ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot
ወንድሜ ሆይ! ሚስትህ እና ልጆችህ አስጠሉህ???
እህቴ ሆይ! ባልሽ እና ልጆችሽ አስጠሉሽ???
ልጆች ሆይ! አባት እና እናቶቻችሁ አስጠሏችሁ???
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በመልክተኞች መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ቀጥታ ወደ ነጥቡ እንግባ፡፡
1) ወንድሜ ሆይ! ሚስትህ እና ልጆችህ አስጠሉህ???
ምን ነክቶህ ነው ወንድሜ ስንት ሽማግሌ አስልከህ ያገባሃትን፤ የአላህ ቃል ኹጥበቱል ሃጃ የተቀራበትን ሰለዋት ተወርዶ ‹‹ብልቷ›› የተፈቀደልህን ሚስት፤ ብሎም ከሷ ያገኘሃቸውን ምርጥ ልጆች አስጠልተውህ፤ ሰልችተውህ ነው፤ ከነሱ ጋር መጫወቱን ትተህ
- ኳስ
- ቃና
- ጫት
- ፊልም
- ከረንቡላ
- ፑል
- ዜና፤ ታላቅ ፊልም፤ ፖለቲካ እና የመሳሰለውን እያልክ እነሱን ዞር ብለህ እንኳን የማታያቸው፡፡ አረ መጀመሪያ ጀመዐ ሰላት ትተህ፤ ፊልም፤ ዜና፤ ኳስ ላይ አምሽተህ ፈጅር ሰላትን እያሳለፍክ፤ ለሚስትህ እና ለልጆችህ ክብር ትሰጣለህ ተብሎ አይገመትም፡፡ ጌታውን ማውሳት የሰለቸው እና ቀልቡ የደረቀ ብቻ ነው አላህን ከማውሳት ይልቅ በእንደዚህ አይነት ነገር እራሱን የሚወጥረው፡፡
ልጆች እኮ ሊሳሙ፤ ዲናቸውን ልናስተምራቸው፤ በፍቅር አይን ልናያቸው እንጂ የወለድናቸው እነሱን ላለማጫወት እና ከነሱ ጋር ጊዜን ላለማሳለፍ ‹‹የአእምሮ ጭንቀት›› እንዳለበት ሰው ካርቶን ፊልም እና ሌላን እያዩ መሳቅ የእብደት ምልክት ይመስላል፡፡
አደለም በእንደዚህ ባለ የማይረባ ነገር፤ አላህን በመገዛት ላይ እንኳን ቢሆን፤ ለቤተሰቦቻችን ግዜ እንድንሰጥ ኢስላም ያስተምራል፡፡ ‹‹ለነፍስህም ሃቅ አላት፤ ለሚስትህም ሃቅ አላት፤ …..›› ታድያ ይህንን ታላቅ መርሆ የት እረስተን ነው፤ ሚስት እና ልጆች ያስጠሉት ይመስል፤ ቤቱ ይገባል ጨዋታው ከጌም፤ ከቲሌቭዥን፤ ከኳስ ጋር የሆነ ስንት ሰው ሞልቷል፡፡ እንጠንቀቅ
2) እህቴ ሆይ! ባልሽ እና ልጆችሽ አስጠሉሽ???
- ሙሰልሰል
- ሰው ለሰው
- ቃና፣ MBC
እና የመሳሰለውን እያልሽ ባልሽ እና ልጆችሽን የረሳሽዋስ ምን ነው እባክሽ??? ኢስላም ካንቺ ይሄን ነው የሚጠብቀው??? ባልሽ ሚስቴ ብሎ ይጠራሻል፤ አንቼ ሙሰልሰል ላይ ያለው ወንድ ላይ ስታፈጪ ታመሻለሽ፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ወንድም ሴትን አይመልከት ሴትም ወንድን አትመልከት›› ታድያ አንቺ ሙሰልሰል ላይ ያለ እንደ ሴት ‹‹ሜክ አፕ›› የሚቀባ ወንድን ስታፈጪበት ታመሻለሽ፡፡ ልብሽ ይደርቃል፡፡ መቼም ኢትዬጵያው ባል አላህ ሲፈጥረው ጠይም፤ ጠቆር ያለ፤ አንዳንዱን ቀይ አድርጎ ነው የፈጠረው፤ አንቺ ፊልም ላይ ያለን ‹‹ሜክ አፕ›› የሚቀባ ወንድ ስታይ እያመሸሽ ልብሽ ተሸርሽሯል፡፡ ታድያ ለባልሽ ትክክለኛ ፍቅር መስጠት ያቃተሸ በዚህ አይመስልሽም???
እስቲ ፊልም ላይ የምታሳልፊውን 10/100 አላህን በመገዛት ላይ ታሳልፊዋለሽ?????????????????????
ጥያቄውን ላንቺው ልተወው፡፡ እንዳትረሺ የሰው ልጅ ለአላማ ብቻ ነው ወደዚህ አለም የመጣው፡፡ ለሰራውም ይጠየቃል፤ ላጠፋውም ጊዜ እና ወጣትነት ይጠየቃል፡፡ መልስ አዘጋጅተሻል????????????
ልጆችሽ እማዬ ብለው ቢጠሩሽም አትሰሚም፤ ብተሰሚም ወደ ውድ ልጆችሽ መሄድ እና እነሱን ማስተናገድ ዲናቸውን ማስተማር ከብዶሻል፡፡ አረ ተይ አላህን ፍሪ፡፡ ትጠየቂባቸዋለሽ፤ መልስ አዘጋጅተሻል???
አንቺ እንዲ እየራቅሻቸው ይወዱኛል ብለሽ ትገምቻለሽ??? እወቂ ዛሬ ባደረግሺላቸው ቅርርብ እና ግንኙነት ነው ፍቅር የሚዳብረው፡፡
3) ልጆች ሆይ! አባት እና እናቶቻችሁ አስጠሏችሁ???
አባት እና እናት በዘመናቸው ልጅ ሲወልዱ ስንት ነበር ያሉት ‹‹ሙሃመድ አድጎልኝ እሱን ድሬ የልጅ ልጅ አይቼ….››፤ ‹‹ሙኒራ አድጋ አግብታ፤ ወልዳ፤ ከነ ልጆቿ እየመጣች ትጠይቀናለች›› ብለው ተመኝተው ነበር፡፡ ዛሬ አላህ ካዘነላቸው ውጭ አደለም ከእናት ከአባቱ ጋር አብሮ መንገድ ላይ ሊታይ፤ ሊያዋራቸው፤ እነሱ ሊያዋሩት እየፈለጉት እሱ/ እሷ ወይ ፌስቡክ ቻት ወይንም ፊልም እና የመሳሰሉት ላይ ናቸው፡፡
እስቲ ከዚህ ከአርቲፊሻል የማሽን (ቲቪ፤ ዲሽ፤ ጌም…እና የመሳሰሉት) ወጣ ብለን እውነተኛ ህይወትን እንደ ኢስላም እንኑር፡፡
ወንድሜ ሆይ! ሚስትህ እና ልጆችህ ጋር ተጫወት ፈታ በል፤ ከማሽን ጋር ያለህን ህይወት ቀንሰው፤ ካርቶን እና ሌላ ፊልም እያየህ እራስህን አታታል፤ አንተ ሰው ነህ ከሰዎች ጋር ተጫወት፡፡ ከሚስትህ፤ ከልጆችህ እና ከወላጆችህ ጋር፡፡ ካርቶን ፊልም የጤነኝነት ምልክት አይመስልም፡፡ ሰውን ለሰው ነው የፈጠረው፡፡
እህቴ ሆይ! ፍቅር ማለት ኢስላም ያሳየው፤ ለሰው ልጆች የደነገገው፤ አላህን መፍራት የተሞላበት እንጂ ፊልም ላይ ያለ ‹‹fiction›› አይደለም፡፡ ስለዚህ አጅነቢ ወንድ ላይ ተተክለሽ አምሽተሸ ነገ ሞት ቢመጣ ‹‹አሽሃዱ አላ ኢላሃኢለላህ ወአነ ሙሃመደን ረሱሉላህ›› የሚለው እንዲህ በቀላሉ ይመጣል ብለሽ ትገምቻለሽ?????????
