dreyob | Unsorted

Telegram-канал dreyob - Dr. Eyob Mamo

80341

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

Subscribe to a channel

Dr. Eyob Mamo

Best Gift Ever!

ለቅርብ ወዳጆቻችን ልንሰጣቸው ከምንችላቸው የቁሳቁስ ስጦታዎች ይልቅ የላቀው ስጦታ የአብሮነት ስጦታ ነው፡፡

እውነተኛ የሆኑ ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ ፍቅረኞች፣ የትዳር አጋሮች . . . ከሁሉም በፊት የሚፈልጉት የእኛን አብሮነት ነው፡፡

ይህ አብሮነት ጊዜን በመስጠት፣ የሚያሳስባቸውን ነገር በማድመጥ፣ በስሜታቸው ላይ ሳይፈርዱ በመገንዘብ፣ ደስ ሲላቸው ሳንቀና አብሮ ደስ በመሰኘትና በችግራቸው ጊዜ ባለመሸሽ ይገለጣል፡፡

ምንም ነገር ባንሰጣቸውም እንኳን ለምንም ነገር አሳልፈን እንደማንሰጣቸው ማወቃቸው ብቻ ይበቃቸዋል፡፡ ምንም አቅርቦት ባይኖረን እንኳን ራሳችንን ካቀረብንላቸው ያረካቸዋል፡፡

ጣፋጭ እንቅልፍ ይሁንላችሁ፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

እውነተኛው ሰው!

በሕይወታችሁ ከምንም አይነት የግል ፍላጎትና ጥቅም ሳይነሳ እውነቱንና የሚነግራችሁ ቢያንስ አንድ ሰው የመኖሩን ጉዳይ እርግጠኞች ሁኑ፡፡

• ከሰጣችሁ ሃሳብና ከነገራችሁ የግሉ አመለካከት የተነሳ ቅር ብትሰኙበትም እንኳን እናነተን ለማትረፍ ሲል ያንን የሚያደርግ ሰው ያስፈልጋችኋል፡፡

• ከመከራችሁ ምክር የተነሳ በምትወስኑት ውሳኔ ውስጥ ምንም ጥቅም እንደማያገኝ እያወቀ ሃሳቡን የሚነግራችሁ ሰው ያስፈልጋችኋል፡፡

• ምክሩን ብትሰሙትም ሆነ ባትሰሙት በእናንተ ላይ ያለው አመለካከት ፈጽሞ የማይለወጥ ሰው ያስፈልጋችኋል፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ብቻውን የቀረ ማንነት!

“ሰዎችን በውጪ ለማስቀረት በዙሪያችሁ የገነባችሁት ግንብ እናንተንም በውስጥ አጥሮ እንደሚያስቀራችሁ አስታውሱ” (Today's Wisdom)

ከአላስፈላጊ ሰዎች ለመራቅ የምታደርጉት ውሳኔ አስፈላጊ የመሆኑን ያህል፣ በማሕበራዊ ብልህነት ከሰዎች ጋር ተቻችሎ የመኖርንም ልምምድ አክሉበት፡፡

አለዚያ ብቻችሁን መቅረታችሁ ነው፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የጭንቀት ጅዋጅዌ

“ጭንቀት ማለት ልክ እንደ ጅዋጅዌ ጨዋታ ነው፡ ወዲህና ወዲያ ያደርጋችኋል፣ ነገር ግን የትም አያደርሳችሁም” (Quote of the day)

መፍትሄ የሚገኝለትን መፍትሄ ፈልጉለት፡፡ መፍትሄ የማይገኝለትን ለፈጣሪ ተውለት!

አዎን ከባድ ነው! አማራጩ ግን እሱ ነው!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ምርጫ ማድረግን ምረጡ! ለመወሰን ወስኑ!

ጥሩ ጥሩ ምርጫና ውሳኔዎች የሚመጡት ከልምድ ነው፡፡

ልምድ ደግሞ የሚመጣው ሕይወትን በመጋፈጥ፣ በመኖርና ከባባድ ውሳኔዎችን በመወሰን ከሚሰሩ ስህተቶችና ትምህርቶች ነው፡፡

ጸሎት አድርጉ! አስቡ! ወስኑ! ውጡ! ስሩ!

የተሳካው ያሻሽላችኋል፡፡

ያልተሳካው ያስተምራችኋል፡፡


ከዚህ ውጪ ሌላ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የምርጫ እና የውሳኔያችሁ ጉዳይ!

ምርጫዎቻችሁ እና ውሳኔዎቻችሁ የሚያሳዩት ከሁለት አንዱን ነው . . .

