fikir_yishalegnal | Adults only

Telegram-канал fikir_yishalegnal - Relationships

7834

በቅርቡ የፍቅር ነክ ጽሁፎች ውድድር @fikir_yishalegnal 👉የፍቅር ደብዳቤ ለመጻፍ 👉የልደት መልካም ምኞት 👉የፍቅር ጥቅሶች 👉ሌሎችም ✨✨✨✨✨✨✨✨ እኛን ለማግኘት ❇️ @mer677_bot . . .

Subscribe to a channel

Relationships

ለካ አዝኖ ኖሯል

አንቺ ስትወለጅ ያወረደው ዶፉን፡
በደመና ጋርዶ ያጨገገው ቀኑን፡
ውሽንፍሩን ለቆ ያሸበረው ህዝቡን፡
ዛሬ ምን ሆነክ ነው ብለው ቀና ብዬ፡
ልዕልቴን ነጠቁኝ አለኝ በእዬዬ፡
ለካ እንዲ ያረገው ሰማይን ያስቆጣው፡
ወደ ምድር ስትመጪ ስትወለጂ ነው፡
እናም ልንገርሻ ዛሬ ነች ያቺ እለት፡
ሰማይም አልቅሶ እዬዬ ያለባት፡
እውነትም ድንቅ ነሽ ፈረድኩ ያየሁሽ ቀን፡
ማንባትም አነሰው ሰማይ አጥቶ አንቺን፡
ፍዝዝ ብዬ ቀረው አንቺን ያየው ለታ፡
ውብትሽ ገዳይ ነው ተማረከች ነፍሴ እጇን ላንቺ ሰታ፡
በጣም ነው ምታምሪው እንደ ጊዮርጊስ እናት እንደ ቲዮቢስታ፡
እንኳንም ተወለድሽ እንኳንም መነደግሽ፡
እግዜሩ ይመስገን ለዚ ያደረሰሽ፡
መልካም ይሁንልሽ ልደትሽ ያማረ፡
የሚታወስ እንጂ አይሁን የነበረ፡
አንቺ ስትወለጅ ዘንቧል ብለው ያሉሽ፡
ሰማይ ሲያለቅስ ነው አንቺኑ ስላጣሽ፡
እኔ ምኞቴ እንዲያምር ልደትሽ፡፡

Lechannelachen Relationship ke admin Rich de habeshan gal😘😘
Andega ametachenen mekeniyat bemadereg❤️🎂🎂

Читать полностью…

Relationships

✨✨✨✨✨✨✨✨
ተራርቆ ፍቅር ዉጤታማ ይሆን?

ከአንድ የቻናላችን ተከታይ የደረሰን ጥያቄ ነው።
💖💖💖💖💖
በእርግጥ ፍቅራችሁ ወደ ተሻለ ምዕራፍ የመሸጋገር እድል ይኖረዋል። ይሁንና ተራርቆ ፍቅር እንደመሆኑ መጠን ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ከወዲሁ በመገንዘብ በተቻለ መጠን ለማስወገድ ጥረት ማድረግ ይኖርባችኋል። እንደሚታወቀው ለቀናትና ለወራት ተነፋፍቆ መገናኘት አጓጊና አስደሳች የመሆኑን ያህል አደጋወችም አሉት ምክንያቱም ተነፋፍቃችሁ ከርማችሁ ስትገናኙ ጉጉታችሁ ሁሉ ለመተያየት እንጅ የፍቅር ግንኙነታችሁን በአትኩሮት ለማስተዋል አይሆንም። ይህ ተራርቆ የሚመሰረት የፍቅር ግንኙነት በአጠቃላይ ሶስት ችግሮች አሉበት።

💓💓💓💓
1 የፍቅረኛችን ትክክለኛ ባህሪና ማንነት ለማወቅ ይከብደናል፡ ከፍቅረኛችን ጋር ለምሳሌ ለ3 ቀናት አብረን ብናሳልፍ በእነዚ ቀናት በተቻለን አቅም በውስጣችን የሌለንን ጨምረን ጥሩ ባህሪ ነው ለማሳየት የምንሞክረው፤ መቼም አስቸጋሪ ባህሪዎቻችን ለ72 ሰዓታት መደበቅ አያቅተነም። ይህ ደግሞ እርስ በእርስ እንዳንተዋወቅ ትልቅ እንቅፋት የሚሆንብን ነገር ነው። ጓደኛችን ለማወቅ ትንሽ ጨነቅነቅ ሲል...ለምሳሌ ችግር ሲገጥመው፣ ሲፈራ፣ ሲታመም...ወዘተ ነው ማየት ያለብን። በእነዚህ ጊዜያት ትክክለኛ ባህርያቱ ይገለጣሉና።

💓💓💓💓💓
2 ችግሮችን ከመጋፈጥ ይልቅ ችላ ማለት እና መሸሽ ይታያል።
በእንዲህ አይነቱ ግንኙነት ዉስጥ ችግር ሲከሰት፣ በጋራ የመጋፈጡ ነገር እምብዛም አይስተዋልም። ለምሳሌ ከፍቅረኛህ ጋር በተለያያቹ በሁለት ወራችሁ ተገናኝታችሁ እራት እየበላችሁ እሷ ድንገት አንድ የሚያናድድ ነገር ነገር ትናገራለች እንበል።ታዲያ አንተ ለዚህ ምላሽ ሰጥተህና ሁኔታውን ተጋፍጠህ ምሽቱንና በቀሪ ቀናት የሚኖራችሁን ጣፋጭ ጊዜ ታበላሻለህ ወይስ ዝም ትላለህ? ብዙዎች ለጊዜው ስሜታቸው እንዳይጎዳ የሚመርጡት ዝምታን ነው። ይህ ዝምታ ሁለታችሁ በጋራ ችግሮቻችሁን መፍታት እንዳትማሩ እና ግንኙነታችሁን ጥልቅ ወደሆነ የመግባባት እና የመጣጣም ደረጃ እንዳታሳድጉ እንቅፋት ይሆንባችኋል። እነዚህ ያልተፈቱ ችግሮችና ያላወጣናቸው የተለያዩ ስሜቶች ደግሞ አንድ ቀን የሚፈነዱ ፈንጅዎች/emotional time bomb/ ናቸው። የፍቅር ግንኙነታችሁ ላይ ላይውን ጤናማ ቢመስልም ማንኛውም ጤናማ የፍቅር ግንኙነት ሊያልፍ የሚገቡትን ደረጃዎች እንዲያልፍ አልፈቀዳችሁለትም።