አላህ ሆይ! የመጀመሪያው ተውልድ ሰሃባዎች እንዳመኑት እንድናምን ሃቁን ምራን፤ እውቀትን ጨምርልን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
ያለ ቦታው ነገር አናጥብቅ!
~
ወዳጅ ቤተሰብ የሞተባቸውን ሰዎች ተዕዚያ ማለት የፈለገ ሰው የግድ ቤታቸው ሄዶ መሰባሰብ አይጠበቅም። በቤት፣ በቀብር ቦታ፣ መንገድ ላይ፣ በስራ ቦታ፣ በመስጂድ ፣ ... ባገኛቸው ቦታ ተዕዚያ ማለት ይችላል ፣ በቂም ነው። [አሕካሙል ጀናኢዝ ፡ 320፣ 210] በስልክም ሊሆን ይችላል። እቤቴ አልመጡ ብለን ሰዎችን ልንቀየም አይገባም። ይሄ አጉል ነገር ማጥበቅ ነው። ሰዎች ጋር እንዳንቀያየም ካልፈራን በስተቀር ለዚህ ጉዳይ ተብሎ አገር አቆራርጦ መሄድም አያስፈልግም። የኛ እንግልት ለሟች የሚያተርፈው ነገር የለም። ሞቱ የኛ ከሆነም ሰዎች አገር አቋርጠው እንዳይመጡ እንንገራቸው። ከሰዎች እንግልት የሚደርሰን ነገር የለም።
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል :-
/channel/IbnuMunewor
•
"አህለል በይት ሁላ ተዳር እስተዳር
ሁሉም ባንድ ሁኖ እሞስጦፋ ጋር
ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር።"
•
አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(يَا أَيُّهَا النَّاسُ ضُرِبَ مَثَلٌ فَاسْتَمِعُوا لَهُ ۚ إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ لَنْ يَخْلُقُوا ذُبَابًا وَلَوِ اجْتَمَعُوا لَهُ ۖ وَإِنْ يَسْلُبْهُمُ الذُّبَابُ شَيْئًا لَا يَسْتَنْقِذُوهُ مِنْهُ ۚ ضَعُفَ الطَّالِبُ وَالْمَطْلُوبُ)
((እናንተ ሰዎች ሆይ! ምሳሌ ቀርቧልና አድምጡት፡፡ እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው ዝንብ አይፈጥሩም፣ ለዚሁ አላማ ቢሰበሰቡ እንኳን፡፡ ዝንቡ የሆነን ነገር ቢነጥቃቸውም አያስጥሉትም፡፡ ከጃይም ተከጃይም ደካሞች ናቸው፡፡)) (አል-ሐጅ፡ 73)
((ወይስ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ ማነው? ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሠጹም፡፡)) (ነምል፡ 62)
•
"ሙሐመዱሰማን ገፍታሪው ቀደር
የመዕሪፋ አረቂ አቅምሶ እሚያሰክር።"
•
ሱብሓነላህ!!
(وَلَا يَحْزُنْكَ الَّذِينَ يُسَارِعُونَ فِي الْكُفْرِ ۚ إِنَّهُمْ لَنْ يَضُرُّوا اللَّهَ شَيْئًا ۗ يُرِيدُ اللَّهُ أَلَّا يَجْعَلَ لَهُمْ حَظًّا فِي الْآخِرَةِ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ)
((እነዚያም ወደ ክህደት የሚቻኮሉት አያሳዝኑህ፡፡ እነርሱ ፈፅሞ አላህን በምንም አይጎዱምና፡፡ )) (ኣሊ ዒምራን፡ 176)
Ibnu Munewor
🏷 سنن أبي داود للإمام الحافظ أبي داود سليمان بن الأشعث السجستاني
الفن: الحديث
الكتاب: #سنن_أبي_داود
👈أول كتاب الأطعمة ٠١
👈رقم الحديث ٣٧٣٦-٣٧٥٢
🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም -ሐፊዞሁሏህ-
👉👉ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ጠዋት ከ5፡15 እስከ 6፡10 በቀጥታ ይተላለፋል
👉ቦታ ፉሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ
"نورها الله تعالى بمنه وكرمه بنور التوحيد والسنة "
📚 የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በ pdf መልክ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ
/channel/SheikhMuhammedZainAdam/584
📍ትምህርቱን ለመከታተል ይህን ቻናል ይቀላቀሉ
👇👇👇
/channel/SheikhMuhammedZainAdam
Or
/channel/abuhuzeyfashaikhmohammedzeyn
እኔ ካገር ቤት ከናፈቀኝ ነገር አንደኛው ለረዥም ጊዜ ከተራራቅናቸው ወንድሞች መገናኘት ነው ያረብ በሰላም አገናኝን በፍቅር በደስታ
Читать полностью…🛑👉ሁለት እጮኛሞች ከኒካህ በፊት ግኑኝነት ቢያደርጉ መጋባት ይችላሉን?
📍መልስ ከሸኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው
«አንድ ሰው ከኒካህ በፊት ከእጮኛው ጋር ግኑኝነት ካደረጉ ትክክለኛ ተውበት እስኪያደርጉና ከኢዳዋ እስካሎጣች ድረስ መጋባት አይችሉም። ከዚህ በኋላ ኒካህ ያስራል። በዛ ግኑኝነት ልጅ ከመጣ የዝሙት ልጅ ነው። ወደ አባቱ ይጠጋም (የሚጠጋው ወደ እናቱ ነው)። በዝሙት የተገኘ የሷ ልጅ ነው የሚሆነው።…… የዝሙት ልጅ ከሌላቸው፣ ትክክለኛ ተውበት ካደረጉና ኢዳዋ ከጨረሰች ከዛ በኋላ የሚወለዱ ልጆች ሸሪአዊ ልጆቻቸው ይሆናሉ።»
👆👆👆👆
📍ሸኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው
እኛ ሀገር አንድ የተለመደ አሰራር አለ። በዝሙት እንዳረገዘች ከታወቀ ወዲያው ኒካህ ይታሰር ይባላልና ልጁ በሰውየው ስም ይጠራል። ይህ ስህተት ነው። በዝሙት አርግዛ እያለ ኒካህ የታሰረ ከሆነ ኒካህ መጀደድ (ባዲስ መታሰር ይኖርበታል)። ተውበት ካደረጉ በኋላ ከሷ ጋር ኒካህ ማድረግ ከፈለጉ እስክትወልድ ድረስ መጠበቅ አለበት። ምክንያቱም በዝሙትም ይሁን ከዝሙት ውጪ እርጉዝ በሆነች ሴት ላይ እስክትወልድ ድረስ ኒካህ አይታሰርምና።
𝐓𝐞 «t.me/Sadik_Ibnu_Heyru»
✅ ሶብር {ትዕግስት}
〰➖〰➖〰
↷አንዳንዴ ወደኋላ መለስ ብለን እራሣችንን መፈተሽ ጥሩ ነውና ትዕግስታች ትዕግስት
ስለሚያስፈልገው እስኪ ከዚ ኮከብ መካሪያች መክርን እንቀበል!
