66224
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
ምን ቢርበው ላሙን
ምን ቢርበው ዘሩን አይበላም ገበሬ ፤
እኔስ ጨከንኩና
ቆርጥሜያት አደርኩኝ ነፍሴን እንደ ጥሬ ።
By Tedros kassa
@getem
@getem
@paappii
ና ገነትን እንኑራት…………..
ከርምጃህና እርምጃዬ
ከትከሻህና ትከሻዬ
ከሸባበተዉ ፀጉርህና ጠጉሬ መሀል
የመላዕክት ዝማርያቸዉ ይሰማሀል?
ምርኩዝህን አይተሀዋል እንደሙሴ…………
ድካምህን
ወንድነትህን
ማጣትና ማግኘትህን
አሉባልታ ስሜትህን
ከፈልክበት
ተሸለምከዉ ተደገፍከዉ።
ማርያምን ስወደው ሽብሽብ ገፅህን
የፈዘዘዉ ቅንድብህን
የጐደጐደዉ አይንህን
እኔልሙት……..
ስትስቅ እኮ ምድር ቀዉጢነዉ ምትሆነዉ
ደመና ሳቋን - መቆጣጠር አቅቷት
ዝናቧንም የምትለቀዉ።
ና ገነትን እየኖርናት
ነፋሴና ነፍስህ ይሙቃት
ትዝታ ወልዴ✍️
@Tizita21
@getem
እኔ አፍቅሬያት ሌላ አፍቅራ
እሱም ቀርቶ ወልዳ አግብታ
እያየሁ
እቀናለሁ
ባለፈው ትላንቷ በዛሬው እኔነቴ
እቀናለሁ ጅልነቴ
አወየው ጉዳቴ አወዬው ፈተና
አትታደል ፍቅር ተብያለሁ ቅና
ካንድ አምላክ ቸርነት ብማፀን ብጠና
እኔው ባወራኋት በኔው እቀናለው
ወዳታለሁና
እኔ አፍቅሬያት ሌላ አፍቅራ
አወየው ጉዳቴ አወየው መከራ
ዮኒ
ኣትን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
አበባዬ ብዬ አላሸታት ነገር
ወይ ውሃ አላጠጣት አላስታቅፍ አፈር
ወይ አትመጣ ከኔ ፍቅሬን አልናገር ...
ጠረኗ አልደረሰኝ ሆና ከሩቅ ሀገር
ግና ቆም ብዬ ሳስበው
እሷ ንግሥት ሆና ሀገሬን ብታየው
እኔ ንጉሥ ሆኜ ጠረኗን ብምገው
አበባዋን ቀጥፋ
ተፈጥሮውን ለየው ብላ ብጠይቀኝ
አሳያት ነበረ ያ ጠቢብነቴን
መስኮት ዳር ወስጄ በጠረኑ ብቻ ንብ መንጋ መጥራቴን
by ዳግማዊ@Dagimawisisay
@getem
@getem
@paappii
እርግማን ነው
////////////////
አፈር ይብላው፣
ያ ገላሽን
መቼስ እንደው አይቀርለት፣
እርጅና ይብላው፣
ያ መልክሽን
እሱም እንደው አይቀርለት።
መርገም አላውቅ
መንገድ ጠፋኝ፣
አንችን ብዬ
ሳላገኝሽ በጣም ከፋኝ፣
ልራገም ነው በይ ተቀበይ፣
ልብሽ እንደው
እኔን አንዴ ባፈቀረኝ።
እርግማን ነው አትሳቂ፣
ሳያገኙ ማፍቀር
ህመሙን እወቂ።
እርግማን ነው
ብሸዬሽ የለ፣
ቂም እንደሆን በፍቅር የለ።
ያኔ ድሮ
ገፍተሽኛል አዎ አውቃለሁ፣
ይህ እርግማን ሲደርስብሽ
ቂሙን ትቼ እወድሻለሁ።
ሞኝ አደለው።
@abela_black
@getem
@getem
@getem
አሜን በይ ልመርቅሽ
ቆሻሻው ተቃጥሎ ሀገር ምድሩ ፀድቶ
ታፍኖ የቆየ ፍቅር አገርሽቶ
በጦቢያ ምድር ህዳሩ ሲታጠን
በለተ ሚካኤል አሜን ሰላም ይስጠን::
አሜን!
