ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot
ዝሙት፣ አደጋዎቹና መጠበቂያ መንገዶች
~
① ዝሙት የአላህን ቁጣ ያስከትላል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
يا أمةَ محمدٍ، واللهِ إنه لا أحدَ أغيرُ من اللهِ أن يزنيَ عبدُه أو تزنيَ أَمَتُه، يا أمةَ محمدٍ، والله لو تعلمون ما أعلمُ لضحِكتُم قليلاً ولبكيتُم كثيراً
"እናንተ የሙሐመድ ህዝቦች ሆይ! ወላሂ አንድ ባሪያ በሚዘሙት ወይም አንዲት ባሪያው በምትዝሙበት ጊዜ እንደ አላህ የሚቀና የለም። እናንተ የሙሐመድ ህዝቦች ሆይ! ወላሂ እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ጥቂትን በሳቃችሁና ብዙ ባለቀሳችሁ ነበር።" [ቡኻሪና ሙስሊም]
② ዝሙት እጅግ ሰቅጣጭ ዱንያዊ ቅጣት የተወሰነበት ወንጀል ነው። አላህ እንዲህ ይላል:–
﴿الزَّانِيَةُ وَالزَّانِي فَاجْلِدُوا كُلَّ وَاحِدٍ مِنْهُمَا مِائَةَ جَلْدَةٍ وَلا تَأْخُذْكُمْ بِهِمَا رَأْفَةٌ فِي دِينِ اللهِ إِنْ كُنْتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَلْيَشْهَدْ عَذَابَهُمَا طَائِفَةٌ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ﴾
"ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን (ያላገቡ ከሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፏቸው፤ በእነርሱም በአላህ ፍርድ ርህራሄ አትያዛችሁ፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆናችሁ (አትራሩ)፡፡ ቅጣታቸውንም ከምእምናን ጭፍሮች ይገኙበት፡፡" [ኑር: 2]
የርህራሄ ተምሳሌት ከሆነችው እናት በላይ አዛኝ የሆነው ጌታ ከባድ ቅጣት ከማስተላለፉም በላይ ቅጣቱን የሚፈፅሙት ርህራሄ እንዳይዛቸው ማሳሰቡ የወንጀሉን ከባድነት ነው አጉልቶ የሚያሳየን። በዚያ ላይ ቅጣቱ ለሌሎች መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ከፊል ህዝብ እንዲመለከተው እያስታወሰ ነው። ይሄ መቶ ግርፋት እንግዲህ ዝሙተኛው አግብቶ የማያውቅ ከሆነ ነው። አግብቶ የሚያውቅ ከሆነ ግን በድንጋይ ተወግሮ ነው የሚገደለው። እነዚህ ዱንያዊ ቅጣቶች ናቸው። ጥፋቱን ፈፅሞ ሳይቶብት የሞተ ሰው የሚኖረው አኺራዊ ቅጣቱ ደግሞ የከፋ ነው የሚሆነው።
③ ዝሙት በቀብር አስፈሪ ቅጣት የሚከተለው ጥፋት ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
رأيتُ الليلةَ رجلين أتياني فأخرَجاني، فانطلقتُ معهما فإذا أنا ببناءٍ على مثلِ التنُّورِ، أعلاه ضيِّقٌ وأسفله واسعٌ، يوقد تحتَه نارٌ، فيه رجالٌ ونساءٌ عراةٌ، فإذا أُوقدت النارُ ارتفعوا حتى يكادوا يخرجون، وإذا خمَدَت رجعوا، فقلتُ للرَّجُلينِ: من هؤلاء؟ قالا: هم الزناةُ
"ዛሬ ሌሊት ሁለት ሰዎች ወደኔ መጥተው አየሁኝ። ይዘውኝ ወጡ። ከነሱ ጋር ተጓዝኩ። እንደ ምድጃ ባለ ግንብ ዘንድ ደረስኩ። ላዩ ጠባብ ታቹ ሰፊ ነው። ከስሩ እሳት ይቀጣጠላል። በውስጡ እርቃን የሆኑ ወንዶችና ሴቶች አሉ። እሳቱ ሲቀጣጠል ሊወጡ እስከሚቀርቡ ወደላይ ይወጣሉ። ሲከስም ይመለሳሉ። ‘እነማን ናቸው እነዚህ?’ ብየ ሁለቱን ሰዎች ስጠይቅ ‘ዝመተኞች ናቸው’ ይላሉ።" [ቡኻሪ፡ 7047]
④ ዝሙት በአኺራ ድርብርብ ቅጣት ከተዛተባቸው ሺርክና ሰው መግደል ጋር አብሮ የተጠቀሰ የወንጀል አይነት ነው። አላህ እንዲህ ይላል:–
(وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا * يُضَاعَفْ لَهُ الْعَذَابُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَيَخْلُدْ فِيهِ مُهَانًا)
"እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡ በትንሣኤ ቀን ቅጣቱ ለእርሱ ይደራረባል፡፡ በእርሱም ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ይኖራል፡፡" [ፉርቃን፡ 68–69]
ኢማሙ አሕመድ "ከግድያ ቀጥሎ ከዝሙት የከፋ ወንጀል አላውቅም" ብለዋል።
⑤ ዝሙት ከባድ ማስጠንቀቂያ የመጣበት የባለጌዎች መንገድ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:–
﴿وَلا تَقْرَبُوا الزِّنَى إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلاً﴾
"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በርግጥ ብልግና ነውና፡፡ መንገድነቱም ከፋ!" [ኢስራእ: 32]
⑥ ዝሙት ኢማንን የሚያራቁት አደገኛ ወንጀል ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
لا يزني الزاني حين يزني وهو مؤمنٌ
"ዝሙተኛ ዝሙትን በሚፈፅመው ጊዜ ሙእሚን ሆኖ አይደለም የሚፈፅመው።" [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይሄ እጅግ እጅግ አስፈሪ ሐዲሥ ነው።
⑦ በዱንያም የአላህን ቁጣና ቅጣት ያስከትላል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–
إذا ظهر الزنا والربا في قرية فقد أحلوا بأنفسهم عذاب الله
"ዝሙትና ወለድ በአንዲት መንደር ላይ ከተንሰራፋ በራሳቸው ላይ የአላህን ቅጣት አስወስነዋል።" [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 679]
