በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox
🛎 የነሐሴ ፰ ግጻዌ
መልእክታት
1. ሮሜ ፱፥፳፬-ፍጻሜ/9፥24-ፍጻሜ
2. ፩ኛ ጴጥሮስ ፬፥፲፪-ፍጻሜ/4፥12-ፍጻሜ
3. የሐዋ ሥራ ፲፮፥፴፭-ፍጻሜ/16፥35-ፍጻሜ
ምስባክ
መዝ ፶፯፥፰/57፥8
"ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ
ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ኅለተ ኮነ
ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ፡፡"
"እሳት ወደቀች ፀሓይንም አላዩዋትም
እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ
ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይነጥቃችኋል፡፡"
ወንጌል
ማቴዎስ ፯፥፲፪-፳፮/7፥12-26
"¹² እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግም ነቢያትም ይህ ነውና።
¹³ በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
¹⁴ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
¹⁵ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።
¹⁶ ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
¹⁷ እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።
¹⁸ መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።
¹⁹ መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
²⁰ ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።
²¹ በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።
²² በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህም.....።
"
ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ(ጎሥዓ)።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ነሐሴ ፯
ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ደጋግ ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሄርም በሰውም ዘንድ የተመሰከረለላቸው ባለጸጎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን መካን ስለነበሩ የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውም፡፡
አንድ ቀን ጴጥርቃ ቴክታን እንዲህ አላት፡- ‹‹እኅቴ ሆይ! ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን? ልጅ የለን የሚወርሰን አንቺም መካን ነሽ፣ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹ወንድሜ ሆይ! አምላከ እስራኤል ለእኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ›› ብላ ብታሰናብተው ‹‹እንደዚህ ያለ ነገር እንኳንስ ላደርገው በልቦናዬም እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቃል›› አላት፡፡ እርሷም ‹‹አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም፣ ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማኅፀኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ፣ ጨረቃዋም ፀሐይን ስትወልድ አየሁ›› አለችው፡፡ እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሄዶ የነገረችውን ሁሉ ነገረው፡፡ ያም ህልም ፈቺ ‹‹እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችኋል በሳህሉ መግቧአችኋል፣ 7 አንስት ጥጆች መውለዳችሁ 7 ሴቶች ልጆችና የልጅ ልጆች ትወልዳላችሁ፣ ከቤታችሁ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለዷ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁ፤ የፀሐይ ነገር ግን አልታወቀኝም›› አለው፡፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ለሚስቱ ነገራት፡፡ እርሷም ‹‹እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል!›› ብላ ዝም አለች፡፡ ከዚያም ፀንሳ ሴት ልጅ ወለደች፡፡ ስሟንም ሔሜን ብለው አወጡላት፤ ሔሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ ባል አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች፣ በስምንተኛ ቀኗም ዴርዲ ብለው ስም አወጡላት፡፡ ዴርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደችና ቶና አለቻት፣ ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሲካር አለቻት፣ ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሴትና አለቻት፣ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ሔርሜላ አለቻት፣ ሔርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽህት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የወለደቻትን ቅድስት ሐናን ወለደች፡፡
ይኽችም ቅድስት ሐና በሥርዓት አድጋ ለአእምሮ ስትበቃና አካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግስት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፡፡ እነርሱም እጅግ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡ አንድ ልጅ እንኳ ስላልነበራቸው እጅግ ያዝኑ ነበር፡፡ ወደ ቤተ መቅደስ እየሄዱ እግዚአብሔር ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ አጥብቀው ይለምኑት ነበር፡፡ መብዓ ይዘው ለሊቀ ካህኑ ሲሰጡት ሊቀ ካህኑም እንኳ ሳይቀር ‹‹እግዚአብሔር ብዙ ተባዙ ያለውን ሕግ በእናንተ ላይ እንዳይፈጸም አድርጎ ልጅ የከለከላችሁ ኃጢአተኛ ብትሆኑ ነውና መብዓችሁን አልቀበልም›› ብሎ በእጅጉ አሳዝኗቸዋል። በሊቀ ካህኑ እያዘኑና እየተከዙ ሲመለሱ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ ዛፍ ሥር ተቀመጠው ሳለ እርግቦች ጫጩቶቻቸውን ሲያጫውቱ ተመልክተው ‹‹ለእነዚህ ወፎች እንኳ ልጆችን የሰጠህ አምላክ ለእኛስ መች ይሆን ልጅ የምትሰጠን?›› ብለው እጅግ አምርረው አለቀሱ፡፡
ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ውኃ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን›› ብለው ስዕለት ገቡ፡፡ ዘካርያስም ‹‹እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስዕለታችሁን ይቀበልላችሁ የልቦናችሁን ሀሳብ ይፈጽምላችሁ›› ብሎ አሳረገላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅድስት ሐናና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩስ እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም ‹‹ሰባቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› አላት፡፡ ‹‹ወፍ›› የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው፤ ‹‹ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ›› ማለቱ የኢያቄምን (የሰውን) ባህርይ ባህርይ እንዳደረገው ዕወቅ ሲል ነው፡፡ ሰባቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይው ምልአቱ ስፍሃቱ ርቀቱ ልእልናው ናቸው፡፡ ቅድስት ሐናም ‹‹እኔም ደግሞ አየሁ እንጂ›› አለችው፡፡ ‹‹ምን አየሽ?›› ቢላት ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ›› አለችው፡፡ ‹‹ርግብ›› የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፣ ነጭነቱ ንጽህናዋ ቅድስናዋ ድንግልናዋ ነው፡፡ ‹‹ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅፀኔ ስትተኛ አየሁ›› ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሷን ነው፡፡ ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው፡፡ እነርሱም እንዲህ ያለ ራእይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም ይልቁንም ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን ‹‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሉአት› ብሎ ያበሰረ አምላክ ለእኛስ ይልክልን የለምን!›› ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ሰባት ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ፡፡ ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ‹‹ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ ብሎሏችኋል ጌታ›› ብሎ መልአኩ ለሐና ነገራት፡፡ በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ተፀነሰች፡፡
እግዚአብሔር አምላክ አብርሃምንና ሳራን የተመለከተ አምላክ በኢያቄምና ሃና አማካኝነት ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነችውንና ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቦና ታስባ ትኖር የነበረች የተነገረላት ትንቢት ሊፈጸም የአባት የእናቷ የቅድመ አያቶቿ ራእይ ሊተረጎም ጌታ የፈቀደበት ጊዜ ሲደርስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እሁድ እለት ነሐሴ 7 ቀን በ16 ዓ.ዓ ተፀነሰች፡፡
እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው፡፡ ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ከአጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ፡፡ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት፡፡ ቅድስት ሐናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት፤ እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላዋ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነሥቶ ‹‹ስብሃት ለኪ ማርያም እሙ ለፀሐየ ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስ ቅዱስ ጽርሃ ቤቱ ተፈስሂ ደስ ይበልሽ" ብሎ ሰገደላት፡፡ አይሁድም ይህ ተአምር ሲደረግ ከዚያው ነበሩና ‹‹ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ?›› ቢሉት እርሱም ‹‹ከዚህች ከሐና ማኅፀን የምትወለደው ሕፃን ‹ሰማይን ምድርን አየርን የፈጠረ አምላክን ትወልዳለች› እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማሁ›› አላቸው፡፡ ዳግመኛም ‹‹እኔንም ያነሣችኝ የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት›› አላቸው፡፡ አይሁድም ‹‹በል ተወው ሰማንህ›› ብለው ቅናት ጀመሩ፡፡ ቅድስት ሐና በእርጅናዋ ጊዜ መፀነሷን የተመለከቱ ዘመዶቿና ያገሯ ሰዎች ተገርመው እየመጡ ይጠይቋት ነበር፡፡ እመቤታችን ማርያም በፅን
የዕለተ ማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ በድምፅ፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
