ቻናሉን ጆይን በሉና ተከታተሉ ። ጥርት ባለው ሰማይ ላይ _ _ሙሉ ጨረቃ እየበራ እይታህን እክል ገጥሞት _ _አይንህ ስራውን ባይሰራ "ጨረቃ የለም"እያልክ _ _ በከንቱ አትገላገል አለም እያየው ነውና_ _ እውነቱን ካዩ ተቀበል {[ኢብኑ munewor ]} ለአስተያት 👉 @Abdurhimsane_bot
🔷 ከዒድ አዳቦችና ሙኻለፋዎች
➬➬➬➬➬➧
➪ እኛ ሙስሊሞች አላህ እንከን የለሽ የሆነ ለሁሉም እነቅስቃሴያችን ስርኣት አድርጎ የተሟላ ዲን ሰጥቶናል። ከእነዚህ ስርአቶች ውስጥ አንዱ የዒድ ስርአት ነው። ሙስሊሞች ሁለት ዒዶች አሏቸው። እነዚህም ዒደል ፊጥርና ዒደል አድኃ ናቸው። በምንም መልኩ ከእነዚህ ሁለት ዒዶች ውጪ ሌላ ዒድ ፈጥሮ ወደ እስልምና ማስጠጋት አይቻልም ከታላላቅ ወንጀሎች አንዱ ይሆናል።
➽ እነዚህ ሁለቱ ዒዶች ሙስሊሞች ሊደሰቱባቸው ሊያስደስቱባቸው ወደ ጌታቸው ሊቃረቡባቸው በመልካም ስራ ላይ መልካም ስራ በመጨመር አምላካቸውን ሊያመሰግኑባቸው ሊያልቁባቸው የተደነገጉ ናቸው። በእነዚህ ዒዶች ልንጠብቃቸው ከሚገቡ ስርአቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፦
=❵> የዒድ ቀን መታጠብና ያለንን ምርጥ ልብስ መልበስ ከተቻለ ነጭ ልብስ
=❵> ለሴት ልጅ አጭር ልብስ ወይም ረጅም ሆኖ ቀጭን ልብስ ሱሪ እና ታይት የመሳሰሉ ጠባብ የሆኑ ልብሶችን መልበስ አይፈቀድም።
=❵> ለወንዶች ሽቶ መቀባት የተወደደ ሲሆን ለሴቶች አይፈቀድም።
=❵> ወደ ዒድ ሲወጡ ተምር ወይም የተገኘውን በልቶ መውጣት ተምር ከሆነ ዊትር ቢሆን ይመረጣል።
=❵> ሴቶችን ህፃናትን ይዞ መውጣት በልማድ ደም ላይ ያሉ ከመስገጃው ቦታ ራቅ ብለው የሶላቱንና ዱዓኡን በረካ በመታደም ተካፋይ መሆን ይችላሉ።
=❵> የሶላት ቦታ እስከሚደርሱ ተክቢራ ማለት
=❵> ዘካተል ፊጥር ከሶላት በፊት ማውጣት (ለሚገባቸው ሰዎች መስጠት)
=❵> ሲመለሱ በሌላ መንገድ መመለስ
=❵> ወደቤት ሲመለሱ ረካዓተይኒ መስገድ ይህ የተረሳ ሱና ነው። ሐይ እናድርገው።
=❵> ዚያራ ማድረግ ስጦታ መሰጣጠት በሰዎች ውስጥ ደስታ መፍጠር በተለይ በየቲሞችና ሚስኪኖች።
➡️ የዒድ ቀን የሚሰሩ ሙኻለፋዎች
➲ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው ❝ዒድ የደስታ ቀን ነው። ይህ ማለት ተፈቶ እንደተለቀቀ ጥጃ ያለ ሸሪዓዊ ገደብ እንደፈለግነው የምንሆንበት ቀን ነው ማለት አይደለም።❞ ሙስሊሞች አላህን በየእለት የህይወታቸው ያመልኩታል። ትእዛዙን ይፈፅማሉ አያምፁትም። በመሆኑም በዒዳቸውም ቀን ከወንጀል ሊርቁ ይገባል። ከእነዚህ የዒድ ቀን ከሚሰሩ የተከለከሉ ተግባሮች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፦
=}> ተበሩጅ (ያልተፈቀዱ ልብሶችን መልበስ) መገላለጥ ስስ የሆኑ ልብሶችን መልበስ
=}> ሴቶች ሽቶና ዴዶራንት ተቀብቶ ተቀንደቦ የተለያዩ እንደ ሊፒስቲክና፣ ፋውንዴሽን፣ ኩል፣ ፌር፣ ፓውደር እና የመሳሰሉ ኮስሞቲክሶችን ተቀባብቶ መውጣት
=}> ከዒድ ሲመለሱ ሴትና ወንድ ተቀላቅሎ መጨፈር!!! በጣም አሳፋሪና የራስንም የእስልምናንም ክብር የሚነካ ተግባር ነው። እንጠንቀቅ።
=}> እቤት ከተመለሱ በኋላ ቴሌቪዥን ላይ አፋጥጦ ሐራም እየተመለከቱ መዋል። ቴሌቪዥን እቤት ማስገባት የተከለከለ ስለሆነ ራሳችንና ልጆቻችንን ከዚህ የወንጀል ረርሽኝ እንጠብቅ።
=}> የተለያዩ የህፃን ፀጉር ሽበት የሚያስበቅሉ የሽርክ አይነት ያለባቸውን መንዙማዎች ከፍቶ በእርጥብ እሳት (ጫት) እየተቃጠሉ መዋል።
=}> ኢስላም የወንድ ጓደኛ የሴት ጓደኛ በሚል ያለ ኒካሕ የሚደረግ የትኛውም ግንኙነት ከልክሏል በመሆኑም ለዒድ ለተቃራኒ ፆታ ጓደኛ ስጦታ ማበርከትም ሆነ ዒድን አብሮ ማሳለፍ አይፈቀድም።
