ethiopian_orthodox | Unsorted

Telegram-канал ethiopian_orthodox - የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

30344

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታል፡፡ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Ethiopian_Orthodox_bot Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Orthodox

Subscribe to a channel

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ነሐሴ ፲፮

የብርሃን እናቱ የክብርት እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ በክብር ወደ ሰማይ ያረገበት ዕለት ነው፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ በሥጋ ከመሞቷ በፊት በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መቃብሩ ቦታ ትጸልይ ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስም ለእመቤታችን ከዚህ ዓለም እንደምትለይ ነገራት፡፡ ጌታችንም በደብረ ዘይት ላሉ ደናግላን ነግሯቸዋልና ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በፍጥነት መጡ፡፡ እርሷም መንፈስ ቅዱስ የነገራትን ለእነርሱ ነገረቻቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እመቤታችን እንዲህ ብላ ጸለየች፡- ‹‹ልጄ ወዳጄ፣ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ልመናየን ተቀብለህ ደቀ መዝሙርህን ዮሐንስን በዚህች ሰዓት አምጣው፤ እንዲሁም ሕያዋን የሆኑትን ሐዋርያትን ሁሉንም ነፍሶቻቸውን የለየሃቸውንም ሁሉ ወደ እኔ አምጣቸው፤ አንተ የሕያዋን አምላክ ነህና ለአንተም ምስጋና ይሁን አሜን›› አለች፡፡

በዚያን ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ ቅዱስ ዮሐንስን ደመና ተሸክማ ወደ እመቤታችን አደረሰችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም በፊቷ ሰገደላትና እንዲህ አላት፡- ‹‹ሰላምታ ይገባሻል፣ ጌታችንን ፈጣሪያችንን መድኃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የወለድሽው ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ ከዚህ ዓለም ተለይተሽ በክብር በምስጋና ወደ ዘለዓለም ሕይወት ትሄጃለሽና፡፡ ይህም ስሙ ክቡር ምስጉን የሆነ ጌታችንና ፈጣሪያችን ድንቅ ድንቅ ተአምራቶችን በአንቺ ላይ ከገለጠ በኋላ ነው›› አላት፡፡ እመቤታችንም ይህን በሰማች ጊዜ እጅግ ደስ አላት እግዚአብሔርንምእንዲህ ብላ አመሰገነችው፡- ‹‹ፈጣሪዬ ጌታዬ ላንተ ምስጋና ይሁን፣ የለመንኩህን ሰጥተኸኛልና፡፡ አሁንም ነብሴን ተቀብለው ወደ ሰማይ ወደ አንተ ሊይሳርጓት ከሚመጡ ቅዱሳን መላእክቶችህ ጋር በመምጣትህ የምለምንህን ሁሉ ስጠኝ›› አለችው፡፡ በዚያም ጊዜ ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡- ‹‹እነሆ አሁን መላእክት ይደርሳሉ፡፡ ሐዋርያትም ሁሉ ከምድር ዳርቻ በደመና ተጭነው ለሰማይና ለምድር ጌታ ለኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ወደሆነች ወደ ቅድስት ድንግል ይደርሳሉ፡፡ ወዲያውም ሁሉም ሐዋርያት የሞቱት ከመቃብራቸው ተነሥተው በሕይወት ያሉትም ሁሉም ወደ እመቤታችን ደርሰው ሰገዱላት፡፡ ‹‹አምላካችን ከአንቺ የተወለደ ጸጋን የተመላሽ ሆይ! ደስ ይበልሽ፣ እርሱ ከዚህ ዓለም ለይቶ ቃል ኪዳን እንደሰጠሽ በክብር በምስጋና ከእርሱ ጋር ያሳርግሻልና›› አሏት፡፡

በዚያንም ጊዜ እመቤታችን በዐልጋዋ ላይ ተቀመጠችና ሐዋርያትን እንዲህ አለቻቸው፡- ፈጣሪዬ ፈጣሪያችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እንደሚመጣ እናንተንም እንዳየኋችሁ እንደማየው አሁን ዐወቅሁ፡፡ ከዚህ ከሥጋዬ ወጥቼ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እሄዳለሁ፡፡ ነገር ግን ትነግሩኝ ዘንድ እሻለሁ፣ እኔ ከዚህ ዓለም እንደምለይ ከወዴት ዐወቃችሁ?›› ብላ የጠቀቻቸው፡፡ በመጀመሪያ ቅዱስ ጴጥሮስ ከዚያም ሁሉም ሐዋርያት ‹‹ወደ አንቺ እንመጣ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ አዘዘን፣ በደመና ላይም በተጫን ጊዜ እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥነን ደረስን›› አሏት፡፡

እመቤታችንም ይህን ነገር ከሐዋርያት በሰማች ጊዜ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ አለች፡- ‹‹ጌታዬና ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈጽሜ አመሰግናለሁ፣ የእኔን የአገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ ኃይልን አድርገህልኛልና ከእንግዲህ ወዲያ ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሰግኑኛል›› አለች፡፡ ጸሎቷንም ስትጨርስ ሐዋርያትን ‹‹ዕጣን አምጥታችሁ በማጠን የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ስሙን ጥሩት›› አለቻቸው፡፡ እነሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ፡፡ በዚያም ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን እልፍ አእላፍ ቅዱሳን መላእክቱ አጅበው እያመሰገኑት መጣና እመቤታችንን አረጋጋት፡፡ ያዘጋጀላትንም ተድላ ደስታ ነገራት፡፡ በዚያም ጊዜ ድንቆቸ የሆኑ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ዓይነ ሥውራን ማየት ቻሉ፣ ደንቆሮች መስማት ቻሉ፣ ዲዳዎች ተናገሩ፣ ለምጻሞች ነጹ፣ ሐንካሶች መሄድ ቻሉ፣ ደዌ ያለበትም ሁሉ ዳነ፡፡ የብርሃን እናቱ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ወደ አለችበት ቤት በቀረቡ ጊዜ ከደዌአቸው ሁሉ ይፈወሳሉና፡፡