💓💓💓💓💓
3 በውስጣችን ከእውነታው የራቀ ምስል ይቀረጻል።
ከፍቅረኛችሁ ጋር በምታሳልፉት ሁለትም ሆነ ሶስት ቀናት ዉስጥ ምናልባት ወደ ተለያዩ ምግብ ቤቶችበመሄድ የመረጣችሁትን ምግብ ትመጋባላችሁ። ወደ ሲኒማ፣ትያትር፣ጭፈራ ቤት ...የተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች በመሄድ ደስታን በየ አይነቱ ትሸምታላቹ።ሁሉም ሲሰለቻቹ ደግሞ ወደ ያዛችሁት ክፍል ገብታችሁ አንዳችሁ በሌላኛችሁ ዉስጥ በፍቅር ትቀልጣላችሁ። ጓደኛ የለ፣ቤተሰብ የለ ዘመድ የለ...ሁለታችሁ ብቻ! ይህ ግን ስለ ግንኙነታችሁ ሆነ ወደፊት በጋራ ስለሚኖራችሁ ህይዎት የተሳሳተ መረጃ ነው የሚሰጣችሁ። እንደውም ኮ ከፍቅር ጓደኛችሁ ይልቅ መዝናናቱ ይበልጥ ሊያስደስታቹህ ይችላል። ለዚህ ነው ብዙ ጥንዶች አብረው መኖር ሲጀመሩ ማኩረፍና ማጉረምረም የሚጀምሩት።”እንዲህ ኮ አልመሰለኝም” ማለት የሚመጣው። እውነታው ግን ይሄ ነው። ትዳር ወይም አብሮ መኖር ማለት የአንድ ወይም የሁለት ቀናት ፓርቲ ሳይሆን የዘወትር አብሮነት ነው።
💝💝💝
በአጭሩ በተለያየ ስፍራዎች ሆነው በፍቅር ግንኑነት ዉስጥ ያሉ ጥንዶች ፍቅራቸውን ወደ ጤናማና ዘላቂ ግንኙነት ለማሸጋገር አብረው መኖር ይገባቸዋል። ይህ ሲሆን ብቻ ነው አንዳቸውከሌላኛቸው ጋር አብረው የሚሄዱ መሆናቸውን በትክክል ማስተዋል የሚጀምሩት።ሆኖም በአንድ ጣራ ስርመኖር እስኪጀምሩ ድረስ ባሉበት ሆነው የሚከተሉትን ጠቃሚ ምክሮች ተግባር ላይ ቢያውሉት ጥሩ ዉጤት ሊያገኙበት ይችላሉ።

💝💝💝💝
1 በምትገናኙበት ወቅት ሁሉንም ነገር የበዓል ድግስ አታስመስሉት። በመጠነኛ ወጭ የተለመዱና ከእለት ተእለት ኑሯችሁ ጋር ተቀራራቢ የሆኑ ነገሮችን ብቻ አድርጉ።

💝💝💝💝
2 አስቸጋሪ የስብዕናችሁ ክፍሎችንና እውነተያ ባህሪያችሁን ከጓደኛችሁ አትደብቁ። በተቻለ መጠን ራሳችሁን ለመሆን ሞክሩ።

💝💝💝
3 እውነተኛ ስሜታችሁን አትደብቁ። ግጭቶች ሲፈጠሩም ወዲያው በመጋፈጥ ለማስወገድ ሞክሩ።

💝💝💝💝
በፍቅር እንኑር
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
🌷🌷🌷🌷🌷
#share

Читать полностью…

Relationships

በተጨማሪም ያላችሁን
💌የፍቅር ደብዳቤ፣
✉️የይቅርታ ደብዳቤ እና
🎉የመልካም ልደት ምኞት ወደ @mer677 ላኩልን፡፡
#share
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

💚💛❤️ 💚💛❤️
ሰላም የRelationships ቤተሰቦች ቻናላችን ሰኞ ሀምሌ 30/2010 አንደኛ አመቱን ያከብራል፡፡
በመሆኑም ልዩ 💘 የፍቅር ሳምንት 💘መሰናዶዎችን አዘጋጅተናል፡፡
በዚህ ሳምንት
❣የጠበሳ ዘዴዎች
❣በፍቅር ውስጥ የሚነሱ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
❣የፍቅር ደብዳቤዎችና
❣የፍቅር ታሪኮች
❣የይቅርታ ደብዳቤዎች ይቀርባሉ፡፡
✨✨✨✨✨✨✨✨
በተጨማሪም ከሰኞ ጀምሮ
💝በፌስቡክ እና
💝በYouTube ዝግጅቶቻችን ወደ እናንተ ማስተላለፍ እንጀምራለን፡፡
#share
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

መሰማት ያለበት ምርጥ ሙዚቃ

ከሰማችሁ በኃላ #Share አድርጉ🙏🙏

Читать полностью…

Relationships

Yetiya hulame keleba afekrshalhu.....yanchen bateseboche hulam akebrelshalhu hulam anche endalshign yehonal yetiya anche kena gar hulame hugilegn endezaraw fkrachen yelemelem yekoyilen
####Ermi to yetenayet

