fanatelevision | Unsorted

Telegram-канал fanatelevision - Fana Media Corporation S.C (FMC)

205011

This is FMC's official Telegram channel. For more updates please visit https://fanamc.com

Subscribe to a channel

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ከ310 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ተመርቆ ሥራ የጀመረው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ እስከ አሁን ከ310 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቀረበ፡፡ ፋብሪካው ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሲገባ በቀን 15 ሺህ ቶን (150 ሺህ ኩንታል) ሲሚንቶ የማምረት አቅም እንዳለውም ለፋና ዲጂታል አስታውቋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በከፊል…

https://www.fanabc.com/archives/276558

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ሀገር አቋራጭ መንገዶች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተደረገባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017(ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር አቋራጭ መንገዶች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እየተደረገባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፋንታ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ትላልቅ መንገዶች ላይ አስተማማኝ ጥበቃ እየተደረገ ነው፡፡ ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ባሕርዳር፣ ሰመራ፣ ጅቡቲ፣ ሞያሌ፣ ነቀምቴ፣ ደምቢዶሎ፣…

https://www.fanabc.com/archives/276553

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የፈረንጆቹን የገና በዓል ለሚያከብሩ ሁሉ መልካም ምኞታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመላው ዓለም የፈረንጆቹን የገና በዓል ለሚያከብሩ ሁሉ የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላለፉ፡፡

በመልዕክታቸውም ለኢትዮጵያ ወዳጆች፣ ለዳያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት እና ለአጠቃላይ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በዓሉ በሰላም፣ በጤና እና በአብሮነት የተሞላ እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የዕለቱ የምንዛሪ ዋጋ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

https://www.youtube.com/watch?v=l2HeVVaQGH0

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የሰላም ሚኒስቴርና ቤተ-ክርስቲያኗ በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን በሀገራዊ የሰላም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል። የሰላም ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሀገሪቱ የተጀመረውን ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል በሚችልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በውይይቱ÷ ቤተ-ክርስቲያኗ ከመንግስት…

https://www.fanabc.com/archives/276532

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የሞባይል ቀፎዎችንና ካርዶችን ለግል ጥቅሙ አውሏል የተባለው ሰራተኛ በእስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የሞባይል ቀፎዎችንና ካርዶችን ለግል ጥቅም አውሏል የተባለው የቀድሞ የህዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር ሰራተኛ በእስራት መቀጣቱ ተነግሯል፡፡ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የድሬዳዋ ምድብ ጅግጅጋ ተዘዋዋሪ ወንጀል ችሎት ዛሬ በዋለው ቀጠሮ መስፍን ኣሰፋ በተባለ ተከሳሽ ላይ የግራ ቀኝ ማስረጃዎች መርምሮ ጥፋተኛ በማለት…

https://www.fanabc.com/archives/276526

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የአሜሪካ አየር መንገድ በረራዎች እንዲቆሙ ተደርገው እንደነበር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በዛሬው ዕለት በቴክኒክ ችግር ምክንያት የአሜሪካ አየር መንገድ በረራዎች በመላው ሀገሪቱ እንዲቆሙ ተደርገው እንደነበር ተገለጸ። ለአንድ ሰዓት ገደማ የቆየው እገዳ አሁን ላይ የተነሳ ሲሆን÷ አየር መንገዱ ችግሩን በተቻለ መጠን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ እየሰራ መሆኑን አስታውቆ ደንበኞቹን ይቅርታ ጠይቋል። በረራዎች በሚበዙበት በገና ዋዜማ ወቅት የአሜሪካ አየር…

https://www.fanabc.com/archives/276520

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ናሳ ለፀሐይ ቅርብ በሆነ ርቀት መንኮራኩር ለማሳለፍ ጥረት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ጣቢያ (ናሳ) ፓርከር ሶላር ፕሮብ ለፀሐይ ቅርብ በሆነ ርቀት መንኮራኩሩን ለማሳለፍ ጥረት እያደረገ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ ከምድር በ6 ነጥብ 2 ሚሊየን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው መንኮራኩር ፀሐይን በቅርብ ርቀት ለማሳለፍ እየጣረ ሲሆን፤ ሙከራው እስከዛሬ ከተደረጉት ሙከራዎች የአሁኑ ለፀሐይ የቀረበ መሆኑ ተነግሯል። መንኮራኩሩ…

https://www.fanabc.com/archives/276510

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ መሰረተ ቢስ መሆኑን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ዶሎ በተባለ ከተማ በተፈጠረው ክስተት የኢትዮጵያ ኃይሎችን መክሰሱ ኢትዮጵያን ማስቆጣቱን እና ክሱም ሀሰተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሀሰተኛ ውንጀላው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማስተካከል የተጀመረውን ጥረት ለማስተጓጎል የታለመ ነው ብሏል።…

https://www.fanabc.com/archives/276499

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

https://www.youtube.com/watch?v=hMCM5H50VH0

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የአንካራው ስምምነት እንዳይፈጸም የሚጥሩ አካላትን ተፅዕኖ ለመከላከል መከሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የደኅንነት ተቋማት የአንካራው ስምምነት ተፈጻሚ እንዳይሆን እንቅፋት የሚፈጥሩ አካላትን ተፅዕኖ ለመከላከል ምክክር አደረጉ፡፡

