gfyygy | Unsorted

Telegram-канал gfyygy - አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

883

ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot

Subscribe to a channel

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

(በ 561 ዓ.ሂ የሞቱት) ሸይኽ ዐብዱል-ቃዲር ጂላኒ (ረሒመሁሏህ) ስለ ዑሉው፣ኢስቲዋ፣ ኑዙል...ስለ ጀህሚየህ፣ሙዕተዚለህ እና አሽ'ዓሪዎችን አስመልክተው ምን አሉ?!

ሸይኽ ዐብዱል-ቃዲር ጂላኒ (ረሒመሁሏህ) «ጉንየቱ ጧሊቢን»፣ (1/73)] ላይ እንዳህ ይላሉ፦

❝...አላህ ከዐርሽ በላይ ነው ያለው!፤ ዕውቀቱ ግን በሁሉም ነገራቶች ላይ ያካተተና ያካበበ ነው!።❞

📚[ጉንየትቱ ጧሊቢን፣ (1/73)]

አሁንም ሸይኽ ዐብዱል-ቃዲር ጂላኒ (ረሒመሁሏህ) በዚሁ ኪታብ ላይ (ገንየቱ ጧሊቢን) ላይ እንዲህ ይሉናል፦

ኢስቲዋ ( አላህ ከዐርሽ በላይ በዛቱ  መሆኑን) ያለ ተዕዊል (ያለ ማንሻፈፍ) ማመንና ማረጋገጥ ይገባል። ኢስቲዋ ሲባል ደግሞ፣ ሙጀሲማዎችና ከራሚያዎች እንደሚሉት፣አላህ ከዐርሹ ላይ ተቀምጧል ወይንም ተነካክቷል ብለው እንደሚሉት አይደለም!፤እንደዚሁም  አሽዓሪያዎች ከዐርሽ የበላይ አይደለም እንደሚሉት፣ ሙዕተዚላዎች  ተቆጣጥሯል (አሽንፏል)  ብለው እንደሚሉት አይደለም...እንደዚህ አይነት አባባሎች ደግሞ በሸሪዓ የመጣ ነገር የለም፣ ከሶሃቦችም፣ከታብዕይዮችም፣ከሰለፉነ ሷሊህ፣ከሐዲስ ባለቤቶችም...አንዲትም ነቅል (ማስረጃ) የለም፣ይልቁንም ኢስቲዋ የመጣው አላህ ከዐርሽ በላይ መሆኑንና ሁኔታው ሳይገለፅ ነው።❞

📚 [ጉንየቱ ጧሊቢን፣(1/73)]

አሁንም በድጋሜ ሸይኽ ዐብዱል ቃዲር ጂላኒ (ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ፦

❝... ከፍ ያለው ጌታችን አላህ፣በሁሉም ሌሊቶች ወደ ቅርቢቷ ሰማይ እንደፈለገና በፈለገው ሁኔታ ይወርዳል። ወንጀልን ለሰሩት፣ለተሳሳቱት፣ለአመፁት... ባሪያዎቹ ለፈለገው ይምራል። ከአላህ ወጭ በሐቅ (በእውነት) የሚመለክ አምላክ የለም!። እሱ (አላህ) ያማሩና የተዋቡ ስሞች አሉት። ኑዙል (መወረድ) ሲባል ደግሞ፣ ሙዕተዚላዎችና አሽዓሪያዎች... አዝነቱ ወይም ሰዋብ (አጅር) ማለት አይደለም። አላህ በዛቱ በሚያምርበት ሁኔታ ይወርዳል።

📚 [ጉንየቱ ጧሊቢን፣(1/74)]

መጣጥፍ (➊ን) ለማግኘት👇
/channel/semirEnglish/1076

መጣጥፍ (❷ን) ለማግኘት👇
/channel/semirEnglish/1097

መጣጥፍ (➌ን) ለማግኘት 👇
/channel/semirEnglish/1099

መጣጥፍ (➍ን) ለማግኘት 👇
/channel/semirEnglish/1302

📝 እንግሊዛዊው ሸይኽ አቡ ዒያድ (ሀፊዘሁሏህ)

አማርኛ ትርጉም፦ አቡ ሐፍሳህ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🟢 ቲቪ ከቤት ይውጣ

♨️እንደ ልብ ካንሰር

♨️የወንጀሎች መዳረሻ




🟢የፈትዋ ቁጥር 1⃣7⃣8⃣




መልስ
🔊አሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሳሊህ አልኡሰይሚን


በዚህ የፈታዋ ብቻ ቻናል⤵️
/channel/FATTAWAS


የፈትዋ ጥያቄ ለመጠየቅ⤵️
https://forms.gle/1iDs6V7JPMHREx4GA

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

እናንተ የሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሂዝቦች ሆይ! ከናንተ ዘንድ አንድ ወንድማችሁ ገንዘብ ዎስዶባችሁ ወይም ሰድቦዋችሁ ሞቶ ሊሆን ይችላል ለአላህ ብላችሁ ከልባችሁ አፉ በሉት።

አላህ ይቅር ባይ ።ይቅር ባዮችን ደሞ ይወዳል።እናንተ የሙሐመድ ሂዝቦች ሆይ! በየትኛውም በኩል  በስድብ ፣ገንዘብ በመውሰድ ፣ስም በማጥፋት፣ ወዘተ የበደሏቹሁን  ሰዎች  ቢሞቱም በሂይወት ቢኖሩም ወይ አገር ቢቀይሩ  ለአላህ ብላችሁ ከልብ አፉ በሏቸው ።እኛን አላህ ስንት ወንጀላችንን ሸፍኖልን ከስንት መከራ ገላግሎት አላህ በፉርዱ ቀንም ይቅር ባዮችን ይወዳልና እንዲዮደን ይቅር ማለት እናብዛ ።

አንዱ በድሎክ  "ይቅር በለኝ"ለማለት እድል ሳያገኝ ሞቶ ወይም አገር ቀይሮ ሊሆን ይችላል አስታውሰህ አፉ በለው ።አላህ አፉ ባዮችን ይወዳልና!

አንዱ በድሎካል ግን "አፉ በለኝ" እንዳይልህ አላህ ዘንድ በፍርዱ ቀን ያለውን ከባድ የሂሳብ ቀን ከልቡ አልተረዳውምና! አንተ አስታውሰህ አፉ በለው ።አላህ አንተንም በሱ ሰበብ ይቅር ይልህ ይሆናል።

ጌታዬ አላህ ሆይ!እኔ ሙስሊም ሆኖ ማንም በኔ ምክንያት አንተ ፊት ከመጠየቁ በፊት ከልቤ አፉ ብዬዋለሁኝ መስክርልኝ ያረብ!የሞቱትንም በሂይወት ያሉትንም!!

ያረብ መንገድህን ምራን አጅራችንን አብዛልን በትንሳኤው ቀንም ከማይዋረዱት ፊታቸው ከሚያበሩት አድርገን ኣሚን ወሰላሙ አለይኩም ወረሕመቱሏ