↷ትዕግሥት ፍርሐት ሣይሆን የመፍትሔ አቅጣጫ ነው።
↷ትዕግስትን ተማር/ተለማመድ
↝የሆነ ሰው ስልክህ ላይ ደውሎ ማን ልበል ቢልህ እራስህ አይደል የደወልከው ብለህ ቱግ አትበል።
🎙በ𝐔𝐬𝐭𝐚𝐳 𝐈𝐛𝐧𝐮 𝐌𝐮𝐧ewor
/channel/gfyygy
#ኡድሂያ ምታርዱ ሰዎች ይህን ከወዲሁ ልብ በሉ
ዛሬ ሀሙስ ዘል ቀዕዳ 26 ነው
أخرج مسلم عن أم سلمة أن رسول الله صلى الله
عليه وسلم قال
إذا دخلت العشر واراد أحدكم أن يضحي فلا يمس من شعره وبشره شيئا
وفي رواية : فلا يأخذن شعرا ولا يقلمن ظفرا
ከልጅነቴ ጀምሮ ስመኘው የነበረውን ያለኔት ቁርአኑ እየታዬ የሚቀራ ሰላሳ ጁዝ አፕልኬሽን ለማዘጋጀት በመታደሌ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል ፦ ምርጥ አፖች ናቸው በመረጣችሁት ቃሪእ የትም ቦታ ሆናችሁ ቁርአንን ማድመጥ መቅራት ያስችሏችኋል ያለኔት ።
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ አቡበከር አሻጢሪ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Abu Bakr Al Shatri Full Quran"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.shatri
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ ሱደይስ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Abdul Rahman Al-Sudais Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.sudais
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ ያሲር ዶሳሪ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Yasser Al Dosari Full Quran"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.dosari
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ ሰኡድ ሹረይም አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Shuraim Full Quran Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.shuraim
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ አብዱልወዱድ ሀኒፍ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
Check out "Abdul Wadud Full Quran Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.wadud
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ ሱደይስ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Abdul Rahman Al-Sudais Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.sudais
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ ሚንሻዊ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Al Minshawi Full Quran Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.minshawi
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ አብደላህ በስፈር አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Abdullah Basfar Full Quran"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.basfar
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ አብደላህ መጥሩድ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Abdullah Matrood Quran Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.abdullahmatroud
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ ሙፍቲ መንክ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
"Mufti Menk Full Quran Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.muftimenk
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ ሰእድ አልጋሚዲ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ "Saad al Ghamdi Full Quran"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.ghamidi
30 ጁዝ ቁርአን እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ አብዱልባሲጥ አብዱሰመድ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ
Check out "Abdul Basit Full Quran Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.abdulbasit
30 ጁዝ ቁርአኑ እየታዬ በድምጽ ያለኔት በቃሪእ አልሑዘይፊ አዘጋጅተንለታል አውርዳችሁ ተጠቀሙ
Check out "Al Huthaify Full Quran Offline"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hussenapp.huzaifi
ከፕለይስቶር ስታወርዱ 5 ኮከቦችን መስጠት አትርሱ
አፖችን ስታወርዱ ፕለይስቶር ላይ 5 ኮከቦችን (★★★★★) መስጠት አትርሱ ።አፑን ለዓለም ሕዝብ ለማስተዋወቅ ያግዘናልና።የዚህ አይነት አፖችን ማሠራት ለምትፈልጉ +251912767238 በዚህ ስልክ ቁጥር ያናግሩን ።
T.me/islamicappdeveloper
ኢስላማዊ አፕልኬችኖችን በትእዛዝ እናዘጋጃለን ።
አስተማሪና መሳጭ ታሪክ!
በስዑዲ የሚኖር አንድ የመኒ ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ታሪክ እንዲህ ይተርከዋል፡፡
ከፊሌ የዘካ ገንዘብ ሊያከፋፍል ፈልጎ ከሱ ጋር ወጣሁ፡፡ የድሃ መንደሮች ወዳሉባቸው ጠረፍ አካባቢ ተጓዝን፡፡ የዘካው ገንዘቦች በፖስታ የታሸጉ ነበሩ፡፡ እያንዳንዱ ፖስታ በውስጡ 5 ሺ ሪያል ይዟል፡፡ ከአንዱ መንደር ወጥተን የጂዳ-ጂዛን መስመር ስንይዝ አንድ የ70 አመት አካባቢ ሽማግሌ አገኘን፡፡ ሽማግሌው ብርቱና ጤናማ ነው፡፡ ጎዳናውን ይዞ ይጓዛል፡፡
ወዳጄ “ይሄ ደግሞ በዚህ ሰዓት በዚህ በረሃ ምን ይሰራል?” አለኝ፡፡
ሹፌሩ “ህገ ወጥ የመኒ ነው” አለ፡፡
ካጠገቡ ደርሰን ቆምንና ሰላም አልነው፡፡
“ከየት ነው ወንድም?”
“ከየመን”
“የት ነው የምትሄደው?”
“የአላህን ቤት ናፍቄያለሁ”
“ህጋዊ ነህ?”
“አይደለሁም”
“ለምን ህጋዊ አልሆንክም?”
“ለዋስትና 2 ሺ ሪያል ማስያዝ ይጠበቅብኛል፡፡ እኔ ያለኝ 200 ብቻ ነው፡፡ በመቶዋ ተሳፈርኩባት፡፡ የቀረኝ መቶ ብቻ ነው” አለ፡፡
“እሺ አጎቴ! በጉዞ ላይ ምን ያክል ሆነህ?” አለው ጓደኛየ፡፡
“ስድስት ቀን!”
“እየፆምክ አይደለም?”
“አይ ፆመኛ ነኝ፡፡”
“ጥሩ፡፡ አንተ ከ 5 በላይ የፍተሸ ኬላዎችን አልፈሃል፡፡ እንዴት ነበር የምታልፋቸው?” ሲለው
“ከሱ በስተቀር እውነተኛ አምላክ በሌለው አላህ እምላለሁ! የማልፈው በነሱው ዘንድ ነው፡፡ ግን አንድም ያናገረኝ የለም!!” አለ፡፡
“ለስራ ነው አመጣጥህ?”
“በጭራሽ ወላሂ! እኔ የአላህን ቤት ናፍቄ ነው የመጣሁት፡፡ ዑምራ ማድረግ ነው የምፈልገው፡፡ ወደ መካ ነው የምጓዘው፡፡”
“በአስፋልት ላይ ስትጓዝ ተዘዋዋሪ ዘቦች /ፓትሮል/ አልያዙህም?”