=}> የዒድን ቀን ቲያቲር ቤት ፊልም ቤትና የመሳሰሉ ቦታዎች ቤተሰብን ይዞ መሄድ የዒድን አላማ የሚፃረር ተግባር ነው። መራቅ አለብን።
➧ እነዚህ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው። አላህ ዒዱ የደስታና የሰላም የሱን ውዴታ የምናገኝበት ያድርግልን።
📝 ኡስታዝ ባህሩ ተካ አቡ ዑበይዳህ ሀፊዘሁሏህ
/channel/bahruteka/1387
/channel/bahruteka/1387
እስኪ ዛሬ የሳዳት ከማልን ዳዕዋ ልጋብዛችሁ።
ትናንት በአጋጣሚ በሆነ መስጅድ ዙህርን ስሰግድ ቆንጆ ዳዕዋ አድርጓል። አሪፍ ነጥቦችን ስላነሳ በተለይ ወጣቶች ብታደምጡት ትጠቀማላችሁ።
ሸይኽ ሳሊሕ አል ፈውዛን
ተራዊህና ተሀጁድ አንድ ላይ በአንድ ለሊት በመጨረሻዎቹ 10 ቀኖች መስገድ አይቻልም የሚሉ መሰረት በሌለው ቅርንጫፍ ላይ እየተንጠለጠሉ የሚዘሉ ምስኪኖችን እንዴት እንደሚገልፁዋቸው
– እነዚህ ሰዎች ድክመታቸውንና ስልቹነታቸውን ሱና እንከተላለን በሚል የሚሸፍኑ ናቸው
– በሱና እንሰራለን ይላሉ ሱናን አያውቁትም
– ሰዎችን ከመልካም ስራ እንዲርቁ የሚያደርጉ ናቸው
– ሰዎችን በዲናቸው የሚፈትኑ ናቸው
– ሰዎችን በክርክር ከመልካም ስራ የሚያዘናጉ ናቸው
አትስሙዋቸው አላህ ይምቸው ይላሉ
/channel/bahruteka
ቁርዓንን በ8 የተለያዩ ቃሪኦች እያዳመጣችሁ መቅራት የምትችሉበት አፕልኬሽን ቀስቷን ነክተው ያውርዱ
/channel/ISLAMICBOOKSANDAPPS/222895
#ሼር_በማድረግ_እንተባበር
ውድ ወዳጆቼ እህትና ወንድሞቼ ኩብራ አሊ የተባለች እህት በቅርቡ ከአረብ ሃገር ተመልሳ ሃገር ገብታ ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥሟት ወደ ጭንቅላት ደም መፍሰስ አጋጥሟት ራሷን ስታ ለቀናቶች ደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ተኝታለች…ለተሻለ ህክምና የአቅም እጥረት በመኖሩ የሁሉም ሰው ትብብር አስፈልጓልና ሁላችንም ለአሏህ ስንል በቻልነው እንርዳት
የቻልም በገንዘብ ያልቻልን በዱዓ እናግዛት #ሼር_አድርጉላት
ለበለጠ መረጃ
ከሪም አሊ
0937445870
0912997469
ድጋፍ ለማድረግ
የባንክ አካውንት 1000516060836
ሊሚያ ኑረዲን
እና
ኑሪያ ሰዒድ
የትም ብትሆን አላህን ፍራ
~
ዛሬ ረመዷን 11/1444 በፉሪ ሰልሰቢል መስጂድ የቀረበ ምክር
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me//IbnuMunewor
👉 የዘንድሮ የብር ዋጋ
የንግድ እቃ ዘካ ለሚስኪኖች ሲባል በብር መተመኑ የተወደደ መሆኑ ዑለሞች ይናገራሉ በመሆኑም የዘንድሮ የዘካህ ኒሷብ ( አንድ ለንግድ የቀረበ እቃ ካፒታሉ ስንት ሲሆን ዘካ ይወጅብበታል የሚለውን ለማወቅ ) የአንድ ግራም ብር ዋጋ ማወቅ ይኖርብናል ። በመሆኑም የዘንድሮ ገበያ ላይ ያለው የአንድ ግራም ብር ዋጋ በአማካይ 150 ብር ነው ።
አንድ ዲርሀም በግራም 2 ,975 ሲሆን ዘካ የሚወጅበው በ200 ግራም ዲርሀም ነው ። 200 × 2,975 = 595 ግራም ይሆናል ።
ይህ ማለት 595 ግራም × 150 ብር = 89,250 ብር ይሆናል
ስለዚህ የአንድ ሰው የሱቁ ካፒታል 89,250 እና ከዛ በላይ ሆኖ አመት ዞሮ ከመጣበት ዘካ ይወጅብበታል ማለት ነው ።
ነጋዴዎች ተጠንቅቃችሁ ዘካ በማውጣት የድሆችን ሐቅ አድርሱ ምንዳችሁ ከአላህ ፈልጉ ዘካ አለመስጠት ያለው ዛቻ በጣም አስፈሪ ነውና ለአኼራ ቅጣት ራሳችንን አናጋልጥ ። ዘካህ ሰጥተን ንብረታችንን እናፋፋው እናሳድገው ዘካ ንብረት ያሳድጋል እንጂ አይቀንስም ።
/channel/bahruteka
📍 ይህ የእድሜህ የመጨረሻው ረመዷን እንደሆነ አስበህ ፁም!!