Читать полностью…

Relationships

ይህ የኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናሎች ደምጽ ነው፡፡በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በደረሰው የቦንብ ፍንዳታ ለተጎዱ እንዲሁም ህይወታቸው ላለፈ በሙሉ በቻናሎቻችን ስም መፅናናትን እንመኛለን😢😥😪
🇪🇹ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር🇪🇹

Читать полностью…

Relationships

የእውነት እንደሚያፈቅረኝ እና እንደሚያዛልቀኝ እንዴት አውቃለሁ?
ጾታዊ ፍቅር ውስጥ በብዛት ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል ዋናው እንዴት እንደሚወደኝ እና ወደፊት አብሮኝ እንደሚዘልቅ እርግጠኛ እሆናለሁ የሚለው ነው፡፡ ከዚህ በፊት እወድሃለሁ አንተን ብቻ ነው ማግባት የምፈልገው ብላህ አሁን ከሌላ ሰው ጋር ህይወቷን እየቀጠለች ያለችው የቀደሞ የፍቅር አጋርህ ትዝ አለችህ ? እወድሻለሁ ያላንቺ ህይወቴ ባዶ ነው ብሎሽ ወሲብ ከፈጸማችሁ በኋላ አይንሽ ላፈር ያለሽስ? በቅርቡ አንድ ወዳጄ ወንድ ልጅ ሲወድ/ሲያፈቅር በምን ያስታውቃል ብላ ጠየቀችኝ፤ እርግጥ ነው ይህ ጥያቄ የብዙዎቻችን እንደሚሆን አልጠራጠርም  ሁሉም ሰው የእራሱ የሆነ የማፍቀር እና ፍቅሩን/መውደዱን የመግለጪያ መንገድ ቢኖረውም ብዙዎቻችንን ሊያስማሙ የሚችሉ መልሶችን እስኪ አብረን እንያቸው፡፡

1. ያስተዋውቅሻል

ወንድ ከወደደሽ እና ካፈቀረሽ በሄደበት ቦታ ሁሉ ተመሳሳይ ወሬ ከተነሳለት ስላንቺ የሆነ ነገር ያወራል፡፡ ከጓደኞቹ ወይም ከቤተሰቦቹ ጋር ያስተዋውቅሻል አልፎ አልፎም አንድ ላይ እንድታሳልፉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡ አንቺም አብረሽው ለመታየት አና አብራችሁ በምታደርጉት ነገር በአብሮነታችሁ በአጠቃላይ አታፍሪም፡፡

2. ይንከባከብሻል/ለደስታሽ ይጨነቃል

ደስታን ያስገኙልሻል ብሎ የሚያስባቸውን ነገሮች ሁሉ ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም፡፡ በተጨማሪም  በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይንከባከብሻል፡፡ ጠንካራ ሰራተኛ ቢሆንም በስራው ቅድሚያ ግን ላንቺ ነው የሚሰጥሽ፡፡ በችግርሽም ሆነ በደስታሽ ጊዜ ቀድመው ከሚደርሱልሽ ሰዎች መካከልም አንዱ ነው፡፡

3. ኮከብህ ከኮከቡዋ ይገጥማል

መሠረታዊ በሆኑ ነገሮች ላይ ማለትም ስለወደፊት እቅዳችሁ ስታስቡ ተመሳሳይነት ይታይበታል ለምሳሌ ስለ ትዳር ስለ ልጅ የሚኖርህ እቅድ እሷም ከሚኖራት ጋር ይመሳሰላል፡፡ እዚህ ጋር ግን ልብ የምትልልኝ ነገር መሰረታዊ የሚባሉት ነገሮች ላይ ትኩረት እንድትሰጥ ነው፡፡ ወደፊት ካንተ ጋር ተጣምራ ለመኖር ስታስብም ሰርጉ ሳይሆን ይበልጥ የሚያስደስታት ወደፊት ከአንተ ጋር የምታሳልፋቸው ጊዜያቶች ናቸው፡፡

4. እንደ እራስህ አድርጋ ትቀበልሃለች

በፍቅር ግንኙነት ውስጥ ከሚፈጠሩ ችግሮች መካከል ዋነኛው የፍቅር አጋርን አኛ እንደምንፈልገው ቀርጸን ነው እንጂ እሱ እንደሆነው አይደለም  የምንቀበለው፡፡ ስዚህ ወዳጄ የምትወድህ ከሆነ አንደሆንከው አድርጋ ትቀበልሃለች፡፡

5. የረጅም ርቀት ፍቅር ያሳለፋቹ እንደሆነ

ለብዙዎቻችን ፍቅር በርቀት እንደ ጦር የሚፈራና አይሳኩልንም ብለን ከምናስባቸው ተግባራት መካከል የሚመደብ ነው፤ ሆኖም ግን ፍቅራችሁ በረጅም ርቀት ውስጥ ተፈትኖ ያለፈ እንደሆነ አብራችሁ እስከ መጨረሻው የምትዘልቁበት ዕድል ሰፊ እንደሆነ ጥናቶች እና የአንዳንድ ጥንዶች ተሞክሮዎች ያመለክታሉ፡፡

6. ሁሌም ያበረታታሻል

በጥረትሽ እና በሙከራሽ ውስጥ የሚያበረታታሽ ሲሆን እንዲሁም እንድታሳኪም አልፎም የተሻለች አንቺ እንድትሆኚ የራሱን አስተዋጽኦ የሚያደርግ ከሆነ ይህ ሰው ባል የሚሆን ወንድ ነው ማለት ነው፡፡

