fanatelevision | Unsorted

Telegram-канал fanatelevision - Fana Media Corporation S.C (FMC)

209814

This is FMC's official Telegram channel. For more updates please visit https://fanamc.com

Subscribe to a channel

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉን አስመልክቶ ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል:- እንኳን ለኢሬቻ መልካ በሰላም አደረሳችሁ ኢሬቻ የኦሮሞ የምስጋና ስርዓት ነው፡፡ ኦሮሞ የሰው ዘር አፍርቶ የሚባዛው የተዘራው ሞቶ በመነሣት ፍሬ የሚያፈራው በፈጣሪ ድጋፍና እርዳታ ነው…

https://www.fanamc.com/archives/301839

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ኢትዮጵያ የገነባችው የነዳጅ ማጣሪያ የኢነርጂ ሉዓላዊነት ጉዞ አንዱ አካል ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቻይናው ጂሲኤል ግሩፕ ፕሬዚዳንት ዡ ጎንግሻን ኢትዮጵያ የገነባችው የነዳጅ ማጣሪያ የሀገሪቱ ኢነርጂ ሉዓላዊነት ጉዞ አንዱ አካል ነው አሉ።

በዛሬው ዕለት የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ምርቃት እና ሁለተኛ ዙር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

መርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ዡ ጎንግሻን የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት ካፈራው ፍሬ መካከል በጎዴ ላይ የተገነባው የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት አንዱ ነው ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት ኢትዮጵያ ጠንካራ እድገት ያላት ኢኮኖሚ ባለቤት ሆናለች፤ ይህም የጂሲኤል ግሩፕ ከሀገሪቱ ጋር እንዲሰራ ይበልጥ አነቃቅቶታል ነው ያሉት።

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ ለምታደርገው የኢንዱስትሪ እና የኢነርጂ ሽግግር አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተው÷ ለኢትዮጵያ እና ቻይና የጠነከረ የሁለትዮሽ ትስስርም ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።

ለፕሮጀክቱ መጠናቀቅ አስተዋጽዖ ላበረከቱ የኢትዮጵያን መንግሥትን ጨምሮ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ እና ሌሎች አጋር አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በሶስና አለማየሁ

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የዳንጎቴ ግሩፕ አፍሪካን አፍሪካዊያን ናቸው የሚያለሙት ብሎ ያምናል – አሊኮ ዳንጎቴ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዳንጎቴ ግሩፕ አፍሪካን አፍሪካዊያን ናቸው የሚያለሙት ብሎ ያምናል አሉ የግሩፑ ባለቤት አሊኮ ዳንጎቴ። በሶማሌ ክልል የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚገነባው የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀምጧል። የዳንጎቴ ግሩፕ ባለቤት አሊኮ ዳንጎቴ በዚህ ወቅት÷ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ኢንቨስተሮችን መሳብ የምትችል ሀገር…

https://www.fanamc.com/archives/301826

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ምርቃት እና ሁለተኛ ዙር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በምስል፡-

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

አሊኮ ዳንጎቴ ስለ ማዳበሪያ ፋብሪካው እና ኢትዮጵያ ምን አሉ?

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የኢትዮጵያውያን ብልጽግና ሳናረጋግጥ አንተኛም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያውያን ብልጽግና ሳናረጋግጥ አንተኛም አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ ባስቀመጡበት ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያውያን የብልጽግና ደረጃ ላይ ለማድረስ ስራችንን በትጋት እንጀምራለን ተግተንም እንጨርሳለን። ተግተን ጀምረን ተግተን እንድንጨርስ፤ ተግተው የሚተቹ እና…

https://www.fanamc.com/archives/301820

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ መቀመጡን ተከትሎ ያስተላለፉት መልዕክት፡-

👉ትላልቅ ነገር ለመጀመር፣ የጀመርነውን ለመጨረስ፣ የኢትዮጵያን ልክ ለማስተካከል፣ ወደሚገባን የብልጽግና ማማ ለመውጣት በምናደርገው ጥረት ሁሉ መከናወን የሰጠን የተናገርነውን እንድንተገብር የረዳን ፈጣሪያችን የተመሰገነ ይሁን

