድን ከ“ፋጢሚዮች” ጋር በማያያዝ የጠቀሰው ጥንታዊ የታሪክ ፀሐፊ ኢብኑ ጡወይር ነው። ኢብኑ ጡወይር ለነዚህ “ለፋጢሚያ” መንግስት ፀሐፊ ሆኖ አገልግሏል። ኋላ በሶላሑዲን አልአዩቢ ሲደመሰሱም በአይኑ ተመልክቷል። በዚህኛው ስርኣትም ውስጥ ዳግም አገልግሏል። በ“ፋጢሚያዎች” መንግስት ስለሚዘጋጀው መውሊድና ስለተትረፈረፈ ምግቡ “ኑዝሀቱል ሙቅለተይን ፊ አኽባሪ ደውለተይን” በተባለ ኪታቡ ላይ በዝርዝር አትቷል። “ማን ያውራ የነበረ፣ ማን ያርዳ የቀበረ” ይላል ያገራችን ሰው። ለናሙና ያክል ቀንጨብ ላድርገው፡-
ذكر جلوس الخليفة في الموالد الستة في تواريخ مختلفة، وما يطلق فيها، وهي مولد النبي صلى الله عليه وسلم، ومولد أمير المؤمنين علي بن أبي طالب، ومولد فاطمة عليها السلام، ومولد الحسن، ومولد الحسين عليهما السلام، ومولد الخليفة الحاضر
“ኸሊፋው በተለያዩ ጊዜያት በስድስቱ መውሊዶች ላይ የሚያደርጋቸውን መስሰየምና ምን ተብለው እንደሚታወቁ ማውሳት፡- እነሱም የነብዩ ﷺ መውሊድ፣ የአሚረል ሙእሚኒን ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ መውሊድ፣ የፋጢማ ዐለይሃ ሰላም መውሊድ፣ የሐሰን መውሊድ፣ የሑሰይን - ዐለይሂመ ሰላም - መውሊድና የዘመኑ ኸሊፋ መውሊድ ናቸው፡፡ …” [ኑዝሀቱል ሙቅለተይን፡ 217-219]

3. አሕመድ ብኑ ዐሊይ አልቀልቀሸንዲ (821 ሂ.):—

ስለ “ፋጢሚያ” መሪዎች ጉባዔ ሲያወሩ “ሶስተኛው ጉባዔ በረቢዐል አወል ወር 12ኛ ቀን ላይ በነብዩ ﷺ መውሊድ ላይ የሚኖረው ጉባዔ ነው” ካሉ በኋላ ዝርዝር አፈፃፀሙን ይተርካሉ፡፡ [ሱብሑል አዕሻ፡ 3/576]

ስናጠቃልል የመውሊድ በዓል ጀማሪዎች “ፋጢሚያ” ሺዐዎች እንደነበሩ ለጥርጣሬ ቀዳዳ የማይሰጡ መረጃዎች አሉን ማለት ነው፡፡ ልብ በሉ! የመጨረሻው የ“ፋጢሚዮች” ንጉስ አልዓዲድ ሊዲኒላህ የሞተው በ 567 ሂጅሪያ ነው፡፡ ሱፍዮች “መውሊድ ጀመረ” የሚሉት ሙዞፈር የተሾመው ደግሞ ከ19 ዓመታት በኋላ በ586 ሂ. ነው፡፡ ይህንን ተጨባጭ ታሪካዊ መረጃ እያየ “አይኔን ግንባር ያርገው” የሚል ካለ የለየለት ቂላቂል ነው፡፡ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ የሚጠቁሙ ግልፅ ማስረጃዎች እየቀረቡ እያዩ “እከሌ እንዲህ ብለዋል” “እንቶኔ እንዲህ ብለዋል” እያሉ ነገር መዘብዘብ ራስን መሸወድ ብቻ ነው፡፡
“ሙዞፈር ነው የጀመረው” ያሉት እንደ ሲዩጢ ያሉ የኋለኛው ዘመን ሰዎች ከመሆናቸውም በላይ ያጣቀሱት ተጨባጭ ማስረጃ የለም፡፡ በነገራችን ላይ እነዚህ መውሊድ በሙዞፈር ነው የተጀመረው የሚሉ አካላት ኢብኑ ከሢርን ሲያጣቅሱ ማየት የተለመደ ነው፡፡ ኢብኑ ከሢር የሙዞፈርን መውሊድ ከመጥቀሳቸው ውጭ “ጀማሪ ነው” አላሉም፡፡
መቅሪዚ እንደጠቀሱት እነዚህ የሺዐዎቹ መውሊዶች ኋላ ላይ ለተወሰኑ ጊዜያት ተቋርጠው ነበር፡፡ [አልመዋዒዝ ወልኢዕቲባር፡ 1/432] ኋላ ላይ በተተካው የ“ፊጢሚዮቹ” ንጉስ አልኣሚር ቢአሕካሚላህ (524 ሂ.) ነው የተጀመሩት፡፡ ልብ በሉ! ይህ ዳግም የተጀመረው መውሊድ እራሱ ከሙዞፈር መውሊድ በዓል ብቻ ሳይሆን ከራሱ ሙዞፈር መወለድም የቀደመ ነው፡፡
በነገራችን ላይ ሱፍዮች መውሊድን ጀመረ የሚሉትን ሙዞፈርን ቅዱስ አድርገው የሚጠቅሱት ወይ ታማኞች ስላልሆኑ ነው፡፡ ወይ ደግሞ በሰውየው ላይ የቀረቡ ሂሶችን ያልተመለከቱ ናቸው፡፡ አብዛኞቹ የሚያደርጉት ለገበያቸው የሚሆናቸውን እየመረጡ ማቅረብ ነው፡፡ ንጉሱ በከፊል የታሪክ ፀሐፊዎች ከመወደሱም ጋር የሰላ ሂስ የሰነዘሩበትም አሉ፡፡ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ፡-
ያቁት አልሐመዊ ይባላሉ፡፡ በ626 ሂ. የሞቱ ታዋቂ የታሪክ ምሁር ናቸው፡፡ ሙዞፈርን አስመልክተው እንዲህ ይላሉ፡-
“የዚህ ሰውየ ባህሪ እርስ በርሱ የሚቃረን ነው፡፡ እሱ ሲበዛ በዳይ፣ ህዝቦቹ ላይ ጨካኝ እንዲሁም አግባብ ባልሆነ መልኩ ገንዘቦችን የሚወስድ ነበር፡፡ ይህ ከመሆኑ ጋር ለድሃዎች የሚቸርና ለእንግዶች በብዛት የሚሰድቅ ነበር፡፡ እጅግ በርካታ ገንዘቦችን አፍስሶ ከከሃዲዎች እጅ ምርኮኞችን ነፃ ያወጣ ነበር፡፡ በዚህ ላይ ባለቅኔው እንዲህ ይላል፡-