⑧ ዝሙት ሲበዛ በሐዲሥ እንደተገለፀው ቀድሞ የማይታወቅ በሽታና ወረርሺኝ ይመጣል። ለምሳሌ ኤድስን አስታውሱ።
…………
ከዝሙት መራቂያ መንገዶች
-
① በመጀመሪያ አንተ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ ድረስ። ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም።
② እይታህን ገድብ። "አይኖች ይዘሙታሉ። ዝሙታቸው ያልተፈቀደ እይታ ነው" ተብሏል በሐዲሥ።
③ ከአጅነቢ ጋር ከመቀላቀል፣ ከአጅነቢ ጋር ተገልሎ ከመቀመጥ ተቆጠብ። አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ለብቻ መሆኑ ብልግና የመፈፀሙን እድል በጣም ከፍ ያደርገዋል። "አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር አይገለል። ይህ ሲሆን ሶስተኛቸው ሸይጧን ነውና" ተብሏል በሐዲሥ። ሰው በሌለበት የባልሽ ወንድም እንዲገባ አታድርጊ። "የባል ወንድም ሞት ነው" ብለዋል ነብዩ ﷺ።
④ ከመጥፎ ጓደኞች ራቅ። "እግሮች ይዘሙታሉ። ዝሙታቸው (ወዳልባሌ ቦታ) መሄድ ነው" ተብሏል በሐዲሥ።
⑤ አጅነቢ ከመጨበጥ ተቆጠብ። "እጆች ይዘሙታሉ። ዝሙታቸው መንካት/ መጨበጥ ነው" ተብሏል በሐዲሥ።
⑥ ምላስህን ዝሙትን ከሚያስታወሱ ነገሮች አርቅ። በሐዲሥ "ምላስም ይዘሙታል" እንደተባለ እናስታውስ።
⑦ እንደ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ልቦለድ፣ እርቃን ምስሎችና የብልግና ቪዲዮዎች በከባዱ ወደ ዝሙት የሚጣሩና የዝሙት ፍላጎትን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ናቸው። አብዛኞቹ ዘፈኖች ስለ ሴት ገላ፣ ከሴት ጋር ስለማደርና መዋል ነው የሚያጠነጥኑት። ዘፈን የዝሙት መሰላል፣ የንፍቅና መብቀያ ነው። አብዛኞቹ ፊልሞች የዝሙት ሙቀዲማዎች ይገኙባቸዋል።
⑧ አኺራህን አስብ። ነገ ከአላህ ፊት መቆምና ከባድ ምርመራ እንዳለ አስታውስ። አላህ እንዲህ ይላል:–
(يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ)
ዛሬ የሸዋል ጨረቃ እንዳልታየች የሰዑዲያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አረጋግጧል። ስለዚህ ዛሬ የመጨረሻውን የተራዊሕ ሶላት እንሰግዳለን ኢንሻአላህ። ዒዱ ረቡእ ይሆናል።
Читать полностью…ለሽያጭ ወይም ለንግድ ታስቦ የተዘጋጀ ቤት ወይም መሬት ከታሰበበት ጊዜ ጀምሮ አመት ከሞላው ቢሸጥም ባይሸጥም ዘካ አለበት።
* ለሽያጭ የተዘጋጀ ሳይሆን ነገር ግን ጉዳዩን ጨርሶ ወይም ሐሳቡን ቀይሮ ሊሸጠው ወሰነ። በዚህ ላይ እያለ ገዢ አጥቶ ሳይሸጥ አመት ቢቆይ እንኳ ዘካ የለበትም። ከተሸጠ በኋላ ገንዘቡ አመት ሲሞላው ዘካ አለበት።
* መኪናም ቢሆን እንዲሁ ነው። ለሽያጭ ከተገዛ ባይሸጥ እንኳ ወቅታዊ ዋጋው ተገምቶ ዘካ ማውጣት ግድ ነው። ለመገልገያ ከተገዛ ግን የለበትም።
=
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
ጥቂት ነጥቦች ስለ ኢዕቲካፍ!
~
* ትርጓሜው፦ ለአላህ ዒባዳ ለመፈፀም በማሰብ መስጂድ ውስጥ መቆየት ማለት ነው።
* ብይኑ፦ በቁርኣን በሱና የተረጋገጠ ሙስተሐብ (የተወደደ) ዒባዳ ነው። ስለት ለተሳለበት ሰው ግዴታ ይሆናል። አዕቲካፍ ለሴቶችም የተፈቀደ ነው።
* አላማው፦ ልብንም አካልንም ስብስብ አድርጎ በዒባዳ መጠመድ ነው። ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ከትርፍ ወሬ፣ ከትርፍ ቅልቅል፣ ከትርፍ እንቅልፍ መቀነስ ይገባል።
* ጊዜው፦ አብዛኞቹ ዑለማእ ዘንድ በረመዷንም ይሁን ከረመዷን ውጭ መፈፀም ይቻላል። በላጩ ጊዜ ግን ረመዷን ነው። ከረመዷንም የመጨረሻዎቹ አስሮቹ የበለጡ ናቸው።
* ቦታው፦ ለወንድም ይሁን ለሴት መስጂድ ውስጥ ብቻ ነው።
* የጀመረ ሰው መጨረስ ግዴታ ነው? የሚያስገድድ ማስረጃ የለም።
* ዝቅተኛው ጊዜ ምን ያህል ነው? ገደብ የለውም። ያሰኘውን መጠን ያክል ነይቶ መቀመጥ ይችላል።
* ኢዕቲካፍ የገባ ሰው ለመፀዳዳት መውጣት ይችላል። የታመመን ለመጠየቅ፣ ጀናዛ ለመሸኘትና መሰል ጉዳዮች ግን አይወጣም። ግንኙነት፣ ግብይት፣ ስራ መስራት አይቻልም። ኢዕቲካፍ ላይ እያለ የታመመ ሰው መታገስና መቆየት የሚችል ከሆነ መውጣት የለበትም።
* የረመዷን የመጨረሻዎቹን አስር መግባት የፈለገ መቼ ይጀምር? የረመዷን 20ኛው ቀን ፀሐይ ስትጠልቅ።
* የሚወጣበት ደግሞ ረመዷን ተጠናቆ የዒድ ሌሊት ሲገባ ነው። ወላሁ አዕለም።
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- /channel/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
“ሰባቱ አጥፊ ወንጀሎች”
~
ረመዷን 14/1445 በፉሪ ሰልሰቢል መስጂድ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል:-
/channel/IbnuMunewor
* በወር አበባ ጊዜ የሚሰማ ህመም (Dysmenorrhea) - ዶ/ር ሀብታሙ አውለው
( የማህፀን እና ፅንስ ሬዝዳንት ሀኪም)
* በወር አበባ ወቅት የሚሰማ ህመም በጉልምስና እና አዋቂነት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን በብዛት ከሚያጋጥሟቸው የጤና ችግሮች ውስጥ አንዱ ነው።
*ህመሙ እየጠና ሲሄድ የእለት ከእለት እንቅስቃሴን በማወክ የችግሩ ሰለባዎች አጠቃላይ ጤናማ እና ደስተኛ ህይወትን እንዳይኖሩ ያደረጋል።
እንዲሁም ከትምህርት ገበታ እና ከስራ ቦታ በማስቀረት የስራ ውጤታማነትን እና ትርፋማነትን ይቀንሳል።
* በሽታው መንስኤው የማይታወቅ ( primary dysmenorrhea) እና መንስኤው የሚታወቅ (secondary dysmenorrhea) በመባል በሁለት ይከፈላል።