1. ተስፋ

ወደ ፊት ስለሚታያችሁ ተስፋ አስባችሁ ምርጫና ውሳኔ ስታደርጉ ከምንም አይነት አሉታዊ ተጽእኖ ውጪ ስለምትሆኑ ትክክለኛውን ምርጫና ውሳኔ የሚያደርግ ብሩህ አእምሮ ይራችኋል፡፡

2. ፍርሃት

አንድ ነገር ይደርስብኛል ወይም አንድ እድል ያመልጠኛል በማለት በፍርሃት ምርጫ እና ውሳኔ ስታደረጉ የማመዛዘን አቅማችሁ ይጨልምና በኋላ የምትጸጸቱበትን ስሜታዊ ምርጫና ውሳኔ ታደርጋላችሁ፡፡

ምርጫ እና ውሳኔዎቻችሁ ከተስፋ የመነጩ ይሁንላችሁ!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል

የዛሬዋ ቀን ሳታልፍ አንድ ነገር ላሳስብ፡- በዚህ አመት የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡

“ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” – Brian Tracy

አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡

ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡

የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡

ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡

“ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” –Henry David Thoreau

“የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” – Nora Roberts

“ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ” - Unknown Source

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

አስቸጋሪ ሰዎችና ሁኔታዎች

በሕይወታችሁ በራሳቸው በሚሄዱ ችግሮችና መፍትሄ ካልፈለጋችሁላቸው እየባሱ በሚሄዱ ችግሮች መካከል የመለየትን ጥበብ አዳብሩ፡፡

አንዳንድ ሁኔታዎች ትኩረት ስትነፍጓቸውና ዋና ዓላማችሁ ላይ ስታተኩሩ በራሳቸው እየደከሙ ይሄዳሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን የግድ ተገቢው ትኩረት ሊሰጣቸውና መፍትሄ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

የችግር ፈጣሪ ሰዎችንም ሁኔታ በዚሁ መልኩ በማየት በጥበብ ያዙት፡፡

ዛሬ ከመተኛታችሁ በፊት ያሉባችሁን ከሁኔታዎችም ሆነ ከሰዎች የሚመጡ ችግሮች ከእነዚህ ከሁለቱ የመፍትሄ መንገዶች መካከል በየትኛው መልኩ እንደምትቀርቧቸው አስባችሁ እደሩ፡፡

የሰላም እንቅልፍ ተመኘሁላችሁ!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የማይካድ ሀቅ!!!

• ከዋና ዓላማችሁ በመነሳት ለራሳችሁ ፕሮግራም ካላወጣችሁ፣ ሰዎች ፕሮግራም ያወጡላችኋል፡፡

• የራሳችሁን ሕይወት ካልመራችሁ፣ ሰዎች ወደፈለጉበት ይመሯችኋል፡፡

• ሕይወታችሁን በመልክ በመልኩ ካላደረጃችሁት፣ የመጣውን ሁኔታ ሁሉ እየተቀበላችሁ ለመኖር ትገደዳላችሁ፡፡

• እቅድ አውጥታችሁ የምትከተሉት ነገር ከሌላችሁ፣ ከሁኔታዎች እንደሸሻችሁ ትኖራላችሁ፡፡

• ብዙ እምቅ ብቃት ኖሯችሁ ካለምንም እቅድ እና አደረጃጀት ከኖራችሁ፣ ምንም እውቀት የሌላቸውና የተደራጁት እንደነዷችሁ ትኖላችሁ፡፡

የዚህ እውነታ ተጽእኖ ከምታስቡት በላይ እጅጉን ጠንካራ እና ለማስተካከል ጊዜው ካለፈ በኋላ እንድትባንኑ የሚያደርችሁ ጉዳይ መሆኑን አስታውሱ፡፡

ሁኔታው ካሳሰባችሁ፣ የተዘጋጀላችሁን ስልጠና ለመሳተፍ ወሰኑ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

Be intentional! Be proactive!

መድረስ ወይም መሻሻል በምንፈልግባቸው የሕይወት ዘርፎቻችን አንጻር ሆን ብለንና አስበንበት (intentionally) ካልተንቀሳቀስን ሁል ጊዜ ባለንበት እንደረገጥን እንኖራለን፡፡

ይህ ሁኔታ የምላሽ ሰጪነት አቀራረብ (reactive approach) እና የንቁ አቀራረብ proactive approach) ልዩነትን ያሳየናል፡፡

1. “የምላሽ ሰጪነት አቀራረብ” (reactive approach)፡- በአካባቢያችን ለሚከናወኑ ሁታዎች፣ ለወቅቱ ስሜታችንና ሰዎች ለሚያሳዩንም ሆነ ለሚናገሩን ነገሮች ምላሽ እየሰጡ መኖርን ያመለክታል፡፡

2. “ንቁ አቀራረብ” (proactive approach)፡- መሆን እና ማከናወን በምንፈልገው ነገር ዙሪያ ሆን ብሎ አስቦና አቅዶ መንቀሳቀስን ያመለክታል፡፡

በሕወታቸው ስኬታማ የሆኑ ሰዎች “ንቁ አቀራረብ” (proactive approach) ልምምድን ያዳበሩ ሰዎች ናቸው፡፡

ምንም እንኳን በጋጣሚ የሚከናወኑልን ስኬታማ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም፣ በአጋጣሚ የመጣ በአጋጣሚ ሊሄድ እንደሚችል በማሰብ የምናደርጋቸውን ነገሮች በሚገባ አቅደንና አስበንበት መስራት አለብን፡፡

ይህ የሕይወት ልምምድና ዘይቤ ከፍተኛ የሆነን ሕይወትን የማደራጀትን ጥበብ የሚጠይቅ ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ግንዛቤያችሁ እንዲሰፋ እና ሕይወታችሁና ስራችሁ መስመር እንዲይዝ የሚያግዛችሁ ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁና አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

Be intentional! Be proactive!