“ከግማሽ ሰዓት በፊት በ 50 ኪ. ሜ. ርቀት ላይ ይዘውኝ ነበር፡፡ እዚህ ከመድረሴ አንድ ኪ. ሜ. ቀደም ብሎ ድረስ እነሱ ናቸው ያመጡኝ፡፡ የት እንደምሄድ ሲይቁኝ በአላህ ምየ የአላህን ቤት እንደምፈልግ ስነግራቸው ለቀቁኝ” አለ፡፡
“ሱብሓነላህ! ጭራሽ እስከዚህ ቦታ በፍጥነት እንዲያደርሱህ አላህ ፓትሮሎችን አመቻቸልህ” አልኩኝ በውስጤ፡፡
ወዳጄ ሁለት ፖስታዎችን እየሰጠው “እነዚህን ያዝ፡፡ ዘካ ነው” አለው፡፡
እየተቀበለ “ጀዛኩሙላህ ኸይር” አለ፡፡
በፖስታዎቹ ያለው ገንዘብ መጠኑ ምን ያክል እንደሆነ አያውቅም፡፡
“የሰዑዲን ብር ታውቃለህ?” አልኩት፡፡
“አዎ!” አለ፡፡
“ጥሩ፡፡ ፖስታውን ክፈትና እንዳይጠፋብህ ገንዘቡን በቀበቶህ (በሒዛምህ) ውስጥ ደብቅ” አልኩት፡፡
ሲከፍተው 10 ሺህ ሪያል!!
“ይህ ሁሉ ለኔ ነው?” አለ፡፡
“አዎ ላንተ ነው” አልነው፡፡
ከመኪናው ላይ ወደቀ፡፡ እራሱን ሳተ፡፡ ከመኪናው ወርደን በላዩ ላይ ውሃ መርጨት ያዝን፡፡
“ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው? ይህ ሁሉ ገንዘብ ለኔ ነው?” እያለ መጮህ ያዘ፡፡ ቁጭ ብሎ ማልቀስ ቀጠለ፡፡
ወዳጄ፡ “ከኛ ጋር ትንሽ ወደ ፊት እንውሰደው” አለ፡፡
ከኛ ጋር መኪና ላይ ወጣ፡፡ ትንሽ ሲረጋጋ ጠየቅኩት፡
“ምንድን ነው ይህ ሁሉ ለቅሶ?” አልኩት፡፡
“እኔ የመን ውስጥ ከቤቴ ጎን ቦታ አለችኝ፡፡ ለአላህ ሰጥቻታለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቦቼ በሷ ላይ በጭቃና በድንጋይ አድርገን መስጅድ ገንብተንባታል፡፡ ግንባታው ቢጠናቀቅም ምንጣፍና ጥቂት ነገሮች ቀርተውት ነበር፡፡ ለዚህ መስጂድ እንዴት ምንጣፍ እንደማገኝ ተቀምጬ አስብ ነበር” አለ፡፡
ይህን ሲል የእውነት ሁላችንም አለቀስን፡፡ “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው ዱንያ እንዳለች ትመጣለታለች” የሚለውና “አሳቡ ኣኺራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃቱን ከልቡ ውስጥ ያደርግለታል፡፡ ነገሩንም ይሰበስብለታል፡፡ ዱንያ በግዷ ወደሱ ትመጣለች፡፡ አሳቡ ዱንያ የሆነ ደግሞ አላህ ድህነቱን በአይኖቹ መሀል ያደርግበታል፡፡ ነገሩንም ይበትንበታል፡፡ ከዱንያም የተወሰነለት ብቻ እንጂ አይመጣለትም” የሚለው የነብዩ ﷺ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡
በዚህን ጊዜ ወዳጄን ለሰውየው እንዲጨምረው ጠየቅኩት፡፡ ተጨማሪ 2 እሽግ ፖስታ ሰጠው፡፡ በድምሩ 20 ሺ ሪያል አገኘ ሰውየው፡፡ ሰውየው ከመኪናው ከመውረዱ በፊት እያለቀሰ ያጉተመትምና ዱዓ ያደርግ ነበር፡፡
“በአላህ ላይ እውነተኛ የሆነውን መመካት ብትመኩ ኖሮ ልክ ወፍን እንደሚረዝቀው ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ተርባ ወጥታ ጠግባ ትመለሳለች” የሚለው የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መጣብኝ፡፡
የተተረጎመ
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 25/2010)
http://t.me//IbnuMunewor
🚫 ማን ነው በጂሃድ የሚያዘው ?
በመጀመሪያ ደረጃ ሁሉም ሊያወቀው የሚገባው ጂሃድ በኢስላም ትልቅ ቦታ ያለው ለአላህ ተብሎ አንገት የሚሰጥበት የአምልኮት አይነት ነው ። ጂሃድ ምእራባዊያን እንደሚያስቡት አላማው ዝም ብሎ የሰው ሕይወት ማጥፋት አይደለም ። ኢስላም ጂሃድን አስመልክቶ በጣም ግልፅ መርሕ ነው ያለው ።
እንደሚታወቀው በእስልምና የአምልኮ ድንጋጌ አይነቶች በሁለት ይከፈላሉ : –
↪️ በቀጥታ ለራሳቸው ተብለው የታዘዙ በመስፈርታቸው ሁሌም የሚሰሩ ( መቅሱድ ሊዛቲሂ ) የሆኑ እንደ ሶላትና ፆምና ሐጅ የመሳሰሉ የአምኮ አይነቶች እና
↪️ በቀጥታ ለራሳቸው ተብሎ ሳይሆን ለሌላ አምልኮ መዳረሻ ተብሎ የታዘዙ ( መቅሱድ ሊጘይሪሂ ) የሆኑ
ለምሳሌ ውዱእ ማድረግ :– ውዱእ የታዘዘው በዋነኝነት ለሶላት ሲሆን ያለ ውዱእ አይሰሩም ለተባሉ የአምልኮት አይነቶችም ይሆናል ። በመሆኑም አንድ ሰው ውዱእ ማድረግ ግዴታ የሚሆንበት ሶላት መስገድ በሚፈልግ ጊዜ ወይም የፈርድ ሶላት ወቅት ሲደርስ ይሆናል ። ይህ ማለት ውዱእ በራሱ ዒባዳ ከመሆኑ ጋር ። ነገር ግን የሚፈለገው በቀጥታ ለራሱ ሳይሆን ለሌላ የዒባዳ አይነት ነው ።
እንደዚሁ ጂሃድም በቀጥታ ለራሱ ሳይሆን የታዘዘው ለሌላ አምልኮት ነው ። እሱም አላህ ለሰው ልጆች የሕይወት መመሪያ ይሆን ዘንድ ቁርኣንን አውርዷል ። ይህንን መለኮታዊ የህይወት መመሪያ የሆነው ቁርኣን ለሰው ልጆች እንዲያደርሱ መልእክተኞችን ልኳል ። ይህ መለኮታዊ የሕይወት መመሪያ የሆነው የአላህ ቃል መልእክተኞቹ ለሰው ልጅ ሊያደርሱና የሰውም ልጅ ይህ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ ሊደርሰው መብቱ ነው ። በሱና በመብቱ መካከል የሚቆም አካል ሊኖር አይገባም አይ ብሎ በዚህ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ በማድረሱ መንድ ላይ የሚቆም አሜኪላ ወይም ጋሬጣ በሚኖር ጊዜ ይህን ለማስወገድ ነው ጂሃድ የታዘዘው ። ከመሆኑም ጋር እንደ ሌሎቹ ህግጋቶች ሁሉ የራሱ የሆነ መስፈርቶች አሉት ። ልክ ዘካ አቅም ያለው ሰው እንደሚያወጣውና ሐጅም አቅም ያለው ሰው ሌሎች መስፈርቶችን አሟልቶ እንደሚያደርገው ሁሉ ። ጂሃድም አቅም ያለው መሪ ነው የሚያዝበት ። ኢስላም አቅም የሌለውን ዘካ አውጣ ወይም ሐጅ አድርግ እንዳላለው ሁሉ በዳዕዋ መንገድ ላይ የተጋረጠውንም አሜኪላ ለማስወገድ አቅም የሌለውን ጂሀድ አድርግ አላለውም ።