፯. ወደ ደብረ ሲና የወረደው፣ ለሙሴ ሕገ ኦሪትን የሠራ፣ የተራራውን ራስ በጨለማ በእሳት በጽጋግ በነፋስ (በዕበየ ግርማው) የሸፈነ፣ ፈርተው የቆሙትን ፈጥኖ በሚሰማ በረቂቅ ነጋሪት ድምጽ የገሠፀ እርሱ የሰው ልጆችን ለማዳን ፭ ሺሕ ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ሰው ኾኖ የመጣው የአብ አካላዊ ቃል ነው፡፡ በሌላ አንቀጽም ይኸው ሊቅ፡- “እም ደብረ ሲና ወፅአ እሳት ወጽልመት ወእምኔኪ ወፅአ ለነ አምላክ ወሰብእ፡፡ እም ደብረ ሲና ወፅአ ድንጋፄ ወሀውከ ላዕለ አይሁድ ወእምኔኪ ወፅአ ሁከት ወድንጋፄ ዐቢይ ላዕለ አይሁድ ወሄሮድስ ወዲያብሎስ ምስለ አጋንንቲሁ - ከደብረ ሲና እሳት ጨለማ ወጣ፤ ከአንቺ ግን ሰው የኾነ አምላክ ተገኘልን፡፡ በደብረ ሲና በአይሁድ ላይ ድንጋፄ ሀውክ ተደረገ፤ በአንቺም በአይሁድ በሄሮድስ በዲያብሎስና በሠራዊቱ ላይ ጽኑ ድንጋፄ ተደረገ” ብሏል /ዘጸ.፳፡፲፰፣ ዕብ.፲፪፡፲፱፣ ሃይ.አበ.፵፯፡፱-፲/፡፡ እንዲህ ከተባለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፰. “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ” ከሚለው የኢሳይያስ አንቀጽ /ኢሳ.፯፡፲፬/ ስትደርሺ “እኔ በኾንኩኝ” ሳትዪ፤ ይልቁንም “ምነው ከዘመኗ ደርሼ፣ ወጥቼ ወርጄ በድንግልና የምትወልደውን ድንግል ባገለገልኳት” ብለሽ በትሕትና የተናገርሽ ደብር ነባቢት ሆይ! ሰውን የሚወድ፣ ሰውም የሚወደው ጌታ ባሕርዩ ሳይለወጥ ካንቺ ከሥጋሸ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ እንደኛ የሚናገር ሥጋን ነሥቶም ሰው ኾነ፡፡ ጥበብን በሚገልጽ፣ ሥጋዌን በሚያስፈጽም በግብረ መንፈስ ቅዱስ አምላክ በማኅፀንዋ አደረና ፍጹም ሰው ኾነ፡፡ በቸርነቱና በይቅርታው ብዛት አዳምን ያድነው ዘንድ፣ ኃጢአቱንም ያስተሠርይለት ዘንድ፣ በሰማያዊ ቦታ በሰማያዊ መዓርግ ያኖረው ዘንድ /ኤፌ.፪፡፮/፣ ወደ ቀደመው ቦታው ወደ ቀደመው ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ፍጹም ሰው ኾነ፡፡ በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት አዳምን ወደ ቀደመው ቦታ ከመለሰው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፱. የድንግል ክብሯ ሊናገሩት አይቻልም፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ይኸው እየተናርን አይደለምን?” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- “ለርሷ እንደሚገባ አድርጎ መናገር የሚቻለው የለም” ሲል ነው፡፡ “ለምን?” ጌታ መርጧታልና፡፡ አሁንም ከእናንተ መካከል፡- “ታድያ እርሱ ከመረጣትማ ምን ይደንቃል?” የሚል ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም ላይ፡ “በአማን ነጸረ እግዚአብሔር አብ እምሰማይ ምሥራቀ ወምዕራበ ሰሜነ ወደቡበ ወውስተ ኵሉ አጽናፍ አስተንፈሰ ወአጼነወ ወኢረከበ ከማኪ ወሠምረ መዐዛ ዚአኪ ወአፍቀረ ሥነኪ ወፈነወ ኀቤኪ ወልዶ ዘያፈቅር - እግዚአብሔር አብ በሰማይ ኾኖ ምሥራቅንና ምዕራብን ሰሜንንና ደቡብን ዳርቻዎችን ኹሉ በእውነት ተመለከተ፤ ተነፈሰ፤ አሻተተም፤ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፡፡ የአንቺ መዐዛ ወደደ፤ የሚወደውን ልጁንም ወደ አንቺ ላከ” ብሎ እንደተናገረው እንድትመረጥ ኾና ተገኝታለችና ነው /ቅዳ.ማር.ቁ.፳፬/፡፡
ሐዋርያው “ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል” እንዲል /፩ኛ ጢሞ.፮፡፲፮/ በመመርመር ገንዘብ በማድረግ የሚቀርበው በሌለው ብርሃን ባሕርዩ አድሮ የሚኖረ እርሱ /ሃይ.አበ.፴፫፡፫/ ሰው ኾኖ በማኅፀንዋ አደረ /ዮሐ.፩፡፲፬/፡፡ ዘጠኝ ወር ከአምስተ ቀን በማኅጸንዋ ኖረ፡፡ ሰውም ከመኾኑ አስቀድሞ ሰውም ከኾነ በኋላ የማይመረመር እርሱን ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው፡፡ ሰውም ከመኾኑ አስቀድሞ ሰውም ከኾነ በኋላ ከማይመረመረው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፲. ነቢዩ ዳንኤል ያየውና እጅ ሳይፈነቅለው ከረጅም ተራራ የወረደው ደንጊያ /ዳን.፬፡፩-፴፭/ ከአብ ዘንድ የወጣው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ያ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ከረዥሙ ተራራ እንደተፈነቀለ ኹሉ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስም ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ዘር ምክንያት ሳይኾነው ከድንግል ተወለደ፡፡ ዳንኤል በአምሳለ እብን (ደንጊያ) ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፲፩. ሐሩረ ፀሓይ ያልወደቀባት፣ ነፋስ ያልወዘወዛት፣ ለታብቁል (ታብቅል) ባለው ቃል ከልምላሜ፣ ከጽጌ፣ ከፍሬ የተገኘች ዐፅቀ ሠሉስ (የማግሰኞ ቅርንጫፍ) አንች ነሸ /ኩፋ.፪፡፲፪/፡፡ እንዲህ ማለቱ ነው፡- “በዕለተ ሠሉስ የተገኙ ቅጠሎች፣ ቅርንጫፎች ፀሐይ እንዳላጠወለጋቸው፣ ነፋስ እንዳልወዘወዛቸው ኹሉ አንቺም የኃጢአት ፀሐይ አልለወጠሽም፡፡ በሥጋሽ፣ በነፍስሽ፣ በኅሊናሽም ድንግል ነሽ እንጂ” /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን፣ ክፍል ፩፣ ገጽ ፲/፡፡ አባ ጊዮርጊሥም፡- “በበደል ምሣር የማትቈረጪ፣ ከኀጢአት ዐውሎ ነፋስ የተነሣ የማትነዋወጪ፣ ዘወትር ፍጹም የምትለመልሚ፣ በዘመኑ ኹሉ የምታፈሪ፣ በወሮች ኹሉ የምትለቀሚ፣ ከዕፅዋት ኹሉ ይልቅ የምታምሪ እመቤቴ ማርያም ሆይ! የተባረክሽ ዕፅ ነሽ” ይላታል /እንዚራ ስብሐት፣ ገጽ ፲፬/፡፡ አምላክን የወለድሽ ንጽሕት፣ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ኅትምት የምትኾኝ ሆይ! ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ስለ ማዳን ሰው ኹኗልና (አካላዊ ቃልን ወልደሽልናልና) የሃይማኖትም (የክርስቶስም) ሙዳይ (መገኛ) ነሽ፡፡ (በልጅሽ ላመኑ) የአባቶቻችን የቀናች ሃይማኖታቸው ነሽ፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ከኾነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፲፪. የከበርሽ አምላክን የወለድሽ ሆይ! የማይመረመር ቃልን የወሰንሺው የብርሃን እናቱ አንች ነሽ፡፡ እርሱንም ከወለድሽው በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ኖረሻልና በአፍኣ በውስጥ በሥጋ በነፍስ ያከብሩሻል፤ ያገኑሻል፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
@Ethiopian_Orthodox
፲፫. ወዮ! ስለ አንቺ ድንቅ ኾኖ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? ቅድመ ዓለም ያለ እናት ተወልዶ፣ ድኅረ ዓለም ያለ አባት እንደምን እንደወለደሽው መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? የአካላዊ ቃል እናቱ ንጽሕት ደንግል ሆይ! ኪሩቤል ለሚሸከሙት ለንጉሥ ማደሪያ ኾንሽ፡፡ ንዕድ ክብርት ሆይ! እኛም ክብርሽን ገናንነትሽን ዕፁብ ዕፁብ እያልን እናመሰግንሻለን /ሉቃ.፩፡፵፰/፡፡ የአካላዊ ቃል እናቱ መልካሟ ርግብ (ርግበ ኖኅ) ማርያም ሆይ! ስምሽን በትውልደ ሴም፣ በትውልደ ካም፣ በትውልደ ያፌት እንጠራለን፡፡ ሊቁ እመ አምላክን “መልካሟ ርግብ” አላት፡፡ ይኸውም የኖኅ ርግብ “የጥፋት ውሃ ጐደለ፤ የጥፋት ውሃ ተገታ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰላም ነው” ስትል የምሥራቹን የዘይት ቅጠል ይዛ እንደታየች ኹሉ /ዘፍ.፰፡፲፩/ እመቤታችንም “የኀጢአት ውሃ ጐደለ፤ የመርገም ውሃ ተገታ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ዘመነ ሰላም ነው” ስትል ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔን ኣሳልፎ ዓመተ ምሕረትን የተካ፣ ለዓለሙ ኹሉ ታላቅ የምሥራች የኾነ፣ የዓለም መድኃኒት ክርስቶስን ወልዳልናለችና፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
እርሷ “ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም)” ስትባል እንደምትኖር ኹሉ እርሱም “አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው)” ሲባል ይኖራል /ሃይ.አበ.፷፯፡፯/፡፡ ተፈትሖ ሳያገኛት (ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ) እንደምን እንደወለደችው ግን የማይመረመር አንድም ሊነገር የማይችል፣ ከኅሊናት ኹሉ የሚያልፍ ድንቅ ነው፡፡ በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፪. “ቃል ሥጋ ኾነ” እንዲል በእርሱ ፈቃድ /ዮሐ.፩፡፲፬/፣ “ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” እንዲል በአባቱ ፈቃድ /ዮሐ.፫፡፲፮/፣ “በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም እንደ ቀባው” እንዲልም /ሐዋ.፲፡፴፰/ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ሰው ኾኖ አዳነን፡፡ ሊቁ እንዲህ ማለቱ “ወልድ ያለ ፈቃዱ ሰው ኾነ” የሚሉ መናፍቃን ስላሉ ነው፡፡ ሌሎች ሊቃውንትም፡- “የእግዚአብሔር ልጅ ያለ ፈቃዱ ሰው እንደ ኾነ የሚያምን፤ የሚያስተምር፤ ወይም የአብ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የወልድ ፈቃድ ሌላ ነው፤ የመንፈስ ቅዱስም ፈቃድ ሌላ ነው የሚል ቢኖር፤ ፈቃዳቸው አንድ፤ መንግሥታቸውም አንድ እንደኾነ የማያምን ሰው ቢኖር ውጉዝ ይኹን” ብለው አስተምረዋል /ሃይ.አበ.፻፳፫፡፪/፡፡
በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ፍጽምት የምትኾኚ እመቤታችን ሆይ! በድንግልና ጸንተሽ ብትገኚ ላንቺ የተሰጠሸ ጸጋ ፍጹም ነው፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ቢኾን አንድም በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሸልና ለአንቺ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ ይህ ከቃላት በላይ የሚያልፈው ባለሟልነቷ ቅዱስ ባስልዮስ ከሌሎች ቅዱሳን ጋር እያነጻጻረ ሲያብራራው፡- “የዚህ ዓለም ነገር ኹሉ አይመጥናትምና የሚመጥናትን ምን ዓይነት ምስጋና እናቅርብላት? ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ቅዱሳን ሲናገር ዓለም አልተገባቸውም /ዕብ.፲፩፡፴፰/ ካላቸው ከከዋክብት በላይ ኾና እንደምታበራው ፀሐይ ለኾነችው ለአምላክ እናትማ ምን ልንል እንችል ይኾን?... ምን ምሥጢር እንደተከናወነ ተመልከት፤ ኅሊናን አእምሮን የሚያልፍ ነገር እንደኾነም አስተውል፡፡ ታድያ የአምላክ እናት ታላቅነት እንደምን ኹሉም ሰው አይናገር? ማንስ ነው ከቅዱሳን ኹሉ በላይ እንደኾነች ያላስተዋለ? እግዚአብሔር ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠና የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፣ ጥላቸው ያረፈበት ተአምር ከተፈጸመለት፣ ጴጥሮስ በጥላው ካዳነ /ሐዋ.፭፡፲፭/፣ የጳውሎስ የልብሱ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ /ሐዋ.፲፱፡፲፩/ ለእናቱማ ምን ዐይነት ሥልጣንና ኀይል ተሰጥቷት ይኾን? በምን ዓይነትስ ሥጦታ አስጊጧት ይኾን? ጴጥሮስ፡- ክርስቶስ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ስላለው ብፁዕ ነህ ከተባለና የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ ከተሰጠው /ማቴ.፲፮፡፲፮-፲፱/ እርሷማ ከኹሉም ይልቅ እንዴት ብፅዕት አትኾን? /ሉቃ.፩፡፵፭/ ጳውሎስ ታላቅ ክብር ያለውን የክርስቶስን ስም በመሸከሙ ምርጥ ዕቃ ከተባለ /ሐዋ.፱፡፲፭/ የአምላክ እናትማ የምእመናን ምግብ የኾነ መናውን ሳይኾን የሕይወት ሰማያዊ እንጀራን ያስገኘች እርሷ ምን ዓይነት ልዩ ዕቃ ትኾን? … ነገር ግን ስለ እርሷ ብዙ እናገራለሁ ብዬ ስለ ክብሯ ጥቂት በመናገር ራሴን በኀፍረት ውስጥ እንዳልጨምር እፈራለኁ፡፡ ስለዚህ ከአሁን ወዲህ የንግግሬን መልሕቅ ስቤ በዝምታ ወደቤ ላይ ማረፍን መርጫለሁ” ይላል /መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፣ ነገረ ማርያም በሐዲስ ኪዳን፣ ገጽ ፺-፺፩ ይመልከቱ/፡፡
ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲፰-፲፱/፡፡ መተርጕማኑ ይህ ምን ማለት እንደኾነ ሲያብራሩ፡- “ከምድር እስከ ሰማይ መድረሷ የልዕልናዋ፣ በላይዋ ላይ ዙፋን ተነጽፎባት ንጉሥም ተቀምጦባት ማየቱ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀኗ ለመሸከሟ፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ማየቱ ደግሞ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰው የጸለየውን ጸሎት ያቀረበውን መሥዋዕት ለማሳረግ አይወጡም አይወርዱም ነበር፤ ጌታችን ከእመቤታችን ሰው ከኾነ በኋላ ግን ለተልእኮ የሚወጡ የሚወርዱ ኾነዋልና ሲል ነው” ይላሉ /ሉቃ.፪፡፲፬፣ ሐዋ.፲፡፫-፬፣ የኦሪት ዘልደትን ትርጓሜ ይመልከቱ/፡፡ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ በአምሳለ ንጉሥ ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፫. ነደ እሳት ሰፍሮባት፤ በነደ እሳት ተከባ (ጫፎቿ) ሳትቃጠል ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፫፡፩-፫/፡፡ ነደ እሳትም ያልኹት ሰው ኾኖ በማኅፀንሽ ፱ ወር ከ፭ ቀን ያደረው ወልደ እግዚአብሔር ነው፡፡ ምንም እንኳን አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ቢኾንም እሳተ መለኮቱ አላቃጠለሽም፡፡ አባ ሕርያቆስ ይህ ከኅሊናት የሚያልፈውን ነገር ሲያደንቅ ፡- “ቅድስት ድንግልን ለኹሉ ድንቅ የሚኾን የፅንሷን ነገር እንዲህ እያልን እንመርምራት፡፡ ድንግል ሆይ! እሳተ መለኮት በማኅፀንሽ ባደረ ጊዜ አካሉ እሳት ነው፤ መጐናጸፍያው እሳት ነው፤ ቀሚሱ መቋረፍያው እሳት ነው፡፡ እንደምን አላቃጠለሽ? ብለን እንመርምር፡፡ ሰባት የእሳት ነበልባል መጋረጃ በማኅፀንሽ ወዴት ተዘጋጀ? ወዴት ተጋረደ? በቀኝ ጐንሽ ነውን? ወይስ በግራ ጐንሽ ነውን? ሦስት ክንድ ከስንዝር ቁመት የተወሰንሽ ስትኾኚ እንደምን ቻልሽው? የአሥራ አምስት ዓመት ቆንጆ ስትኾኚ አጎበሩ ሻኩራው ነደ እሳት የሚኾን፤ ዐይን የሚበዘብዝ ኪሩቤል የተሸከሙት መንበር ወዴት ተዘረጋ? ወዴት ቆመ?” ይልና /ቅዳ.ማር.ቁ.፸፯-፸፰/ “ኅሊናዬ ይህን አልመረምርም ብሎት ወደ ቀደመ አኗኗሩ ይመለሳል” ብሎ ይቋጨዋል /ቁ.፹፬/፡፡
🔔 ዛሬ ምን ይቀደሳል?