‘ልክ እንደዚያች ወጥ ረገጥ
በብልቷ ነግዳ ለበጎ ስራ የምትሮጥ
መስሚያ ካለሽ ወዮ ላንቺ!
ምፅዋትሽ ይቅር ይልቅ አትዘሙቺ፡፡’ ” [ሙዕጀሙዑል ቡልዳን፡ 1/138]

ያቁት አልሐመዊ ከሙዞፈር ጋር አንድ ዘመን የኖሩ በመሆናቸው ዘግይተው መጥተው ስለ ንጉሱ አድናቆት ብቻ ከሰፈሩ ፀሐፊዎች በተሻለ ምስክርነታቸው ሚዛን የሚደፋ ነው፡፡ በነገራችን ላይ ሙዞፈር ፃድቅ እንኳ ቢሆን፣ አይደለም እንጂ መውሊድ በሱ የተጀመረ ቢሆን እንኳ ይሄ ከቢድዐነት አያወጣውም፡፡ ከነቢዩ ﷺ ህልፈት በኋላ ስድስት መቶ አመታት ዘግይቶ የሚጀመር አዲስ ፈሊጥ ጥመት እንጂ ፈፅሞ ፅድቅ ሊሆን አይችልም፡፡ እምነታችን ከቁርኣንና ከሐዲሥ የሚቀዳ እንጂ እንደ ሌሎች እምነቶች ማንም እየተነሳ አዳዲስ ነገሮችን የሚለጥፍበት አይደለም፡፡
=
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

መውሊድን በተመለከተ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር የተዘጋጁ ከፊል ፅሁፎችን በቀላሉ እንዚህን ሊንኮች በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ።👇👇👇👇👇👇

1, ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ?
/channel/IbnuMunewor/893

2, መውሊድን ማን ጀመረው? በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ
/channel/IbnuMunewor/869

3, መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ?
/channel/IbnuMunewor/876

4, መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!}
/channel/IbnuMunewor/884

5, “በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ
/channel/IbnuMunewor/2227

6, የሰኞ ፆም እና መውሊድ
/channel/IbnuMunewor/2214

7, ዐቂቃ ሌላ መውሊድ ሌላ!
/channel/IbnuMunewor/2261

8, ዓሹራን ለመውሊድ?
/channel/IbnuMunewor/2269

9, መውሊድ ውስጥ እነዚህ አደጋዎች አሉ!
/channel/IbnuMunewor/2294

10, በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
/channel/IbnuMunewor/882

11, መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም!
/channel/IbnuMunewor/2298

12, መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው!
/channel/IbnuMunewor/886

13, እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል?
/channel/IbnuMunewor/2234

14, ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
/channel/IbnuMunewor/898

15, ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ
/channel/IbnuMunewor/2277

16, እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል?
/channel/IbnuMunewor/878

17, በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል” በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ
/channel/IbnuMunewor/34

18, ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
/channel/IbnuMunewor/1624

19, መውሊድ ተከሽኖ
/channel/IbnuMunewor/2309

20, ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው?
/channel/IbnuMunewor/918

21, መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች የመጨረሻው ምሽግ
/channel/IbnuMunewor/2302

➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵➵

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

መሀል ሰፋሪ የመውሊድ ጠበቆች
~
መውሊድ ከነሷራዎች ተኮርጆ በባጢኒያ ሺዐዎች የተጀመረ እምነትን የሚያናጉና የሚያጠለሹ ብዙ ጥፋቶችን (ሺርካሺርክ፣ ቢድዐዎችንና ብልግናዎችን) ያጨቀ ቢድዐ ነው። ስለሆነም ስለዚህ የቢድዐ ድግስ ወገንን ማንቃት እና መረጃዎችን ማሰራጨት ይገባል።
እንደሚታወቀው ረቢዕ በተቃረበ ቁጥር ሱፊዩ ለዚህ ቢድዐ ወጥሮ ሲሟገት፣ ሱኒዩ ደግሞ አጥብቆ ይኮንናል። ሌላ ደግሞ የመውሊድ ተቃውሞ የሚረብሸው መሀል ሰፋሪ የሆነ ሶስተኛ ቡድን አለ። "ለምንድነው መውሊድ በመጣ ቁጥር የምትጨቃጨቁት?" እያለ ለደዕዋ እንቅፋት ሊሆን ይነሳል። የምንጨቃጨቀው መውሊድ የሺርክ፣ የቢድዐ እና የብዙ ጥፋት መናሀሪያ መሆኑን በማስገንዘብ ወገንን ከጥፋት ለመጠበቅ ነው። የምንጨቃጨቀው ጥፋትን ማውገዝ፣ ወገንን ከጥፋት መከላከል፣ ሃይማኖታችንን ከሚያጠለሹ ሰርጎ ገብ አመልካከቶች መጠበቅ ኢስላማዊ ኃላፊነት ስለሆነ ነው። የምንጨቃጨቀው እንዳንተ አይነቱን ሳይነቃ እንደነቃ የሚያስብ ምስኪን ወገን ለማንቃት ነው። እንጂ ለክፋት አይደለም። እንጂ የጭቅጭቅ ሱስ ስላለብን አይደለም።
"የፈለገ ያክብር፣ የፈለገ ይተው" የሚለው የመሀይም ፈትዋ ነው። ለመሀይም ጩኸት ደግሞ መደንገጥም መቀዝቀዝም አይገባም። ይሄ ሁሉ ጉድ የማይጎረብጠው በመልካም ብንገምተው መሀይም ስለሆነ ነው። ያለበለዚያ ግን ምርጫው ሌላ ነው። ለማንኛውም የማንም ጩኸት ሳይበግረን የመውሊድን ቢድዐነት አጉልተው የሚያሳዩ የዑለማኦችን ስራዎች ማሰራጨት ላይ ልንተጋ ይገባል። አደራ!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewo

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ምርኩዝ በተባለው ፕሮግራም ላይ አቡበክር ፣ ዑመር እንዲሁም ሌሎች ሶሐቦች
الرَّحْمَنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىَ
በሚለው ዙርያ ዝም ብሎ ነው የሄዱት አቋማቸው አይታወቅም ብሎ ህዝቡን አምታቶ ሹብሀውን ለበተነው ሰውዬ በቂ ምላሽ።እሄንን ድምፅ ፋይል በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ሼር በማድረግ ትክክለኛውን የሶሀቦችን አቂዳ ለህዝቡ አድርሱት።

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

      t.me/Darutewhide

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ኸጢቦች ጥንቃቄ ብታደርጉ
~
ባለፉት ሳምንታት ጁሙዐን በተለያዩ ሰፈሮች ሰገድኩኝ። ሁሉም ጋር የገጠመኝ ዝናብ እየጣለ ረጅም ኹጥባ ነው የሚያቀርቡት። ዝናቡን ስላላወቁ ነው እንዳይባል ኹጥባቸውን ሲያገባድዱ ውጭ ላይ ዝናብ ስላለ ጠጋ ጠጋ በሉ ይላሉ። ይህንን ካሉ በኋላም በሶላታቸው ላይ እንደ ወትሮው አድርገው ቁርኣን ይቀራሉ። አንድ ሰው ቢያደርገው ራሱ የሚገርም ነው። በተለያዩ ሰፈሮች እንዲህ ሲደጋገም ግን የበለጠ ይደንቃል። "ይሄ ገርሞ፣ ገርሞ የሚገርም ነው" አሉ ሸይኽ መሐመድ ወሌ።
ኸጢቦቻችን ሆይ! ኹጥባችሁንም ሶላታችሁንም ሰጋጁንና ወቅቱን ታሳቢ እያደረጋችሁ መጥኑ'ንጂ። ዝናብ እየጣለ የምታደርጉት ኹጥባ በሌላ ጊዜ ከምታደርጉት ኹጥብ እንዴት ተመሳሳይ ይሆናል? ብዙ ሰጋጅ ዝናብ ላይ እያለ የሚፈፀም ሶላት እንዴት ከሌላው ጊዜ ጋር ተመሳሳይ ይሆናል?ይሄኮ ግዴለሽነትን ነው የሚያሳየው። ለምን ሰው በዚያ መልኩ እንዲያስባችሁ ታደርጋላችሁ? ለምን ሰው ተረባብሾ ተቀይሞ እንዲሰግድ ታደርጋላችሁ? ራሳችሁን ዝናብ ላይ ያሉ ሰጋጆች ቦታ በማድረግ የሚኖራቸውን ስሜት አስቡ እስኪ። ሰው ዝናብ እየተመታ የምታስረዝሙትስ ቁርኣን ሱና የሚሆን መስሏችሁ ነው? ሱናው የሰዎችን ሁኔታ ከግምት ያስገባ አፈፃፀም ነው። ነብያችን ﷺ የሚያለቅስ ልጅ ድምፅ ሲሰሙ እናቱ እንዳትረበሽ ብለው ሶላት ያሳጥሩ ነበር። እባካችሁ! ቢቻል በየትኛውም ጊዜ ኹጥባ በልክ አድርጉ። ካልሆነ ቢያንስ ቢያንስ በዝናብ ጊዜ እንኳ ትኩረት አድርጉ። ያለንበት ወቅት ክረምት መሆኑም አይረሳ።
መልእክቱን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለማይኖሩትም አድርሱልኝ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አስቸኳይ
~
በሑዘይፋ መስጂድ ዘወትር እሁድ የሚሰጠው የደርስ ፕሮግራም በዛሬው እለት አይኖርም። በመስጂዱ ውስጥ የሚካሄድ የሴቶች ፕሮግራም እንዳለ ስለተነገረን ነው። ሰዎች እንዳይንገላቱ ይህንን መልእክት በማሰራጨት ወይም ለምታውቋቸው በመደወል አድርሱልን።
جزاكم الله خيرا

