66224
✔በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን። ✔ @getem @serenity13 ✔ @wegoch @Words19 ✔ @seiloch @shiyach_bicha ✔ @zefenbicha @leul_mekonnen1
, ( ጨረቃ ነሽ ወይ ፀሀይ )
አንዲት ፍሬ ልጅ ሞትን ምታስንቂ
በውድቅት ለሊት
ደውል ሆነሽ መተሽ ሰውን ምታነቂ
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ከሩቅ አብረቅራቂ
ብርድ እና ሙቀትን የሆንሽ አስታራቂ
በድቅድቅ ጨለማ ያለን በጠራሞት
ነጥቀሽ የምታዎጭ በዕድን ስጋን ከሞት
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አንቺዬ
ለምጀው እንድኖር ሀሩርና ቁሩን እንደምንም ቺዬ
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አንቺዬ
ከዬትኛው ስነ ፍጥረት ልመድብሽ
ከጨረቃ ከክዋከብት ከፀሀይ ጋር ልደርብሽ
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ንገሪኝ አለሜ
አንቺን የሳልኩበት ሳይጠፋ ቀለሜ
እኔማ እኔማ
አንቺ ካልነገርሽኝ አልፅፍ ቃላትን
አልገነባም ጎጆን የሚፈርስ ቤትን
ስንቴ የሰራሁት ቤቴ ፈርሶ አልቆ
አለም አንቺን ሚሞቅ በእኔ ላይ ተሳልቆ
ጨረቃ ነሽ ወይስ ፀሀይ ???????
By Habtish
@getem
@getem
@getem
ወዴት ነህ?🚶🏻
ለመኖር ለመሞት ሲመሽ ሚጣደፉ
ተራማጅ እግሮች አያለሁ ከሰልፉ::
የፀሐይን መጥለቅ መሽኮርመም ጠብቀው
በመውጣት በመውረድ መንገዱን አጣበው÷
ወዴት ማዝገማቸው አውቀው ያላወቁ
ከተራማጅ መሃል ሰልፉን ሚያደምቁ÷
ብዙ እግሮች አሉ ወርደው የሚወጡ
መፅደቅ ወይም መርከስ አንዱን የመረጡ::
By @Abuugida
@getem
@getem
@paappii
ከለታት ባንዱ ቀን
ህይወት ግቧን አውቀን
ኖረን ኖረን መጥቀን
በንባ ውዝፍ ስቀን
ከለታት ባንዱ ለት
ገፋንና ብረት
ቡጢ ተሰናዝረን በእጃችን ውጥረት
ግባችን ልንመታ ግብን አስተካክለን
አስቆጣሪ ጀግና በኛ ስም ወክለን
አክለን
በጥድፊያ
በልፊያ
ሰዓት አቀባብለን
ጊዜ ተቀባብለን
አንድ ሁኑ ስንባል ለየግል ተቆጥረን
ተዋደድን ብለን ካንገት ተወጣጥረን
ተመንጥረን
እንዳልሳቅን
አለቀስን
ፌዝ እንዳልያዝን በልባችን
ይበለን የታባታችን
ኖረን ኖረን መጥቀን
በንባ ውዝፍ ስቀን
አዙሮ
አዙሮ
ጊዜ ጣለን ከቀን።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
ገና እሰክርሻለው
.................................
አለሜ ዞረብኝ
አለምሽን ጠጥቼ፣
አንቺን እንዳልሰክር
የሚያስቆም አጥቼ፤
አንቺን መንገዳገድ
አንቺን መፈራረጥ፣
ትቦው ስር ተኝቶ
ነፍስሽን ማዳመጥ፤
ሚያነሳኝም የለ ስሜ በአንቺ ጠፍቷል
ከአፋቸው ትችትን ብያኔን ለምዶታል!
.