🎙الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله
/channel/kurantejwid
🔷 ከንቱ ድካም
عن أبي هريرة – رضي الله عنه – قال أن النبي – صلى الله عليه وسلم – قال
” ربَّ صائمٍ ليسَ لَه من صيامِه إلَّا الجوعُ وربَّ قائمٍ ليسَ لَه من قيامِه إلَّا السَّهرُ “
أخرجه ابن ماجه
وصححه الألباني
🔹አቡ ሁረይራ ባወሩት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል : –
" ብዙ ሰው አለ ከፆሙ ረሀብ እንጂ የሌለው, ብዙ ለይል የሚሰግድ አለ ከመቆሙ እንቅልፍ ማጣት እንጂ የሌለው "
👉 ከዚህ የነብዩ ንግግር የምንረዳው አንድ ሰው ፆመኛ ሆኖ የተከለከለውን ካልተወ ( ከውሸት ንግግር ፣ ከውሸት ተግባር ፣ ከሐራም ነገሮች ፣ ከመሳደብ ፣ ከመላፋት እና የመሳሰሉት ካራቀ ) ማለት ነው ።
የውሸት ንግግር ሲባል ሽርክ ያዘሉ መንዙማዎችንና ነሺዳዎችን ያጠቃልላል ።
ለይል እየቆመ እንቅል ማጣት እንጂ ማለት ሶላቱ ኢኽላስ የሌለው ለዩልኝ ለዩስሙልኝ የሚሰግድ ከሆነ ነው ። የለይል ሶላት ጊዜው ከሪያእና ሱሙዓ የራቀ ቢሆንም ሰጋጁ ጠዋት ለሰዎች ማታ ትንሽ ስሰግድ ቆይቼ ነበር እንቅልፍ አለብኝ ካለ እዩልኝ ስሙልኝ ውስጥ ገባ ማለት ነው ።
🔹 የዚህ አይነት ሰው ሙሉ በሙሉ አጅሩን ያጣል ። ከሀዲሱ የምንረዳው የአጅሩን ሙሉነት እንደሚያጣ ቢሆንም ምክንያቱም ሐዲሱ ንያው ያልተስተካከለ ሰውን ስራ ስለሚያመላክት ። ከዛ አልፎ ወደ ተግባር ከገባ አጅሩ ከነአካቴው ይበላሻል ።
ሰርቶ መና ከመሆን አላህ ይጠብቀን ።
ቁምነገሩ ዒባዳ መስራቱ አይደለም ። ዋናው ዒባዳውን ከሚያበላሸው ነገር መጠበቅ ነው ።
/channel/bahruteka
ፈገግታ ሶደቃ ነው
~
አንዳንዱ የረመዷንን ቀናት ተኮሳትሮ ነው የሚያሳልፈው፣ በትንሽ በትልቁ እየተነጫነጨ። ወንድሜ! ሲርበው የሚነጫነጨው ህፃን ነው። "ርቦት ይሆን እንዴ? እስቲ ጡት ስጪው" ሲባል አልሰማህም?
አንተ ግን ህፃን አይደለህም። ፆም ዒባዳ ነውና በደስታ ፈፅመው። ፈገግታ አይለይህ። ፈገግታህ በራሱ አጅር የሚሸመትበት ሶደቃ እንደሆነ አይረሳ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
የሰዎችን ንግግር አጣመን አንረዳ
~
የሰዎችን የድምፅም ይሁን የፅሁፍ ንግግር በቀጥታ ነው መረዳት ያለብን። ቃላቱ ከሚሸከሙት ውጭ ሌላ ትርጉም መስጠት ተገቢ አይደለም። አንዳንዶች ግን ከሆነ አካል ጋር ልዩነት ሲኖራቸው ንግግሩን ሁሉ ጥላቻ ላይ ተመርኩዘው በክፉ መተርጎም ላይ ያተኩራሉ። ይሄ ለራስም አይበጅም። ዛሬ ማጠልሸቱ ሊሳካልን ይችላል። ግን የኋላ ኋላ ራሳችንን ነው የሚጎዳን። ሰዎችን ብንሸውድ አላህን አንሸውድም።
በራስ መንገድ አጣሞ በመተርጎም "በዚህ የፈለገው እኛን መንካት ነው"፣ "ለነ እከሌ መከላከል ነው"፣ "ጥቅም ፈልጎ ነው"፣ "እንዲህ ማለቱ ነው"፣ "እንዲያ ማለት አስቦ ነው"፣ ... እያሉ የግምት ትርጉም ከሰጡ በኋላ አቧራ ማስነሳት ጤነኛ አካሄድ አይደለም። ቃላቱ በቀጥታ የተሳሳተ ትርጉም የሚሰጡ ከሆነ ኒያው ከራሱ ጋር ነው። የተናገረውን እንጂ ያሰበውን ማወቅ አንችልም። ምን ማለቱ እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆን ግን በመሰለኝ ሰዎችን መወንጀል የለብንም። አንዳንዱ ሰው በባህሪው የመሰሉትን ነገሮች ከማስረገጥ ይልቅ ደምድሞ መናገሩ ይቀለዋል። ይሄ ልክ አይደለም። ካጠራጠረን "ምን ማለትህ ነው?" "እንዲህ ማለትህ ነው ወይ?" ብሎ መጠየቅ ቀላል ስራ ነው።