የነሐሴ ፮(6) ግጻዌ
መልእክታት
1. ፩ኛ ቆሮንቶስ ፫ ፥ ፲ - ፳፪ /3 ፥ 10-22
2. ፩ኛ ጴጥሮስ ፫ ፥ ፩ - ፯ / 3 ፥ 1 - 7
3. ግብረ ሐዋርያት ፲፮ ፥ ፲፫ - ፲፱ /16 ፥ 13-19
ምስባክ
መዝ ፵፭ ፥ ፲፪ - ፲፫ /45 ፥ 12-13
"ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ።
ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር።
ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን።"
"የጢሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መንሻን ይዘው ይሰግዱለታል።
የምድር ባለጠጎች አሕዛብ በፊትህ ይማለላሉ።
ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብርዋ ነው"
ወንጌል
የማርቆስ ወንጌል ፲፮ ፥ ፱ - ፲፱ /16 ፥ 9-19/
"፱
ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሣ ጊዜ፥ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግደላዊት ማርያም ታየ።
፲
እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው፤
፲፩
እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም።
፲፪
ከዚህም በኋላ ከእነርሱ ለሁለቱ ወደ ባላገር ሲሄዱ በመንገድ በሌላ መልክ ተገለጠ፤
፲፫
እነርሱም ሄደው ለሌሎቹ አወሩ፤ እነዚያንም ደግሞ አላመኑአቸውም።
፲፬
ኋላም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ተገለጠ፥ ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኑአቸው አለማመናቸውንና የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ።
፲፭
እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
፲፮
ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።
፲፯
ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥
፲፰
የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።
፲፱
ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።"
ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) አው ዘሠለስቱ ምዕት (በግዕዝ ዜማ)።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
፰. የሰው ኹሉ አእምሮ በአፍአ በውስጥ በሥጋ በነፍስ ደስ ይላታል፡፡ “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ- አምላክ ለኾነ ለሥጋ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በአንድነት ምስጋና ይገባዋል፡፡ በምድርም ዕርቅ ተወጠነ፡፡ የሰው ግዕዛኑ ይሰጠው ዘንድ” እያሉ ከመላእክት ጋራ (እንደ መላእክት) ንጉሥ ክርስቶስን ያመሰግኑታል /ሉቃ.፪፡፲፬/፡፡ አንድም “ዮም አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ በቃለ አሚን- ” እንዲል የሰው ፍቅር አገብሮት አምላክ ሰው ቢኾን ሰውም አምላክ ቢኾን በመላእክት ዘንድ ምስጋና ተደረገ፡፡ በምድርም አንድነት ተደረገ፤ ኖሎት (እረኞች) ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው አመሰገኑ /ሉቃ.፪፡፳/፡፡ “ኃጢአትን አጠፋ፤ በመስቀልም ተሰቅሎ ፍዳን አጠፋ፡፡ በመቃብርም ፈርሶ በስብሶ መቅረትን አጠፋ፡፡ በሲዖልም ሞተ ነፍስን አጠፋ፡፡ ሥራ በሠራበት ኹሉ ድኅነትን አደረገልን” እንዲል የቀደመ መርገመ ሥጋ መረገመ ነፍስን አጥፍቷልና ኖሎት ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው አመሰገኑ /ሃይ.አበ.፹፱፡፳፬/፡፡ የጸላኢ የዲያብሎስ ምክሩን አፍርሶበታልና ኖሎት ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው አመሰገኑ፡፡ በመቅድመ ወንጌል “ወበከመ ኮነ በጉህለት ተኀብአ ሰይጣን ውስተ ሥጋ ከይሲ ከማሁ ኮነ ድኅነትነ በተሰውሮ ቃለ እግዚአብሔር ዘመድነ- ሰይጣን በተንኰል በሥጋ ከይሲ እንደተሠወረ እኛም ከፍዳ መዳናችን ቃለ እግዚአብሔር በባሕርያችን በመሠወሩ ኾነ” እንዲል በሥጋ ከይሲ ተሰውሮ ቢያስትበት በሥጋ ተሰውሮ አድኖበታልና ኖሎት ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው አመሰገኑ፡፡ ዲያብሎስ “ሥጋን በመቃብር ነፍስን በሲኦል ተቆራኝቼ እኖራለሁ” ብሎ ነበርና የመከረባቸውን ሥጋንና ነፍስን ተዋሕዶ አድኖበታልና ኖሎት ከመላእክት ጋራ አንድ ኾነው ንጉሥ ክርስቶስን አመሰገኑ፡፡ ይኸውም ጥበበኛው ሰሎሞን “ጠቢብ የኃያላንን ከተማ ይገባባታል፥ የሚታመኑበትንም ኃይል ያፈርሳል” እንዳለው ነው /ምሳ.፳፩፡፳፪/፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፤ የአዳምንና የሔዋንን የዕዳ ደብዳቤቸውን አጥፍቶላቸዋልና /ቈላ.፪፡፲፬/ “አምላክ ለኾነ ለሥጋ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በአንድነት ምስጋና ይገባዋል፡፡ በምድርም ዕርቅ ተወጠነ፡፡ የሰው ግዕዛኑ ይሰጠው ዘንድ” እያሉ መላእክት አመሰገኑት /ሉቃ.፪፡፲፬/፡፡ ዲያብሎስ በአዳምና በሔዋን የጨለማ መጋረጃ ጋርዶ ሥቃይ አጽንቶ “ስመ ግብርናት ጽፋችሁ ብትሰጡኝ አቀልላችኋለሁ” ብሏቸው አዳም ገብሩ ለዲያብሎስ ሔዋንም አመቱ በዲያብሎስ ብለው ጽፈው ሰጥተውት ነበር፡፡ ዲያብሎስም ያንን በእብነ ሩካም ጽፎ አንዱን በዮርዳኖስ አንዱን በሲኦል ጥሎት ነበር፡፡ አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ኾኖ ሲመጣ ግን ዲያብሎስ በዮርዳኖስ የጣለውን ሲጠመቅ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ እንደ ሰውነቱ ተረግጦ አጥፍቶታል፤ በሲኦል የጣለውንም በዕለተ ዐርብ በአካለ ነፍስ ወርዶ አጥፍቶላቸውና መላእክት አመሰገኑት /ቈላ.፪፡፲፬/፡፡ በዳዊት ሀገር ከዳዊት ባሕርይ የተወለደ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ሔዋንን ነጻ አድርጓቸዋልና አመሰገኑት /መዝ.፻፴፪፡፲፩/፡፡ አዳምንና ሔዋንን ነጻ ካደረጋቸው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፱. በዚህ ዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ኹሉ የምታበራ (ዕውቀትን የምትገልጥ)፣ ጠፈር ደፈር የማይከለክልህ፣ መዓልትና ሌሊትም የማይፈራረቅብህ ብርሃን ዘበአማን (እውነተኛ ብርሃን) ክርስቶስ ሆይ! ስለ ሰው ፍቅር ልሙት ልሰቀል ብለህ ወደ ዓለም በመምጣትህ ፍጥረት ኹሉ ደስ አለው፡፡ አዳምን ከስሕተት፣ ሔዋንንም ከሞት ፃዕረኝነት (ከመጣባቸው ፍዳ) ነፃ አድረገኻቸዋልና ለእኛ በተደረገው ክብር መላእክት ከእኛ ጋር ደስ አላቸው /ሃይ.አበ.፷፰፡፴፪/፡፡ የሰው ፍቅር አገብሮህ ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስነህ ሲያዩህ “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር” ብለው መላእክት አመሰገኑ፡፡ ከዚህም የተነሣ በጣዕም ላይ ጣዕም በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋል፡፡ እኛም ቅብዐ ትፍስሕት የሚኾን መንፈስ ቅዱስን አንድም ሀብተ ልደትን ተቀብለን ከመላእክት ጋር ደስ አለን፤ አመሰገንንህም፡፡ እንስሳት፣ አራዊት ስንኳ ሳይቀሩ ሰው ከፈጣሪው ጋር በመታረቁ ደስ ብሏቸዋል፡፡
ጽንዕት በድንግልና ቅድስት እመቤታችን ሆይ! ብርሃን ከሚባል ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ይህንን ሲጨርስ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ባርካው ዐረገች፤ እርሱም እጅ ነሥቶ ቀርቷል፡፡
አነሣሥቶ ላስጀመረን አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
“ለምኚልን” ሲልም ልክ በዚህ ምድር እንደነበረው ዓይነት ልመና ከዚያ በኋላ ኖሮባት አይደለም፡፡ ስንኳን በሷና በሌሎችም የለባቸውም፡፡ በቀደመ ልመናዋ የምታስምር ስለ ኾነ እንዲህ አለ እንጂ፡፡ ይኸውም በቃል ኪዳኗ ማለት ነው፡፡ አንድም በቁሙ ይተረጐማል፡፡ ማዘከር (ማሳሰብ) አለና፡፡
“ሰአሊ ለነ ቅድስት” የሚለው ቅዱስ ኤፍሬም የተናገረው አይደለም፡፡ “ታድያ ይህን የጨመረው ማን ነው?” በሚለው ላይም ኹለት ዓይነት አመለካከለት አለ፡፡ “ቅዱስ ያሬድ ለዜማ መከፈያ ተናግሮታል” የሚሉ አሉ፤ “የኋላ ሊቃውንት ተናግረውታል” የሚሉም አሉ፡፡
፪. ወዶም አልቀረም ዘር ምክንያት ሳይኾነው ከድንግል በሥጋ ተወለደ፡፡ “አኮ ወልደ ማርያም በመለኮቱ አላ በከመ ሥርዓተ ትሥብእቱ- በመለኮቱ የማርያም ልጅ አይደለም፤ በተዋሐደው ሥጋ ነው እንጂ” እንዲል ድርሳነ ቄርሎስ በመለኮት ሳይኾን በሥጋ ተወልዶ አዳነን፡፡
ከእናንተ መካከል፡- “ልደቱ በዘርዕ ያላደረገው እንበለ ዘርዕ ያደረገው ስለ ምንድነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡-
· አንደኛ፡ “ልደት ቀዳማዊ ተዐውቀ በደኃራዊ” እንዲል ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን ሲፈጸም ከእመቤታችን ያለ አባት መወለዱ ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት እንደ ተወለደ ለማጠየቅ፤
· ኹለተኛ ደግሞ ሊቃውንቱ እንደሚነግሩን በዘርዕ በሩካቤ ተወልዶ ቢኾን ኖሮ መናፍቃን “ዕሩቅ ብእሲ ነው” ባሉት ነበርና ነው፡፡ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ ይህን ሲያብራራው፡- “ሰውም በኾነ ጊዜ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ አልተወለደም፤ አምላክ ሰው ኾነ እንጂ፡፡ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢኾንስ ብዙ ሰዎች በተሳሳቱ ነበር፤ አምላክ ሰው መኾኑንም ሐሰት ባደረጉት ነበር” ይላል /ሃይ.አበው. ፷፡፲፱/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም፡- “እንደ እኔስ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢኾን ብዙ ሰዎች ዕሩቅ ብእሲ ባሉት ነበር፤ አምላክነቱንም በካዱት ነበር” ይላል /ሃይ.አበ. ፷፮፡፴፪/፡፡
አሁንም ከእናንተ መካከል፡- “ያውስ ቢሆን ተፈትሖ ካላት ያላደረገው፣ ተፈትሖ ከሌላት ያደረገው ስለ ምንድነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡-
· አንደኛ “እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች” ተብሎ የተነገረውን /ኢሳ.፯፡፲፬/ ለመፈጸም ሲኾን፤
· ኹለተኛው ደግሞ ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ ይኸውም አዳም ከኅቱም ምድር ተገኝቷል /ዘፍ.፩፡፳፮/፤ ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል /ሕዝ.፵፬፡፩/፡፡ ሔዋን በኅቱም ገቦ (ጐን) ተገኝታለች /ዘፍ.፪፡፳፩/፤ ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል፡፡ ቤዛ ይሥሐቅ የሚኾን በግዕ ከኅቱም ጉንድ ተገኝቷል /ዘፍ.፳፪፡፲፫/፤ ቤዛ ዓለም ክርስቶስም በኅቱም ማኅፀን ተወልዷል፡፡ ጽምዐ እስራኤልን ያበረደ ውሃ ከኅቱም እብን (ዐለት) ተገኝቷል /ዘጸ.፲፯፡፮/፤ ጽምዐ ነፍሳትን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተገኝቷል፡፡ ጽምዐ ሶምሶንን ያበረደ ውሃ በኅቱም መንሰከ አድግ (የአህያ መንጋጋ) ተገኝቷል /መሳ.፲፭፡፲፱/፤ ጽምዐ ኃጥአንን ያበረደ ማየ ሕይወት ጌታም በኅቱም ማኅፀን ተገኝቷል፡፡ የዚህ ኹሉ ምሳሌ ፍጻሜው አንድ ነው፡፡ ይኸውም ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ‘ከመ ትኩን መራሒተ ለሃይማኖት ዐባይ - ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ’ /ሃይ.አበ.፷፮፡፴፪/ እንዲላት እመቤታችን ጌታን ብትወልደው ማኅተመ ደንግልናዋ እንዳልተለወጠ ኹሉ እርሱም ሰው ሲኾን አምላክነቱ ላለመለመጡ ምሳሌ ነው፡፡ ዳግመኛም እርሷ “ድንግል ወእም” ስትባል መኖሯ እርሱም “አምላክ ወሰብእ” ሲባል ለመኖሩ ምሣሌ ነው፡፡
እናም አዳምን ያድነው ዘንድ የፈቀደ አምላክ ከይሲ ዲያብሎስ ያሳታት ሔዋንን “ጻርሽን ጋርሽን ምጥሽን አበዛዋለሁ” ብሎ እግዚአብሔር ከፈረደባት በኋላ ሊቁ አባ ሕርያቆስ “ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኀያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት- የሰው ፍቅር ከዙፋኑ ስቦ ጐትቶ አወረደው፤ ከሞትም አደረሰው” እንዲል /ቅዳ.ማር. ቁ. ፻፳፭/ ሰውን ወደደና ሔዋንን ነጻ አደረጋት /ገላ.፭፡፩/፡፡ ሔዋንን ነጻ ካደረገ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፫. ከታላቅ ፍቅሩ የተነሣ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ የፈቀደ፣ ሔዋንንም ወድዶ ነጻ ያደርጋት ዘንድ ሰው የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /ዮሐ.፩፡፲፬/፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚለው ስም የመለኮት ብቻ ወይም የትስብእት ስም ብቻ አይደለም፡፡ “ወእነግር አነሂ ከመ ኢመፍትው እስምዮ ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ ዘእንበለ ትስእብት ወኢ ለትስብእት ዘእንበለ መለኮት ክርስቶስሀ ይሰመይ ወእም ቅድመ ትሥጉት አልቦ ዘይሰምዮ በዝንቱ ስም ለቃለ እግዚአብሔር ክርስቶስ- ክርስቶስ ሲል ብትሰማ ብቻ አምላክ እንደኾነ ብቻ ሰውም እንደኾነ አታስብ፡፡ አንድ እንደ መኾኑ ሰው የኾነ አምላክ ነው እንጂ” /ሃይ.አበ.፷፰፡፵/ እንዲል ከኹለት አካል አንድ አካል ከኹለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ቢኾን የወጣለት ስም ነው እንጂ፡፡
አዳምን ነጻ ያደርገው ዘንድ ሰው የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ ላይ አደረ /ዮሐ.፩፡፲፬/፡፡ ለአባቱ እንደ አንድ ልጅ ክብር የሚኾን ክብሩንም አየንለት፡፡ ልጅ ለአባቱ አንድ የኾነ እንደኾነ ደጃፍ የመለሰው ማጄት የጎረስው ኹሉ ገንዘቡ ነው፡፡ ለእርሱም “እስመ ኵሉ ዘቦ ለአቡየ ዚኣየ ውእቱ- ለአብ ያለው ኹሉ የእኔ ነው” /ዮሐ.፲፮፡፲፭/ እንዲል የአብ ገንዘብ ኹሉ ገንዘቡ ነውና ለአባቱ እንደ አንድ ልጅ የሚኾን ክብሩን አየንለት፡፡ “ወይሰገድ ከመዋሕድ- እንደ አባቱ ይመለካል” እንዲል ለአባቱ እንደ አንድ ልጅነቱ የሚኾን ክብሩን አየንለት፡፡ የአባቱን ጌትነት በደብረ ሲና እንዳየነ /ዘጸ.፲፱/ የእርሱንም ጌትነት በደብረ ታቦር አየንለት /ማቴ.፲፯፡፩-፰/፡፡ አባቱ በኤልያስ አድሮ አንድ ምዉት /፩ኛ ነገ.፲፯/፣ በኤልሳዕ አድሮ ኹለት ምዉት ሲያስነሣ እንዳየነው /፪ኛ ነገ. ፬/፤ እርሱም ሥጋን ተዋሕዶ የአራት ቀን ሬሳ አልዓዛርን ሲያስነሣ አየነው /ዮሐ.፲፩/፡፡ ይህን ጠቅለል አድርጐ ቅዱስ ባስልዮስ ሲናገረው፡- “ስለ አብ የተናገርነው ኹሉ ለወልድ ገንዘቡ ነው፡፡ በመልክ ይመስለዋል፤ በባሕርይ ይተካከለዋልና፡፡ ወንጌላዊው ዮሐንስ ለአባቱ አንድ እንደ ኾነ ልጅ ክብር ያለ ክብሩን አየን አለ” ይላል /ዮሐ.፩፡፲፬፣ ሃይ.አበ.፴፫፡፳፰/፡፡
የመጽሐፍ ልማድ ኾኖ የብሉዩን ለአብ የሐዲሱንም ለወልድ ሰጥቶ ተናገረ እንጂ ኹሉም በኹሉ አሉ፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ያውስ ቢኾን (ቅዱስ ኤፍሬም) ወዴት ነበርና ነው አየንለት የሚለው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- አየንለት የሚለው የብሉዩን የእነ ሙሴን ዐይን ዐይን አድርጎ፤ የሐዲሱን ደግሞ የእነ ጴጥሮስን ዐይን ዐይን አድርጎ መናገሩ ነው፡፡ ይኸውም አባ ሕርያቆስ የሓዋርያትን መብል መብል አደርጎ፡- “በላዕነ ወሰተይነ ምስሌሁ - ከእርሱ ጋር በላን ጠጣን” እንዳለው ማለት ነው /ቅ.ማር. ቁ.፹፮/፡፡
ይህ ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የኾነው ክብሩን ያየንለት ወዳጅ ይቅር ይለን ዘንድ ወደደ፡፡ ይቅር ይለን ዘንድ ከወደደ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና፤ እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
የሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም እመቤታችን ከባረከችው በኋላ ምስጋናውን የጀመረው “ፈቀደ እግዚእ…” ብሎ ነው፡፡
፩. በመቅድመ ወንጌል “ወአልቦቱ ካልእ ሕሊና ዘንበለ ብካይ ላዕለ ኃጢያቱ - በኃጢአቱ ከማዘን፣ ከማልቀስ በቀር ሌላ ግዳጅ አልነበረውም” እንዲል ጌታ ፭ ሺህ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ ያዝን ይተክዝ የነበረ አዳምን ነጻ ያደርገው (ያድነው) ዘንድ ወደደ፡፡ ምድራዊ ንጉሥ የተጣላውን አሽከር “ሰናፊልህን (ልብስህን) አትታጠቅ፤ እንዲህ ካለ ቦታም አትውጣ” ብሎ ወስኖ ያግዘዋል፡፡ በታረቀው ጊዜ ግን ርስቱን፣ ጉልበቱን፣ ቤቱን፣ ንብረቱን እንደሚመልስለት ኹሉ ንጉሠ ሰማይ ወምድር እግዚአብሔርም “ጥንቱንም መሬት ነህና ወደ መሬት ተመለስ” /ዘፍ.፫፡፲፱/ ብሎ ፈርዶበት የነበረ አዳምን ይቅር ብሎ ወደ ቀደመ ቦታው ወደ ገነት፣ ወደ ቀደመ ክብሩ ወደ ልጅነት ይመልሰው ዘንድ ወደደ /ሉቃ.፳፫፡፵፫/፡፡
🔔
የነሐሴ ፭(5) ግጻዌ
መልእክታት
1. ፪ኛ ቆሮንቶስ ፲፪ ፥ ፲ - ፲፯ (12:10-17)
2. ፩ኛ ዮሐንስ ፭ ፥ ፲፬ - ፍጻሜ (5:14-ፍጻሜ)
3. የሐዋርያት ሥራ ፲፭ ፥ ፩ - ፲፫ (15:1-13)
ምስባክ
መዝ ፲፯ ፥ ፵፫ /17 ፥ 43
"ወትሠይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ።
ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ።
ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ።"
"የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥
የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።
በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፤"
ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል ፲፭ ፥ ፩ - ፲፩ (15:1-11)
፩
ቀራጮችና ኃጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር።
፪
ፈሪሳውያንና ጻፎችም። ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው አንጐራጐሩ።
፫
ይህንም ምሳሌ ነገራቸው እንዲህ ሲል።
፬
መቶ በግ ያለው ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፥ ዘጠና ዘጠኙን በበረሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሄድ ከእናንተ ማን ነው?
