29777
በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
✞ንብ ሁኑ ዝንብ አትሁኑ!
አንዳንድ ሰዎች በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚመለከቱት ትክክል ያልሆኑ ነገሮች እጅግ ሐፍረት እንደሚሰማቸው በማዘን ይነግሩኛል። ለነዚህ ሰዎች እንዲህ ብዬ እነግራቸዋለሁ:- ዝንብን “እዚህ አካባቢ አበቦች ይታዩሻል” ብላችሁ ጠይቋት።
ዝንቧም “ ስለ አበባዎች አላውቅም። ነገር ግን እዚያ ጋር ትልቅ የቆሻሻ ክምር አለ በዚያ የምትፈልጉትን አይነት የሚሸት ቆሻሻ ታገኛላችሁ” ብላ ትመልስላችኋለች። ካስፈለገ ስለ ቆሻሻው ዝርዝርና በቦታው ስለሚገኝ ንጹህ ያልሆነ ነገር በቂ ማብራሪያ ትሰጣችኋለች። ንብን ደግሞ “በዚህ አካባቢ ንጹሕ ያልሆነ ቆሻሻ ቦታ ታውቂያለሽ” ብላችሁ ብትጠይቋት “ ቆሻሻ? በጭራሽ! እዚህ አካባቢ አይቼም አላውቅም! ይህ ቦታ እጅግ ውብ በሆኑ ቆንጆ መዓዛ ባላቸው አበቦች የተሞላ ነው” ብላ ትመልስላችኋለች። በአትክልት ስፍራውና በሜዳው ስላሉ አበቦች ውበትና ዝርዝርም ትነግራችኋለች። አስተዋላችሁ? ዝንብ የምታውቀው ቆሻሻንና ቆሻሻ ያለበትን ቦታ ነው ንቢቱ ግን ውብ አበቦች እና ሰናይ መዓዛ ያለበትን ቦታ ነው የምታውቀው።
አንዳንድ ሰው እንደ ዝንብ ነው። አንዳንድ ሰው ደግሞ እንደ ንብ። እንደ ዝንብ የሚያስቡት በሁሉም አጋጣሚ የሚያዩት መጥፎውን ሲሆን በመጥፎው ሃሳብም ቀድመው የተሞሉ ናቸው። መልካም ቢኖር እንኳ አይታያቸውም። ንቦቹ ግን በሚመለከቱት ነገር ውስጥ ሁሉ መልካሙን ያያሉ። ስሑት የሆነ እና በጎ ሕሊና የሌለው ሰው ሁሉን ነገር ስሑት አድርጎ ያስባል። ሁሉንም ነገር በመጥፎ መንገድ ይመለከታል። በጎ ሕሊና ያለው ሰው ግን ምንም ዓይነት ነገር ቢመለከት ምንም አይነት ነገር ብትነግሩት መልካምና ቀና ሀሳብን እንደያዘ ይቀጥላል።
አንድ ጊዜ የሆነ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪ ወደኔ በዓት መጣና በበሩ ላይ ባለው የመጥሪያ ብረት አንኳኳ። በወቅቱ በርግጥ ብዙ ደብዳቤዎችን እያነበብኩ ቢሆንም ምን እንደፈለገ ወጥቼ ለማየት ወሰንኩ። “ ምን ፈለግክ የኔልጅ?” አልኩት። “ የአባ ፓይሲዮስ በዓት ነው?” ሲል ጠየቀኝ። አክሎም “አባ ፓይሲዮስን ላገኛቸው እፈልጋለሁ” አለኝ። “በርግጥ የአባ ፓይሲዮስ በዓት ነው ነገር ግን አባ ፓይሲዮስ ሲጋራ ሊገዛ ወጥቷል” ስል መለስኩለት። “ የሆነ ሰው ሊረዱ ነው የሄዱት በርግጠኝነት” ሲል መለሰልኝ። “አይ ለራሱ ነው የሚገዛው ሲጋራውን” አልኩት። “የነበረውን በሙሉ አጭሶ ጨርሷቸዋል። ሲጋራ በጣም ነው የሚወደው። እኔን እዚህ ብቻዬን ትቶኝ ነው የሄደው መቼ እንደሚመለስ እንኳን አላውቅም። የሚቆይ ከሆነ እኔ ራሱ ጥዬ መሄዴ ነው” አልኩት። የተማሪው ዐይን እንባን አቅርሮ ውስጣዊ ስሜቱን አሳበቀበት። ነገር ግን አሁንም በበጎ ሕሊና እና በቀና ሀሳብ “አባ ፓይሲዮስን እንደኔ ያለነው ነን ያሰቃየናቸው” ሲለኝ “ ቆይ ለምን ልታገኘው ፈለግህ” አልኩት “ቡራኬ ልቀበል ነው” አለኝ “ አንተ ሞኝ ከእርሱ ምን አይነት ቡራኬ ነው የምትጠብቀው ለራሱ የተታለለ ሞኝ ነውኮ! እኔ በደንብ አውቀዋለሁ። በርሱ ውስጥ ምንም ጸጋ እግዚአብሔር የለም። ይመለሳል ብለህ እሱን በመጠበቅ ጊዜህን አታባክን ጠጥቶም ሊሆን ይችላል የሚመጣው በጣም ጠጪም ነው በዛ ላይ” አልኩት። ይህንን ሁሉ እየነገርኩት ሁሉ ያ ወጣት ልጅ አሁንም መልካም ማሰቡንና በጎ ሕሊናውን አልጣለም። በመጨረሻም “ ይኸውልህ እኔ እስኪመጣ ጥቂት እጠብቀዋለሁ ምን ልንገርልህ ንገረኝና ሂድ” ስለው “ የምሰጣቸው ደብዳቤ አለ በዚያም ላይ ሲመጡ ቡራኬ ተቀብዬ ነው የምሄደው” ብሎ ከነገርኩት ከዚህ ሁሉ ቆሻሻ ውስጥ መልካም ነገር ብቻ እንዴት እንዳየ ተመለከታችሁ? ምንም ያህል መጥፎ ነገር ብነግረው በመልካም ሀሳብ ነበር የሚወስዳቸው። ስለ ሲጋራ እንኳ እየነገርኩት አይኑ እንባ አቅርሮ “የሆነ ሰው ሊረዱ ሄደው ነው” ብሎ ያስብ ነበር። ብዙ የተማሩና ታላላቅ ነገሮችን ያነበቡ ሰዎች እንኳ የዚህን ወጣት ተማሪ ያህል በጎ ሕሊና የላቸውም። መልካም ሀሳቡን በመጥፎ ስታጠፉበት ደግሞ ሌላ በጎ ሀሳብ ይፈጥርና በዚያም ተመስርቶ በጎ ድምዳሜ ላይ ይደርሳል። በርሱ በጣም ተደነቅሁ እንዲህ ያለ ነገር ሳይ የመጀመሪያዬ ነው።
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
ንብ እንሁን ዝንብ አንሁን!
