ethio_fun | Technologies

Telegram-канал ethio_fun - Afrihealth TV

58193

Afri Health has a vision to create awareness, transfer knowledge/skill on preventive health and empower the community to manage their health status.

Subscribe to a channel

Afrihealth TV

የኢፌዲሪ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ የዘንድሮ የደመራና የመስቀል በዓልን በማስመልከት ያስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ

ለአገራችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ዘንድሮ ለሚከበረው የደመራና የመስቀል በዓልን በሰላም አደረሳችሁ!
በአገራችን መንፈሳዊ እሴትን ከባህላዊ ትውፊት ጋር አጣምሮ በአደባባይ በልዩ ድምቀት ከሚከናወኑ ክብረ በዓላት መካከል የደመራና የመስቀል በዓል በጉልህ ይጠቀሳሉ።

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የአለም ቅርስ ይሆን ዘንድ እውቅና የተቸረው የመስቀል በዓል ለአገራችን ከፍተኛ ክብርን ከማጎናፀፍና ለህዝቦቿም የኩራት ምንጭ ከመሆን ባሻገር በዚህ አስደማሚ የአደባባይ ትዕይንት ላይ ለመታደም በየአመቱ ከተለያዩ አገራት ለሚመጣው የቱሪስት ፍሰትም ምክንያት ብሎም ለምጣኔ ሀብታዊ ግኝት እጅግ የላቀ አስተዋፅዖ ሲያበረከት መቆየቱ ይታወሳል።

ይሁንና የዘንድሮው የደመራና የመስቀል በዓል የሚከበረው ኮቪድ 19 በአገራችን በተከሰተበት ወቅት መሆኑ ከወትሮው ለየት ያደርገዋል።
እንደሚታወቀው ስርዓተ ክዋኔው በባህሪው በርከት ያሉ ሰዎች በተሰባሰቡበት አውድ የሚፈፀም በመሆኑና ይህም ደግሞ ለቫይረሱ ስርጭትና መስፋፋት መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር በመሆኑ ወቅቱን ባገናዘበና የሚሰጡ የጥንቃቄ መመሪያዎችንም መሰረት ባደረገ መልኩ በዓሉን ማክበር እንደሚገባና በዚህ ረገድም ህዝበ ምዕመናኑ ይህንኑ ታሳቢ ያደረገ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በሌላ በኩል የደመራ በዓል እንደድልድይ ሆኖ ሃይማኖታዊ ግዴታን ይፈፅሙ ከመንፈሳዊ ማዕዱም ተቋዳሽ ይሆኑ ዘንድ ምዕመናን ከተለያየ ግን ደግሞ ላስተሳሰራቸው የጋራ ዓላማ በአንድ የሚገናኙበት፣ የሚሰባሰቡበትና እርስ በእርስ የሚቀራረቡበት መድረክ እንደመሆኑ መጠን በተለይ የመደመር እሳቤን የሰነቀውን የአገራችን የለውጥና የብልፅግና ጉዞ ከዳር በማድረስ ረገድም እንዲሁ ሁላችንም በአንድነት መሰለፍና በጋራ መረባረብ እንደሚያስፈልግ በዚህ አጋጣሚ መልዕክቴን
አስተላልፋለሁ።

መልካም በዓል!
(የኢፌዲሪ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣አዲስ አበባ)

Читать полностью…

Afrihealth TV

የአርቲስት አልማዝ ኃይሌ የቀብር ስነ-ስርዓት ተፈፅመ

የአንጋፋዋ የአርቲስት አልማዝ ኃይሌ /ማሚ/ የቀብር ስነ-ስርዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን በዛሬው እለት ተፈፅሟል።

በተወዛዋዥነት፣ በፊልምና ትያትር እንዲሁም በማስታቂያ ስራዎቿ የምትታወቀው አርቲስት አልማዝ ኃይሌ በ1938 ዓ.ም ነበር በቀድሞው የሀረር ክፍል ሀገር ልዩ ስሙ አሰበ ተፈሪ የተወለደችው።

አርቲስቷ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ትያትር ከታህሳስ 8 ቀን 1958 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 35 ዓመታት በሀገር ባህል በተወዛዋዥነት፣ በተዋናይነት፣ በድምፃዊነት፣ በሜካፕ ባለሙያነት ትያትር ቤቱን አገልግላለች።

አርቲስቷ ባጋጠማት የደም መርጋት በሽታ ምክንያት የህክምና ክትትል ስታድርግ ቆይታ መስከረም 15 ቀን 2013 ዓ.ም ማለዳ በተወለደች በ75 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

አልማዝ ኃይሌ የአራት ልጆች እናት ነበረች።
[ebc]

Читать полностью…

Afrihealth TV

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ መስከረም 15 /2013 ዓ.ም ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።

በስብሰባውም በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ ከተወያየ እና ከመከረ በኋላ የሚከተሉትን ውሳኔዎች በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
1. የወቅቱ ዓለም አቀፍ ስጋት የሆነው Covid-19 ወረርሽኝ በአገራችን እንዲሁም በከተማችን ከተከሰተበት ከመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም ጀምሮ የህክምና አገልግሎት በመስጠት እንዲሁም በማስተባበር የተሠማሩ በከተማው አስተዳደሩ ስር በሚገኙ የጤና ተቋማት ሁሉ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ይህ ወረርሽኝ በአገራችን ስጋት መሆኑ እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ የከተማ አስተዳደሩ የገቢ ግብር ወጪያቸውን ለመሸፈን ውሳኔ አሳልፏል።

2. የከተሞች ዕድገት እና ልማት ከአካባቢያቸው ጋር ሲተሳሰር የህዝባችን የጋራ ተጠቃሚነት ፣የአብሮነት አስተሳሰብ እና ሰላማዊ ግንኙነትን ያዳብራል፡፡
አዲስ አበባም በዙሪያዋ ካሉ አካባቢዎች ለእድገት እና ልማቷ ብዙ ግብዓቶችን እያገኘች እድገት እና መስፋፋቷም ሲፋጠን በዙሪያዋ ላሉ ነዋሪዎች ትሩፋት እንጂ መከራና መሰደድ መሆን የለበትም ፡፡

ለአብነትም በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ አካባቢዎች ለከተማዋ የውሀ፣ የመሬት፣ የኮንስትራክሽን ግብአቶች በማቅረብ እንዲሁም በርካታ የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት፣ የግል ሠራተኞች እና የከተማዋ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች መኖሪያ ሆነው ሳሉ ከፍተኛ ለሆነ ማህበራዊ ችግር እና የመሠረተ ልማት እጥረት የተጋለጡ ሆነዋል።