መድረስ ወይም መሻሻል በምንፈልግባቸው የሕይወት ዘርፎቻችን አንጻር ሆን ብለንና አስበንበት (intentionally) ካልተንቀሳቀስን ሁል ጊዜ ባለንበት እንደረገጥን እንኖራለን፡፡

ይህ ሁኔታ የምላሽ ሰጪነት አቀራረብ (reactive approach) እና የንቁ አቀራረብ proactive approach) ልዩነትን ያሳየናል፡፡

1. “የምላሽ ሰጪነት አቀራረብ” (reactive approach)፡- በአካባቢያችን ለሚከናወኑ ሁታዎች፣ ለወቅቱ ስሜታችንና ሰዎች ለሚያሳዩንም ሆነ ለሚናገሩን ነገሮች ምላሽ እየሰጡ መኖርን ያመለክታል፡፡

2. “ንቁ አቀራረብ” (proactive approach)፡- መሆን እና ማከናወን በምንፈልገው ነገር ዙሪያ ሆን ብሎ አስቦና አቅዶ መንቀሳቀስን ያመለክታል፡፡

በሕወታቸው ስኬታማ የሆኑ ሰዎች “ንቁ አቀራረብ” (proactive approach) ልምምድን ያዳበሩ ሰዎች ናቸው፡፡

ምንም እንኳን በጋጣሚ የሚከናወኑልን ስኬታማ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም፣ በአጋጣሚ የመጣ በአጋጣሚ ሊሄድ እንደሚችል በማሰብ የምናደርጋቸውን ነገሮች በሚገባ አቅደንና አስበንበት መስራት አለብን፡፡

ይህ የሕይወት ልምምድና ዘይቤ ከፍተኛ የሆነን ሕይወትን የማደራጀትን ጥበብ የሚጠይቅ ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ግንዛቤያችሁ እንዲሰፋ እና ሕይወታችሁና ስራችሁ መስመር እንዲይዝ የሚያግዛችሁ ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁና አያምልጣችሁ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ጥያቄ፡-

ሰላም ዶ/ር፣ ጥር 1 ቀን ለሚጀምረው ስልጠና አሁኑኑ መመዝገብ አለብን? ካልሆነስ መቼ ነው መመዝገብ ያለብን?

መልስ፡-

ለሚሰጠው ስልጠና ከአንድ ወር በፊት ማሰታቂያ የምንናገረው . . .

1. በቶሎ ተመዝግበው የመቆየት ልምምድ ያላቸው ሰዎች ያንን ማድረግ እንዲችሉ

የዚህ አስቀድሞ የመመዝገብ ጥቅሙ፣ ስልጠናውን ልውሰድ ወይስ አልውሰድ ከሚል መወላወልና ያለመወሰን ሁኔታ እንድንጠበቅና ቁርጠኞች እንድንሆን ስለሚያግዘን ነው፡፡ በተጨማሪም፣ ቀደም ብሎ የመዘጋጀትን የአደረጃጀት ብቃት እንድንለምድ ያደርገናል፡፡
2. ቀደም ብለው በማወቅ ለመዘጋጀት ጊዜን የሚፈልጉ ሰዎች ጊዜ እንዲያገኙ

የዚህ ዝግጅት ጥቅሙ፣ የጊዜ መጨናነቅ ያለባቸው ሰዎች ጊዜያቸውን አስቀድመው እንዲያቅዱ እና የገንዘብ እጥረት ያለባቸው ሰዎች ለዚያ ዝግጅት በቂ ጊዜ እንዲኖራ ነው፡፡

በአጠቃላይ የሚመከረው ግን ለእንደዚህ አይነት ወሳኝና ጠቃሚ ነገር አስቀድሞ መመዝገብና የአእምሮ ዝግጅት እያደረጉ መቆየት ነው፡፡

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የድግግሞሽ አዙሪት

በየቀኑ እየተነሳችሁ ከቤት ወጥታችሁ በሚኖራችሁ ስምሪት፣ የምትሰሩት ስራ፣ የምትውሉበት አካባቢ፣ የምታገኟቸው ሰዎችና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከሰለቻችሁና የትም እንደማያራምዳችሁ ካሰባችሁ “የድግግሞሽ አዙሪት” ውስጥ እንዳላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡

የድግግሞሽ አዙሪት ምልክቶች፡-

1. ተስፋ መቁረጥ፣

2. ሁሉም ነገር የማስጠላት ስሜት፣

3. ነገሮች እንደማይለወጡ ማሰብ፣

4. ኋላ የመቅረት ስሜት እና የመሳሰሉት ስሜቶች ናቸው፡፡

ከዚህ አዙሪት ለመውጣት መውሰድ የምንችላቸው እርምጃዎች፡-

1. ራእያችን ወይም የሕይወታች ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ መለየት፣

2. ከራእያችን አንጻር ወደ አዲስ ነገር ለመግባት መወሰን፣

3. በወሰንነው ውሳኔ ዙሪያ በየእለቱ የሚወሰዱን ትንንሽ እርምጃዎች መጀመር፣

4. የጀመርነውን እርምጃ በፍጹም አለማቆም፣

5. በምክር ሊያግዘን የሚችል ሰውን በመለየት ምክርን መቀበልና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የዛሬን ዛሬ የመተግበር አደረጃጀት!