ወደ ርእሴ ስመለስ የዚህ አይነቱ ትልቅ የሸሪዓ አካል የሆነውን ጂሃድ ማን ነው የሚያዝበት ከተባለ የሙስሊም መሪ መስላሐና መፍሰዳውን አይቶ አቅሙን መዝኖ በመንገዱ ላይ የቆመውን አሜኪላ አቅም አመዛዝኖ ከሚመለከታቸው የዲኑና የሀገር ህልውና አደራ ከተጣለባቸው አጋሮቹ ጋር በመሆን የሚያዝበት ነው ።
በመሆኑም በኢስላም ጂሃድ ማንም ሰው ተነስቶ የሚያውጀው ወይም ተነሱ የሚልበት ሳይሆን በጣም ትልቅ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነው ። ለዚህ ነው የአላህ መልእክተኛ ወሕይ እየወረደላቸውም ሙሃጅሮችንንና አንሷሮችን ያወያዩበት የነበረው ። እነ አቡበከር ዑመር በዚሁ መልኩ ትላልቅ የሙሃጅርና የአንሷር ሶሓቦችን ሰብስበው ያወያዩ የነበረው ።
በጣም የሚገርመው ዛሬ ሀገራችን ላይ ማን እንደሆኑና የት ሆነው እንደሚያዙ የማይታወቁ አካላት ጂሃድ እያወጁና ተነሱ እያሉ ነው !!!!!! ። እነዚህ አካላት ሊያውቁት የሚገባው ወይ የኢስላም ጠላት ተላላኪዎች ናቸው ። ሙስሊሞችን ለማጥቃት ይህን ምክንያት አድርገው መንቀሳቀስ የሚፈልጉ የኢስላም ጠላቶች ወይም በስሜት ፈረስ የሚጋልቡ ከጂሃጅ ስሙን እንጂ ርቀቱንና ሸሪዓዊ ብይኑን የማያውቁ ። የሚያሳዝነው እነዚህ ሙስሊሙን ወጣት ለጂሀድ ተነስ የሚሉ አካላት ሚስቶቻቸው ወይም እህቶቻቸው በየወሩ ወይም በወሊድ ጊዜ ስለሚፈሳቸው ደም ሸሪዓዊ ብይን ቢጠይቁዋቸው መመለስ የማይችሉ ናቸው ‼። ነገር ግን በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው ማኪያቶ እየጠጡ በኡማው ደም ላይ ፈትዋ ይሰጣሉ ። ሙስሊሞች ሆይ በፖለቲካ ወይም በመሬት ስራ የከሰሩ ማንነታቸው የማይታወቁ የኢስላም ጠላት ተላላኪዎች ተነሱ ጂሃድ ስላሉዋችሁ ወይም በእንቅፋት አለያም ትንታ ትሞታላችሁ እቺን እርካሽ ህይወት ለዲን ሰጥታችሁ በጀነት በራፍ ላይ የጀነት ሙሽራ አበባ ይዛ ብተቀበላችሁ ይሻላችኋል ‼ ብለው እያሰከሩ እንዳይነዱዋችሁ ።
የወንድምነት ምክሬ መጀመሪያ ዲናችሁን እወቁ ተማሩ ስሩበት አውቃችሁ የሰራችሁበትን እውቀት ለሌሎች በማድረስና ከሽርክና ቢዳዓ እንዲወጡ ሰበብ በመሆን በነፍሳችሁ ላይ ጂሃድ አድርጉ ይህ ለናንተ ትልቅ ጂሃድ ነው ። ስለሺርክና ቢዳዓ ሳታውቁ ስለጣሃራና ሶላት ሳታውቁ ወደ አኼራ እንዳትሄዱ ተጠንቀቁ ።
የሱና ዑለሞች ፣ ኡስታዞችና ዱዓቶች ሙስሊሙን ከእነዚህ አካላት መጠበቅና ግንዛቤ ማስጨበት ወቅታዊ ግዴታችሁ ነውና አማናችሁን ተወጡ ኡማውን ታደጉ ።
አላህ ሐቅን አውቆን የምንሰራበትና ባጢልን አውቆን የምንርቀው ያደርገን ።
/channel/bahruteka
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ማስታወሻ
ዙል ቀዕዳህ 15/1444
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
ምንተዳደረው በሸሪኣ ህግ ነው
መስጂድ ላፈረሰ ቅጣቱ ምንድነው ?
መጅሊሱም ይንገረን ትእዛዙንም ይስጠን
እኛኮ ለጂሃድ ሁሌም ዝግጁ ነን
መስጂዴን አፍርሰህ ሀገር ልትገነባ
የማነህ ደፋር ሰው እንከፍ ሆዳም ጀዝባ
የናድካትን መስጂድ ቶሎ ቶሎ ገንባት
ቀድምቷ ኢትዮጲያ ሰላም እንድቶናት
ወንድማችን አንዋር ከመሞቱ ቀናት በፊት የተናገረው አላህ ይርሀመው ከሸሂዶችም አድርገው !!
🔹القارئ سعد الغامدي
قناة القرآن الكريم .. 👇
🍃 /channel/qraan1
قناة تلاوات القارئ : سعد الغامدي 👇
🎋 /channel/saad_alghamdi
💢በምላስህ ጉዳይ አላህን ፍራ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✅ ሱፍያን አስሰውርይ አላህ ይዘንለትና ለጓደኞቹ እንዲህ በማለት ገሰፃቸው።
🔹ሱፍያን አሰውርይ
🔺🔺🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹አንድ ንጉስ ቢኖርና የምትናገሩት ነገር ሁሉ ወደንጉሱ የሚያደርስ ሰው ከናንተ ጋር ቢኖር ንጉሱን የሚያስቀጣና የማይወደው ንግግር ትናገራላችሁን❓አላቸው።
🔹ጓደኞቹም
🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹ኧረ በጭራሽ አንናገርም ብለው መለሱ።
🔹ሱፍያን አስሰውርይ
🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺⤵️⤵️
🔹ታዳ ከናንተ ጋር እኮ በግራና በቀኝ ተቀምጠው የምትናገሩትን ሁሉ ፅፈው ወደ አላህ የሚያደርሱ መላኢካዎች እኮ አሉ። ስለዚህ እሱን ከሚያስቆጣና ከማይወደው ንግግር ለምን አትቆጠቡም❓ በማለት መከራቸው።
📚 التبصرة لابن الجوزي( 2/237 )
↪️አላህም በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ ይላል።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
【إِذْ يَتَلَقَّى ٱلْمُتَلَقِّيَانِ عَنِ ٱلْيَمِينِ وَعَنِ ٱلشِّمَالِ قَعِيدٌ】
🔘ሁለቱ ቃል ተቀባዮች (መላእክት) ከቀኝና ከግራ ተቀማጮች ኾነው በሚቀበሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
【مَّا يَلْفِظُ مِن قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ】
🔘አንድ ሰው ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላኢካዎች) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡
📚 سورة "ق" (18-17)
/channel/emfwazen
/channel/+VgzWTJOEeEVkNDNk
ፆም እያለበት የሞተ ቤተሰብ አላችሁ?