/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

እስኪ ተብሊጎችን እንይ የአህባሽ አጎት
ከተብሊጎች ግርም ከሚለኝ ነገር ኹሩጅ የወጣው ሁሉ ተረኛ
እየሆነ ሲናገር በአንድ አይነት ነገር መጀመራቸው ነው፡፡ “እና
ምን ችግር አለው ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በኹጥበተል
ሐጃ እንዲጀመር አስተምረው የለ?” እንዳይባል፡ ፡በሱ
ቢጀምሩማ እንዴት በታደል ነው?! እንዳውም
የነብዩሰለላሁዐለይሂወሰለም ኹጥባ መክፈቻ ውስጥ ያለውን
“መጤ ነገር ሁሉ ቢድዐ ነው፡፡ ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው፡፡ጥመት
ሁሉ ወደ እሳት ነው” የሚለውን ሲሰሙ ውስጣቸው የሚጓሸው
ቀላል አይደሉም፡፡ ልክ የኛ ንግግር የሆነ ይመስል፡፡ አንዱ ይነሳና
“ኢንሻ አላህ የዒሻ ሶላትን በጀማዓ አሰጋገደን ልናመሰግነው
ይገባል ኢንሻአላህ ካመሰገናችሁኝ እጨምራችኋለሁ ከካዳችሁ
ግን ኢንሻአላህ አያያዜ የበረታ ነው ይላል ኢንሻአላህ፡፡ ስለዚህ
አልሐመድሊላህ ማለት አለብን፡፡ ” ከዚያበጀማዓ
“አልሐምዱሊላህ” ይላሉ፡፡ “ኢንሻአላህ አዛን የተደረገው
ለሁሉም ሰው ነበር፡፡ የመጣነው ግን እኛ ብቻ ነን፡፡ እኛ ብልጥ
ስለሆን አይደለም ኢንሻአላህ፡፡ እኛ ጀሃነምን ስለፈራን ጀነትን
ስለፈለግን አይደለም የመጣነው ኢንሻአላህ፡፡ አላህ መርጦን
ነው በተውፊቁ ነው ያመጣን ኢንሻአላህ፡፡” “እሳት ለማቃጠል
የአላህ ፍቃድ ያስፈልገዋል ኢንሻአላህ፤ ቢላዋ ለመቁረጥ ኢንሻ
አላህ የአላህ ፍቃድ ያስፈልገዋል፡፡” ይቀጥላሉ፡፡ “ኢንሻ አላህ
ወንድሞቼ ሰማዩን የፈጠረው አላህ ነው ኢንሻ አላህ
ተራራውንም ባህሩንም መሬቱንም የፈጠረው ኢንሻአላህ አላህ
ነው፡፡ የሚረዝቀን አላህ ነው ኢንሻአላህ፡፡” በዚህ አይነት ቋንቋ
ሰርክ ሲደጋግሙ አስቡት፡፡ አስርም ፣ መግሪብም ፣ ዒሻም ላይ
የተነሳው ያለምንም መሰልቸት እንዲሁ ይላል፡፡ ሱብሐነላህ!!!
አንዳንዶቹ “ይህን የሰጠን አላህ ይህን የሰጠን አላህ ” እያሉ
አይናቸውን ፣አፍንጫቸውን … ተመስጠው ይነካካሉ፡፡ እስኪ አሁን
ይሄ ማስተማር ነው ማስተኛት? ሸይኽ ሙቅቢል አላህ
ይማራቸውና የነኚህን ሰዎች ደዕዋ “የሞተ ደዕዋ ነው” ይላሉ፡፡
እንጂ ማ ይህንን እውነታ እነ አቡ ጀህልስ መቼ ዘነጉት? ይሄው
እኮ ቁርኣን እየተናገረ!!!
((“ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማነው?
መስሚያዎችንና መመልከቻዎችን የሚቆጣጠረው ማነው?
ህያውን ከሙት ሙቱን ከህያው የሚያወጣውስ? ነገርን ሁሉ
የሚያስተናብረውስ ማነው?” በላቸው፡፡ “አላህነው” ይሉሃል፡፡
“ታዲያ (ለምንታጋራላችሁ) እሱን አትፈሩትምን ?” በላቸው፡፡))
(ዩኑስ፤ 31)
((ማን እንደፈጠራቸው ብትጠይቃቸው በርግጥም “ አላህነው ”
ይሉሃል፡፡)) (አዝዙኽሩፍ፡ 87)
(( “ሰማያትንና ምድርንም ማን ፈጠራቸው?” ብለህ
ብትጠይቃቸው “አሸናፊው ጥበበኛው (አላህ) በርግጥም
ፈጠራቸው” ይላሉ፡፡)) (አዝዙኽሩፍ፡ 9)
ወንድሜ ሆይ! ከእንዲህ አይነት የቢድዐ አካሄድ እራስህን አርቅ፡፡ ያለበለዚያ በዲንህም በዐቅልህም ላይ ስትቀልድ ነው
የምትኖረው፡፡

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን ሙሃደራዎች
〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰


🎙በአማረኛ ቋንቋ የተደረጉ ሙሀደራዎች

     ↷⇣🎙⇣↶
t.me/MuhaderahChannel/7
t.me/MuhaderahChannel/7
          ↷⇣🎙⇣↶
t.me/MuhaderahChannel/335
t.me/MuhaderahChannel/335
     ↷⇣🎙⇣↶
t.me/MuhaderahChannel/488
t.me/MuhaderahChannel/488

🎙በትግርኛ ቋንቋ የተደረጉ ሙሀደራዎች

     ↷⇣🎙⇣↶
t.me/MuhaderahChannel/512
t.me/MuhaderahChannel/512

     ↷⇣🎙⇣↶
t.me/MuhaderahChannel/539
t.me/MuhaderahChannel/539
     ↷⇣🎙⇣↶
t.me/MuhaderahChannel/569
t.me/MuhaderahChannel/569

ለናሙና ያክል የተዉጣጡ በዉስጡ የተለያዩ ሙሃደራዎችን ያገኛሉ!!⇧⇧⇧

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🟢ሱረህ መርየም

👉 አላህ ለጀግና ወልዮቹ አዛኝ ነው
👉 ለመረጠው ሳሊህ ልጅ ይሰጣል
👉አላህ ከክርስቲያኖች ቅጥፈት ሁሉ የጠራ ነው።
👉 ትልቁ ስኬትና ከባዱ ክስረት
👉👉👉👉👉👉


{إِنَّ هَٰذَا الْقُرْآنَ يَهْدِي لِلَّتِي هِيَ أَقْوَمُ وَيُبَشِّرُ الْمُؤْمِنِينَ الَّذِينَ يَعْمَلُونَ الصَّالِحَاتِ أَنَّ لَهُمْ أَجْرًا كَبِيرًا}

《ይህ ቁርኣን እኮ ለዚያች እርሷ ቀጥተኛ ለሆነችው መንገድ ይመራል》

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ልብ በሉ! እንዲህ የሚንደፋደፉት ለጀይላኒይ ያላቸው የተጋነነ ቦታ እና የጀይላኒይ ብርቱ ፀረ አሽዐሪያ አቋም አልጣጣም ብሎ ስላስቸገራቸው ነው። ከቅርቃሩ መውጫ መንገድ እውነቱን መቀበል ብቻ ነበር። ግን በራሱ ላይ ቆልፎ ስለ ተቀመጠ አካል ምን ማለት ይቻላል?!
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 16/1444 (ሚያዚያ 28/2015))
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የወጣትነት ሁለት ገፆች
~
ወጣትነት ፀጋ ነው። ለስራም ሆነ ለእውቀት ከየትኛውም የእድሜ ክልል በተለየ መነሳሳት የሚኖርበት ምቹ ጊዜ ነው። ወጣትነት በባህልም ይሁን በእምነት የመጡ ብልሹ ውርሶችን ለማራገፍ፣ የተዛነፉ ትርክቶችን ለማቃናት የተሻለ ድፍረትና ወኔ የሚገኝበት እድሜ ነው። ወጣቶች በኢስላም ታሪክ በተለያዩ የአለም አፅናፋት የእውቀትን ችቦ የለኮሱ የእውቀት ቀንዲሎች፣ የጥጋበኞችን እብሪት ያስተነፈሱ የነብር ጣቶች፣ በተለያዩ ዘርፎች ላይ አለምን በመልካም ያነቃነቁ የለውጥ ሞተሮች፣ ታሪክ በደማቅ ብእር ያወሳቸው አሻራቸውን ለትውልድ ያሻገሩበት የእድሜ ክልል ነው። ወጣትነት ሌሎችም በዋጋ የማይተመኑ በርካታ ውድ ፀጋዎች አሉት።

በሌላ በኩል ወጣትነት በጥንቃቄ ካልያዙት ራስን፣ አልፎ ሌሎችንም የሚበላ እሳት ሊሆን ይችላል። በወጣትነት ውስጥ በእድሜና በተሞክሮ የሚገኝ ልምድ የለም። የእውቀት ማጠር ይጠበቃል። መንቀዝቀዥ ወይም የስክነት መቅለል፣ ጥሬነት ወይም የብስለት ማነስ፣ በተለያየ ዘርፍ ጤነኛ ያልሆነ ወሰን ያለፈ ድፍረት ወይም ጀብደኝነት፣ ራስን አለማሸነፍ፣ አደጋ ላይ የሚጥል ጉጉት፣ ስሜታዊነት፣ ... ይጎላበታል፣ ወጣትነት። በወጣቶች የተቀሰቀሱ ወይም ወጣቶች ፊታውራሪ የሆኑባቸው ዳፋቸው ሺህ አመታትን አቋርጦ ለዛሬም የተረፉ ብዙ ፈተናዎች ደርሰዋል። በወጣቶች ታላላቅ ኸሊፋዎችና በጀነት የተመሰከረላቸው እንቁዎች ህይወታቸው ተቀጥፏል። እልፍ አእላፍ የኡማው ብርቅየ ፍሬዎች አልቀዋል። ሃገራት ፈርሰዋል። የዑሥማን ግ.ድ. ያ ፣ የኸ.ዋ.ሪ.ጅ ንቅናቄ፣ የዘመናችን የተ^ ክ^ ፊ^ ር ጥንስስና መስፋፋት፣ ... ላይ የጉርምስና ግለት ድርሻው ከባድ ነበር። ሌላው ቀርቶ የዑሥማኒያ (የኦቶማን ተርክ) አገዛዝ ራሱ በከማል አታቱርክ ኦፊሻሊ መፍረሱ ከመታወጁ በፊት አውሮፓ ተምረው በመጡ ወጣቶች ሴራ ቀድሞውኑ ጣእረ ሞት ላይ ደርሶ ነበር። እነዚህ ጥራዝ ነጠቅ ወጣቶች "ኸሊፋዎቹን" በራሳቸው እስከመቀየር፣ ጥርስ የሌለው ውሻ አድርገው እስከ ማንገላታት ደርሰው ነበር። ብዙ ሰው ይህንን እውነታ አያውቅም። ስለ ኦቶማን ተርክ አገዛዝ የሚያወራው ቡድናዊ አላማ ያነገቡ አካላት የሚያቀርቡትን የሂደቱን የመጨረሻ ክፍል ብቻ ነው፣ ያውም በተዛነፈ መልኩ።