#ተስፋን ቆራረጥኩት እብደቱ ተስማማኝ
#እምነትንም ጣልኩት ጤናን ስላስጠማኝ
#ፍቅርሽን ግን....
ልቤም ሊፍቅ ዳዳው
ውሳኔን አጣለት
ዘላለም ይመስል
ላይጠፋ ማለለት!
እንዴት አልስከርሽ
እንዴትስ አልጩህሽ
እንደሌላው አትፈርጂም
ዝም እኮ ነው መልስሽ!
ዝም..
ቁዝም...!
ጭጭ....
ረጭ....፣
ትዝታን አስታውሶ
ሰክሮ መነጫነጭ!
ሁከት...፣
ጩኸት....!
የውስጥን አፍኖ
ላይን ማሰቃየት!
(ገና እሰክርሻለው)
By @Weyblann
@getem
@getem
@getem
ጥርስሽ ሀዘን ጠሪ
ሳቅሽ መርዶን አርጂ
ደስታ በእጄ ገባች
ጥለሽኝ ስትሄጂ፤
በበደል ላይ በደል
ሰርክ እየደራረብሽ
ማስመሰልሽ ከፍቶ
ልቤን እያሳዘንሽ፤
ብዙ አመት ታገሰ፣ይሄ ቻዩ ሆዴ
ወትሮም ቅን ነውና የህይወት መንገዴ፤
ሂጂ..
ሂጂ..!
አው ሂጂ እየደላሽ፣
ልክ እንደ እንደኔ አይነቱን
ባላሰበው መንገድ
አሳር እያበላሽ!
ሂጂ
By @Weyblann
@getem
@getem
@getem
ሞልታ ለማትሞላ ለዚች ድንቡሎ አለም
መታገል ነው እንጂ መነፋረቅ የለም
ቻለው ችግርህን እጅ አትስጥ ለማንም
የደከምን ለታ ይብሳል ህመምም
ላገደመ ሁሉ ብሶትን አታውጋው
እራስህ ላንተ ኑር
ቃልን ውጠህ ዝጋው።
ቧልተኛ ነው ሁሉም
አይኑርህ አንድ ሰው
የሚገፋህ ካለ
ክንድህን አጉርሰው።
አርግፍለት ጥርሱን
አቅምሰው የጅን ጥም
"መታገል ነው እንጂ
መነፋረቅ የለም" ይላል ይሄ ግጥም።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
ካላንተ አልኖርም፤
ብኖርም አልደምቅም፤
እያልኩኝ ዘርዝሬ፤
ቃላትን መንጥሬ፤
አልሸነግልህም።
በጣም እንዲገርምህ፤
እንደዉም ልንገርህ፤
ከተራራቅን ወዲህ...
ካገኘሁት ጋራ፤
ካገኘሁት ስፍራ፤
ካገናኘኝ መንገድ፤
እንባዬ እስኪወርድ፤
ፈገግታ አበዛለሁ፤
ናፈቅኸኝ መሰለኝ...
አብዝቼ እስቃለሁ።
በዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
አለቀለት ያሉት
(በእውቀቱ ስዩም)
ከጅረት አጠገብ ፥ቆሞ የኖረ ዛፍ
መብረቅ ገነደሰው
አሁን ድልድይ ሁኖ፥ ያሸጋግራል ሰው ::
“አለቀለት” ያሉት፤ ተልኮው መች አልቆ
ቆሞ የጠቀመ፥ መላ አያጣም ወድቆ፤
@getem
@getem
@paappii
( እልፍ ሰላም )
============
ሲፈለግ የማይታጣ
ሲታሰብ የማይዘገይ
ታይቶ የማይሰወር
ሰጥቶ የማይታበይ
ማግኘት ማጣት ማይለውጠው
መሄድ መምጣት ማይቀይረው
በቅንጣት ጽድቅ ሚያሞጋግስ
ግዙፍ በደል የማይቆጥረው
ባዶነትን ማያናንቅ
መገፋትን ማይሰቀቅ
እርሱ ብቻ ተነጥሎ
ሁል ጊዜ የሚናፈቅ
የጎደፈን ማይጠየፍ
የሸሸውን ማይጥል ማይተው
ከወደደ እስከ ህይወት ጥግ
ይቅር ማለት ማይታክተው
መለያየት በሌለበት
በሱ ግዛት በሱ ዓለም
እልፍ ሰላም ካልሆን በቀር
ሞት ጥላቻ ክህደት የለም !!