“ከባድ ስራ ማለት ማጠናቀቅ በሚገባህ ሰዓት ሳታጠናቅቅ ያለፍከው ቀላል የነበረ ስራ ማለት ነው” - Bernard Meltzer

• ሰኞ - ዛሬ ተራራውን ለመውጣት አስቤ ነበር … ግን ገና እንደ ጀመርኩት ተጫጫነኝና ተመለስኩ፡፡

• ማክሰኞ - ዛሬ ተራራውን ለመውጣት አስቤ ነበር … ግን ገና ስጀምር መጨላለም ጀመረና ተውኩት፡፡

• ሮብ - ዛሬ ተራራውን ለመውጣት አስቤ ነበር … ግን ብርዱ አስፈራኝና ሃሳቤን ለወጥኩ፡፡

• ኃሙስ - ዛሬ ተራራውን ለመውጣት አስቤ ነበር … ግን ብዙ ማከናወን ያሉብኝ ነገሮች ትዝ አሉኝና አስተላለፍኩት፡፡

• አርብ - ዛሬ ተራራውን መውጣት እንዳለብኝ ረስቼው ነበር … ጓደኛዬ መጥቶ እስኪያስታውሰኝ ድረስ፡፡ ያንን ተራራ ወጥቶ መመለሱ ነበር፡፡ ድካሙን አይቼ ፈራሁና ቀረሁ፡፡

• ቅዳሜ - ዛሬ ተራራውን ለመውጣት አስቤ ነበር … ግን ገና ስጀምረው ትልቅነቱን አሰብኩና የማልጨርሰውን ነገር ባል ጀምረው ይሻለኛል ብዬ ተመለ ስኩ፡፡

• እሁድ - ዛሬ ተራራውን መውጣት አስቤ ነበር … ለካ ሰንበት ነው፡፡

እንደዚህ አይነቱ ሁኔታዎችን ለነገ የማስተላለፍ ልማድ የሚመጣው ከአደረጃጀት ክህሎት ወይም ከዲሲፕሊን ማጣት ነው፡፡ ከዚህ አይነቱ ሁኔታ ለመላቀቅ የሚረዳችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

ልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29 (ለአምስት ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የመራራነት ጣጣ

የነጮች የበላይነትና ባርነት ሕጋዊ በነበረበት ዘመን አንዲት ለነጮች ብቻ የተዘጋጀች የመዝናኛ መርከብ ነበረች፡፡ እነዚህ ነጮች እጅግ ዘረኞች ስለነበሩ አንድም ጥቁር አብሯቸው እንዲዝናና አይፈቅዱም ነበር፡፡

አንድ ቀን በመዝናናት ላይ እያሉ ባልተጠበቀ አደጋ በድንገት መርከቧ ተናወጠችና መስጠም ጀመረች፡፡ ነጮቹ በፍርሃት ተሰበሱቡና ምን እናድረግ ሲሉ፣ አንዱ፣ “ጥቁሮቹ የሚያደርጉትን እናድረግ” በማለት መከረ፡፡ ግራ የገባው ሌላኛው፣ “ጥቁሮች የሚያደርት ምንድን ነው?” ሲለው፤ “ጥቁሮችማ ሁል ጊዜ በመከራ ውስጥ ስላሉ እንደጸለዩ ነው፡፡ እኛም ዛሬ መከራ ውስጥ ስላለን እንጸልይ!” በማለት አብራራ፡፡

እነዚህ ነጮች ችግራቸው፣ በመካከላቸው ማንም ሰው ከዚህ በፊት ጸልዮ የሚያውቅ ሰው ስለሌለ ጸሎት የሚያደርስ ጠፋ፡፡ ትዝ ሲላቸው በመርከቢቱ ውስጥ ለአብሳይነት የተቀጠረ አንድ ጥቁር እንዳለ አስታወሱ፡፡ ይህ ጥቁር በመርከቧ የታችኛው ክፍል ተዘግቶበት ለማብሰል ብቻ ነው የሚጠቀሙበት፡፡ ወደላይኛው ክፍል እንዲመጣ በፍጹም ባይፈቀድለትም ለዚያ ጊዜ ግን ለጸሎት ሲሉ ህጋቸውን በመጣስ አስጠሩት፡፡

ይህ ጥቁር ግራ ገብቶት እየተደናበረ መጣ፡፡ እንዳይመጣ በማስጠንቀቂያና በዛቻ ወደተነገረው ቦታ በክብር መጠራቱ አስገርሞታል፡፡ ፊቱ ግን ሊፈታ አልቻለም፤ ምክንያቱም መልቀቅ የማይፈልገው የብዙ አመት የመገለል መራራነት ውስጡ አለ፡፡