ይህንን ማወቃችን በወጣትነት የሚገኘውን ኸይር በወጣትነት ዘመን የሚመጡ ሸሮች እንዳያጠፉት ለመጠንቀቅ ይረዳል። ዑመር ብኑል ኸጧብ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ለአንዱ ወጣት እንዲህ ይሉታል፦
«قد يكون في الرجل عشرة أخلاق، تسعة منهن حسنة وواحدة سيئة، فتفسد الواحدة التسع، فاتَّقِ طيرات الشباب».
"በአንድ ሰው አስር የስነ ምግባር ቀንዘሎች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ዘጠኝ መልካምና አንድ መጥፎ። ያቺ አንዷ ቀንዘል ዘጠኞቹን ልታጠፋ ትችላለችና የወጣት ጥሬነቶችን ተጠንቀቅ።" [ሸርሑል ዑምደህ፣ 5/22]

=
( Ibnu Munewor ፣ ሸዋል 16/1444 (ሚያዚያ 28/2015))
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

الفتوي الحموية -١

አል-ፈትዋ አልሀመዊያ -1

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ቁራ የሰውን ልጅ ማስተማሩን ቀጥሏል
~
ግ -ድ -ያን ምድር ላይ ለጀመረው የአደም ልጅ የሟች ወንድሙን አስከሬን እንዲቀብር ያስተማረው ቁራ ነበር። አላህ ታሪኩን እንዲህ ገልፆቷል:-
{ فَبَعَثَ ٱللَّهُ غُرَابࣰا یَبۡحَثُ فِی ٱلۡأَرۡضِ لِیُرِیَهُۥ كَیۡفَ یُوَ ٰ⁠رِی سَوۡءَةَ أَخِیهِۚ قَالَ یَـٰوَیۡلَتَىٰۤ أَعَجَزۡتُ أَنۡ أَكُونَ مِثۡلَ هَـٰذَا ٱلۡغُرَابِ فَأُوَ ٰ⁠رِیَ سَوۡءَةَ أَخِیۖ فَأَصۡبَحَ مِنَ ٱلنَّـٰدِمِینَ }
"የወንድሙንም ሬሳ እንዴት እንደሚደብቅ ያሳየው ዘንድ አላህ መሬትን የሚጭር ቁራን ላከለት፡፡ 'ወይኔ! የወንድሜን ሬሳ እደብቅ ዘንድ እንደዚህ ቁራ ብጤ መሆን አቃተኝን' አለ፡፡ ከፀፀተኞችም ሆነ።" [አልማኢዳህ፡ 31]

ይህንን ሳስብ "የቁራ መልእክተኛ" የሚለው ቁራን ዝቅ የሚያደርገው አማርኛ ብሂል ኮሰኮሰኝ። ቁራኮ በታሪክ በደለኛውን የኣደምን ልጅ የቀብር ስርአት ሊያስተምር ከአላህ ተልኮ የነበረ ነው።
ለማንኛውም ቁራ ይህንን የሰውን ልጅ ማስተማሩን የቀጠለ ይመስላል። ግን በሌላ ዘርፍ። ያያያዝኳቸው ቪዲዮዎች ለዚህ ምስክር ይሆናሉ። በመጀመሪያው ቪዲዮ ላይ ቁራው የግፈኛዋን ሃገር የእስራኤልን ሰንደቅ አውርዶ ሲጥል ይታያል። ክስተቱ ማህበራዊ መገናኛዎች ላይ ሰፊ መነጋገሪያ ሆኗል። ሌሎቹ ቪዲዮዎች ደግሞ በተለያዩ ጊዜያት የተቀረፁ ይህንኑ የግፍ አርማ እየቦጫጨቁ የሚጥሉ ቁራዎች ናቸው የሚታዩት። ነገሩ እንዴት ነው?

ቁራ ሰብአዊነት የለውምi
ቁራ አሸባሪ ነውi
ቁራ ፀረ ሴማዊ (anti semitic) ነውi
ህህ
እነሱኮ አይሉም አይባልም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አንድ እውነት በአሕ ^ባሽ ስብከት ለተሸወዳችሁ ሁሉ
~
ቀደምት የአሽዐሪያ መሪዎች የአላህን ከፍጡራን በላይ መሆን ያምኑ ነበር። "አላህ ከዐርሹ በላይ ነው" የሚሉ ሰዎችን ከኢስላም በማስወጣት ለሚታወቁት አሕ - ባሾች ይህንን መቀበል ከባድ ነው። መረጃው ይሄውና፡-

1. ኢብኑ ኩላብ (240 ሂ.)፡-

አሽዐሪዮች ዘንድ የተከበረ “የኛ” የሚሉት ሸይኽ ነው። የዛሬ አሽዐሪዮች ከዚህ ሰውየ የቀዱት መሰረታዊ ዐቂዳ ስላላቸው እውነተኛው የአሽዐሪያ መዝሀብ መስራች ኢብኑ ኩላብ ነው እስከሚባል ተደርሷል። አሽዐርዮቹ አቡ መንሱር አልበግዳዲይና ሸህረስታኒም ሸይኻቸው እንደሆነ መስክረዋል። [ኡሱሉዲን፣ በግዳዲይ፡ 104] [ኒሃየቱል ኢቅዳም፡ 303] ባጭሩ ከመሆኑም ጋር በያዝነው ጉዳይ ላይ ያለው ዐቂዳ ግን ከነሱ የተለየ ነው። ይሄውና ቃሉ፡-
ولو لم يشهد لصحة مذهب الجماعة في هذا الفن خاصة إلا ماذكرنا من هذه الأمور لكان فيه ما يكفي، كيف وقد غرس في بنيه الفطرة ومعارف الآدميين من ذلك مالا شيء أبين منه ولا أوكد؟ لأنك لا تسأل أحدا من الناس عنه، عربيا ولا عجميا، ولا مؤمنا ولا كافرا فتقول: أين ربك؟ إلا قال: في السماء إن أفصح، أو أومأ بيده أو أشار بطرفه إن كان لا يفصح
“ለ(አህሉ ሱና) ወልጀማዐ መዝሀብ ትክክለኝነት በዚህ ዘርፍ ላይ የጠቀስናቸው ነገሮች እንጂ ሌላ ምስክር ባይኖር እንኳ በዚህ ውስጥ የሚበቃ ነገር አለ። በንፁህ ተፈጥሮና በሰው ዘር እዝነ ልቦና ላይ የተተከለ ነገር እንዴትስ ብሩህና የፀና አይሆን? ምክንያቱም ዐረብም ይሁን ሌላው አማኝም ይሁን ከሃዲ ማንንም ሰው ‘ጌታህ የት ነው?’ ብለህ ስለሱ አትጠይቅም መግለፅ ከቻለ ‘በሰማይ’ የሚልህ፣ መግለፅ ካልቻለ በእጁ ወይም በአይኑ የሚያመላክትህ ቢሆን እንጂ።” [ደርእ፡ 6/194] [አልጁዩሽ፡ 1/435]

"የተጠቀምካቸው ምንጮች የኢብኑ ተይሚያ ኪታቦች ናቸው" የሚል ተቃውሞ የሚያነሳ ካለ ኢብኑ ኩላብ የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን በሚገባ ያፀድቅ እንደነበር አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይና አቡ መንሱር አልበግዳዲይም አረጋግጠዋል። [መቃላቱል ኢስላሚዪን፡ 299] [ኡሱሉዲን፡ 113]

ኢብኑ ኩላብ ዛሬ አሕባሾች የሚያራምዱትን አቋም እንዲህ ሲል ኮንኖታል፡-
“ከአእምሯዊ ምልከታም ከቁርኣንና ሐዲሥም የመጨረሻ ያፈነገጠው ደግሞ ‘አለም ውስጥም አይደለም፣ ከሱ ውጭም አይደለም’ በማለት እኩል ያራቆተው ነው። ምክንያቱም ‘እስኪ ባለመኖር ግለፀው’ ቢባል ከዚህ በበዛ ስለሱ ምንም ሊል አይችልምና። ቀጥተኛ የሆኑ የአላህን ዘገባዎች ነው የመለሰው። ከማስረጃም ከአመክንዮም አንፃር የማይሆን ነገር ነው በዚህ ላይ የተናገረው። የጠራው ተውሒድ ይሄ እደሆነ ሞግቷል። ጥርት ያለው ማራቆት እነሱ ዘንድ ጥርት ያለው ማፅደቅ ሆኗል።” [ደርእ፡ 6/119] [በያኑ ተልቢሲል ጀህሚያ፡ 1/44]