ሰላም ውሎ ይደር ቀዬው አድባሩ
ከመስጊዱ አዛን ቅዳሴው ከደብሩ
አይስተጓጎሉ ኬር ሆኖ መንደሩ::
አሜን!
አቦል ጀባ ጀባ ቶና እና በረካ
አቦ ሀጃ ይውጣ ጠጥተን እንርካ
ኑሯችን ይስመር እንደ ፅጌ ይፍካ::
አሜን!
አሜን በይ ይሁን ከአሜን ይቀራል
የከረመ በቀል በፍቅር ይሻራል!
ቤትሽ ፍቅር ይሙላው ካምናው እጥፍ አርጎ
ውልቅ ይበል ችግር ማጣት ተጠራርጎ::
አሜን!
ልጆችሽ ይደጉ በእውቀት በምግባር
ሰውሮ ያቆያቸው ከጦርነት ግንባር
አሜን ልብ ይስጣቸው የሚታይ በተግባር::
አንደበትሽ ይጣፍጥ የነካሽው ይብዛ
ያንቺን ስራ አይቶ ሰውዘር አደብ ይግዛ::
አሜን!
By @Abuugida
@getem
@getem
@paappii
እንደ ፍያታዊ መስቀል
ተቀብሮ እንደተረሳ
ወይ እንደ መበለት ቀሚስ
ተሰጥትቶ እንዳልተነሳ
ኖርኩ ለማለት ያህል
የ-የዕለት ሌት እያነጋሁ
እንዲሁ በዝምታ እንደረጋሁ !
ያው የ ሰማንያ እድሌን
ከህይወት ሳልጠጋ ብቻዬን
የምቀር ይመስለኛል
By Bo Hamian
@getem
@getem
@paappii
እነዚያ ቀናቶች.......
በትዝታ ማህደር ያጠራቀምናቸው፤
ትላንት፣
ከትላንት ወዲያ፣
አምናና ካች አምና
ብለን ምንጠራቸው፤
ትዝ አሏቹ አይደል? ያለቀስንባቸው፤
በተስፋ ተሞልተን ጎንበስ ያልንባቸው፤
ክፉንም ደጉንም ስንት ያየንባቸው........
አይገርምም?
ጊዜ ዳኛ ሆኖ ይኸው ዛሬ አለፉ
በትዝታ ገፅ ላይ ደብዝዘው ተፃፉ::
ተመስገን!
By @Abuugida
@getem
@getem
@getem
የቀይ አስኳል ፍም ገላ
የልጅነት ምጥን ቅጠል
አንቺን ነክቶ ማስመለስ ነው
ሲያድሩ ውለው ለመቃጠል
የለሆሳስ አዝራር ድምፅ
የዝግታ ውበት ካላ !
ያንቺን መርጋት የሚያክል
ሌላ ኩሬ ወዴት አለ ?