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አባካኝነትን እንራቅ
~
ሁሉም ነገር ልክ አለው። እዝነት ልክ አለው። መስዋእትነት ልክ አለው። ዒባዳ ልክ አለው። ቸርነት ልክ አለው። ደግነት ልክ አለው። መልካም ነገር ከልኩ ሲያልፍ ስሙ ይቀየራል። ደግነቱ ሞኝነት ይሆናል። ጥንቃቄው ፍርሃት ይሆናል። ብልህነቱ አጉል ብልጣብልጥነት ይሆናል። ያኔ ውበቱን መልኩን ያጣል። ያኔ ጉዳዩ ወደ ውጉዝነት ተሸጋግሯል ማለት ነው።
ይህ እንዳይሆን ትኩረት መስጠት ይገባል። በልክ መሆን ውበት ነው። በልክ መሆን ጨዋነት ነው። በልክ መሆን ታስቦበት ሲሆን ዒባዳ ነው። በልክ መሆን ሞገስ አለው።
ልክ ማለት ወደ ላይም ወደ ታችም ድንበር አለማለፍ ነው። በአቋምህ ድንበር አትለፍ። በንግግርህ ድንበር አትለፍ። በገንዘብ አያያዝህ ድንበር አትለፍ። በጊዜ አጠቃቀምህ ድንበር አትለፍ። ለሁሉም ነገራችን ለከት ሊኖረው ይገባል። ለምሳሌ ገንዘብ ጋር የተያያዘውን አባካኝነት ላንሳ። ጌታችን አላህ አባካኝነትን ይነቅፋል። እንዲህ ይላል፦
{ وَلَا تُبَذِّرۡ تَبۡذِیرًا (26) إِنَّ ٱلۡمُبَذِّرِینَ كَانُوۤا۟ إِخۡوَ ٰ⁠نَ ٱلشَّیَـٰطِینِۖ وَكَانَ ٱلشَّیۡطَـٰنُ لِرَبِّهِۦ كَفُورࣰا (27) }
"ማባከንንም አታባክን፡፡ አባካኞች የሰይጣናት ወንድሞች ናቸውና፡፡ ሰይጣንም ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው።" [አልኢስራእ፡ 26-27]
በዚህ ቦታ ላይ አባካኝነት ከግልፅ ክልከላ ባለፈ በጥብቅ እየተኮነነ ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው እንዲህ ዓይነቱን ማሳሰቢያ እንደዋዛ ሊያልፈው አይገባም። ስለዚህ፦
* አመጋገባችን ላይ ብክነት እንዳይኖር እንጠንቀቅ። በልካችን እናቅርብ። በልካችን እንመገብ። አላህ አባካኞችን አይወድም።
{وَكُلُوا۟ وَٱشۡرَبُوا۟ وَلَا تُسۡرِفُوۤا۟ۚ إِنَّهُۥ لَا یُحِبُّ ٱلۡمُسۡرِفِینَ }
"ብሉ፤ ጠጡም፤ አታባክኑም፡፡ እርሱ አባካኞችን አይወድምና።" [አልአዕራፍ፡ 31]
* ስንታጠብ፣ ውዱእ ስናደርግ፣ እቃ ስናጥብ ውሃ አናባክን። ነብያችን ﷺ በውዱአቸውም በትጥበታቸውም ላይ የውሃ አጠቃቀማቸው የተመጠነ ነበር። በመኖሪያ ቤቶችም ይሁን በመስጂዶች ወይም በሌላ ቦታዎች የውሃ አጠቃቀማችን በልክ ይሁን። ስንጨርስ ቧንቧዎችን በትክክል እንዝጋ። የተበላሸውን እንጠግን።
* ያለ ፋይዳ መብራቶችን አናብራ። በማይፈልግ ቦታና ጊዜ የሚበሩትን እናጥፋቸው። የቤታችንን መብራት፣ ማገዶ፣ ናፍጣ፣ ነዳጅ፣ ሲሊንደር ጋዝ፣ ... ያለ ፋይዳ ሲሰራ አይተን አንለፍ።
* በጥቅሉ ልብሳችን፣ ገንዘባችን፣ ሞባይላችን፣ ኮምፒተራችን፣ ... ሁሉም አይነት ንብረታችን ባግባቡ ሊይያዝ የሚገባ የጌታችን ስጦታ ነው። ያለ አገልግሎት የትኛውም ሃብት ሊባክን አይገባም። ጌታችን ስለዋለልን ኒዕማዎች ከማመስገን ውስጥ አንዱ ፀጋዎቹን ባግባቡ መጠቀም ነው። ይሄ ከደጋግ የአረሕማን ባሪያዎች መታወቂያዎች ውስጥ ነው። የላቀው ጌታ እንዲህ ይላል፦
{ وَٱلَّذِینَ إِذَاۤ أَنفَقُوا۟ لَمۡ یُسۡرِفُوا۟ وَلَمۡ یَقۡتُرُوا۟ وَكَانَ بَیۡنَ ذَ ٰ⁠لِكَ قَوَامࣰا }
"እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑ የማይቆጥቡትም ናቸው፡፡ በዚህም መካከል (ልግስናቸው) ትክክለኛ የሆነ ነው።" [አልፉርቃን፡ 67]
ባይሆን አታባክን ማለት ሰስት ማለት አይደለም። አላህ የሰጠንን ፀጋ እሱ በሚወደው ቦታ ላይ ባግባቡ ማውጣት የታዘዝንበት አደራ ነው። ብቻ ሁሉም በልክ ሲሆን ያምራል።
{ وَلَا تَجۡعَلۡ یَدَكَ مَغۡلُولَةً إِلَىٰ عُنُقِكَ وَلَا تَبۡسُطۡهَا كُلَّ ٱلۡبَسۡطِ فَتَقۡعُدَ مَلُومࣰا مَّحۡسُورًا }
"እጅህንም ወደ አንገትህ የታሰረች አታድርግ፡፡ መዘርጋትንም ሁሉ አትዘርጋት፤ የተወቀስክ የተቆጨኽ ትኾናለህና።" [አልኢስራእ፡ 29]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ከማስታወቂያ ነጻ የሆነ የኢሞ አፕልኬሽን
/channel/ISLAMICBOOKSANDAPPS/224571