በጥፋት ለሚታወቁ አካላት መልካም ግምት እናሳድር እያልኩ አይደለም። ይሄ ሊሆንም አይገባም። ይህ ማለት ግን የማንንም ንግግር የፈለገ ብንጠላው እንኳ፣ በጥፋት የታወቀ ቢሆን እንኳ በራሳችን መንገድ እንተረጉማለን ማለት አይደለም። በማንም ላይ ቢሆን ፍትህን ልናዛንፍ አይገባም። ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል:-
{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ٰمِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ }
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ፡፡ ህዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡" [አልማኢዳህ: 8]
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor
ሶደቃ
~
በረመዷን ከሚወደዱ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሶደቃ ነው። የሶደቃ መስኩ ብዙ ነው። ለምሳሌ፦
* ምስኪኖችን ማብላት፣ መርዳት
* ወላጆችን፣ ዘመዶችን፣ ጎረቤቶችን ማገዝ
* ማስፈጠር (በተለይ ችግረኞችን፣ በየመጠለያው የወደቁ ተፈናቃዮችን፣ ...)፣
* ችግር ላለባቸው ሰዎች ስንሸጥ ከዋጋው ለቀቅ፣ ከእቃው መርረቅ ማድረግ፣
* ችግር ካለባቸው ሰዎች ስንገዛ ደግሞ በምንችለው መልኩ ማገዝ፣
* ሃኪሞችና ሃኪም ቤቶች ደካማ ታካሚዎችን ቢያግዙ፣ በነፃ ወይም በቅናሽ ቢያክሙ ትልቅ ሶደቃ ነው።
* ትራንስፖርት ላይ ለደካሞች መክፈል፣
* መኪና ያላችሁ ስጋት እስከሌለ ድረስ ሰዎችን ማሳፈር (በተለይ ደግሞ ነፍሰ ጡር የሆኑ፣ ልጅ የያዙ እናቶችን፣ አቅመ ደካሞችን፣ ... እያዩ ማለፍ አይገባም።)
* ቁርኣን፣ ኪታብ የሚፈልጉ ደካሞችን መርዳት፣
* መሻይኾችን፣ ኢማሞችን፣ ዱዓቶችን፣ እየለመኑ ዲን የሚማሩ ደረሶችን ማስታወስ፣
* ጂልባብ፣ ኒቃብ፣ የሚፈልጉ አቅመ ደካማ እህቶችን መርዳት፣ ወዘተ.
ሶደቃ ኢማን ይጨምራል። ልብን ያረጥባል። ወንጀልን ያረግፋል። የአላህ ውዴታን ያስገኛል። ደረጃን ከፍ ያደርጋል። በላእን ይመልሳል። ብቻ ሶደቃን አነሰ ብለን ሳንንቅ ያቅማችንን እንፈፅም። የትኛው ስራችን ጀነት ለመግባት፣ ከእሳት ለመራቅ ሰበብ እንደሚሆነን አናውቅም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
https://www.facebook.com/100028494635500/posts/343536176606201/?mibextid=lHq8ho93yyMVAwp7
Читать полностью…https://www.facebook.com/100064504847663/videos/536851044095599/?mibextid=lHq8ho93yyMVAwp7
Читать полностью…ነፃ ካልወጡ ነፃ አውጪዎች ተጠንቀቂ!
~
የፊታችን ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው አሉ፡፡ ወይ ፈረንጅ! አመቱን በሙሉ እኮ “የምንትስ ቀን” እያሉ ሊዘጉት ነው፡፡ ፈረንጅ ሲስል የሚስለው ሌላው ክፍል ነጩ ሰው “የግብረ ሰዶማውያን ቀን” ብሎ ቢጀምር ያለምንም ማመንታት ይከተላል፡፡ አሁንም ስላለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ብቻ ማርች ስምንትን ለሴቷ ሰጧት አሉ፡፡ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት!!”