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
<<ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ። ወፈድፋደሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ። እስመ አንሥአ (አሕየወ) ሙታነ ወሕሙማነ ፈወሰ። ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ። ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ።>>
<<ማርያም ሆይ የፍቅርሽ ተአምር በጻድቃን ማኅበር ዘንድ ተመሠገነ። ይልቁንም በኃጢያተኞች ላይ ነገሠ። ሙታንን አድኗልና ፤የታመሙትንም ፈውሷልና። "የደረቀውን እንዲያብብ አድርጓል" የሚል አለ። "ተራሮችን አፈለሰ የሚልም "አለ።>>
እንኳን አስፈጸመን!🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
" የጴጥሮስን እንባ "
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"በቁስሌ ላይ"
ዲ/ን ዘማሪ በኃይሉ ተበጀ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥቅምት ፳፯
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ
ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ 3:00 ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
¤ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና: ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት: አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
¤ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
¤ራሱንም በዘንግ መቱት::
¤እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
¤በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::
በሠለስት (3:00 ላይ) አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ 6,666 ገረፉት::
ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት:: 6:00 ላይ በረዣዥም ብረቶች 5 ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::
7 ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ:: ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ 7 ቃላትን
ተናገረ:: ከቀኑ 9:00 አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::
በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ::
11:00 ላይ ደጋጉ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት:: በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::
ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት 27 ቀን ቢሆንም በዓሉ ወደ ጥቅምት እንዲመጣ ያደረጉት አበው ሊቃውንት ናቸው:: ምክንያቱም ብዙ ጊዜ መጋቢት 27 የሚውለው ዓቢይ ጾም ውስጥ በመሆኑና የንግሥ በዓላት በዓቢይ ጾም ስለማይፈቀዱ ነው::
ምንም እንኩዋ በቅርብ ጊዜ በዓቢይ ጾም የሚያነግሡ አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት ቢኖሩም አባቶቻችን ግን እንዲህ ያለውን ሥርዓት አላቆዩልንም:: ከበሮና የቸብቸቦ ዝማሬም በወቅቱ የተፈቀደ አይደለም::
+በዚህም ምክንያት የበዓለ ስቅለት ንግሡ ወደ ጥቅምት 27 ሲመጣ: የመጋቢት 5 ገብረ መንፈስ ቅዱስ ንግሥ ወደ ጥቅምት 5: የመጋቢት 10 መስቀል ወደ መስከረም 17 መጥቶ እንዲከበር ሆኗል::
አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ይማረን ለሀገራችን ሰላሙን ይላክልን፤ አሜን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"ማርያም ጎየይኪ"
ማርያም ጎየይኪ እምገጸ ሄሮድስ/፪/
ለአርእዮ/፬/ ተአምረ ግፍዕኪ/፪/
ትርጉም፦ ማርያም ሆይ የግፍሽን ተአምር ለማሳየት ከሄሮድስ ፊት ሸሸሽ ፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
የ፳፻፲፰ ዓ.ም የጥቅምት ፲፮(የሦስተኛው ሰንበት) የጽጌ ማኅሌት
ዘሣልሳይ ሰንበት
መልክአ ሥላሴ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፩ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ዚቅ
፪ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ዚቅ
፫ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፬ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፭ኛ. ሰቆቃወ ድንግል
ዚቅ
መዝሙር በ፫
"የስደት ዘመንሽ"
መከራን ታግሰሽ ገሊላ የገባሽ ፣
ለዓለም መፅናኛ ነው የስደት ዘመንሽ
በጠላት ፈተና ከሀገር ተሰደሽ
ስትንከራተቺ አምላክን ታቅፈሽ
ከገሊላ አንስቶ እስከ ግብፅ በረሃ
የሚያዝንልሽ አጣሽ የሚሰጥሽ ዉኃ
አዝ......
አዝ......
አዝ......
አዝ......
፬ኛ የልጇን ጫማ በወሰዱባት ጊዜ
ከነጥጦስ የተረፈው የጌታችን ጫማ ዲያብሎስ ባስቀመጣቸው የመንደር ምልምሎች ከመወሰድ አልዳነም፡፡ ነገሩ እዲህ ነው፡- ከዕለታት አንድ ቀን ቁራሽ ልመና ስትሄድ የልጇን ልብስ እና ጫማ ከአንድ ዋሻ ውስጥ አስቀምጣ ነበር የሄደችው፤ ብትሄድ ሰይጣን እንደ ፈርዖን የሰውን ልብ አፅንቶት ምንም ቁራሽ ሳታገኝ ተመለሰች፡፡ እንኳን ቁራሽ እፍኝ ውኃ መስጠትንም ከለከሏት፤ ከዚህም ብትመለስ የልጇን ጫማ አጣች፤ ያን ጊዜ “ሰአልክወሙ ማየ ኢወሀቡኒ በሕቅ ወኀጐልኩ ለወልድየ አሳዕኖ ዘወርቅ፤ ጥቂትን ውኃን ለመንሁ አልሰጡኝም የልጄን ጫማም አስወሰድኩ” ስትል አምርራ አለቀሰች፡፡
ቤተክርስቲያን በዚህ ዓለም ክርስቶስን ተሸክማ በስሙ ተጠርታ እስከ ዓለም ፍጻሜ የምትሰደደውን መሰደድ ድንግል ጀመረችው፡፡ በዚህም በመጻሕፍት ሁሉ ስሟ ሲጠራ እመ ስማዕታት መዋዕያን፤ ያሸናፊዎች ሰማዕታት እናት እየተባለች ትጠራለች በተለይም በዘመኑ መጨረሻ ሐሳዊ መሲሕ ነግሦ ቤተክርስቲያንን ለአርባ ሁለት ወራት የሚያሳድዳት መሆኑን አስቀድሞ በሄሮድስ ንግሥና እመቤታችን ለአርባ ሁለት ወራት በመሰደዷ ነገረን፡፡
እመቤታችን የስደቷ መከራ እያንዳንዱ ቢነገር አስገራሚ እና አሳዛኝ ሲሆን ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ በኋላ ግንቦት ሃያ ስድት ቀን ተጀምሮ ኅዳር 6 ቀን በድል ተጠናቀቀ፡፡ ብዙ ሕጻናትን የፈጀው ሄሮድስ ሐሳቡ ሳይሳካ ግብዓተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ የሕፃናቱ ጩኸት፣ የእናቶቻቸውም ለቅሶ እና ዋይታ የተሰማባት ገሊላ ዛሬ ስለ ልጆቿ መጽናናትን እምቢ የምትለዋ ራሔል ሳትሆን የምታለቅስበት የንጉሥ ቤተሰቦች የለቅሶ ስፍራ ናት፡፡
የዚህ ዓለም ደስታ በፈረቃ ነውና ከ1260 ቀናት በኋላ ያዘነችው ድንግል ደስ ይላት ዘንድ በበረሐ ሳለች “መከራዬን አይቶ ይረዳኝ ዘንድ ትጸንሻለሽ ብሎ ያበሠረኝ መላክ ወዴት ነው?'' ስትለው የነበረው መላክ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ነገራቸው፡፡
ጌታ ጠላቶቹን መምታት የጀመረው ከሄሮድስ ጀምሮ ነው፤ የመጨረሻው ዲያብሎስ ነው፡፡ እንዲህ የሚመስሉ ብዙ የመዳን ተስፋዎችን የያዘው የግብፅ መልሳቸው ከዚህ በላይ የአበው ነቢያት ተስፋ ትንቢትን ፍጹም ያደረገ ቀን ነበር፡፡ በትንቢታቸው ቅዱስ መጽሐፍ ከመዘገባቸው ዐበይት እና ደቂቅ ነቢያት ቃለ ትንቢታቸው ተናግረውት እስካልተመዘገበላቸው የቃል ነቢያት ድረስ የመመለሱን ዜና ለዓለም አውጀዋል፡፡