ከዚህም በኋላ እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ‹‹በአየር ውስጥ ተበትነው ከሚኖሩ ከሚያስነግጡ ግሩማን መላእክት የተነሣ ከእሳት ባሕርም የተነሣ እፈራለሁ›› ባለችው ጊዜ እርሱም ‹‹እናቴ ሆይ ከእነርሱ ለማንም በአንቺ ላይ ሥልጣን የለውም›› አላት፡፡ ከሥጋዋም የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ሐዋርያትንና ደናግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ለመኗት፡፡ እመቤታችንም እጇን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ጌታችን ቅድስት ንጽሕት ነፍሷን ከሥጋዋ ለይቶ በመለኮታዊ እጆቹ ይዞ በብርሃን ልብስ አጎናጽፎ ወደ ከፍተኛ መኖሪያ ከእርሱ ጋር አሳረጋት። ሥጋዋን ግን እንደሚገባ ገንዘው፤ ወደ ጌቴ ሰማኒ ተሸክመው እንዲወስዷ ሐዋርያትን አዘዛቸው፡፡ ነፍሷ ከሥጋዋ ከመውጣቷ በፊት በሰው አንደበት ይህ ነው ተብሎ የማይነገር ብርሃን እያየች ነበር፡፡ የክብር ባለቤት ጌታችንም ‹‹እንግዲህ ሥጋሽን ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት አፈልሳለሁ፡፡ ዳግመኛም ሥጋሽን ከነፍሽ ጋር አዋሕጄ አስነሥቼ መላእክት በፊትሽ ሆነው በሚያመሰግኑበት አምሳያ በሌለው ተድላ ደስታ ባለበት መኖሪያ አኖርሻለሁ›› አላት፡፡

እመቤታችንም እንዲህ አለች፡- ‹‹አቤቱ በረቀቀ ጥበብህ ይህን ሁሉ የሠራህ አመሰግንሃለሁ፤ ሁለተኛም ልመናየን ትሰማ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ በስሜ ወደ አንተ የሚለምነውን ሁሉ፤ ልመናውን ተቀበለው በመከራም ውስጥ ሁኖ ስሜን ጠርቶ ወደ አንተ የሚለምነውን ከመከራም ሁሉ አድነው፤ በሰማይም በምድርም በሥራው ላይ ሁሉ አንተ ከሃሊ ነህና መታሰቢያየን በውስጧ የሚያደርጉባትን ቦታ ሁሉ ባርክ፣ በእኔ ስም የሚያቀርቡትን የሁሉንም መሥዋዕታቸውን ተቀበል›› አለችው፡፡ ጌታችንም እንዲህ ብሎ መለሰላት፡- ‹‹የለመንሽኝን ሁሉ አደርግልሻለሁ፤ ደስ ይበልሽ፣ ከእኔ ከአባቴ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ጸጋ ክብር ባለሟልነት ተሰጥቶሻልና ስምሽንም ጠርቶ የሚለምን ሁሉ በዚህ ዓለምም በወዲያኛው ዓለምም ከቶ አይጠፋም›› አላት፡፡ እመቤታችንም በታላቅ ክብር ካረፈች

ኋላ ጌታችን እንዳዘዘ ወደ ጌቴ ሰማኒ ሊወስዷት ሐዋርይት ገንዘው ተሸከሟት፡፡ አይሁድም በሰሙ ጊዜ ሥጋዋን ሊይቃጥሉ ወጡ፡፡ ከእርሳቸውም አንዱ ከምድር ይጥላት ዘንድ የእመቤታችንን አልጋዋን ያዘ፡፡ ያን ጊዜም ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ መልአክ እጆቹን በእሳት ሰይፍ ቀጣውና እጆቹ በአልጋው ላይ ጠንጠለጠሉ፡፡ ያን ጊዜ በጌታችን አምኖ ወደ እመቤታችን እያለቀሰ እንዲህ ብሎ ለመነ፡- ‹‹የእውነተኛ አምላክ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እናት ሆይ! አንቺ በእውነት ድንግል ይሆንሽ በእኔ ላይ ይቅርታ ታደርጊ ዘንድ አለምንሻለሁ፡፡›› በሐዋርይትም ልመና እጆቹ ተመልሰው እንደቀድሞው ደኅነኞች ሆኑ፡፡ ሐዋርያትም እመቤታችንን በቀብሯት ጊዜ ከዚያ ሶስት ቀን ኖሩ፣ ዕረፍቷም የሆነው እሑድ ቀን ጥር ወር በ21 ቀን ነበረ፡፡ ጌታችንም ብርሃናውያን መላእክትን ላከ፣ እነርሱም ሥጋዋን ከመቃብር ወስደው በገነት ውስጥ በዕፀ ሕይወት ሥር አኖሯት፡፡ በጌታችን ትእዛዝ መልአኩ የእመቤታችንን ቅዱስ ሥጋ ከወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር በክብር አኑሮታል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት ዮሐንስ ከተመለሰ በኋላ ‹‹እመቤታችን እንደምን አለች?›› አሉት፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም «ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች» አላቸው፡፡ እነርሱም ዮሐንስ ዐይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ፡፡ @Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🔔የነሐሴ ፲፭ ግጻዌ