ቶሎ ጸሎቱን እንዲያደርግ ሲያጣድፉት እንዲህ አለ፣ “ፈጣሪ ሆይ፣ በራበኝ ጊዜ ወደ ምግብ ቤት ለመመገብ ስሄድ፣ ምልክቱ ለነጮች ብቻ ይላል፡፡ ወደ ሕዝብ መጸዳጃ ቦታ ስሄድ፣ ምልክቱ ለነጮች ብቻ ይላል፡፡ እዚህም መርከብ ውስጥ ወደላይኛው መዝናኛ ክፍል ለመምጣት ሞክሬ፣ ምልክቱ፣ ለነጮች ብቻ ያላል፡፡ ሁሉም ነገር ለነጮች ከሆነ፣ ፈጣሪ ሆይ! አሁን የምጸልየው ጸሎት ምንም እንኳን ኃይማኖቴ ካስተማረኝ ትምህርት ጋር ባይስማማም እባክህ ስማኝ፣ ሁሉም ነገር ለነጮች ብቻ ሲባል እንደከረመው ሁሉ፣ ይህች መርከብ ስትሰጥም የሚከሰተው ችግር ሁሉ ለነጮች ብቻ እንዲሆን እለምንሃለሁ”፡፡

ማንኛውም ሕብረተሰብም ሆነ ግለሰብ (እኛንም ጨምሮ) ከውስጡ የሚያወጣውን ሃሳብ በሚገባ ካጤንነው አምቆ የያዘውን ስሜት ጠቋሚ ነው፡፡ ማንኛውም በውስጣችን አምቀን የያዝናቸው አሉታዊ ስሜቶች በየጊዜው በትክክለኛው መንገድ ካላናፈስናቸውና ካልተነፈሱ በየእለት ንግግራችንና ተግባራችን መገለጣቸው አይቀርም፡፡

አየህ ያልተናፈሰና የታመቀ የመራራነት ስሜት ምንም ነገር ከማድረግ እንዳንመለስ “በቂ ምክንያት” ይሰጠናል፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ ያልተናፈሰ መራራነት፣ “የማድረግ መብቴ ነው” እና “የይገባቸዋል” ስሜትን በውስጣችን የመፍጠር ጉልበት ስላለው ከትክክለኛው ጎዳና ያወጣናል፡፡ ቤተሰብ መክሮ ያሳደገን ሌላ፣ ንግግራችንና ስራችን ግን ሌላ … ኃይማኖታችን ያስተማረን ሌላ ንግግራችንና ስራችን ሌላ … ማድረግ እንደሚገባን የምናውቀው እውነታ ሌላ፣ የእኛ ተግባር ግን ሌላ … የሚሆነው በውስጣችን የተጠራቀመ መራራነት ሲኖረን ነው፡፡

ለመራራነት ሊኖረን የሚገባ ብቸኛ ምላሽ ከውስጣችን ማውጣት ብቻ ነው፡፡ ያማረሩህ ቤተሰቦች፣ ፍቅረኛህ፣ አለቃህ፣ የአካባቢህ ባለስልጣን፣ የሕዝብ አገልግሎት መስሪያ ቤት ሰራተኞች፣ ዘረኝት የተጠናወታቸው የሃገርህ ዜጎች . . . ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ይህ መራራነትህ በክፉ ቃላትና በጭካኔ ተግባር ከመገለጡ በፊት አናፍሰው፣ አስተንፍሰው! የእነሱ ሰለባ ከመሆን ይልቅ ከዚያ በላይ እንደሆንክ ራስህን አሳምን፣ አቅጣጫ ቀይር፣ ተሽለህ ተገኝ፡፡ ይህንን ማድረገ ከባድ የሆነ ነገር ነው፤ ነገር ግን ምርጫው ይህ ብቻ ነው፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

አዲስ የtelegram (online) ስልጠና!

“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ባለፈው ከነበረን የtelegram (online) ስልጠና በኋላ ባደረግነው ጥናት አብዛኛዎቻችሁ በየሶት ወሩ ስልጠና እንዲሰጥ በጠየቃችሁት መሰረት የተዘጋጀ!

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ከመወሰናችሁ በፊት!

ዛሬ የምትኖሩት ኑሮ የትናንትና ምርጫና ውሳኔያችሁን አመልካች ነው፡፡ የዛሬው ደግሞ የነገውን ኑሮ ይወስናል፡፡ እናንተ ባትመርጡና ባትወስኑ እንኳን እሱ በራሱ “ያለመምረጥ ውሳኔ” ይባላል፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲወስኑላችሁ የመምረጥ ውሳኔ!