7. አብረሃት ስትሆን ራስህን መሆን ከቻልክ

ብዙ ወንዶች የምንወዳት ሴትን ለመማረክ እሷ እንደምትወደው ዓይነት ወንድ ሆኖ ለመገኘት እንጥራለን፡፡ ሆኖም ግን ቅሉ ያለው ከርሷ ጋር ስትሆን ራስህን መሆን ከቻልክ ነው፡፡ አብሮነቷ አንተነትህን እንድትቀይር የማያስገድድህ ከሆነ ወንድሜ ይህቺ ሴት ሚስትህ ለመሆን እጅግ በጣም ቅርብ ናት::

#share

@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

Enkuan teweledk yene fkr 🎂🎂🎂🎂🎂

የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ
የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ

🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸

የኔ ፍቅር ገኖ ካንተ በላይ
ወድጄህ ከንፌ አዲስ ሆኜ ብታይ
ለካ ይሄ ነው
የእውነት ጣዕም ውበቱ
ሳየው አፍቅሬ
ሳውቀው ገባኝ ስሜቱ

ያላረፈ ዓይኔ ወስዶ ካንተ ጣለኝ
አሳረፈው ልቤን በፍቅርህ ረታኝ
ለካ ይሄ ነው ክፍያው
ለታገሰ ጉርሻ ደሞዙ
ቆይቶ ሲክሰው በፈቀደው መያዙ



የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ
የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ

የወደድኩት አብልጬ
ሌላ የለኝም በቃ
ዉሰድ ሙሉ ፋንታህን
ልቤ ያንተ ነው በቃ
የወደድኩት አብልጬ
የለም ሌላ ሌላ ሰው
ሀገሬ ይወቅ እኔ ልኩራ
ልውጣ በከተማው

ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ


🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸



የመጀመሪያዬ ነው . . . . .

ለ አቡሽ ❤️
ያንተው ፌቩ

Читать полностью…

Relationships

መስተፋቅር ለወንዶች ክፍል 4
የመጀመሪያ ቀን ስትገናኙ ምን ማድረግ እንዳለብህ እንይ
👉ፈገግ በል
👉የሰውነት እንቅስቃሴህን ተቆጣጠር እጅህን አፍህ ላይ ወይም ራስህ ላይ አታድርግ።እንዲሁም እጅህን የማይታይ ቦታ ላይ አታድርግ። ሴቶች በተፈጥሯቸው ዉስብስብ ስለሆኑ ሳያውቁት(unconciously) የሆነ ነገር እየደበቅክ እንደሆነ ማሰብ ይጀምራሉ።
👉 ጠይቅ መጠየቅ እንዳለብህ የታወቀ ነው ነገር ግን የማይጠይቁ ብዙ ወንዶችም አሉ።ምትወደውን ነገር ጠይቃት። ምታወራውን ነገርም አዳምጣት። ደሞ ጥያቄ እያከታተልክ ፈተና ላይ ያለች አስመስልባት አሉህi
👉በራስ መተማመን ያለህ ሁነህ ቅረብ።
👉ቀልዶችን ጣል አድርግ። ቀለል እንዲላት ያደርጋል። ነገር ግን በጣም ቀልድ አታብዛ።
👉ከእምነትና ከፖለቲካ ጋ የተያያዘ ወሬ አታውራ።
👉ደህና እደሪ ብለህ መሰናበት እንዳትረሳ ስንብትህ በመጨባበጥ፣በማቀፍ ወይም ጉንጮቿን በመሳም ሊሆን ይችላል።

💝
💝


ከእኛ ጋር ይቆዩ።

❤️በፍቅር እንኑር❤️
👫👫👫👫👫👫👫👫
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

አካላዊ እንቅስቃሴዎች ለሴቶች
ባንች ላይ ፍላጎት እንዳሳደረ ማወቅ የምትችይባቸው 15 መንገዶች

1. አንችን ሲያይ ብቻ ፈገግ የሚል ከሆነ
2. አይናችሁ ደጋግሞ ከተጋጨ
3. ሙሉ ለሙሉ ፊት ለፊትሽ ከተቀመጠ
4. በወሬዎችሽ ከሳቀ
5. ድምጹን ከፍ አድርጎ ካወራ
6. ልብሱንና ጸጉሩን ደጋግሞ ካስተካከለ
7. ደጋግሞ እየሰረቀ ሲያይሽ ካየሽው
8. አለባበስሽንና ሁኔታሽን የሚያደንቅ ከሆነ
9. አብራችሁ ስትሆኑ ስልክ ማይነካካ ከሆነ
10. ይከላከልልሻል ለምሳሌ በሰው በተጨናነቀ መንገድ ስትሄዱ ሰዎች እንዳይገፉሽ ያደርጋል
11. ከሌላ ወንድ ጋ ስታወሪ ፊቱን ይጥላል
12. ቻው ብሎሽ ግን መሄድ ካቃተው
13. ቻው ካለሽ በኋላ ዙሮ ካየሽ
14. የምትፈልጊውን ነገር ከሁኔታሽ ከተረዳ
15. ስትራመዱ ባንች እርምጃ ልክ የሚራመድ ከሆነ
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
በፍቅር እንኑር
👫👫👫👫👫👫👫
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

አሁን⏸

⏸አካላዊ እንቅስቃሴዎች
🕕
⏭ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ለሴቶች
🕖
⏭⏭አካላዊ እንቅስቃሴዎች ለወንዶች
🕙6:00

ከእኛ ጋር ይቆዩ
📲📲📲📲📲
አስተያየታችሁን @urmessagebot አድርሱን፡፡

💚💛❤️በፍቅር እንኑር💚💛❤️
💞💞💞💞💞💞💞💞💞💞

@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

መስተፋቅር ለሴቶች ክፍል 3
በመጀመሪያ ቀጠሯችሁ ማድረግ የሌለብሽ ❌❌10 ነገሮች

1 መዘግየት
2. አስተናጋጆችን በትህትና አለማናገር
3. አለመጠየቅ
4. ስለበሽታ ማውራት
5. ስለድሮ ፍቅረኛ ማውራት
6. መጠጥ ማብዛት
7. ስልክ መነካካት 📵
8. ብዙ ማውራት በተለይ ስለራስሽ
9. ጉራ
10. የእምነት ነክ ወሬዎች