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ሚስትህን በፍቺ አታስፈራራት

🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

/channel/Achachir_mkroch

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ኢልምን ከአሊም ስር ሁኖ መቅሰም ማጣጣም ምንኛ ያስደስታል ያአላህ ⤴️
🇸🇦🌹

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

https://vm.tiktok.com/ZMrowVaKw/

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ማሳሰቢያ ይህ ደርስ የሚሰጠው ሰኞ ፣እሮብና አርብ እንደሆነ ማታ ኡስታዝ ነግሮኛል ሰአቱም ኪታቡም ይቀየር የሚል ካለም አስተያት እንቀበላለን።

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeSbff2ftGw81XwZU7JBjg3b_oLbhHMn-saduLHn1_ra-IRjg/viewform?usp=sf_link

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አስነጥሶን 'አልሓምዱሊላህ' ብለን 'የርሓሙከላህ' ከተባልን:

'የህዲኩሙላሁ ወዩስሊሑ ባለኩም' ብለን ነው መመለስ ያለብን።
'ጀዛከላህ' እና ሌሎች መሰል ምላሾችን መጠቀም ልክ አይደለም።

ለምን?

ነቢያችን ﷺ ያስተማሩን ከላይ ያለውን ስለሆነ። ኸይር ቢሆን ኑሮ ሌሎች ምላሾችን ባስተማሩን ነበረ።

ኮፒ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ስለሚወዷቸው ይዋሹባቸዋልi
~
ሙሐመድ አወል በመንዙማው አማካኝነት በከፍተኛ መጠን ሺርክን አስፋፍቷል። "የኢትዮጵያ ዑለማዎች ታሪክ" የሚለው መንዙማው በሺርክ ስንኞች የታጨቀ ነው። ባጠመማቸው ሁሉ እንዳይጠየቅ ሞት ሳይቀድመው በፊት ተውበት ቢያደርግ ራሱ ነው የሚጠቀመው። ሙሐመድ አወል "አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን" እያለ የተለመደውን የአሽዐሪያ ቅዠታዊ ፍልስፍና የሚያስተጋባበትም አለው። በተያያዘው ድምፅ ላይ ደግሞ በውዱ ነብያችን ﷺ ላይ ባደባባይ ሲቀጥፍባቸው ይታያል። ቃል በቃል እንዲህ ነው ያለው፦

"ሐዲሥ አደለም እምነግራችሁ። የዑለማዎች አነጋገር ነው። 'መውሊድ ሰምቶ በጆሮው፤ መውሊድ ሰምቶ የቀረ አይወደኝም' ብለዋል ነብያችን። ተጠርቶ ደግሞ የቀረ ይጠላኛል' አሉ።"

በቅድሚያ በእሱና መሰል ሰዎች ለምትሽወዱ ወገኖቻችን! ወላሂ በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ላይ ምላሽ የምንሰጠው ብሽሽቅ እያማረን አይደለም። ይልቁንም በእምነታችሁ ጉዳይ የማንም መጫወቻ ከመሆን እንድትወጡ ለማንቃት ነው። እነዚህ ሰዎች በኢስላም ስም ኢስላምን የሚያጠለሹ፣ ነብዩን ﷺ በመውደድ ስም በሳቸው ላይ የሚዋሹ ሰዎች ናቸው።

1ኛ፦ ሰውዬው "ሐዲሥ አደለም እምነግራችሁ" ካለ በኋላ "መውሊድ ሰምቶ በጆሮው፤ መውሊድ ሰምቶ የቀረ አይወደኝም ብለዋል ነብያችን" ይላል። ሐዲሥ ምን እንደሆነም አያውቅም። ስለ ሐዲሥ ያለው ግንዛቤ በዚህ መጠን ነው። አያሳፍርም? ወይስ ሌሎችን ለመወንጀል ያለው ጉጉት ነው እስከሚዋሽ ያደረሰው? ሐዲሥ ካልሆነ ለምንድን ነው "... ብለዋል ነብያችን" የምትለው? ያላሉትን በስማቸው ትቀጥፍባቸዋለህ? ልብ በሉ! ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
لا تكذبوا علي فإنه من كذب علي فليلج النار
"በኔ ላይ አትዋሹ። በኔ ላይ የዋሸ ሰው እሳት ይግባ!" [አልቡኻሪይ፡ 106]
በሌላ ሐዲሣቸውም እንዲህ ብለዋል፦
إن من أعظم الفِرَى أن ... يقول على رسول الله (ﷺ) ما لم يَقُلْ
"ከከባባድ ቅጥፈቶች ውስጥ የሆነው አንድ ሰው በአላህ መልእክተኛ ላይ ያላሉትን ማለቱ ነው።" [አልቡኻሪይ፡ 3509]