መልእክታት
1. ፩ኛ ቆሮንጦስ ፲፪ : ፲፰ - ፍጻሜ
2. ይሁዳ ፩ : ፲፯ - ፍጻሜ
3. ግብረ ሐዋርያት ፩ : ፲፪ - ፲፭

ምስባክ
መዝ ፲፰ ፥ ፫ – ፬ /18:3-4
"አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ ።"
" ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም። ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።"

ወንጌል
ማቴ ፲ ፥ ፩-፲፭/10 ፥ 1-15
"፩
አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው።

የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥

ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥

ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።

እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ፦ በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤

ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ።

ሄዳችሁም፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ።

ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።

ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፥
.
.
.


፲፭
እውነት እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል።"

ቅዳሴ
ዘሐዋርያት(ዘበደኀሪ)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🔔የነሐሴ ፲፬ ግጻዌ

+ መልእክታት ዘቅዳሴ:-
1. ወደ ዕብራውያን ፲፩ : ፰ - ፲፮
2. ፪ኛ ዮሐንስ ፩ : ፩ - ፯
3. ግብረ ሐዋርያት ፩ : ፲፫ - ፲፭

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
"አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር
እምአይቴ ይምጻእ ረድኤትየ።
ረድኤትየሰ እምኀበ እግዚአብሔር።"
ትርጉም፦
" ዓይኖቼ ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።"

(መዝ ፻፳ : ፩ - ፪ /120:1-2)

+ ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ፩ : ፴፱ - ፵፮ /1:39-46
"፴፱
ማርያምም በዚያ ወራት ተነሥታ ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ከተማ ፈጥና ወጣች፥

ወደ ዘካርያስም ቤት ገብታ ኤልሳቤጥን ተሳለመቻት።
፵፩
ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥
፵፪
በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች፦ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።
፵፫
የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?
፵፬
እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።
፵፭
ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።"

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ(ጎሥዓ)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቡሄ በሉ
ቡሄ በሉ /2/ ሆ ልጆች ሁሉ ሆ
የኛማ ጌታ ሆ የዓለም ፈጣሪ ሆ
የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ
በደብረ ታባር ሆ የተገለፀው ሆ
ፊቱ እንደ ፀሀይ ሆ በርቶ የታየው ሆ
ልብሱ እንደብርሀን ሆ ያንፀባረቀው ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና /2/
የቡሔው ብርሀን ለኛ በራልን/2/

ያዕቆብ ዮሀንስ ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ
አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ
አባትም አለ ሆ 'ልጄን ስሙት' ሆ
ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ

ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ
ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ
ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ

በተዋህዶ ሆ ወልደ የከበረው ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወ/ማርያም ነው
ቡሄ በሉ ሆ ቡሄ በሉ ሆ
የአዳም ልጆች ሆ ብርሀንን ሆ ተቀበሉ ሆ

አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ካጐቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ

የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣ ሆ
ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ
ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ስለመጣ ሆ
የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይውጣ ሆ

ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ አላችሁ ሆ
ባህላችሁን ሆ ያዙ አጥብቃችሁ ሆ
ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ
ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ

አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ
የቡሄን ትርጉም ሆ ያስተማሩን ሆ
እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ
ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ

ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ
ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ
በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ
ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ

ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ
በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ
በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችን ይድረስ ሆ

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ምስባክ ዘቅዳሴ አመ ፲ወ፫ ለነሐሴ(በዓለ ደብረ ታቦር)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ነሐሴ ፲፫
ደብረ ታቦር

ደብረ ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው:: ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ: ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር:: በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው: አንድም ገና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም::

+ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም: በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር:: በርግጥ ያንን ነደ እሳት: ሰማያት የማይቸሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም::

+ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል:: እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል:: ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ:-
1.ትንቢቱ ሊፈጸም (መዝ. 88:12)
2.ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና)
3.ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ1,500 ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም
4.አንድነቱን: ሦስትነቱን ለመግለጽ
5.ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
6.ተራራውን ለመቀደስ
7.የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው::

+ነሐሴ 7 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልዾስ ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቁዋቸው ነበር:: እነርሱም የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ: አንዳንዶቹም ሙሴ: ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት::

+ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ደንግጠው ዝም አሉ:: የሃይማኖት አባት: ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ዼጥሮስ ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው - የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለው:: በዚያን ጊዜ ቃለ-ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው:: (ማቴ. 16:13)

+መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከ6ኛው ቀን በሁዋላ ጌታችን 12ቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው:: ዘጠኙን በእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ 3ቱን (ዼጥሮስን: ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ:: እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ::

+በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ 7 እጅ አበራ: ከመብረቅም 7 እጅ አበረቀ:: "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል:: ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ::

+በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ:: አንዳንዶቹ ጌታን 'ነቢይ' (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ:- "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል: እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት: አመሰገኑት::

+ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም:: መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ: ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል::

+በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ: ንግበር ሠለስተ ማሕደረ: አሐደ ለከ: ወአሐደ ለሙሴ: ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው:: በዚህም 3 ዳስ እንሥራ:: አንዱን ላንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል::

+ቅዱስ ዼጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ" በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል:: ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው::

+እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው:: አብ ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት" ሲል ተናገረ::

+ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ ነበር:: (ማቴ. ማር. ሉቃ. )

+በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ 3ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት 12ቱ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል::

+ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል:: ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል:: (ኢሳ.)
ሊቁም የደብረ ታቦርን ምሥጢር ሲያደንቅ እንዲህ ብሏል:-

"ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ:
ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ:
አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ:
መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ:
ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::"

ማቴ. ፲፯፡፩-፭ በቤተ ክርስቲያን ደብረታቦር ከቤተክርስቲያን ውጭ አከባበሩ ቡሄ እየተባለ የሚከበረው በዓል በሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ ፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ በዚህ መሰረት የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት 'ቡሄ' የሚለውን ስያሜ አገኘ። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብረሃን የታየበት ድምጸ መለኮት የተሰማበት ስለሆነ፤ ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓልም ይባላል፡፡

በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። መነሻ የሆናቸው ትውፊት ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል ፡፡ያንን ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡
የንጋት ወጋገን ሲፈናጠቅ ልጆች በከባድ ድምጽና በጅራፍ ጩኸት የሚታጀብ፣ በገደላገደል ስር እንዲያስተጋባ ተደርጎ ብዛት ባላቸው ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ የሚዘመር ነው ቡሄ። የጅራፉ ጩኸትም እግዚአብሔር አብ “የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት” ሲል ሐዋርያት ራሳቸውን ስተው የወደቁበትን የመለኮት ድምፅ ለማስታወስ ነው፡፡

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ምስባክ ዘቅዳሴ አመ ፲ወ፪ ለነሐሴ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🔔የነሐሴ ፲፪ ግጻዌ

❖ ምስባክ ዘነግህ
መዝ ፻፴፯ ፥ ፩-፪/137፥1-2
"በቅድመ መላእክቲከ እዜምር ለከ፣
ወእሰግድ ውስተ ጽርሐ መቅደስከ።
ወእገኒ ለስምከ፤"
ትርጉም፦
"በመላእክት ፊት እዘምርልሃለሁ።
ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤
ስምህንም አመሰግናለሁ።"

❖ ወንጌል ዘነግህ
ማቴዎስ ፳፭ : ፴፩-ፍጻሜ /25:31-ፍጻሜ

መልእክታት
➊. ፩ኛ ቆሮንቶስ ፱ : ፲፯ - ፍጻሜ /9:17-ፍጻሜ
➋. ይሁዳ ፩ : ፰ - ፲፬ /1:8-14
➌. የሐዋ/ሥራ ፳፬ : ፩ - ፳፪ /24:1-22

ምስባክ ዘቅዳሴ
መዝ ፸፩ : ፩ /71:1
"እግዚኦ ኲነኔከ ሀቦ ለንጉሥ።
ጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ።
ከመ ይኰንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ።"

"አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ፥
ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥
ሕዝብህን በእውነት ይዳኝ ዘንድ።"

ወንጌል ዘቅዳሴ
የማቴዎስ ወንጌል ፳፪ : ፩ - ፲፭ /22:1-15
"፩
ኢየሱስም መለሰ ደግሞም በምሳሌ ነገራቸው እንዲህም አለ።

መንግሥተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች።

የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ ሊመጡም አልወደዱም።

ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ። የታደሙትን። እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፥ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፥ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ በሉአቸው አለ።

እነርሱ ግን ቸል ብለው አንዱ ወደ እርሻው፥ ሌላውም ወደ ንግዱ ሄደ፤

የቀሩትም ባሮቹን ይዘው አንገላቱአቸው ገደሉአቸውም።

ንጉሡም ተቈጣ፥ ጭፍሮቹንም ልኮ እነዚያን ገዳዮች አጠፋ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ።

በዚያን ጊዜ ባሮቹን። ሰርጉስ ተዘጋጅቶአል፥ ነገር ግን የታደሙት የማይገባቸው ሆኑ፤
.
.
፲፬
የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።"

ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ ወይም ዘዮሐንስ አፈወርቅ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

"ልጄ እስከ ሽሮሜዳ አድሺኝ እባክሽ እግሬ እምቢ ብሎኝ..."

ምንም ሳላወራ በሩን ከፍቼላቸው ተጠጋው። ሲስ ሁኔታውን ከማየት በቀር መልስ አልሰጠም።እማማ መላእክቱን እየጠሩ ይመርቃሉ...

"ሚካኤል አለሁ ይበልሽ..እመቤቴ በሰላም ትገላግልሽ...የማህፀንሽን ፍሬ እዪ....ወልደሽ ሳሚ....የጭንቅ አማላጇ ትቅረብሽ....ከለላ ትሁንሽ....ምጥሽን ታቅለው.."

"እማማ ይተዉኝ!!እኔ ለልጅ አልታደልኩም!!ልጄን በማህፀን ገድዬ የቀበርኩ ነኝ!!እማማ ፈጣሪዬ አሳይቶ ነሳኝ" ሳላውቀው የሚታገለኝ እንባ ከአይኔ አምልጦ ጉንጬ ላይ ተንደረደረ።

"ውይ ውይ እኔን አፈር ይብላኝ።ይቅር በይኝ ልጄ እኔማ መመረቄ ነው የሆድሽን መች አውቄ? በይ አይዞሽ አታልቅሺ እንዲህ መርቄሽማ ድንግል አታሳፍረኝም ከሆስቢታሉ በፊት አንድዜ ደጇን እርገጩ እሷ መላውን ታውቃለች በሉ እንመለስ..."