እለቱን ሳስታውስ አንድ ነጭ አስተማሪ ስለ ሴቶች “መብት” እንቅስቃሴ እያወራ የተናገረው ነገር ከአመታት በኋላ ትዝ አለኝ፡፡ የሴቶችን መብት ካፋጠኑ ነገሮች አንዱ ብስክሌት ነው ነበር ያለው፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ይደንቀኝ ነበርና ኢንተርኔት ገብቼ ሳስስ ለካንስ ሀሳቡ የሱ ብቻ አይደለም፡፡ ይሄ ነገር ሰዎቹ ምን ያክል ቂ ሎ ች እንደሆኑ እና ነፃነት ሲሉም ግርማ ሞገስ ያለውን አለባበሷን ማስጣል እና በቤት እመቤትነቷ እንድትሸፍት ማድረግ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ብቻ አላማቸው የሴቶችን መብት ማክበር እንዳልሆነ ከሙስሊም ሴቶች አንፃር ያላቸው አተያይና ፖሊሲ በተጨባጭ አይን ላለው ሁሉ እያሳየ ነው፡፡ እርቃንነትን እስከ ጥግ እየፈቀዱ ሙስሊሟን ግን አለባበሷን ምክኒያት በማድረግ፣ ከትምህርት ገበታ፣ ከስራ ቦታ ማፈናቀሉን ተያይዘውታል፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ስለ ሴቶች መብት የሚያቀነቅኑት፡፡ ከባህልም ከሞራልም ያፈነ ገጡ አለባበሶች ላይ ትንፍሽ ሳይሉ ለሙስሊሟ ሲሆን ግን በየመንገዱ ይጎነትላሉ፡፡ አልፈውም ህገ-ደንብ ያወጣሉ፡፡ ፖሊሲ ያረቃሉ፡፡ ከዚያም አያፍሩም ስለ ሴቶች መብት ይደሰኩራሉ፡፡ “የምትለብሺውን እኔ ካልመረጥኩልሽ” ከማለት በላይ ምን አፈና አለ?!!
እህቴ ሆይ! ተጠንቀቂ!! ብዙዎቹ የሴቶች “ነፃ አውጪዎች” የሰይጣን ተልእኮ አራማጅ የሆኑ የሀሰት ጥሩ ንባዎች ናቸው፡፡ እውነት ተቆርቁሮልሽ እንዳይመስልሽ፡፡ ቢሆንማ ለእርቃን እሩብ ጉዳይ መሆንን ፈቅዶ መልበስሽን ለምን ይቃወምሻል?! እውነት ለመብትሽ ተሟጋች ከሆነ ስትራቆቺ ገልፍጦ ስትለብሺ ለምን ደሙ ይፈላል?! ለምንስ በየመንገዱ ይጎነትላል?! ለምንስ ከየተቋሙ ያባርራል?! እመኚኝ “ነፃ ውጪ” የሚለው በየጎዳናው በነፃነት በነፃ ወይም በርካሽ እንዲያገኚሽ ነው፡፡ አስተውይ! ልብስሽን ስለጣልሽ ነፃ አትወጭም፡፡ ነፃ መሆን ልብስ በመጣል ከሆነ ነፃ ሰዎች ማለት እብ - ዶች ናቸው፡፡ የሚጮኸው ስለ ክቡር ማንነትሽ ሳይሆን ስለ እርቃን ገላሽ ነው፡፡ የነቁበት ነቅተውበት እየተመለሱ ነው፡፡ ይሄውና በምዕራቡ አለም ከሚሰልሙት ውስጥ 80% ሴቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች ለሀጫቸው የሚዝረበረብለትን የምዕራቡን “ነፃነት” ሸሽተው ወደ ኢስላም “ጭቆና” ይጎርፉ ይዘዋል፡፡ በጊዜ ንቂ፡፡ ብልጥ ማለት በሌሎች ላይ ከደረሰው ቀድሞ የሚማር ነው፡፡ ምሳሌሽን በትክክል ምረጪ፡፡ በአኢሻ ስብእና እያፈርሽ አሊሻን መሆን ካማረሽ ግን ግፊበት፡፡ ጀሀነምን የሚቋቋም ገላ ካለሽ መንገዱን ጨርቅ ያርግልሽ፡፡
ንቂ! ያለበለዚያ ይሄ በስጋዊ ፍላጎት የታወረው “ጠበቃሽ” የኮንዶም ማስታወቂያ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ! ያለበለዚያ ይሄ ካንገት በታች እንጂ ካንገት በላይ የሌለው ርካ ሽ በ ድ ን ከምንም በታች አርክሶሽ የሱ ርካሽ ሸቀጥ ማሻሻጫ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ! ሙስሊም ወንድምሽ ስለበደለሽ በኢስላም ላይ ብታምጪ ኢስላምን ቅንጣት ታክል አትጎጂውም፡፡ ብቻ በዱንያም ላታተርፊ ሁለቱንም አገር የከሰርሽ ከሁለት ያጣሽ ትሆኛለሽ፡፡ እራስሽን ሁኚ፡፡ የገደል ማሚቶ አትሁኚ፡፡ ሌሎች ስለሳሉ አትሳይ ስላነጠሱም አታነጥሺ፡፡ የተፈጠርሺው ለክቡር አላማ ነው፡፡ አላማ ቢስ አትሁኚ፡፡ ያለበለዚያ ኮምፓስ እንደሌለው መርከብ ዋለሽ ዋለሽ አስከፊ ፍፃሜ ላይ ትደርሻለሽ፡፡