By @kiyornad
@getem
@getem
@paappii
መሔጃ የለኝ !
ካይኖችሽ ብሸሽ ፥ ቅንድብሽ ስር ነኝ ።
ወዴትም ብዞር
ገላሽ ብቻ ነው ፥ የሚያዋስነኝ ።
ቅርቤም - ሩቄ
ኩነኔም - ጽድቄ
ከህጎች በልጦ ፥ ልብሽ የሚያዘኝ
አይንሽ ብቻውን ፥ የሚያናዝዘኝ
ያንቺው ታሳሪ ፥ ግዞተኛሽ ነኝ ።
ካንቺው ቀምቼ ፥ ላንቺ ምሰጥሽ
ከገዛ ራስሽ ፥ የማስበልጥሽ
ምንም ቢሰማኝ ፥ የማላመልጥሽ
ወስልቼ ብሄድ ፥ ከገላሽ ምሕዋር
ተኝቼ ምገኝ ፥ ከትዝታሽ ጋር
ወዲህም ሳራ ፥ ወዲህም አጋር !
ካንቺ ጋር መሮኝ
ሌላ ሴት አምሮኝ
ጥዬሽ ለመሄድ ፥ አስር ብወራጭ
አንቺን ነው ማገኝ ፥ ልክ እንደ አማራጭ ።
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
ያላንቺ ይቅርብኝ!
(የሞገሴ ልጅ)
ዐየሽ የኔ ናፍቆት-
ካንቺ በፊት እኔ - ኖሬአለሁ ለናቴ፣
ቆንጥጣ አባራኝ - በሚናፈቅ ቤቴ።
ያኔ ግን - ልጅነት-
ከጎኔ ስትለይ - ናፍቆት ቢቀጣኝም፣
አቅፋኝ እየተኛች፣
በናፍቆቷ መራብ - - ጭራሽ አያውቀኝም።
ጭራሽ አደግ ስል...
እሷን መውደድ ሳልተው - አንቺን በልብ ይዤ፣
አጠገቤ ሆነሽ፣
ናፍቆትሽን ፃፍኩት - ማግኘቴን ሰርዤ።
እንደው ግን የምልሽ?
እለት እለት ጾሜ፣
ያለኝን መፅውቼ፣
ከገነት ለመግባት - የምጠባበቀው፣
ካንቺ ጋራ ስሆን፣
ከሚሰማኝ ምቾት - እንዴት ነው ሚልቀው?
እንጃ ያሳስባል-
ካንቺ በላይ ናፍቆት የሚያስይዝ ቢመጣ፣
ከሆነ ነው እንጂ፣
አንችው ሰማይ ሆነሽ - ልቤ በልብሽ ላይ ገነት ተቀምጣ።
በዛ አትበይ እንጂ...
ካንቺ ተለይቶ - መኖር የሳት ባሕር፣
ካንቺጋራ ሆኖ - ሲኦል መግባት ክብር፣
ከነ’ንትንሽ መሳም - የዘላለም እረፍት፣
ማፍቀርሽን መግፋት - ኦሜጋ ስህተት፣
አንችን አለማሰብ - የድርቀትም አያት፣
ፈልጎሽ መኳተን - የክብር ኁሉ አናት፤
ይመስለኛል እኔ.....