2ኛ፦ ምናልባት " 'ሐዲሥ አደለም እምነግራችሁ። የዑለማዎች አነጋገር ነው' ብሏል። ከራሱ አልተናገረምኮ" የሚል ካለ ይሄ ከተጠያቂነት ነፃ አያደርገውም። ሐዲሥ እንዳልሆነ እያወቀ የቀጣፊዎችን ንግግር በነብያችን ﷺ ስም ማውራት በቂ ጥፋት ነው። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
مَنْ حَدَّثَ عَنِّي بِحَدِيثٍ يُرَى أَنَّهُ كَذِبٌ، فَهُوَ أَحَدُ الْكَاذِبِينَ
"ውሸት እንደሆነ የሚታሰብን ወሬ በኔ ላይ ያወራ ሰው እርሱ ራሱ ከውሸታሞቹ አንዱ ነው።" [ሙስሊም፡ ገፅ፡ 7]

ልብ በሉ! ውሸት ከሙናፊቅ ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው። ውሸት አፀያፊ ወንጀል ነው። ውሸትን ክፉኛ በሚኮንኑት ነብይ ስም ሲፈፀም ደግሞ ይበልጥ የከፋ ይሆናል። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል:-
إن كذبا علي ليس ككذب على أحد، من كذب علي متعمدا فليتبوأ مقعده من النار
"በኔ ላይ መዋሸት በማንም ላይ እንደመዋሸት አይደለም። በኔ ላይ እያወቀ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ።" [አልቡኻሪይ፡ 1291]

3ኛ፦ ይህንን ከንቱ ንግግር "የዑለማዎች አነጋገር ነው" የሚለውም ሌላ ቅጥፈት ነው። ይሄ የዑለማእ ሳይሆን በዲን ስም የሚነግዱ ቀጣፊዎች ንግግር ነው። ዑለማእ በሌላ ሰው ላይ ያውም በነብዩ ﷺ ላይ አይዋሽም። ኢማሙ አሕመድ በነብዩ ላይ የሚዋሽን ሰው ፋሲቅ ነው፣ አመፀኛ! ምስክርነቱም ዘገባዎቹም ተቀባይነት የለውም። ቢመለስና ሁኔታው ቢስተካከል እንኳ! በሱ ላይ ለማክበድ ሲባል! አብዛኞቹ በነብዩ ﷺ የሚዋሹ ሰዎች ኢስላምን ማጥፋት የሚሹ መና. .ፍቃን ናቸው ይላሉ።

4ኛ:- " 'መውሊድ ሰምቶ የቀረ አይወደኝም' ብለዋል" የሚለውን አስተውሉት። የዚህ ቅጥፈት አላማው ሁለት ነው። አንዱ የሸሪዐ እውቀት የሌላቸውን ሰዎች አስፈራርቶ የመውሊድ አጫፋሪ ማድረግ ነው። ሁለተኛው አላማ መውሊድ የሚቃወሙ ሰዎችን በጠላትነት ለመፈረጅ ነው። በነዚህ አካላት የምትሸወዱ ወገኖቼ ሆይ! ወላሂ በነዚህ ለራሳቸው እንጀራ ሲሉ እናንተን እሳት ላይ በሚማግዱ ሴረኞች ተንኮል እንዳትሸወዱ። ፈፅሞ ለነዚህ በነብዩ ﷺ ስም እንኳ ከመዋሸት ለማይመለሱ አሳሳቾች እንዳትሟገቱ። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ إِنَّاۤ أَنزَلۡنَاۤ إِلَیۡكَ ٱلۡكِتَـٰبَ بِٱلۡحَقِّ لِتَحۡكُمَ بَیۡنَ ٱلنَّاسِ بِمَاۤ أَرَىٰكَ ٱللَّهُۚ وَلَا تَكُن لِّلۡخَاۤىِٕنِینَ خَصِیمࣰا }
"እኛ በሰዎች መካከል አላህ ባሳወቀህ ልትፈርድ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት አወረድን። ለሸፍጠኞችም ተከራካሪ አትሁን።" [አኒሳእ፡ 105]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ነግረናችሁ ነበር በአጥር ተንጠልጥለን
ከኢስላም ህግ በስተቀር ፍትሃዊ ህግ የለም ብለን
ለሀገር ለወገን የሚጠቅም እንጀትን የሚያርስ

ኢስላም"የገደለ_ይገደል"

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ውሻ እየተበላ ነው እንጠንቀቅ‼️

➨ምን አይነት ጭካኔ ነው⁉️

አፈሩን አቡክተው ነጭ ጤፍ ነው ሲሉን?
በዚያ በዚህ ብለው ብዙ ሲያታልሉን⁉️
አሁን ደግሞ ጭራሽ ውሻ አርደው አበሉን!?

የአምላክን ትዕዛዝ ህጉን እየረሱት፡
በደል እየሰሩ ህዝቡን አስጨረሱት፡
ውሻ እየመገቡ ጭራሽ ሊያናክሱት⁉️

አሏህ ታግሶናል አልወረደም በላ፡
ማንንም ሳናማ ሳንሔድ ወደ ሌላ፡
ምን ኸይር ተገኘ ውሻ እየተበላ‼️

ጉድ ብለን ሳንጨርስ የአህያው ሲገርመን‼️
እየባሰ መጣ የውሻም ደገመን፡
ወደ ማን እንጩህ ማን ሰሚ አለን ከቶ፡
ቂያማ እየቀረበ ሳይነጋልን መሽቶ‼️