# የበሽታው ስፋት እና ስርጭት ምን ይመስላል?
ከ 50 - 90% የሚሆኑ ከ 15 - 49 አመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በወር አበባ ጊዜ ህመም እንደሚሰማቸው ጥናቶች ያሳያሉ።
ከነዚህ ውስጥ አብዝሀኞቹ ወጣቶች ሲሆኑ የበሽታው አይነትም በብዛት ምክንያቱ የማይታወቅ (primary dysmenorrhea) ነው ።
# በበሽታው የመጠቃት እድልን የሚጨምሩ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
- እድሜ ( በጉልምስና የእድሜ ክልል ውስጥ መሆን)
- ጭንቀት
- ሲጋራ ማጨስ
- የህመሙ ተጠቂ የሆነ ሌላ የቅርብ ቤተሰብ ካለ
# እንዴት ይከሰታል?
* ህመሙ የሚከሰተው በዋናነት የወር አበባ መፍሰስ በሚጀምርበት ጊዜ የውስጠኛው የማህፀን ግድግዳ ሲፈርስ የሚለቀቀው ፕሮስታግላንድን የተባለ ሆርሞን ማህፀን ጡንቻወች ከመጣን በላይ እንድኮማተሩ ስለሚያደርግ ነው ።
# ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?
- የወር አበባ የሚፈስበትን ጊዜ ጠብቆ በታችኛው የሆድ ክፍል የሚሰማ ከቀላል እስከ ከባድ የሆነ የሆድ ቁርጠት
* ህመሙ የወር አበባ ከመፍሰሱ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ወይንም የወር አበባ መፍሰስ ሲጀምር አብሮ የሚጀምር ሲሆን በቀጣይ ባሉት ከ 12-72 ሰዓታት ውስጥ እየቀነሰ ይሄዳል ።
- ከዚህ በተጨማሪ አልፎ አልፎ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ድካም ፣ ራስ ምታት እና ድብርት የመሳሰሉት ምልክቶች ሊኖረት ይችላሉ ።
* መንስኤው የማይታወቀው የህመም አይነት በለጋነት ዩእድሜ ክልል ውስጥ የሚጀምር ሲሆን እድሜ እየጨመረ ሲሄድ እንድሆም የመጀመርያ ልጅ ከተወለደ በኋላ እየቀነሰ የሚሄድ ሲሆን በአንጻሩ መንስዔው የሚታወቀው የወር አበባ ህመም (secondary dysmenorrhea) ዘግየት ብሎ የሚጀምር ሲሆን እድሜ በጨመረ ቁጥር ህመሙም አብሮ እየጨመረ ይሄዳል።
ይህ አይነቱ የህመም አይነት የሚድነው የታወቀው መንስኤ ሲታከም ነው ።
# የሚሰጠው ህክምና ምን አይነት ነው?
* ህክምናው እንደየ ህመሙ አይነት ፣ ደረጃ እና ለመድሀኒት ባለው ምላሽ የሚለያይ ሲሆን ለምሳሌ ያህል :-
- ምክንያቱ የሚታወቅ ከሆነ መንስኤውን ማወቅ እና ማከም
- እንቅስቃሴ ማድረግ
- የተለያዩ የህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች
- የእርግዝና መከላከያ ክኒኖችን ፣ ከቆዳ ስር እንድሁም ማህፀኝ ውስጥ የሚቀመጡ የእርግዝና መከላከያወች
- ፊዚዮቴራፒ
- የስነልቦና እና ምክር አገልግሎት
- የተለያዩ የነርቭ ማነቃቂያ ህክምናወች
- የደረቅ መርፌ ህክምና ( Acupuncture and acupressure)
* እንድሁም ከዚህ ከነዚህ ሁሉ ህክምናወች በኋላ ለውጥ የማይኖር ከሆነ ማህጸንን እስከማውጣት የሚያደርስ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል።
References፡
-Williams Gynecology, 4th edition
- Up to date
የተቀማጭ ወይም የንግድ ገንዘብ ዘካ ሂሳብ አሰራር
~
የሚወጣው የአጠቃላይ ገንዘቡን 2•5% ነው። ስለዚህ:
ጠቅላላ ገንዘቡ x በ 2.5%= የዘካ መጠን ይሰጣል።
ወይም ዘካ የሚወጣለትን ጠቅላላ ገንዘብ ለ 40 ስናካፍል የዘካውን መጠን ይሰጠናል።
ሁለት ምሳሌ እንመልከት፡
* ምሳሌ አንድ:- 500,000 ብር ያለው ሰው የሚያወጣው የዘካ መጠን ስንት ነው?
500,000 × 2.5%=12,500 ብር
ወይም
500,000 ፥ 40=12,500 ብር
||
* ምሳሌ ሁለት 1,000,000 ብር ያለው ሰው የሚያወጣው የዘካ መጠን ምን ያህል ነው?
1,000,000 × 2.5%=25,000 ብር
ወይም
1,000,000 ፥ 40=25,000 ብር
||
የቴሌግራም:-
/channel/IbnuMunewor
የአሕባሽ ብልሹ አካሄድ
ኢብኑ ሙነወር
የካቲት 30/2016 በወራቤ ከተማ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መስጂድ የተሰጠ ትምህርት
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
ሙስሊም ላልሆኑት መስጠት ከተፈለገ አንድ ሰው ከራሱ ንበረት ሶደቃ ቢሰጥ ችግር የለውም፡፡ግን ዘካ የሚሰጠው ለሙስሊም ነው ፡፡
Читать полностью…🔷 ሰበር ዜና
أعلنت المحكمة العليا السعودية مساء يوم الأحد أن يوم الاثنين الموافق لـ 11 مارس 2024م هو غرة شهر رمضان المبارك للعام 1445هـ.
የሳውዲ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነገ ሰኞ የረመዳን ወር የመጀመሪያ ቀን መሆኑና ፆም የሚያዝ እንደሆነ አስታውቋል ።
http://t.me/bahruteka
🟢 ያልገዙትን ንብረት መሸጥ እንዴት?