ክንዴ ስር ያለው ሙቀት
አንገትሽ ነው የሚያውሰው
ወዝ ሆኜ መልካም ጠረን
ካንቺ ሌላ ማን አዋሰው
ይሄ እግሬ በረድ ሆኖ
ሌቱን ሙሉ ሚቀዘቅዝ
ያንቺን ትንፋሽ እስኪያነቃው
ከብርድ ጋር ይቋመራል
በእንቅጥቅጥ የእርክዝ
'
'
@geez_mulat🦘
ግዕዝ ሙላት
@getem
@getem
@getem
ጥቁር እሳት
እ..ፍ🔥 እ..ፍ💧
አጥፉት ሳቱን
ሊያቃጥለን ከደጅ ደርሷል፣
አፈር አምጡ ወይም ቅጠል
ውሃ ያልነው ሰደድ ሆኗል ፣
እባካችሁ አትጩኹ
ፀጥታ ነው የሚያጠፋው፣
ድብልቅልቅ መሆኑ ነው
ጩኸታችን ሚያኮላትፈው፣
( አንቺ ሴት )
እሪ አትበይ ከጥግ ከጥግ
አትለውጭም ምንም ለእሳት ፣
አንድያውን ካገር መጥፋት
ወይም አፈር ቅጠል ማንሳት ፣
አትቅለስለስ ጎረቤቴ
አትደበቅ ካልሆነ ፍም ፣
ቀን ይፈጅ ይሆን እንጅ
ይሄ እሳት ካንተ አያልፍም ፣
(አንተ )
'
አልጋ ስር አትደበቅ
እንዳልሰማ ጩኸታችን ፣
እሳትህ ነው አይባልም
እኔ ስልህ እሳታችን ፣
የችግኝ ዛፍ ቁረጭልኝ
ባገር በዝቷል ቅጠል ችግኝ ፣
እሳቱ ጋር አለሁበት
ከለምለም ጋር አትፈልጊኝ ፣
ባንድ ሰፈር ጎጆ ሰርተን
የኔ ደጅ ላይ ቢቃጠልም ፣
እሳት ሲባል ተጓዥ እንጂ
በተናጥል አያቃጥልም ፣
የከመርኩት የጤፍ ቦታ
ቀድሞ ከእኔ ቢያስርበኝም፣
የጎረቤቴ ዝምታ እንጂ
ራህብማ አልጎዳኝም፣
አይደርስ መስሎት ሰደድ እሳት
እንደለኮስኩ ለሰው አማኝ ፣
ቢነደኝ ነው የእሳት እሳት
ሳያወድመኝ የሚያጣቃኝ ፣
እፍ በይ ይሄን እሳት
እፍ በለው ተባበረኝ፣
ዘንቦ እስኪቆም የእግዜር እንባ
የውሃ አምላክ እስኪፈርደኝ ፣
..............ለዚህ እሳት ዕንባ አውሰኝ፣
ግዕዝ ሙላት 🦘
@geez_mulat
@getem
@getem
@getem
ማነሽ?
.
የነፋስ ኃይል
እንደጣላት ቢጫ ቅጠል
በመኖር ዳር እጣ ጥዬ
በርጥብ መሬት ተንጋልዬ
አፈር ሆኜ ለመሬቱ
ትንፋሽ ሆኜ ለዋሽንቱ
ስንት ዘመን ስንት ጊዜ
ብኩን ጥላ
የምታቀፍ
በተስፋ ስም የሞት ገላ
ስንት ንጋት
የምደገፍ?