2. ሓሪሥ አልሙሓሲቢይ (243 ሂ.)፡-

አሽዐሪዮች እንደ ሸይኻቸው የሚወስዱት ነው። [ኡሱሉዲን፡ 208-209] የአላህን ከፍጡራን በላይ መሆን በሚገባ ያፀድቃል። ለምሳሌ ይህን የሚያመላክቱ ማስረጃዎችን ከዘረዘረ በኋላ እንዲህ ብሏል፡-
فهذا مَقْطَعٌ يوجبُ أنَّهُ فوقَ العرشِ، فوقَ الأشياءِ، منزَّهٌ عَنِ الدُّخولِ في خلقهِ، لا يخفى عليهِ منهم خافية، لأنَّهُ أبانَ في هذهِ الآياتِ أنَّ ذاتَهُ بنفسهِ فوقَ عبادهِ
“ይሄ እርሱ ከዐርሹ በላይ፣ ከነገሮች በላይ እንደሆነ በፍጡሮቹ ውስጥ ከመግባት የጠራ እንደሆነና ከነሱ የትኛዋም ስውር ነገር እንደማትሰወረው የሚያስረግጥ ክፍል ነው። ምክንያቱም በነዚህ አንቀፆች ውስጥ እሱ ዛቱ በራሱ ከባሮቹ በላይ እንደሆነ ግልፅ አድርጓልና። …” ቀጥሎም ማስረጃዎችንና ዘለግ ያሉ ትንታኔዎችን ይሰጣል። [ፈህሙል ቁርኣን፡ 349 - 352]
በሌላ ቦታም ስለ ቁርኣን ሲያወራ እንዲህ ብሏል፡-
وَقد تكلم بِهِ بِنَفسِهِ من فَوق عَرْشه وأنزله مَعَ الْأمين من ملايكته إِلَى أَمِين أهل الأَرْض
“በርግጥም በሱ (በቁርኣኑ) ከዐርሹ በላይ ሲሆን በራሱ ተናግሯል። ከመላእክት ውስጥ ከታማኙ (ጂብሪል) ጋር ከምድራውያን ውስጥ ታማኝ ወደሆነው (ሙሐመድ) አውርዶታል።” [ፈህሙል ቁርኣን፡ 309]

3. አቡል ዐባስ አልቀላንሲይ፡-

ከአቡል ሐሰን አልአሽዐሪይ ጋር አንድ ዘመን ከመሆኑ በስተቀር የውልደቱም የህልፈቱም አመት በውል አይታወቅም። ከአሽዐሪያ ኢማሞች እንደሆነ ግን እራሳቸው መስክረዋል። [ኡሱሉዲን፡ 310]
አቡ መንሱር አልበግዳዲይ በኢስቲዋእ ዙሪያ አሽዐሪዮች ያንፀባረቋቸውን የተለያዩ ሀሳቦች ሲዘረዝር እንዲህ ብሏል፡-
ومنهم من قال: إن استواءه على العرش كونه فوق العرش بلا مماسة، وهذا قول القلانسي وعبد الله بن سعيد
“ከነሱም ውስጥ ‘ኢስቲዋኡ ያለ መነካካት ከዐርሹ በላይ መሆኑ ነው’ ያለ አለ። ይህ #የቀላንሲይ እና የዐብደላህ ብኑ ሰዒድ (ኢብኑ ኩላብ) አቋም ነው።” [ኡሱሉዲን፡ 113]
ከኢብኑ ዐሳኪርም እንዲህ የሚል ማረጋገጫ እናገኛለን፡-
وَهُوَ من جملَة الْعلمَاء الْكِبَار الْأَثْبَات واعتقاده مُوَافق لاعْتِقَاده فِي الْإِثْبَات
“እርሱ (ቀላንሲይ) ከታላላቅና ታማኝ ዑለማዎች ውስጥ ሲሆን እምነቱም ከሱ (ከአቡል ሐሰን) የማፅደቅ እምነት ጋር ተመሳሳይ ነው።“ [ተብዪን፡ 398]
ኢብኑ በዚዛም (662 ሂ.) እንዲህ ብሏል፡- “ከአሽዐሪያ መሻይኽ ውስጥ የሆነው አልቀላንሲይ በሸሪዐ የተዘገቡ ጉልህ ማስረጃዎችን በመንተራስ ‘የላቀው አላህ በሁሉም ቦታ ሳይሆን በአንድ ቦታ ነው፤ እርሱ በሰማይ ነው’ ወደሚል አቋም ተጉዟል።” [አልኢስዓድ ፊ ሸርሒል ኢርሻድ፣ ኢብኑ በዚዛ፡ 225]

4. አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይ (324 ሂ.)፡-

አህሉ ሱና “የላቀው አላህ በምድሩ ሳይሆን ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ እንደሆነም ኢጅማዕ አድርገዋል። ... የኢስቲዋኡ ፍቺ ቀደሪያዎች (ሙዕተዚላዎች) እንደሚሉት መቆጣጠር ማለት አይደለም” ብሏል። [ሪሳላ ኢላ አህሊ ሠግር፡ 130-131]
ስለ አቡል ሐሰን ዐቂዳ ዝርዝር የፈለገ ከዚህ በፊት የፃፍኩትን በዚህ ሊንክ ማግኘት ይችላል፦ https://tinyurl.com/5y8k639h

5. ዐሊይ ብኑ መህዲ አጦበሪይ (380 ሂ.)፡-

የአቡል ሐሰን አልአሽዐሪ ተማሪ ነው። እንዲህ ብሏል፡-
اعلمْ - عصمنا الله وإيَّاكَ مِنَ الزيغِ برحمته - أنَّ الله سبحانه في السَّمَاء فوقَ كلِّ شيءٍ، مستوٍ على عرشهِ، بمعنى أنَّه عَالٍ عليه
“እኛንም አንተንም አላህ በእዝነቱ ከጥመት ይጠብቀንና - የጠራው አላህ - ከሁሉም ነገር በላይ በሰማይ እንደሆነ፣ በዐርሹ ላይ ከፍ ያለ ነው በሚል ፍቺ ኢስቲዋእ ያደረገ እንደሆነ እወቅ።”

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

#ይድረስ_ለእናቴ
~
ከዚህ በታች የሚቀርበው እውነተኛ  ደብዳቤ አንድ ልጅ ለእናቷ የፃፈችው ሲሆን በውስጡ ብዙ ነገሮችን የያዘ በመሆኑ በአንክሮ  እንከታተለው

#እናቴ_ሆይ! ትሰሚኛለሽ?እስኪ የምነግርሽን በፅሞና ተከታተይኝ።ለመሆኑ ጩኸቴንና ለቅሶዬን ታዳምጫለሽን?!!

#እማማ! እውነት የምታፈቅሪኝ ከሆነ አሁን እነሆ አብሬሽ ነኝና ልቤም በእጆችሽ መሃል ነውና ደስ የሚልሽን ነገር አድርጊ ።ውድ #እናቴ_ሆይ! አሁን እንቀራራብ!ከዚያም እንደልጅነት ዘመኔ እቅፍ አድርጊኝ።ያኔ ሀዘኔና ጭንቀቴ ቀነስ ያደርግልኛል ።ነይና እንባዬን  ከጉንጮቼ ላይ ጥረጊልኝ እንዲሁም እያሳደዱኝ ካሉት ስግብግብ አዳኞች ነፍሴን ታደጊያት ።እስኪ የእናትነት ፍቅርሽን ልቅመሰው ።አንድ አፍቃሪ እናት ለምትወዳት ልጇ ልትሰጣት ከምትችለው ከማር የጣፈጠ ምክር ድርሻዬን ስጭኝ።ነይና በብቸኝነቴ ጥላ ተከልለው ደካማነቴን አይተው በግፈኛ እጃቸው የትርፍ ማጋበሻ ሊያደርጉኝ ካሰፈሰፉት እርጉም የሆኑ ሰዎች መዳፍ አውጪኝ።

#ውድ_እናቴ!አላህ አንቺን እንደ አንድ መልካም እናት እኔን በተመለከተ ልትወጪው ስለሚገባሽ ኀለፊነትሽ ነገ በፍርዱ ቀን ይጠይቅሻል።ሒጃብ እንድለብስና አላህን እንድገዛው ብታበረታችኝ ነገ የሚኖርሽ ምንዳ ከእሳት መዳንና በጀነት ውስጥ የደስታ ሕይወት ማግኛት ነው።ያን የማታደርጊ ከሆነ ግን በአስከፊው የጀሀነም እሳት ስትቀጪ መኖር እጣ ፋንታሽይሆናል አላህ ከዚህ አደጋ እንዲጠብቅሽ እለምነዋለሁኝ።

#እማማ!  ታስታውሻለሽ ገና ልጅ  እያለሁ በፋሽን የተንቆጠቆጡ አልባሳትን ነበር የምታለብሺኝ ።እርቃኔን  እንድሄድና  የፀጉር አቆራረጤ ሳይቀር ወንዶችን እንዲመስል ታደርጊ  ነበር። #እማማ! እውነቱን ለመናገር  ከድርጊትሽ ሁሉ በጣም ያበሳጨኝ የነበረው  ሳላውቀው ሌሎችን

ሞዴሎችን እንድመስል ተፅዕኖ ሴታደርጊብኝ የነበረውን ሁኔታ ነው።

ሕይወቴን የሚያስተካክልልኝንና ነፍሴን ከአደጋ የሚጠብቃት የሆነውን የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መንገድ እንድከተል ለምን አላደረግሽም?!አንቺ ግን አዎ!እንድከተል  የመረጥሽልኝ መንገድ ነጣቂዎች ሴትን ልጅ እንዳስፈለጋቸው የሚረግጡበትንና ርካሽ ስሜታቸውን ለማርካት ባሪያ አድርገው የሚጠበቁበትን  የወሲብና የእርቃን አሻንጉሊትነትን ነው።ይህም መጨረሻው አሳፋሪ ነው።

#እማማ አላህ ያለውን ሰምተሽ ወይስ አንብበሽ ታውቂያለሽ?