ይህን ጉዳይ በአሁኑ ጊዜ ሊያስተውሉ የሚገባቸው በተለይም:
👉አየር በአር የሚነግዱ
👉ኦንላይን በሚዲያ የሚነግዱ
👉ከባንኮች በኩል እቃ የሚገዙ
《አንተ ጋር የሌለን ነገር አትሽጥ》
🔊አሸይኽ ሙሀመድ ሳሊህ አልኡሰይሚን
/channel/FATTAWAS
ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ ያልተጨነቀ አይደሰትም ያልታገሰ አይጣፍጠውም ያልተቸገረ አይደላውም ያለፋ አያርፍም ይልቁንስ ባሪያ ትንሽ ከለፋ ረጂም ጊዜ ያርፋል የሰአታት ትዕግስት ለዘላለማዊ ህይወት ትመራዋለች የዘውታሪ ፀጋ ባለቤቶች ያሉበት ሁሉ የጥቂት ሰአት ትዕግስት ውጤት እንጅ ሌላ አይደለም።
📚 مفتــاح دار الـســعادة【2/15】
👆
የኪታቦቹPDF እንዚህ ናቸው። የቻለ ሰው ፕሪንት አድርጎ ቢከታተል የተሻለ ነው።
📚አራት ምርጥና አንገብጋቢ የሆኑ ኪታቦችን በ 4 ቀን ብቻ ያጠናቁ!
•በዚህ ቻናል ከነገ ጀምሮ (ማለትም የካቲት 21/06/2016 ሐሙስ) ለተከታታይ 4 ቀናት መሰጠት ይጀምራሉ።የሚሰጡት ኪታቦችም ከግዜው ጋር የገጠሙ ናቸው ተብሎ ተጠንቶበት ነው።
• ከ መንሐጁ
• ከ ረቃኢቅ
• ከ አኽላቅ
• ከ ፊቅህ(ፆም)
💡እዚህ ደውራ ላይ ብንገኝ በአላህ ፈቃድ ተጠቃሚ እንሆናለን።―መልዕክቱትን ለሌሎች ሼር ያድርጉት!―
🌐ትምህርቱ ቀጥታ የሚተላልፍበት ቻናል፦👇
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
“በሸይኽ ረቢዕ ላይ ድንበር ማለፍ”
ኢብኑ ሙነወር
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor/5455
ወንድም እህቶችዬ እንኳን ለ1445ኛው ኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።በዓሉ የደስታ የሰላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
ኢድ -ሙባረክ።
የሌሊት ሶላት
~
ተራዊሕ፣ ተሀጁድ እና የሌሊት ሶላት የሚባሉት ለተለያዩ ሶላቶች የተሰጡ የተለያዩ ስያሜዎች አይደሉም። ይሄ የኢስጢላሕ ጉዳይ ነው። ትኩረት ልንሰጥ የሚገባው ከቃሉ ይልቅ ጭብጡ ላይ ነው። የሌሊት ሶላት የሚለው ተሀጁድንም፣ ተራዊሕንም ይገልፃል። ተራዊሕ የሚለውን ቃል ዑለማኦች በረመዷን ወር ከዒሻእ በኋላ በጀማዐ የሚሰገደውን ሶላት ለመግለፅ ይጠቀሙታል። ልብ በሉ! ከአፈፃፀሙ በስተቀር አመቱን ሙሉ ካለው የሌሊት ሶላት የተለየ አይደለም።
ተሀጁድ ሰዎች ሌሊት ተነስተው የሚሰግዱት ሶላት ነው። የሌሊት ሶላት ወቅቱ ከዒሻእ ሶላት በኋላ ጀምሮ እስከ ፈጅር ድረስ መሆኑ ይታወቃል። ስለዚህ እነዚህ ሶስት ስያሜዎች (ተራዊሕ፣ ተሀጁድ እና የሌሊት ሶላት) የአንድ ሶላት መጠሪያዎች ናቸው ማለት ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ትንሽ ማለት የፈለግኩት አመት ጠብቆ መነታሪኪያ ስለሚሆን ነው። ነጥቡን ለማጥራት ከመሞከሬ በፊት አንድ ቀዳሚ ነጥብ ላንሳ። እሱም በርእሱ ላይ የትኛውንም አቋም ብንይዝ ሃሳባችን ቢለያይ እንኳ በልክ እንሁን። ዑለማኦች የተለያዩበት፣ ከመለያየታቸውም የጎሪጥ ያልተያዩበት ጉዳይ እንደሆነ አውቀን እነሱ በያዙት መጠን እንያዘው። ዑለማኦች ብቻ ሳይሆኑ ራሳችንም በጉዳዩ ላይ ያለን አቋም ሊቀያየር ይችላል። ከስሜት ነፃ እስከሆን ድረስ ይሄ የሚጎዳ አይደለም። ወደ ነጥቦቹ ልግባ፦
1. የተራዊሕ ሶላት "መልካም" ቢድዐ ሳይሆን በቀጥታ ከነብዩ ﷺ የተገኘ ሱና ነው። [ቡኻሪይ፡ 872] [ሙስሊም፡ 1271] ከዚያም በአንድ ጀማዐ መስገዱ ተቋርጦ ከፊሉ በጥቂት በጥቂት ተከፋፍሎ ከፊሉ ደግሞ በተናጠል ሲሰግድ ከቆየ በኋላ ልክ በነብዩ ﷺ ኢማምነት ተጀምሮ እንደነበረው በአንድ ጀማዐ በዑመር አማካኝነት ተሰብስቧል። [ቡኻሪይ፡ 2010]
2. ቁጥሩ ከነብዩ ﷺ በተግባር የተገኘው እስከ 11 ረከዐ ድረስ ነው። ይህንን ይዘው ጭማሪው ቢድዐ ነው ያሉ አሉ፤ የብዙሃን ዑለማእ ምርጫ ባይሆንም። የነብዩን ﷺ ቃላዊ መረጃዎች እና የቀደምቶችን አፈፃፀም ለተመለከተ ግን ጉዳዩ በቢድዐ ለመግለፅ የሚያስደፍር አይደለም። ስለዚህ ከአንድ አቅጣጫ ጥናት በመውጣት ጠለቅ ብሎ በማየት ጥንቃቄ ቢኖረን ይመረጣል። ከመሆኑም ጋር አፈፃፀማችንን ከነብዩ ﷺ ተግባራዊ አፈፃፀም ማለትም 11 ረከዐ ጋር ብናጣጥም የበለጠ ነው፣ ወላሁ አዕለም።
3. በረመዷን የመጨረሻው 10 ላይ ሌሊት ላይ ተነስቶ መስገዱ ቢድዐ ይደርሳል? በፍፁም!