"እማማ እግዜር ይስጦት ግን አይሆንም እኛ በጌታ ነን ሃይማኖታችን አይፈቅድም በምናቀው ተማፅነናል በዛላይ ሰዓቱ ረፍዷል  ትንሽ ከቆየን ሚስቴን አጣታለሁ!!"

"አይ እንግዲ በጌታ የሆነ በናቱ ቢማፀነው ምን ይከፋል??እሺ በሉኝ.. በተአምሯ  ትደሰታላችሁ  በሱባኤዋ አታሳፍራችሁም ስላችሁ??"

"እማማ ይውረዱ ሽሮሜዳ ደርሰዋል!!" ሲስ ብስጭት ያለ ይመስላል እንዲህ ሰው አውርቶ አያውቅም። ጴንጤ ብሆን እንኳ እማማ ያመጡትን ሀሳብ ተቀብዬ ለመጨረሻ ጊዜ ልሄድ ፈልጌ ነበር ባምጥ ማርያም ማርያም ይባል የለ?ጨንቆኝ ብሄድ ምን ችግር አለው??በዚህ ሰዓት ማንም ምንም ቢል ልጄን ለማዳን ምንም እሆናለሁ...

ሆስፒታል ደረስን።ነብሴን መርጬ ልጄን የምጥልበት ሰርጀሪ ክፍል ለመግባት እግሬን እየጎተትኩ ሳለሁ ግን እግርና እግሬ መሀል ቀጭን ፈሳሽ እየተንሸራተተ ተሰማኝ። ትንሽ ቆይቶ ሆዴን ሲቆርጠኝ በትንሹ አቃሰትኩኝ። ጩኸቴ ጨመረ። ከዛ በኋላ ምን እንደተፈጠረ ሳላውቅ ከሰርጀሪ ክፍል በአልጋ እየጎተቱኝ ማዋለጃ ክፍል ሲያስገቡኝ፤ ብዙ ሴቶች ከበው እየጮኹ "ግፊ ግፊ ግፊ" እያሉ ሲያበረቱኝ፤ሳቃስት፤ሳለቅስ፤ስወራጭ ማርያም ማርያም ሲባል በደቂቃወች ውስጥ የህፃን ድምፅ ስሰማ ብቻ ትዝ ይለኛል። በእውኔ ይሁን በሕልሜ ታሪክ ተቀይሮ ልጄን ሲያሳቅፉኝ ባለማመን እያየኋቸው የሞት ሞቴን አወራሁ....

"እንዴት?? እንዴት ሆነ ዶክተር?? አትወልጂም ተብዬ??" ዶክተሩ 'ሚመልሰው ጠፍቶት አይን አይኔን ሲያየኝ በሩ ተከፍቶ ሲስ እየሮጠ ገባ ማን እንደሆነ ባላቅም በእልልታ ታጅቦ ሲቀርበኝ እኛን የመረቁኝ አሮጊት ከስሩ ብቅ ሲሉ አየኋቸው። የእናትነት ፈገግታቸው እያበራ...

"አይ አንቺ...አታሳፍሪኝምኮ!!ቀየርሽው አደል!!እሺ አልሺኝ አደል??ሰማሺኝ አደል??አማላጄዋ.. እናቴዋ.. የኔ ገራገር.. እመ ልቤ.. እሰይ እሰይ እሰይ..." እማሆይ ግንባሬን እየሳሙኝ በመሀል እልልታቸውን አቀለጡት።

"እማማ እንዴት መጡ ግን??"

"ተአምሯን ላይ ነዋ!!እንደምታደርገው አውቃለሁኮ...አየሽ ዳቤዋን የቀመሰ.. ይጣፍጥ የለ??" እኔና ሲስን አፈራርቀው እያዩን።

"የምን ዳቤ እማማ? መች ያቀመሱንን??"

"አይ ልጄ ተው አትዋሽ ከኔ ብትሰውር ከሷ አይሰወርም። ልጄ ስታለቅስብኝ አንተም እንቢ ስትለኝ ከደብሯ  ቆርሼ የያዝኩትን ዳቤ...."

"አዎ እማ በልቼዋለሁ!! ሲስ ትክክል ናቸው...'አንቺ ካለሽ እቺን አድርጊልኝ፤ የተሳሉሽ የደረሰላቸው እውነት ከሆነ አሁን ለኔም ድረሺ፤አዋልጂኝ ቅረቢኝ' ብዬ እየተሣልኩ እማማ ጥለው የወጡትን ዳቤ በልቻለሁ። ሲስ እሷ ናት የሰማቺኝ ኪዳነምህረት ናት ያዋለደቺኝ" ሳቅና እንባ የቀላቀለ ፊቴን እያየ ሲስ መጥቶ እቅፍ አደረገኝ እማማ እልልታቸውን እያቀለጡት።