"አንተ ነብዩ ሆይ!ለሚስቶችህ ለሴቶች ልጆችህም ለምዕመናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው።ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች)እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው።አላህም መሃሪ አዛኝ ነው።"{] አል-አሕዛብ 59[}

ውድ #እናቴ መቼም ወቀሳዬ  ሳይበዛብሽ አልቀረም ።እስኪ አድምጭኝ ።ሰውነቴን በሜካፕ እንዳዝጎረጎርኩ ሽቶ ተቀብቼ  ወደ ውጭ እንድሄድ ትፈቅጅልኝ ነበር ።የወንዶችን ፍላጎት በሚቀሰቅስ ሁኔታ እርቃኔን አጋልጬ  ስሄድ ቅር አይልሽም ነበር እንዲያውም አሁን አሁን ሳስበው በሁኔታዬ በጣም ነበር ደስ ይልሽ የነበረው።አንድም ቀን አልገፀሽኝም እንዲሁም ጨዋና አይነፋር  እንድሆን አልመከርሽኝም ።በፊትሽ  ከተለያዩ ወንዶች ጋር በአይኔ ስጠቃቀስ ምንም አይመስልሽም ነበር አላህ እንደሚከተለው ማለቱን  ዘንግቼና ችላ ብዬው ነበር።

"ለምዕመናትም  ንገራቸው ።ዐይኖቻቸውን ይከልክሉ ።ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ጌጣቸውንም ከርሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ ።መከናነቢያዎቻቸውንም በአንገትጌጦቻቸው ላይ ይልቀቁ ...."(አል-ኑር )31)

#ውድ_እናቴ  እኔኮ አይነፋርነቴን እና ሒጃቤን ከዚያም ጠቅላላውን ኃይማኖቴን  የለቀኩ ብሆንም አንቺ ግን ምንም ነገር እንዳልተፈጠረና ጭራሽ የምሰራው ነገር ሁሉ ልክ እንደሆነ ሁሉ  አንዳች አይነት ተግሳፅ  ሰጥተሽኝ አታውቂም ።
ወይ ጥፋት!!ይህ ሁሉ ሁኔታሽ እኔን እኔን እንዳይከፋኝ ወይም ደስተኛ እንድሆንልሽ በመፈለግሽ እንደሆነ ብገምትም ባጠቃላይ  ሁኔታዬን ሳየው ግን  ያ የተሞላቀቀ አስተዳደግ ለእኔ ያተረፈልኝ ነገር መጨረሻዬ ወደ ጀሀነም መውረድ እንዲሆን የሚያደርግ አካሄድ ነበር።

#እማማ ነገ በፍርዱ ቀን አላህ ፊት ከምንወቃቀስ ዛሬ ብንወቃቀስይሸላል ብዬ ነው ።እናም እነዚያ ጋጠወጥ ጓደኛ ተብዬዎች  እነዚያ ወደ አዘቅት ሲነዱኝ የት ነበር ያለሺው ?!

#እማማ ከወሰደን ጭልጥ ያለ እንቅልፍ መንቂያው ሰአት አሁን ነው

አሁን ልቤ ሲቃጠል ይሰመኛል አይኖቼም እንባ በጉንጮቼ ያዘንባሉ። እጄን  ይዘሽ የአላህን መንገድ አሳይኝ  እባክሽን! እባክሽን !ተይ እማምዬ ተየይዘን አንጥፋ ! እየመራሽኝ ወደ ጀነት አብረን እንግባ ።

ስለሆነም

<>ከእግዲህ ሒጃቤን እንዳስተካክል እርጅኝ!!

<>መጥፎ ጓደኛች እንዳይኖሩኝ ተቆጣጠሪኝ!!

<>ከኃጢያት አዘቅት መንጭቀሽ በማውጣት ሰው አድርጊኝ!!

<>አላህ የሚወሳባቸውን ቦታዎችና የቁርኣን ትምህርት ፣የሚሰጥባቸውን ስብስቦች (ሃለቃዎች)ላይ እንድገኝ አበረታችኝ!!

#እማማ ይህ እንግዲህ የደብዳቤዬ የመጨረሻ ክፍል ነው ሆኖም ደብዳቤ ለመፃፍ የመጨረሻይ ግን አይደለም ።አላህን ለማመፅና ጠማማውን መንገድ ለመከተል አንዳችም ሰበብ የሚሆን ነገር የለም።ከእኛ ደካማነት በስተቀር ።ለዘህ ሁሉ ኪሳራችን ደግሞ በፀፀታችን ምክንያት ከመፍሰስ የሚታገድ  እንባ ሊኖር አይገባም ይህን ሁሉ ስፅፍልሽ የሁሉም ነገር ተጠያቂዋ አንቺ ነሽ ብዬ ከደሙ ንፁህ ለመሆን አይደለም ።ሁኔታውን ሳስበው

ልቤን እየናጠ ውስጤን ስላስለቀሰው ስሜቴን ላጋራሽ ብዬ እንጂ በዚህ ደብዳቤዬ ትንሽ ወጣ ያሉ ቃላትንና ከስነምግባር አንፃር ላንቺ ለውዷ #እናቴ ያልተገቡ አገላለፆች እንዳሉ አሳምሬ እገነዘባለሁኝ።ሆኖም ነገ ሁላችንም ተዋርደን በጀሀነም እሳት ከምንቃጠል እዚህ የሆነው ሆኖ ብንስተካከል ብዬ ነው ።ልጅ  ለእነቷ ምጥ እንደማታስተምር አውቃለሁ።ሆኖም #እማዬ ይህ የመጪው አለም ጉዳይ ልጅ እናት አይልም ሁሉም ።ሁሉም ለነፍሱ ማወቅ አለበትና።በይ እንግዲህ ለሁሉም ከላይ ለዘረዘርኩት ጥፋቴ ለአላህዬ ብለሽ ከልብ ይቅር በይኝ ።አላህ እኔንም አንቺንም ቀናውን መንገድ አስይዞ ነገ ከሚደሰቱት ባሮቹ  ያድርገን  ዘንድ እለምነዋለሁኝ። ልጅሽ...

ተጠናቀቀ!


ይህን ድንቅ ደብዳቤ  ሁላችሁም ሼር አድርጉ

ሼር     Share       ሼር       ሼር


/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ለሚያስተውሉ ክርስትያኖች!!
~
በወንድም ኢብኑ ሙነወር
ኒቃብ (አይነ ርግብ) መልበስ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው
~
ብዙ ክርስቲያኖች የሙስሊም ሴቶችን አለባበስ (በተለይም ኒቃብን) የዐረብ ባህል እያሉ ሲተቹ ይሰማሉ። በመሰረቱ የፈረንጅ ባህል ተከትለው ሴቶች ከሚራቆቱበት ባህል የዐረብ ባህል ቢሆን እንኳ ግብረ ገብነትን የሚጠቁመው አለባበስ የተሻለ ስርአት ያለው እንደሆነ ግልፅ ነው። ዛሬ የማርያም ምስል ነው ብለው ክርስቲያኖች በሚገልፁት ምስል ላይ ያለው አለባበስ ሙስሊሞች ዘንድ እንጂ ክርስቲያኖች ዘንድ የለም። ለምን የሚለውን ክርስቲያኖች ራሳቸውን ቢጠይቁ መልካም ነው።
ከአለባበስ ጋር ተያይዞ ሙስሊሞች የሚያራምዷቸው መርሆዎች - ፊት መሸፈንን ጨምሮ - በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ እንደሆኑ ክርስቲያኖች ሊያውቁ ይገባል። ብዙ ክርስቲያኖች ለመፅሀፋቸው ባይተዋር ስለሆኑ ጥቂት ምሳሌዎችን እጠቅሳለሁ፦

1- በኢስላም በሴት የሚመሳሰል ወንድ እና በወንድ የምትመሳሰል ሴት የተረገሙ ናቸው። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል?
"ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ። ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።" [ኦሪት ዘዳግም 22፥5]