ለገነት ለሲኦል - አንቺ ነሽ ሚዛኔ፣
ጨርሼ መጽደቄ - ወይም መኮነኔ፣
ፈዋሿ መስቀሌም - ገዳዩዋ መብረቄ፣
የሰማዩን እማ.........አልተወለድኩኝም በፅንፀት አውቄ።
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
( ከይቅርታ ኋላ )
============
ጆሮ እልፍ ቢያደምጥ
አይን ሺህ ቢያማትር
እግር ሩቅ ቢያስስ
እጅ ብዙ ቢጥር ....
ውብ ከቶ አያገኙም
ከይቅርታ ኋላ እንደሚኖር ፍቅር !!
By @Kiyorna
@getem
@getem
@paappii
ተጓዡ ተራማጅ ሀሳቤ ልጓሙን እስኪያገኝ……………
እድሜ ወረተኛ ገስግሶ ገስግሶ
ትምክተኛ መልኬ በሽብሽብ ተወርሶ
ርግበ እምነቴ ማረፊያዉን ሲያጣ
ጠባቂ እንደሌለዉ እንደስጥ ተስፋዬ በወፎች ሲበላ
ጠብቀኝ…………..
ባጣ ቀየኝ…………….
ዘመንህን - እድሜ መኖርህን በኔ እድሜ ለዉጠኝ።
ትዝታ ወልዴ✍️
@Tizita21
@getem
ገና ያኔ ድሮሮ
ከሩቅ ዘመን በፊት፣
አማኝ በሞላበት
ፈላስፎችም አሉ ብቻ ትንሽ ጥቂት፤
ታድያ በዛ ዘመን
መሬት ክብ ነበረች
ምጣድ ምትመስል፣
ለጥ ብላ ምትኖር
የማትዞር ማትዋልል፥
ያችኛዋ መሬት
አሁን ከነበረው በጣም ትለያለች፣
ምንም አድሎ የለም
ሁሉን ታበቅላለች፤
ታድያ እነዛ ጥቂት
የሚፈላሰፉ፣
ከንቱ ሀሰበቸውን
በሰው ውስጥ አስፋፉ፤
መሬት ክብ ሳትሆን
ሰማይ የምታክል፣
እንቁላል ነገር ነች
አሎሎ ምትመስል፤
ብለው ማይሆን ወሬ
ምድር ላይ በተኑ፣
ደበራት መሰለኝ
እንደዚ ሲሆኑ፤
አሁን በኛ ዘመን
ትንሽ መረጋጋት ያለ ከመሰላት፣
ለስሟ ነዉ መሰል
ድርቅና ቸነፈር
ጦርነት አይቀራት።
@getem
@getem
@paappii
ተመስገን🙏🙏🙏
.
.
.
መስከረም ሲያከታትም አልፎ ሲተካ ጥቅምት፤
ፀደይ ብራ ሲሆን ሰማዩ በዛች መጀመሪያ ዕለት፤
በእልልታ ታጅቤ ወደዚች ዓለም መጣሁኝ፤
የለቅሶን ሸማ ደርቤ ዛሬን ነው የተወለድኩኝ፤
አዲስ እድሜን ለንስሐ ጨመረልኝ፤
መከራዬን አሳልፎ ለዚች እለት አደረሰኝ፤
አንዳች ፍሬ ቢታጣብኝ ምንም ምግባር ባይኖረኝም፤
ከአጠገቤ ሳይለየኝ ለሴኮንዳት አልተወኝም።
ትናትናም አልሸሸኝም ሳማርረዉ በአንደበቴ፤
ዛሬም አለ ተነሽ ብሎ እያነሳኝ ከዉድቀቴ፤
ወዳጅ ያልኩት ሰዉ ቢርቀኝ፤
ለአፍታም እንኳ ቸል አላለኝ፤
በምሕረቱ አስጠልሎ ሳይገባኝ ስላኖረኝ፤
ተመስገን ነዉ እንጂ ሌላ ምን ቃል አለኝ።
🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊
🎂🎂01/02/2018🎂🎂
✍️ ዔደን ታደሰ
@ediwub
@getem
@getem
ቤት እማ ጨዋ ነሽ፣
እንኳን ሌላ ሌላ እኔንም አታይም፣
ግን እድሜ ለሱሱ፣
ወተሽ ወዳጅ ካየሽ አታልፊም አትተይም።
የሸመገለን ወንድ፣
በሰለቸ ዐይንሽ ዕያየሽ ወጠምሻ፣
የሱን መድሃኒት፣
አርገሽ ለቀን ያዝሽው የኔን ማስታገሻ።
By @eyadermoges
@getem
@getem
@paappii
📍GHOST VOTE .