3.1. ከጊዜ አንፃር፦ ሙሉ ሌሊቱ የሶላት ወቅት ነው። እንዲያውም ለሚችል ሰው የሌሊቱ መጨረሻ ከመጀመሪያው በላጭ ነው። በላጭ በሆነ ወቅት ላይ መሰባሰቡ ከቢድዐ ጋር የሚገናኝበት ነጥብ የለም።
3.2. አፈፃፀም፦ በጀማዐ መስገድም ቢሆን ተጨባጭ መረጃ የመጣበት ስለሆነ በዚህም በኩል ክፍተት የለም።
3.3. በመጨረሻው አስር ላይ ትጋት መጨመሩ፦ ተጨባጭ መረጃዎች የመጡበት ነው። አንድ ሁለት ልጥቀስ፦
ከእናታችን ዓኢሻ ተይዞ እንዲህ ብላለች፦
كان رسول الله صلى الله عليه وسلم إذا دخل العشر أحيا الليل، وأيقظ أهله، وجدَّ وشدَّ المئزر
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ የመጨረሻው አስር ሲገባ ጊዜ ሌሊቱን በንቃት ያሳልፉ፣ ቤተሰባቸውን ያነቁ፣ በእጅጉ ይጣጣሩና ትጥቃቸውን ያጠብቁ ነበር።" [ቡኻሪይ፡ 2024] [ሙስሊም፡ 1174]
* ሌሊቱን በንቃት ያሳልፉ ነበር ማለት በዒባዳ ንቁ ሆነው ማለት ነው።
* ቤተሰባቸውን ያነቁ ነበር ማለት ለሌሊት ሶላት ነው።
* ትጥቃቸውን ያጠብቁ ነበር ማለት ከሴት ያገሉ ወይም ዒባዳ ላይ ያላቸውን ትጋት ከቀደመው ይጨምሩ ነበር ማለት ነው። [ፈትሑልባሪ፡ 4/316]
በሌላም መረጃ እናታችን ዓኢሻ እንዲህ ብላለች፦
كان رسول الله صلى الله عليه وسلم يجتهد في العشر الآخر ما لا يجتهد في غيره
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ በመጨረሻው አስር ላይ በሌላው ላይ የማይተጉትን በተለየ ይተጉ ነበር።" [ሙስሊም፡ 1175]
3.4. ቁጥሩ፦ ከ11 በላይ መስገድ ይቻላል የሚል ሰው እዚህ ላይ ጥያቄ ሊያነሳ አይገባም። አይቻልም ለሚል አካል ግን ዐምር ብኑ ዐበሰህ ረዲየላሁ ዐንሁ "የትኛው የሌሊቱ ክፍል ነው ይበልጥ ለዱዓእ ተቀባይነት በላጭ የሆነው?" ብለው ሲጠይቋቸው ነብዩ ﷺ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦
فصلِّ ما شئتَ فإنَّ الصَّلاةَ مشْهودةٌ مَكتوبةٌ حتّى تصلِّيَ الصُّبحَ
"ያሻህን ስገድ። በዚህ ጊዜ የሚሰገድ ሶላት መላእክት የሚጣዱባት ነችና። ፈጅር እስከምትሰግድ ድረስ።" [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 1277]
በተጨማሪም እንዲህ ብለዋል፦
صلاة الليل مثنى مثنى فإذا خشي أحدكم الصبح صلى واحدة توتر له ماقد صلى.
"የሌሊት ስግደት ጥንድ ጥንድ ነው። አንዳችሁ ንጋትን ከሰጋ የሰገደውን ዊትር ታደርግ ዘንድ አንድ ረከዐ ትሰግዳለህ።" [ቡኻሪይ፡ 472] [ሙስሊም፡ 749]
3.5. በአንድ መስጂድ ላይ ድጋሚ ጀማዐ መቋቋሙም ቢሆን ለተቃውሞ የሚቀርብ አይደለም። ምክንያቱም ዑመር በአንድ እስከሚሰበስቡት ድረስ በአንድ መስጂድ ውስጥ የተለያዩ ጀማዐዎች ሲቋቋሙ ነበርና።
ስለዚህ ማታ ለሰገደም ይሁን ላልሰገደ ሌሊት ላይ በጀማዐም ይሁን ለብቻ መስገድ ይችላል። ከዊትር በኋላ መስገድም መረጃ መጥቶበታል። ባይሆን ሁለት ጊዜ ዊትር አይሰገድም። "በአንድ ሌሊት ሁለት ዊትር የለምና።" [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7567]
ወላሁ አዕለም!
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- /channel/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
ችግረኛችን ማብላት ያለው ዋጋ
~
1ኛ፦ የደጋጎች ስራ ነው። አላህ ደጋጎችን ከገለፀባቸው ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነው፦
{ وَیُطۡعِمُونَ ٱلطَّعَامَ عَلَىٰ حُبِّهِۦ مِسۡكِینࣰا وَیَتِیمࣰا وَأَسِیرًا }
"ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድሃ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ፡፡" [አልኢንሳን: 8]
2ኛ፦ ለጀነት መግቢያ ሰበብ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፦
«وَأَطْعِمُوا الطَّعَامَ، وَصِلُوا الْأَرْحَامَ، وَصَلُّوا بِاللَّيْلِ وَالنَّاسُ نِيَامٌ تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ بِسَلَامٍ»
"ምግብን አብሉ። ዝምድናን ቀጥሉ። ሰዎች ሲተኙ በሌሊት ስገዱ። ጀነትን በሰላም ትገባላችሁ።" [ቲርሚዚይ]
3ኛ፦ ከጀሃነም እሳት መዳኛ ሰበብ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«اتّقُوا النّارَ ولَو بشِقّ تَمرَة»
"በተምር ክፋይም (ሶደቃ) ቢሆን ከእሳት ተጠበቁ።" [ቡኻሪይና ሙስሊም]
4ኛ:- ምግብን ማብላት በላጭ ተግባር ነው። አንድ ሰው ነብዩን ﷺ "ከኢስላም ቀንዘሎች ውስጥ በላጩ የትኛው ነው?" ብሎ ቢጠይቃቸው እንዲህ ሲሉ መለሱ፦
«تُطْعِمُ الطَّعَامَ وَتَقْرَأُ السَّلَامَ عَلَى مَنْ عَرَفْتَ وَمَنْ لَمْ تَعْرِفْ»
"ምግብን ልታበላ፣ ሰላምታን በምታወቀውም ላይ ይሁን በማታውቀው ላይ ልታቀርብ ነው።" [ቡኻሪይና ሙስሊም]
በሌላም ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል፦
«أَحَبُّ الأَعْمَالِ إِلَى اللَّهِ سُرُورٌ تُدْخِلُهُ عَلَى مُسْلِمٍ ، أَوْ تَكْشِفُ عَنْهُ كُرْبَةً ، أَوْ تَطْرُدُ عَنْهُ جُوعًا ، أَوْ تَقْضِي عَنْهُ دَيْنًا»
"ከአላህ ዘንድ ተወዳጅ ተግባር ማለት በሙስሊም ውስጥ የምታሰገባው ደስታ፣ ወይም ከሱ ላይ የምትገፈው ጭንቅ፣ ወይም ከሱ የምታባርረው ረሃብ፣ ወይም ለሱ እዳውን መክፈልህ ነው።" [ሶሒሑል ጃሚዕ]
ያለንበት ወር ረመዷን ነው። ረመዷን የሶደቃ፣ የልገሳ፣ የቸርነት ወር ነው። ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"በረመዷን ወር ድሃዎችን በማብላት ማገዝ ከኢስላም ሱናዎች ውስጥ ነው።" [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 25/298]
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- /channel/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
የዘካ ፋይዳና ዘካን ያለመስጠት አደጋ
~
/channel/IbnuMunewor/5568
የወርቅ ዘካ
~
/channel/c/1464859193/612
ዘካን ለቤተሰብ መስጠት
~
/channel/c/1464859193/611
የወረቀት ብር ኖት ዘካ
~
/channel/c/1464859193/610
ዘካ የሚመለከታቸው ንብረቶች
~
/channel/IbnuMunewor/5542
ዘካ የሌለባቸው ንብረቶች
~
/channel/c/1464859193/608
ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው?