2- ሴት ፀጉሯን እንድትሸፍን ኢስላም በጥብቅ ያዛል። መፅሀፍ ቅዱስስ ምን ይላል? ይሄውና :- "ሴትም ራስዋን ባትሸፍን ጠጉርዋን ደግሞ ትቆረጥ፤ ለሴት ግን ጠጉርዋን መቆረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር ከሆነ ራስዋን ትሸፍን።" [1ኛ ቆሮንቶስ 11 ፥ 6]

3- ሴት ፊቷን መሸፈኗ በኢስላም ከጥንት ጀምሮ የነበረ ሐቅ ነው። በመፅሀፍ ቅዱስስ የለም? በሚገባ አለ። ይሄውና፦

* "ርብቃም ዓይኖችዋን አቀናች፥ ይስሐቅንም አየች፥ ከግመልም ወረደች። ሎሌውንም፦ ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው? አለችው። ሎሌውም፦ እርሱ ጌታዬ ነው አላት እርስዋም መሸፈኛ ወስዳ #ተከናነበች።" [ዘፍጥረት 24፣ 64- 65]

* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭሽን እንደተከፈለ ሮማን ናቸው።" [መሀልየ ዘሰለሞን 6፡7]
ልብ በሉ! አይነ ርግብ ማለት ኒቃብ ወይም የፊት መሸፈኛ ነው።

* "ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።" መሀልየ ዘሠለሞን 5፡6]

* "በአይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ አይኖችሽ እንደርግብ ናቸው።" [መሀልየ ዘሠለሞን 4፡1]

ስለዚህ ሙስሊም ሴቶች እየተገበሩት ያሉት በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝን እውነት ነው ማለት ነው። ለምንድነው ታዲያ ይሄ ጉዳይ ክርስቲያኖችን የሚያበሳጨው? ከሙስሊም ሴቶች ጎን መቆም ሲገባ ጭራሽ ማንገላታትና ከትምህርት ገበታ ማራቅ ፈፅሞ የማይገባ ነውረኛ ተግባር ነው።
ደግሞም እወቁ! ብዙ ጭቆናዎች በሂደት እንደተቀየሩት ይሄም ያለ ጥርጥር ዛሬ ወይም ነገ ይቀየራል። ለትውልድ የሚቀረው የናንተ የጭቆና ታሪክ ነው። በታሪክ ጥቁር መዝገብ ላይ ስማችሁ እንዲቀር ነው የምትፈልጉት? ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ አስቡበት።

* ባያያዝኩት ምስል ላይ ፊታቸውን ሸፍነው የሚታዩት ሙስሊሞች አይደሉም። ይልቁንም አይሁዶች ናቸው። የሙስሊም ሲሆን ሁሉ ነገር ለሚያስጨንቃቸው አካላት ማስታገሻ ይሆናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

🟢የፈትዋ ቁጥር 1⃣9⃣


ስሜት በራስ ማርካትና ፈሳሽ❓

መልስ
🔊በሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አለተሚይ


በዚህ የፈታዋ ብቻ ቻናል⤵️
/channel/FATTAWAS

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አሰላሙ ዐለይኩም ወንድሞች እና እህቶች!
~
ይህቺ 13 ገፅ አጭር የፅሑፍ ፋይል ቁርኣን የአላህ ንግግር መሆኑን በሚያስተባብሉት አሕባሾች / አሽዐሪዮች ዙሪያ የቀረበች ዳሰሳ ነች። ብዙ ሰው ይሄ የጥመት አንጃ እንዲህ አይነት ሰቅጣጭ ዐቂዳ እንደሚያራምድ ስለማያውቅ በነሱ የተሸወደ ወገናችን ይነቃ ዘንድ ይህንን ፅሑፍ በማንበብና በማሰራጨት የበኩላችሁን ኃላፊነት እንድትወጡ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ።

ወንድማችሁ ኢብኑ ሙነወር
=
የቴሌግራም ቻናል :-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የሐራም ፍቅር!

ኢብኑል ቀይም አል-ጀውዚያ ፍቅርን በሶስት ደረጃ ሲያስቀምጡት፦"ፍቅር ጅማሮው ጣፋጭና ደስ የሚል ፣ መሀሉ ሐሳብ ጭንቀትና የልብ በሽታ እና መጨረሻው ደሞ ህመም ጥፋት ሞት ነው አፍቃሪውን አላህ ካርዳው "ይላሉ ረሒመሁላህ

እናም "ውሃ ሲዮስድ እያሰሳቀ ነው" እንደሚባለው ፍቅርም በማድነቅ አሳዘነችኝ ልምከራት ላስተምራት በማለት ነውና የሚጀምረው ጠንቀቅ!!

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ቄሱ ፦ አንድ ሰው ከአንድ በላይ ሚስት ሊኖረው ይችላል የሚለውን እንዴት ጭንቅላታቸው እንደተቀበለው አላውቅም።

ሙስሊሙ፦ አንተ ይሄ ይገርምሃል'ንዴ? የአንዳንዶቹ ጭንቅላትኮ ሶስት አምላኮችን ተቀብሏል!
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ከተገበርናት  ሂይወታችንን ሙሉ የምትቀይር ንግግር ከነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰዎች በጣም ደጋግመው ይናገሯታል ግን አንተገብራትም ሰዎች ሆይ! እሷ ድንቅ የነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር የትኘዋናት?

እሷማ ፦"በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር ከልሆነ ዝምምምም ይበል"የምትለዋ ናት

ለምሳሌ፦ ሀሜት ንግግር ነው ግን መልካም  ንግግር ነው? አይደለም!ስለዚህ ይህችን ሐዲስ ተግባር ላይ ብናውላት ከሀሜት እንቆጠባለን አላህ ያግራልን።

ሶሻል ሚድያ ላይ ያልተጠራን ወሬ ማሰራጨት በግምት መናገር  አፀያፊ ቃላቶችን በያ comment ከመመላለስ እንቆጠባ!!

ደሞኮ ሙስሊም ሱንኒ ሰለፊይ ነን እያልን ከኛ መልካም ስነምግባር ሌሎችም  በተግባር ማስተማር የለብንም ወንድም እህቶች?

የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነግግር እደግመዋለሁ"በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር አልያ ዝምምም ይበል"

ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏ


/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የኢኽላስ ድካም ከባድ ነው!!
———
ታላቁ ዓሊም ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
«ወንድሞቼ ስራን ለአላህ ማጥራት (ኢኽላስ) ከባድ ድካም አለው። ሰዎች በትንሹም ቢሆን እንኳን ከይዩልኝ (ሪያእ) አይጠሩም። አላህ ይጠብቀንና በትንሹም ቢሆን እንኳን በራስ ከመደነቅም አይጠሩም። ወዮላችሁ! ከዚህ ተግባር ተጠንቀቁ‼።

ልብህን አጥራ!፣ ስራህን ለላቀው አላህ ብለህ ስራ!፣ አንተ የአላህ ባሪያ እንጂ የፍጡሮች ባሪያ አይደለህም!። የሚጠቅምህም ሆነ የሚጎዳህ አላህ ነው። ያ ጀነት የሚያስገባህ ከጀሀነም የሚያርቅህ አላህ ነው። የሁሉ ነገር ስልጣን በእጁ ያለው (ጌታ) እርሱ አላህ ብቻ ነው።»
ሸርህ ሚሽካት አልመሳቢህ 1/143
✍🏻ትርጉም:- ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
/channel/IbnShifa
/channel/IbnShifa

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ሶብር {ትዕግስት}
〰➖〰➖〰


አንዳንዴ ወደኋላ መለስ ብለን እራሣችንን መፈተሽ ጥሩ ነውና ትዕግስታች ትዕግስት
ስለሚያስፈልገው እስኪ ከዚ ኮከብ መካሪያች መክርን እንቀበል!