ከነቢያት አንዱ “እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ፤ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" ሆሴ 11፥1 ብሎ ስለ ግብፁ ስደተኛ ክርስቶስ በባሕርይ አባቱ ዘንድ የታሰበውን ሲገልጽ ሌላው ነቢይ ደግሞ “አንቺ ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ ተመለሽ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ" መኃ 7፥1 ሲል ናፍቆቱን ይገልጽላታል፡፡
ከቃል ነቢያት አንዱ ስሙ ያልታወቀ ነቢይም “ልጄ ናዝራዊ ይባላል" ብሎ የተናገረው ሳይደርስ እንደደረሰ፣ ሳይደረግ እንደተደረገ አድርጐ የተናገረው እንዲፈጸም ከቦታዎቹ ሁሉ ናዝሬትን መርጠው ተቀመጡ፡፡
ልብ በሉ! የእመቤታችን ወደ ናዝሬት መመለስ የእኛን ወደ ገነት የመመለስ ምሥጢር የያዘ በመሆኑ ነው በነቢያት ሁሉ በናፍቆት ይጠበቅ የነበረው፡፡ ይህ ደግሞ የተፈጸመው ነፍሰ ገዳዩ ንጉሥ ሄሮድስ ዓለምን ተሰናብቶ ማለቂያ ወደ ሌለው የጨለማ ዓለም ከተዛወረበት በኋላ መሆኑ ከጥንት ጀምሮ በእውነት የማይቆመው ነፍሰ ገዳዩ የአባቶቻችን ከሳሽ ዲይብሎስ ከተገደለ በኋላ አማናዊው የሰው ልጆች መዳን የሚፈጸም መሆኑን አመላካች ነው፡፡
፩ኛ ምጽአተ ዮሳ ወልደ ዮሴፍ
ዮሳ በመጽሐፍ የጌታ ወንድሞች ተብለው አይሁድ ከዘረዘሯቸው ስዎች አንዱ ሲሆን ማቴ 13፥55 የስደቱ ታሪክ በተጀመረበት ሌሊት አብሮ ከዚህ ታሪክ ተካፋይ ነበር፡፡ ጥቂት እንደሄደ ግን ከበረከተ ስደቱ ሊካፈል የማይገባው ሰነፍ ሰው በመሆኑ ከጐዳናው ላይ ተለይቶ ቀረ፡፡
በኋላ ግን ዘመዶችህን ሊያስገድል ሄሮድስ ጭፍራ ሰደደ ሲሉ ቢሰማ እግሮቹ ለበረከት ባይሆንም ለመርገም ፈጣኖች በመሆናቸው ማንም ሳይቀድመው ለስደተኞች የወሬ ስንቅ ተሸክሞላቸው ሮጠ፡፡ ሲደርስ ደክመው ጥላ ሥር አርፈው አገልጋይቱ ሰሎሜ ሕጻኑ ኢየሱስ ክርስቶስን ስታጥበው ከወንዝ ዳር ነበር ያገኛቸው፡፡ ከመድረሱ ቸር ዋላችሁ፣ ቸር አደራችሁ እንኳን አላለም፤ ይህን ሕጻን ልታስገድሉት ከዚህ ተቀምጣችኋል ሄሮድስ ጭፍሮችን በየሀገሩ አሰማርቷል ሲል እመቤታችን ከሰሎሜ እጅ ሕጻኑን ተቀብላ ይህን ሁሉ መከራ የተቀበልኩት ላላድንህ ነው ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች፡፡
፪ኛ ሁለቱ ወንበዴዎች ባገኟት ጊዜ
ጥጦስን እና ዳክርስን ያስተባበራቸው ቃል ኪዳናቸው ውንብድና ነው፡፡ ለማንም ላይራሩ ተማምለው ሥራውን ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ በጥጦስ መምህርነት፣ በዳክርስ ተማሪነት የተጀመረው ይህ ተግባር በድሃውም በባለጠጋውም እንዲጨክኑ አድርጎአቸዋል፡፡
በዚህ ወቅት ነው ድንግል ከነልጇ በዚህ ጫካ ያገኘቻቸው፤ የጠፉትን ፍለጋ የመጣው ጌታችን ግን የራሱ የሆነ ጉዳይ ነበረው ወደ ዚህ በረሐ የመጣበት፤ ከነዚህ ሽፍቶች አንዱ ከደጋጉ ቅዱሳን ከነ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ተቀድሞ ደመ ማኅተሙን ይዞ ገነት የሚገባ ነውና አስቀድሞ ይህን የምሥራች ሊነግረው ወደ ዚህ መጣ፡፡
ሊቀሟቸው እየተሯሯጡ ሲመጡ ሰሎሜ አስቀድማ ልብሷን ጥላ ሸሸች የእመቤታችን መጐናጸፊያውንና የጌታን ሰብአ ሰገል የገበሩለትን የወርቅ ጫማና ቀሚስ ነጥቀው ወሰዱ፡፡ አዳም እና ሔዋን የብርሃን መጐናጸፊያቸውን ተገፈው ነበርና ለዚያስ ካሳ እንዲሆን ነው፡።
እመቤታችንን ያስለቀሳት ግን የልብሱ መነጠቅ ሳይሆን ጥቂት አለፍ ብለው ነገር መጀመራቸው ነው፡፡ እነሱ የሚመክሩት የቀሙትን ልብሳቸውን የሚመልሱበትን መንገድ ሲሆን እመቤታችን ደግሞ ሌባ አዩኝ አላዩኝ ብሎ ያገኘውን ዘርፎ ይሄዳል እንጂ እንዲህ የልብ ልብ ተሰምቶት ይቆማልን? እኒህማ ልጄን ሊገድሉ የተላኩት ይሆናሉ ስትል ስለ ልጇ ዳግመኛ አምርራ አለቀሰች፡፡ በቅዱሳት እጆቹ የተወደደ ልጇ እንባዋን ከዓይኗ እስከጠረገላት ድረስ በተወደደ ልጇ ደረት ላይ እንባዋን አፈሰሰች፡፡
፫ኛ ቤተ ኮቲባ
አንዳንዱ ቤት ከሰው እስከ ስማያዊው አምላክ የሚስተናገዱበት፣ የሰማዩ አባታችን የእግዚአብሔር ፈቃድ የሚፈጸምበት ማኅደረ እግዚአብሔር ይሆናል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ሰይጣን ጥላውን ይጥልበትና በረከት አልባ፣ ሊተኙበት የሚያባባ፣ ባል እና ሚስትን የማያግባባ፣ አስቸጋሪ ይሆናል ቤተ ኮቲባም እንዲህ ነበር፡፡
በወቅቱ ከነበሩት የምድር ባለጠጐች የአንዱ ቤት ሲሆን ከብዙ ሀብት መካከል ጥቂት ቸርነት ካልተገኘ አስቸጋሪ ነውና እመቤታችን ስመ እግዚአብሔር ጠርታ ስትለምን የተመለከተች የቤቱ ባለቤት ልብን ከመዶሻ ይልቅ የሚሰብር ጨካኝ ቃላትን ተናገረች፡፡ የሰነፍ ሰው ንግግር እንደ አሸዋ ከባድ ነው፤ እንደ ፍላፃም ተዋጊ ነው፡፡ “አንቺ ሴት ደረቅ ሴት ነሽ መስለኝ እንጂ እንደ አንች ያለ መልከ መልካም ሴት ከመጋረጃ ይወጣ ነበርን" ስትላት አረጋዊው ዮሴፍ ተቀብሎ "ለለማኝ ቢኖር ይሰጡታል ባይኖር ካለው ያድርስህ ይሉታል እንጅ እንዲህን በነገር ይወጉታል” አላት፡፡
ኮቲባ የተሰኘችው አገልጋይ ደርቡን እያናወጠች ወርዳ ዮሴፍን በጥፊ ቃጥታ ጌታን ከእመቤታችን ጀርባ ነጥቃ ከመሬት ቀላቀለችው፤ ሕጻኑ ትክን ትክን ብሎ ሲያለቅስ እመቤታችንም ጩኸት እና ድንጋጤ የከበበው ብርቱ ለቅሶን አልቅሳለች፡፡
ይቀጥላል .....
(ሕይወተ ማርያም - በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
እመቤታችን ከመልአከ ብሥራቷ ከቅዱስ ገብርኤል በተረዳችው መሠረት ወደ ምድረ አፍሪቃ ይዛው ስትመጣ ያን ጊዜ አባቶቿ ነቢያት የተናገሩት ተፈጸመ “ጌታ በፈጣን ደመና ተጭኖ ወደ ግብጽ ይመጣል" ኢሳ 19፥1 የነቢያት ቃል እንዲፈጸም ብቻም ሳይሆን በዓለማችን ልዩ ልዩ ክፍላት ተሰማርተው ጣዖት ያስመልኩ፣ ኃጢአት ያሠሩ የነበሩ አጋንንት፣ ሊቃነ አጋንንት ከምድር ጨርሰው እስኪሰደዱ ጌታ ተሰደደ፡፡
እመብርሃን ድንግል በዚያ ወቅት በብዙ መንገድ ተፈተነች፤ የሄሮድስ ሠራዊቶች ከተማ ለከተማ ይሄዱ፣ ጐዳናውን ይዘው ይከታተሏቸው ነበርና ከዚያ ለማምለጥ ጫካ ለጫካ ይሄዱ ስለነበር በከባድ ረሐብና በታላቅ ውኃ ጥም ተፈተኑ፡፡ የእስራኤልን መና፣ የዐለቱን ልብ አላልቶ ውኃን የሚያጠጣውን ጌታ በጀርባዋ ይዛ ተራበች፣ ተጠማች፤
አባቷ አዳም እናቷ ሔዋንን ከዘለዓለማዊ የነፍስ ረሐብና ጥም የሚያድነውን ጌታ ነውና የያዘችው ተራበች፣ ተቸገረች፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን እንኳን ወደ መንደር ገብተው ቁራሽ እንጀራ ጥርኝ ውኃ ሲለምኑ የሚሰጣቸው አልነበረም፡፡ ዓለም ምን አላትና ሁሉን በእጁ ለያዘው ምን ትሰጠዋለች ጌታ ራሱን እስኪሰጠን ድረስ የምንሰጠው አንዳች ነገር የሌለን ድሆች ነበርን፤ ባለጠጐች የሆንነው ባለጠጋው ጌታ ራሱን የሰጠን ጊዜ ነው፡፡ ከረሐቡ ጋር አብሮ የማይረሳው ደግሞ በግብፅ ምድረ በዳ የተደረገው ጉዞ ነው፤ የግብፅ በረሐ በአሸዋ የተሞላ ሰውነትን የሚያሳርፍ ምንም ዓይነት ለምለም ነገር የሌለው፣ አሸዋው እግርን የሚያቃጥል የፀሐዩ ግለት ነፍስን ከሥጋ ለይቶ የሚጥል እሾህ እና አሜካላን የሚያበቅል ምድረ በዳ ነው፡፡
ከአዳም በደል የተነሣ የረከሰችውን ምድር ሊቀድሳት የተረገመችውን ሊባርካት የመጣው ጌታ የሰውን ሕማም በሥጋው መከራን ሲቀበል ዳግማዊት ሔዋን እመቤታችንም እንደ እናቷ ሔዋን ከብርቱ እንባ ጋር መከራን ተቀበለች፡፡ ሔዋን በሕማም፣ በምጥ እንድትወልድ ሲፈርድባት ላለቀሰችው እንባ አምሳል የሚሆን እንባ በመውለዷ ጊዜ ይህ ሁሉ ያልደረሰባት እመቤታችን አነባች፡፡ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ መከራው ያልተለያት ቢሆንም በተለይ አራቱ ፀዋትወ መከራዎቿ ሁል ጊዜ ሲታወሱ ይኖራሉ፡፡
ይቀጥላል .....