~
/channel/c/1464859193/607
የተቀማጭ ወይም የንግድ ገንዘብ ዘካ ሂሳብ አሰራር
/channel/c/1464859193/606
የንግድ ሸቀጦች ዘካ እና ተያያዥ ነጥቦች
~
/channel/IbnuMunewor/5550
🌐 የውይይቱ ርዕስ 🌐
🌀እየሱስ ሰው ነው ወይስ አንድ አምላም⁉️🌀
ክፍል 1⃣
🎙🎙በኡስታዝ ወሒድ እና በወገናችን ሳሙኤል 💎💎
ሰላም የተሞላበት ውይይት 👇
/channel/Wahidcom
ወጣቶች ናቸው፡፡እሩቅ መስጂድ ሄደው መስገድ ውስጣቸው ነው፡፡ ግን ለተራዊሕ ሶላት እሩቅ መስጂድ እየሄዱ የኢሻ ሶላት ጀመአ ያመልጠቸዋል እና ማሻአላህ ጎበዝ እንበላቸው?!!
Читать полностью…አላሁ አክበር !
ሰዎች ወደ ኢስላም እየመጡ ነው ሳይሆን እያጎረፉ ነው፡፡ እኔ በምኖርበት ሰፈር በአንድ ግቢ ብቻ ብዙ ወጣቶች ሴቶችንም ጨምሮ በቅርብ ሰልመዋል ፡፡በትላንትናው እለትም አንድ ወጣትና አንድ እህታችን መስጂድ ቅዱስ ቁርኣን እዘናቸው በመሄድ ተወዳጁንና አላህ ዘንድም ተቀባይነት ያለውን ግልፅና የመያሻማ የሆነውን የሁሉንም ነብያት ሃይማኖት ኢስላምን እንዲቀበሉ አላህ ዎፍቆቸዋል ፡፡አልሐምዱሊላህ አላሁ አክበር ፡፡
ጥብቅ ማሳሰቢያ ፦
ከሙስሊሞች ብዙ ስራ ይጠበቅበቸዋል ፡፡ወደ ኢስላም የሚገቡ ሰዎችን ማበረተታት ፣ህግጋቱን ማስተማር ጠቃሚ መፅሐፍቶችን በቋንቋቸው የተተረጎመውን ገዝቶ መስጠት ፣
እንዲያውም በዚህ ዙሪያ በቅርቡ ኡስታዝ ነጅሙዲን ሙሐመድ ቅዱስ ቁርኣን ላይ ገንቢ ሐሳብ አንስቶ ብዙ ነገሮችን አውርቶ ነበር ፡፡
በዚያው እለት ከተነሱ ነጥቦች ውስጥ በየ ሰፈሩ ወይም በየ መስጂዱ የተወሰኑ ሰዎች ተደራጅተው ኮሚቴ ተቆቁሞ ገንዘብ አዋቶ ስራ ለሌላቸው ማደሪያና ልብስ መሰል ነገሮች ለሚቸግራቸው ለሆኑ ሰለምቴዎች እገዛ ቢደረግ ወዘተ የሚል ሐሳቦች ተነስተው ብዙ ተወርቶ ነበር ፡፡መጨረሻ ላይ ምን ላይ እንደ ተደረሰ እኔጃ ጉዳዩ ችላ ባይባልና በመካከላቸው ያለውን ልዩነት ወደ ጎን በመተው አንድ ቁም ነገር ቢሰሩ መልካም ነበር አላህ ያግዛችሁና ፡፡
ሰዎች እኛ ሳይሆን ኢስልምና መንገዱ ራሱ ጠርቶዋቸው ይመጣሉ እኛ መስጂድ ውስጥ ስማቸውን ቀይረን አላሁ አክበር ብለን እንሸኘቸዋለን ከዚያ ቦኀለ ያ ሰለምቴ የት ይድረስ ምን ይቸግረው ከኛ ምን ይፈልጋል የለም ሰም ቀይረን ማባረር ነው ፡፡ ይህ በጣም አሳዛኝ ነው ለኛ ነውርም ነው፡፡አላህ ይዘንልን
ወንድማችሁ አብዱረሒም ነኝ ከአዳማ
/channel/gfyygy
ለአቅመ አዳም ወይም ለአቅመ ሄዋን የሚደረሰው መቼ ነው?!