"አየሽ እንዲያው እኛ ተለያየንባት እንጂ የጴንጤዋ ማርያም የኦርቶዶክሷ ማርያም ብሎ ነገርኮ የለም 'ማርያም እናቴ' ብሎ ለጠራት የሁሉ ናት። ለተማፀኗት ለተማመኗት አደለም ላልጠሯት ለማያውቋትም አማላጅነቷን ለማያምንም ትደርሳለች። ለውሻም ትራራለች። አንቺማ ጣድቋን ቆርሰሻል በላኤሰብኮ በስሟ ጥርኝ ውኃ ሰጥቶ ነው የዳነባት። ቆይንጂ ደሞ...እናንተ ቅድም እናት ብሆን አደል አዝናችሁ በመኪና የሸኛችሁኝ??እናንተ ያዘናችሁልኝ ልጇ አምላኳ የሆነ ድንግል ብትጠይቀው እንዴት እምቢ ይላል? ብትማልደው እንዴት ይጨክናል?? ኃጢአታችን ከአምላክ ቢከልለን በማርያም በኩል ግን ይታረቀናል። 'ስለ ሔዋን የገነት በር ተዘጋ ዳግመኛም ስለ ድንግል ማርያም ተከፈተልን' የተባለውኮ ለዚህ ነው። የተደመደመ ተስፋ በአማላጅነቷ እንደሚለመልም ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሲነግረን እኮ ነው። እየውልሽ እኛ ጎራ ፈጥረን እንጂ እሷኮ ለነውራችን መጋረጃ፤ ለእንባችን መሀረብ፤ ለመንገዳችን ስንቅ፤ለቤታችን ውብት፤ለጭንቃችን ደራሽ ናት።እንግዲህ በሉ እኔ ወደቤቴ ልሂድ..."

"እማማ መች ነው ተመልሰው ሚመጡት??" (በስስት እያየኋቸው) "እንግዲህማ እናት አትለፋም ልጅ ነው እንጂ ሚመጣው። እዚያው ኪዳነምህረት ደጇ ላይ ብትመጪ እኔንም ወለላዬንም ታገኚናለሽ" ከንፈራቸውን ሸብበው በስሱ ጥርሳቸውን እያሳዩኝ።

"እማ ማርያምን መጣለሁ!!አልኳቸው።" ከልቤ ነው ልጄንም የማርያም ብያታለሁ።

©ቻቻ
@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ክፍል ፬

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ይወዳል መብረርን ኅሊናዬ
[ቅዳሴ ማርያም]

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም  ትርጓሜ
ክፍል ፫

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም  ትርጓሜ በድምፅ!
ክፍል ፪

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ በድምፅ!
ክፍል ፩

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ክፍል ፰

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ክፍል ፯

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ዓመት ዓውዳመት ድገምና ዓመት ድገምና
  በጋሽዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
  ያውርድ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
  ወርቅ ይፍሰስበት ድገምና ዓመት ድገምና
  በእማምዬ ቤት ድገምና ዓመት ድገምና
  ይግባ በረከት ድገምና ዓመት ድገምና
  ማርና ወተት ድገምና ዓመት ድገምና
  ይትረፍረፍ በእውነት ድገምና ዓመት ድገምና

እንዲሁ እንዳላችሁ በፍቅር አይለያችሁ በፍቅር
ላመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሳችሁ በፍቅር
ክርስቶስ በቀኙ በፍቅር ያቁማችሁ በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርጋችሁ በፍቅር
እንዲሁ እንዳለን በፍቅር አይለየን በፍቅር
ለዓመቱ በሰላም በፍቅር ያድርሰን በፍቅር
አማኑኤል በቀኙ በፍቅር ያቁመን በፍቅር
የመንግስቱ ወራሽ በፍቅር ያድርገን በፍቅር

የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት /2/ ይግባ በረከት/2/
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት /3/

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ክፍል ፮

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የነሐሴ ፲፫ ግጻዌ

+ መልእክታት ዘቅዳሴ:-
1. ወደ ዕብራውያን ፲፩ : ፳፫ - ፴
2. ፪ኛ ጴጥሮስ ፩ : ፲፭ -ፍጻሜ
3. ግብረ ሐዋርያት ፯ : ፵፬ - ፶፩

✞ ምስባክ ዘቅዳሴ
ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ
ወይሴብሑ ለስምከ።
መዝራእትከ ምስለ ኃይል።
ትርጉም፦
ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል።
ስምህንም ያመሰግናሉ።
ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፤
(መዝ ፹፰ : ፲፪ - ፲፫/88:12-13)

+ ወንጌል ዘቅዳሴ
የሉቃስ ወንጌል ፱ : ፳፰ - ፴፰ /9:28-38
፳፰
ከዚህም ቃል በኋላ ስምንት ቀን ያህል ቈይቶ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ያዕቆብንም ይዞ ሊጸልይ ወደ ተራራ ወጣ።
፳፱
ሲጸልይም የፊቱ መልክ ተለወጠ፤ ልብሱም ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ።

እነሆም፥ ሁለት ሰዎች እነርሱም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር፤
፴፩
በክብርም ታይተው በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ስለ መውጣቱ ይናገሩ ነበር።
፴፪
ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።
፴፫
ከእርሱም ሲለዩ ጴጥሮስ ኢየሱስን። አቤቱ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውና አንድ ለአንተ አንድም ለሙሴ አንድም ለኤልያስ ሦስት ዳሶች እንሥራ አለው፤ የሚለውንም አያውቅም ነበር።
፴፬
ይህንም ሲናገር ደመና መጣና ጋረዳቸው፤ ወደ ደመናውም ሲገቡ ሳሉ ፈሩ።
፴፭
ከደመናውም። የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፥ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።
፴፮
ድምፁም ከመጣ በኋላ ኢየሱስ ብቻውን ሆኖ ተገኘ። እነርሱም ዝም አሉ። ካዩትም ነገር በዚያ ወራት ምንም ለማንም አላወሩም።
፴፯
በነገውም ከተራራ ሲወርዱ ብዙ ሕዝብ ተገናኙት።