፭
ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል፤
፮
ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ። የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል።
፯
እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።
፰
ወይም አሥር ድሪም ያላት አንድ ድሪም ቢጠፋባት፥ መብራት አብርታ ቤትዋንም ጠርጋ እስክታገኘው ድረስ አጥብቃ የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
፱
ባገኘችውም ጊዜ ወዳጆችዋንና ጐረቤቶችዋን በአንድነት ጠርታ። የጠፋውን ድሪሜን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ትላቸዋለች።
፲
እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።
፲፩
እንዲህም አለ። አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት።"
ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ) አው ዘሠለስቱ ምዕት (በግዕዝ ዜማ)።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች ዕመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን፤ ሃገራችንን ኢትዮጵያ ከጥፋት፣ ቤተክርስቲያንን ከመናፍቃን፣ ህዝቦቿን ከስደት ትጠብቅልን።
ጾሙን ጾመ ሥርየት፤ ጾመ መድኃኒት ያድርግልን- አሜን ፡፡
ልመናዋ ክብሯ የልጅዋም ቸርነት ከኹላቸን ጋራ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር አሜን፡፡
ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ለሕዝበ ክርስትያን ይዕቀቦም እመዓተ ወልዳ።
ጸሎታ ለማርያም ወስእለታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ይዕቀባ እመዓተ ወልዳ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የሰንበተ ክርስቲያን(እሑድ) ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
በዚህ ዕለት እመቤታችን ከወትሮው ይልቅ ቀደም ብላ መጥታለች፡፡ “ዛቲ ዕለት ተዓቢ እምኩሎን ዕለታት፤ ወውዳሲያቲሃኒ የዓብያ እምኵሉ ውዳሴያት - ከዕለታት ኹሉ ይህቺ ዕለት ታላቅ ናት፤ ከውዳሲያቱም ኹሉ የዚች ዕለት ውዳሴ ታላቅ ነው” አለችውና ባረከችው፡፡ እርሱም በቤተ መቅደስ ባሉ ንዋያት ማለትም፡- በመሶበ ወርቅ፣ በተቅዋመ ወርቅ፣ በማዕጠንተ ወርቅ፣ በበትረ አሮን እየመሰለ ሲያመሰግናት አድሯል፡፡
፩. ተሰመይኪ ፍቅርተ ኦ ቡርክት እምእንስት አንቲ ውእቱ ዳግሚት ቀመር እንተ ተሰመይ ቅድስተ ቅዱሳን ወዉስቴታ ጽላተ ኪዳን። ፲ቱ ቃላት እለ ተጽሕፍ በአፃብዒሁ ለእግዚአብሔር ቀዲሙ ዜነወነ በየዉጣ እንተ ይእቲ ቀዳሜ ስሙ ለመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ውላጤ። ወኮነ ዓራቄ ለሐዲስ ኪዳን። በውኂዘ ደሙ ቅዱስ አንጽሐሙ ለማሃይማን ወለሕዝብ ዝጹሐን። ሰአሊ ለነ ቅድስት።
ንዕድ ክብርት ሆይ! ከሴቶች ተለይተሽ የሥላሴ ባለሟል ተባልሽ፡፡ ከተለዩ የተለየሽ፣ ከከበሩ የከበርሽ፣ ቅዱሳን ኪሩቤል የተሣሉብሽ፣ ቅዱሳን ካህናት የሚያመሰግኑሽ ኹለተኛ ክፍል አንቺ ነሽ /ዘጸ.፳፮፡፩-፴/፡፡
ሕግ የተጻፈባት ጽላት ያለብሽ የምትባዪ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፴፪፡፲፭-፲፱/፡፡ ኪዳንም ያልኹት በእግዚአብሔር ጣቶች የተጻፉ (በግብር አምላካዊ የተገኙ) ዐሥሩ ቃላት ናቸው፡፡ ዐሥርቱ ቃላትን በጽላቱ ጽፎ እንዳኖረ ኹሉ ዋሕድ ቃለ እግዚአብሔርም በአፃብዐ መንፈስ ቅዱስ (ያለ ወንድ ዘር፣ በግብረ መንፈስ ቅዱስ) በማኅፀንሽ እንዲቀረጽ ኾኗልና የሙሴ ጽላት አንቺ ነሽ /ቅዳ.ማር. ቁ.፴፫/፡፡ ዐጤ ዘርዐ ያዕቆብም በነገረ ማርያም መጽሐፉ፡- “.. ወማኅፀናሰ ለማርያም ድንግል በክልኤ ይትሜሰል በጽላት ዘተጽሕፈ ውስቴታ ዐሠርተ ቃላት፡፡ ወዐሠርተ ቃላት ቀዳሜ ስሙ ለወልዳ ውእቱ ዘውእቱ የውጣ ዘተሰምየ በኈልቄ ዐሠርተ ቃላት -..በኹለት ወገን ድንግል የምትኾን የማርያም ማኅፀንስ ዐሥሩ ቃላት በውስጧ በተጻፈ ጽላት ይመሰላል፡፡ ዐሥሩ ቃላትም የልጇ የኢየሱስ ክርስቶስ የመዠመርያ ስሙ ነው፤ ያውም የውጣ በዐሥሩ ቃላት የተጠራ ነው” ብሏል /ነገረ ማርያም በብሉይ ኪዳን፣ ክፍል ፩፣ ገጽ ፻፳፰ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ/፡፡
ከአንቺ ሳይለወጥ ሰው ኾነን፡፡ ለኦሪት ሳይኾን ለወንጌል ሊቀ ካህናት ኾነን፡፡ ለምድረ ርስት ሳይኾን ለመንግሥተ ሰማያት አስታራቂ ኾነን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን፤ እርሱም የበደላችን ስርየት ነው” እንዲል በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን አዳናቸው /ኤፌ.፩፡፯/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም የኤፌሶንን መልእት በተረጐመበት በአንደኛው ድርሳኑ ላይ፡- “ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኘነው ሥርየተ ኃጢአት በርግጥ ታላቅ ነው፡፡ ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው በልጁ ደም መኾኑ ግን ከምንም በላይ ታላቅ ነው” በማለት የእግዚአብሔር ከኅሊናት የሚያልፈውን የማዳን ምሥጢር (ፍቅር) በመደነቅ ተናግሯል፡፡
በከበረ ደሙ ፈሳሽነት በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን ካዳነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኩለሄ ዘግቡር እምዕፅ ዘኢይትቅዝ ይትሜሰል ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ ዘኮነ ሰብአ ዘእንበለ ፍልጠት ወኢዉላጤ፡ መለኮት ንጹሕ ዘአልቦ ሙስና ዘዕሩይ ምስለ አብ ወቦቱ አብሠራ ለንጽሕት፡ ዘእንበለ ዘርእ ኮነ ከማነ በኪነ ጥበቡ ቅዱስ፡ ዘተሰብአ እምነኪ ዘንበለ ርኩስ፡ ደመረ መለኮቶ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።
፪. ኹል ጊዜ ንጽሕት የምትኾኚ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ! ስለዚህ ነገር ኹላችን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለንም፡፡ ሰውን ከሚወድ ሰው ከሚወደው ከርሱ ይቅርታን እናገኝ ዘንድ ኹል ጊዜ ዓይነ ልቦናችንን ወዳንቺ እንሰቅላለን፡፡ ሸምሸር ሰጢን ከሚባል ከማይነቅዝ (በአምልኮተ ጣዖት ከማይለወጥ) እንጨት የተቀረጸ በአፍአ በውስጥ በወርቅ የተለበጠ ታቦት አካላዊ ቃልን ይመስልልናል /ዘጸ.፳፭፡፱-፳/፡፡ ይህ ንጹሕ የሚኾን፣ መለወጥ የሌለበት እርሱ ባለመለወጡ አለመለወጧን ነገራት፤ ከአብ ዕሪና ባለመለየቱም አለማለየቷን ነገራት (አምላክ ወሰብእ ኾኖ እርሷም እም ወድንግል መኾኗን ነገራት)፡፡ ከጥበብ በሚበልጥ ጥበብም ዘር ምክንያት ሳይኾነው እንደ እኛ ሰው ኾነ፡፡ አበው፡- “ዓለሙን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ ሰው ኾኖ ዓለሙን ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል” የሚሉትም ስለዚሁ ነው፡፡ አደፍ ጉድፍ ሳያገኝሽ መለኮቱን አዋሕዶ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ መለኮቱን አዋሕዶ ሰው ከኾነ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
መቅደስ ዘይኬልልዋ ኪሩቤል እለ ሥዑላን በሥዕለ እግዚአብሔር፡ ቃል ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ዉላጤ ኮነ ሠራዮ ኃጥአትነ ወደ ምሳሴ አበሳነ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።
፫. እግዚአብሔር በፈጠራቸው በኪሩቤል አምሳል፤ ሙሴ የሣላቸው ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደሰ ሙሴ አንቺ ነሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በፈጠራቸው በኪሩቤል አምሳል፣ ሰሎሞን የሣላቸው ኪሩቤል የሚጋርዱሽ መቅደሰ ሰሎሞን አንቺ ነሽ፡፡ ጌታ በማኅፀንሽ ያደረብሽ አማናዊቷ መቅደስ አንቺ ነሽ፡፡ ሳይለወጥ ካንቺ ሰው የኾነው አካላዊ ቃል በውስጥ በአፍአ በነፍስ በሥጋ ኃጢአታችንን የሚያስተሠርይልን ኾነ፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
አንቲ ዉእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ እንተ ዉስቴታ መና ኅቡእ፡ ኅብስት ዘወረደ እምሰማያት ወሀቤ ሕይወት ለኩሉ ዓለም፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።
፬. መና ያለብሽ መሶበ ወርቅ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፲፮፡፴፫-፴፬/፡፡ ይኸውም መና የተባለው ከሰማይ የወረደና ፱ ወር ከ፭ ቀን በማኅፀንሽ የተሸከምሽው ነው፡፡ እርሱም “አበዊክሙሰ መና በልዑ በገዳም ወሞቱ - አባቶቻችሁ በምድረ በዳ መና በሉ፤ ሞቱም” እንዳለው ያይደለ፤ ይልቁንም ለሰው ኹሉ ሕይወት የሚያድል ኅብስት ነው /ዮሐ.፮፡፶/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን ላይ፡- “አስተማሰልናኪ ቅድስት ወብፅዕት ስብሕት ወቡርክት ክብርት ወልዕልት በመሶበ ወርቅ ዘውስቴታ ኅብስተ ሕይወት ዘወረደ እምሰማያት ወሃቤ ሕይወት ለኵሉ ዘየአምን ኪያሁ ወይበልዕ እምኔሁ በአሚን ወበልብ ሥሙር ምስለ እለ በየማኑ - የተለየሽና ደግ የኾንሽ የተመሰገንሽና የተባረክሽ የከበርሽና ከፍ ከፍ ያልሽ ሆይ! የሕይወት ኅብስት ባለበት በወርቅ መሶብ መሰልንሽ፡፡ የሕይወት ኅብስትም በቀኙ ካሉ ጻድቃን ጋር እርሱን ለሚያምን በሃይማኖትና ፈቃደኛ በኾነ ልብ ከእርሱ ለሚበላም ኹሉ ሕይወትን የሚሰጥ ከሰማይ የወረደ ነው” ብሏል /ቁ.፯/፡፡ ዳግመኛም አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫ፡- ኦ መሶብ ቤተ ልሔማዊት ዘወለደቶ ለኅብስተ ሰማይ ዘኢያብቌልዎ ዝናማት ወዘኢሐፀንዎ አየራት - ዝናማት ያላበቀሉትን አየራት ያላሳደጉትን የሰማዩን እንጀራ የወለድሽው ቤተ ልሔማዊት መሶብ ሆይ” በማለት መስክሯል /አርጋኖን ዘረቡዕ/፡፡ ከአባቶች አንዱም፡- “ድንግል ሆይ! በእውነቱ አንቺ ከታላላቅ ይልቅ ታላቅ ነሽ፡፡ ማኅደረ ቃለ አብ ሆይ! አንቺን ሊተካከል የሚችል ታላቅ ማን ነው? ድንግል ሆይ! ከየትኛው ፍጥረት ጋር አወዳድርሻለሁ? አንቺ ቀድሞ በወርቅ ካጌጠችው የሕጉ ታቦት ይልቅ በንጽሕና ያጌጥሽ ታላቅ ነሽ! እውነተኛውን መና የተሸከምሽ
የዕለተ ቅዳሜ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ በድምፅ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
፩. ንጽሕት ነሽ፤ ብርህት ነሽ፡፡ በአፍአ በውስጥ ንጽሕት ነሽ፡፡ ሊቁ “ዲያተሳሮን” በተባለው የወንጌል ትርጓሜ መጽሐፉ የእመቤታችንን ንጽሕና ሲናገር፡- “የማርያም ሰውነት የምድር ላይ መቅደስ ነው፡፡ በዚሁ መቅደስም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በኀጢአት፣ በሞትና በርግማን ፈንታ የበረከትን ዘር ሊዘራ መጣ፡፡ የኤልሳቤጥም ሰላምታ ይህንን አረጋገጠ፡፡… አንተና እናትህ ብቻ በማንኛውም ረገድ ንጹሐን ናችሁ፡፡ ጌታ ሆይ! በአንተ ውስጥ ምንም ነቅዕ የለም፤ በእናትህም ውስጥ ምንም ምልክት የለም” ብሏል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Tatian’s Diatesaron, pp 91-92/፡፡