(ሕይወተ ማርያም - በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
የ፳፻፲፰ ዓ.ም የጥቅምት ፱(የሁለተኛው ሰንበት) የጽጌ ማኅሌት
ዘካልኣይ ሰንበት
መልክአ ሥላሴ
ዚቅ
፩. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፪. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፫. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፬. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
ሰቆቃወ ድንግል
ወረብ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ መዝሙር በ፫
ሰላም በ፱
. ቅድስት ሥላሴ
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
በ ‹‹ምሥጢረ ሥላሴ›› ትምህርት እንደምንረዳው ቅድስት ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ ‹‹ሥላሴ›› የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ፤ ሦስት አደረገ›› ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ (መጽሐፍ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ገጽ ፮፻፷፱)
ቅድስት ሥላሴ ስንልም አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ማለታችን ነው፡፡ ‹‹ቅድስት›› ተብሎ ደግሞ በሴት አንቀጽ /ቅድስት ሥላሴ/ ይጠራል፤ ‹‹ቅድስት›› እና ‹‹ልዩ ሦስት›› የሚባልበትም ሃይማኖታዊ ምሥጢር፡-
፩. ቅድስት
ሥላሴ ‹‹ቅድስት›› ተብለው በሴት አንቀጽ መጠራታቸው ሴት /እናት/ ልጅዋን መውለዷን እንደማትጠረጥረው ሁሉ ሥላሴም ይህን ዓለም መፍጠራቸውን ስለማይጠረጥሩ ነው፡፡ ሁሉም ከእነርሱ፣ ለእነርሱ፣ በእነርሱ ሆኗልና፡፡ ሴት ወይንም እናት ልጅዋ ቢታመምባት እንዲሞትባት አትሻም፤ ሥላሴም ከፍጥረታቸው አንዱ እንኳን በጠላት ዲያብሎስ እንዲገዛባቸው አይፈቅዱም፡፡ ሴት ፈጭታ ጋግራ ቤተሰቦቿን እንደምትመግበው ሥላሴም በዝናም አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረቱን ሁሉ ስለሚመግቡ ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እያልን እንጠራቸዋለን፡፡
፪. ልዩ ሦስትነት
በትምህርተ ሃይማኖት ሥላሴ በቅድምና፣ በፈጣሪነት፣ በሥልጣን፣ በመመስገን፣ በክብር፣ በፈቃድ አንድ /እግዚአብሔር/ ሲሆኑ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት መሆናቸውን ይገልጻል፡፡
ሀ. በስም
የቅድስት ሥላሴ የስም ሦስነትነት አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ተብለው መጠራታቸው ነው፡፡ አብ በራሱ ስም አብ ይባላል እንጂ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ አይባልም፡፡ ወልድም ወልድ ይባላል እንጂ አብ ወይንም መንፈስ ቅዱስ አይባልም፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ቢባል እንጂ አብ ወይንም ወልድ አይባልም፤ ስማቸው ፈጽሞ የማይፋለስ ነውና፡፡
ከቅዱስ ጴጥሮስ ቀጥሎ በሦስተኛነት በአንጾኪያ ተሹሞ የነበረው ቅዱስ አግናጥዮስ ‹‹አብሂ ውእቱ አብ ወኢኮነ ወልደ ወኢ መንፈሰ ቅዱሰ፣ ወልድሂ ውእቱ ወልድ ወኢኮነ አበ ወኢ መንፈሰ ቅዱሰ፣ ወመንፈስ ቅዱስሂ መንፈስ ቅዱስ ውእቱ ኢኮነ አበ ወኢ ወልደ፣ ኢይፈልስ አብ ለከዊነ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፣ ወኢ ወልድ ለከዊነ አብ ወወልድ፤ ወኢ መንፈስ ቅዱስ ለከዊነ አብ ወወልድ፤ አብም አብ ነው እንጂ ወልድን መንፈስ ቅዱስን አይደለም፤ ወልድም ወልድ ነው እንጂ አብን መንፈስ ቅዱስንም አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ አብን ወልድን አይደለም፤ አብ ወልድን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም፤ ወልድም አብን መንፈስ ቅዱስን ወደመሆን አይለወጥም፤ መንፈስ ቅዱስም አብን ወልድን ወደመሆን አይለወጥም›› ብሏል፡፡ (ሃይ. አበው ዘቅዱስ አግናጥዮስ ምዕ. ፲፩. ገጽ. ፴፯)
የቅድስት ሥላሴ ስማቸው ከአካላቸው፣ አካላቸው ከስማቸው ሳይቀድም ቅድመ ዓለም የነበረ ስም ነው እንጂ ድኅረ ዘመን የተገኘ አይደለም፡፡ ቅድምናቸው ዘመኑን ቢወስነው እንጂ ዘመኑ ቅድምናቸውን አይወስነውምና፡፡ (መንገደ ሰማይ-በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ገጽ. ፴፪)
ስለዚህም ሊቁ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ‹‹ወናሁ ንቤ ካዕበ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወአኮ እሉ አስማት ዘቦኡ ላዕሌሆሙ ድኅረ አላ እሙንቱ እስመ አካላት፡፡ ወብሂለ ሰብእሂ አኮ ውእቱ ስም ዳዕሙ ፍጥረት ውእቱ… ወአካሎሙኒ ለሥሉስ ቅዱስ ወአስማቲሆሙ አልቦ ውስቴቶሙ ዘይዴኀር አላ እሉ እሙንቱ ብሉያነ መዋዕል እምቀዲሙ ዘእንበለ ጥንት ወዘመን፤ አሁን ደግሞ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንላለን ግን አካላት ተቀድመው ተገኝተው እሊህ ስሞች ኋላ የተጠሩባቸው አይደለም፤ ሰው ማለት ኋላ የወጣ ስም አይደለም፡፡ ባሕርዩ ነው እንጂ የሥላሴ አካላቸውም ቀድሞ ስማቸው ከአካላቸው በኋላ የተገኘ አይደለም፡፡ ጥንት ሳይኖራቸው ዘመን ሳይቀድማቸው የነበሩ ናቸው እንጂ›› ብሎ ተናግሯል፡፡ (ሃይ-አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራት ፲፫፥፬-፰ ገጽ ፵)
ለ. በአካል
የቅድስት ሥላሴ የአካል ሦስትነታቸው ደግሞ አብ ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ ወልድም ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል፣ ፍጹም ገጽ፣ ፍጹም መልክእ አለው፡፡ ሊቁ አቡሊዲስ ስለ ሥላሴ የአካል ሦስትነት ሲገልጽ ‹‹ነአምን በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ከመ ሠለስቱ ገጻት ፍጹማነ መልክእ ወአካል እሙንቱ እንዘ አሐዱ መለኮቶሙ ዘበአማን፤ ባሕርያቸው በእውነት አንድ ሲሆን በመልክ፣ በአካል ፍጹማን እንደሆኑ ሦስት ገጻት እንደሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን›› ብሏል፡፡ (ሃይ. አበ. ዘአቡሊዲስ ምዕ. ፴፱፥፫ ገጽ ፻፴፯)
ሐ. በግብር