አንድን ነገር የማድረግ ወይም የመተው ውሳኔ ሲኖርባችሁ፣ ከአንድ ሰው ጋር የመቀጠል ወይም የመለየት ውሳኔንም ስትጋፈጡ፣ መመለስ ያለባችሁ የመጀመሪያ ጥያቄ፣ “ይህንን ውሳኔ የግድ መወሰን ያለብኝ ጊዜ መቼ ነው?” የሚለውን ነው፡፡

የግድ ለመወሰንና ለመቁረጥ የተወሰነ ጊዜ ካላችሁ አሁኑኑ መወሰን እንደሌለባችሁ አስታውሱ፡፡

• መውሰድ የምትችሉትን ያህል ጊዜ ውሰዱ - ይህንን ማድረግ ጊዜ በራሱ የሚያሳያችሁን እውነታ የማየትን እድል ይሰጣችኋል፡፡

• ማሰብ የሚገባችሁን ሁሉ አስቡ - ይህንን ማድረግ ስሜታችሁን በማረጋጋት ውሳኔያችሁ ስሜታዊ ከመሆን ይልቅ ምክንያታዊ እንዲሆን ያግዛችኋል፡፡

• ማማከር የሚገባችሁን ተገቢ ሰው ሁሉ አማክሩ - ይህንን ማድረግ እናንተ ያላያችሁትን ሌላ ጎንና ገጽታ ከጥበበኛ መካሪ እንድታገኙ መንገዱን ያመቻችላችኋል፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የግል ሕይወትን ማደራጀት!

ዘመኑ የሚጠይቀው አይነት የተደራጀ ሕይወት መኖርና ተግባር ማከናወን ከፈለጋችሁ እነዚህ ጥያቄዎች መመለስ የግ ነው፡-

1. የግል ሕይወቴን እንዴት ላደራጀው?

2. ሃሳቤን እንዴት መስመር ላይዘውና ላደራጀው?

3. ማሕበራዊ ሕይወቴን እንዴት በተደራጀ መልኩ ልያዘው?

4. ጊዜዬን እንዴት ላደራጀውና ለስኬት ልጠቀምበት?

5. ሃብቴን እንዴት በማደራጀት ላሳድገው?

6. የየእለት ተግባሮቼን እንደት ላደራጃቸውና ውጤታማ ላድርጋቸው?

በዚህ ርእስ ላይ ወሳኝ የሆኑ የክህሎት ግንዛቤዎችን የሚሰጣችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና ዛሬውኑ ተመዝገቡ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ከዶ/ር ኢዮብ በሚከተሉት መንገዶች አገልግሎትን ማግኘት ትችላላችሁ

1. ጥያቄ እና መልስ

በዶ/ር ኢዮብ በየቀኑ ማለዳ በነጻ በሚሰጡት ትምህርቶች አማካኝነት ጥያቄ ካላችሁ በግሉ inbox በማድረ ለጥያቄያችሁ በነጻ መልስን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

2. የምክር አገልግሎት

በአንዳንድ ግራ በገባችሁ የሕይወት ሁኔታዎች ላይ የአንድ ወይም የተወሰኑ የምክር ክፍለ ጊዜያት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ጥያቄ ለማቅረብና መረጃ ለማግኘት inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

3. ስልጠና

በቴሌግራም (live) በሚሰጠው ስልጠና ላይ በመመዝገብ ስልጠናውን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ስልጠና ለመውሰድ በመተላለፍ ላይ ያለውን ማስታወቂያ በመመልከት በመመሪያው መሰረት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

4. የቡድን የአካል (in person) ስልጠና

ከጓደኞቻችሁ ጋር ቁጥራችሁ ከ10 ባላነሰ ሁኔታ በግሩፕ በመደራጀት ዶ/ር ኢዮብን በማግኘት ስልጠናን መውሰድ ትችላላችሁ፡፡

5. ኮቺንግ

ከዶ/ር ኢዮብ ጋር ለተወሰኑ ሳምንታት በግል ሕይወታችሁ፣ በስራችሁና በመሳሰሉት ዘርፎች ላይ የኮቺንግ አገልግሎት መቀበል ትችላላችሁ፡፡ ይህንን ጥያቄ ለማቅረብና መረጃ ለማግኘት inbox ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

ለዶ/ር ኢዮብ መልእክት ለመላክ የሚከተለውን ይጠቀሙ

/channel/DrEyobmamo

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ማንነት ሲጨመቅ!

“ሎሚ ትክክለኛ ማንነቱ እና መራራው ጣእሙ የሚወጣው ሲጨመቅ ነው” ይባላል፡፡

የሚያጋጥማችሁ ነገርና የምትገቡበት ሁኔታ የውስጥ ማንነታችሁን ያወጣዋል እንጂ የሌላችሁን ማንነት አይሰጣችሁም፡፡

የማንነት ለውጥ ሆን ተብሎ ተሰርቶበት የሚመጣ ነገር ነው፡፡

ለምሳሌ . . .

• ገንዘብ ማግኘት ለጋስም ስግብግብም አያደርገንም፣ በውስጣችን የነበረውን ለጋስነት ወይም ስግብግብነት እድል ሰጥቶ ነው የሚያወጣው፡፡

• ማሕበራዊ ሚዲያ የመጠቀም መድረክ አስተማሪም ተሳዳቢም አያደርገንም፣ በውስጣችን የነበረውን አስተማሪነት ወይም ተሳዳቢነት እድል ሰጥቶ ነው የሚያወጣው፡፡

• በሰው መተው እና ብቻ መሆን ጠንካራም መራራም አያደርገንም፣ በውስጣችን የነበረውን ጠንካራን ወይም መራራነት እድል ሰጥቶ ነው የሚያወጣው፡፡

• ስልጣን ማግኘት ትሁትና ሰው ጠቃሚም ሙሰኛና በሰው ተጠቃሚ አያደርገንም፣ በውስጣችን የነበረውን ጠቃሚነት ወይም ጥቅመኛነት እድል ሰጥቶ ነው የሚያወጣው፡፡

ምንም አይነት ነገር ከማግኘታችሁና የትኛውም ሁኔታ ውስጥ ከመግባችሁ በፊት ራሳችሁን ፈትሹ፣ ራሳችሁ ላይ ስሩ!