ጌታን በማኽል እጅሽ የያዝሽው ሆይ! ምልዕተ ክብር ሆይ! (ተፈስሒ) ደስ ይበልሽ እያሉ ፍጥረት ኹሉ ከአንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ከአንቺ ጋር አንድ ባሕርይ ቢኾን ባለሟልነትን አግኝተሻልና (ተፈስሒ) ደስ ይበልሽ፡፡ ግርምት ድንግል ሆይ! ክብርሽን ገናንነትሽን ዕፁብ ዕፁብ እያልን እናመሰግናለን (እናደንቃለን)፡፡ ከማኅፀንሽ ፍሬ የባሕርያችን ድኅነት ተገኝቷልና ከመልአኩ ጋር እንደ መልአኩ ምስጋና እናቀርባለን፡፡ የማኅፀንሽ ፍሬ ከአባቱ ጋር አስታርቆናልና እንደ መልአኩ ምስጋና እናቀርብልሻለን፡፡ ሊቁ ቅድም በጠቀስነው መጽሐፉ፡- “… መልአኩ ወደ አንዲት ድንግል ተላከ፡፡ ወደ እርሷ ገብቶም “እነሆ ድንግልናሽ ሳይነዋወጽ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” አላት/ሉቃ.፩፡፴፩//፡፡ ይኸውም በሥጋ ተገልጦ ሊመጣ ስላለው ስለ አካላዊ ቃል ሲናገር ነው፡፡ ሲነግራት “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” አላት እንጂ “ኢየሱስ የተባለው” እንዳላላት ልብ በሉ፡፡ ይኸውም የሰው ልጆች ወልደ እግዚአብሔር በለበሰው ሥጋ የሚድኑበት ስም መኾኑን የሚያመለክት ነው፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ ማለት በዕብራይስጥ “መድኅን” ማለት ነውና፡፡ መልአኩ “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ” ሲላት መድኅን ትዪዋለሽ ማለቱ ነው፡፡ ለምን? ሕዝቡን ኹሉ ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና” ብሏል /ማቴ.፩፡፳፩/፡፡ ከአባቱ ጋር ካስታረቀን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፪. አባ ሕርያቆስ፡- “እግዚአብሔር አብ በሰማይ ኾኖ ምሥራቅንና ምዕራብን ሰሜንና ደቡብን ዳርቻዎችንም ኹሉ በእውነት ተመለከተ፤ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም፡፡ የአንቺን መዓዛ ወደደ፤ የሚወደው ልጁንም ወደ አንቺ ሰደደ” እንዲል /ቅዳ.ማር. ቁ.፳፬/ እንደ ሰርግ ቤት አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ኾነሽ ቢያገኝሽ መንፈስ ቅዱስ አድሮብሻልና፤ ኃይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ለብሷልና አንድም መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ ግብራት ከልክሎሻልና ኃይለ ልዑል ወልድም ከሦስቱ ግብራት ከልሎሻልና ለዘለዓለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃልን ወለድሽልን /ሃይ.አበ.፻፲፡፳፱/፡፡ ሰው ኾኖ ከኃጢአት አዳነን /ማቴ.፩፡፳፩/፡፡ ሰው ኾኖ ከኃጢአታችን ፍዳ ካዳነን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፫. መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በሥጋ ወልደሽልናልና ከዳዊት ሥር የተገኘሽ ባሕርይ አንቺ ነሽ /ሉቃ.፩፡፴፪/፡፡ ቅድመ ዓለም የነበረ፣ ከአብ ባሕርይ ዘእም ባሕርይ አካል ዘእም አካል የተወለደ፣ ተቀዳሚ ተከታይ (ታላቅም ታናሽም) የሌለው አካላዊ ቃል ባሕርዩን በሥጋ ሠወረ፡፡ ከአንቺም አርአያ ገብርን ነሣ /ፊል.፪፡፯/፡፡
ከእናንተ መካከል፡- “አካላዊ ቃል አርአያ ገብርን ነሥቶ (የባሪያን መልክ ይዞ) በሰውም ምሳሌ ኾኖ ራሱን ባዶ አደረገ ሲል ምን ማለት ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ራሱን ባዶ አደረገ ሲል የእኛን ባሕርይ ገንዘብ ባደረገ ጊዜ ባሕርየ መለኮቱ ተለውጧል ማለት አይደለም፡፡ ባሕርየ መለኮቱን ትቶ መጣ ማለትም አይደለም፤ በፈቃዱ ደካማ ባሕርያችንን ገንዘብ አደረገ ማለት ነው እንጂ፡፡ ወልደ እግዚአብሔር ራሱን ባዶ ያደረገው በመቅድመ ወንጌል “ከጥንት ዠምሮ በባሕርያችን እስኪሠለጥን ድረስ ሰይጣን በተንኰል በሥጋ ከይሲ እንደተሠወረ፤ እኛም ከፍዳ መዳናችን ቃለ እግዚአብሔር በባሕርያችን በመሠወሩ ኾነ” ተብሎ እንደተጻፈ የእኛን ባዶነት በጸጋው ለመሙላት ነው፡፡ ሰው የኾነው እኛን አማልክት ዘበጸጋ ያደርገን ዘንድ ነው፡፡” የባሪያውን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ኾኖ ስለ እኛ ብሎ ራሱን ባዶ ካደረገ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፬. አደፍ ጉድፍ ሳይኖርብሽ አምልክን የወለድሽው እመቤታችን ሆይ! በኃጢአት ብርድ የተያዘውን ዓለም ኃጢአቱን ያርቅለት ዘንድ ፀሐየ ጽድቅ ጌታ ከአንቺ ተወልዷልና፤ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው እንደተናገሩም ዘር ምክንያት ሳይኾንሽ፣ መለወጥ ሳያገኝሽ ወልደሸዋልና ከምድር በላይ ያለሽ ኹለተኛ ሰማይ አንቺ ነሽ፡፡ ኢትዮጲያዊው ቄርሎስም፡- “ኦ ሰማይ ዳግሚት ዘወለደቶ ለፀሐየ ጽድቅ ዘውእቱ ብርሃነ ቅዱሳን ዘሰደዶ ለጽልመት - ጨለማን ያሳደደውን (ያስወገደውን) የቅዱሳን ብርሃን የሚኾን አማናዊ ፀሐይን የወለደች ኹለተኛይቱ ሰማይ ሆይ! …” እያለ ያወድሳታል /አርጋኖን ዘረቡዕ/፡፡ ዘር ምክንያት ሳይኾንሽ ከወለድሽው ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
@Ethiopian_Orthodox
፭. ከተለዩ የተለየሽ፣ ከከበሩ የከበርሽ በውስጧም ሕግ የተጻፈበት ኪዳን ያለብሽ የተሠወረ መና ያለበት መሶበ ወርቅ ያለብሽ ደብተራ (ድንኳን) አንቺ ነሽ /ዘጸ.፳፮፡፩-፴/፡፡ ይኸውም መና የተባለው ሰው ኾኖ በማኅፀንሽ ያደረው ወልደ እግዚአብሔር ነው፡፡ መተርጕማኑ ይህን የበለጠ ሲያብራሩት፡- “ድንኳኗ የእመቤታችን ምሳሌ፤ ቅድስት የነፍሷ፤ ቅዱሳን የሥጋዋ፤ ታቦቱ የመንፈስ ቅዱስ፤ ጽላት የልቡናዋ፤ ቃሉ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጸላት ምሥጢር ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ቅዱሳን የሥጋዋና የነፍሷ፤ ቅድስት የልቡናዋ፤ ታቦት የማኅፀኗ፤ ጽላት የትስብእት፤ ቃሉም የመለኮት ምሳሌ ነው” ይላሉ /ውዳሴ ማርያም ንባቡና ትርጓሜው፣ ገጽ ፻፸፬/፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በአርጋኖን ዘሐሙስ ላይ፡- “ተፈሥሒ ኦ ደብተራ ብርሃን ማኅደሩ ለዐቢይ ሊቀ ካህናት - የታላቁ ሊቀ ካህናት ማደርያ የብርሃን ድንኳን ሆይ! ደስ ይበልሽ” በማለት የሊቀ ካህናት የባሕርይ አምላክ የክርስቶስ እናት አማናዊት ድንኳን መኾኗን አስተምሯል፡፡
አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፡፡ የክብር ባለቤት እርሱን በዚህ ዓለም ወለደችው፡፡ ለዘለዓለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃል ሰው ኾኖ ከኃጢአታችን ፍዳ አድኖናልና ሰው ኾኖ ያዳነን የነባቢ በግዕ (የሚናገር በግ የክርስቶስ) እናቱ ደስ ይላታል /ዮሐ.፩፡፳፱/፡፡ ለዘለዓለሙ ጸንቶ የሚኖር አካላዊ ቃል ሰው ኾኖ ከኃጢአታችን ፍዳ ካዳነን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ሃና እና እያቄም በስለት ያገኙሽ:
ድንግል እናታችን በጣም ደስ ይበልሽ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ስ እያለች ብዙ ታምራትን አድርጋለች። ከእነዚህም መካከል ዐይነ ስውር የነበረችው የአርሳባን ልጅ ወደ ሐና መጥታ እውነትም ሐና መፀነሷን ለማረጋገጥ ሆዷን ዳሰሰቻት፡፡ እርሷም ሳታስበው ዐይኗን ስትነካ ዐይኗ በራላት፡፡ እመቤታችንም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት 1 ተወለደች፡፡
ክብርት እናቱን እናት አድርጎ ለሰጠን ለመድኀኔዓለም ክርስቶስ ክብርና ምስጋና ይግባው! በቃልኪዳኗ በምልጃዋ ይማረን፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
🔔
የነሐሴ ፯(7) ግጻዌ
መልእክታት
1. ዕብራውያን ፱ ፥ ፩ - ፲፩ /9:1-11
2. ፩ኛ ጴጥሮስ ፪ ፥ ፮ - ፲፰ /2:6-18
3. የሐዋ/ሥራ ፲ ፥ ፩ - ፴ /10:1-30
ምስባክ
መዝ ፺፫ ፥ ፲፪ /93 ፥ 12
"ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ።
ወዘመሃርኮ ሕገከ። ከመ ይትገኃሥ እመዋዕለ እኵያት።"
"ከክፉዎች ዘመናት ይወገድ ዘንድ፦ አቤቱ አንተ የገሠጽከው፣ ሕግኽንም ያስተማርከው ሰው ብፁዕ ነው።"
ወንጌል
ማቴዎስ ፲፮ ÷ ፲፫ - ፳፬ /16÷13-24
"፲፫
ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን። ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
፲፬
እነርሱም። አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።
፲፭
እርሱም። እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።
፲፮
ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ። አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።
፲፯
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።
፲፰
እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።
፲፱
የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም
የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል።
፳
ያን ጊዜም እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለማንም እንዳይነግሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው።
፳፩
ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።
፳፪
ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ፦ አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም ብሎ ሊገሥጸው ጀመረ።
፳፫
እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስን፦ ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው።
፳፬
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ። "
ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ (ጎሥዓ)።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
፲፬. እናትነትን ከአገልጋይነት ጋር /ሉቃ.፩፡፴፰/ ያለሽ እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ በክንድሽ የያዝሺውን (የታቀፍሽውን) መላእክት ያመሰግኑታልና፡፡ እሳታውያን የኾኑ ሱራፌልም ሳያቋርጡ ክንፋቸወን ዘርግተው፡- “የክብር ባለቤት ይህ ነው” ይላሉ፡፡ “በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት የሰውን ኹሉ ኃጢአት ለማስተሥረይ ሰው የኾነ የክብር ባለቤት ይህ ነው” እያሉ በፍርሐት በረዐድ ኾነው ያመሰግኑታል፡፡ የሰውን ኃጢአት በቸርነቱ ብዛት ከሚያሰተሠርይ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
ይህን ሲጨርስ በያዘችው መስቀለ ብርሃን ባርካው ታርጋለች፡፡ እርሱም ተባርኮ እጅ ነሥቶ ይቀራል፡፡
አነሣሥቶ ላስጀመረን ፤ አስጀምሮም ላስፈጸመን ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
ሙሴ ያየው ሐመልማል ነበልባሉን እንዳላጠፋው ኹሉ ጌታም ምንም እንኳን ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽም ነፍስ ነሥቶ ቢዋሐድም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ አንቺ ነሽ ፡፡ ሙሴ በአምሳለ ሐመልማል ወነበልባል ካየው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
@Ethiopian_Orthodox
፬. አንቲ ውእቱ ገራኅተ ዘኢተዘርዐ ውስቴታ ዘርዕ - ዘር ያልወደቀባት፣ ገበሬ ያልጣረባት ያልጋረባት፣ ለታብቁል (ታብቅል) ባለው ቃል ብቻ ከልምላሜ፣ ከጽጌ (ከአበባ)፣ ከፍሬ የተገኘች ገራኅተ ሠሉስ (የማክሰኞ እርሻ) አንቺ ነሽ፡፡ የወንድ ዘር ሳይወድቅብሽ ፍሬ ሕይወት (የሕይወት መገኛ) ጌታ በግብረ መንፈስ ቅዱስ ካንቺ ተወልዷልና፡፡ አረጋዊው ዮሴፍ በትሩፋተ ደሙ የዋጀሽ /ቅዳ.ማር. ቁ. ፻፳፰/፣ ዕንቁ የተባለው መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም ያገኘብሽ /ሃይ.አበ.፺፮፡፶፭/ የተቈለፈች ሣጥን አንቺ ነሽ፡፡ በዚህ አለ፣ በዚያ የለም የማይሉት ሙሉዕ በኵለሄ የኾነ አካላዊ ቃል በማኅፀንሽ አደረ /መዝ.፻፴፱፡፰/፤ በዚህ ዓለምም ማኅተመ ድንግልናሽ እንደተቈለፈ ወለድሽው /ሕዝ.፵፬፡፩-፪/፡፡ በዕንቁ ከተመሰለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፭. ሥጋዌውን ተልከው ለነቢያት ሲነግሩ የነበሩ፣ አሁን ደግሞ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ አይተውት “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር” ብለው በደስታ ያመሰገኑትን ጌታን የወለድሽው ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡
የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ንጽሕት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡- “ኦ ድንግል አምሳል ወትነቢት ዘነቢያት- ነቢያት ትንቢት የተናገሩልሽ ምሳሌ የመሰሉልሽ…” ይላታል /ቅ.ማር.ቁ.፴፯/፡፡ እግዚአብሔር ከነፍስሽ ነፍስ ከሥጋሽ ሥጋ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ባሕርይ ኾኗልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ የሰው ኹሉ ደስታ የሚኾን የመልአኩን ቃል እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ /ዮሐ.፫፡፬-፱/ እንደ ዘካርያስም ሳትጠራጠሪ /ሉቃ.፩፡፳/ አምነሻልና ደስ ይበልሽ /ሉቃ.፩፡፵፭/፡፡ ሃያውን ዓለም የፈጠረ ጌታ የወለድሽው ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
፮. በእውነት ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም በሚገባ ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፡- “ብልህ ሸክላ ሠሪ የሚሠራውን የለዘበ ጭቃ በአገኘ ጊዜ ከእርሱ መልካም ዕቃ እንዲሠራ፤ እንደዚህም ጌታችን የዚህችን ድንግል ንጹሕ ሥጋዋን ንጽሕት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ሥጋ ሊዋሐደው ፈጠረ” /ሃይ.አበ.፷፮፡፲፬/ እንዲል በቅተሸ ብትገኚ ወላዲተ አምላክ ተብለሻልና ደስ ይበልሽ፡፡
የሔዋን ደኅንነቷ ሆይ! ደስ ይበለሽ፡፡ ሊቁ ያዕቆብ ዘሥሩግም እንዲህ ይላል፡- “የሕዝቦች ሴቶች ልጆች ሆይ! ከአባቶቻችሁ ስሕተት ነጻ ያወጣችሁን ቅረቡት፤ እርሱንም ማመስገን ተማሩ፡፡ ያ ሔዋን የዘጋችውን የማይናገር አፍ አሁን በእመቤታችን ማርያም ተከፍቷልና ለእኅታችሁ ምስጋናን ለመዘመር ቅረቡ፡፡ አሮጊቷ ሴት (ሔዋን) በምላሶቻችሁ ዙርያ የዝምታን ገመድ ቋጠረች፤ የድንግል ልጅ ግን ጮኻችሁ ታመሰግኑ ዘንድ እሥራታችሁን ፈታ…” /A Metrical Homily on Holy Ephrem, pp 47/፡፡ ከአባቶች አንዱም፡- “እንግዲህስ ሴቶች ኹሉ ሐሴት ያድርጉ፤ አሁን ሴቲቱ ዕፀ በለስን ሳይኾን ዕፀ ሕይወትን አስገኝታለችና፡፡ ዳግመኛም ደናግላን እናቶች ኹሉ በፌሽታ ይዝለሉ፤ ያለመታዘዝን ዕፅ በሴት ተፈውሷልና፡፡ እነሆ ክብሩ ከመላእክት ይልቅ የከበረ ኾኗልና ከእንግዲህ ወዲህ የሴትነት ጾታ የሞትና የውድቀት ምልክት መኾኑ ቀርቷል፡፡ ሔዋን ተፈወሰች፤ ድንግል ግን ከበረች፡፡ እነሆ ድንግሊቱ እናትም አገልጋይም፣ ደመናም ድንኳንም፣ ደግሞም የጌታ ታቦት ኾናለችና፡፡ እንግዲያውስ ኑ! አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ፤ የሔዋን መድኃኒቷ አንቺ ብቻ ነሽ፤ ዓለምን በደሙ የሚገዛትን ጌታ ያስገኘሽ አንቺ ብቻ ነሽ እያልን እናወድሳት” ብሏል፡፡
ፍጥረትን ኹሉ በፀሐይ አብስሎ በዝናብም አብቅሎ የሚመግበውን እርሱ ጡትሽን ይዘሽ አጥተሸዋልና ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም ለመንፈሳውያን ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበውን እርሱን ጡትሽን ይዘሽ አጥብተሸዋልና ደስ ይበልሽ፡፡
ተጠምቀው ሕያዋን ኾነው የሚኖሩበት ማየ ገቦ ከአንቺ ከተገኘ ከጌታ የተገኘ ነውና የሕያዋን የጻድቃን እናታቸው ንእድ ክብርት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ መቅድመ ተአምርም፡- “ሕይወትየ ይቤላ አዳም ለብእሲቱ አእሚሮ ከመ ትወጽእ እግዝእትነ ማርያም እምሐቌሁ ወእምከርሠ ብእሲቱ - አዳምም እመቤታችን ማርያም ከሱ አብራክ እንድትከፈል ከሔዋንም ማኅፀን እንድትወለድ ዐውቆ ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር” ይላል /መቅድመ ተአምር ቁ. ፲/፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግም፡- “አዳም ያለ ሩካቤ ድንግል የኾነች ሔዋንን አስገኘ፤ የሕይወት እናት ብሎም ጠራት፡፡ በዚህም ነቢይ ኾነ፤ በኹለተኛ ልደት ከእርሷ የሚያበራ ሕይወት ይገለጣልና፤ በድንግልናዋም የእግዚአብሔር ልጅን ታስገኛለችና፡፡ በአዳም ትንቢት የእውነት ሕይወት የኾነው የጌታችንን መምጣት በምሳሌ ተናገረ፡፡ እናቱም ድንግል ማርያም ኾነች፡፡ ሔዋንን የሕያዋን ኹሉ እናት ብሎ ጠራት፤ ሕይወትን አስገኝታለችና፡፡ እርሱም ኢየሱስ የተባለው ጌታችን ነው” ይላል /Jacob of Serug, On the Virgin, pp 36/፡፡ አንድም “ነዋ ወልድኪ- እነሆ ልጅሽ” /ዮሐ.፲፱፡፳፮/ ባለ ጊዜ በዮሐንስ እኛን ለእርሷ መስጠቱ ነውና የሕያዋን ኹሉ እናታቸው ንዕድ ክብርት ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ለምኚልንና ትልምኝልን ዘንድ ዓይነ ሕሊናችንን ወደ አንቺ እንሰቅላለን፡፡
፯. ድንግል ሆይ! ንዕድ ክብርት ሆይ! ጌታን የወለድሽው ሆይ! እኛን ለማዳን ድንቅ የሚያሰኝ ተዋሕዶ በአንቺ ቢደረግ ንጉሥን ወለድሽልን፤ መንክር በአርያሙ የሚባል ጌታ በማኅፀንሽ አደረ፡፡ ነገር ግን በብዙ ኅብረ መልክእ፣ በብዙ ፆታ መልክእ ሃያ ኹለቱን ሥነ ፍጥረት የፈጠረ፣ ሀብተ መንፈስ ቅዱስን በብዙ ፆታ በብዙ ዕድል እንደየ ሰዉ የአእምሮ ስፋት የሃይማኖት ጽናት የሚያድል፣ ልዕልናውን ገናንነቱን በብዙ መንክር ራዕይ በብዙ ወገን (ለምሳሌ በፀሐይ፣ በቀላይ፣ …) የተመሰለ እርሱን የጌትነቱን ነገር ጠንቅቀን (ፈጽመን) መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል፡፡ ዳግመኛም በብዙ ኅብረ ትንቢት (ለምሳሌ ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ተብሎ) የተነገረ፣ በብዙ ኅብረ አምሳል (ለምሳሌ በአምሳለ ነበልባል ወሐመልማል፣ በአምሳለ ጠል ወፀምር፣ በአምሳለ አንበሳ፣ በአምሳለ እብን ቅውም) የተመሰለ የርሱን የሥጋዌውን ነገር ጠንቅቀን (ፈጽመን) መናገር አይቻለንምና ናርምም (ዝም እንበል)፡፡
ሥጋዌው በአምሳለ ነበልባል ወሐመልማል፣ በአምሳለ ጠል ወፀምር ከተመሰለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ለምስጋና ኹለተኛ፣ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን በሚኾን በዚህ ቀንም እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ምንጻፍ ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኾናም፡- “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ ኤፍሬም” ትለዋለች፡፡ እርሱም ታጥቆ እጅ ነሥቶ ይቆማል፡፡ ክርክር በዕለተ ሰኑይ አልቋልና “ባርክኒ” ብሎ ተባርኮ “አክሊለ ምክሕነ” ብሎ ምስጋናውን ይጀምራል፡፡
@Ethiopian_Orthodox
፩. ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ቢባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻለውም /፩ኛ ሳሙ.፲፮፡፲፫/፡፡ ኢያሱ ምንም የስሙ ትርጓሜ መድኃኒት ቢኾንም የደኅንነታችን መጀመሪያ መኾን አልተቻለውም፡፡ ኤልያስም ምንም ንጹሕ፣ ድንግል ቢኾንም የንጽሕናችን መሠረት መኾን አልተቻለውም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ፣ የደኅንነታችን መጀመሪያ፣ የንጽሕናችን መሠረት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ የመመኪያችን ዘውድ “አክሊለ ሰማዕት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የደኅንነታችን መጀመርያ “ጥንተ ሕይወት” የሚባል ጌታችን ነው፡፡ የንጽሕናችን መጀመርያም ኹሉ በእጁ የተጨበጠ፣ ዓለምንም በመዳፉ የያዘ፤ በጠፈር ላይ የሚቀመጥ ፣ ዳግመኛም መሠረቱን ከታች የሚሸከም “መሠረተ ዓለም” የሚባል ጌታችን ነው /ቅዳ.ማር. ቁ.፶፩/፡፡ እርሱም አካላዊ ቃልን በወለደችልን በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡ እኛን ስለማዳን ሰው ኾነ፤ ሰውም ከኾነ በኋላ ግን ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ እንደ ወለደችው ኹሉ እርሱም አምላክነቱ ሳይለወጥ ሰው ኾነ፡፡
የዕለተ ሰኞ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ በድምፅ፡፡
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
፬. ነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት በሚገልጽ መንፈስ ቅዱስ የአማኑኤልን ምሥጢር አየና አሰምቶ ተናገረ፡፡ አማኑኤል ማለት ሰው የኾነ አምላክ ማለት ነውና “ሕፃን ተወለደልን፤ ወልድ ለሕማም ለሞት ተሰጠልን፡፡ አንድም ወልድ ለኩነተ ሥጋ ተሰጠልን ፤ ሕጻንም ኾኖ ተወለደልን” ብሎም ጮኸ /ኢሳ.፱፡፮/፡፡ አትናቴዎስ ሐዋርያዊም “ስለ ድኅነተ ሰብእ የአዳምን ባሕርይ ገንዘብ አደረገ፤ ካሣ ይከፍልልን ዘንድ ቃል ሥጋ ኾነ” ይላል /Ep. 61:3./፡፡ ወልድ ዘበላዕሉ ሕፃን ዘበታሕቱ ከሚባል ልጅሽ እመቤታችን ጽንዕት በድንግልና ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፭. ባሕርየ ዕጓለ እመሕያው (ሰው) ሆይ! እግዚአብሔር ሰውን ወዶታልና በውሰጥ በአፍአ፣ በነፍስ በሥጋ ደስ ይበልህ፡፡ “ወዶ ምን አደረገለት?” ትለኝ እንደኾነም “በእርሱ የሚያምን ኹሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” ተብሎ እንደተጻፈ /ዮሐ.፫፡፲፮/ ልጁን ለሕማም ለሞት እስከ መስጠት ደርሶ ለቤዛ ሰጥቶለታል ብዬ እመልስልሃለሁ፡፡ ልዑል እግዚአብሔር ረቂቅ ክንዱን ሰደደልን /ኢሳ.፶፩፡፱፣ ፶፫፡፩/፡፡ ነገር ግን ቅ.ዮሐንስ አፈወርቅ የዕብራውያንን መልእክት በተረጐመበተ በ፫ኛው ድርሳኑ “ወልድ ዋሕድ እንደ መላእክት በተላከ ጊዜ ቦታውን የለቀቀ አይደለም፤ በአንድ ፈቃድ ከአባቱ ጋር እያለ ነው እንጂ” ብሎ እንደተናገረው በለቢሠ ሥጋ ነው እንጂ በመለኮት የተላከ አይደለም፡፡ ክንድ ከአካል ሳይለይ የወደቀውን ዕቃ አንሥተው ይመልሱበታል፤ የራቀውንም ያቀርቡበታል፡፡ የአብ ኃይል፣ ክንድ የሚባለው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የወደቀውን አዳምን ያዳነው ከባሕርይ አባቱ፣ ከአባቱ አንድነት ሳይለይ ነው፡፡
እዱ መዝራዕቱ ከሚባለው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡
፮. ሊቁ ምስጋናውን ሲቀጥል “እምቅድመ ዓለም የነበረው፣ ዓለምን አሳልፎ የሚኖረው፣ ለኩነት ሥጋ የመጣው፣ ዳግመኛም ዓለሙን ለማሳለፍ የሚመጣው አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርሰቶስ ካንቺ ሳይለወጥ ፍጹም ሰው ኾነ” ይላል፡፡ ይኸውም በሌላ አንቀጽ “ባሕርዩን ከፍሎ አልተዋሐደም፤ ባሕርዩንም ሕፁፅ በማድረግ ኹለተኛ እንስሳ አልኾነም፡፡ አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመኾን ምሉ ፍጹም ሰው ነው እንጂ፡፡ የአምላክነትን የሰውነትንም ሥራ ይሠራል፤ ይህስ ባይኾን አንዱ ተለይቶ በቀረ ነበር” ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው /ዮሐ.፩፡፩-፲፬፣ ሃይ.አበ.ዘኤፍሬም ፵፯፡፴፪/፡፡
“ተቀዳሙ ተካታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ በሥራው ኹሉ ከነሣው ሥጋ አልተለየም፡፡” ይህም በኹለት መልኩ ይተረጐማል፡-
፩ኛ፡- “አካላዊ ቃል አንድ ግብር፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ አካል ነው እንጂ” ማለት ሲኾን፤
፪ኛ፡- ደግሞ “ተቀዳሙ ተካታይ የሌለው ወልድ ዋሕድ ሰውም ቢኾን ከአብ ከባሕርይ አባቱ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ አልተለየም፡፡ አካላዊ ቃል አንድ ኅብረ መልክዕ፣ አንድ ባሕርይ፣ አንድ አገዛዝ ነው እንጂ” ማለት ነው፡፡
ሰውም ቢኾን ከአብ ከባሕርይ አባቱ፣ ከመንፈስ ቅዱስ ከባሕርይ ሕይወቱ ካልተለየ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኝል፡፡
፯. ዳግማይ አዳም (ክርስቶስ) ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ የቀደመ ሰው አዳምን ከሲዖል ወደ ገነት ከኀሣር ወደ ክብር ይመልሰው ዘንድ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ሊቁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዳግማይ አዳም ማለቱ ከቀዳማዊ አዳም ጋር የሚያመሳስለው ምን ስላለው ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- በቀዳማዊ አዳም ምክንያት የሰው ልጅ በሙሉ በርደተ መቃብር ላይ ርደተ ገሃነም ተፈርዶበት ነበር፤ በዳግማይ አዳም በክርስቶስ ግን የጽድቅ በር ለኹሉም ተከፍቷል፡፡ ከቀዳማዊ አዳም ጋር አብረው ዕፀ በለስን ያልበሉት ስንኳ ሞት ነግሦባቸው ይኖር ነበር፤ በዳግማይ አዳም በክርስቶስ ትሩፋት ግን የሰው ልጅ በሙሉ የድኅነት መንገድ ተሰጥቶታል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ዳግማይ አዳም ሲባል በአዳም የመጣው በደል ክርስቶስ ከሰጠው ጸጋ ጋር ወይም ደግሞ በአዳም ምክንያት የመጣው ሞትና በክርስቶስ የተሰጠው ሕይወት ለማስተካከል ሳይኾን አዳም ለሚሞቱት ኹሉ አባት እንደኾነ ኹሉ ክርስቶስ ደግሞ ትንሣኤ ሕይወት ላላቸው ኹሉ አባታቸው መኾኑን ለመግለጥ ነው /St. John Chrysostom on Romans, Hom.10/፡፡ አንድም በጥንተ ተፈጥሮ ይመስሏልና፡፡
በዕፅ ምክንያት የወደቀ (ከገነት የወጣ፣ ከክብሩ የተዋረደ) አዳም ንስሐ ቢገባም፣ ጩኸቱን ሰምተው ነቢያት ካህናት ቢነሡም እንደ እርሱ ንጽሐ ጠባይዕ አድፎባቸዋልና በግዝረታቸው በመሥዋዕታቸው አዳምን ማዳን አልቻሉም /ኢሳ.፷፬፡፮/፡፡ ነገር ግን “አንሥእ ኃይለከ፤ ፈኑ እዴከ” /ኢሳ.፶፩፡፱/ ያሉትን ልመናቸውን ሰምቶ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወለደ (ሰው ኾነ)፡፡ የአዳምን ባሕርይ ባሕርይ አድርጐ “አዳም ጥንቱንም መሬት ነህ ወደ መሬትነትህ ተመለስ” ብሎ በአዳም የፈረደበትንም የሞት ፍርድ (መከራ) ተቀብሎ ያድነው ዘንድ ካንቺ ባንቺ ባሕርይ ተወልዷልና፣ የነቢያት ሀገረ ትንቢታቸው ቤተ ኀብስት እመቤታችን ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ብዙ ኃጢአት ካለች ዘንድ ጸጋ እግዚአብሔር ትበዛለች /ሮሜ.፭፡፳/፡፡ “በአንድ ሰው (አዳም) ምክንያት የገባች ኃጢአት ሕግ በተሰጣቸውና ባልተሰጣቸው ኹሉ እንዲህ ከነገሠች፣ በዳግማይ አዳም በአካላዊ ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠች ጸጋማ እንዴት አብልጣ አትበዛ?” /St. John Chrysostom, Ibid/፡፡ ዳግማይ አዳም ከሚባል ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኚልን፡፡
ሊቁ (ቅዱስ ኤፍሬም) በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፱ ያለውን ኃይለ ቃል ሲተረጕምም እንዲህ ይላል፡- “ቸር ወዳጅ የኾነው እግዚአብሔር አዳምና ሔዋን ወዲያው እንደተሳሳቱ ፍርዱን አላስተላለፈባቸውም፤ ታገሣቸው እንጂ፡፡ ይኸውም ምኅረት ቸርነቱን ይለምኑት ዘንድ ነው፡፡ እነርሱ ግን አልለመኑትም፡፡ እግዚአብሔርም ምንም ሳይናገራቸው በገነት ውስጥ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱን ቀጠለ፡፡ አዳምና ሔዋን ግን አሁንም አልመለስ አሉ፡፡ በመጨረሻም አምላክ ድምፁን ማሰማት ጀመር፡፡ ‘አዳምን ወዴት ነህ?’ ይላቸው ጀመር፡፡ አስቀድሞ በእግር እንደሚመላለስ ሰው ኾኖ በድምፅ ብቻ መጥራቱ መንገድ ጠራጊው ዮሐንስን እንደሚልክላቸው፣ ቀጥሎ ድምፅ አሰምቶ ወዴት ነህ ብሎ መፈለጉም ወልደ እግዚአብሔር ራሱ በተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ ሊያድናቸው እንደ ፈቀደ ያጠይቃል” ይላል /St. Ephrem the Syrian, Commentary on Genesis/፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ኦሪት ዘልደትን በተረጐመበት በ፲፯ኛው ድርሳኑ ላይ፡- “በዚህ ንግግሩ የእግዚአብሔር ከአእምሮ የሚያልፈውን ፍቅሩን እንመለከታለን፡፡ አንድ አባት ልጁ የማይረባውን ነገር በማድረግ ከክብሩ ቢዋረድም አባቱ እጅግ እንዲወደውና ወደ ቀደመ ክብሩ ይመልሰው ዘንድ እንዲደክም፤ እግዚአብሔርም ከሰው ልጆች ጋር ይህን የመሰለ ፍቅር ሲያሳይ እናስተውላለን፡፡ አንድ ሐኪም ወደ ታማሚው አልጋ ጠጋ ብሎ በሽተኛውን እንዲጠይቀውና አስፈላጊውን ኹሉ እንደሚያደርግለት፣ ሰው ወዳጁ እግዚአብሔርም ወደ አዳም ጠጋ ብሎ ሲያነጋግረው እንመለከታለን” ይላል፡፡
ዳግመኛም በሌላ አንቀጽ “አዳም ሆይ ወዴት ነህ” ማለቱ፣ ለአቅርቦት መኾኑን ሲገልጥ፡- “አዳም ሆይ! ምን ኾንክብኝ? በመልካም ቦታ አስቀምጬህ ነበር፤ አሁን ግን ቦታህ ተለወጠብኝ፡፡ ብርሃን ተጐናጽፈህ ነበር፤ አሁን ግን ጨለማ ውስጥ አይሃለሁ፡፡ ልጄ! ወዴት ነህ? ይህ ኹሉ እንደምን ደረሰብህ? በአንተ ውስጥ ያኖርኩት መልኬ ማን አበላሸብኝ? በዚህ ያህል ፍጥነት የጸጋ ልብስህን ገፎ የጽልመት ልብስ ያከናነበህ ማን ነው? ውዴ! ባለጸጋ አድርጌ ፈጥሬህ አልነበረምን? ታድያ አሁን ድኽነት ውስጥ የከተተህ ማን ነው? ያን የግርማ ልብስህን ሰርቆ ዕራቆትህ ትኾን ዘንድ ያደረገህ ማን ነው? እኮ የጸጋ ልብስህን እንድታጣ ያደረገህ ማን ነው? ይህን የመሰለ ቅጽበታዊ መለወጥ ከወዴት መጣብህ? የከበረ ዕንቁህን እንድትጥል ያደረገህ ምን ቢገጥምህ ነው? አክብሮ በተወደደ ቦታ ካስቀመጠህና ኹል ጊዜ በስስት ዐይን ሲያነጋግርህ ከነበረው አምላክህ ተደብቀህ እንድትሸሸግ ያደረገህ ምንድነው? ማንም የወቀሰህ ሳይኖር፣ እንዲህ እንዲህ አድርገህ በድለሃል ብሎ የመሰከረብህ ሳይኖር ይህን ያህል በፍርሐት መናጥ ከወዴት አገኘህ?” ይላል /Daily Readings of St. John Chrysostom/፡፡
ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ሆይ! ፭ ሺሕ ከ፭፻ ዘመን በግብርናተ ዲያብሎስ የነበረ አዳምን ነፃ ካደረገው ልጅሽ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡ “ቅድስት” ማለቱ ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት ልዩ ሲል ነው፡፡ ይኸውም፡-
· ሌሎች ሴቶች ከነቢብ ከገቢር ቢነጹ ከሐልዮ አይነጹም፡፡ እሷ ግን የዕንቆራው ኤጲስ ቆጶስ ቅዱስ ቴዎዶጦስ “ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ ድንግል በሕሊናሃ ወድንግል በሥጋሃ- ከፈጠራት ጀምሮ በምንም በምን (በሕሊናዋም በሥጋዋም) ከድንግልናዋ አልተለወጠችም” /ሃይ.አበ.፶፫፡፳፪/ እንዲል ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከሐልዮ ኃጢአት ንጽሕት ናትና፡፡
· ጽንዕትም አለ፡፡ ሌሎች ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው፤ ኋላ ተፈትሖ አለባቸው፡፡ እሷ ግን ቅድመ ፀኒስ ጊዜ ፀኒስ፤ ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ ጽንዕት (ወትረ ድንግል) ናትና፡፡
· ክብርትም አለ፡፡ ሌሎችን ሴቶች ብናከብቸው ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትን ወለዱ ብለን ነው፡፡ እሷን ግን ወላዲተ አምላክ ወልዳልናለች ብለን ነውና፡፡
· ልዩም አለ፡፡ እናትነትን ከድንግልና፣ አገልጋይነትን ከእናትነት፣ ወተትን ከድንግልና ጋር አስተባብራ የተገኘች፤ በድንግልናም እያለች ከጡቶቿ ወተት ተገኝተው በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግብ መጋቤ ፍጥረታት አምላክን የወለደች፤ እሳታውያን የሚኾኑ ኪሩቤል ሱራፌልም በፍርሐት በረዐድ ኹነው ዙፋኑን የሚሸከሙት እሳተ መለኮት ጌታን ፱ ወር ከ፭ ቀን በማሕፀኗ የተሸከመች፣ በክንዷ የታቀፈች፣ በዠርባዋ ያዘለች ከእመቤታችን በቀር ሌላ ሴት የለችምና፡፡
ፀምር ዘጌዴዎን
ሊቀመዘምራን ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስ
ፀምር ዘጌዴዎን(፪) እመቤታችን/፪/
የአማኑኤል እናት የልብሱ መሣሪያ
እርሱን የጸነስሺው የሆንሺው ማደሪያ
ዝሐው የአዳም ሥጋ ማጉም ያንቺ ሥጋ
መወርወሪያው ቃል ነው አልፋና ዖሜጋ
አዝ---
ሠሪው መንፈስ ቅዱስ ረቂቅ ጥበብ
ወዮ እጹብ ድንቅ አንቺን ስናስብ
የአዳም ተስፋ አንቺ ነሽ የሴም ቸርነት
የአቤል የውሃት የሔኖክ በረከት
አዝ---
የኖኅ መርከብ አንቺ የሴም ቡራኬው
ዮሴፍንም ቆመሽ የምታጽናኚው
ድልድያቸው የሆንሽ የቀድሞ አባቶች
የሰማይ መሰላል ኃጢአት 'ምታስፈች
አዝ---
የሣሙኤል ዘይት የሽቱ ሙዳይ
አንቺ ነሽ እመቤት እመ አዶናይ
ሰረገላው የሆንሽ የአሚናዳብ
የኤልሳ ጋን አንቺ መሶበ ጥዑም
አዝ---
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የዕለተ ሰንበት ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ በድምፅ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
መሶበ ወርቅ አንቺ ነሽ፡፡ መና የተባለውም መለኮት የተዋሐደው ሥጋው ነው” ብሏል፡፡ ኅብስተ ሕይወት ከሚባል ልጅሽ ጸንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፭. እንቲ ውእቱ ተቅዋም ዘወርቅ እንተ ፆርኪ ማኅቶተ ፀዳል ኩሎ ጊዜ። ዘውእቱ ብርሃኑ ለዓለም። ብርሃን ዘእምብርሃን ዘአልቦ ጥንት። አምላክ ዘእምአምላክ ዘበአማን። ዘተሰብአ እምኔኪ ዘእንበለ ውላጤ። ወበምጽአቱ አብርሃ ላዕሌነ ለእለ ንነብር ዉስተ ጽልመት ወጽላሎቱ ሞት። ወአርአትዐ እገሪነ ዉስተ ፍኖተ ሰላም በምሥጢረ ጥበቡ ቅዱስ። ሰአሊ ለነ ቅድስት።
ብርሃንነት ያለውን ፋና የተሸከምሽ የወርቅ ተቅዋም (መቅረዝ) አንቺ ነሽ /ዘጸ.፳፭፡፴፩-፵/፡፡ ይኸውም ፋና ለሰው ኹሉ ዕውቀትን የሚገልጽ ብርሃን ነው፡፡ ጥንት ከሌለው ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ነው፡፡ ከባሕርይ አምላክ የተገኘ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ ሳይለወጥ ካንቺ ሰው የኾነው ነው፡፡ ሰውም በመኾኑም በድንቁርና በቀቢጸ ተስፋ ለምንኖር ለኛ አበራልን (ዕውቀትን ገልጸልን)፡፡ በጥበቡ ባደረገው ሥጋዌ እግረ ልቡናችንን ወደ ሕገ ወንጌል ጎዳና አቀናልን /ኢሳ.፱፡፩-፪፣ ማቴ.፬፡፲፬-፲፮/፡፡ ታላቁ የዜማ አባት ሊቁ ቅዱስ ያሬድም፡- “አንቲ ውእቱ ተቅዋም ዘወርቅ ዘኢገብራ እደ ኬንያ ዘሰብእ… - የብልሐተኛ እጅ ያልሠራት በውስጧም መብራት የሚያበሩባት የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ፤ ራሱ የአብ ብርሃን ያበራባታል እንጂ፡፡ ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ወደ አንቺ መጥቶ አደረ፡፡ አምላክነቱም በዓለም ኹሉ አበራ፡፡ ጨለማን ከሰዎች ላይ አራቀ፡፡ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ በብርሃኔ እመኑ፤ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ ብሎ በሚያድን ቃሉ አዳነን” ብሏል /ቁ.፰፣ ዮሐ.፲፪፡፴፭፣ ፩ኛ ዮሐ.፩፡፭/፡፡ በጥበቡ ባደረገው ሥጋዌ እግረ ልቡናችንን ወደ ሕገ ወንጌል ጎዳና ከአቀናልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፮. አንቲ ውእቱ ማዕጠንት ዘወርቅ። እንተ ፆርኪ ፍሕመ እሳት። ብሩክ ዘነሥአ እመቅደስ ዘይሠሪ ኃጢአተ ወይደመሰስ ጌጋየ። ዝ ውእቱ ዘእግዚአብሔር ቃል ዘተሰብአ እምነኪ ዘአዕረገ ለአቡሁ ርእሶ ዕጣነ ወመሥዋዕተ ሥሙረ። ሰአሊ ለነ ቅድስት።