የቅድስት ሥላሴ የግብር ሦስትነታቸው ሲተረጎም የአብ ግብሩ መውለድ ማሥረፅ ነው፤ ወልድን ወልዷል፣ መንፈስ ቅዱስንም አሥርፇልና፡፡ የወልድ ግብሩ መወለድ ነው፤ ከአብ ተወልዷልና፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩ መሥረፅ ነው፤ ከአብ ሠርፇልና፡፡
አብ ወልድን ቢወልድ፣ መንፈስ ቅዱስንም ቢያሠርፅ እንጂ አይወለድም፣ አይሠርፅም፡፡ ወልድ ቢወለድ እንጂ አይወልድም፤ አይሠርፅም፤ አያሠርፅም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አይወለድም፤ አያሠርፅም፤ በመሆኑም ቅድስት ሥላሴ በዚህ ግብራቸው አብ ወላዲ፣ ወልድ ተወላዲ፣ መንፈስ ቅዱስ ሠራፂ ተብለው ይጠራሉ፡፡
በእርግጥ ምሥጢረ ሥላሴን በሚገባ መርምሮ መረዳት ለማንም ቢሆን አይቻለውም፡፡ እርሱ ባወቀ ግን ምሥጢረ ሥላሴ በምሥጢረ ጥምቀት ተገልጧል፡፡ እንግዲህ እምነታችንን በቅድስት ሥላሴ ላይ በማድረግ በቀናች ሃይማኖት ልንጸና ይገባል፡
©Mahibere kidusan
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ንግስተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል (2):
ተፈጸመ(5) ማኅሌተ ጽጌ።🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌹 @Ethiopian_Orthodox 🌹
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
የ፳፻፲፰ ዓ.ም የጥቅምት ፴(የመጨረሻ ሰንበት) የጽጌ ማኅሌት
ዘኀምስ ሰንበት/ዘተፈጸመ/
መልክአ ሥላሴ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፩ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፪ኛ.ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፫ኛ.ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፬ኛ.ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
ሰቆቃወ ድንግል
ወረብ
ዚቅ
መዝሙር በ፮
«ኢየሱስም ዘወር ብሎ ተመለከተው»
ጴጥሮስ ጌታውን ለሦስተኛ በካደበት ጊዜ ጌታችን ከሸንጎው ታስሮ ወደሚያድርበት ምድር ቤት እየተወሰደ ነበር፡፡ ጴጥሮስ «ሰውዬውን አላውቀውም» እያለ ሲምልና ሲገዘት «ያንጊዜ ዶሮ ጮኸ፡፡ ጌታም ዘወር ብሎ ጴጥሮስን ተመለከተው ፤ ጴጥሮስም፦ ዛሬ ዶሮ ሳይጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ እንዳለው የጌታ ቃል ትዝ አለው፡፡ ጴጥሮስም ወደ ውጪ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቃሰ።» ሉቃ፳፪፥፰-፳፪
የዋሑ ጴጥሮስ በሎሌዎች ተከብቦ ሰውየውን አላውቀውም እያለ በሚያስረዳበት ሰዓት መምህሩ ክርስቶስ ዘወር ብሎ ተመለከተው።ጴጥሮስ ሦስት ጊዜ አላውቀውም ብሎ የካደው ጌታ «እኔ ግን አውቅሃለሁ» ሲል ዘወር ብሎ ተመለከተው።ክርስቶስ እንደታሰረ በዓይኖቹ ተመለከተው 'ጴጥሮስ ሆይ አታውቀኝምን? በገሊላ ባሕር ዓሣ ስታጠምድ የጠራሁህ፤ በባሕር ላይ እንድትራመድ ያደረግኩህ ፤ ከዓሣው ሆድ ውስጥ ገንዘብ አውጥተህ ለእኔ እና ለአንተ ግብር ክፈል ያልኩህ፤ከሰዓታት በፊት እግርህን ያጠብሁህ... እኔን አታውቀኝም?'የሚሉ ዓይኖች ጴጥሮስን ተመለከቱት።
ጴጥሮስ በካደባት በዚያች ቅጽበት የጌታን ዓይኑን ሲመለከት ምን ተሰምቶት ይሆን? እስከ ልብ ድረስ ዘልቀው የሚያዩት አምላካዊ ዓይኖች ለዚህ ሐዋርያ ምን መልእክትን ተናግረው ይሆን? ይህን ሐዋርያ አግኝቶ ማን ጠይቆ በነገረን? እሱ ያየውን ጌታ ከሦስት ጊዜ አልፈን ሦስት ሺህ ጊዜ በኃጢአታችን ለካድነው ለእኛ ማን ጠይቆ በነገረን? እንደ ጴጥሮስ ስንክደው ዘወትር የሚያየንን ጌታ ማየት ለተሳነን ለእኛ የጌታን የዓይኑን መልእክት ማን ጠይቆ በነገረን?
ጴጥሮስ የጌታን ዓይን ባየበት ቅጽበት ልቡ ድረስ የሚወጋው፤ በኀዘን የሚያቃጥለው ጸጸት ተሰማው።የጌታ ዓይኖች በቁጣ የተሞሉ አልነበሩም። ጴጥሮስን ግን በጸጸት ጦር ልቡን የሚወጉት ሆኑ።ቀድሞ ያልተሰማው የዶሮ ጩኸት አሁን ዘልቆ ተሰማው « ሌሎች ቢክዱህ እኔ አልክድህም» ብሎ ተናግሮ ሦስት ጊዜ መካዱን አሰበ 'ከሁሉ ይልቅ ስወደው ከሁሉ ቀድሜ እክደው ?' ብሎ ተንገበገበ። ስለዚህም ለክህደት ከዳረገው እሳት ከሚሞቅበት ግቢ በሕሊናው ዓይን የጌታን ዓይኖች በሕሊናው ጆሮ የዶሮውን ጩኸት እየሰማ ወጣ ከአጥር ውጪ ወጥቶም ምርር ብሎ አለቀሰ።
ጴጥሮስ 'ጌታ ሆይ ይቅር በለኝ፤ በድንገት ፈርቼ ነው ነው የካድኩህ ፤ሎሌዎቹ ሲያዋኩብኝ ነው' እያለ ይቅርታ አልጠየቀም። «አለቀሰ እንጂ ይቅርታ አልለመነም ምክንያቱም የዕንባ ዘለላዎች ይቅርታን ያገኛሉ እንጂ ይቅርታን አይለምኑም»እንዳለ ሊቁ አምብሮስ። ስለዚህ የዋሁ ጴጥሮስ ቃል ሳይተነፍስ በጨለማ ውስጥ ብቻውን ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡ ጌታ አይቶታል እና ስለ በደሉ ምርር ብሎ አለቀሰ። "ጌታችን ሆይ ወደ እኛም ተመልከት ስለ ኃጢአታችንም እንድናለቅስ አድርገን።" ይላል ሊቁ አክሎ።
ዕንባ በእርግጥም ኃይል አለው፡፡ የሰው ልጅ ኃያሉን እግዚአብሔር የሚያሸንፈው በዕንባው ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚያለቅሱ ዓይኖች ላይ ኣይጨክንም፡፡ በፍጹም ጸጸት የምታለቅስን ነፍስ አይቶ እግዚአብሔር “አውከውኛልና ዓይኖችሽን ከእኔ መልሺ" ይላል።(መኃ ፮፥፭) ስለዚህ እንዲህ ዓይነቱን ዕንባ ለማፍሰስ በጌታችን ዓይን መታየት ይፈልጋል።
ጴጥሮስ“ በዕንባ ውኃ ክህደቱን አጠበው" (ወሐጸቦ ለክህደቱ በማየ አንብዑ) ይህንን ዕንባ እንዲሰጠን በአባቶቻችን እና በእናቶቻችን ዕባ በራሰው የቤተ ክርስቲያን ቅጽር እንዲህ ኢያልን በዘወትር ጸሎት ተሰብስበን ወደ ጴጥሮስ አምላክ ላይ እንጮኻለን፦
« አቤቱ በደሌንና ነውሬን የሚያጥብ ዕንባ ስጠኝ፤
አቤቱ አንተን የሚያገለግል ዕንባን ሥጠኝ
አቤቱ የሚያቃጥል ዕንባን ሥጠኝ፤
አቤቱ ከዓይኔ ፈስሶ የአካሌን እድፍ የሚያጥብልኝ ዕንባ ሥጠኝ፤
የተጸጸቱ ሰዎችን ዕንባ የምትቀበል ጌታ ሆይ አንተ የተቀበልከውን ጽኑ ለቅሶ እንዳለቀሰ እንደ ጴጥሮስ ያለ ዕንባን ሥጠኝ፤
አቤቱ እንደ ባሕርም በምትፈስስ ዕንባ እጠበኝ፤
የማያቋርጥ የዕንባን ጎርፍ አፍስስልኝ።»(ውዳሴ አምላክ ዘእሑድ)
[ ሕማማት - በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ]
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
የ፳፻፲፰ ዓ.ም የጥቅምት ፳፫(የዐራተኛው ሰንበት) የጽጌ ማኅሌት
ዘራብዓይ ሳምንት
ለገባሬ ኵሉ
ዚቅ