❤️በፍቅር እንኑር❤️


@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

https://youtu.be/6Ve_OQtkwj0

Читать полностью…

Relationships

መስተፋቅር ለወንዶች ክፍል 2

ቀርበህ ተዋወካት። ከዛስ?🤔🤔 ሌላ ቀንም ኮ መገናኘት አለባችሁ።ስልክ 📱ቁጥሯን መቀበል ይኖርብሃል።ስልክ ቁጥሯን መቀበል ያለብህ በሞዛዛነትና በመነዝነዝ አይደለም። ስልኳን ለመቀበል ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለህ አታሳይ አለበለዚያ አትሰጥህም።ስልኳን ስትጠይቅ እንደምትሰጥህ ሙሉ እምነት እንዳለህ በሚያሳይ ና በራስ በመተማመን መንፈስ ይሁን።
😍😍😍
ስልክ ቁጥር ተቀብለሃል።አሁን ሁለት አማራጮች አሉህ። መደወል ወይም ቴክስት ማድረግ። የትኛው ይበልጥ ተመራጭ ነው?ከምን ያህል ጊዜስ በኋላ ነው መደወል/ ቴክስት ማድረግ ያለብህ?
⏩⏩⏩⏩
በክፍል 3 እንቀጥላለን።
💝💝💝💝💝💝💝
በፍቅር እንኑር
👫👫👫👫👫👫👫👫
@fikir_yishalegnal

Comment @urmessagebot

Читать полностью…

Relationships

የእናንተንም ጥያቄዎች እዚህ ላይ @mer677
@kal143
ላኩልን እናስተናግዳለን እየተቀበልን እናስተናግዳለን፡፡

Читать полностью…

Relationships

💖💖💖💖ዉድ የቻናላችን ተከታዮች ቻናላችን ዛሬ አንደኛ አመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።
ይህን በማስመልከት ሳምንቱን በሙሉ እናንተን ይጠቅማሉ እና ያዝናናሉ ያልናቸውን የተለያዩ ፍቅር ነክ ጽሁፎችን ወደ እናንተ እናስተላልፋለን።
🌹🌹🌹
በቻናላችን ላይ እንዲተላለፍ የምትፈልጉትን
🌷የፍቅር ታሪክ፣
🌷 የፍቅር ደብዳቤ
🌷 የመልካም ልደት ምኞት ወይም
🌷ካነበባችሁት ልታጋሩን የምትፈልጉት ነገር ካላቹ ወደ
✨ @mer677
✨ @kal143 ብትልኩልን በደስታ እናስተላልፋለን።
🥇🥇🥇
እንዲሁም ቻናላችን እዚህ ለማድረስ መልዕክቶቻችን ለሌሎች በማጋራት እና በአስተያየት ለደገፋችሁን በሙሉ ምስጋናችን በያላችሁበት ይድረሳችሁ ብለናል።
ወደፊትም ቻናላችን ከዚ የተሻለ እንዲሰራ አስተያየታችሁ አይለየን። የቻናላችን ተደራሽነት ለመጨመርም መልዕክቶቻችን ለጓደኞቻችሁ በማጋራት እርዱን። ሁላችሁንም እናከብራችኋለን፣እንወዳችኋለን፣ እናመሰግናለን።
💓💓💓💓💓💓
በፍቅር እንኑር
💓💓💓💓💓💓
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
#share

Читать полностью…

Relationships

ያላችሁን የፍቅር ታሪክ ወደ @mer677 ላኩልን፡፡ ብዙ like ለሚያገኘው ሽልማት አለው፡፡
#share
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

9 ወር አርገዛ ስንት ዓመት አጥበታ
ሳዝን እያዘነች ስስቅ እየሳቀች ይኸዉ
ዉለታሽን ልከፍል ብነሳ ያንቺ ፍቅር እጅጉን ከበደኝ ዘለአለም ብለፋ ፍቅርሽ በልጦ ታየኝ ዉዷ እናቴ ከስኬቴ ጀርባ
ያለሽዉ አንቺ ነሽ እምዬ ቃላት አጣሁልሽ
ስምሽን ስጠራዉ ጭንቄ ይለቀኛል መጭዉ አመት 2⃣0⃣1⃣1⃣ የሰላም የጤና ይሁንልሽ ከማንም እና ከምንም በላይ እወድሻለሁ

🤵ከ -- 9 ወር የተሸከምሽዉ ልጅሽ
👩 ለ - ዉዷ እናቴ
አስቲ 💝Like 💝like 💝share 💝share

Читать полностью…

Relationships

ለፍቅረኛህ አንድ ነገር ማድረግ ትፈልጋለህ ግን ምን ማድረግ እንዳለብህ አታውቅም፡፡ ወደ እኛ ብቅ በል በፍቅረኛህ ፎቶ ምርጥ ምርጥ የቴሌግራም ስቲከሮች እንሰራለን፡፡ እመነኝ ምርጥ surprise ነው፡፡ ትወድልሀለች፡፡

ስቲከር በትዕዛዝ አሳምረን እየሰራን ነው፡፡

ለማሰራት&
ቻናሉን ለመቀላቀል Click to join

Читать полностью…

Relationships

አብ ለሳላት🗯
አምላክ በጥበቡ አሳምሮ ሰራሽ
ከሁሉ ለይቶም የኔ ብቻ አረገሽ
እስትንፋሴ እስኪቆም ኑሮዬ እስኪያበቃ
ስወድሽ ኖራለው በማንም ሳልተካ
ሳፈቅርሽ ኖራለው በምንም ሳልተካ፤
የአምላክ ውድ ልጅ የራሱ አምሳያ
በጆቹ የሳለሽ የሌለሽ እኩያ
የኔው በኔው ተስፋ ለኔው መኖሪያዬ
ከኔው ያገኘውሽ የደም ክፍያዬ
ፍቅርን ሊያስተምረኝ እኔም እንዳስተምር
አንቺን ለኔ ዳረ እኛም ልጆች ልንድር
ከብቸኝነት ማቅ ከሀዘን ሊያወጣኝ
በጆቹ ሳለና አንቺን ለኔ ሰጠኝ
አብ ሳል አረገና እኔን ላንቺ አረገኝ
💚💛❤️
💙💜
🖤