👉እያንዳንዱ ስኬት ተሰናስሎ የኢትዮጵያ ማንሰራራት እውን ማድረግ እንዲችል ነው ዋና ትልሙ

👉ይህ ቀን ለኢትዮጵያዊያን ታላቅ ቀን ነው፤ ስለሆነም ለመላው ኢትዮጵያዊንና የኢትዮጵያ ወዳጆች እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ

👉ዛሬ ለሶማሌ የብልጽግና ፀሐይ ወጣላት፤ ይህ ብርሃን በመላ ኢትዮጵያ እስኪረጋገጥ እያንዳንዱ ዜጎቻችንን ካሉበት የድህነት አረንቋ አውጥቶ ወደሚገባቸው የብልጽግናና የልማት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ እኔና እናንተ የሚጠበቅብን መትጋት መስራትና መጨረስ ብቻ ነው

👉እኛ እንጀምራለን፣ እኛ ተግተን እንሰራለን፣ እኛ እንጨርሳለን፤ ተግተን ጀምረን እንድንጨርስ ግን ተግተው የሚተቹና ተግተው የሚዋሹ ያስፈልጋሉ፤ እነሱ ይዋሻሉ እኛ እንሰራለን፤ እነሱ ያወራሉ እኛ እንከናወናለን

👉በስራዎቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን ከፍ እናረጋለን፤ በስራዎቻችን ሁሉ ብልጽግናን እናረጋግጣለን ይህ እስኪሆን ድረስ የማንተኛ መሆናችንን በድጋሚ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መግለጽ እወዳለው

በአድማሱ አራጋው

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ከጎዴ https://youtu.be/yN3sok5R_7o

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ህልማችን ሩቅ ነው ፤ ተስፋችን የሚጨበጥ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ኢትዮጵያ በመድኃኒት ቁጥጥር የዓለም ጤና ድርጅትን 3ኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ ማግኘቷ...

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት 3ኛ ደረጃ የብቃት ማረጋገጫ (ማቹሪቲ ሌቭል ስሪ) ማሳካቷ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው። የጤና ሚኒስቴር እና ኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ኢትዮጵያ በዓለም ጤና ድርጅት በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገራት የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካላት ምደባ ማቹሪቲ ሌቭል ስሪ ላይ መድረሷን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። “ማቹሪቲ ሌቭል…

https://www.fanamc.com/archives/301810

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለው የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ምርቃት በምስል፡-

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የሰላም እና የዕርቅ ምልክት ሲንቄ …

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኦሮሞ እናቶች በቁመታቸው ልክ በተዘጋጀች እና ቀጥ ካለ የተመረጠ የሃሮሬሳ ዘንግ የምትዘጋጅ የሲንቄ በትር ያገባች ሴት የምትይዘው ልዩ መለያቸው ናት። የሲንቄ በትር በቀላሉ የማይሰበር፤ ልጃገረድ በሰርግ ቀን በእናቷ ለሙሽሪት የሚሰጥ የክብር ስጦታዋ ሲሆን በኦሮሞ ባሕል ውስጥ ትልቅ እና ልዩ ስፍራ ይሰጠዋል። ይህች የሲንቄ በትር ለዕይታ…

https://www.fanamc.com/archives/301800

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩ የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች መደበኛ የዳኝነት አገልግሎት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በከፊል ዝግ ሆነው የቆዩ የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል፡፡ የክልሉየዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ ዳኛ ፈዬራ ሀይሉ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ በክረምቱ በከፊል ዝግ የነበሩ ፍርድ ቤቶች ዳኞች ውዝፍ መዝገቦችን በማጥራት እና የዜጎችን መብት ለማስከበር በተረኛ ችሎት አገልግሎት ሲሰጡ ነበር። እነዚህ…