በመሆኑም ዛሬ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በከተማዋ የተጀመረውን የትምህርት ተሞክሮ እና አገልግሎቶች በአካታች ልማት |inclusive development| መርህ መሰረት በፊንፊኔ ልዩ ዞን በሚገኙ 346 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ (152,000)ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ ጫማ እና የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ አስር ሽህ ሰባት መቶ ሰማንያ ብር (669,210,780 ብር) በጀት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በልዩ ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል።

Читать полностью…

Afrihealth TV

ፌዴራል ፖሊስ ከመስከረም 25 በኋላ “ህጋዊ መንግስት የለም” በሚል ትርምስ ለመፍጠር የሚጥሩ ሃይሎችን እንደማይታገስ ገለጸ

ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከመስከረም 25 በኋላ “ህጋዊ መንግስት የለም” በሚል አገራዊ ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ ጠንካራ እርምጃ ለመስድ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። ኮሚሽኑ የደመራና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወኑ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉንም አስታውቋል።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓል ቅድመ ዝግጅትን እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም፤የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓላት በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።

የበዓሉን እንቅስቃሴ ለማደፍረስ ዕቅድ ያላቸው ሀይሎች እንዳሉ ፖሊስ በምርመራ እንደደረሰበት የጠቆሙት ኮሚሽነር ጀነራሉ፤ እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቀቆጠቡ አሳስበዋል።
በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ወደ አዲስ አበባ መግቢያ በሮች በሱሉልታ፣ ለገጣፎ፣ ቡራዩ፣ ገላንና ሰበታ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በበዓሉ ለመታደም የሚመጡ ምዕምናንና እንግዶች የይለፍ ባጅ ማድርጋቸውን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ይህን ተላልፎ በሚገኝ ማንኛውም አካል ላይ ፖሊስ እርምጃ እንደሚወስድ በመግለጽ ተመሳሳይ የይለፍ ባጅ አሰርተው ለመግባት የሚሞክሩ አካላት መለየት የሚያስችል አሰራር ስላለ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አሰተላልፈዋል።

የዘንድሮው መስቀል እና ኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቅ ፓሊስ አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት አድርጓል ብለዋል።
በዓላቱን ተገን አድርገው ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስን ማንኛውንም አካል ፖሊስ አይታገስም ብለዋል።
ኮሚሽነር ጀነራሉ አክለውም ከመስከረም 25 በኋላ “መንግስት የለም” በሚል አገራዊ ትርምስ ለመፍጠር በሚሰሩ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ህዝቡን ለአመፅ እንዲነሳሳ የሚያደርጉ መልዕክቶችን በስፋት የሚያሰረጩ አካላት እንዳሉ ጠቅሰው እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው።
በባአሉም ይሁ በሌላ አጋጣሚ ህብረተሰቡ ለየት ያለ እንቅስቃሴ ሲመለከት የተለመደ ትብብሩንና ጥቆማውን ለፖሊስ እንዲያደርስም ጠይቀዋል።
(ኢዜአ)

Читать полностью…

Afrihealth TV

የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት ጊዜ ለመስጠት ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከል መሰረት ያደረጉ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ የ12ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሰጥ በቅድሚያ ትምህርት ቤቶች ኮቪድ-19 መከላከልን መርህ ባደረገ መልኩ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ከፈተናው አስቀድሞም የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት የማረጋገጥ ስራ በትምህርት ሚኒስቴር እንደሚሰራም ተገልጿል።
የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እና ምዝገባ በኦንላይን እንደሚካሄድ እና ተማሪዎች የ45 ቀን የማካካሻ እና የቴክኖሎጂ መለማመጃ ጊዜም እንደሚሰጣቸው ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱት እና ፈተናም የሚሰጠው ትምህርት ቤቶች አስፈላጊውን ቅድመ ጥንቃቄ ማሟላት ሲችሉ ብቻ መሆኑም ተገልጿል።
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች እንዲከፈቱ ያስቀመጣቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሸራረፉ እንዲተገበሩ ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቅርቧል።
[ የትምህርት ሚኒስቴር]

Читать полностью…

Afrihealth TV

በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ የሚደረጉ መንገዶች ይፋ ተደረጉ፡፡

በዚህም መሰረት
- ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ
- ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ
- ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት
- ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መ/ቤት አካባቢ
- ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ
- ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ
- ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
- ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ
- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
- ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ ፣ ለገሀር መብራት የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት አካባቢ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ሲሆን፣ ደመራው የሚደመርበት መስቀል አደባባይ እና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲዬም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሰፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገድ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ የሚደረግ ይሆናል፡፡
በመሆኑም ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Читать полностью…

Afrihealth TV

ትምህርት ቤቶች በሶስት ዙር ትምህርት እንዲጀምሩ ሊደረግ ነው፡፡

ትምህርት ቤቶችን ዳግም መክፈት በሚቻልበት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፋዎችና ሌሎች ሚኒስትሮችም ተገኝተዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት ስለቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ገለፃ አድርገዋል።

የትምህርት ቤቶች ትምህርት ማስጀመር ሂደት በሶስት ዙር እንደሚከናወን የሚል ምክረ ሃሳብ ቀርቧል፡፡
በገጠር ወረዳና ቀበሌ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በመጀመሪያው ዙር ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሃሳብ ቀርቧል።

በሁሉም የዞንና የክልል ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ደግሞ በ2ኛ ዙር ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ ነው ምክረ ሃሳብ የቀረበው።
በአዲስ አበባና በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የሚገኙ ትምህርት ቤቶችም ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ትምህርት እንዲጀምሩ የውሳኔ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል።

የ8ኛና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን አስመልክቶም ሁሉም ተፈታኞች ለፈተና እንዲቀመጡ የሚል የውሳኔ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ተገልጿል።
የ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሕዳር 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን ፈተና ላይ መቀመጥ የሚችሉት 7ኛ ክፍልን ተምረው ያጠናቀቁና የ8ኛ ክፍልን የአንደኛ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መውሰድ የሚችሉት የ11ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቁና የ12ኛ ክፍልን የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት የተከታተሉ ብቻ ናቸው ተብሏል።
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሕዳር 28 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥም በምክረ ሀሳቡ ላይ ተጠቅሷል።
የትምህርት አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ለመንግስት ትምህርት ቤቶች የሚወጣው መመዘኛ በግል ትምህርት ቤቶችም ተፈጻሚ ይሆናል ተብሏል፡፡

በቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ የሚደረገው ውይይት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
[የትምህርት ሚኒስቴር]

Читать полностью…

Afrihealth TV

የዓለም ባንክ 80 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ሰጠ

በሚ/ር መ/ቤቱ ሲተገበር የቆየው የሁለተኛ ዙር የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ፕሮጀክቶች ማስጨረሻ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት በዓለም ባንክና በገንዘብ ሚኒስቴር ተፈረመ፡፡