~
ብዙ ሰዎች ሸሪዐዊ ሃላፊነት ለመሸከም የሚደረስበትን እድሜ ሲያስቡ 15 አመት መድረስን ብቻ ነው ከግንዛቤ የሚያስገቡት፡፡ እውነታው ግን ሌሎች ተጨማሪ መለኪያዎች መኖራቸው ነው፡፡ በጥቅሉ አንድ ሰው እንደማንኛውም "አዋቂ" ሙስሊም ተቆጥሮ በሚሰራው ስራ የሚጠየቅበት (ባጭሩ ስራዎቹ የሚመዘገቡበት) የእድሜ ክልል የሚደርሰው ከሚከተሉት አራት ምልክቶች ውስጥ ቀድሞ በተከሰተው ነው፡-
1. በህልምም ይሁን በውን የዘር ፈሳሽ መውጣት መጀመር፣
2. በብልት ዙሪያ ፀጉር መብቀል (መባለቅ)፡-
መጠኑም ፀጉሩ ለመላጨት የደረሰ ብዛት ሲኖረው ነው፡፡ እዚህ ላይ የፂም ወይም የብብት ፀጉር መለኪያ አይሆንም፡፡ የጡት መውጣት፣ የድምፅ መጎርነንና መቅጠን መለኪያ አይደሉም።
3. ለሴት የወር አበባ ማየት፡-
እነዚህ ሶስት ምልክቶች ከታዩ ልጅዎ ለሸሪዐዊ ሃላፊነት ደርሷል ወይም ደርሳለችና ያስገንዝቡ ይከታተሉ፡፡ 15 አመት መድረስን እየጠበቁ ተዘናግተው እንዳያዘናጉ፡፡ ደግሞም ከልጆችዎ ጋር ለጉዳዩ የሚያስፈልገውን ያክል ግልፅ ውይይትና መነጋገር ይኑር፡፡ ጉዳዩን ቀድሞው ካወቁ ራሳቸውን ለሃላፊነት ያዘጋጃሉና፡፡ ካላወቁ ግን እድሜያቸው ደርሶ ላይሰግዱ ላይፆሙ ይችላሉ፡፡ ልክ እንዲሁ ካላወቁ ወይም ደግሞ አጉል መተፋፈር የሚኖር ከሆነ ከነ ጀናባቸው ሊሰግዱ፣ የወር አበባ ላይ ሆነው ሊፆሙና ሊሰግዱ ይችላሉ፡፡ ይሄ ከባድ ጥፋት ነው። ስለዚህ ለልጆችዎ ወይም ደግሞ ለእህት ወንድሞችዎ በቂ ግንዛቤ ያድርሱ፡፡ መተፋፈሩ ሐቅ እንዳይሸፍን ይጠንቀቁ፡፡
4. የመጨረሻው ምልክት 15 አመት መድረስ ነው።
ከላይ ከተራ ቁጥር አንድ እስከ ሶስት የተጠቀሱት ምልክቶች ባይታዩም 15 ከተደረሰ ቀጥታ የልጅነት የእድሜ ክልል ታልፏል ማለት ነው፡፡
ምልክቶቹ ከ 15 አመት ቀድሞ መታየት የጀመሩ ከሆነ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እንደማንኛውም አዋቂ ሰው ሸሪዐዊ ህግጋትን በጥብቅ መከታተል ይገባል፡፡ ምልክቶቹ ቀድመው ታይተው ሳለ ሳይፅፆም የታለፈ የረመዳን ፆም ካለ ቀዷ ማውጣት ግድ ይላል ይላሉ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ፡፡ በማህበረሰቡ ዘንድ ስለጉዳዩ ጭራሽ ግንዛቤ ከሌለ ግን ቀዷእ ማውጣቱ ግዴታ እንዳልሆነ ፍንጭ የሰጡበት ፈትዋ አለ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
በነገራችን ላይ 15 አመት መድረስ ሲባል የሚፈለገው በኢስላማዊው የሂጅራ አቆጣጠር እንጂ በፀሐይ አቆጣጠር አይደለም፡፡ (የሂጅራው አቆጣጠር የጨረቃ አቆጣጠር ሲሆን የኢትዮጵያውና የፈረንጆቹ ግን የፀሐይ አቆጣጠር እንደሚባል ያስተውሉ፡፡) በጨረቃ አቆጣጠር አንድ አመት 354 ቀን አካባቢ ሲሆን በፀሐይ አቆጣጠር ግን 365 ቀን አካባቢ ነው፡፡ እናም አንድ ልጅ በሂጅራው አቆጣጠር 15 አመት የሚደርሰው ከፀሐዩ አቆጣጠር ቢያንስ ከ 5 ወራት በፊት ቀድሞ ነው ማለት ነው፡፡
ስለዚህ አንድ ልጅ ከ 15 ዓመት በፊት ከላይ ከአንድ እስከ ሶስት ካሉት ምልክቶች አንዱ ከታየበት ወይም ደግሞ እነዚህ ሳይታዩ ቀርተው 15 አመት ከደረሰ ጊዜ ጀምሮ እንደማንኛውም አዋቂ ሰው ለሸሪዐዊ ህግጋት ተገዥ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ በኋላ ባእድ ሴቶችን መጨበጥ፣ መመልከት፣ ከባእድ ሴት ጋር ለብቻ ተገልሎ መቀመጥ የለበትም፡፡ በቃ ከዚህ በኋላ በደረሱ ወንዶች ላይ የሚከለከሉ ነገሮች ሁሉ ለሱም ክልክል ናቸው፡፡ የደረሱ ወንዶችን የሚመለከቱ ግዴታዎች ሁሉ ይመለከቱታል፡፡ ሴቷንም እንዲሁ፡፡ አለባበስን ጨምሮ ነገሮችን በጥንቃቄ ልትከታተል ይገባታል፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 2/2009)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
እንደሚታወቀው ብዙ ሰው ዘካ የሚያወጣበት ጊዜ ላይ ነን፡፡
ብዙዎች ዘካ ያወጡ እንጂ ለማን መስጠት እንዳለባቸው ግን የዘነጉ ይመስላል ፡፡ወይም አያቁም ወይም እነሱ የሚያሳስባቸው ገንዘቡ ከነሱ እጅ መውጣቱ እንጂ መስፈርቱ ምን ይሆን አየሳስባቸውም ፡፡
በነገራችን ላይ በሶላት በፆም በሐጅ እንደታዘዝነው በዘካም ታዘናል፡፡
ለሶላትና ለፆም ለሐጅ መስፈርትና የአተገባበር ስራኣት በሐዲስና በቁርኣን እንደመጣልን ሁሉ ለዘካም መች ማውጣት ና ለማን ማስጠት እንዳለብን መቶልናል
በዚህ ላይ ኻጢቦች በየ መስጂዱ ለሂዝቡ ግልፅ በሚሆንለት መልኩ በሰፊው ቢያስተምሩ ብዙዎች ይነቁ ነበር፡፡
ምክንያቱም ብዙዎች ሙስሊም ያልሆኑትንና ሙስሊሞችን በአንድ ላይ ሰብስቦ ነው እየሰጡ ያሉት ፡፡
ሙስሊሙ ወንድሜ የዘካ ገንዘብ ያንተ አይደለም አንተ አይደለህም የምታዝበት ባለቤት አለው ባለቤቱም አላህ ነው ፡፡አላህ ደሞ ሐቁን ለማን ማድረስ እንዳለብህ ደንግጎልሃል ፡፡ስለዚህ ተማር ካልተማርክ ደሞ ጠይቅ ፡፡መስጠት ላይቀር የሚያምር አሰጣጥን ስጥ ፡፡ነገ የማታፍርበትን ታላቅ ሚንዳን የምትመነዳበትን ፡፡
አላህዬ "የማታቁትን ከሚያቁት ጠይቁ"ይላል አይደል??