ቡሩክ አሮን ከቤተ መቅደስ ይዞሽ የወጣ እሳትነት ያለውን ፍሕም የተሸከምሽ ማዕጠንተ ወርቅ አንቺ ነሽ /ዘጸ.፴፡፩-፰/፡፡ ፍሕም የተባለውም በአፍኣ በውስጥ በሥጋ በነፍስ ኃጢአትን የሚያስተሠርይ ነው፡፡ ይኸውም ከአንቺ ሰው የኾነውና “ወአንከረ አብ እምዝንቱ መሥዋዕት - ከዚህ መሥዋዕት የተነሣ አብ አደነቀ” እንዲል /ሃይ.አበ.፷፰፡፳፫/ ለአባቱ ራሱን ያማረ የተወደደ መሥዋዕት አድረጎ ያቀረበ አካላዊ ቃል ነው /ኤፌ.፭፡፪/፡፡ ራሱን ያማረ የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ካቀረበ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፯. ተፈሥሒ ኦ ማርያም ርግብ ሠናይት። ዘወለድኪ ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ። አንቲ ውእቱ ጽጌ መዓዛ ሠናይ እንተ ሠረፀት እምሥርወ ዕሤይ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።
አካላዊ ቃልን የወልድሽልን መልካም ርግብ ማርያም ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ከእሴይ ሥር የወጣሽ መዓዛ ሠናይ አበባ አንቺ ነሽ፡፡ መዐዛ ሰናይ የተባለውም የቅዱሳን መዐዛ የሚኾን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው /መጽሐፈ ድጓ፣ ገጽ.፻፺፱/፡፡ መዐዛ ሠናይ ከተባለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፰. በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ዘኢንበለ ተክል ወኢሠቀይዋ ማየ። ከማሃ አንቲኒ ኦ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክነ ዘበአማን ዘእንበለ ዘርእ መጽአ ወአድኅነነ። ሰአሊ ለነ ቅድስት።
ሳይተክሏት የበቀለች፣ ውሃ ሳያጠጧትም የለመለመች ያበበች ፲፪ በኵረ ሎሚ ያፈራች የአሮን በትር ነበረች /ዘኁ.፲፯፡፩-፲/፡፡ ከቤተ መቅደስ ፲፪ ዓመት ኑረሽ፣ ዘር ምክንያት ሳይኾነው ሰው ኾኖ ያዳነን እውነተኛ አምላካችንን ክርስቶስን የወለድሽልን አንቺም እንደርሷ ነሽ /ኢሳ.፯፡፲፬/፡፡ አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫም በአርጋኖን ዘሰኑይ ላይ፡- “ዕፀ ከርካዕ እንከ እሰምየኪ እስመ ከርካዕ ሠናየ ይጸጊ፤ ወሠናየ ይፈሪ፤ ወሠናየ ይጼኑ፤ ወከመ በትር ይቡስ ዘቦ ላዕሌሁ ወፅአ ዑፃዌ ክህነት አሥረጸ አዕጹቀ ወአቊጸለ ከርካዕ ምዑዘ፤ ወከማሁ አንቲኒ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ዐሠርተ ወክልኤተ ክራማተ ወፀነስኪዮ ለኢሱስ ዘእንበለ ዘርዐ ብእሲ - እንግዲህ የሎሚ ዕንጨት ብዬ እጠራሻለሁ፡፡ ሎሚ መልካሙን ያብባል፤ መልካሙን ፍሬ ያፈራል፡፡ በጐ በጐ ይሸታልና ዕጣ እንደ ወጣበት ደረቅ በትር ሳይተከል በቤተ መቅደስ ለምልሞ፣ ቅንጣት አውጥቶ፣ አብቦ ተገኘ፡፡ ሽታው ያማረ የተወደደውን ሎሚ አፈራ፡፡ እንዲሁም አንቺ በቤተ መቅደስ ዐሥራ ኹለት ዓመት ተቀምጠሸ ያለ ወንድ ዘር መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀነስሺው” በማለት አብራርቶታል፡፡ ዳግመኛም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ፡- “ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር በቤተ መቅደስ ነበረች፡፡ ለካህናት ዝግጁ ያደረጋት ነበረች፡፡ አንቺም በቅድስናና በንጽሕና ጸንተሸ እንደ እርሷ በቤተ መቅደስ ኖርሽ፡፡ ከቤተ መቅደስም በክብር በታላቅ ደስታ ወጣሽ፡፡ በእውነት የሕይወት ፍሬ የኾነ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከአንቺ ተገኘ፡፡ ቅድስት ሆይ! ከመልአኩ እንደተረዳሽው ከወንድ ያለመገናኘት ልጅን አገኘሽ፡፡ መልአኩ መንፈስ ቅዱስ መጥቶ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጸልልሻል ብሎ ነግሮሽ ነበርና” በማለት አማናዊቷ የአሮን በትር እርሷ መኾኗን አስተምሯል /ቁ.፲፩/፡፡ ሰው ኾኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፱. ለኪ ይደሉ ዘእምኩሎሙ ቅዱሳን ተስአሊ ለነ ኦ ምልእተ ጸጋ አንቲ ተዐብዮ እምሊቃነ ጳጳሳት ወፈድፍደ ትከብሪ እምነቢያት ብኪ ግርማ ራእይ ዘየዐቢ እምግርማ ሱራፌል ወኪሩቤል። አንቲ በአማን ምክሐ ዘመድነ ወሰአሊት ሕይወተ ለነፍሳቲነ ሰአሊ ለነ ኅበ እግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ያፅንዐነ በርትዕት ሃይማኖት ዉስተ አሚነ ዚአሁ። ይጽግወነ ሣህሎ ወምሕረቶ። ይሥረይ ኃጢአተነ በብዝኅ ምሕረቱ፡ ሰአሊ ለነ ቅድስት።
ምልዕተ ክብር ሆይ! ከቅዱሳን ኹሉ ይልቅ ትለምኚልን ዘንድ ላንቺ ይጋባል፡፡ ከሊቃነ ጳጳሳት አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ከመምህራን፣ ከሐዋርያት፣ ከ፸ አርድእትም አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ከሱራፌልና ከኪሩቤል ይልቅ የሚበልጥ የመወደድ የመፈራት ግርማ አለሽ፡፡ ሊቁ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡- “ኦ ሙኃዘ ፍስሐ! ፈድፋደ ብኪ ግርማ ራዕይ ዘየዐቢ እም ኪሩቤል እለ ብዙኃት አዕይንቲሆሙ ወሱራፌል ፮ ክነፊሆሙ - የደስታ (የጌታ) መገኛ የምትኾኚ እምቤታችን ሆይ! ዐይናቸው ብዙ ከሚኾን ከኪሩቤል፣ ክንፋቸው ስድስት ከሚኾን ከሱራፌል ይልቅ በምእመናን ዘንድ የመወደድ፣ በአጋንንት በአይሁድ በመናፍቃን ዘንድ የመፈራት፣ በሥላሴ ዘንድም የባለሟልነት መልክ አለሽ” ይላል /ቁ.፳፪/፡፡ በእውነት የባሕርያችን መመኪያ አንቺ ነሽ፡፡ ለሰውነታችን ሕይወትን የምታማልጅን አንቺ ነሽ፡፡ አንድነቱን ሦስተነቱን በማመን አጽንቶ ሥጋዌውን በማመን ያፀናን ዘንድ፣ “ጸጋሰ ሥርየተ ኃጢአት ይእቲ” እንዲል በቸርነቱ ብዛት ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ አማልጅን፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
🔔
የነሐሴ ፬(4) ግጻዌ
መልእክታት
1. ሮሜ ፲፪(12) ፥ ፲፰(18) እስከ ፍጻሜ
2. ፩(1)ኛ ጴጥ ፭(5) ፥ ፮(6) - ፲፪(12)
3. ግብ ሐዋ ፲፯(17) ፥ ፳፫(23) - ፳፰(28)
ምስባክ
መዝ ፳(20) ፥ ፩(1) - ፪(2)
"እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ። ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ። ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ።"
ወንጌል
ሉቃስ ፲፬(14.) ፥ ፴፩(31) እስከ ፍጻሜ
" ³¹ ወይም ሌላውን ንጉሥ በጦርነት ሊጋጠም የሚሄድ፥ ከሁለት እልፍ ጋር የሚመጣበትን በአንድ እልፍ ሊገናኝ የሚችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ንጉሥ ማን ነው?
³² ባይሆንስ ሌላው ገና ሩቅ ሳለ መልክተኞች ልኮ ዕርቅ ይለምናል።
³³ እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
³⁴ ጨው መልካም ነው፤ ጨው አልጫ ቢሆን ግን በምን ይጣፈጣል?
³⁵ ለምድር ቢሆን ለፍግ መቈለያም ቢሆን አይረባም፤ ወደ ውጭ ይጥሉታል። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።"
ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ አው ዘቄርሎስ።
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
፮. እርሱን ከወለድሽ በኋላ ማኅተመ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ኑረሻልና የክርስቶስ እናቱ ተባልሽ፡፡ ድንቅ በሚያሰኝ ተዋሕዶ አማኑኤልን ወልደሸዋልና ባለመለወጥ አጸናሽ፡፡ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን መምህር ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለማንም ሴት ያልተሰጠ ለድንግል ማርያም ብቻ የተሰጠ ድንግልና ከእናትነት ጋር አስተባብራ ስለ መገኘቷ ሲገልጥ “ወሰቦሂ ወለደቶ ዐቀበ ድንግልና፣ ዘእንበለ ርኩስ ከመ በፀንሳ መንክር ትኩን መራሂተ ለሃይማኖት ዐባይ - ከድንግል ተወለደ፤ በወለደችውም ጊዜ ድንግልናዋ ያለመለወጥ አጸና፡፡ ድንቅ የሚኾን ፅንሷ ለደገኛው ሃይማኖት መሪ ትኾን ዘንድ” በማለት ቅድስት ድንግል ማርያም አምላክን ስትወልድው ማኅተመ ድንግልናዋ እንዳልተለወጠ ጌታም ሰው ሲኾን ባሕርየ መለኮቱ ላለመለወጡ፣ እርሷ ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም) ስትባል እንደምትኖር አካላዊ ቃል ክርስቶስም አምላክ ወሰብእ (ሰው የኾነ አምላክ) ሲባል የሚኖር የመኾኑን የተዋሕዶ ልዩ ምሥጢርን ያወቅንባት የተረዳንባት እርሷ ብቻ መኾኗን አስተምሯል /ሃይ.አበ.፷፮፡፴፪/፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፯. ከምድር እስከ ሰማይ ደርሳ፣ በላይዋ ዙፋን ተነጽፎባት፣ በዚያ ላይ ንጉሥ ተቀምጦባት፣ መላእክት ሲወጡባት ሲወርዱባት ያዕቆብ በፍኖት ሎዛ ያያት የወርቅ መሰላል አንቺ ነሽ /ዘፍ.፳፰፡፲-፳፪/፡፡. ሰው ከመኾኑ አስቀድሞ ሰውም ከኾነ በኋላ የማይመረመር እርሱን በተፈትሖ በማይታወቅ በማኅፀንሽ ችለሸዋልና እኛን ስለማዳን ከአንቺ ሰው ከኾነ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ሰዋስው (አማላጅ) ኾንሽን፡፡ እኛን ስለማዳን ከአንቺ ሰው ከኾነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፰. ጽርሐ ንጽሕት ሆይ! እነሆ ጌታ የፈጠረውን ዓለም ኹሉ በቸርነቱ ብዛት ያድን ዘንድ ከአንቺ ተወለደ፡፡ ቸር ሰው ወዳጅ ነውና በአፍአ በውስጥ እናመስግነው፡፡ ቸር ሰው ወዳጅ ከኾነ ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
፱. አደፍ ጉድፍ የሌለብሽ ድንግል ምልዕተ ክብር ሆይ! ደስ ይበልሽ፡፡ ከእናትሽ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ጠብቆሻልና የዓለም ኹሉ መክበሪያ ንጽሕት ጽዋዕ ነሽ (ከሥላሴ ለምንጠጣው ክብር ምክንያት አንቺ ነሽ)፡፡
እንደ ደብተራ ኦሪቷ ማለትም ሙሴና አሮን በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት አብርተው በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት እንደሚያጠፏት ፋና ያይደለሽ የማትጠፊ ፋና ነሽ /ዘጸ.፳፭፡፴፩-፵/፡፡
እንደ ቀደመችው የኦሪት ቤተ መቅደስ ያይደለሽ የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ /፩ኛ ነገ.፯፡፵፰-፶/፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫም፡- “አንቲ ውእቱ መቅደስ ዘሐነጸ ሰሎሞን ወአስቀጸላ በሜላትሮን ወለበጠ ዳቤራ በውሳጥያተ መቅደስ፤ … - ሰሎሞን ያሠራት እንደ ዝናር እንደ ዐምድ ባለ ወርቅ የጠፈሯን ዙርያ ያስጌጣት፤ በመቅደስ ውስጥ ያለቺውን ቅድስተ ቅዱሳንዋን ዐውደ ምሕረቷን ግድግዳዋን በጥሩ ወርቅ ያስጌጣት፤ ቁመቱ ሃያ ክንድ፤ ክንፉ ዐሥራ አምስት ክንድ የሚኾን ኪሩብን በውስጧ ያሣለባት ቤተ መቅደስ አንቺ ነሽ” በማለት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ሰሎሞን ባሠራት የወርቅ ቤተ መቅደስ መስሎ ኹለንተናዋ በንጽሕና በቅድስና ያጌጠች የተዋበች መኾኗን አስተምሯል /አርጋኖን ዘዐርብ/፡፡ ዳሩ ግን እመቤታችን በንጽሕናዋ በቅድስናዋ በሰሎሞን ቤተ መቅደስ ብትመሰልም ሊቁ (ኤፍሬም) እንዳለው ክብሯ የላቀ ነው፤ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ናትና የማትፈርስ መቅደስ ናት /መዝ.፹፮፡፩-፭/፡፡
የማትለወጥ የቅዱሳን ሃይማኖታቸው (ቅዱሳን የሚያምኑበት ክርስቶስን የወለድሽላቸው አንቺ) ነሽ፡፡ ድንግል ሆይ! በውስጥ በአፍአ በነፍስ በሥጋ ይቅር ይለን ዘንድ፣ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ፅንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
አነሣሥቶ ላስጀመረን አስጀምሮ ላስፈጸመን ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው አሜን!!!
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox
የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
@Ethiopian_Orthodox
በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጠፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናዉን ጀምሯል፡፡