https://www.fanamc.com/archives/301796

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ለባሕር በር ጥያቄ ምላሽ የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሻራ …
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ያነሳችው የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል አሉ ምሁራን። ምሁራኑ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያውያን ለጥያቄው ምላሽ ማግኘት አቅማቸው በሚፈቅደው ልክ አሻራቸውን ማኖር አለባቸው። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአሜሪካና አውሮፓ ጉዳዮች አማካሪ ሽመልስ ኃይሉ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ…

https://www.fanamc.com/archives/301736

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ፕሮጀክቶቹ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ስኬት ናቸው - አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሃመድ በጎዴ የተገነባው የነዳጅ ማጣሪያ እና የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካዎች የኢትዮጵያ ታሪካዊ ስኬቶች ናቸው አሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር ምርቃት፣ ሁለተኛ ዙር ማስጀመሪያ እንዲሁም የዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ የመሰረተ ድንጋይ አስቀምጠዋል።

አቶ መስጠፌ ሙሃመድ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንዳሉት÷ ፕሮጀክቶቹ ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗን ያሳየ ነው።

ትላንትና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማጠናቀቅ አጀንዳችን የነበረ፤ ዛሬ ደግሞ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ስራ ከአጀንዳዎቻችን መካከል አንዱ ይሆናል ሲሉ አስረድተዋል።

የሶማሌ ክልል እምቅ ሃብት ያለው በመሆኑ ኢንቨስተሮች ወደ ክልሉ በመምጣት እድሎችን እንዲመለከቱም ጥሪ አቅርበዋል።

በሶስና አለማየሁ

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

በሶማሌ ክልል የተጀመሩትን ሜጋ ፕሮጀክቶች በተመለከተ የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ ያስተላለፉት መልዕክት

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

መትጋት፣ መስራት፣ መጨረስ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የቻይናው ጂሲኤል ኩባንያ ሊቀመንበር በኦጋዴን ጋዝ ፕሮጀክት ምረቃ ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

https://youtu.be/48SLQmAaC6M

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

3 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዛሬ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቀን ሪቫን እንቆርጣለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእርግጠኝነት ለኢትዮጵያውያን ማረጋገጥ የምፈልገው 3 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዛሬ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን አጠናቅቀን ሪቫን እንቆርጣለን አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የመጀመሪያ ዙር የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ባስመረቁበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ፕሮጀክቱ 1 ሺህ ሜጋ ዋት (በኢነርጂ የማምረት አቅም የሕዳሴን…

https://www.fanamc.com/archives/301823

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ኢትዮጵያውያን በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማምጣት አብረን መስራት አለብን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያውያን ዓይናችንን ገልጠን በማየት በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማምጣት በጋራ አብረን መስራት አለብን አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሌ ክልል ለተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች መሰረተ ድንጋይ ባስቀመጡበት እንዲሁም ባስመረቁበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢትዮጵያን ለማስተዳደርና ለማልማት ያላትን ፍሬ እየበተንን ሳይሆን እየሰበሰብን መሆን አለበት…

https://www.fanamc.com/archives/301817

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

የእያንዳንዱ ስኬት ዓላማ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ዕውን ማድረግ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የእያንዳንዱ ስኬት ዓላማ ተሰናስሎ የኢትዮጵያን ማንሰራራት ዕውን እንዲሆን ማድረግ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ መሰረተ ድንጋይ መቀመጡን ተከትሎ ባስተላለፉት ምልዕክት ነው ይህንን ያሉት። ዛሬ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አነቃቂ እና ለኢትዮጵያ…

https://www.fanamc.com/archives/301793

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ዛሬ የተጀመረው ሁለተኛው ዙር የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት…

👉በዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ሊትር ጋዝ የማምረት አቅም አለው

👉ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1000 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ዛሬ የተመረቀው የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ…

👉በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችል ነው

👉የመጀመሪያ ዙር የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ነው

👉ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረታችን የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል

👉ለኃይል ማመንጫ እና የክሪፕቶ ማይኒንግ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ያቀርባል

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ልማት በሰጠችው ትኩረት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሰረት እየጣለች ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ልማት በሰጠችው ትኩረት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሰረት እየጣለች ነው አሉ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ። በኢትዮጵያ መንግሥትና በዓለም ባንክ በጋራ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ የሰው ሃብት ልማት ፎረም 2025 በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው። አፈ ጉባዔ ታገሰ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የሀገርን ሁለንተናዊ እድገትና…

https://www.fanamc.com/archives/301806

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር የሚያመርተው የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በሶማሌ ክልል ካሉብ በዓመት 111 ሚሊየን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀናል ብለዋል።

በተመሳሳይ በዓመት 1 ነጥብ 33 ቢሊየን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር አስጀምረናል ነው ያሉት፡፡

ከፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ ምርት ባሻገር በኃይል ማመንጫ ዘርፉም 1 ሺህ ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም በመያዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

ከሁሉም በላይ ፕሮጀክቱ የጋዝ ማምረቻ ብቻ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ ለማዳበሪያ ማምረቻ ወሳኝ የሆነውን ግብዓት በማቅረብ ለምግብ ሉዓላዊነት ጥረታችን የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

ለኃይል ማመንጫ እና የክሪፕቶ ማይኒንግ ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን እንደሚያቀርብም አብራርተዋል።

ዛሬ በሶማሌ ክልል የተጀመሩት ከተያያዥ መሠረተ ልማቶች ግንባታ ጋር በአጠቃላይ ወደ 10 ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ሜጋ ፕሮጀክቶች በተገቢ ክትትል እስከ መጠናቀቂያቸው ይደርሳሉ ነው ያሉት፡፡

የጀመርነውን ለመጨረስ ሁልጊዜም በጽናት እንደሠራነው ሁሉ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ይደርሳሉ ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) አጽንኦት ሰጥተዋል።

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ማስታወቂያ!

መቼም ስለ አዲሱ የቴክኖ ካሞን 40 ስልክ የካሜራ ብቃት ሰምታችኋል!

በበተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በካሞን 40 ብቻ የተነሱ እጅግ አስገራሚ ፎቶዎችን መመልከት የሚችሉበት፣ ስልኩን በቅርበት ማየት እና መሞከር የሚችሉበት፣ የቴክኖ ምርቶችን እና በርካታ ሽልማቶች የሚያሸልሙ ጨዋታዎችን የሚጫወቱበት እና በሙዚቃ ዝግጅት ፈታ ዘና የሚሉበት ትልቅ ኤግዝቢሽን ተዘጋጅቷል።

ይሄ ሁሉ ጥቅምት 1 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ እስከ አመሻሽ ሳሊተምህረት መንገድ የተባበሩት አደባባይ በሚገኘው በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ለእናንተ በቴክኖ ኢትዮጵያ ተዘጋጅቷል፡፡

ኑ ተዝናኑ፣ ተሸለሙ ሀገራችሁን በፎቶ ይመልከቱ ቅዳሜ ጥቅምት 1 አይቀርም!

#TecnoCamon40Series #FlashSnap #TecnoAI

@tecno_et

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

ኢሬቻ በድምቀት እንዲከበር ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት እየተሠራ ነው - ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፌደራል ፖሊስ የሆረ ፊንፊኔ እና ሆረ ሀርሰዲ ኢሬቻ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል። ፌደራል ፖሊስ የኢሬቻ በዓላት አከባበርን በተመለከተ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ጋር ውይይት አካሂዷል። ‎ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የፀጥታና ደኅንነት መዋቅሩ ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር ኃላፊነቱን እየተወጣ በመሆኑ…

https://www.fanamc.com/archives/301788

Читать полностью…

Fana Media Corporation S.C (FMC)

አዲስ የተገነባው የሶማሌ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

Читать полностью…
Subscribe to a channel