ተጠንቀቂ!! ከሸሪዐው አጥር ውጭ ያለ የመብት ጥያቄ አትጠይቂ፡፡ የፈጠረሽ ጌታ አንቺ እራስሽን ከምታውቂው በላይ ያውቅሻል፡፡ ላንቺም ከተኩላው “እንባ ጠባቂ” ቀርቶ ከራስሽም በላይ ያዝንልሻል፡፡ ደግሞም አትዘንጊ፡፡ ህይወት ማለት የአኺራ ህይወት ነው፡፡ አላህ አድሎሽ ሰማንያ ዘጠና አመት ብትኖሪ እንኳ በጊዜ ከኢስላም ባቡር ውስጥ ካልተሳፈርሽ ሲመሽ ይቆጭሻል፡፡ ምን ብትኖሪ ህይወትሽ መጨረሻ አለው፣ ሞት፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ዘላለማዊ ህይወት፡፡ የዛሬው ቅቤ አንጓች “እንባ ጠባቂ” ተኩላ ግን የአኺራ ምንነቱም አይገባውም፡፡ ለዚያ ቀርቶ ለዱንያ እንኳ ጤነኛ ህልም የለውም፡፡ ለአኺራማ እንኳን ላንቺ ለራሱም አይሆንም፡፡ የአህያ ባል ከጂብ አያስጥልም፡፡ ለናቱ፣ ለሚስቱ፣ ለልጁ፣ ለእህቱ የማይሆን ሰካ - ራም ነፃ ያወጣኛል ብለሽ ከገመትሽ የመጨረሻ ቂ ል ነሽ፡፡ እሱ እራሱ በስሜቱ የሚገዛ የስሜት ባሪያ ሆኖ በየትኛው ሞራሉ ነው አንቺን ነፃ የሚያወጣሽ?! ቀድሞ ነገር ምን ሲደረግ ለሰካ - ራም ጆሮሽን ሰጥተሽ?! ቦታ ከሰጠሽውማ የአለም እዝነት የሆኑትን ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠላትሽ እንደሆኑ ቀስ እያለ እያዋዛ ያሰርፅብሻል፡፡ በጊዜ ካልነቃሽ መውጣት ከማትችይበት የስሜት አሮንቃ ውስጥ ይነክርሻል፡፡ በደጋሚ ምላሱ ጭንቅላትሽ ላይ ተብትቦብሽ የስሜት ባሪያ ሆነሽ ረክሰሽ፣ ከማንም በላይ ብቁና ንቁ የሆንሽ ይመስልሻል፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ስለቀረበ እንዳያታልልሽ፡፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ሐያእሽ ባለመሟጠጡ በግልፅ ባታወጪው እንኳ ውስጥሽ ለኢስላም ይደፈርሳል፡፡ ለነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ያለሽ ክብርም ምናልባት ካልጠፋ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ግን እስቲ እኔ ልጠይቅሽ፡ እውነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላንቺ ስለማይቆረቆሩ ነው ከመቶ ሺ በላይ ሶሐቦቻቸው በተሰበሰቡበት ታላቅ ቀንና ታላቅ ቦታ ላይ “የሴቶችን ነገር አደራ” እያሉ አዋጅ ያሰሙት? እርግጥ ነው ብዙ በደል አለብሽ፡፡ ግን አስተውይ ከበደሎቹ ሁሉ የከፋው ዘላለማዊ ክብር የሚያጎናፅፍሽን ኢስላምሽን እንዳታውቂ መደረግሽ ነው፡፡ እናም እልሻለሁ፡ በኢስላም ከኢስላም መብትሽን ፈልጊ፡፡ ለወዳኛው ህይወትሽም ትጊ፡፡ የተኩላ ሰለባ እንዳትሆኚ ንቂ፡፡ የአላህ ሰላም ላንቺ ይሁን፡፡
(ኢብኑ ሙነወር)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
/channel/IbnuMunewor
عيدكم مبارك!
تقبلﷲ منا ومنكم صالح الأعمال!
ኢዳችሁ የተባረከ ይሁን! አላህ ከኛም ከናንተም መልካም ስራችንን ይቀበለን!
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ
ከረመዷን በፊት ወደነበርክበት አመፅና ወንጀል ለመመለስ በማኮብኮብ ላይ ያለህ ወንድሜ ሆይ ! አላህን ፍራ! የረመዳኑ ጌታ የተቀሩት ወራቶችም ጌታ ነው ... አሏህን ፍራ!
ፈጣሪህን በመፍራት የታዘዝከው በዚህ ወር ብቻ አይደለም ... ከፀያፍ ነገሮች መራቅ የእድሜ ልክ ግብ እንጂ የአንድ ወር አላማ አይደለም !
ሁሌም ለአላህ እጅ የሰጠህ ሙስሊም ለመሆን ታገል ...
ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ
وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّى يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡
/channel/Muhammedsirage
https://www.facebook.com/100079752493752/videos/1434363997371958/?mibextid=FG1OuXcoECp1WxxK
Читать полностью…* [ ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ] *
••••••••••••••••••••••
የፊታችን እሁድ ሚያዚያ 1 / 2015 በወራቤ ከተማ አቡ በክር መስጂድ ታላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ይጠብቀዎታል በእለቱም :-
(1) ሳዳት ከማል (አቡ መርየም)
(2) ሙሐመድ አሕመድ (ኢብኑ ሙነወር)
(3) ሙሐመድሲራጅ ሙሐመድኑር (አቡ ዒምራን) እና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ይሳተፋሉ።
🌐 /channel/Abulbuhari
👉 የረመዳን ግማሽ
<==========>
💡ሰዎች አላህ ያዘዛቸውን ሰርተው ሳይጨርሱ ወደ አላህ እንቃረባለን እያሉ አዳዲስ ፈጠራዎችን ያመጣሉ። በእስልምና ዲን ወደ አላህ እቃረብበታለሁ ተብሎ የሚሰራ ማንኛውም ስራ ከቁርኣንና ሐዲስ መረጃ ሊኖረው ይገባል ካልሆ ስራው ወደባለቤቱ ተመላሽ ነው አላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም።
➩ በአብዛኛው በእስልምና ላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን አላህን በመገዛትና ወደርሱ በመቃረብ ስም የሚያመጡት ራፊዳዎችና ሱፍዮች ናቸው።
➺ እነዚህ አካላት ካመጡዋቸው ቁጥር ስፍር የሌላቸው አዳዲስ ፈጠራዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የቀብርና የሙታን መንፈስ አምልኮ ፈጠራ ነው።
➫ ይህ ከእስልምና የሚያወጣና የዘላለማዊ ጀሀነም ባልተቤት የሚያደርግ የኩፍር ተግባር ነው። ታዲያ እነዚህ በኢስላም ስም ሙስሊሙን የሚያከፍሩ አካላት እነዚህን የኩፍር ተግባራት የተለያየ ስም በመስጠት እንጂ ፊት ለፊት ይዘው አይመጡም።
➡️ ለቀብርና ለሙታን መንፈስ አምልኮት ከሚሰጡዋቸው ስሞች አንዱ ረመዳን ግማሽ ( نصف رمضان ) የሚል ነው። ከዚህ የሚፈልጉት በረመዳን 15 የአምዋት ( ጀምዑ መይት) ቡና በሚል ወደ ሙታኖች ደም በማፍሰስ ለመቃረብ የሚታረድ እርድ ነው።
➽ ይህ ተግባር (ደም በማፍሰስ) ትልቅ የአምልኮ ክፍል ሲሆን ለአላህ ከሆነ በጣም ትልቅ ዒባዳ ነው። ነገር ግን ሸሪዓ ባላዘዘው መልኩ ጊዜ ገድቦ ከተደረገ ለአላህ ተብሎም ቢሆን ቢዳዓ ነው። ከአላህ ውጪ ላለ አካል ከሆነ ግን ከእስልምና የሚያወጣ ኩፍር ነው።
✅ አምዋት በየትኛውም ወርና ቀን ቡና አያስፈልጋቸውም ሱስም የለባቸውም። ነገር ግን ደካሞችን በእምነታቸው መፈተን የሚፈልጉ የኢስላም ጠላቶች የህፃን ፀጉር ሽበት የሚያስበቅልን የኩፍር ተግባር ቀለል አድርገው ስም ቀይረው ሙስሊሙን ይግቱታል።
➲ ረመዳን ግማሽን ከሌሎች ቀናቶች በተለየ መልኩ የሚደረግ ዒባዳ የለውም። በመሆኑም የረመዳን ግማሽ በሚል ወደ ሙታን ለመቃረብ የሚደረገው እርድም ሆነ ሌሎች የትኞቹም ተግባራት እስልምናችንን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚከት ስለሆነ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
➫ አንድ ሰው በዚህ ቀን አጥቼ ነው እንጂ ለአምዋት አርድ ነበር ወይም ቅርጫ እገባ ነበር ብሎ ኑፍሮ ቢቀቅል አርዶ ወደ ሙታን እንደተቃረበ ሰው ነው።
አዳዲስ ፈጠራ ከማምጣታችን በፊት የታዘዝነውን ሰርተን እንጨርስ። አላህ ለሚወደውና ለሚፈቅደው ይወፍቀን።
➘➘➘
/channel/bahruteka
በደል እና አደጋዎቹ
~
ዛሬ ረመዷን ዐ4/1444 በወለቴ ሑነይን መስጂድ የተሰጠ ምክር
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me//IbnuMunewor
" #በፆሙ_ልጄን_ብቻዬን_መፈለግ_ከበደኝ😭" አባት
ህፃን #ማሂር ሳይገኝ #2ወራት ተቆጠሩ‼️
#የት_ሄደ??? #ምን_ሆነ???
ጋምቤላ ሜቲ ከተማ ጥር16 ከቀኑ 8ሰዓት አካባቢ እናት ተጂያ ቤት ውስጥ ሆና ያመለጣትን ዙህር ሶላት እየሰገደች የ2ዓመት ከ6ወሩ ተወዳጅና ብቸኛ ልጇ #ማሂር_ሰይድ ደግሞ ግቢ ውስጥ እየተጫወተ
"ባባ ባባ"ሲል እናት የሰማችው ቢሆንም ሲጫወት ወድቆ ነው በሚል ሀሳብ ሰላቷን ጨርሳ ስትወጣ ማሂር ቦታው ላይ የለም😭
እናትና አባት ስራቸውን ትተው ወደ ቤታቸው ሳይገቡ ያለፉትን 2ወራት ፖሊስጣቢያና በየከተማው ለፍለጋ ቢሰማሩም እስካሁን አየን የሚል ሰው አላገኙም!!
እባካችሁን #እየፀለይንላቸው #ሼር በማድረግ እንረባረብላቸው🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
0911334363-ሰይድ(አባት)
0917753035-ሁሴን
0910161697-ሰይድ
🔹 ፆመኛን ማስፈጠር
عن زيد بن خالد الجهني – رضي الله عنه – قال :- قال رسول الله – صلى الله عليه وسلم
"من فطَّر صائمًا كان له مثلُ أجره، غير أنه لا ينقصُ من أجر الصائمِ شيئًا"
أخرجه الترمذي وقال حديث حسن صحيح
↪️ ዘይድ ኢብኑ ኻሊድ አል ጁሀንይ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል፦
"ፆመኛን ያስፈጠረ ሰው የፆመኛው አይነት አጅር አለው። ይህ ከፆመኛው አጅር ምንም ሳይቀንስ ነው።"
/channel/bahruteka
የረመዷን ጨረቃ ባለመታየቷ ኢንሻ አላህ ረመዷን የመጀመሪያው ቀን ሀሙስ ይሆናል
ረመዷን ሙባረክ
/channel/medresetulislah
እንዲህ አይነት ጠንከር ያለ ኩርኩም ያስፈልገናል።
ሸይኽ በድር ብኑ ዐሊይ አልዑተይቢይ
ትላንትም ደም ነው ሲያስፈስሱ የነበረው። ዛሬም ነው ደም ሲያስቀዱ የነበረው !