✞ ቅዳሴ ~ ዘእግዝእትነ / ዘዲዮስቆሮስ {በዕዝል ዜማ}

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ደብረታቦር ወይም ቡሄ በአብነት ተማሪዎች “ስለ ደብረ ታቦር" እያሉ እህል፣ ለምነው ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን በመጋበዝ በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህ ትውፊት መምህረ ሐዋርያት የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ይዞ ሄዶ የተገለጠ ምስጢር ስለሆነ ከመምህራቸው ጋር በመሆን በዓለ ደብረ ታቦርን /ቡሄን ያከብራሉ፡፡ ስሙን ይጠራሉ፡፡

ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዐይነ ልቡናችንን ያብራልን:: ከበዓሉ በረከትም ያሳትፈን::

©ዝክረ ቅዱሳን
©ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ
ክፍል ፭

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ምስባክ ዘነግህ አመ ፲ወ፪ ለነሐሴ

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ምን ይሆን ውለታሽ
በኵረ መዘምራን ኪ/ጥበብ ወ/ቂርቆስ

ምን ይሆን ውለታሽ ድንግል የምከፍልሽ(፪)
ለአንቺ በመንገሬ ተፈታ ችግሬ(፪)።

የደካሞች ምርኩዝ የኃጥአን ተስፋ(፪)
ፈጥነሽ ትደርሻለሽ የሰው ልጅ ሲከፋ(፪)
ምን በግዞት ቢሆን ጨለማ ቢወርሰው(፪)
እንዳዘነ አይቀርም አንቺን የያዘ ሰው(፪)

አዝ ............

ድንግል ሆይ በምልጃሽ አስቢኝ አሁንም(፪)
ደካማ ነኝና መሳሳት አይቀርም(፪)
ቅዱሳን ስምሽን ምግባቸው አርገው(፪)
ይኖራሉ ባንቺ በሀሴት ጠግበው(፪)

አዝ ..........

አትርሺኝ እመአምላክ ቤዛዊተ ኵሉ(፪)
ላንቺ ሰጥቻለሁ ሕይወቴን በሙሉ
ውዳሴ ማርያምን አልነጥልም ከአፌ(፪)
በእርሷ አይቼዋለሁ ፈተናን ማለፌ(፪)

አዝ ..........

የዘነጋሽ ሁሉ ሲቸገር ቢጠራሽ(፪)
አትይውም ችላ አላውቀውም ብለሽ(፪)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

የጴንጤዋ ማርያም
የ ዘጠኝ ወር ልፋት እንዲሁ “አትወልጂም“ በምትል በአንዲት ቃል ሲጠቀለል ምን ይባላል??እድሜ ልኬን ተስዬ ለምኜ ያገኘኋት የማህፀኔ ፍሬ እንደ እፉኚት ከወለድሻት ትገልሻለች መባልስ ምን ማለት ነው??ፈጣሪስ ገና ወጥታ እሹሹሩ ካላልኳት፤ ካላጠባኋት፤ካልሳምኳት፤ካልታቀፍኳት ከገዛ ልጄ ጋር እንዴት ፀብ ውስጥ ይከተኛል???

ለምን ይሄ ሁሉ መከራ በኔ እንደመጣ ባላውቅም እግዚአብሔር ብዬ የለመንኩት አምላክ እንደሌለ ግን አረጋግጫለሁ።  ቢኖርማ ለምን ሰጥቶ ይነሳኛል??ለምን ሰምቶ ዝም ይለኛል??ደግ ከሆነስ ነብሴና ልጄን ሚዛን ላይ አስቀምጦ እንዴት ይተወኛል??ጨካኝ ቢሆን እንጂ....

ሲስ (ባሌ) ጠዋት ዜናውን ከሰማ ጀምሮ ትንፍሽ አላለም።አላማረረም።አላለቀሰም። ግን ደሞ ከኔ በላይ እየታመመ እንዳለ ፊቱ ጥቁር ብሎ በመሀል በመሀል ከፊቱ ባለች ጠባብ መስታወት ያየኛል።ከኋላ የተቀመጥኩት ጎኑ ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ ሕመሙን እንዳልጨምርበት ብዬ እንጂ ከአጠገቡ ስርቅ አይወድም።ያለወትሮው መኪናዋን ቀስ እያለ ነው ሚነዳት ሆስፒታል እንድንደርስ ሁለታችንም አልፈለግንም።ያላየናት ልጃችንን ገድለን እራሳችንን ለማትረፍ የምንጣጣር ራስ ወዳድ መሆናችን ተሰምቶን ይሁን?...አላቅም። ብቻ ግን የቀጠሯችን ሰዓት ደርሷል ሰዓቱ 9 ሰአት አናቱ ላይ ይላል።ከፊት ደሞ ከእንጦጦ ኪዳነምህረት አስቀዳሽ ምእመናን ቅዳሴ ጨርሰው ከቤተክርስትያኗ እየወጡ መንገዱን ዘግተወታል።ፍዝዝ ብዬ የሚተራመሠውን ሕዝብ እያየሁ የመኪናችን መስታወት በስሱ ሲንኳኳ ብንን ብዬ ዞርኩ።ጭርጭስ ያሉ አሮጊት በመስታወቱ አጮልቀው እያዩኝ የማልሰማውን ነገር እየለፈለፉ ሳይ መስታወቱን ዝቅ አደረግኩት....