~
በህመም፣ በጉዞ፣ በወር አበባ፣ በወሊድ፣ በእርግዝና፣ በማጥባት የተነሳ የግዴታ ፆም እያለበት/ እያለባት በተለያዩ ምክንያቶች ሳይፆም / ሳትፆም የሞተ /ች ሰው ቤተሰብ ይፆምለታል / ይፆምላታል። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
مَنْ مَاتَ وَعَلَيْهِ صِيَامٌ صَامَ عَنْهُ وَلِيُّهُ
"ፆም እያለበት የሞተ ሰው ቤተሰቡ ይፀምለት።" [ቡኻሪ፡ 1952] [ሙስሊም፡ 1147]
መፆም የሚጠበቀው ታዲያ ሟቹ ቀዷእ ማውጣት የሚችልበት ሁኔታ ከነበረ በኋላ ሳይፈፅም ከሞተ ነው። እንጂ ለመፆም የሚችልበት ሁኔታ ሳይኖረው ከሆነ የሞተው የፆም ግዴታ ስለሌለበት ለሱ ተብሎ መፆም አይጠበቅም። ምስኪን ማብላትም አይጠበቅም። ምክንያቱም ነፍስ ከአቅም በላይ በሆነ ጉዳይ ተጠያቂ አይደለችምና። የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦
{لَا یُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفۡسًا إِلَّا وُسۡعَهَاۚ لَهَا مَا كَسَبَتۡ وَعَلَیۡهَا مَا ٱكۡتَسَبَتۡۗ}
"አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርሷ የሰራችው አላት፡፡ በርሷም ላይ ያፈራችው (ሃጢአት) አለባት።" [አልበቀረህ: 286]
Ibnu Munewor
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor
የሺርክ ዶፍ ከሙሐመድ አወል መንዙማ
የሺርክ ዶፍ ከሙሐመድ አወል መንዙማ~~~~~~~~
"ጌታዬ ለመንኩህ ባንቢዎቹ ስር
በሩሱል ባውሊያ አንድ እንኳን ሳይቀር
አቤት ብየ ልጩህ እባሮቹ በር።"
•
አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(وَيَعْبُدُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنْفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِنْدَ اللَّهِ ۚ قُلْ أَتُنَبِّئُونَ اللَّهَ بِمَا لَا يَعْلَمُ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ ۚ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَىٰ عَمَّا يُشْرِكُونَ)
((ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይገዛሉ፤ እነዚህም አላህ ዘንድ #አማላጆቻችን ናቸው ይላሉ። «አላህን በሰማያትና በምድር ውስጥ የማያውቀው ነገር ኖሮ ትነግሩታላችሁን» በላቸው፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፤ ላቀም፡፡)) ዩኑስ፡ 18
•
"ቀልቤን ወደሳቸው አድርጌ ሰንዘር
አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር።"
•
አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّنْ يَدْعُو مِنْ دُونِ اللَّهِ مَنْ لَا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَنْ دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ)
((ከአላህ ሌላ እስከ ቂያማ ቀን ድረስ መልስ የማይሰጠውን እንደሚጣራ ሰው የጠመመ ማነው እነሱ ከመጠራታቸው የዘነጉ ሆነው ሳለ)) (አልአሕቃፍ፡ 5)
•
"ተሙስጠፋ ይዤ እስተ አቡል በሸር
አንቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር።"
•
አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِنْ كُنْتُمْ صَادِقِينَ)
((እነዚያ ከሱ ሌላ የምትጠሯቸው የናንተው አምሳያ ባሪያዎች ናቸው፡፡ ጥሯቸው እስኪ ይመልሱላችሁ እውነተኞች ከሆናችሁ)) (አዕራፍ፡ 194)
•
"ደሞ አራተኛቸው ዐልዩ ሐይደር
ነበረ ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር
ዒልመል ገይብ ተሱ ይጠየቅ ነበር።"
•
አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(قُلْ لَا يَعْلَمُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ ۚ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ)
(በሰማያትም በምድርም ያለን የሩቅን ምስጢር አላህ እንጂ ማንም አያውቅም፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም በላቸው) (ነምል፡ 65)
•
"በዘበን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር
ቀኝ አጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር።"
•
አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِنْ شِرْكٍ وَمَا لَهُ مِنْهُمْ مِنْ ظَهِيرٍ * وَلَا تَنْفَعُ الشَّفَاعَةُ عِنْدَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ ۚ حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَنْ قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ)
((እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በነሱ ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡)) (ሰበእ: 22-23)
•
"ሺሊላ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር
መቼም አለናንተ ሁሉም አያምር
በናንተ የሸሸ ምነዜም አያፍር።"
•
አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(مَثَلُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِنْ دُونِ اللَّهِ أَوْلِيَاءَ كَمَثَلِ الْعَنْكَبُوتِ اتَّخَذَتْ بَيْتًا ۖ وَإِنَّ أَوْهَنَ الْبُيُوتِ لَبَيْتُ الْعَنْكَبُوتِ ۖ لَوْ كَانُوا يَعْلَمُونَ)
((የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች ሸረሪት ብጤ ነው፡፡ ከቤቶችም ሁሉ በጣም ደካማው የሸረሪት ቤት ነው፡፡ ቢያውቁ ኖሮ (አማልክት አድርገው አይግገዟቸውም ነበር))፡፡ (አል-ዐንከቡት፡ 41)