ይህ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት የሚያተኩረው ግብርና ሚኒስቴር በሁለተኛ ግብርና ዕድገት ፕሮግራም በተለያዩ ክልሎች የአርሶ አደሮች ኑሮ እንዲያሻሻል የግብርና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ፣ የተጨማሪ ገቢ ማገኘት የሚያስችላቸውና የግብርና ምርት ዕሴት ሰንሰለት እንዲጎለብት እየተገበረ ለነበሩ ፕሮጀክቶች ማስጨረሻና የአነስተኛ አርሶ አደሮች የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚውልና የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጾል፡፡

የድጋፉ ስምምነቱ የተፈረመው በመንግስት በኩል በክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትርና በአለም ባንክ በኩል ደግሞ በክቡር ሚስቴር ኦስማን ዲዮን በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ናቸው፡፡

የዓለም ባንክ ግብርና ሚኒስቴር የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሮች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያስችሉና በአጠቃላይ ድህነትን ለመቀነስ የሚያካሂደውን የተለያዩ ዓይነት የልማት ፕሮግራሞች በገንዘብና በቴክኒክ እየደገፈ የሚገኝ መሆኑ ይታወሳል፡፡
[የግብርና ሚንስቴር ]

Читать полностью…

Afrihealth TV

በትላንትናው ዕለት በጤና ሚንስቴር የፌደራል ኤች አይቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር የሀይማኖት ተቋማት በኤችአይቪ ኤድስ መከላለልና መቆጣጠር ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር የምክክር መድረክ አካሂደናል።

ኤች አይቪ ኤድስን መከላከልና መቆጣጠር ላይ ላለፉት በርካታ አመታት በሁሉም ዘርፍ በተሰራው ስራ ከፍተኛ ውጤት የታየበት ቢሆንም አሁንም የጤና ስጋት ነው። ስለዚህም ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በመመርመር ራሳቸውን እንዲያውቁ፣ ቫይረሱ በደማቸው ያለ ደግሞ መድሀኒት ሳያቋርጡ ሊወስዱ ይገባል። በተለይም በዚህ የኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት የመከላከል ስራውን የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በቅንጅት በሁሉም ደረጃ አጠናክረን መቀጠል እንደሚያስፈልግ ተስማምተናል።

Читать полностью…

Afrihealth TV

መስቀል እና ኢሬቻን የሚያከብሩ ምዕመናን ባጅ ወይንም የይለፍ ካርድ መያዝ አለባቸው - የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

የፊታችን ቅዳሜና እሁድ የሚከበሩት የደመራ እና የመስቀል በዓል እንዲሁም መስከረም 23 እና 24 ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል የሚታደሙ ሰዎች ባጅ ወይንም የይለፍ ካርድ የያዙ መሆን እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የጤና ሚኒስትር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ባጅ ወይንም የይለፍ ካርድ የያዙ ብቻ እንዲገቡ እንደሚደረግ ፖሊስ አሳውቋል፡፡
በበዓላቱ ላይ ህጋዊ ዕውቅና የሌላቸው አርማዎችን ሰንደቅ አላማዎችን እንዲሁም ብሄርን ከብሄር ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ ጽሑፎችን መያዝ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑንም ፖሊስ አሳስበዋል፡፡

ይህንን በሚተላለፉ አካላት ላይ ህጋዊ የሆነ እርምጃ እንደሚወስድ እና ነዋሪው የመዲናዋን ጸጥታ ለማደፍረስ የሚሞክሩ ኃይሎች መጠቀሚያ እንዳይሆን እራሱን እንዲጠብቅም ፖሊስ ገልጿል፡፡

እንዲሁም ከተፈቀደለት አካል ውጪ በዋዜማው በተናጠልም ሆነ በቡድን በሚደረጉ የደመራ በዓላት ላይ ርችት መጠቀም አይቻልም፡፡

በዓላቱ በሰላም ተጀምረው በሰላም እንዲጠናቀቁ የመዲናዋ ነዋሪዎች ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት በጋራ ሰላሙን እንዲጠብቅ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Читать полностью…

Afrihealth TV

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ 6ኛው አገራዊ ምርጫንና ሌሎችተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ

ፓርላማ፤ መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም.፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ተገሰ ጫፎ ትላንት ም/ቤቱ ያሳለፈውን ውሳኔ በተመለከተ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አፈ ጉባኤው በመግለጫቸው በ2012 ዓ.ም ሊካሄድ የነበረው 6ኛው አገራዊ ምርጫ በተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት መራዘሙን ጠቁመው፤ በተያዘው ዓመት አገራዊ ምርጫ ለማከላሄድ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ላይ ምክር ቤቱ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ አገራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውሰው፡፡ ምርጫ ቦርድና የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅት ማድረግ መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡

የአስቸኳ አዋጁ ጊዜ ገደብ ያለቀ በመሆኑ መንግስትና ሌሎች ተቋት የሚመሩባቸው የህግ ማዕቀፎች በመተግበር የትምህርት ስርአቱ፤ የትራንስፖርት አገልግሎቶች፤ ሆቴሎችን እና የቱሪዝም አገልግሎቶቸው እንዲሁም ስብሰባዎችን እንዴት መምራት እንደሚቻል የህግ ማዕቀፎችን በማስቀመጥ ስራቸውን በተገቢው መንገድ መከናወን እንዳለባቸው ጤና ሚኒስቴር በስራ አስፈፃሚው አካል የተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሰረት ማስፈፀም እንዳለበት አሳሰበዋል፡፡

አያይዘውም ህብረተሰቡ ከጤና ሚኒስቴር የሚሰጡትን መመሪዎችና የግንዛቤ ስራዎችን በመረዳት ዜጎች ራሳቸውን ከኮሮና መሽታ በመከላከል አገራዊ ምርጫን ለማካሄድ መዘጋጀት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ አቶ ተገሰ ጫፎ አክለውም ከትምህርት ተቋማት ጋር በተያያዘ በየደረጃው ያለው አመራርና ህብረተሰቡ እንዲሁም ተማሪዎችን ጭምር በወያየትና በማሳተፍ በቂ ግንዛቤ በመያዝ አስፈላጊ የትምህርት፤ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን፤ የመማሪያ ክፍሎችን በማመቻቸት የትምህርት ስርአቱን ማስጀመር እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡
[hopr]

Читать полностью…

Afrihealth TV

ዋሺንግተን ዲሲ —
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ታሪካዊ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ይከፈታል። በድርጅቱ የሰባ አምስት ዓመታት ታሪክ የአባል ሃገሮች መሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ የጉባዔው መክፈቻ ንግግራቸውን በአካል ሳይሆን በተቀረፀ ድምጽ ካሉበት ሆነው ያስተላልፋሉ።

ዛሬ የብራዚል ፕሬዚዳንት ጄይር ቦልሶናሮ የመጀመሪያው ተናጋሪ ሲሆኑ የአስተናጋጇ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የተቀረጸ ንግግር ይደመጣል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ንግግራቸው ለቻይና ጠንካራ መልዕክት ያካተተ እንደሚሆን ትናንት አስታውቀዋል።
[VOA]

Читать полностью…

Afrihealth TV

ምክር ቤቱ 6ኛውን ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ማካሄድ እንደሚቻል ገለጸ

ዜና ፓርላማ ፤ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው 6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የመከላከል ስራውን ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ በ2013 በጀት አመት ማካሄድ ይቻላል በሚል የቀረበለትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አጽድቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅትና የኢትዮጵያ ህብርተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባስቀመጡት ምክረ- ሀሳብ መሠረት ቫይረሱን በመከላከል ምርጫውን ማከናወን እንደሚቻል ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 18 ቀን 2012 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ የዳሰሳ ጥናት አድርጎ ምርጫ ማካሄድ እንደማይቻል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረቡ ምክንያት ምርጫው እንዲራዘም መደረጉን ያስታወሱት ወ/ሮ አበባ ካሉት ትንበያዎች አንጻር ወረርሽኙ ረዘም ላለ ጊዜ አብሮን ሊቆይ የሚችል በመሆኑ ይህንኑ ግምት ውስጥ ያስገባ የምርጫ ስነ-ምግባር ደንብና መመሪያ በማዘጋጀት ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መኖሩን የጤና ሚኒስቴር ባቀረበው ሪፖርት ማረጋገጥ እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡

የምክር ቤት አባላት በበኩላቸው ማህበረሰቡ በቫይረሱ ዙሪያ ያለውን ግንዘቤ በማስፋትና መዘናጋት እንዳይፈጠር ሰፊ የንቅናቄ ስራዎችን በመስራት ምርጫውን ማካሄድ እንደሚቻል አብራርተዋል፡፡
ከቫይረሱ ጋር ሆነው ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ምርጫ ያከናዎኑ ሃገራት ለአብነት ከውጭ ፈረንሳይና እስራዔል፤ ከአፍሪካ ደግሞ ጊኒ፣ ቡሩንዲ፣ ማሊና ዝምባብዌ ምርጫ ማካሄድ እንደቻሉ የምክር ቤቱ አባል አወቀ አጥናፉ /ዶ/ር/ በምሳሌነት አንስተዋል፡፡

ወ/ሮ አበባ በበኩላቸው በቫይረሱ ላይ ጥብቅ የክትትልና ቁጥጥር ስራ እንደሚሰራ ገልጸው ፣ ምርጫ ቦርድም ከዛሬ ጀምሮ ወደ ዝግጅት ምዕራፍ መግባት የሚያስችለው ሁኔታ መኖሩን ነው የገለጹት፡፡
የውሳኔ ሃሳቡም የውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 16/2013 ሆኖ በአንድ ተቃውሞ በ8 ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ጸድቋል፡፡

ምክር ቤቱ መስከረም 8/2013 ባካሄድው 5ኛ ዙር 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ አሰጣጥና ቀጣይ እርምጃዎች የቀረበውን ሪፖርትና ምክር ሃሳብ በዋናነት ለሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ለህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለዝርዝር እይታ መመራቱ ይታወሳል፡፡
[hopr]

Читать полностью…

Afrihealth TV

ዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይረክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሓኖም በአኖርወይ ኦስሎ በመገኘት የዓለም "የ2020 ብሪጅ ሜከር" በሚል ያሸነፉበተን ሽልማታቸውን ተረከቡ።

Читать полностью…

Afrihealth TV

በተለያየ ጊዜ የተሰረቁ በርካታ የመኪና እቃዎችን ከሶስት ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአብነት አካባቢ ፖሊስ አስታወቀ

በልደታ ክ/ከተማ በተለያየ ጊዜ ተሠርቀው የተከማቹ በርካታ የመኪና እቃዎችን ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን የአብነት አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ገለፀ::

የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመኪና ዕቃ ስርቆት ወንጀልን ለመከላከል የክትትልና ኦፕሬሽን ቡድን አዋቅሮ ወደ ተግባር በመግባት ህብረተሰቡ የራሱን ንብረት በራሱ ገንዘብ እንዲገዛ የሚገደድበትን ህገ ወጥ ድርጊት ለማስቀረት እየሠራ መሆኑን አሰታውቋል፡፡

በዚህ እንቅስቃሴም በክፍለ ከተማው ወረዳ 4 በተለምዶ ሱማሌ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባባቢ ከተለያዩ ክ/ከተሞች የተሠረቁ የመኪና እቃዎችን ከህብረተሰቡ በደረሠ ጥቆማና ተጨማሪ ጥናትን መሠረት በማድረግ መስከረም 6 ቀን 2013ዓ.ም በ4 ቤቶች ላይ በተካሄደ ብርበራ ተሰርቀው የተከማቹ በርካታ የመኪና ዕቃዎች ሊያዙ መቻላቸውን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ስዩም አስፍሃ ገልፀዋል፡፡

የአብነት አካባባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ዋና ሳጅን ታመነ መገርሳ በበኩላቸው በብርበራው ወቅት የመኪና ስፖኪዮ ፣ ፍሬቻ ፣ የነዳጅ ታንከር (ሰልባቲዮ) ክዳን እና ሌሎች የመኪና እቃዎች ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር ተይዘው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

አሽከርካሪዎች ተሽከርካሪያቸውን ሲያቆሙ ከእይታቸው አልያም ከጥበቃ ባልራቀ ሁኔታ ቢሆን እንደሚመረጥ እና ፖሊስም የሚያደርገው ክትትል እና ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገሩት የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ስዩም አስፍሃ በተለያዩ ክ/ከተሞች በተለያየ ጊዜ የመኪና ዕቃ የተሠረቀባቸው ግለሰቦች ወደ ፖሊስ መምሪያው በመምጣት ንብረታቸው ስለመኖሩ አረጋግጠው እና ለይተው መውሰድ የሚችሉ መሆኑን አሳስበዋል።
(ኢፕድ)

Читать полностью…

Afrihealth TV

እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ!!!
በለውጣችን ተፈላጊነትንም አስፈላጊነት እናረጋግጣለን
አፍሪኸልዝ ቴሌቭዥን

Читать полностью…

Afrihealth TV

የሚኒስትሮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 90ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

Читать полностью…

Afrihealth TV

የ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

Читать полностью…

Afrihealth TV

አርቲስት አልማዝ ኃይሌ ከዚህ አለም በሞት ተለየች

በበርካታ የትያትርና ፊልም ስራዎች የምትታወቀው አርቲስት አልማዝ ኃይሌ (ማሚ) ከዚህ አለም በሞት ተለየች።

ባለፉት ሁለት ሳምንታት የህክምና ክትትል ሲደረግላት የቆየችው አርቲስት አልማዝ በዛሬው ዕለት ህይወቷ አልፏል።

አርቲስት አልማዝ ለ42 ዓመታት በብሄራዊ ትያትር ቤት በተዋናይነት፣ ተወዛዋዥነት እና ሜካፕ አርቲስትነት ማገልገሏ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው።

እንዲሁም ከብሄራዊ ትያትር ቤት ተሳትፎዋ ባሻገር በበርካታ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራሞች፣ ፊልሞች እና ማስታወቂያዎች ላይ ተሳትፎ አድርጋለች።

Читать полностью…

Afrihealth TV

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል በግል የምናደርገው ጥንቃቄ ውጤቱ በማህበረሰብ ብሎም በሀገር ላይ አስተዋፆው የጎላ በመሆኑ ሁላችንም ሀላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፡- ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ
በስራ ቦታ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት አስመልክቶ በሀዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝትና የቢልቦርድ ምርቃት ተካሄደ፡፡

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአሠሪ እና ሠራተኛ አካላት ጋር በመሆን የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት በሀዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ በመገኘት የጎበኙ ሲሆን "እኔም ሀላፊነት አለብኝ! እናንተስ?" በሚል መልዕክት የተዘጋጀ ቢልቦርድ አስመርቀዋል፡፡

የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ አየለች እሸቴ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ህብረተሰቡ ራሱን ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እንዲጠብቅ መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃን በመደገፍ አሰሪና ሰራተኛው ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ከወትሮው በተሻለ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የእያንዳዳችን ጥንቃቄ ውጤት በሀገር ላይ ያለው አስተዋፆው የጎላ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ኮቪድ-19 በስራው አለም ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ሁላችንም ጥንቃቄ ሊለየን አይገባም ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርክ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አሰሪና ሰራተኛን የሚይዝ ቦታ በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራውን አጠናክሮ በመቀጠል፤ እራስን ከኮሮና በመከላከል ስራን የማስቀጠል አራአያ የሚሆን ተግባር ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የሰራተኛው እና የስራ ዋስትና ቀጣይነት እንዲኖረው ኮሮና ቫይረስን በመከላከል ስራን ለማስቀጠል እንደ ሀገር የተከተልነው መንገድ ትክክል መሆኑ በተግባር ታይቷል ያሉት የአሰሪና ሰራተኛ ከፍተኛ አመራሮች ለጥንቃቄ ትኩረት በመስጠት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ስራን ለማስቀጠል እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በስራ ቦታ ለመከላከል እየተተገበረ ያለው የስራ ቦታ ምላሽ ፕሮቶኮል እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የአፈፃፀም መመሪያ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል ወሳኝ ድርሻ እያበረከተ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የሠራተኛና ማሀበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአሠሪና ሠራተኛ አካላት እና ጥሪ ከተደረገላቸው አመራሮች ጋር በመሆን በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፖርክ ችግኝ ተተክሏል፡፡
በአዲስ አበባ ቦሌ ለሚ ኢንደስትሪ ፓርክ፣ በደብረ ብርሀን ኢንደስትሪ ፖርክ የስራ ቦታን ከኮሮና ወረርሽን ለመከላከል ከሚደረገው እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ መሰል ስራ ወሰራቱ የሚታወስ ነው፡፡
[የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ]

Читать полностью…

Afrihealth TV

መስከረም 13/01/2013 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ለአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የምዘና ውጤት አሳወቀ፡፡

በምዘና ውጤት አሰጣጡ ላይ በተደረገ ውይይት የማሰልጠኛ ተቋማት የግምገማ ውጤታቸውን ሪፖርት የተቀበሉ ሲሆን የውጤት አሰጣጥጡ ላይ ያለቸውን ቅሬታ ለተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ከመስከረም 14/01/013 ዓ.ም እስከ መስከረም 18/01/ 013 ዓ.ም ባሉት 3 የስራ ቀናት ማቅረብ እንደሚችሉ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም ምክሩ ተናግረዋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አኪያጅ አንደተናገሩት በ2009 ዓ.ም የማሰልጠኛ ተቋማት ምዘና የተካየሄደ ሲሆን የ2012 ዓ.ም ምዘና ዓለማም በአዲሱ አመት የሚከሰተውን የትራፊክ አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል እንዲያስችል ነው፡፡

ምዘና ከተደረገባቸው የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ተቋማት መካከል በውጤታቸው መሰረት ተቋማቱ ላይ የማስተካከያ እርምጃዎች የሚወሰድ ይሆናል፡፡ በዚሁ መሰረት የሚዘጉ፤ማስጠንቀቂያ የሚሰጣቸው፤ለተወሰነ ወራት ከስራ የሚታገዱ እንዳሉ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ በሰው ህይወት እና በንብረት እየደረሰ ያለውን አስከፊ የትራፊክ አደጋ ለመከላከል የተጣለብንን ሀላፊነት ተግተን የምንሰራ ሲሆን የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ተቋማትም ራሳቸውን ዝግጁ በማድረግ ብቃት ያለው አሽከርካሪ በማፍራት የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
[በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁ/ባለስልጣን]

Читать полностью…

Afrihealth TV

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ተቋማትን መልሶ ለመክፈት እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች ላይ ያተኮረ ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ተቋማትን መልሶ ለመክፈት እየተደረጉ ያሉ ዝግጅቶች እና ኮቪድ 19ን ከመከላከል አኳያ የነበሩ ተግባራዊ ምላሶች ላይ ያተኮረ የሁለት ቀን ምክክር በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡

በመድረኩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የተቋረጠውን ስልጠና ለማስቀጠል መደረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎችና ስልጠናውን ለማስጀመር መደረግ ስላለባቸው ዝግጅቶች በመመካከር ስልጠናው የሚጀምርበት አቅጣጫ ይቀመጣል ብለዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ወረርሽኙኝ ለመከላከል የሚያግዙ የቴክኖሎጂ ማሸጋገርና ያበረከቷቸው የፈጠራ ስራዎች ከፍተኛ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ሙሉ ለስልጠና ተቋማቱ ቀደም ብሎ የቅድመ ዝግጅት ስራ እንዲያከናውኑ አቅጣጫ መሰጠቱንና በዚያም መሰረት ጥሩ የዝግጅት ደረጃ ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በበኩላቸው በአገራችን ለኮቪድ 19 ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ስራ መሰራቱን ጠቁመው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፉም የነበረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ መሰል ወረርሽኞች ሲፈጠሩ ሳይንስ ምላሽ ይዞ ይመጣል፡፡ ሰፊ የሳይንሳዊ ስራዎች ከሚሰሩባቸው መስኮች አንዱ ትምህርትና ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

በኮቪድ 19 ምክንያት ተማሪዎች ከገፅ ለገፅ ትምህርት ከተለያዩ 6 ወራት እንደሆናቸው አንስተው አሁን ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥንቃቄዎችን አጠንክረን እየሰራን ወደስራችን እንመለስ የሚለውን በመወሰኑ የጤና ሚኒስቴር የሚያወጣውን የጥንቃቄ ፕሮቶኮል ተከትሎ ወደ ስልጠና መመለስ አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል፡፡

ፕሮፌሰር አፈወርቅ እንዳሉት አዲሱ የስራ ዝግጅት ኮቪድን እየተከላከልን ስራዎችን ማስቀጠል እንደመሆኑ አመራሩ ከሰራተኛ ስምሪት፣ ትስስር ከመፍጠር ጀምሮ ለይቶ መምራትና መደገፍ ያስፈልጋል ብለው ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን በመለየትና መፍትሔ በማስቀመጥ ሊሆን እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡

ፕሮፌሰር አፈወርቅ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ነው ብለዋል፡፡ ዘርፉ በግብርና በኢንዱስትሪ በአገልግሎትና አስቻይ በሚባሉ ዘርፎች ገብቶ የአገርን ኢኮኖሚ የሚገነባ ወሳኝ ዘርፍ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መፍጠር ስልጠናውን ጥራት ያለው ማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ስለነገ መነጋገር ዘርፉን ወደልህቀት ለመውሰድ አስተዋፅኦ እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ትምህርትና ስልጠና የእድገት ቁልፍ መሆኑን በመረዳት የተሰሩ ስራዎች እንደአገር ውጤት አምጥተዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና መመሪያ ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማልማት ጥቃቅንና አነስተኛ ላይ የተሰማሩትን በኢንዱስትሪ ለመደገፍ አስችሏል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ሴክተሩ ብቁና በቂ የሰው ኃይል ከማፍራት አንፃርም ኃላፊነት የተጣለበት እንደመሆኑ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ኮቪድ 19 የጤና ስጋት እየሆነ መምጣቱን በመገንዘብ የሰዎች ንክክ የሚበዛባቸውን ሰልጣኞች ወደቤተሰብ መልሶ ዘግቶ እንደነበረ ጠቅሰው ነገር ግን በጥንቃቄ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም ጉዳቱን ለመቀነስ የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራት ረገድ የተለያዩ አበረታች ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡ ከነዚህም ርቀትን ማስጠበቂያ መተግበሪያ፣ ጭንብል፣ የህክምና ባለሙያ ጋወን፣ የለይቶ ማቆያ አልጋ፣ በሴንሰር የሚሰራ የእጅ መታጠቢያና ሳኒታይዘር ማድጊያ፣ በፔዳል የሚሰራ የእጅ መታጠቢያ፣ ሳኒታይዘር እና ሌሎች ምርቶችንም እንደሚገኙበት ገልፀዋል፡፡

አሁንም ትምህርትና ስልጠናውን ለማስቀጠል በሁሉም ክልሎች ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆናቸውንና አብዛኞቹ በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

ምክክሩ ለሁለት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን የንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ጉብኝትና የ2012 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ እንዲሁም የጂቲፒ 2 አፈፃፀም ቀርቦም ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡

በምክክሩ የፌደራልና የክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የስራ ኃላፊዎች፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቴክኖሎጂና የሰው ሃብት ቋሚ ኮሚቴ ተወካዮች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
[የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር]

Читать полностью…

Afrihealth TV

ፎርጅድ የሆኑ አዲሱ የብር ኖቶች ገበያ ውስጥ እየተሰራጩ እንደሆነ ከተለያዩ ምስሎች ጋር በስፋት ሶሻል ሚድያ ላይ እየተፃፈ ነው።

ኢትዮጵያ ቼክ ከብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ ማብራርያ አግኝቷል።

አዳሲሶቹ የብር ኖቶች ላይ ያለው አብረቅራቂ መስመር (security thread) አቀማመጥ ከብር፣ ብር ይለያያል። ለምን?

ዶ/ር ይናገር: የዚህ Security Thread ወይም Rolling Star አቀማመጥ በእኛም ሆነ በገንዘቡ አታሚ ድርጅት ቀድሞ የሚታወቅ ነው፣ ከህትመት በፊት እናውቀዋለን፣ ውይይት አርገንበት የነበረ ነገር ነው። ይህ ልዩነት የመጣው የአሁኑ የብር ኖት የደህንነት መጠበቂያዎች (security features) ለማተሚያ ማሽኑ አዲስ ስለሆኑ ነው።

ይህ በራሱ ችግር አይደለም?

ዶ/ር ይናገር: ፈፅሞ ችግር አይደለም፣ እውነታው ይህ ነው። ዋናው ነገር ይህ የደህንነት መጠበቂያ መኖሩ ነው።
ስለዚህ አሁን በዝውውር ላይ ያለው አዲሱ የብር ኖት ብቻ ነው? ፎርጅድ አለ ስለሚባለው ጉዳይ የሚያውቁት ወይም የደረሳችሁበት መረጃ አለ?
ዶ/ር ይናገር: በአሁን ሰአት በዝውውር ላይ ያለው አዲሱ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በብሄራዊ ባንክ የታተመው ነው። ምንም ፎርጅድ ወይም ሀሰተኛ ብር የለም። ሆን ብለው ብዥታን የሚፈጥሩ አካላትን መከላከል አለብን፣ እውነታው ይህ ነው።

Читать полностью…

Afrihealth TV

ታዋቂው ድምጻዊ አሊ ቢራ ህመም አጋጥሞት ህክምና ላይ ይገኛል።

የ73 ዓመቱ አርቲስት አሊ ቢራ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ እና አዳማ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል።

"በፊት ላይ በጣም አሞኝ ነበር። አሁን ተሽሎኛል። አሁን ያለሁበት ሆስፒታል ጥሩ ክትትል እያደረጉልኝ ስለሆነ ፈጣሪ ይመስገን እየተሻለኝ ነው" ብሏል አሊ ቢራ።

አሊ ቢራ በአሁኑ ወቅት የውስጥ ደዌ ህክምና እየተደረገለት ሲሆን ከዚህ ቀደምም የልብ እና የስኳር በሽታዎች ታማሚ መሆኑን ይናገራል።
[BBC]

Читать полностью…

Afrihealth TV

በትግራይ የግእዝ ቋንቋ በመደበኛ ትምህርት መርሀግብር ሊሰጥ ነው

በትግራይ ክልል የግእዝ ቋንቋን በመደበኛ የትምህርት መርሀ ግብር ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ቋንቋዎች አካዳሚና ትምህርት ቢሮ አስታወቁ።

የትግራይ ቋንቋዎች አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳንኤል ተክሉ እንደገለፁት በሀገሪቱ በግእዝ ቋንቋ የታተሙ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጥንታዊ የብራናና የመጽሀፍት ህትመቶች አሉ።

“አዲሱ ትውልድ ፅሁፎችን በማንበብ የሀገሩን ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ታሪክና ማንነት ጠንቅቆ እንዲያውቅ ለማበረታታት የቋንቋውን ትምህርት መስጠት አስፈልጓል” ብለዋል።

በተያዘው 2013 አመት በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምሀርቱን ለመስጠት ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል ።
ከትግርኛ፣ ኩናምኛና ሳሆኛ ቋንቋዎች ቀጥሎ ግዕዝ አራተኛ ቋንቋ ሆኖ በክልሉ በሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።

ቢሮው የመማር ማስተማር ስራውን እንዲጀምር በክልሉ ምክር ቤት በአዋጅ መጽደቁንም አስታውቀዋል።
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ባህታ ወልደሚካኤል በበኩላቸው የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን በክልሉ በሚገኙ ከ2 ሺህ በላይ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለማስጀመር የመምህራንና የመማሪያ መፃፍት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

ከስድስት ወራት በኋላ ትምሀርቱን ለመጀመር እቅድ መያዙን አመላክተዋል ።
በመቐሌ የሃወልት ክፍለ ከተማ ነዋሪና የሰላም አካዳሚ የትግርኛ ቋንቋ መምህር ሃዱሽ አታክልቲ የግዕዝ ቋንቋ በመደበኛ የትምህርት መርህ ግብር እንዲሰጥ መታቀዱ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

የትምህርቱ መሰጠት በየአብያተ ክርስትያናትና ገዳማት ውስጥ የሚገኙና በግዕዝ ቋንቋ ተጽፈው የታተሙ ጥንታዊና ታሪካዊ መፃህፍቶችን በቀላሉ አንብቦ ለመገንዘብ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል ።

ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ልማት እድገትም ያለው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።
“አዲሱ ትውልድ በመጤ ቋንቋዎችና ባህሎች ከመበረዝ ይልቅ የሀገሩን ባህልና ቋንቋ በሚገባ እንዲያውቅና እንዲጠብቅ ያስችለዋል” ሲሉም መምህር ሃዱሽ አስታውቀዋል።
[ኢዜአ]

Читать полностью…

Afrihealth TV

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከ2020 የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተቱ

የዘንድሮው የ“ብሪጅ ሜከር አዋርድ” አሸናፊ የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከታይም መጽሔት የ2020 የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ 100 ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካትተዋል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴድሮስ ከዓለማችን 100 ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል አንዱ ሆነው ሊመረጡ የቻሉት በተለይ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ሁሉም ሰው እኩል የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እንዲያገኝ በያዙት ጠንካራ አቋም ነው ተብሏል።

በተጨማሪም፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ ለመከላከል በተደረገው ጥረት የራሳቸውን አበርክቶ ማድረጋቸውም ተጠቃሽ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የ2020 “ብሪጅ ሜከር አዋርድ” ሽልማታቸውን በትላንትናው እለት የተቀበሉ ሲሆን ሽልማቱ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል ግንባር ቀደም ሆነው እያገለገሉ ላሉ የጤና ባለሙያዎች መታሰቢያ ይሁንልኝ ሲሉ የምስጋና መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Читать полностью…

Afrihealth TV

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ስለ ’’ገበታ ለሀገር’’ ፕሮጀክት ገለጻ ተደረገ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ‘’ ገበታ ለሀገር’’ ፕሮጀክት ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ዛሬ ገለጻ አድርጓል።

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዳሉት ባለፈው ዓመት ጠቅላይ ሚኒስርትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሃሳብ አፍላቂነት የሸገር ፓርክ ፕሮጀክት ይፋ ተደርጎ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ ደረጃውን የጠበቀ ፓርክ ተገንብቶ መመረቁን ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት የሸገር ፕሮጀክት ይፋ ሲደረግ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ እንደማይቻል ስጋት የነበረ ቢሆንም፣ ነገር ግን በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖረው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አጋር አገሮች፣ የዲፕሎማተክ ማህበረሰቡ እና የበላይ አመራሩ የላቀ ቁርጠኝነት ፕሮጀክቱ በተያዘለት ጊዜ ለፍጻሜ መብቃቱን በማስታወስ በዚህ ፕሮጀክት መሳካት የተሳተፉትን ሁሉ ክቡር አቶ ገዱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሸገር ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ ሰሌዳ እና ጥራት በመፈጸሙ በተገኘው ተሞክሮ መሰረት በዚህ ዓመትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአገር አቀፍ ደረጃ ‘’የገበታ ለሀገር’’ አማካኝነት የሚተገበሩ ካለይ የተጠቀሱት ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች ለመጀመር እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ መሆኑን አቶ ገዱ በንግግራቸው አብራርዋል።

‘’የገበታ ለሀገር’’ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ ለወጣቱ የስራ እድል በመፈጠር እንዲሁም የአገሪቱን የአረንጓዴ ልማት በማፈጠን እንድ አገር የተያዘውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና አንደሚኖራቸው ገልጸዋል።

እንደ ሸገር ፕሮጀክት ሁሉ የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ‘’በገበታ ለሀገር’’ ፕሮጀክቶችም ተመሳሳይ ተሳተፎ በማደረግ አሻራችሁን እንድታሳርፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ በማለት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል።
(ኢፕድ)

Читать полностью…

Afrihealth TV

ማይክሮሶፍት የመስከረም ወር የዊንዶዉ-10 የደህንነት ማዘመኛዉን ለደንበኞቹ አቀርቧል

አዲስ አበባ መስከረም 12/2013፡-ማይክሮሶፍት ኩባንያም ለዊንዶዉስ-10 በኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የተፈጠሩ ክፍተቶችን ለመድፈን የመስከረም ወር የደህንነት ማዘመኛዉን ለደንበኞቹ አቀርቧል
ማይክሮሶፍት በየወሩ ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች የኦፕሬቲንግ ሲስተም ስህተቶችን እና የደህንነት ተጋላጭነትን ለማስተካከል የሚሆን ክፍተት መሙያ /Patch/ ይለቃል፡፡

ማይክሮሶፍት ከወርሃዊ መደበኛ ክፍተት መሙያዎች በተጨማሪ ለሁሉም የዊንዶዉስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚሆኑ ተጠቃሚዎ የግድ መጠቀም የማይጠበቅባቸዉን የአማራጭ የዊንዶውስ-10 ማዘመኛንም በየወሩ ያቀርባል፡፡
ማይክሮሶፍት አዲሱን ክሮሚየም ላይ የተመሠረተ ማይክሮሶፍት ኤጅ /Microsoft Edge/ በዊንዶውስ-10 ውስጥ እንዲጭኑ የሚያስገድዱ አዳዲስ አስገዳጅ ዝመናዎችን እየጫነ ነው።