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🔔የነሐሴ ፲፩ ግጻዌ
መልእክታት

1. ፩ኛ ቆሮንቶስ ፭፥፲፩-ፍጻሜ /5፥11- ፍጻሜ
2. ፩ኛ ዮሐንስ ፪ ፥ ፲፬ - ፳ /2 ፥ 14 - 20
3. ግብረ ሐዋርያት ፲፪፥፲፰ - ፍጻሜ/12፥18-ፍጻሜ

ምስባክ
መዝ ፵፬፥፲፮-፲፯ /44፥16-17
"ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ።
ወተሰይሚዮሙ መላእክተ ለኵሉ ምድር።
ወይዘክሩ ስመኪ በኲሉ ትውልደ ትውልድ።"
"በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች ተወለዱልሽ፥
በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ። ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ፤ "

ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል ፮፥፳ - ፳፬/6፥20-24
"፳
እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሣ እንዲህም አላቸው። እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና።
፳፩
እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና።
፳፪
ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ።
፳፫
እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።
፳፬
ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና።"

ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ /ጎሥዓ/ (በግዕዝ ዜማ)

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🔔 የነሐሴ ፲ ግጻዌ

መልእክታት
1. ዕብ ፲፪፥፳፪-ፍጻሜ/12፥22-ፍጻሜ
2. ፩ኛ ጴጥ ፩፥፮-፲፫/1፥6-13
3. ግብ ሐዋ ፬፥፴፩-ፍጻሜ/4፥31-ፍጻሜ

ምስባክ
መዝ ፸፫፥፪/73፥2
"ተዘከር ማኅበረከ ዘአቅደምከ ፈጢረ።
ወአድኃንከ በትረ ርስትከ።
ደብረ ጽዮን ዘኃደርከ ውስቴታ።"
"አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን አስብ።
የተቤዠሃትንም የርስትህን በትር።
በርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ።"

ወንጌል
የሉቃስ ወንጌል ፲፮፥፱-፲፱ / 16፥9-19
"፱
እኔም እላችኋለሁ፥የዓመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘላለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥በእርሱ ወዳጆችን ለራሳችሁ አድርጉ።

ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፥ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ ዓመፀኛ ነው።
፲፩
እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል?
፲፪
በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ፥የእናንተን ማን ይሰጣችኋል?
፲፫
ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ባርያ ማንም የለም፤ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፥ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
፲፬
ገንዘብንም የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው ያፌዙበት ነበር።
፲፭
እንዲህም አላቸው። ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፥ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኵሰት ነውና።
፲፮
ሕግና ነቢያት እስከ ዮሐንስ ነበሩ፤ከዚያ ጀምሮ የእግዚአብሔር መንግሥት ይሰበካል፤ሁሉም ወደ እርስዋ በኃይል ይገቡባታል።
፲፯
ነገር ግን ከሕግ አንዲት ነጥብ ከምትወድቅ ሰማይና ምድር ሊያልፍ ይቀላል።
፲፰
ሚስቱንም የሚፈታ ሁሉ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል"

ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ(በግዕዝ ዜማ)።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ሰንበት ትምህርት ቤቶችን እናበረታታ!

ይህ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የየረር በር ጽርሓ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ጽድቅ ሰ/ት/ቤት ሚዲያ ክፍል ነው። የሁሉም ማኅበራዊ ሚዲያዎቻቸው ማለትም:
👉 Telegram
👉 Facebook
👉 fnotetsidik?si=t5mtjXmi-FEeF6NK&sub_confirmation=1">YouTube
👉 Instagram
👉 fnote_tsidik">Tiktok
በእነዚህ ሊንኮች እየገባን እንቀላቀል። ለሌሎች በማጋራትም እናበረታታቸው!
ሁሉንም ሊንኮች በአንድ ላይ ለማግኘት 👉 https://linktr.ee/fnote_tsidik_ss

@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

🔔የነሐሴ ፱ ግጻዌ
መልእክታት
፩. ፊልጵስዩስ ፩፥፲፪-፳፬
፪. ፪ኛ ዮሐንስ ፩፥፮-ፍጻሜ
፫. ግብረ ሐዋርያት ፲፭፥፲፱-፳፭

ምስባክ
መዝ ፵፬ ፥ ፱/44፥9
"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ።
በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት።
ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ እዝነኪ።"
"በወርቅ ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና
ንግሥቲቱ በፊትህ ትቆማለች።
ልጄ ሆይ ስሚ እዪ÷ ጀሮሽንም አዘንብዪ። "

ወንጌል
ዮሐንስ ፲ ፥ ፩-፳፪/10፥1-22
፩. እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤......

ቅዳሴ
ዘእግዝእትነ/ዘባስልዮስ (በግዕዝ ዜማ)።

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…

የኦርቶዶክስ አስተምህሮዎች

ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ። PDF

@Ethiopian_Orthodox
@Ethiopian_Orthodox

Читать полностью…
Subscribe to a channel