Join @fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

በጆቼ እየዳሰስኩ እንዳላጫውትሽ
ሰው ከማይደርስበት ጋራ ስር ነው ቤትሽ
ጋራ ስር ነው ቤትብሽ
ጋራ ስር ነው ቤትሽ

🌹ከባርች ለሂንዲያ

Читать полностью…

Relationships

በቀጣይ ⏩⏩
የእውነት እንደሚያፈቅረኝ እና እንደሚያዛልቀኝ እንዴት አውቃለሁ?

#share
#invite

Читать полностью…

Relationships

Someone Like u:
🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸

የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ
የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ

የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ
የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ

🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸

የኔ ፍቅር ገኖ ካንተ በላይ
ወድጄህ ከንፌ አዲስ ሆኜ ብታይ
ለካ ይሄ ነው
የእውነት ጣዕም ውበቱ
ሳየው አፍቅሬ
ሳውቀው ገባኝ ስሜቱ

ያላረፈ ዓይኔ ወስዶ ካንተ ጣለኝ
አሳረፈው ልቤን በፍቅርህ ረታኝ
ለካ ይሄ ነው ክፍያው
ለታገሰ ጉርሻ ደሞዙ
ቆይቶ ሲክሰው በፈቀደው መያዙ

የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ
የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ

የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ
የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ

የወደድኩት አብልጬ
ሌላ የለኝም በቃ
ዉሰድ ሙሉ ፋንታህን
ልቤ ያንተ ነው በቃ
የወደድኩት አብልጬ
የለም ሌላ ሌላ ሰው
ሀገሬ ይወቅ እኔ ልኩራ
ልውጣ በከተማው

ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ

🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸

የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ
የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ

የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ
የመጀመሪያዬ ነው (ይሄ ለኔ)
ሰው ስወድ አምርሬ

🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸🎸

ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ
ሽር ልበል በጎዳናው ላይ
ይፋ ይውጣልኝ ማፍቀሬም ይታይ

የመጀመሪያዬ ነው . . . . .

Читать полностью…

Relationships

አካላዊ እንቅስቃሴዎች ለወንዶች
1. ከፍ ያለ ቅንድብ ከፈገግታ ጋር 2. ከንፈሯን ታረጥባለች/ትነክሳለች
3. የአይኗ ብሌን ይሰፋል
4. ከተለምዶው ፈጠን ያለ የአይን መርገብገብ
5. ወዳንተ ጠጋ ብላ ጠረጰዛውን ተደግፋ ትቀመጣለች
6. ጸጉሯን በእጇ እየጠቀለለች ታይሃለች
7. አንገቷንና ከንፈሯን የምትዳስስ ከሆነ ወይም ባደረገችው ጌጥ የምትጫወት ከሆነ
8. በያዘችው እቃ የምትጫወት ከሆነ 
✔️እንቅስቃሴዋ ቀስ ያለ ከሆነ ትኩረት እንድትሰጣት ፈልጋለች ማለት ነው። 
✔️የያዘችውን ነገር በጣቷ የምትጠበጥበው ከሆነ ተነስታ መሄድ ፈልጋለች ማለት ነው።
9 እግሮቿ ከተጣመሩና ላይኛው እግሯ ወዳንተ ከዞረ
10 በጨዋታ መሃል የምትነካህ ከሆነ
11 አይኖቻችሁ በተደጋጋሚ ይገናኛሉ
12. ከሌሎች ሰዎች ጋ ከምትስቀው በተለየ ካንተ ጋ ትስቃለች
13 አንተ የምታደርገውን የምታደርግ ከሆነ
14 ከላይ እስከ ታች አይታህ ፈገግ ካለች
15 ጭንቅላቷ ወዳንተ ዘመም ካለ
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
በፍቅር እንኑር
👫👫👫👫👫👫👫
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

አካላዊ እንቅስቃሴዎች

የሰዎችን ሁኔታ ከአካላዊ እንቅስቃሴያቸው ማወቅ ይቻላል። እንዲያውም ከቃላትም በላይ በሆነ መንገድ እንድናውቅ ይረዱናል። ሰዎች በአንደበታቸው ሊዋሹ ይችላሉ። ሰውነታቸው ግን አይዋሽም። በፍቅር ዉስጥ ደግሞ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን መረዳት ከብዙ ስህተት ያድነናል። አስደሳች ጊዜንም ለማሳለፍ ይጠቅመናል።
እኛም ለእናንተ ዉድ❣❣❣ ተከታዮቻችን እጥር ምጥን ባለና በሚስብ መልኩ አዘጋጅተንላችኋል።

ከእኛ ጋር ይቆዩ


በፍቅር እንኑር @fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

አምስቱ የፍቅር ቋንቋዎች

የሰው ልጆች ፍቅራችን የምንገልጽባቸው 5 ቋንቋዎች አሉን። እንደዚ ስል አማርኛ፣እንግሊዝኛ.....ለማለት አይደለም። እያንዳንዳችን ከ5ቱ የፍቅር ቋንቋዎች ዉስጥ ቢያንስ አንዱ የኛ መገለጫ ይሆናል። ፍቅረኛችን እኛ እየወደድናቸው እነሱ ግን እንደማንወዳቸው ሊሰማቸው ይችላል። ለዚህ ደሞ መፍትሄው 5ቱን የፍቅር ቋንቋዎች መረዳት ነው።