፩ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፪ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
፫ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
ዓዲ ዚቅ
፬ኛ. ማሕሌተ ጽጌ
ወረብ
ዚቅ
ሰቆቃወ ድንግል
ወረብ
ዚቅ
መዝሙር በ፭
«ድንግል ሆይ አንቺን ያሳደደሽ ሄሮድስ እኔን የማያሳድደኝ ጌታ በእቅፌ ስለሌለ ነው። እኔ በልቤ ያነገሥሁት 'የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ' ስላልሆነ ሄሮድስ ከእኔ ጋር ጠብ የለውም ። የሄሮድስን ስልጣን አደጋ ላይ የሚጥል ንጉሠ ሰላም በእኔ እቅፍ የለም። አሁን ግን ፍቀጂልኝና ሄሮድስን ማስደሰት ትቼ ልጅሽን በልቤ ልቀበለው ።የልቤን ክርስቶስ ሄሮድስ እንዳይገድልብኝ እኔም እንዳንቺ ልሰደድ።እርሱን አቅፌ መከራን ቢደርስብኝ እንኳን ጽናት እንደማገኝ በአንቺ አይቻለሁ እና የልጅሽን ፍቅር በልቤ አኑሪልኝ። ለሦስት ቀናት ከፊትሽ ዘወር ቢል ፍለጋ የወጣሽዋ ድንግል ሆይ ከእኔ ሕይወት ልጅሽ ከተሠወረ ቆይቶአልና ያለ እርሱ መሰንበት የማልችል የፍቅሩ ምርኮኛ አድርጊኝ ።»
[የብርሃን እናት-በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ]
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"አቡነ አረጋዊ"
ጽድቅህ ጠርቶናል አባትነትህ
በቅድስና ያማረ ሕይወትህ
ጌጥ ውበታችን አባ አረጋዊ
መናኝ መነኩሴ መልአክ ምድራዊ (፪)
ተቃኝተህ ስላደግክ በመንፈስ ቅዱስ
ወደ ፅርዕ ተጓዝክ ወደ አባ ጳኩሚስ
ተዘጋጅተህ ነበር ለችግር ፈተና
ዘሚካኤል አለህ ሰጥቶህ ምንኩስና (፪)
አዝ---
ለኢትዮጵያ ምእመናን አባት ተብለሃል
ወንጌል በማስተማር ብዙ አትርፈሃል
መጻሕፍት ተርጉመህ ያበረከትክ ለአበው
የአንተስ ትሩፋት እፁብ ነው ድንቅ ነው (፪)
አዝ---
የዓለም ጨው ሆነህ አጣፈጥካት ምድርን
በልባችን ሳልካት ቤተ ክርስቲያንን
ደብረ ሀሌ ሉያ ደብረ ዳሞ ቅድስት
የፈውስ ቦታ ናት መካነ ትኅርምት (፪)
አዝ---
ልክ እንደ አባቶችህ አስተዋይ ስለሆንክ
ገና ወጣት ሳለህ አረጋዊ ተባልክ
የሥጋን ሞት ሳታይ ተሰውረህ ከምድር
ብሔረ ሕያዋን ተቀላቀልክ በክብር (፪)
አዝ---
በቦሌ ደብረ ገነት ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት መዘምራን
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥቅምት ፲፬
ጻድቁ አቡነ አረጋዊ
‹‹ወበዛቲ ዕለት ኮነ ተዝካሩ ለዐብይ ወክቡር አቡነ አረጋዊ ዘይሰመይ ዘሚካኤል››
‹‹በዚህች ቀን የታላቁ እና የከበረ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዘሚካኤል የሚባለው መታሰቢያ ነው››
አባታችን ‹‹አቡነ አረጋዊ›› በሀገራችን ስም አጠራራቸው ከከበሩ አባቶች አንዱ ጻድቅ ናቸው፡፡ ጻድቁ የተወለዱት በ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አከባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው አባታቸው ንጉሥ ይስሐቅ እናታቸው ደግሞ ቅድስት እድና ይባላሉ፡፡ የተወለዱት ደግሞ በታላቋ ሮም ነው፡፡ ስማቸው ብዙ አይነት ነው ወላጆቻቸው ‹‹ ዘሚካኤል›› ሲሏቸው፣ በበረሀ ‹‹ገብረ አምላክ ››ተብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ደግሞ ‹‹አረጋዊ›› ይባላሉ፡፡ አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጽሐፍ ተምረዋልና ጠፍተው ገዳም ገቡ፡፡ በዚያም በገዳሙ ዳውንስ (ግብፅ) የታላቁ ቅዱስ "ጳኩሚስ" ደቀ መዛሙርት ሆነው ከነአባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል፡፡ ከመነኮሱ ከዓመት በኋላ ወደ ሀገራቸው ሮም ተመልስው በማስተማር ሰባት ያህል የቤተ መንግሥት ስዎች ወደ ምናኔ ማርከዋል ፡፡
451 ዓ.ም በተካሄደው የኬልቄዶን ጉባዔ ላይ የሁለት ባሕርይ ትምህርት አንቀበልም በማለታቸው በቤዛንታይን ነገሥታት ስቃይ እና መከራ ፀናባቸው :: በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ ከሁለት ባሕርይ ትምህርት የፀዳች እና ታላቅ አምልኮተ እግዚአብሔር እንደሚፈፀምበት ስለ አወቁ ከሌሎች ስምንት ቅዱሳን ጋር በሁለተኛው የኢትዮጲያ ጳጳስ በአባ ሚናስ ጊዜ በንጉሥ አልዓሜዳ ዘመነ መንግሥት በ5ተኛው መቶ ክ/ዘመን ማብቂያ 480/81 ዓ.ም ወደ ሀገራችን ገቡ፡፡ ከአባታችን ከአቡነ አረጋዊ ጋር የነበሩት ስምንቱ ቅዱሳን ከሮም ፤ከቤዛንታይን ፤ ታናሿ እስያ፤ሶሪያ ግዛትና አካባቢዎች የመጡ ናቸው፡፡ ስማቸውም አባ ገሪማ (አባ ይስሐቅ) ፣ አባ ጰንጠሌዎን፣ አባ አሌፍ፣ አባ ጉባ ፣አባ ሊቃኖስ ፣ አባ ይምዓታ ፣አባ ጽሕማ፣አባ አፍጼ ናቸው :: ስለ ተሰዓቱ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት መንገድ ሁለት ዓይነት ምንጮች ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያው አምደ ሃይማኖት ኢትዮጲያዊው ቄርሎስ የሚባለው ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ቅዱሳኑ ወደ ኢትዮጲያ ሲመጡ ነገሥታት እና መኳንንትን አስከትለው መጽሐፍትን ይዘው ስለነበር የመጡት ሀገር ለመውረር መስሏቸው ኢትዮጲያውያን ደንግጠው ነበር ፡፡ ነገር ግን በእጃቸው የተለያየ ተአምራትን ማየት ስለቻሉ ለመንፈሳዊ ተልዕኮ መምጣታቸውን ተረዱ ከተአምራቱ መካከል በዕራፈ የእሳት ፍም የቋጠሩ፣ ጠዋት ዘርተው ለሠርክ ቅዳሴ ማድረሳቸው (አቡነ ገሪማ)፣ በወንፊት ውሃ ተሸክመው መሄዳቸው፣ አሥሩ የእጅ እና የእግር ጣቶቻቸው እንደ ፀሐይ ያበሩ መሆናቸውን አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ጠቅሰዋል ሁለተኛው ምንጭ አባታችን አቡነ አረጋዊ መጀመሪያ ብቻቸውን መጥተው የኢትዮጲያውያንን ደግነት እና ታማኝነት ስለተረዱ ተመልሰው ሄደው ለ8ቱ ቅዱሳን በመግለፅ ይዟቸው መጥተዋል የሚሉ ምንጮች ናቸው ::