ምንድነው ይሔ ጉድ አልገባኝም እኔ፡
ኸረ ምን መጣብን ንገረኝ ወገኔ⁉️
መች ነው የለመድነው ይህንን ጭካኔ፡

እንደዚህ ነው ድፍረት የህፀፅ መነሻ‼️
የውድቀት የውርደት የግፍ መጨረሻ⁉️
ከሰጋቱራ አልፈው ጀመሩልን ውሻ⁉️


በዛሬው እለት ነሐሴ 04/2016 ኮንቦልቻ ከተማ ላይ የውሻ ስጋ ተያዘ...አልገረማችሁም ወይ‼️

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ኹፍ ላይ ስለማበስ
~
በኹፍ ላይ ወይም በካልሲ ላይ ስለማበስ ግንዛቤ ብንይዝ ለራሳችንም እንጠቀማለን፤ ሌሎችንም እንጠቅማለን፡፡
① ኹፍ ማለት ከስስ ቆዳ የሚዘጋጅ ከስር ጀምሮ እስክቁርጭምጭሚት ድረስ ወይም ከዚያም በላይ የሚሸፍን በእግር ልክ የሚዘጋጅ የእግር ልብስ ነው:: ስለዚህ ቁርጭምጭሚት የማይደርሱ አጫጭር ካልሲዎች ከኹፍ ውስጥ አይካተቱም ማለት ነው።
② በኹፍ ላይ ማበስ ማለት አንድ ሰው የተለመደውን የሶላት ውዱእ እያደረገ መጥቶ እራሱንና ጆሮውን ካበሰ በኋላ እግሮቹን ግን በማጠብ ፋንታ በእርጥብ እጅ አበስ ማድረግ ማለት ነው፡፡
③ የሚታበሰው ላይኛው እንጂ ታችኛው ማለትም ምድር የሚረግጠው ክፍል (ፋናችን) አይደለም፡፡ ዐልይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “ዲን ባስተያየት ቢሆን ኖሮ ኹፍ ከላይኛው ክፍሉ ይልቅ የታችኛው ነበር የሚታበሰው፡፡ ነገር ግን የአላህ መልእክተኛን ﷺ የኹፋቸውን ላይኛውን ክፍል ሲያብሱ አይቻለሁ፡፡” [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 153] ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ታች እግራቸውን ማበሳቸው ከከፊል ምሁራን የተገኘ ቢሆንም መረጃ የሚደግፈው አይደለም ማለት ነው፡፡ በርግጥ ደካማ ስለሆነ እንጂ ነብዩ ﷺ “ከታችም ከላይም አብሰዋል” የሚል ሐዲስ አለ፡፡ [ዶዒፉ ሱነኒ ቲርሚዚ፡ 77]
④ አለባበሱን በተመለከተ ሁለት እግሮቹን አጥቦ ከጨረሰ በኋላ መልበስ ወይም በየተራ ቀኙን እንዳጠበ የቀኝ ኹፉን፣ ግራውን አጥቦ ሲጨርስ ደግሞ የግራ ኹፉን መልበስም ይችላል፡፡
⑤ በኹፍ ላይ ማበስ የሚቻለው በጦሀራ (ውዱእ) ላይ እያለ ኹፉ ከተለበሰ ነው፡፡ [አልኢስቲዝካር፡ 2/256] [አልሙግኒ፡ 1/361]
⑥ የሚታበስበት የጊዜ ርዝማኔ ለነዋሪና ለመንገደኛ የተለያየ ነው፡፡ ለመንገደኛ (ሙሳፊር) 3 ቀን እና 3 ሌሎቶች ሲሆን ሙቂም ማለትም በሃገሩ ላይ ተቀማጭ የሆነ ግን ለአንድ ቀንና ሌሊት ነው፡፡ (24 ሰዓት፡፡) [ሙስሊም፡ 276] ታዲያ ጊዜው መቆጠር የሚጀምረው ኹፉ ከተለበሰበት ወቅት ጀምሮ ሳይሆን ማበስ ከተጀመረበት አንስቶ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ በሃገሩ ኗሪ (ሙቂም) የሆነ ሰው ዐስር ላይ ውዱእ አድርጎ ኹፉን ቢለብስና በዚሁ ውዱእ ዐስርን፣ መግሪብንና ዒሻን ቢሰግድ ከዚያም ኹፉን ሳያወልቅ ተኝቶ ማለዳ ላይ ውዱእ አድርጎ እግሩን ቢያብስ መቁጠር የሚጀምረው ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ነው፡፡
⑦ አስተባበሱ ቀኝ እግርን በቀኝ እጅ፣ ግራ እግርን በግራ እጅ #በአንዴ ማበሱ በላጭ እንደሆነ ዑለማዎች ይገልፃሉ። በየተራ ቢሆንም ችግር የለውም።
⑧ ኹፍን ማውለቅ ውዱእ አያበላሽም፡፡ የጊዜ ገደቡ ሳያልቅም ይሁን ከተጠናቀቀ በኋላ ኹፋችንን ብናወልቅ ሌሎች ውዱእን የሚያጠፉ ነገሮች እስካልገጠሙን ድረስ ውዱኣችን እንዳለ ነው፡፡
⑨ የማበሻ ጊዜውን ሳይጨርስ በፊት ኹፍን ያወለቀ ሰው እንደገና ቢያስገባም የማበስ ብይኑ ተቋርጧል:: ስለሆነም በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ ሰው ውዱእ ቢያጠፋ እንደ ማንኛውም ውዱእ እግሩንም ጭምር ማጠብ እንጂ ካወለቀ በኋላ ባስገባው ኹፍ ላይ ማበስ አይችልም፡፡
(10) ኹፉ ቀዳዳ ቢኖርበትም በላዩ ላይ እያበሱ መጠቀም ይቻላል፡፡ ቀዳዳ ካለው በላዩ ላይ ማበስ አይቻልም ያሉ ቢኖሩም መረጃ የሚደግፈው ግን አይደለም፡፡ ታላቁ ሰለፍ ሱፍያን አሥሠውሪ ረሒመሁላህ ኹፍን አስመልክተው “እግርህ ላይ እስካለ ድረስ አብስበት፡፡ የሙሃጂሮችና የአንሳሮች ኹፎች የተበሳሱ፣ የተቀዳደዱና የተጣጣፉ እንጂ ሌላ ነበሩ ወይ?!” ይላሉ:: [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ፡ 753]
ኹፍ የሚመለከተው ወዱእን ብቻ ነው:: ስለዚህ በጀናባም ይሁን በሌላ ምክንያት ትጥበት ግዴታ በሚሆንበት ጊዜ ኹፍን አውጥቶ ሙሉ አካልን ውሃ ማስነካት ግዴታ ስለሆነ በዚህ ጊዜ በኹፍ ላይ ማበስ አይቻልም፡፡ [ኢርዋኡል ገሊል፡ 104] “በኹፍ ላይ ማበስ ውዱእን ብቻ የሚመለከት ነው፡፡ እንጂ ከሙሉ የሰውነት ትጥበት ጋር ግንኙነት የለውም፡፡ በዚህ ላይ ኢጅማዕ አለ።” [አልፈትሕ፣ ኢብኑ ሐጀር፡ 206]
(11) እስካሁ በኹፍ ላይ ስለ ማበስ ያሳለፍናቸው በካልሲ ላይ ማበስንም የሚመለከቱ ናቸው።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ታህሳስ 28/2009)
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ልጆች እና መስጂድ
~
ልጆችን ከመስጂድ ማባረር ተገቢ አይደለም። ባይሆን እንደ እድሜያቸው ሁኔታ ከግንዛቤ መግባት ያለባቸው ነገሮች አሉ።
1 - መስጂድ እንዳይነጅሱ መጠንቀቅ። ይህንን ማድረግ የማይቻል ከሆነ ሊመጡ አይገባም።
2 - ሌሎች ሰጋጆችን እንዳይረብሹ ቤተሰብ ከጎን ሊይዛቸው ይገባል።
3 - ልጆች ከእኩዮቻቸው ጋር ሲሰበሰቡ ሶላትንም፣ ኹጥባንም ይበጠብጣሉ። ስለዚህ መለያየት ተገቢ ነው።
4 - ቀጥታ የመጀመሪያ ሶፍ ላይ ከኢማሙ ኋላ ሲሆኑ ወደ ኋላ ማድረግ ይገባል። ይሄ ቦታ ኢማሙ ቢሳሳት የሚያርሙ ፤ ቢወጣ የሚተኩ በሰል ያሉ ሰዎች ናቸው ሊገቡበት የሚገባው።
5 - ሰጋጆችን እንዳያቋርጡ ማስተማር ይገባል።
6 - ሰባት አመት የሞላቸውን ወይም ማስተዋል የሚችሉትን ስለ ውዱእ አፈፃፀም፣ ስለ የውዱእ አፍራሽ ነገሮች፣ ስለ ጦሀራ እና ነጃሳ፣ ስለ አሰጋገድና ተያያዥ አደቦች በመጠኑ ማስተማር ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🔹ዱንያን ከልክ በላይ መውደድ የሚያመጣው ጉዳት
ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል :-
ومحب الدنيا لا ينفك من ثلاث : هم لازم ، وتعب دا ئم ، وحسرة لا تنقضي
وذلك أن محبها لا ينال منها شيئا إلا طمحت نفسه إلى ما فوقه ،
كما في الحديث الصحيح عن النبي صلى الله عليه وسلم : "لو كان لابن آدم واديان من مال  لابتغى لهما ثالثا" متفق عليه
የዱንያ ወዳጅ ከሶስት ነገሮች አይወገድም
-  የማይለቅ ሐሳብ
-  የዘወትር ልፋት
-  የማይቋረጥ ጸጸት
👉የእርሷ ወዳጅ አንድም ከእርሷ (ከዱንያ) አያገኝም ፣  ከነበረው በላይ ለማግኘት ነፍሱ  የምትቋምጥ ቢሆን እንጅ።
በትክክለኛ ሐዲስ ነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - እንደተናገሩት
"የሰው ልጅ ሁለት ሸለቆ ገንዘብ ቢኖረው ለሁለቱ (ሸለቆ) ሶስተኛ ይፈልግላቸው ነበር" (ሐዲሱ ቡኻሪና ሙስሊም የተስማሙበት ነው)

"ጢቡል ቁሉብ" ገጽ 221

/channel/alateriqilhaq

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የምትችለውን አድርግ
~
ገቢህን ለመጨመር አማራጭ ካለ ተግተህ ፈልግ። ወጭህን ቀንስ። ዱዓህን አድርግ። በአላህ ላይ ተወከል። አለቀ ደቀቀ። ከዚህ ውጭ ትልቅ ትንሹን፣ ቀልዱንም ቁም ነገሩንም፣ ... ሳያጣሩ ማራገብ ነጋዴውን እያስደነበሩ ባላሰቡት አቅጣጫ ለኑሮ ውድነቱ እገዛ ከማድረግ ውጭ የሚፈይደው ነገር የለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ዛሬ ዛሬ በተለይ ከገጠርም አልፎ ከተማ ውስጥ መሽጎዋል።

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

      t.me/Darutewhide

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ሙስሊም የሆናችሁ አትፍዘዙ ሼር እያደረጋችሁ የውሸን ገንዳዎችን አጋልጡ ነቃ በሉ

Читать полностью…
Subscribe to a channel