1 የሙገሳ(የማበረታቻ) ቃላት
የምንለው ተጓዳኛችን ማበረታታት፣ ማድነቅ፣ሊሰሩ ባሰቡት ነገር ላይ የተሻለ ጥንካሬና ብርታት እንዲኖራቸው ማድረግን ይመለከታል።

2. ጣፋጭ ና የማይረሱ ጊዜያትን አብሮ ማሳለፍ
እንደዚህ ስል ማለት የፈለኩት አብረን በምንሆንበት ጊዜ ለፍቅረኛ ሙሉና ያልተከፋፈለ አትኩሮት መስጠት ና በአካል ብቻ ሳይሆን በስሜት ደረጃም መቀራረብ ማለት ነው።

3 ስጦታዎችን መቀበል 💝🎁🌹
ስጦታ ማለት ስጦታውን ስትቀበሉ “ስለኔ እያሰበ ነበር” ወይም “አስታውሳኛለች” ብላቹ እንድታስቡ የሚያደርጋችሁ የፍቅር መገለጫ ነው። ስጦታ ማሳየት ያለበት ለፍቅረኛችሁ ማሰባችሁን ስለሆነ የግድ ዉድ ነገር መሆን አይጠበቅበትም።

4. በራስ በጎ ፈቃድ ለፍቅረኛ/ለትዳር ጓደኛ አገልግሎትን ማበርከት
ይሄ ማለት ለፍቅረኛ የሚፈልጉትን ነገር ማድረግን ና በስራ መርዳትን ይመለከታል።

5. አካላዊ ንክኪ አካላዊ ንክኪ ስንል እጅ ለእጅ👫 መያያዝ፣መተቃቀፍ፣ማሳጅ፣መሳሳም፣ ጾታዊ ግንኙነት የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።



የራሳችን የፍቅር ቋንቋ እንዴት ማዎቅ እንችላለን?
i. ነዝናዛ🙄 እስክትባሉ የምትጠይቁት ነገር
ii. ሳይደረግላቹ ቀርቶ የተጎዳችሁበት ነገር😥
iii. ፍቅራችሁን ለመግለጽ የምትጠቀሙበትን መንገድ በማስተዋል


እጅግ በጣም በአጭሩ ስለ 5ቱ የፍቅር ቋንቋዎች አቅርበንላችኋል የበለጠ ለማዎቅ ና ለአስተያየት Contact us @urmessagebot


Join @fikir_yishalegnal @fikir_yishalegnal @fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

መሰተፋቅር ለወንዶች ክፍል 3

sms ወይስ መደወል?

እኔ የምመክርህ እንድትደውል ነው።ለምን እንደሆነ እንይ

በመጀመሪያ ስልኳን የምትሰጠው ላንተ ብቻ አይደለም። በተለይ ቆንጆና ተፈላጊ ከሆነች።ስለዚህ አንተ ከሌሎቹ የተለየህ ሁነህ መገኘት አለብህ።ስለዚህ ከሁለት ሰዓታት በኋላ መደወል አለብህ ነገር ግን በጣም አትዘግይ ቢበዛ 12 ሰዓታት ከዛ አታሳልፍ።ስትደውል እንገናኝ ወይም ከዛ ጋ የተያያዘ ነገር መጠየቅ የለብህም።
አንተ፡ ሄይ “ስምህን” ነኝ።የሆነ ወሳኝ ነገር ሳልነግርሽ ረስቸው”

እሷ፡ ምን?
አንተ፡ “ጫማሽ ከልብስሽ ጋ አብሮ ይሄዳል” እመነኝ በጣም ትገረማለች።ማንም ከዚህ በፊት እንደዚ ብሏት እንደማያውቅ እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። በቀጣዩ ቀን ደውለህ እንገናኝ ብለህ ጠይቃት። የፈለከውን ብቻ መናገር ይኖርብሃል፣ዙሪያ ጥምጥም አትሂድ።ብዙ አታውራ።
አንተ፡ “ሃይ “ስምህን” ነኝ አስታወሺኝ?”
እሷ : አዎ
አንተ: “ትላንት አሪፍ ጊዜ ነበረን።ለምን ከሰሞኑ ተገናኝተን ራት አልጋብዝሽም አርብ ወይ ቅዳሜ”
እሷ፡”እእእ አላውቅም.....አርብ?”

አንተ፡ “ጥሩ ማታ 2 ላይ?”

እሷ፡”አንድ”
አንተ፡”እሽ እንገናኛለን”

💠ለምን መደወል አስፈለገ?ለምን sms አለመላክ አስፈለገ?
ምክንያቱም መደወልህ ወንድነትህን ያሳያል።ለመደወል እንዳልፈራህ ያሳያል።በ sms ጀርባ ለመደበቅ እንዳልወሰንክ ያሳያታል። ይሄ ደሞ እሷን ወዳንተ ይስብልሃል።
💠ለምን በቀጣዩ ቀን ደውለህ እንገናኝ ማለት አስፈለገ?
ምክንያቱም እሷም እያሰበች ነው ምትሆነው።”ትላንት ያወራሁት ልጅ ደስ ብየው ይሆን?” “ይደውል ይሆን?” እያለች ነው ሚሆን ስለዚህ ደውለህ የሁለታችሁንም ጉጉት መቁረጥ አለብህ።