Ghost'ን vote እናድርግ
Ghosty’f sagalee kennaa
ጎስት'ነ ድምጺ ሃቡሉ
Ghost'ya keettidaa aayize
ጎስት vot አምሮዊ
Vote for Ghost
Vote por Ghost
投票给阿比伊,صوّتوا لأبيي
- ለጎስት ቮት ! 👇 🙏
https://www.tca2025.com/category/21
SHARE @getem
ከልቤ መዝገብ
ሰርዤ በደንብ
ደልዤ በደንብ
ያጠፋሁው መስሎኝ
ስኮራ ስሞኝ
ከየትኛው ጥግ
ከፀዳው ልቤ
ብቅ ትይና
'ባሳብ ምናቤ
እንደረሳሁሽ
እኔ ብል 'ባምንም
ልቤ ይከዳል ትዝ ትይኛለሽ
ምን ደስ ቢለኝ ምን ቢከፋኝም
መስከረም 13/18 ዓ/ም @DannyShy
@getem
@getem
@getem
ኗሪ መስለሽኝ ነውኮ ያኮረፍኩሽ
ላናግርህ
ላውራህ ፥ ስትይ ዝም ያልኩሽ ።
አንቺኮ አታፍሪም ይሄኔ
ቂም ትይዥ ይሆናል በእኔ
እባክሽ ላንዳፍታ ንቂልኝ
እንደምወድሽ እወቂልኝ ።
By Habtamu hadera
@getem
@getem
@paappii
ሁለቱም ይኑሩ!
(የሞገሴ ልጅ)
አለመተዋወቅ..
አለመቀራረብ..
አለመነጋገር..
አለመደራረብ፤
ዶግማ ይሁን እና-
ብዙ ይራራቁ፣
አይነፋፈቁ፣
አይተዋወቁ፤
አንድ አይሁኑ እንጂ-
ችግር እንዳይመጣ፣
ኁለቱም ይኑሩ፣
ዐይን’ና ሚጥሚጣ።
By @eyadermoges
@getem
@getem
@paappii
ሰማሽ ወይ...
ያደለው ለሃገር - ጥይቱን ይጠጣል፣
ያላደለው ደግሞ - ቢራ ያማርጣል፤
ያገኘ ላምላኩ - እጁን ይዘረጋል፣
ተስፋ ያጣ ሃገር - ጥሎ ይጠረጋል፤
ታዳጊው ጎርምሶ - ለትዳር ይታጫል፣
ያመለጠው ኖሮ - በትላንት ይቆጫል፤
ኁሉም የየራሱን - እያነሳ ጣለው፣
ያንችን እና የኔን..........እኔስ ምን ልበለው?
By @eyadermoges
@getem
@getem
@getem
ለምን ትመጫለሽ?
ወና መሆን ለምዷል
ባይተዋር ነው ሆዴ
ትራስ አቅፎ ማደር
ለምዶበታል ክንዴ።
ገላዬ ቀዝቅዟል
ልቤ ተሰቅዟል
እንስት ላለማመን
ዜሮ ነኝ ስተመን
ብትመጭም ከንቱ ነው
መመለስሽ ምንም
ስታወሪ አልስቅም
በእንባሽ አልቆዝምም
በድን ነኝ አልድንም ።
ለምን ትመጫለሽ?