ትዕግሥት ፍርሐት ሣይሆን የመፍትሔ አቅጣጫ ነው።
↷ትዕግስትን ተማር/ተለማመድ

የሆነ ሰው ስልክህ ላይ ደውሎ ማን ልበል ቢልህ እራስህ አይደል የደወልከው ብለህ ቱግ አትበል።

🎙በ𝐔𝐬𝐭𝐚𝐳 𝐈𝐛𝐧𝐮 𝐌𝐮𝐧𝐞𝐰𝐨𝐫

↷↷↷↷↷⇊🍃⇊↶↶↶↶
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የሃያት ናስር ማስፈራሪያ
ለ ዘምዘም እና ሂጅራ ባንክ፣
ለባል ኸይር እርዳታ ድርጅት እና ለሌሎችም
/channel/SadatKemalAbuMeryem

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

አሕ ^ባሽ እና ዐብዱል ቃዲር አልጀይላኒይ (561 ሂ.)
~
ተስፈንጣሪው የአሕ ^ ባሽ አንጃ "አላህ ከፍጡራን ሁሉ በላይ ነው" የሚሉ ሙስሊሞችን ከኢስላም በማስወጣት (በማ^ ክ^ ፈ^ር) የታወቀ ነው። የቡድኑ ቁንጮዎች በዚህ ፅንፈኛ አቋማቸው የተነሳ እነ ኢማሙ ዳሪሚይን፣ እነ ኢብኑ ኹዘይማን፣ እነ ኢብኑ መንደህን እስከማብጠልጠል ደርሰዋል። ይሄ አጉል የሆነ አካሄዳቸው ግን ሳያስቡት ቅርቃር ውስጥ ሲከታቸው ይታያል። "እናከብራቸዋለን" ከሚሏቸው ዑለማዎች ውስጥ የአላህን ከፍጡራን በላይ መሆን የሚያፀድቁ ያጋጥሟቸዋልና። ጀይላኒይ ረሒመሁላህ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ መሆን ይችላሉ። የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን አንዴ ሳይሆን ደግመው ደጋግመው አስረግጠው ገልፀዋል። ይህንን እውነት የማይቀበሉትን ኮንነዋል። ከዚህም አልፈው አሻዒራን በስም ጠቅሰው አብጠልጥለዋል። ይሄ ለአ^ ሕ^ባሾች ከባድ ራስ ምታት ነው። አይቀበሏቸው እነሱ ዘንድ የማይሆን ነገር ነው። ሌሎችን እንደ - ሚያ* ከ^ ፍሩ እንዳያከ * ፍ- ሯ ^ቸው በሱፊያው ዓለም ያላቸው ቦታ እጅግ የገዘፈ ነው። ሌሎችን በሚያ* ከ^ ፍሩበት ጉዳይ እሳቸውን ሲያልፉ ደግሞ አጭ በርባሪነታቸው ገሃድ ይወጣል። ምን ይሻላል? ሽምጥጥ አድርገው መዋሸትን እንደ ዘዴ መርጠው ነበር። ችግሩ ግን ውሸቱም የነሱን ዝቅጠት ከማጋለጥ ባለፈ የሚፈይድ አለመሆኑ ነው።
ቀጥሎ ጀይላኒይ የአላህን ከ0ርሹ በላይ መሆን ያፀደቁባቸውን ንግግሮች እጠቅሳለሁ፦

[1ኛ]:-
وأن الله تعالى خلق سموات بعضها فوق بعض، وسبع أرضين بعضها أسفل من بعض، ومن الأرض العليا إلى السماء الدنيا مسيرة خمسمائة عام، وبين كل سماء وسماء مسيرة خمسمائة عم، والماء فوق السماء السابعة، وعرش الرحمن فوق الماء، والله تعالى على العرش
“የላቀው አላህ ሰማያትን ከፊሎቹን ከከፊሎቹ በላይ፣ ሰባት ምድሮችን ደግሞ ከፊሎቹን ከከፊሎቹ በታች አድርጎ ፈጥሯል። ከላይኛዋ ምድር እስከ ታችኛዋ ሰማይ ድረስ አምስት መቶ አመት የሚያስኬድ ርቀት አለ። ከእያንዳንዱ ሰማይ እስከ ቀጣዩ ሰማይ ድረስ እንዲሁ የአምስት መቶ አመት ጉዞ ርቀት አለ። ውሃው ከሰባተኛው ሰማይ በላይ ሲሆን የአረሕማን ዐርሽ ከውሃው በላይ ነው። ከፍ ያለው አላህ በዐርሹ ላይ ነው።” [አልጉንያ፡ 1/123]

[2ኛ]:-
وَهُوَ بِجِهَةِ العُلُوِّ، مُسْتَو عَلَى العَرْشِ، ... واللهُ تَعَالَى عَلَى العَرْشِ وَلاَ يَخْلُو منْ عِلْمِهِ مكانٌ، وَلاَ يجوزُ وصفهُ بأنَّهُ فِي كلِّ مكانٍ، بلْ يقالُ: إنَّهُ فِي السَّمَاءِ عَلَى العَرْشِ
“እርሱ በላይ አቅጣጫ ከዐርሹ በላይ ከፍ ብሎ ነው። … የላቀው አላህ በዐርሹ ላይ ነው። ከእውቀቱ የሚራቆት ቦታ የለም። ‘እርሱ ሁሉም ቦታ ነው’ ብሎ መግለፅ አይፈቀድም። ይልቁንም እርሱ በሰማይ በዐርሹ ላይ ነው።” [አልጉንያ፡ 1/121]

[3ኛ]:-
وهو باين من خلقه، لا يخلو من علمه مكان، ولا يجوز وصفه بأنه في كل مكان، بل يقال: إنه في السماء على العرش
“እርሱ ከፍጡሩ ተለይቶ ነው ያለው። ከእውቀቱ የቱም ቦታ አይራቆትም። ‘በሁሉም ቦታ ነው’ ብሎ እሱን መግለፅ አይፈቀድም። ይልቁንም በሰማይ በዐርሹ ላይ ነው ይባላል።”
ይህን ካሉ በኋላ የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃዎችን ዘርዝረዋል። አለፍ ብለውም “የኢስቲዋእን መገለጫ ያለ ‘ተእዊል’ (ቁልመማ) በዐርሹ ላይ ከፍ ማለት ነው ብሎ ያለ ገደብ መረዳት ይገባል” ካሉ በኋላ ከርራሚያ፣ #አሽዐሪያና ሙዕተዚላን ከነ ተሳሳተው ትርጓሜያቸው ጋር በስም ጠቅሰው አውግዘዋል። [አልጉንያ፡ 1/124]

[4ኛ]:-
كَوْنُهُ عزَّ وجلَّ عَلَى العَرْشِ مذكورٌ فِي كلِّ كتابٍ أُنزلَ عَلَى كلِّ نبيٍّ أُرسلَ بلا كَيْفٍ
“አሸናፊውና የላቀው - ያለ አኳኋን - በዐርሹ ላይ መሆኑ በሁሉም የተላከ ነብይ ላይ በተወረደ መፅሐፍ ውስጥ ሁሉ ተጠቅሷል።” [አልጉንያ፡ 1/125]

[5ኛ]:-
وأنه تعالى ينزل في كل ليلة إلى سماء الدنيا، كيف شاء وكما شاء، فيغفر لمن أذنب وأخطأ وأجرم وعصى لمن يختار من عباده ويشاء، ... لا بمعنى نزول رحمته وثوابه على ما ادعته المعتزلة والأشعرية
“የላቀው (አላህ) በየሌሊቱ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ በሚሻው ሁኔታ፣ እንደ መሻቱ ይወርዳል። ሃጢአት ለፈፀመ፣ ለተሳሳተ፣ ለወነጀለ፣ ላመፀ ይምራል፤ ከባሮቹ ለመረጠውና ለፈለገው። እንጂ ሙዕተዚላና #አሽዐሪያ እንደሞገቱት የእዝነቱና የምንዳው መውረድ አይደለም።” [አልጉንያ፡ 1/125]

በጀይላኒይ ላይ ወሰን በማለፍ ለሚታወቁት በርካታ ሱፊዮች ይሄ እጅግ አስደንጋጭ ነገር ነው። በቁርኣንና በሐዲሥ ላይ እንደለመዱት አይቆለምሙት፣ አይመችም። ጭራሽ “አሽዐሪያ” እያሉ በስም ጠርተው ነው ደጋግመው ያብጠለጠሏቸው። ምን ይሻላል? ቢጨንቃቸው ሁለት ዓይነት ማምለጫዎችን ዘይደዋል።

[ማምለጫ አንድ]፦
አንዳንዶቹ: “ሌሎች ሰዎች በኪታባቸው ውስጥ አስገብተውባቸው እንጂ እሳቸው ይህን አላሉም” በማለት አይናቸውን በጨው አጥበው የተከራከሩ አሉ። ለምሳሌ ሀይተሚይ (974 ሂ.)። [አልፈታወል ሐዲሢያህ፡ 145] ግና ከሀይተሚይ በፊት ያለፉ ታላላቅ ዑለማዎች - ሱፊዮች ጭምር - ያረጋገጡት ሐቅ በእንዲህ አይነት ድንጋጤ በወለደው ባዶ ሙግት አይፈርስም። ሲጀመር ሀይተሚይ በመሰል ጉዳዮች ላይ ሚዛናዊነት የለውም። እንደ ኢብኑ ዐረቢይ ላሉ አፈንጋጮች እየተሟገተ እነ ኢብኑ ተይሚያን በሃሰት የሚወነጅል ነው።