ሰመሀር ተክሌን ተጠንቀቁት !
🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ
/channel/Darutewhide
➪ታላቅ ምክር !!
___
𒊹︎︎︎የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቁ የዘመናችን ሼይኽ
ዶ/ር ሷሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን ሐፊዘሁሏሁ ወረዓሁ የሰጡት ልባዊ ምክር!!
☞︎︎︎ተጠየቁ:-
____
“የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?
ما نصيحتكم بمناسبة اقتراب شهر رمضان؟ الشيخ صالح الفوزان حفظه الله
السؤال : ما نصيحتكم للمسلمين بمناسبة اقتراب شهر رمضان؟
“𒊹︎︎︎የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”
الجواب:
الواجب علىالمسلم يسأل الله أن يبلغه رمضان وأن يعينه على صيامه وقيامه، والعمل فيه،
☞︎︎︎"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት።
لأنه فرصة في حياة المسلم: مَنْ صَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ، مَنْ قَامَ رَمَضَانَ إِيمَانًا وَاحْتِسَابًا غُفِرَ لَهُ مَا تَقَدَّمَ مِنْ ذَنْبِهِ ،
𒊹︎︎︎ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው። ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ:-
𒊹︎︎︎‹‹ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል። ‹‹ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል››
فهو فرصة في حياة المسلم قد لا يعود عليه مرة ثانية.
☞︎︎︎ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው።
فالمسلم يفرح بقدوم رمضان ويستبشر به، ويستقبله بالفرح والسرور، ويستغله في طاعة الله ليله قيام، ونهاره صيام وتلاوة للقرآن والذكر فهو مغنم للمسلم،
➪ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው። ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።
أما الذين إذا أقبل رمضان يعدون البرامج الفاسدة والملهية والمسلسلات والخزعبلات والمسابقات ليشغلوا المسلمين فهؤلاء جند الشيطان، الشيطان جندهم لهذا،
𒊹︎︎︎ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ።እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው።
فعلى المسلم أن يحذر من هؤلاء ويحذر منهم،
➪አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።
رمضان ما هو وقت لهو ولعب ومسلسلات وجوائز ومسابقات وضياع للوقت.
𒊹︎︎︎ረመዳን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"
🤲አላህ የረመዳን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን
የሸይኹን ነሲሓ ቀጥታ ካንደበታቸው ለመስማት ሊንኩን ይከተሉ⤵
http://alfawzan.af.org.sa/sites/default/files/29_7.mp3
☞︎︎︎ሼር በማድረግ ሌሎችንም የምክሩ ተካፋይ እናድርግ።
ጠቃሚ ፅሑፎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
☟︎︎︎☟︎︎︎☟︎︎︎☟︎︎︎
𝐓𝐞:/channel/dawatulanbiya
የሰለፎች ሁኔታ በረመዷን ውስጥ
①) የሰለፎቻችን ረመዷን አቀባበል
②) ረመዷን ውስጥ የነበራቸው ጥረት
③) ረመዷን ካለቀ በኋላ ሁኔታቸው
🎙በ አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
/channel/Sadik_Ibnu_Heyru
እዳን በሌላ ሀገር ብር መክፈል ብይኑ ምንድን ነው
Читать полностью…አዲስ ወደ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ወንድም እህቶቻችን ከታች ወደተዘረዘሩት 9 ዩኒቨርሲቲዎች የምትገቡ በሊንኩ በመግባት የተቀባዮችን አድራሻ ማግኘት ትችላላችሁ!
ወንድም እህቶቻችሁ፦
- ጊቢ ስትገቡ ዶርማችሁን በማሳየት
- ሙሉ ምዝገባ በማስጨረስ
- መስጂድ በማሳየት
- በትምህርት ጉዳይ በመርዳት
- በተለያዪ ጉዳዮች በመርዳት ያግዟችኃል።
ችላ ሳትሉ ቀድማችሁ በመደወል አመቻቹ!!!
N.B እህቶች ደግሞ የእህቶቻችሁን አድራሻ ወንድሞችን በመጠየቅ ማግኘት ትችላላችሁ።
አድራሻቸው የተገኙት በሚከተሉት ዩኒቨርሲቲዎችየሚገኙት ናቸው።
1ኛ ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6523
2ኛ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6524
3ኛ ደብረማርቆስዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6529
4ኛ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6537
5ኛ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6541
6ኛ ወራቤ ዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6553
7ኛ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6556
8ኛ ወሎ ዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6560
9ኛ ወለጋ ዩኒቨርስቲ
➘➘➘➘➘
/channel/AbuImranAselefy/6563
በአላህ ፍቃድ የሌሎችንም ለመልቀቅ እንሞክራለ።