/channel/gfyygy
ዝቅጠት ማለት ይሄ ነው!!ካፊር ጓደኛን ገጥሞ 👉በአላህ ስም መማል አፍሮ ለሱ(ለካፊሩ)ሞራል ብሎ"ኤግዝያብሄርን"! የሚል ወጣት ምንኛ የዘቀጠ ነው። እንዴት ይህን ትልቅ ሀይማኖት ኢስላምን ተሸክሞ የወረደውን የዘቀጠውን ሀይማኖት ሰውሰራሹን ሀይማኖት በሚከተል ሰው ይተፈራል?!!ወላሂ ብዙ ቦታ አገጥሞኛል ።ደሞ ካፊሩኮ አንድም ቀን ለሙስሊሙ ሞራል ብሎ በአላህ ስም አለመማሉ ነው!!
ሙስሊሙ ወገኔ ሆይ!የተሸከምከው ሀይማኖት የሁሉም ነብያት ሀይማኖት ምድር ሰማይ የቆመለት ሰውም ጂኑም የተፈጠረለት ሀይማኖት(ኢስላም ነው) ልታፍርበትና ልትሽማቀቅበት አይገባም በል እንዲያውም ልትኮራበት ይገባል
/channel/gfyygy
"ከዐርሹ በላይ"
ኢብኑ ሙነወር
የካቲት 24/2016 በቡታጂራ ከተማ ሙሳ ራማሽ መስጂድ የቀረበ
=
የቴሌግራም ቻናል
/channel/IbnuMunewor
"ውሃቢያ"ተባልን
አላህን ብቻ ተገዙ ሺርክን ራቁ ቢድዐን ራቁ ሱናን ተከተሉ ስላልን
የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትእዛዝ ከየትኛውም ኡስታዝ (ሸይኽ)ይቅደም ስላልን
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቅድምያ ለሰጡት እኛም ቅድምያ እንስጥ ስላልን
በሰላዋት አይጨፈርም ሰላዋት አምልኮ ነው ልክ በታዘዝነው መሰረት እንስራ(እነውርድ) ስላልን
በተውሒድ በሱና አንድ እንሁን ስላልን ልዩነታችን በቁርኣን እና በሐዲስ እንፍተ አንድ እንሁን ስላልን
በሶሐባዎች ዘመን ዲን የልነበራ አድስ ፈጠራ ዛሬ ዲን ሊሆን አይችልምና እንራቀው ስላልን
{ [ "ውሃቢያ"ተባልን]}
ስንት ፍጡር አለ?~~~
አባቱ ላይ የሚጀነን … እናቱ ላይ ’ሚደነፋ
ወላጆቹ የሚፈሩት … ስነ ምግባሩ የከረፋ
ስንት ከንቱ ፍጡር አለ … አኺራውን እሚያጠፋ?
ጉርምስናውን ተጠቅሞ ወላጆቹን የሚገፋ
ሳይሞቅ ፈላ የጥጃ ቀንዳም ሽቅብ ምራቁን የሚተፋ
|
አራስ ነብር ሆኖ ገብቶ … ሳር ቅጠሉን የሚያስጨንቅ
ከባእድ ጋ እየተላፋ … ሚስቱን ልጁን የሚያሳቅቅ
ስንት ብኩን ፍጡር አለ … አስተሳሰቡ የተዘጋ
ለቤተሰብ የማይመች … የውጭ አልጋ የቤት ቀጋ
|
ምላሷ እንደ ጦር የሚዋጋ … እንደ ብጉንጅ የምትነዘንዝ
ለባሏ ጀርባ ሰጥታ … ከባእድ ጋር የምትላዘዝ
ስትወጣ ጥርሷ 64 … ምላሷ ማር የሚተፋ
ከቤቷ የእሳት ወላፈን … ሁለ ነገሯ የጠፋ
ስንት ከንቱ ፍጡር አለች … ኢስላም፣ ሞራል የማይገዳት
በራሷ ዛቢያ የምትዞር … መላ ቅጡ የጠፋባት?
/channel/IbnuMunewor
✅✅✅✅✅
☞ለላጤዎች ምክር!
♻️ያላገባህ እንደሆነ በተቻለህ መጠን ለማግባት ሞክር!
♻️ስለ ትዳር በቂ እውቀት ይዘህ ወደ ትዳር ግባ!
♻️ ማግባት ካልቻልክ ግዜህን በመልካም ነገር አሳልፍ፦ በፆም፣ በንባብ፣ መልካም ኢስላማዊ ትምህርቶችን በመማር፣ በመስማትና በማየት.......
♻️በብዛት ብቻህን ከመሆን ተቆጠብቀ
♻️አላህን ከዚህ ቀፋፊ ወንጀል ነፃ እንዲያረግህ ተማፀን!
♻️መልካም ሰዎች ጋር ለመቀማመጥ ሞክር!
♻️ሸይጣን ይህን ወንጀል ባስታወሰህ ቁጥር ቆራጥ ሆነህ ላለመመለስ ሞክር! መጀመሪያው ቢከብድብም በሂደት አላህ ይረዳሃል!
≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅≅
☞ለባለ ትዳሮች ምክር
♻️አግብተህ ከሆነ ከትዳር አጋርህ ጋር ስለ ወሲብ ህይወታቹህ ያለ እፍረት በግልፅ በመነጋገር የምትፈልጉትን እርካታ ሁሉ ማግኘት እንደምትችል እውቅ!
♻️ በኢስላም ጥላ ስር ያሉ ከወሲብ ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ትምህርቶችንና ጥናታዊ ፅሁፎችን አንብብ!
♻️ በዚህ ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸውን አላህን የሚፈሩ ብለህ የምታስባቸውን ወንድሞችህን አማክር!
♻️ ሚስትም የዘመኑን ክፋት ልትረዳና ነቃ ብላ ከትዳር አጓሯ ጎን ልትቆም ይገባል። በግልፅ ማውራትና ፍላጎቱን ማሟላት ብልግና ሳይሆን ብልጠት መሆኑን አውቃ በተቻለ መጠን ውበቷን በመጠበቅ የባሏ ልብ እንዳይሸፍትና እንዳይሰላች የበኩሏን ጥረት ሁሉ በማረግ ባለቤቷን በየግዜው ማስደመም አለባት!
✖️እነዚህ የተግማሙና የበከቱ ዝሙተኞች ይህች አጭር ህይወትን እንዲያበላሹ አትፍቀድ! ጀግና ሁን!
♻️በመጨረሻም የመልካም ሰዎችን ታሪክ አንብብ! እንዴት አላህን እንደሚጠነቀቁ አስተውል አስተንትን በዚህ ወንጀልህ የሰማያትና የምድር ጌታን እያመፅክ መሆኑ ይሰማህ!
ኮምፒዩተሮችህና ስማርት ስልኮችን የመዋረጃህ ሰበብ አታርጋቸው!
♻️ሁላችንንም አላህ ለሚወደው ሁሉ ይርዳን!
✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