•
"ጌቶቼ አትለፉኝ አደቤም ባያምር
አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር
ባሪያ ሲባል ማጥፋት እለት ነው እድር
ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር
ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር
በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር።"
•
አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-
(لَهُ دَعْوَةُ الْحَقِّ ۖ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُمْ بِشَيْءٍ إِلَّا كَبَاسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى الْمَاءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَالِغِهِ ۚ وَمَا دُعَاءُ الْكَافِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَالٍ)
((እውነተኛ ጥሪ ለሱ ነው፡፡ እነዚያም ከሱ ሌላ የሚጠሯቸው በምንም ነገር መልስ አይሰጧቸውም፤ ወደ አፉ ይደርስ ዘንድ (ከሩቅ ሆኖ) ወደ ውሃ መዳፎቹን እንደሚዘረጋ ሰው ምሳሌ እንጂ፡፡ ነገር ግን ወደ አፉ ደራሽ አይደለም፡፡ የከሃዲዎችም ጥሪ ከንቱ እንጂ (ሌላ) አይደለም፡፡)) (አል-ረዕድ፡ 14)
•
"ሊለግስ ነው መሰል ዳመናው ዟዟረ
የስልካችሁ ንባብ ይሰማ ጀመረ።"
•
አላህ ግን የኢብራሂምን ንግግር እንዲህ ይተርክልናል፡-
(الَّذِي خَلَقَنِي فَهُوَ يَهْدِينِ * وَالَّذِي هُوَ يُطْعِمُنِي وَيَسْقِينِ * وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ * وَالَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحْيِينِ * وَالَّذِي أَطْمَعُ أَنْ يَغْفِرَ لِي خَطِيئَتِي يَوْمَ الدِّينِ * رَبِّ هَبْ لِي حُكْمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ * وَاجْعَلْ لِي لِسَانَ صِدْقٍ فِي الْآخِرِينَ * وَاجْعَلْنِي مِنْ وَرَثَةِ جَنَّةِ النَّعِيمِ * وَاغْفِرْ لِأَبِي إِنَّهُ كَانَ مِنَ الضَّالِّينَ * وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَ * يَوْمَ لَا يَنْفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ * إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ)
((እርሱ ያ የፈጠረኝ ነው፡፡ እርሱም ይመራኛል፡፡ ያም እርሱ የሚመግበኝና የሚያጠጣኝ ነው፡፡ በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል፡፡ ያም የሚገድለኝ ከዚያም ህያው የሚያደደርገኝ ነው፡፡ ያም በፍርዱ ቀን ወንጀሌን እንዲምርልኝ የምከጅለው ነው፡፡ ጌታዬ ሆይ! ጥበብን አድለኝ፡፡ ከደጋጎቹም አስጠጋኝ፡፡ ከኋለኞቹ ትውልዶችች ዘንድም መልካም ዝናን አድርግልኝ፡፡ ሰቀንም አታዋርደኝ፡፡ ያኔ ገንዘብም ልጆችም የማይጠቅሙበት በሆነው ቀን፡፡ ወደ አላህ በንፁህ ልብ የመጣ ሰው ቢሆን እንጂ፡፡)) (አሽሹዐራእ: 78–89)
በነገራችን ላይ
~
ጁሙዐ ቀን ኹጥባ እየተደረገ ማውራት እንደማይፈቀድ ይታወቃል። ሌላው ቀርቶ ወሬ የያዘን ሰው "ዝም በል" ብሎ ማናገር እንኳ አይገባም። "ታዲያ እንዴት አድርገን ዝም እንዲል እናድርግ?" ከተባለ ያለ ንግግር በእጅ በማመላከት መጠቆም ይቻላል። የምልክት ጥቆማ በኹጥባ ቀርቶ በሶላትም ውስጥ ይፈቀዳል። ኢብኑ ዑመር እና መጅዘአ ብኑ ዛሂር አልአስለሚይ - ረዲየላሁ ዐንሁም - ኹጥባ እየተደረገ በጥቆማ ያመላክቱ እንደነበር ተጨባጭ መረጃ መጥቷል። [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ፡ 3/225] [ሙሶነፍ ኢብኒ አቢ ሸይባህ፡ 2/117]
ኢብኑ ረጀብ አልሐንበሊይ ረሒመሁላህ "በጥቆማ ማመላከት እንደሚቻል በዑለማእ መካከል ልዩነት የለም" ብለዋል። [ፈትሑልባሪይ ፡ 5/496]
=
Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
እኔ የማመልከው የተወለደውን አይደለም
ያልወለደውን ያልተወለደውን "አላህን" እንጂ
✅ የዙልሂጃ አስር ቀናቶች ትሩፋት
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🛑👉በአስሩ የዙልሂጃ ቀናቶች ውስጥ የምትሰግደው ሱና ሶላት በረመዷንም ሆነ በሌላ ጊዜ ከምትሰግደው ሱና ሶላት ይበልጣል።
🛑👉በነዚህ አስር የዙልሂጃ ቀናቶች ውስጥ የምትሰግደው ፈርድ ሶላት በረመዷንም ሆነ በሌላ ጊዜ ከምትሰግደው ፈርድ ሶላት ይበልጣል።
🛑👉በነዚህ ውድ አስር ቀናቶች ውስጥ የምትቀራው ቁርአን በረመዷንም ሆነ በሌላ ጊዜ ከምትቀራው ይበልጣል።
🛑👉በነዚህ ቀናቶች የምትዘክረው ዚክር በረመዷንም ሆነ በሌላ ጊዜ ከምትለው ዚክር ይበልጣል።
🛑👉በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ የምትሰጠው ሶደቃ በየትኛውም ጊዜ ከምትሰጠው ሶደቃ ይበልጣል።
📍ፃም ሲቀር…
〰〰〰〰〰
በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ የምትፃመው ፃም ከረመዳን ፃም ጋር በፍፁም አይስተካከልም። ምክንያቱም ረመዷን መፃም ፈርድ ሲሆን እነዚህን የዙልሂጃ ዘጠኝ ቀን መፃም ግን የተወደደ ተግባር ነው።
አላህ መልካሙን ሁሉ ይወፍቀን።
እሱን በመገዛት ላይ ያግዘን።
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://www.facebook.com/100028494635500/posts/1111905893102555/?mibextid=FG1OuXcoECp1WxxK
Читать полностью…وسئل الشيخ ابن عثيمين عن وضع الرجلين باتجاه القبلة عند النوم فقال :
ليس على الإنسان حرج إذا نام ورجلاه في اتجاه القبلة .
فتاوى الشيخ ابن عثيمين 2/ 976
👉 ጁሙዓን የደስታ ቀን እንጂ የመከራ አናድርገው !!!