ራስ ላይ መስራት ማለት . . .

1. ጨዋ የሆነ፣ የከበረ እና ለሕብረተሰቡ የሚጠቅምን ዓላማ መያዝ

2. ለዚያ የከበረ ዓላማ የሚጥን ባህሪይ ላይ መስራት

3. ለዚያ ዓላማ የሚመጥን ዲሲፕሊን ማዳበር
ማለት ነው፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ከማስተላለፍ ወደ ማስቀረት ?!

አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን ለሌላ ቀን ስታስተላልፏው ቀስ በቀስ ተዘንግተው ወደ መቅረት ደረጃ እንዳይደርሱ፣ አሁኑኑ መደረግ ያለባቸውን ነገሮች ዛሬውኑ አድርጓቸው!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ካላችሁ ነገር ጀምሩ!

ያለፈው ታሪካችሁ የሰጣችሁ ልምድና ያስተማራችሁ ትምህርት አላችሁ፡፡ እሱን ለወደፊት ስኬታማነት እንዴት እንደምትጠቀሙና እንደምታተርፉበት በማሰብ ከእሱ ጀምሩ!

ዛሬ የሚባል ፈጣሪ የሰጣችሁ ጊዜ አላችሁ፡፡ እሱን በምን መልኩ እንደምትጠቀሙበትና እንደምታተርፉበት በማሰብ ከእሱ ጀምሩ!

ነጋችሁን ስታስቡ መሆንና ማድረግ የምትፈልጉት ነገር በውስታችሁ አለ፡፡ እሱን እንዴት እንደምታሳድጉትና ትርፋማ እንደምታደርጉት በማሰብ ጀምሩ፡፡

መልካም እሁድ!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የብዙ ሰዎች ጥያቄ!

ቁጥራችሁ ብዙ የሆናችሁ ሰዎች በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸውን መርሆች ከክርስትና እምነት (መጽሐፍ ቅዱስ) አንጻር መማር እንደምትፈልጉ inbox እያረጋችhuልኝ በመሆኑ ይህንን መልስ እሰጣለሁ፡፡

በአጠቃላይ የምሰጣቸው ትምህርቶች አቀራረባቸው በሁለት ይከፈላል፡-

1. እምነት-ተኮር (Faith-Based)

2. እሴት-ተኮር (Value-based)

እንደምታዩት ሁሉ፣ በዚህ ቻናል ላይ የምለቃቸው ትምህርቶች እሴት-ተኮር (Value-based) ናቸው፡፡

ይህ ማለት የማንኛውም እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ለሕይወቱ የሚጠቅሙ ተግባራዊ መመሪያዎችን የሚያገኝባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡

እምነት-ተኮር ትምህርቴን ለምትፈልጉ ወጣቶች በተለይ ለወጣቶች በቅርቡ የጀመርኩት የmentorship network ስላለና ለእሱም ቻናል ስለከፈትኩ እዚያ በመቀላቀል ያንን ትምህርት መከታተልና ወደፊትም በአካል የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ መካፈል ትችላላችሁ፡፡

ከዚህ በታች ባለው link በመጠቀም ቻናሉን join አድርጉ፡፡

/channel/impactyouthmentorship

Dr. Eyob Mamo

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

Be intentional! Be proactive!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ክህሎት እና ዲሲፕሊን

ሕይወትን የማደራጀት ጉዞ ሁለት ወሳኝ ልምምዶችን የጠይቃል፡- 1) ክህሎትን፣ እና 2) ዲሲፕሊንን

የሕይወታችንን አቅጣጫም ሆነ የየእለት ተግባሮቻችንን ከየት ጀምረን ወደ የት እንደምንወስደው፣ መቼ ምን ማድረግ እንዳለብን ቅደም ተከተሉን ማወቅ፣ የማቀድና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ክህሎትን የሚጠይቁ ልምምዶች ናቸው፡፡

ሆኖም፣ የምደርገውን በሚገባ ብናውቅም እንኳን፣ አንድ ነገር ከዛሬ ነገ እያሉ ከማስተላለፍ ይልቅ በወቅቱ መጀመር፣ የጀመርነውን ሳያቆሙ መቀጠል፣ ከስሜት ይልቅ በምክንያታዊነት መኖርና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከዲፕሊን ጋር የተያዙ ናቸው፡፡

እነዚህን እና መሰል የግል ሕይወትን አደረጃጀት በሚገባ መገንዘብ ከፈለጋችሁ የተዘጋጀው ስልጠና ይመለከታቸኋልና ዛሬውኑ ተመዝገቡ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡- “የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የግል ሕይወትን ማደራጀት!

ዘመኑ የሚጠይቀው አይነት የተደራጀ ሕይወት መኖርና ተግባር ማከናወን ከፈለጋችሁ እነዚህ ጥያቄዎች መመለስ የግ ነው፡-

1. የግል ሕይወቴን እንዴት ላደራጀው?

