28497
Afri Health has a vision to create awareness, transfer knowledge/skill on preventive health and empower the community to manage their health status.
HIGHLIGHTS - Equatorial Guinea 🆚 Côte d'Ivoire
Читать полностью…
በኮሎምቢያ ካሊ ከኦገስት 01-06/2022 ላለፋት ስድስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ በሰነበተው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ የተሳተፈው የአትሌቲክስ ቡድናችን በ6ወርቅ፣ በ5ብር እና 1የነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን ተከትለን አትሌቶቻች ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ 3ኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀናል። ይህም ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካችን ዘንድሮ የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛው ሲሆን ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው።
🥇🥇🥇🥇🥇🥇
🥈🥈🥈🥈🥈
🥉
በኮሎምቢያ ካሊ የአለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000ሜ. የወንዶች የፍፃሜ ውድድር
አዲሱ ይሁኔ በ14:03.05 በሆነ ሰዓት 1ኛ🥇
ገበየሁ በላይ በ14:04.55 በሆነ ሰዓት 4ኛ ዲፕሎማ
🇪🇹 እንኳን ደስ አለን!
የሴቶች 800 ሜትር ፍፃሜ ድርቤ ወልተጂ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች ።
1ኛ አሜሪካ
2ኛ እንግሊዝ
3ኛ ኬንያ
4ኛ ድርቤ ወልተጂ 🇪🇹
ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር ሶስት የተለያዩ የቴሌ ብር የፋይናንስ አገልግሎቶችን ይፋ አደረገ።
ኢትዮ ቴሌኮም ከአንድ አመት በፊት ይፋ ባደረገው የቴሌ ብር የፋይናንስ አገልግሎት ከ22 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ከ55 በላይ ተቋማት ጋር ቴሌ ብር እየሰራ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ፍሬ ህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።
ዛሬ ይፋ የተደረጉት የፋይናንስ አገልግሎቶች ሶስት ሲሆኑ እነዚህም፦ቴሌ ብር እንደ ኪሴ፣ቴሌ ብር መላ እና ቴሌ ብር ሳንዱቅ/ቁጠባ ናቸው።
ቴሌ ብር መላ/ብድር፦ ለግለሰብ እስከ 10,000 ብር ለተቋማት ደግሞ እስከ 100,000 ሺህ ብር የብድር አገልግሎት ይሰጣል።
ቴሌ ብር እንደ ኪሴ፦ በቴሌ ብር አማካኝነት ግብይት ሲፈፀም የጎደለ የገንዘብ መጠን ካለ እስከ 2,000 ብር የብድር አገልግሎት ይሰጣል።
ቴሌ ብር ሳንዱቅ/ቁጠባ፦ ከትንንሽ ገንዘቦች ጀምሮ መቆጠብ የሚያስችል የፋይናንስ አገልግሎት።
ብድሩ በዳሽን ባንክ ወጪ የሚደረግ ሲሆን ሲስተሙ ደግሞ በኢትዮ ቴሌኮም የሚመራ መሆኑ ነው የተገለፀው።
የዚህ የፋይናንስ አገልግሎት ለማስጀመር ያስፈለገበት ምክንያት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ አስታውቀዋል።
የቀጣይ ዓመቱ የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር የ2015 የጨዋታ መርሃ ግብርን ዛሬ ረፋድ በጽህፈት ቤቱ አውጥቷል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ከመውረድ የተረፉ 13 ክለቦችና ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደጉት ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ኢትዮጵያ መድህንና ኢትዮ ኤሌክትሪክን አካቶ የ16ቱን ክለቦችን የጨዋታ መርሃ ግብር ዛሬ አውጥቷል፡፡
መስከረም 20 2015 የቀጣይ ዓመቱ የፕሪምየር ሊግ መርሃ ግብር ይጀመራል ያለው አክሲዮን ማህበሩ የመጀመሪያ ዙር የ15 ሳምንት ጨዋታዎቹን ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህ መሰረት በአንደኛ ሳምንት ባህርዳር ከተማ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፣ ወላይታ ድቻ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ፋሲል ከነማ ከአዳማ ከተማ፣ወልቂጤ ከተማ ከአርባ ምንጭ ከተማ፣ ሃዋሳ ከተማ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ መቻል ከሃድያ ሆሳዕና፣ ኢትዮጵያ መድህን ከቅዱስ ጊዮርጊስና ድሬደዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና እንደሚጫወቱ የወጣው ድልድል ይጠቁማል፡፡
በመጀመሪያ ዙር ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል በአምስተኛ ሳምንት በሸገር ደርቢ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና 6ኛ ሳምንት ፋሲል ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
የ2014 የኢትዮጵያ ቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሳይቆራረጥ መካሄዱን በጥንካሬ በየቀኑ ሶስት ጨዋታዎች ማካሄድን በድክመት ያነሱት የአክሲዮን ማህበሩ የውድድርና ስነ ስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢው ዶክተር ወገኔ ዋልተንጉስ ናቸው፡፡
የ2015 የውድድር መርሃ ግብር ካለፉ ስህተቶች ትምህርት የሚቀሰምበት ነው ያሉት ሰብሳቢው ለተግባራዊነቱ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ይደረጋል ብለዋል፡፡
በ18ኛው የኦሪገኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያ ሜዳሊያ አላገኘችም። በውድድሩ ኖርዌይ የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዳለች። ኢትዮጵያን የወከሉት አትሌቶች፦
🇪🇹 ዩሚፍ ቀጀልቻ 8ኛ
🇪🇹 ሰለሞን ባረጋ 12ኛ
🇪🇹 ሙክታር እድሪስ 13ኛ በመሆን አጠናቀዋል።