የተከበራችሁ ሙስሊሞች የጁሙዓ ቀን የሙስሊሞች ሳምንታዊ ዒድ መሆኑ የሚታውቅ ነው ። በተጨማሪ ሙስሊሞች ተገናኝተው የሚመካከሩበት የሚዘያየሩበት ቀን ነው ። የጁሙዓ ሶላት በሳምንቱ ውስጥ የተሰሩ ቀላል ሀጢያቶች የሚታበሱበት የአላህ ምሕረት የሚወርድበት ትልቅ ዒባዳ ነው ። ለዚህ ነው ሙስሊሞች ከፈጅር ሶላት በኋላ እስከ ጁሙዓ ሶላት ወቅት ድረስ መስጂድ እየገቡ ፍፅም በሆነ እርጋታና ሰላም በተሞላበት አኳኃን ጌታቸውን እያወደሱ ፣ እያጠሩ ፣ እያላቁ ፣ ብቸኝነቱን እየመሰከሩ ፣ ምህረትና እዝነት እየጠየቁ ሶላቱን የሚጠባበቁት ። በዚህ ከጌታቸው ታላቅ ምንዳ እንደሚቸራቸው እርግጠኛ ሆነው የሚቀጥለውን ጁሙዓ በናፍቆት የሚጠባበቁት ።
በዚሁ ቀን ሙስሊሞች ከጁሙዓ ሶላት በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር በደስታ ቀኑን ያሳልፋሉ ። ይህም ለቤተሰብና ለልጆች ቀኑን የበለጠ ተናፋቂ እንዲሆን ያደርገዋል ። እንዲህ አይነቱን የቱርፋትና የምህረት ቀን ከደስታ ቀንነቱ ወደ መከራ ቀን እንዲቀየር ማድረግ ፍፁም አያስፈልግም ። መስጂዶች የአላህ ቤቶች ናቸውና ሊከበሩ ይገባል ። ሌላው እንዲያከብራቸው እኛ በተግባር ልናከብራቸው ግድ ይላል ። አዳባቸውን ጠብቀን ለተሰሩለት አላማ እየተጠቀምንባቸው ልባችን ውስጥ ያላቸው የላቀ ቦታ በተግባራችን ማሳየት ይኖርብናል ።
ውድ ሙስሊሞች በተለያየ ጊዜ በሙስሊሞች ላይ ለሚደርሱ በደሎች የተቃውሞ ድምፅ ማሰሚያ ቦታና ጊዜ መስጂዶችና በተለይ ጁሙዓ ቀን ሆነው እያየን ነው ። ይህ ነገር የእውቀት ባልተቤቶች ትኩረት ሊሰጡትና ሊያዩት ይገባል ። ኢስላም የሰላም ምንጭ የሆነ እምነት እንደመሆኑ ሰላምን የሚያስተምር ለሰለም ከምንም ነገር ቅድሜያ የሚሰጥ መለኮታዊ መመሪያ ያለው እምነት ነው ።
በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን ላይ በመስጂዶችና በሙስሊሞች ላይ ለተፈፀመው በደል መንግስት ከእስልምና ምክር ቤት አመራሮች ጋር ያደረገው ውይይትና መግባባት ላይ መድረስ የዚሁ የእስልምና ትልቅ እሴት የሆነው ሰላም ማሳያ ነው ። በመሆኑም እኛ ሙስሊሞች መስጂዶቻችንንና ተናፋቂው የጁሙዓ ቀናችንን ከደስታ ቀንነት አውጥተው የመከራ ሊያደርጉት የሚፈልጉ አካላትን በማሳፈር የተደረሰበትን የሰላም ስምምነት ተቀብለን ለተግባራዊነቱ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል ። ከምንም በላይ ወደ አላህ በመመለስ ከሱ ዘላቂ ሰላምና ፍትሕ መጠየቅ ይኖርብናል ። እኛ ሙስሊሞች ለሰላም ያለንን ቦታ በነገው ጁሙዓ ለማሳየት ሁላችንም እንነይት ። አላህ ይርዳን ።
/channel/bahruteka
ۖ وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا لَا يَضُرُّكُمْ كَيْدُهُمْ شَيْئًا ۗ إِنَّ اللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطٌ
ብትታገሱና ብትጠነቀቁም ተንኮላቸው ምንም አይጎዳችሁም፡፡ አላህ በሚሠሩት ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነውና፡፡(3:220)
በደማው ልባችን እንደዚ መልካም ዜናዋችን መስማት ደስ!! ዛሬ እሁድ ግንቦት 27/2015 ወደ ምዕራብ ኢትዮጵያ በተደረገ በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ቃፊላ የዳዕዋ ጉዞ 500 ሰዎች እስልምናን ተቀብለዋል ፤ ነሲሓ ቲቪ ላይ በጥዑም ዳዕዋዎቹ በምናውቀው በተወዳጁ ኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ እጅ ኢስላምን ተቀብለዋል። አላህ ፅናትና ጥንካሬን እንዲለግሳቸው እንለምነዋለን።
አል- ሐምዱሊላህ! አላሁ አክበር።
አማኞች ስትኖር ቀለል አደርገህ ኑር ይላሉ። አገራችንም አፋሮች እንዲሁ ናቸው። ወደ ሸዋም
የሚኖሩ ኦርቶዶክሶችን እሳርቤት ውስጥ እየኖሩ ፈጣሪ ምን አሳጥቶን ነው ተመስገን ጌታየ እያሉ ሲኖሩ አይቻለሁ። በወሎም አልሀምዱሊላህ ምንኛ የታደለ መሰለህ በሰላም ወቶ የገባ ሰው ይላሉ። ፍቅር መተሳሰብ በድህነት ውስጥ አለች። ሀብት ሆድና ዝና ሀጢያት (ወንጀልን) ታበዛለች ይላሉ።
አረቦች ደሞ እየራባቸው አልሀምዱሊላህ ይላሉ። በሰለጠነው አለም የኤምሬትስ ገዥዎችን የመሰለ መሪ ብዙም የለም። ሀብታቸውን ለዜጎቻቸው ምቹ አድርገውበታል። ጥበብን በህንፃ ቀርፀው የአለም ቱሪስት መዳረሻ አደርገውታል። ታዲያ ይህንን ሳይ የሰው ልጅ ልህቅና በኤምሬት ልጆች ላይ ሲተገበሩት አይቻለሁ። 100°/° ሙስሊም ናቸው። ኢትዮዽያዊያን የክርስትና እምነት ተከታዮች መሬት ስጡንና ማምለኪያ ቤተ እምነት እንስራ ሲሏቸው አልከለከሉም። ሰርተው በክብር መሪዎቻችንን ተቀብለው ነው ቁልፉን ያስረከቡት።
መሰልጠን እንዲህ ነው። ለምን የጆቢራ ገደሉ ዋሻ ፈጣሪየ ነው አትልም አያገባቸውም። ብቻ ሰው ሁን። ብቻ እጅህ ከደምና ከወንጀል ንፁህ ይሁን። ብሄርህን አይጠይቁህም። እምነትህን አያገባቸውም። ከየት መጣህ አይሉህም።
እድለኞቹ ግን እኛ አገራችን ላይ ሰርተን መብላት አልቻልንም። አገሬ ነው ብለን መንቀሳቀስ አልቻልንም። አገሬ ነው ብለን ከተወለድንበት እርቀን ቤት መቀለስ አልቻልንም። ቤታችን መታወቂያችን ስማችን የመኪና ሰሌዳችን ሁሉ የሞት መቆፈሪያችን ተደርጎ ተሰቶናል። 11 ሰንደቅ አላማ አሲዘው ያማምሉናል። ይህንን ሰተው እየገዙን አትግደሉን ከግደሉን በላይ ወንጀል ሆኗል። መማር ማወቅ መሰልጠን ማስተዳደር የት እንዳለ ለኛ ገና ህልማችን ነው። ብቻ ሁሌም መሳቂያ ሆነን እንድንኖር ፈርደውብናል።
ለነ ሽመልስ አብዲሳ እንዲህ ስትናገራቸው የገደልካቸው ይመስላቸዋል። የአረብና የአይሁድ ስም ማንነታችንን አጠፋብን ይሉሀል። አይሁድና አረብ እደረሰበት ለመድረስ ግን ገና አምስት ትውልድ ይጠይቃል። ሁሉም ነገራችን እጅግ የቆሸሸ ከሰውም ከእምነትም የተጣረሰ ነው። ሀቁ ይህ ሆኖ ህብረ ብሄራዊት አገር እየመሰረትን ነው ይሉሀል። አንድ ከተማ ለመመስረት ግን አንድመቶ 17ሺ ዜጎችን በብሄር ለይተው አፈናቅለው ለብርድና ለረሀብ ለጥም አስረክበዋል። ቤተ ክርስቲያንና መስጊድ ሲያፈርሱ አይጨነቁም። እንደውም ጀብደኝነት ነው ለነሱ።
መደመር ምን እንደሁ የጆቢራ ገደሉ እብድ ይወቀው።
ሱሌማን አብደላ
https://www.facebook.com/100016829829342/posts/1396082067629441/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v
Читать полностью…⤴️ በተላያየ ነገር ልባችሁ ጭንቅ ጥብብ ላለባችሁ ምርጥና ጣፋጭ የሆነውን የአለህን ቃል ጋበዝኳቹ
ይደመጥ ይደመጥ አደራ
‟ለአሕባሾች፣ለሱፍዮች፣ለአሽዓሪዮች... አላህ ከዐርሽ የበላይ መሆኑን ለሚያስተባል ሁሉ ይድረሰው!”
Читать полностью…