2. ሃሳቤን እንዴት መስመር ላይዘውና ላደራጀው?

3. ማሕበራዊ ሕይወቴን እንዴት በተደራጀ መልኩ ልያዘው?

4. ጊዜዬን እንዴት ላደራጀውና ለስኬት ልጠቀምበት?

5. ሃብቴን እንዴት በማደራጀት ላሳድገው?

6. የየእለት ተግባሮቼን እንደት ላደራጃቸውና ውጤታማ ላድርጋቸው?

በዚህ ርእስ ላይ ወሳኝ የሆኑ የክህሎት ግንዛቤዎችን የሚሰጣችሁ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋልና ዛሬውኑ ተመዝገቡ፡፡

የስልጠናው ርእስ፡-
“የግል ሕይወትን ማደረጃት” / "Organizing Personal Life"

ስልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Dr. Eyob Mamo

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የድግግሞሽ አዙሪት

በየቀኑ እየተነሳችሁ ከቤት ወጥታችሁ በሚኖራችሁ ስምሪት፣ የምትሰሩት ስራ፣ የምትውሉበት አካባቢ፣ የምታገኟቸው ሰዎችና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከሰለቻችሁና የትም እንደማያራምዳችሁ ካሰባችሁ “የድግግሞሽ አዙሪት” ውስጥ እንዳላችሁ ላስታውሳችሁ፡፡

የድግግሞሽ አዙሪት ምልክቶች፡-

1. ተስፋ መቁረጥ፣

2. ሁሉም ነገር የማስጠላት ስሜት፣

3. ነገሮች እንደማይለወጡ ማሰብ፣

4. ኋላ የመቅረት ስሜት እና የመሳሰሉት ስሜቶች ናቸው፡፡

ከዚህ አዙሪት ለመውጣት መውሰድ የምንችላቸው እርምጃዎች፡-

1. ራእያችን ወይም የሕይወታች ዋና ዓላማ ምን እንደሆነ መለየት፣

2. ከራእያችን አንጻር ወደ አዲስ ነገር ለመግባት መወሰን፣

3. በወሰንነው ውሳኔ ዙሪያ በየእለቱ የሚወሰዱን ትንንሽ እርምጃዎች መጀመር፣

4. የጀመርነውን እርምጃ በፍጹም አለማቆም፣

5. በምክር ሊያግዘን የሚችል ሰውን በመለየት ምክርን መቀበልና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የስልጠና ምዝገባ!

የስልጠናው ርእስ ምንድን ነው?
“የግል ሕይወትን ማደራጀት”
(Organizing personal life)

ስልጠናው የሚሰጠው በማን ነው?
በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

ስልጠናው የሚሰጠው በምንድን ነው?
ስልጠናውን ለመውሰድ ለተመዘገቡ ሰዎች በተዘጋጀው የቴሌግራም ግሩፕ በተጠቀሱት ቀናት live ነው፡፡

ስልጠናው የሚሰጠው መቼ ነው?
ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29 (ለአምስት ኃሙሶች)

ስልጠናው የሚሰጠው በስንት ሰዓት ላይ ነው? አምስቱም ኃሙሶች ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00 (በኢትዮጲያ አቆጣጠር)

የስልጠናው ክፍያ ስንት ነው?
ለአምስቱም ኃሙሶች ጠቅላላ ክፍያ አንድ ሺህ ብር (1,000 ብር) ብቻ

ለስልጠናው እንዴት መመዝገብ እችላለሁ?
በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግና ፍላጎትን በመግለጽ የምዝገባ ሂደቱን መመሪያ በመቀበል

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ውዱ የተባለ ክፍያ የጊዜ ክፍያ ነው!

ሕይወታችሁን መልክ እያስያዛችሁ ካልሄችሁና በሚገባ ካላደራጃችሁት የምትከፍሉት ትልቁ ዋጋ ጊዜያችሁን የማባከን ዋጋ ነው፡፡

ጊዜያችሁ አንዴ ካለፈ፣ በሌላ በምንም ነገር የማይተካና የማይመለስ ሃብታችሁ ነው፡፡

ይህንን ውብ የሆነ የፈጣሪ ስጦታ በተገቢው መልኩ የምትይዙት አመለካከታችሁ፣ እቅዳችሁን፣ ተግባራችሁ . . . በማደራጀት ነው፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ስልጡን እንድትሆኑ በርካቶች እየተመዘገቡ ያሉበት አንድ ስልጠና ተዘጋጅቶላችኋል፡፡

ልጠናው የሚሰጠው፡- በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

የስልጠናው ቀን፡- ጥር 1፣ 8፣ 15፣ 22 እና 29 (ለአምስት ኃሙሶች)

የስልጠናው ሰዓት፡- ከምሽቱ 3፡00 እስከ 5፡00

ስልጠናው የሚሰጥበት መንገድ፡- በonline (telegram live)

የስልጠናው ክፍያ፡- አንድ ሺ (1,000) ብር ብቻ

ለመመዝገብ፡- በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ

Читать полностью…
Subscribe to a channel