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የተቋሙ ስትራቴጂክ አመራሮች ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የሶማሊያ ናሽናል ኢንተለጀንስ ኤንድ ሴኪዩሪቲ ኤጀንሲ ዳይሬክተር አብዱላሂ ሞሐመድ ዓሊ ጋር በወቅታዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የአንካራውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ጋር በተያያዘ ከሁለቱ ሀገራት አቻ ተቋማት የሚጠበቁ የትብብርና የአጋርነት መስኮች ላይ ውይይት መደረጉን አገልግሎቱ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የላከው መረጃ አመላክቷል፡፡

በውይይቱም የኢትዮጵያና ሶማሊያ የደኅንነትና የጸጥታ ተቋማት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዳይሆን እንቅፋት የሚፈጥሩ አካላትን ለመከላከል የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት የጋራ መግባባት መድረሳቸው እና በተለይም በመረጃ ልውውጥ አቅጣጫ መቀመጡ ተገልጿል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/276483

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የባኔ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የ”ማሮ” በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባኔ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የ ”ማሮ” በዓል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቀይ አፈር ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች እየተከበረ ነው። ከጥንት ጀምሮ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እየተከበረ ለዛሬው ትውልድ የተሸጋገረው የማሮ በዓል የተለያዩ ባህላዊ እሴቶች እንዳሉት ተገልጿል። በዓሉ የተጣሉ እርቅ የሚያወርዱበት፣ ለተቸገረ ድጋፍ የሚደረግበትና በአብሮነት የሚከበር መሆኑም ተጠቁሟል።…

https://www.fanabc.com/archives/276474

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

በቱርክ በደረሰ ፍንዳታ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜን-ምዕራብ ቱርክ ባሊኬሲር ከተማ በአንድ የጦር መሣሪያ እና ፈንጂ ፋብሪካ ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ የ12 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡ የአዳጋው መንስዔ አለመታወቁን እና ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ሁኔታውን መቆጣጠር መቻሉን የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዬርሊካያ ተናግረዋል፡፡ አደጋውን ተከትሎ የእሳት አደጋ ቡድንን…

https://www.fanabc.com/archives/276463

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የአረንጓዴ ዐሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር አዋጅ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በደን ዘርፍ ከልማት አጋሮች የምታገኘውን ድጋፍና ጥቅም ለማሳደግ የሚያስችል የአረንጓዴ ዐሻራና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያና አሥተዳደር አዋጅ ፀደቀ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 12ኛ መደበኛ ስብሰባ÷ የአረንጓዴ ዐሻራ እና የተጎሳቆለ መሬት ማገገሚያ ልዩ ፈንድ ማቋቋሚያ እና አሥተዳደር አዋጅን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/276454

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ዋሊያዎቹ የቻን የመልስ ጨዋታቸውን ከሱዳን አቻቸው ጋር ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ከሱዳን አቻው ጋር ያደርጋል፡፡ የሁለቱ ቡድኖች የቻን የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ 11 ሠዓት ላይ በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል። ብሔራዊ ቡድኑ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በሱዳን 2 ለ 0 መሸነፉ ይታወሳል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/276548

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

#Tecno_Phantom_V2_Series

አዲሱ ቴክኖ ፋንተም ፎልድ ቪ2 ከመቼውም በበለጠ ረጅም የባትሪ ቆይታ እንዲኖረው ተሻሽሎ የመጣ ሲሆን በትንሽ የባትሪ ቻርጅ ለረጅም ሰዓት በሁለቱም ስክሪኖቹ በርካታ ስራን ለመከወን ያስችላል፡፡

#TecnoAI #PhantomV2Series #ExtraFoldEasyFlip

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደንበኞች ቁጥር 4 ነጥብ 9 ሚሊየን ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበጀት ዓመቱ 600 ሺህ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየሠራሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል፡፡ ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ጀምሮ 167 ሺህ 952 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን እና አጠቃላይ የደንበኞቹ ቁጥርም 4 ሚሊየን 936 ሺህ 912 መድረሱን ተቋሙ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡ በሀገር…

https://www.fanabc.com/archives/276545

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ለወራት ጠፈር ላይ እንዲቆዩ የተገደዱት ጠፈርተኞች ለገና በዓል መልካም ምኞት ላኩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንኮራኩራቸው በገጠማት የቴክኒክ ችግር ምክንያት ጠፈር ላይ ለወራት እንዲቆዩ የተገደዱት የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ጣቢያ (ናሳ) ጠፈርተኞች ለገና በዓል መልካም ምኞታቸውን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልከዋል፡፡ ሱኒታ ዊልያምስ፣ ባሪ ዊልሞር፣ ዶን ፔቲት እና ኒክ ሄግ የተባሉት እነዚህ ጠፈርተኞች በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሰኔ 5 ቀን2024 ለስምንት ቀናት የሙከራ በረራ ለማድረግ…