ምነው ህይወት ምንድን ፍቺ
ምነው ጊዜ ማነሽ አንቺ
፡፡፡
ሲራክ ወንድሙ
@getem
@getem
@getem
ባካል ከማያቃት በፍቅር ተይዞ
እድለኛ ልቤ ያፈቅራል ተጉዞ
ባካል ላላወቃት ሲገባ ሲወጣ
እድለ ቢስ ልቤ በእንቢታ ተቀጣ
ሰርክ ላይተው ማፍቀሩን
ሰርክ ላይተው መውደዱን
እምቢታውን ታቅፎ
ይኖራል የግዱን።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
Share @Yonny_Athan
Share @Yonny_Athan
ወግና ትዉፊት
------------------
የማይስማማ
ቢሆንም ወግ አጥባቂ፣
ለገላጋይ አይሉት
ለልጅ አዋቂ፤
ጥሩ ነዉ ቢባል
ወይም ጠቃሚ፣
የማይለወጥ
ሀሳቡ ቋሚ፣
ቢሆንም እንኳን
በጥብቅ ባህል
የኖረ በፊት፣
የቀን ጉዳይ ነዉ
መሸራረፉ
ወግና ትዉፊት።
@getem
@getem
@paappii
አሜን አለሜን~~
ልበል አለሜን አየሁ
ነግቶ ሆነሽ ከጎኔ፣
ነቅቼ ወፎች ተንጫጭተው
ሳየው አይንሽን 'ባይኔ።
ልበል አሜን አሜን
ነግቶ ሆነሽ ከጎኔ፣
ፀሀይ ብርሀን ፈንጥቃ
ሳየው አይንሽን 'ባይኔ።``````````````````````````
Sep. 16, 2021, 12:31 PM
by Daniel @DannyShy
@getem
@getem
@getem
የፍቅር ሙከራ
---------------------
አንድ አንዱ ለፍቅር
ይጀምራል በቃል፣
በአይኑ ተመልክቶ
ፍላጎቱ ያልቃል፤
ሌላኛው ይለያል
በትንሽ ደባብሶ፣
ነካክቶ ሳይቀምስ
ይሄዳል ጨራርሶ፤
ያንቺ ግን ሙከራ
ከሁሉም ይልቃል
ከሁሉም ይብሳል፣
ከአብሮ መዋል አልፎ
መተኛት ይደርሳል።
@getem
@getem
@paappii
ልብሱ
ጫማው
ጌጡ ቀርቶ
እህል እንኳን ሳልገዛልሽ ፤
ስለ ዐይኖችሽ
ስለ እጆችሽ
ስለ እግሮችሽ ሳልፅፍልሽ ፤
ሳልጎበኝሽ
ሳልሰልልሽ
የኾንሽውን ሳልጠይቅሽ ፤
እንዲሁ . . . እንዲያው . . . እንደማንም ፤
እንደ ተራ . . . እንደ ምንም ፤
ድምፄን ውጬ ዝም ስልሽ ፤
ረስቼሽ እንዳይመስልሽ ።
፡
ባይልልኝ ነው አበባዬ ፤
ባይሆንልኝ
ባይሞላልኝ ፤
ከዕንባ በቀር በልቤ ላይ
ሌላ ገንዘብ ባይቆይልኝ ፤
እንጅማ አንቺን ፤
እመቤቴን ፤
እንዴት ብዬ እረሳለሁ !?
ቀን በውኔ
ሌት በሕልሜ
ትዝ እያልሽኝ አለቅሳለሁ ፤
ብቻ አንድ ቀን
ሞት ካልለየኝ ፤
ያ ጨለማ ካልቀደመኝ ፤
ዕምባ አርግዤ ብቅ እላለሁ፤
እጆችሽን
እግሮችሽን
ዐይኖችሽን እስማለሁ ፤
ከአንቺ ርቄ የሆንኩትን
አንድ በአንድ ነግርሻለሁ ፤
ወድሻለሁ
ወድሻለሁ
ወድሻለሁ
። ። ። ። ።
By Tedros kassa
@getem
@getem
@paappii
አዲስ ቃላት አይደል
ወይም አዲስ ግኝት
እኔ አንቺን ማፍቀሬ