ሆኖም እነዚህን የደህንነት ማዘመኛዎች ተግባራዊ በሚደረጉበት ወቅት በሌኔቮ ላፕቶፕ ተጠቃሚዎች ላይ ከታየዉ ችግር ባሻገር አንዳንድ ተጠቃሚዎች የዊንዶውስ-10 የስታርት ሜኑ /Start Menu/ መክፈት አለመቻል እና ዝመናዎችን ከጫኑ በኋላ ምላሽ የማይሰጥ እንደሆነባቸዉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይሁን እንጂ አዲስ የዊንዶውስ-10 ማዘመኛዎች ሲለቀቁና ተጠቃሚዎች የክፍተት መሙያዎችን ሲተገብሩ ብልሽቶች ፣ የፍጥነት ፣ የትግበራ እና የመዘበራረቅ ችግር ሲገጥመው ይስተዋላል፡፡

በመስከረም ወር/2020 ዝመናዎች ለዊንዶውስ-10 ቨርዥን (1809 ፣ 1903 ፣ 1909 እና 2004) KB4576754 የተባለ ማዘመኛን ያቀረበ ሲሆን ለዊንዶውስ-10 ቨርዥን ደግሞ (1803) KB4576753 ተለቋል፡፡
ማይክሮሶፍት ባደረገው በዚህ ዝመና የዊንዶዉስ-10 ተጠቃሚዎች በሃርድ ድራይቭ ላይ እየገጠማቸዉ ያለዉን ከፍተኛ ብልሽት የሚያስተካክል መሆኑን ኩባንያዉ ጠቁሟል፡፡

[ኢመደኤ]

Читать полностью…

Afrihealth TV

ደጋፊዎችን የወሩ መጨረሻ ላይ ወደ ስታዲየም የመመለሱ እቅድ ውድቅ ሆነ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን ጨምሮ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች ላይ ደጋፊዎችን ከመስከረም 21 ጀምሮ ወደ ስታዲየም የማስገባቱ እቅድ ወድቅ መደረጉ ተገለጸ።

ይህ የሆነበት ምክንያት በዩናይድ ኪንግደም እና በተቀሩበት የአውሮፓ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ መሆኑን የጠቅላይ ሚንስትሩ ካቢኔ አባል የሆኑት ማይክል ጎብ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው እቅድ እስከ 1ሺህ የሚደርሱ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየም ገብተው ክለባቸውን እንዲደግፉ መፍቀድ ነበር።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ከሼፊልድ ዩናይትድ መስከረም 23 በሚያደርጉት ጨዋታ ደጋፊዎች ወደ ስታዲየሞች ይገባሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ካለፈው መጋቢት ወር ወዲህ በእንግሊዝ የእግር ኳስ ውድድሮች በዝግ ስታዲየም ሲካሄዱ ቆይተዋል።

በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ስፓርታዊ ውድድሮች በዝግ ስታዲየም እንዲደረጉ መወሰኑ በክለቦች ላይ ከፍተኛ የፋይንስ ቀውስ አስክትሏል።

የባህል፣ ሚዲያ እና ስፖርት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ጁሊያን ናይት “ታዳሚዎች ወደ ስታዲየሞች የሚመለሱበትን ብልህ የሆኑ አሰራሮች ካልዘረጋን የስፖርት እና ባህላዊ መሠረተ ልማቶቻችን ተንኮታኩተው ይቀራሉ” ብለዋል።

ከ100 በላይ የስፖርታዊ ውድድሮች አመራሮች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ካጋጠማቸው ኪሳራ ለማገገም ለጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል።

ስፖርት ኢንግላንድ የተሰኘው የመንግሥት አካል 200 ሚሊዮን ፓውንድ ለአስቸኳይ ወጪ መሸፈኛ በሚል ለስፖርት ክለቦች ድጋፍ አቅርቧል። ይሁን እንጂ ይህ ገንዘብ ክለቦች ያጋጠማቸውን ኪሳራ ለመሸፈን በቂ አይደለም ተብሏል።
[BBC]

Читать полностью…

Afrihealth TV

በምስራቅ አፍርካ ሀገራት አንዳንድ አከባቢዎች ከባድ የዝናብ ስርጭት እንደሚኖር ኢጋድ አስጠነቀቀ

በምስራቅ አፍርካ ሀገራት አንዳንድ አካባቢዎች ከመስከረም 12 እስከ 20 /2013 ባሉት ቀናት ውስጥ ከባድ ዝናብ እንደሚጠበቅ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) አስጠነቀቀ።

በምዕራብ ኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች፣ በሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ሱዳንና በምዕራብ ኬንያ አካባቢዎች ከ200 ሚሊ ሜትር በላይ ከባድ ዝናብ እንደሚጠበቅ ጠቁሟል፡፡

በሱዳን ደቡባዊ ክፍሎች፣ በአብዛኛው ደቡብ ሱዳን፣ በምዕራብና በመካከለኛው ኢትዮጵያ፣ በሰሜን ምስራቅ ሶማሊያ፣ በአብዛኛው ኡጋንዳ፣ በመካከለኛውና በምዕራብ ኬንያ እንዲሁም በአብዛኛው ሩዋንዳና ቡሩንዲ ከ50 እስከ 200 ሚሊ ሜትር የሚደረስ መካከለኛ ዝናብ ይጠበቃል ብሏል፡፡

በምዕራብ ኤርትራና ማዕከላዊ ሱዳን፣ የሰሜን፣ የደቡብና የምስራቅ ኢትዮጵያ ክፍሎች የጅቡቲ የባህር ዳርቻዎች፣ የደቡብ ምስራቅ ደቡብ ሱዳን ክፍሎች፣ የሰሜን እና የደቡብ ሶማሊያ ክፍሎች፣ የሰሜን ምዕራብና የደቡብ ምስራቅ ኬንያ፣ የሰሜን ምስራቅና ምዕራብ ኡጋንዳ ጥቂት አካባቢዎችና የሰሜናዊ ምዕራብ እንዲሁም የምስራቅ ታንዛኒያ አካባቢዎች ከ 50 ሚሊ ሜትር በታች የሆነ ቀላል ዝናብ እንደሚጠበቅም ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል በምዕራባዊ ፣ ደቡባዊና ማዕከላዊ ታንዛኒያ አካባቢዎች ፣ በሰሜን እና በሰሜን ምስራቅ ኬንያ ፣ በማዕከላዊ ሶማሊያ ፣ በደቡብ ምስራቅ እና በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ አንዳንድ ክፍሎች ፣ በምስራቅ የኤርትራ ክፍሎች ፣ በጅቡቲ እና በሰሜን ሱዳን ስፍራዎች ደረቃማ ሁኔታዎች እንደሚጠበቅ ባለስልጣኑ ትንበያውን አቅርቧል።
[ENA]

Читать полностью…
Subscribe to a channel