https://www.fanabc.com/archives/276542

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

https://www.youtube.com/watch?v=Qlv-yQOWK-o

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ራምታን ላማምራ ጋር ተወያይተዋል ፡፡ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) በውይይቱ ÷ ለሱዳን ሰላም ለማምጣት በተለያዩ ወገኖች የተጀመሩ ጥረቶችን አሰባስቦ ወደ አንድ ውጤታማ አቅጣጫ መምራት እንደሚገባ ገልጸዋል። ራምታን ላማምራ በበኩላቸው ÷በሱዳን ያለው ግጭት የፈጠረውን…

https://www.fanabc.com/archives/276529

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎ(ዶ/ር)ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸው ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማሻሻል እና በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ማስጠበቅ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

https://www.fanabc.com/archives/276523

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ዩኒቨርሲቲው ለ5 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ለአምስት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት፡- 1. ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም……. በስፔሻል ኒድስ ኤጁኬሽን 2. ዶ/ር አስራት ወርቁ ……………. በጂኦቴክኒክስ ኢንጂነሪንግ 3. ዶ/ር መኮንን እሸቴ ……………. በፕላስቲክ ሰርጀሪ 4. ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ ……………… በፐብሊክ ሄልዝ 5.…

https://www.fanabc.com/archives/276517

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

በድሬዳዋ የመደመር ትውልድ ቤተ-መፃህፍት ግንባታ 50 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢንሼቲቭ እየተገነባ ያለዉ የመደመር ትውልድ ቤተ-መፃህፍት ግንባታ 50 በመቶ መድረሱ ተገለፀ። ቤተ መፃህፍቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተፃፈው የመደመር ትውልድ መፅሃፍ ሽያጭ ገቢ እየተገነባ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ የተመራ ልዑክ የቤተ መፃፍቱን የግንባታ ሂደት…

https://www.fanabc.com/archives/276504

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

https://www.youtube.com/watch?v=esDwgTyrXZE

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ግብፅ ደንግጣለች…አንድ ጉዳይ - ረቡዕ ምሽት ይጠብቁን

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ብሪክስ 9 ሀገራትን በአባልነት እንደሚቀበል ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንጆቹ 2025 መባቻ ብሪክስ ዘጠኝ ሀገራትን በአባልነት እንደሚቀበል ተገለፀ፡፡ በሶስት አህጉራት የሚገኙት አዲስ አባል ሀገራቱ ቤላሩስ፣ ቦልቪያ፣ ኢንዶኖዥያ፣ ካዛኪስታን፣ ኩባ፣ ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኡጋንዳ እና ኡዝቤከስታን መሆናቸው ታውቋል፡፡ የአዲስ አባል ሀገራቱ የአባልነት ጥያቄ ቀደም ሲል በሩሲያ ካዛን በተካሄደው 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መፅደቁ ነው የተገለፀው፡፡…

https://www.fanabc.com/archives/276480

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ኮሚሽኑ የኦሮሚያ ክልልን አጀንዳ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኦሮሚያ ክልልን አጀንዳ ተረክቧል፡፡

ኮሚሽኑ በአዳማ ከተማ ለዘጠኝ ተከታታይ ቀናት ሲያካሄድ የቆየውን የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ አጠናቅቋል፡፡

በዚህም ከአምስቱ ባለድርሻ አካላት የተመረጡ 25 ወኪሎች አጀንዳዎቹን አደራጅተው ለኮሚሽነሮች ያስረከቡ ሲሆን ፥ የአጀንዳ አሰባሰብ ምዕራፉ ነፃና ግልጽ ሆኖ መጠናቀቁን ...

https://www.fanabc.com/archives/276471

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

አምባሳደር ምስጋኑ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ሞሃመድ ኦማር ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸው ÷የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ማጠናከር እና የአንካራውን ስምምነት መተግበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል፡፡ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምን ለማስፈን እና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር እንደሚገባ የተናገሩት…

https://www.fanabc.com/archives/276464

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ያለመ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል ያለመ ሀገር አቀፍ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ በድሬዳዋ ተካሂዷል። መርሐግብሩ ማህበራዊ እሴቶችን ለማጎልበትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑ እንዲሁም ወጣቶችን ከመጤ ባህል ወረርሽኝ ለመጠበቅና በዘርፉ በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ለማስቻል ያለመ ነው ተብሏል። በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችና በእግር ጉዞ መርሐግብሩን ያስጀመሩት የባህልና…

https://www.fanabc.com/archives/276451

Читать полностью…
Subscribe to a channel