ከቶ አይደለ ጥፋት
ንገሪኝ ከሆድሽ ያለሽን አውጥተሽ
ላግኝበት ሰላም
ከሴት ሁሉ ልሽሽ
አትስጊ ንገሪኝ ልቤ ይችለዋል
ስምሽን በመቅበር ዘግቶ ያኖረዋል
የለመደሽ ጎኔ ሁል ጊዜ የሚያቅፍሽ
ሳያገኝሽ ሲቀር ቢልብኝም ኩምሽሽ
እጠነክራለሁ ምን አማራጭ አለኝ
ከአዳምነት አልሸሽ።
by ዳግማዊ@Dagimawisisay
@getem
@getem
@getem
ተቁነጥንጣ ቀረበችኝ
ተቻኮለች እንዳፈቅራት ፣
ተጨነቀች ወዲያው ደሞ
ተቻኩየ ስላቀፍኳት ፣
ትፈጥናለች ለማግኜት
ልቤን አርጋው የቀበሌ ፣
ታምር አርጋ ቆጠረችው
በእሷ ፍቅር መቸኮሌ ፣
መቸኮልን አስለምዳኝ
ተጣድፎ ዝግታየን
አቻኩላ አገባችኝ
እይ ስትል እድሜየን ፣
ተቻኩላ አስለምዳኝ
ረጋ ያለ አረማመድ ፣
ተቻኩየ ጥያት ሄድኩኝ
ቀድማ ከእኔ እንዳትራመድ ፣
@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት 🦘
@getem
@getem
@paappii
ስወድሽ ተረታሁ
በደቂቅ ደቃቁ
ግርማነቴን ጣሉት
ወረድኩ ከሰንደቁ
ስወድሽ ወደኩኝ
ኮኮቤ ነሽ ብዬ ኮኮብ አሰቀልኩኝ
ኮከብነትሽም አልፈየደም አንድም
አንቺም ታደያለሽ ወደራስሽ ግድም
ስወድሽ ተደፋሁ
ይሁን ባልኩኝ ባለም... ተከፋሁ
አይቼ እንዳልገባኝ ስንት ነገር ገፋሁ
ልብሽ ላይፈልገኝ ሁሌ እየነገርሽኝ
በፈገግታሽ ብቻ የግልሽ አረግሽኝ
ስወድሽ አስመሰልኩ
መልስሽን ወሬሽን እንዳላወኩ መሰልኩ
ፍቅር ይሻል ብዬ እያየሁኝ ታዘብኩ
ፈገግ እንዳልገባኝ
ፈገግ እንዳላወኩ
በማስመሰል ንዳድ
በድርጊትሽ ታወኩ
ስወድሽ ተረታሁ
አንቺን ማጣት ፈራሁ
አብዝቼ ፈለኩሽ
አብዝተሽ ገፋሺኝ
አታውቂውም እንጂ እንዲህ ነው ያደረግሽኝ
መለስ ወደኋላ
መለስ ወደፊቴ
የጠቀመሽኝ መስለሽ ገለሺኛል ስንቴ
በበፊት ነገርሽ ዛሬን አግኝተሻል
ዙፋን ላይ ወርጄ ዙፋን ላይ ወተሻል
ጊዜ አይመጣም ብለሽ ጊዜሽን ወስደሻል
ጊዜ ተገልብጦ ጊዜ ይገፋልና
ጠንቀቅ በይ አለሜ ወድሻለሁና
ስወድሽ ተከፋሁ
አይቼ እንዳለየሁ ስንት ነገር ገፋሁ
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
ምን ሊወስድ ይመጣል
(በእውቀቱ ስዩም)
አንቺ ጻድቅ መሳይ፥
ጭምት ለማያውቅሽ
እኔን አርጎ ፈጥሮኝ፥
ስጋ -ለበስ ጥንቅሽ
እንኳንስ መረቄ፥
ቅርፊቴ ማይጣል
ሞት በቀጠሮው ቀን፥
ምን ሊወስድ ይመጣል::
@getem
@getem
@paappii
ቀሚስሽ ደግ ነው መሰሰት አያውቅም
ደጅ ለጠናበት ለጋሽ ነው አይነፍግም
አርሂቡ አርሂቡ ሁሉን ተቀባይ ነሽ
ቀጭን አትይ ወፍራም
ጥቁር አትይ ቀይ መቼ ትመርጫለሽ!
አርሂቡ!
አርሂቡ ግቡ ተቋደሱ
አንተም ያዝ አንተም ያዝ እስኪ ተቃመሱ
.
እንኩ ነው ልሳንሽ ላንኳኳ በሙሉ
ለስሜት አበጋዝ የሚገልብሽ ሁሉ
እንኩ ነው በነጋ
እንኩ ነው በመሸ
ያ ነጩ ቀሚስሽ በመስጠት ጠለሸ
እንካ ያልሽው ተቀባይ
አጣጥሞ ጣለሽ ልክ እንደ ማስቲካ
ወትሮም ቅሉ አያምር በሁሉ የተነካ
[ ጥሩቤል ]
@ebuhbhr
@getem
@getem
@getem
#ሰሞነኛ
ምን ባይኖረን ግራ ግጣም
ካሳባችን አንድ አናጣም
ምን ባንዞር ተተቃቅፈን
ልብ ያወራል አፍ ያፈነን
ምሳር ባልታጣባት በዚች እርኩስ አለም
ሲንግል ሁሉ ነፃ አይደለም!።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
"ልብህን አድምጥ" የምትል መሪ ቃል
አባነነኝ ካለም ፅሁፍ ልብ ያነቃል
ልቤን አዳመጥኩት
ሞልታዋለች እሷ
ፍቅርን አሸተተኝ
ካካሏ ከነብሷ
ሳላስብ ወደድኳት የድንገት የድንገት
ፍቅር ሃሳብ
ፍቅር ስሌት ባንድ እሷ ሞላበት
ተመኘሁኝ እድል ግቤን
ከሷ ጋራ እንዲያጣምረኝ
አልሆነለት ሁለት ወገን
ጊዜን ወስዶ ወይ አልማረኝ
"ልብህን አድምጥ" የምትል መሪ ቃል
አባነነኝ ካለም ፅሁፍ ልብ ያነቃል
ነቃሁኝ
አፈቀርኩ
ሻትኩኝ ልቧን ለኔ
አይ እድል ጠማማው
አላገኛት ጎኔ
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
መውድስ ብቻ
ሳቋ እንደ ፀበል ፥ ያስለፈልፋል
ከንፈሯ እንደ ዛር ፥ ግጥም ያጽፋል
አይኗ ያበራል
ደግሞም ያስፈራል
ልብ ፥ ኩላሊት ይመረምራል ፤
የሰው ልጅ እንዴት እንደዚህ ያምራል ?
የሌለ ውበት
የሌለ እውነት
ታይቶ ፥ ተሰምቶ ፤ የማያውቅ አይነት
ታምር ናት ታምር
ሁሌ ምታምር
የውብ ነገሮች ፥ ጠቅላላ ድምር !
ደማም ፥ መልከ-ጥር
አዳዲስ ቃላት ፥ የምታስፈጥር
አምራ እምራ ማታልቅ ፥ በታየች ቁጥር
ልቤም ተረትቶ
ሌላ የኑሮ ፥ ኮተቱን ትቶ
ከገላዋ ላይ ፥ ውበት ይቆጥራል
ከሰው መሆኗን
ከእኛ መሆኗን ፥ ይጠራጠራል
የሰው ልጅ እንዴት እንደዚህ ያምራል ?
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
በምን ላማልልሽ?
ምን ቃል ይስብሻል የቱ አቀራረብ
ምን ዘዴ ልዘይድ ወዳንቺ ለመቅረብ?
አንቺ ሆይ ንገሪኝ.....
በትዝታሽ ዞትር እንዳልብሰለሰል
ምን ቅኝት ልጋብዝሽ ባቲ ወይስ አምባሰል?
ምን ዘዴ ልጠቀም ልብሽ ለማማለል?
ጦማር ልላክልሽ በፖስታ አሽጌ
ልብሽ ሚያቀልጡ ውብ ቃላት ፈልጌ÷
እንዴት ልግለፅልሽ እንድትሆኝ የግሌ
እኔ ያንቺ እንድሆን ከነ ሙሉ አመሌ፡፡?
አንቺን ሚገልፅልኝ የማማልልበት
አፍቃሪዬ ሆነሽ በእጄ ማስገባበት
ምን ዘፈን ጋብዤሽ ልብሽ ውስጥ ልግባበት?
በግጥም ልንገርሽ በስንኝ ቋጥሬ
ገጣሚ ነኝ ብዬ ቃላትን ደርድሬ÷
እንዴት ላማልልሽ እንዲገባሽ ፍቅሬ?
ነጠላ ለብሼ ቅዳሴ ላስቀድስ
አንቺን ለማማለል ሄጄ ራሴን ላድስ÷
ስንት ሱባኤ ልያዝ የትስ ገዳም ልግባ?
ስለቴ ሰምሮልኝ ልብሽ ውስጥ ልገባ?
ቡሩሽ ልግዛ ቀለም ልሳልሽ በሸራ?
በጥበብ ላማልልሽ ጥሪት ሳላፈራ?
ወይስ እየበተንኩ ገንዘብን በጉራ?
የቱን በጎ ስራ እየሄድኩ ልሳተፍ?
አንቺንም ፅድቅንም ልቤ እንድታተርፍ?
በዱር በገደሉ እየወጣሁ ልደር
ጠላትን ልመክት ዘብ ልሁን ለሀገር?
በምን ላማልልሽ ልጠቀም ምን ዘዴ
እንዴት ልግለፅልሽ እኔ አንቺን መውደዴ?
@Abuugida
by ᵗˢᵉᵍˢʰ
@getem
@getem
@getem
CHAPTER ስንት ? ነን ?
'
'
መቼስ ታውቀዋለህ
ካለም ኋላ መሳነፍን
መቼም ታውቂዋለሽ
ከእዳ ጉንፋን
ጭንቀት ማስነጠስን
እኔስ አውቀው የለ
ማላውቀው ምን አለ፣
ገና ገና እያልኩ
እድሜዬ መምህሬ
ስንት ቻፕተር ዘለለ ፣
'
'
ግዕዝ ሙላት🦘
@geez_mulat
@getem
@getem
@getem
'
'
ማግኜቴ እንኳ ይበቃኛል
ም'ር'ቅ ሳግ ሳላምጥ
በመሳምሽ አረፍ ይላል
በዚች ዓለም ስናወጥ
ተንጠልጥሎ ይታየኛል
እየተውለበለበ
ዛፉ ላይ ገመዱ
ፀጉርሽ እስክዳብስ
ፍዳ ውሎ ነው
የአለም ሰርዶ ግምዱ
አፍንጫየን ይሸተዋል
የሙት ቀብር የሌላቸው
ቁራ ሁሉ የተዋቸው
ክፋት ምኑ አጥመልምሎ
ነፍስ ሰጦ የጣላቸው
እኒያ ዘንዳ ውዬ ውዬ
አንቺ ዘንዳ አልጋችን ውስጥ
የናርሲየስ ጠረንሽን
ይውጠኛል እንደ' ስምጥ
ደሞ ይታየኛል
ጌጡ ምናምኑ
አሳብዶ ሚያንቀዠቅዥ
የእኔ ልብለጥ ዓለም ስሄድ
ባዶ ራቁት የእብድ ቁሻሽ
የሚያፀይፍ ማይወደድ
እነሱ ጋ ውዬ ውዬ...
አንሶላው ውስጥ ገባ ብለን
ባዶ ራቁት ሆነን በእቅፍ
ዓለም ጨርቅ ትለብሳለች
ሀፍረት ክብርን የምትቀጥፍ
ደሞ ሳየ ፀጉራቸውን
እሳት ለግቶ ያወረደው
ክልቲምልቲ ሳሙናው
ጣቱ ምኑ የደረደው
ቅማል ወርሶት የሚዋጋ
ለዓይኔ ስጋ የሚታየው
ከዛ ውዬ ውዬ...