የለሁም በድሮ
ሌላ ነኝ ዘንድሮ
ግዴ አይደለም ነገ
አትገርመኝም ጀንበር
ብራና ክረምቱ …
ቢዛወር ዓመቱ
ጨፍሬ አልደክርም
አልመታም አታሞ
ዓመት አንድ ቀን ነው
ለከሸፈ ታሞ ።
ለምን ትመጫለሽ ?
መምጣትሽ እንደ ቧልት
መመለስሽ ምንም ...
፡
ይህንን እያልኩኝ
ብናገር ብገጥምም
ስትመጪ ስዳበስ
በጣት በመዳፍሽ
ያልኩትን ዘንግቼ
አዲስ ሰው ሆንኩልሽ።
አትሄጂም አይደለ ?🙄
By (ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@paappii
እኔ አንቺን ሳስታውስ
-------------------------
ወጪና ወራጁን
ተመልካቹን ቀርቶ
ቋንቋ ይምታታብኛል
ጠብቆ ይሁን ላልቶ
ብዙ ግዜ እንደሁም
ራሴን ረሳለው
እንዴት ተፈጠርኩኝ
ብዬ አወራለው
መሬት ጠፋች ብዬ
እዬዬ አስነካለው
መሬት ላይ ቁጭ ብዬ
መሬት ፈልጋለው
አንቺን ሳስብ ጊዜ ፤
"የመልኣክ ዝማሬ
ከሰማይ ሰማለው
ረቂቅ ነፍሳትን
መሬት ውስጥ አያለው"
አሁን በቀደም ለት
አንቺን ሳስብ ግዜ
እናት ወይ አባቴ
ብቻ ከሁለት አንዱ
ገፍትሬ አለፍኳቸው
በመንገድ ሲሄዱ
ፀሃዩን ከዝናብ
ገደሉን ከመንገድ
አሶችን ከኣዋፋት
አፈር ይሁን አመድ
ይሄን ሁሉ ነገር
በቃ ረሳለው
በሀሳብ በስብሼ
አንቺን ናፍቀለው
―――――
አንቺ እሱን ትያለሽ!
―――――
እልፍ አዕላፍ መንደር
ከሰማይ የራቀ
ከክዋክብት ግዛት
አልፎ የመጠቀ
ነፋሻማ ቦታ
ቆላ ያልሆነ ደጋ
ተከበን በእዋፋት
በአፅዋቶች መንጋ
እኔና አንቺን ብቻ
ቁጭ ብለን አያለው
በሃሳብ ዥዋዥዌ
ሄጄ ዳክራለው
―――――
እኔ አንችን ሳስታውስ!
―――――
በምናብ መዕበል
አብሬሽ ሄዳለው
አንቺን አወራለው
አንቺኑ አስባለው
እብሰለሰላለው
እኔነቴን ትቼ
አንቺ እኔን እላለው
―――――――
እናልሽ
―――――――
ባንቺ መውጣት መውረድ
ባልዘርፍ ምንም ቅኔ
ዘውድ ማረጌ
ሆነሽ ከምቶኚ የኔ
አንቺን ማስታወሱ
ስላሰጠኝ ደስታ
አልፈልግም መቼም
እንድትመጣ ሰምታ
እሷን ማሰብ ብቻ
ስላለው እርካታ
ስላገኘው እፎይታ
@getem
@getem
@paappii
ያልወረደ እንባ
.
ላዩኝ ሁሉ ደስተኛ ነኝ እስቃለሁ፤
በነሱ ቤት መከፋትን የት አዉቃለሁ፤
.
የሚገርመዉ.....