አባታችን አቡነ አረጋዊ ሲመጡ እናታቸው ቅድስት እድና እና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ :: ንጉሡም ተቀብለው በቤተ ቀጢን ( አክሱም) አሳረፏቸው በዚያ ተቀምጠው መጽሐፍትን እየተረጎሙ ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል፡፡ አባታችን ለብዙ ጊዜ በዓት ፍለጋ ደክመዋል በመጨረሻም ደብረዳሞ ማርካቸዋለች ፡፡ፃድቁ አባታችን እያስተማሩ ደብረዳሞ ሲደርሱ ወደሰማይ ቀጥ ያለች ተራራ ሰው በምንም መንገድ ሊደርስበት ወይም ሊወጣበት የማይቻለውን ቦታ እሳቸው ተመኙ፡፡ ‹‹ አሁን ይህንን ተራራ በምን ልወጣ እችላለሁ›› እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግር ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነብዩ ዳዊት ላይ አድሮ እንደተናገረ ( መዝ 90 (91) ÷11-16) የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስድስት ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሠይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል ፡፡ ወዲያው “ሀሌ ሉያ ለአብ ሀሌ ሉያ ለወልድ ሀሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው አመስግነዋል። ቦታውም <<ደብረ ሀሌ ሉያ>> ተብሏል ፡፡ በዚህችም እለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ግን ምድራዊ ህብስትን አልበሉም፡፡ በሰንበተ ክርስቲያን ከቅዳሴ በኋላ ህብስተ ሰማይ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር ፡፡
ፃድቁ አባታችን የምንኩስና ኑሮ ሥነ ሥርዓት በማስተማራቸውና በማስፋፋታቸው <<አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮጵያ፤ የኢትዮጵያ መነኮሳት አባት>> ይባላሉ። ግዕዝን በመማር መጽሐፍ ወደ ግዕዝ ቋንቋ ተርጉመዋል። ከአፄ ገ/መስቀል እና ከቅዱስ ያሬድ ጋርም ወዳጆች ነበሩ፡፡ በደብረዳሞ ተራራ ግርጌ የኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ለሴቶች ገዳም አድርገው ሰጥተዋል። ቀዳሚ መነኩሴም የሆኑት እናታቸው ቅድስት እድና ናቸው፡፡ በመጨረሻም ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስማቸውን ለሚጠራ መታሰቢያቸውን ለሚያደርግ ቃልኪዳን ተቀበሉ፡፡ በመምህራቸው አባ ጳኩሚስ እንደተማሩት ለልጆቻቸው መነኮሳት ሥርዓተ ማኅበርን ሰሩላቸው፤ ከዚያ በኋላ በእግዚአብሔር ቸርነት እንደሄኖክ እንደ ኤልያስ ከሞት ገፅ ጥቅምት 14 ቀን በደብረ ዳሞ ተሰወሩ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በፃድቁ ጸሎት ይማረን፤ በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ይሄን ሁሉ ምሥጢር መነጽር ሆና ያሳየችን ድንግል ማርያም በገሊላ አውራጃ በምትገኝ የዮሴፍ ደሳሳ ጐጆ ውስጥ ሆና እናታቸውን ያጡ የዮሴፍን ልጆች ጨምራ እናት ሆነቻቸው፡፡ እናት አጥቶ በሞት መዳፍ ውስጥ ለወደቀው ዓለም እናት እስክትሆን እናትነቷን በቤተ ዮሴፍ ጀመረች፡፡ ብዙ ጊዜ ሕጻኑ ልጇ ከሚያደርጋቸው ልዩ ልዩ ተአምራቶች የተነሣ የአካባቢው ሰዎች ስለ ልጇ ይከሷት እና ይወቅሷት ነበር፡፡
እርሱ በመስኮት ዘልቆ ወደ ቤት በሚገባው የፀሐይ ጨረር ላይ ሲራመድ ሕጻናቱ ሲመለከቱ እንደ እርሱ እናደርጋለን እያሉ ከመስኮት እየወደቁ አንዳንዶቹ ሲሞቱ ከሞት የተረፉት ደግሞ ተሰበሩ፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጭቃውን አድቦልቡሎ ሕይወትን የሚያድል እስትንፋሱን ሲለግሳቸው በረው በረው ሲሄዱ ሕጻናቱ ተመልክተው በእስትፋሳቸው ሕይወትን እንፈጥራለን ብለው እፍ ሲሉ ዋሉ፤ ሲመሽ ጉሮሮአቸው አበጠ፣ ልባቸው ወለቀ፡፡
ይህንን የተመለከቱ የገሊላ መንደር ነዋሪዎች በእመቤታችን ላይ በጠላትነት ተነሡባት ልጅሽ ልጆቻችንን ገሏል አሏት፤ ሁሉን ቻይ ልጇ የሞቱትን አሥነስቶ በውኑ የገደልኳችሁ እኔ ነኝን? ብሎ በሕዝቡ መካከል ሙታን ምስክርነትን እንዲሰጡ እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የአባቶቻችን ከሳሽ እርሱ ክሱን አላቆመም ነበር፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያድግ እንደ ሁሉም ምድራውያን ሕጻናት ነውና ለእናቱ በነገር ሁሉ ይታዘዝ ነበር፤ ውኃ እንዲቀዳ ስታዘው ውኃውን በወንፊት ቀድቶ ያመጣላት ነበር፤ ውኃውን ቋጥሮ በነፋስ ምስሶ ላይ ሰቅሎ፣ ስሙን ሰማይ ብሎ ለሚጠራው ለእርሱ በወንፊት ውኃን መቅዳቱ ምን ይገርማል፡፡
እንጨትም ልቀም ከተባለ ለቅሞ በነፋስ ትክሻ ላይ ጭኖ እያመጣላት ለእናቱ እና ለዘመዶቹ ሁሉ ያገለግል ነበር ሉቃ2÷51፡፡ በዚህ ሁሉ ነገር መላእክት እና ሊቃነ መላእክት ይገረማሉ፤ አጋንንት ይደነግጣሉ ባለመታዘዝ የተጀመረውን ኃጢአት በመታዘዝ ሊሽር መጥቷልና፤
ይህን አገልግሎቱን ሲያዩ መላእክት በመገረም ዝም ይላሉ ሊያገለግሉት እንጅ ሊያገለግል የማይገባው ሆኖ ሳለ በፈቃዱ ይህን አድርጓልና፡፡ በነገር ሁሉ እንደ ሕጻናት ሆነ እንጂ ከሕጻናት የተለየበት ምንም መንገድ አልነበረም፡፡ ሁለት የሰው ልጅ ሊያልፍባቸው የሚችሉ ሕግጋትን ፈጸመ47::
❖ ሕግ ጠባይዓዊ - በተፈጥሮ የተሰጠ የፍጥረት ሕግ ሲሆን በቀዳማዊው ልደቱ ይህ አልነበረበትም፤ በደኃራዊ ልደት ከድንግል ሲወለድ ግን ይህን የተፈጥሮ ሕግ ሳያዛባ ከማሕጸን ጀምሮ በየጥቂቱ አሳደገችው እንጂ አምላክ ነኝና ዕለቱን ተወልጄ ዕለቱን ልደግ አላለም፡፡
❖ ሕግ መጽሐፋዊ፡- ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ሕግ ሥር እንዲያልፍ እድሜው ለትምህርት ሲደርስ እመቤታችን ወስዳ ለገማልያል አስተምርልኝ ብላ ሰጠችው፡፡ ሰው የሚሆነውን ለመሆን ይህን አደረገው እንጂ የመምህራን መሪያቸው፣ የአዋቂዎች እውቀታቸው እርሱ እኮ ነው፡፡
እናቱ ድንግል ማርያም ግን ነገሮችን ሁሉ በልብዋ እየጠበቀች ታስቀምጥ ነበር ለበዓል በኦሪታውያን ልማድ ወደ ቤተ መቅደስ የወጣችም እንደሆነ አስከትላው ትሄድ ነበር፤ ወደ ቤተ መቅደስ መሄድን የጀመረው ልክ አስራ ሁለት ዓመት ሲሞላው እንደነበር መጽሐፍ ይመሰክራል፡፡
በሌሎች ሌዋውያን ከሃያ ዓመት በታች እንዳይወጡ ሥርዓት ተሠርቶባቸዋል እርሱ ግን የሚወጣው በሊቃውንቱ መካከል ተገልጦ ለማስተማር ነውና በዚህ ታናሽ እድሜ ወጥቷል፡፡
(ሕይወተ ማርያም - በሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ)
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
"አዝላው ወረደች"
አዝላው ወረደች ወደ ግብፅ /2/
ስደተኛዋ የአምላክ እናት
ይህ ዓለም ለእርሷ መች ተገባት
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
አዝ
ተመለሺ ሱላማጢስ
ተመለሺ ሱላማጢስ ተመለሺ
እናይሽ ዘንድ ተመለሺ (እመቤቴ)
የአባትሽን ቤት አትርሺ
ኢሳይያስ ተንብዮልሽ
ፈጣን ደመና ያለሽ
ጌታን በጀርባሽ አዝለሽ
በግብጽ በረሃ የዞርሽ
የበረሃው ሙቀት ንዳድ
የሌሊቱ ግርማ ከባድ
በአራዊቱ ድምጽ ሁካታ
ልብሽ በጭንቅ ሲንገላታ።
አዝ..............