ፀጉርሽ እንኳ መስክ አደለ
ፍቅር ያለው ሚመስጥ
ከቅብብዝ ባለሽቶ
ከዓለም ፍቅር የሚያቀብጥ፣
ጣቴ እንኳ የሚረጋው
ከሸክሙ ከሽክረቱ
ፀጉርሽን ሲዳብስ ነው
የሚመለስ ጣትነቱ
ያቺ ጎጆ ስናፍቃት
ካለም ስውል እንደ እስር፣
ከዚች ጠበባ የዓለም ግጭት
ማታ አለኝ ያንቺ ፍቅር፣
'
'
@geez_mulat🦘
ግዕዝ ሙላት
@getem
@getem
@getem
አባትህ ገዳይ ፥ እናትህ ገዳይ
ላንተ 'ሚተርፍህ ፥ ድርብርብ ስቃይ !
የሀበሻ ጥል ፥ ከልጅ ወደ ልጅ
ስለሚቀጥል ፣ ....
መቃብር ምሶ ፥ ታሪክ አጣቅሶ
ያገኘህ እንደሁ ፥ ያ'ምናው ተበዳይ
በ'ድልህ እዘን ፥ የራስህ ጉዳይ !
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
"በቅርቡ ከሚወጣው መፅሐፌ ቅምሻ" ❤🙏
ወገቤ ላይ ታላቅ ቁስል
የቁስል ሞት ታመኛለች፣
በስቅታ አፋፍ ሆኜ
ትንሽ መኖር ታምረኛለች
ትንሽ መኖር እያማረኝ
በሞት እቅፍ ሳለሁ እንኳ
የስኳር ማንኪያ ያህል
ኑሮ ራሱ ጣፋጭ ሹካ
ቁስል ሁሉ እከክ ወርሶኝ
በሞት መሃል ሳጣጥር፣
ትንሽ መኖር ታምረኛለች
ትንሽ ትንፋሽ ለመስከር፣
ጥይት ሁሉ ወርዶብኝ
ሰውነቴን ቢበሳሳም፣
ትንሽ መኖር ታሳሳለች
ከሞት ወሲብ ከመሳሳም፣
ትንሽ መኖር ስጭኝ ባክሽ
መኖር ባፌ ጉልበት ልሳም፣
ባክህ ቁስሌ መኖር ስጠኝ
ህመም እንኳ አይደንቀኝም፣
ትንሽ እንኳ መኖር ከቻልኩ
ጠባሳህም አይገለኝም፣
ትንሽ መኖር አማምሮኛል
ለነብሰጡር በሞት ደጅ ፣
ትንሽ ልኑር ባክህ አልሙት
ብወድቅ እንኳ በሰው እጅ፣
ትንሽ ብቻ መኖር መኖር
የአምሮቴን ትንሽ እድል፣
ትንሽ ህመም ለቀቅ አርገኝ
ኗሬለሁ ብዬ እንድል፣
'
'
@geez_mulat 🦘
ግዕዝ ሙላት
@getem
@getem
@getem
የመሰለው
እዛ ሆነሽ እዛ ማዶ፣
መራራቁን ልቤ ለምዶ።
የሚረሳሽ መስሎት ነበር፣
ሰዓት ሲነጉድ ቀን ሲመተር።
እውነቱማ
ምን ሆንኩ እስክል እኔን እኔ፣
መበደሉ በራሴ ልብ ጭካኔ።
እቀዝፋለሁ ባሳብ ባህር፣
ምን እንደማገኝ ሳላቅ
ተሳክቶልኝ ብሻገር።
ሲመጣበት በትዝታ
ሲያጉረመርም የናፍቆት ጉም፣
ይከፋኛል አይገልፀውም
ልቤ አይችለው ልክ የለውም።
By @DannyShy, 2:27 PM, Mon. Oct. 10, 2022
@getem
@getem
@getem