በኔ መፍካት መቅናታቸዉ፤
እኔን መሆን ምኞታቸው፤
መች ያዉቁና ማስመሰሌን፤
የዉስጥ ሀዘን ስዉር ቁስሌን፤
በዉስጤ ታጭቆ ሰላም የሚነሳኝ፤
በነጋ በጠባ ሆድ ሆዴን ሚበላኝ፤
አዉጥቼ እንዳልጥለዉ አፍኖ የያዘኝ፤
ሳቅ የሸፋፈነዉ ያልወረደ እምባ አለኝ።
.......................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
ያልታደልኩት እኔ
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
የሚመሩን ሁሉ መምሪያ ሰነዳቸው
ምን ቢሆን አንድነት
በሬሳ አካላች ቄጤማ ነስንሰው ሰሩልን ሰገነት
ሰብከውን በኪዳን
ሰብከው በመንግስቱ
ተደመርን ብለው ምን ቢያጎበድዱ
የጀርባ ላይ እከክ ሆኑ አንዱ ጎሳ ላንዱ
በመስኮት በመስኩ ምንስ አሸብርቀው ፍቅር ፍቅር ቢሉ
እያቸው አለሜ
ጩቤ ተጨባብጠው ሰላም ሲባባሉ
ያልታደልኩት እኔ
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
አዲስ ኪዳን ቢፈለሰፍ
አዲስ መንግስት ቢዋቀርም
ዱር ጫካ ገብቼ ሳላይሽ አልቀርም
የፈለገ ቢሆን ሰላም ለአደባባይ ለመንደሩ
ለሀገርህ ዝመት ብለው ገበሬን ነው ሚገብሩ
ሰርክ አራሽ መሬቱን
ሰርክ ቀዳሽ ታቦቱን
ነፍጠኛ ተኳሹን
ሀገር ሲሉት የሚነሳን
ወገን ሲሉት አለሁ የሚል
ምን ቢጨቆን አፉን ይዞ ትቅደም ባለ አንድ ሀገሩን
ሜዳ ላይ አጠፉት
ኪዳን ፍቅሩን ጥለው ሰበሩት ማገሩን
ያልታደልኩት እኔ
አይንሽ እርቆብኝ ሰርክ ብንገላታም
ወንድ ልጅ ነኝና ተስፋዬን አልፈታም
አለሜ
አይንሽን ባላይም ቃልኪዳን አልፈታም
ሁሌ እወድሻለሁ
ሚያገናኘን መንግስት እስኪመጣ ድረስ
እናውርድ እላለሁ
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
•
የመንገዴ ፍጻሜ ነሽ
ከአድማስ የአድማስ መጨረሻ
የሀሰሳዬ ፍጻሜ የጉዞዬ መዳረሻ
✻‧
ባለፈው ወይኔ ጎድሎ
እቸረው (እሰጠው) ቢያጥረኝ
ማርያምን መስለሻት መጣሽ
በምልጃሽ ምልአትን ቸረኝ
"አይሆንም" ያልኩት ሆነልኝ
አያልፍም ያልኩት አለፈ
"ከበደኝ ታከተኝ" ያልኩት በፍቅርሽ እየታቀፈ ።
✻‧
ነውሬን አንቺው ሸፈንሽው
ጋረድሽው የሀፍረት ታሪኬን
የህይወት ማይ እየሆንሽኝ
አነጻው እድፋም መልኬን
ወደድኩሽ እስከ ጥ • ግ • ጥ • ጉ
ለፍቅርሽ ነፍሴን አስገዛሁ
አንድ ሆኜ መኖር ያቃተኝ
ዕልፍ ሆኜ በፍቅርሽ በ • ዛ • ሁ ።
#የአብስራ_ሳሙኤል
@YabisraSamuel
@getem
@getem
@getem
ባቀፈሽ ካልቀናሁ፣
ካላማርሽ ካልከፋኝ፣
የያዝሽውን ካልያዝኩ - የጣልሽው ካልከፋኝ፤
ሲአቅፉሽም ሲአሻሹሽ - ፊቴ ካልዳመነ፣
ደግ አረግሽ ብቻ ምኑን ፍቅር ሆነ?
By @eyadermoges
@getem
@getem
@paappii
ቀኑ ሲረፍድ
ዱካክ አካሌ ላይ የሙጢኝ ሲሳፈር
ድርጊቴን አጢነው ሲመጡልኝ ከንፈር
ጥላው ሄደች ብለው እንደሳቀብኝ ሰው
ሀዘን ይሙላት ነፍስሽ ልብሽን ይውረሰው
ባፍሽ ምላስ ያነሳሽው የማልሽልኝ ጠቅሰሽ ኪዳን
መጨረሻሽ ይሁን የሄድሽበት ሁሉ እግርሽ ሄዶ አይደን
በቀል የሱ ሆኖ ምን ባለደርግ ላንቺ በቀል
ተራግሜሽ ይቁረጥልኝ
በሄድሽበት ዝግጅት ላይ ሂውማን ሄርሽ ከቶ ይነቀል
የወደደሽ ልቤን
እንደተውሽው ከመንገድ ላይ
ከወደቅሽበት ማቅ ስትነሺ እንዳላይ!
አይበቃኝም ሰርክ መስደብ
ገና ብዙ እረግማለሁ
ግን
እወድሻለሁ።
ዮኒ
ኣታን @yonatoz
@getem
@getem
@getem
እኔም እንደ አዳም . . .
በገነት ገዳም
ሁሉ ተሟልቶ ፥ ኑሮ ሲመቻች
አድርጎኝ ታካች
ማለት ሲዳዳኝ "ከፀሐይ በታች..."
የዛኔ መጣች !
መጣች ...
"ንቃ" አለችኝ
ጎኔን እየወጋች ፥ ተፈታተነችኝ
ዝም አልኩኝ በግብሯ
ታገስኳት እንዴትም ፤
ለካ እንደመሳሳቅ ፥ ይጥማል ንዴትም ።
( ምቾት ብቻውን መች ያስደስታል ?
መስኩ ለምለም ነው
አፀዱ ሙሉ
ምግቡ ፥ መጠጡ በገነት ሞልቷል
ምስኪኑ አዳም ግን ትቶት ተኝቷል ።
ሳይጠፋበት ጥፋት ፥ ሳይጎበኘው ሐጥያት
ለካስ ይሰለቻል ፥ መንግስተ - ሰማያት ። )
እሷ ግን በቃ
እግዜር ያስተኛኝ በገነት አልጋ
እንዳልነቃበት ስለሚሰጋ
መሆኑን አውቃ
ህይወት ሰጠችኝ ፥ ምቾቴን ነጥቃ ።
By Habtamu Hadera
@getem
@getem
@paappii
ምስጋና
-------------------------
ባንቺ ተማምኜ እምነቴን ጥዬብሽ
አምኜሽ ቆይቼ ቃሌን ጠብቄልሽ፣
ዛሬ ትመጣለች ግድ የለም ወይ ነገ
ፀሃዩ ፍቅራችን ስል መች ገና አደገ፣
እልፍ አላፍ አመታት ጥሎኝ እያለፈ
መንፈቅ በመንፈቅ ላይ ሄዶ እየከነፈ፣
በዋሊት ትዝታ በሀሳብ እየኖርኩኝ
ስቀመጥ ስነሳ አንቺን እያሰብኩኝ፣
ያዘዙኝን ሳደርግ ያሉኝን ስሰራ
ስንቱን አለፍኳቸው ስንቱንስ መከራ፣
ቢሆንም
እንደው ብቅ ብለሽ ካጣሽኝ ከሌለዉ
ጆሮሽን አትስጪ ቸግሮታል ለሚለዉ
የመኖሬ ተስፉ አንቺ ነበርሽና፣
ዘግይተሽ ብትመጪም ይድረስሽ ምስጋና።
@getem
@getem
@paappii