💠ስለልብሷና ጫማዋ ማንሳቱ ለምን አስፈላጊ ሆነ?
ምክንያቱም ሴቶች ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን የሚያጠፉት የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች፣ጸጉር ቤት ና መዋቢያ እቃዎች ላይ ነው።ምክንያቱም መታየትን ይፈልጋሉ፣ ያንተን አትኩሮት መስረቅ ትፈልጋለች።
💠ከፈለግሽ እንገናኝ ብለህ መጠየቅ የለብህም ለምን?
ምክንያቱም አይሆንም እንድትል በር እየከፈትክላት ነው፡፡ በቃ አንተ ማድረግ ያለብህ እሷም ልታገኝህ እንደምትፈልግ አድርገህ ማውራት ነው።
💠ለምን አርብ ወይ ቅዳሜ ማለት አስፈለገ?
ፕሮግራምህ ጋ እስከተስማማ ድረስ የፈለከውን ቀን መምረጥ ትችላለህ። መቼ ብንገናኝ ይሻላል አትበል ምክንያቱም እሷን አነሳሽ እያደረግካት ነው። አንተ ነህ መምራት ያለብህ።በዛ ላይ ማንም ብዙ ማሰብ አይፈልግም።ስለዚህ ሁለት ምርጫ በመስጠት ሃሳብ አቅልላት። እንዲሁም አርብ እንገናኝ ብለህ አታስጨንቃት። አማራጭ ስጣት።
💠በመጀመሪያ ስልክ ብዙ ማውራት የለብህም።ለምን?
ምክንያቱም ለሷ ሊደብራት የሚችል ነገር የመናገር እድልህ ይሰፋል የምትፈልገውን ብቻ ከተናገርክ ስራ ፈትአለመሆንህን ታያለች።ጊዜህን በወሬ እንደማታጠፋ ታውቃለች። ከሁሉም በላይ ስላንተ ብዙ እንዳታውቅ ታደርጋታለህ ይህ ደሞ ስላንተ ለማወቅ ጉጉት እንዲኖራት ታደርጋለህ። “ምን አይነት ሰው ይሆን?” “የሚያመሳስለን ነገር ይኖር ይሆን?” እያለች እንድታስብ ትተዋታለህ።
❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
በክፍል 4 እንቀጥላለን።
👫👫👫👫👫
Comment @urmessagebot
💝💝በፍቅር እንኑር💝💝 @fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal
@fikir_yishalegnal

Читать полностью…

Relationships

መስተፋቅር ለሴቶች ክፍል 2

5 ግልጽ ሁኝለት ስላንች ሳያውቅ ባንች ፍቅር እብድ እንዲሆን አትጠብቂ። በግልጽ ካዋራሽው፣ሃሳባችሽን፣እቅዶችሽን፣ ህልሞችሽን ካካፈልሽው እንዳቀረብሽው ይሰማዋል።

6 ባልጠበቀው ሰአት ተገኝ የሆነ ኬክ፣ኩኪስ ወይ የሆነ የሚጠጣ ነገር ይዘሽለት በመገኘት ሰርፕራይዝ አድርጊው።በጣም ደስ ይለዋል። ሁሌም በሚታወቅና በሚጠብቀው ጊዜና ቦታ የሚያገኝሽ ከሆነ ይሰለቻል።

7 ስራ ፈት አትሁኝ የምትሰሪው ነገር ሊኖር ይገባል።የራስሽን ህይዎት ራስሽ መምራት አለብሽ።ቁጭ ብለሽ ቲቪ ስታይ የምትዉይ መሆን የለብሽም(የጤና እክል እስካላጋጠመሽ ድረስ)

8 ነዝናዛ እንዳትሆኝበት.... በየሰዓቱ ቴክስት እንዲያደርግልሽ ና እንዲደውል አትነዝንዢው። የምትሰሪው ነገር ይኑር ያልኩሽ እዚህ ላይ ነው። የምትሰሪው ነገር ካለሽ በየሰዓቱ ለምን አልደወለም እያልሽ ራስሽን አታስጨንቂም።
⏩⏩⏩
ክፍል 3 ይቀጥላል
💑💑💑💑💑💑💑💑💑💑
በፍቅር እንኑር

@fikir_yishalegnal
Comment @urmessagebot

Читать полностью…

Relationships

መስተፋቅር ለሴቶች ክፍል 1

ወንዶች ብዙም ዉስብስብ አይደሉም።ለመረዳት ቀላል ናቸው። አንድን ወንድ የሚከተሉትን መንገዶች በመጠቀም ካንች ዉጭ እንዳያስብ ማድረግ ትችያለሽ።
1 ራስሽን ሁኚ አንች አንች ነሽ። አንችን የምትመስል ሴት በዚች አለም የለችም። ያንች የሚሆነው ወንድም ያንችን ነገር የሚወድ ስለሆነ ራስሽን መሆን ትልቅ ነገር ነው።

2 በራስሽ ተማመኝ በራሷ የምትተማመን ሴት አበባ ንቦችን እንደምትስብ እሷም ወንዶች እሷን ብቻ እንዲያዩና እንዲያስቡ ማድረግ ትችላለች።

3 ራስሽን የምታከብሪ ሁኝ ማንም ቢሆን መከበርን ይፈልጋል።ለራስሽ ክብር የሌለሽ ከሆንሽ እሱንስ ከየት አምጥተሽ ታከብሪዋለሽ? ስለዚህ ራስሽን የምታከብሪ ና ለራስሽ ዋጋ የምትሰጭ እንዲሁም የራስሽ የሆነ መለኪያ መስፈርት ያለሽ መሆን አለብሽ።

4 ራስሽን ተንከባከቢ አንድን ወንድ ወዳንች ለመሳብ የግድ ሞዴሊስት መሆን አይጠበቅብሽም።ንጽህናሽን በመጠበቅ፥ የሰውነትሽን ቅርጽ በስፖርትና በአመጋገብ በማስተካከል እሱን ማማለል ትችያለሽ።
⏭⏭⏭
ክፍል 2 ይቀጥላል
🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
በፍቅር እንኑር
👫👫👫👫👫👫👫
@fikir_yishalegn


ለአስተያየት @urmessagebot

#share

Читать полностью…
Subscribe to a channel