[ማምለጫ ሁለት]፦
"ኋላ ቶብተዋል" የሚል ነጭ ውሸት ነው። ይህንን ካሉት ውስጥ ያፊዒይ (768 ሂ.) ተጠቃሽ ነው። ያፊዒይ ከላይ የተዘረዘሩትን ንግግሮች የጀይላኒይ መሆናቸውን ይመሰክራል። ይሄ ለሀይተሚይ ምላሽ ይሁንልን።
ነገር ግን በህይወታቸው መጨረሻ ላይ “ዐቂዳቸውን ቀይረዋል ይላል። “ማስረጃው” አስቂኝ ነው። የጀይላኒይ “አላህ ከዐርሽ በላይ ነው” ብሎ ማመን ለኢብኑ ደቂቀል ዒድ ሲደርስ በጀይላኒይ “አፈንጋጭነት” ይገረማሉ። ጀይላኒይም ይሄ ነገር ሲደርሳቸው በህይታቸው ፍፃሜ ላይ ዐቂዳቸውን ቀየሩ ይላል። ያፊዒይ ይቀጥልና ታሪኩን የነገረኝን ነጅሙዲን አልአስፈሃኒይን አልጠረጥረውም። ምክንያቱም እሱ የከሽፍ (መገለጥ) ባለቤት ነውና ይላል። [ሚርኣቱል ጂናን፡ 3/272]
ሱፊያ ሰፈር እንዲህ አይነት በሬ ወለደ ወሬ ብርቅ አይደለም። ያፊዒይም በዚህ የታወቀ ነው። ለማንኛውም ጀይላኒይና ኢብኑ ደቂቀል ዒድ ዘመናቸው አይገናኝም። ኢብኑ ደቂቅ የተወለዱት ጀይላኒይ ከሞቱ ከ64 በኋላ ነው። ምኑን ከምኑ እንደሚያገናኝ ተመልከቱ። ባለ ከሽፉ እንዲህ አይነት መክሹፍ (የተጋለጠ) ውሸት ነው የዋሸው። ታሪኩ ቅጥፈት እንደሆነ ሌሎች ነጥቦችን መጨመር ቢቻልም በዚህ ደረጃ ላለ ቅጥፈት ደክሜ ማድከም አልፈለግኩም።

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

الفتوي الحموية -٢

አል-ፈትዋ አልሀመዊያ -2

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ውዱ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወንዶችን "ልብሳችሁን አሳጥሩ" አሉን ። "ከቁርጭምጭሚቱ በታች አስረዝሞ የለበሰ የእሳት ነውም "አሉን።

የዚህን ጊዜ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወዳጅ የሆነ ሰው ሊል የሚገባው "መርሀበን" ብሎ ለነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትእዛዝ ፈጠን ብሎ እጅ መስጠት ሲገባው "ለኩራት ካልሆነ ችግር የለውም"! ፣"ሱሪ ባሳጠረ አይደለም"!፣ "ሱሪን ማሳጠር የውሃቢያ፣የአክራሪዎች ነው!........."ወዘተ እያሉ ለሀቢቡና ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትእዛዝ በእሳት ላስፈራሩት ትእዛዛቸው ጀርባ መስጠት በፍፁም በፍፁም ተገቢ አይደለም ወላሂ!

አላህ ይምራን በትእዛዙ ላይም ቀጥ ከሚሉት ያድርገን።

ወንድሜ ለአለማት እዝነት የተላኩት ውዱ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለኛ ሁለት አገር ከቅጣት የሚጠብቀንን ነገር ስለነገሩን የውዱ ሰውን ትእዛዝ ላለመቀበል ምክንያቶችን ትደረድራለህ?!!

ለዛውምኮ በጣም ቀላል በሆነ ጉዳይ!

ትምህርት ቤትኮ ሄደ "ሱሪህን አሳጥር ካልሆነ ከትምህርት ትበረራለህ"!ብትባል ምናልባት ልብስ ሰፊ ጋር ከመሄድህ በፊት በምላጭ (በስለት)ነገር ልተሳጥር ሁላ ትችላለህ የአስተማሪውን ትአዛዝ ለማክበር ከመፍጠንህ የተነሳ!

ምነውሳ የውድ ሰውን ትአዛዝ ለማክበር አልፈጠንም?!ምነውሳ የነብዩ ትእዛዝ ሲሆን ለመታዘዝ ከበደንሳ!!!!

ወንድማችሁ አብዱረሒም ሳኒ ከአዳማ

ሼር ማድረግን አይርሱ

ቻናሉንም ይቀላቀሉ

/channel/gfyygy

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

ከዚያም ቁርኣናዊ ማስረጃዎችን የዘረዘረ ሲሆን ቀጥሎም ኢስቲዋእን በኢስተውላ (ተቆጣጠረ) በመተርጎም በሚታወቁት ሙዕተዚላ ላይ የሰላ ትችት ሰንዝሯል። [ተእዊሉል አሓዲሢል ሙሽኪላ፣ ኢብኑ መህዲ፡ 24ኛ ወረቀት] [አልአስማእ፣ በይሀቂ፡ 2/307]
“ኢስቲዋእ በዐረብ ቋንቋ መቆጣጠር ማለት አይደለም” በማለትም ለአክባሪዎቹ አሽዐሪያዎች ምቾት የማይሰጥ ምስክርነት ሰጥቷል። [ተእዊል፡ 25ኛ ወረቀት]
ልብ በሉ! ዐሊይ ብኑ መህዲ አላህ ከሁሉ ነገር በላይ በዐርሹ በላይ መሆኑን ያፀድቅ እንደነበር በይሀቂይም መስክረዋል። [አልአስማእ፡ ቁ. 870]

አሽዐሪዮች “ኢስተዋ” የሚለውን “ኢስተውላ” እያሉ ለመቆልመም (ተእዊል ለማድረግ) የሚጠቀሙትን ስንኝ አስመልክቶም እንዲህ ብሏል፡-
“በዐርሹ ላይ ኢስቲዋእ የማድረጉ ትርጓሜም ገጣሚው … እንዳለው እሱን መቆጣጠር ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም መቆጣጠር ማለት ችሎታና ሃይል ነው። የላቀው አላህ ደግሞ ቻይ፣ ሃያልና አሸናፊ ከመሆን ተወግዶ አያውቅም። {ከዚያም በዐርሹ ላይ ከፍ አለ} ሲል ግን ይህ መገለጫ ካልነበረ በኋላ መምጣቱን ስለሚያሳይ እነሱ የሚሉት ውድቅ ይሆናል።” [አተምሂድ፡ 262]

በአሕ - ባሽ የጥመት ስብከት የተሸወዳችሁ ወገኖቻችን ሆይ! አላህን ፈርታችሁ፣ አኺራችሁን አስባችሁ፣ ህሊናችሁን ከነዚህ አካላት ጫና ነፃ አድርጋችሁ እውነቱን መርምሩ። አላህ ልባችሁን ለሐቅ ክፍት ያድርጋችሁ።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሸዋል 10/1444 (ሚያዚያ 22/2015))
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

በድጋሚ የተለቀቀ ያላነበባችሁት አንብቡት ትጠቀሙበተላችሁ

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

30 ጁዝ ቁርዓንን መቅራት ለምትሹ
👇📚📚📚👇
በቃሪእ ሚሻሪ ረሽድ አልአፋሲ ድምፅ
ቁርዓኑ #እየታዬ #ያለኔት
89 ሜጋባይት ብቻ

በዩቱዩብ ስለ አፕልኬሽኑ ቪድዮ
https://youtu.be/RORCagh5deU
🥀🥀🥀🥀

ከቴሌግራም ለማውረድ
👇📚📚📚👇
/channel/ISLAMICBOOKSANDAPPS/139278

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

👉የጉንችሬዋ ''ላንች ነው'' ጀግናዬ''

ለኒቃቢስቶች እና ዋጋ ለከፈሉልሽ ሁሉ ይሁንልኝ..!!

🔴«ኒቃቧን ለብሳ ትማራለች»🔴

ሸር በማድረግ አድርሱልኝ አደራ ሰጠኋችሁ

👉በዚህ ልክ እንደምሳሳልሽና እንደማከብርሽ ጠላቶች እንዳውቁ እፈልጋለሁና አድርሱልኝ!!

👉በወንድምሽ ኑረዲን አል አረቢ

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

📌አጠር ያለች መልዕክት

ርዕስ ☞ ቅድሚያ ለተዉ
ሒድ

🎙በሸይኽ ሱልይማን አ-ሩሐይሊይ
(አላህ ይጠብቃቸዉ)


/channel/adama_ahlusuna_weljemea

Читать полностью…

አላህ ከዐርሽ "በላይ" ነው።Abdurahim sani

የዒድ አደራ
~
አይናችንን እንስበር፣ አጅነቢይ ከመመልከት እንቆጠብ።
ሀሳን ብኑ አቢ ሲናን - ረሒመሁላህ - ከዒድ ሲመለሱ "ስንት ቆንጆ ሴቶችን ተመለከትክ?" ብላ ሚስታቸው ብትጠይቃቸው
"ወጥቼ እስከምመለስ ድረስ ከአውራ ጣቴ ውጭ አልተመለከትኩም" ብለው ነበር የመለሱት።

ሱፍያን አሠውሪ - ረሒመሁላህ - ደግሞ "በዚህ ቀናችን የመጀመሪያ ስራችን እይታችንን መስበር ነው" ብለዋል።
አደራ በዚህ በተከበረ ቀን ከየትኛውም ሐራም ነገር እንቆጠብ። ጌታችንን አናምፅ።
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሳሊሐል አዕማል።

#ከደጋጎቹ_ቀዬ

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor

Читать полностью…
Subscribe to a channel