አዝ..............
አዝ..............
አዝ..............
✞ሦስት ዓመት ከመንፈቅ
ይህ ዘመን እመቤታችን ከኢየሩሳሌም ውጪ የኖረችበት ዘመን ነው፤ ጌታ በተወለደ በሁለት ዓመቱ ሰብአ ሰገል በመጡበት ወራት ከሄሮድስ ቁጣ የተነሣ ድንግል ከነልጇ በከተማ መቀመጥ አልቻለችም፡፡ ሰይጣን የሰው ልጆችን የመዳን ሥራ ሲጀመር ሲመለከት ዝም አላለም፤ ገና ይወርዳል፣ ይወለዳል ሲባል ትንቢቱን በመስማቱ እነ ኢሳይያስን በመጋዝ አስተርትሮ፣ በኩላብ አሰቅሎ አስገድሎ ነበር ሲወለድም የተወለደውን ሕጻን ማሳደድ ጀመረ፤
በተለይም ሊወለድ ሃያ አምስት ቀን ሲቀረው መላእክት የሚወለድበትን ሥፍራ ቤተልሔምን ተግተው ይጠብቁ ነበርና አጋንንት በጣዖታት አድረው መመለክ ስለተሳናቸው ጣዖታቱም ወድቀው ወድቀው በማለቃቸው ይህንን ምልክት አድርጎ ዲያብሎስ አዳኝነቱን ጀመረ፡፡
የአባቶቻችን አዳኝ እርሱ በእመ አምላክም ላይ ከሰው እስከ አጋንንት የክፋት ሠራዊቶችን አስከትሎ ለሠልፍ ተነሳ፡፡ አስቀድሞ በመጽሐፍ ስለዚች ቀን የተነገረው የመጀመሪያው ትንቢታዊ ቃል በዚህ ጊዜ ተፈጸመ “በአንቺ እና በሴቲቱ መካከል በዘርሽ እና በዘሯም ላይ ጠላትነትን አደርጋለሁ"ይህ ቃል በገነት ውስጥ ከተነገሩ የወደፊት የሰው ሕይወት ጠቋሚ ቃላት አንዱ ሲሆን እመቤታችንና የቀደመው እባብ ተብሎ በሚጠራው ጥንተ ጠላታችን በሠራዊተ አጋንንት እና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መካከል የሚደረገውን ጦርነት የሚያመላክት ቃል ነው፡፡እግዚአብሔር የተናገረው ሊፈጸም ግድ ነውና የንጉሠ ሰማይ ወምድር እናቱ እመቤታችን ድንግል ማርያም የሰይጣን ውጥን ጨራሽ በሆኑ ምድራውያን ነገሥታት ከሀገር ወደ ሀገር ተሰደደች፡፡
ዓለማችን እንዲህ ናት ዓመፀኞች የሚገኑባት፣ እውነት የሚሰደድባት የእሪያ ዓይነት ልማድ ያላት ዓለም ናት፡፡ እሪያ አብሮ የሚኖረው መልኩን ላለማየት እውነተኛ መልኩን ያሳየውን እንቍ ረግጦ ይሰብረዋል፤ ችግሩ እኮ የመልኩ ክፉነት እንጂ እንቍውማ ያለውን መልኩን ነበር ያሳየው፡፡ ዓለማችንም በኃጢአት የበለዘ ፊቷን የሚያሳዩዋት የእውነት መቅረዞችን እንደምንም ተሯሩጣ መርገጥ ትፈልጋለች፤ አሳድዳ የዋጠቻቸው ብዙ ሲሆኑ በለመደችው አሁንም የዋጣትን የኃጢአት ረግረግ ሊያደርቅ የመጣውን ጌታ ለመዋጥ አፏን ከፈተች፡፡
የተከፈተ አንደበቷን ሞት እስኪዘጋው፣ መቃብርም እስኪያትመው ድንግል ከዘንዶው ከሄሮድስ ፊት ሸሸች፤ ከመካከለኛው ምሥራቅ ወደ ምድረ አፍሪቃ ከነልጇ መጣች፤ ከሁለቱ አገልጋዮቿ ከዮሴፍ ከሰሎሜ በቀር ከዘመዶቿ የተከተላት ማንም አልነበረም፡፡
አምላካችን ክርስቶስ ንጉሠ ነገሥት ነውና ከሦስት ነገሥታት ግብርን ተቀበለ ይህን ካደረገ በኋላ ነገሥታቱ ግብራቸውን አቅርበው ሲመለሱ ሰውነቱ ፍጹም እንደሆነ ለማጠየቅ እናቱ ይዛው ተሰደደች በምድር እልፍ እልፍ ሠራዊት የተከተላቸው ሦስት ነገሥታት የሰገዱለት፣ በሰማይ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ሠራዊተ መላእክት የሚገዙለት ሲሆን ተስደደ፡፡
✞ሥላሴ ✞ አምባዬ✞
ሥላሴ አምላኬ ብዬ እዘምራለኹ
ሥላሴ አምባዬ ብዬ እቀኛለኹ
ሰማይና ምድር ደመናት ሳይቀሩ
አዕዋፍ አዝርዕት በእርሱ ተፈጠሩ
አዝ......
አዝ.......
አዝ.......
አዝ......
"የአምላክ አቃቤ ሕግ"
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ጥቅምት ፭
የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (ገብረ ሕይወት) የዕረፍታቸው መታሰቢያ
ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሏቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ፭፻፷፪(562) ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።
ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ፭፻፷፪ ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮጵያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊዮን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።
ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለ'የ'ት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከዕልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።
የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ፻(100) ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።
ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ፳፻(2,000) በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ፰(8)ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ፲፬(14)ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዝዘው መጋቢት ፭(5) ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።
ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል።
ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት ፭(5) ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው። ፍትሃ ነገስት አንቀጽ ፲፭(15) ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ :የመጋቢት ፳፯(27) ስቅለት ጥቅምት ፳፯ ቀን እንደሚከበረው ሁሉ የአባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው ወደ ጥቅምት ፭ ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡
የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው በእኛ በምናምን ላይ ይደርብን!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox