dreyob | Unsorted

Telegram-канал dreyob - Dr. Eyob Mamo

80341

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

Subscribe to a channel

Dr. Eyob Mamo

ጊዜህን በቁጥጥርህ ስር አድርግ

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ትግላችሁ!

“ዛሬ የምታልፉበት ችግር እና ትግል ነገ ለመኖር የምትፈልጉትን ትልቅ ራእይ የምትሸከሙበትን ጉልበት እያዳበረላችሁ ነው” (Meaningful Life)


በርቱ!!!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

መታገሳችን ላይቀር!

በሕይወታችሁ እንዲገባ የፈቀዳችሁለት ሰው በሙሉ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ይጎዳችኋል፡፡ ተጎድታችሁም ቢሆን አብሮነቱን የምትፈልጉትን ሰው የመለየቱ የቤት ስራ ግን የእናንተው ነው፡፡ መጎዳታችሁ ላይቀር በትክክለኛው ሰው ተጎዱ!

የምትሰሩት ማንኛውም ስራ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከባድ ገጽታ አለው፡፡ ከብዷችሁም ቢሆን መስራት የምትፈልጉትን የስራ አይነት የመለየቱ የቤት ስራ የእናንተው ነው፡፡ መሸከማችሁ ላይቀር የትክክለኛውን ስራ ከባድነት ተሸከሙ!

የምትኖሩበት ሃገር ወይም ሰፈር የትም ሆነ የትም በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ አስቸጋሪ ጎን አለው፡፡ አስቸጋሪ ጎኑን ታግሳችሁ የምትኖሩበትን አካባቢ የመለየቱ የቤት ስራ የእናንተው ነው፡፡ ከታገሳችሁ አይቀር የትክክለኛውን የኑሮ አካባቢ ታገሱ!

ሁል ጊዜ ተነጫንጨንና ሁሉን ነገር ሸሽተን አንዘልቀውም!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

አቅርቦት ወይስ አብሮነት?

ለልጆች አቅርቦት ሰጥተን የእኛን አብሮነት ስናሳጣቸው!


የብዙ ወላጆች ውጥረት ለልጆች አቅርቦት ለማምጣት ሲሯሯጡ ራሳቸውንና ጊዜያቸው ከማቅረብ የመጉደል ሁኔታ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ለልጆች ሁሉን አሟልተን እኛነታችንንና እሴቶቻችንንና የማሳጣትን ሁኔታ ይወልዳል፡፡

በዚህና በመሰል ሂደቶች ላይ በሚገባ ለመብሰል የሚረዳ መጽሐፍ ነውና ተጠቀሙ፡፡ (መጽሐፉ በየመደብሩ ይገኛል)

ሃሳቡን ከዚህ በታች ታገኛላችሁ

ማውጫ

የመጽሐፉ መግቢያ - ገጽ 7

ክፍል አንድ - ልጅ የመውለድ ጉዳይ - ገጽ 9
1. “መቼ እንውለድ?” - ገጽ 11
2. “ለምን መውለድ አልቻልንም?” - ገጽ 13
3. “እንዴት ተጸነሰ?” - ገጽ 15

ክፍል ሁለት - ልጆችን መቆጣጠር እና ማሳደግ - ገጽ 17
1. የፈላጭ-ቆራጭነት አቀራረብ - ገጽ 19
2. ልቅ አቀራረብ - ገጽ 22
3. የገለልተኝነት አቀራረብ - ገጽ 25
4. ተጽእኖ አሳዳሪ አቀራረብ - ገጽ 28

ክፍል ሶስት - ልጆችን ማወቅ እና መቀበል - ገጽ 31
1. የልጆችን ውልደተ-ማንነት መገንዘብ - ገጽ 33
2. የልጆችን እድገተ-ባህሪ መገንዘብ - ገጽ 36
3. ልጆችን ካለምንም ቅድመ-ሁኔታ መቀበል - ገጽ 39

ክፍል አራት - ልጆች የሚማሩባቸው መስኮች - ገጽ 42
1. ከማሕበራዊ “ሚዲያ” ይማራሉ - ገጽ 44
2. ከአቻዎች ይማራሉ - ገጽ 46
3. ከትምህርት ቤት ይማራሉ - ገጽ 48
4. ልጆች ከወላጆች ጋር ባላቸው መስተጋብር ይማራሉ - ገጽ 50
5. ወላጆች እርስ በእርሳቸው ካላቸው መስተጋብር ይማራሉ - ገጽ 52
6. ወላጆች ከኑሯቸው ጋር ካላቸው መስተጋብር ይማራሉ - ገጽ 54
7. ከወላጆች ማሕበራዊ መስተጋብር ይማራሉ - ገጽ 55

ክፍል አምስት - ልጆችን ማስተማር የሌለብን ነገሮች -ገጽ 58
1. በሌላ ልጅ እንዳይበለጡ ተፎካካሪነትን የማስተማር ስህተት - ገጽ 60
2. ስህተት ጠቋሚነት ትክክል እንዳልሆነ የማስተማር ስህተት - ገጽ 63
3. አሉታዊ ስሜታቸውን እንዳይገልጹ የማስተማር ስህተት - ገጽ 66
4. ሰዎች ቅር እንዳይሰኙባቸው የማስተማር ስህተት - ገጽ 69
5. የትምህርት ውጤትንና ስኬታማነትን የማምታታት ስህተት - ገጽ 72
6. ፍላጎታቸውን ሁሉ ወዲያው የመሟላት ስህተት - ገጽ 75
7. እንዳይሰለቻቸው አጉል የመጠንቀቅ ስህተት - ገጽ 78
8. ለልጆች የገቡትን ቃል ያለማክበር ስህተት - ገጽ 81
9. ጓደኝነትን ከወላጅነት ጋር ያለማመዛዘን ስህተት - ገጽ 84
10. በልጆች አለመግባባት በአድሎ ጣልቃ የመግባት ስህተት - ገጽ 87
11. በልጆች ላይ የሚያንቋሽሹ ቃላትን የመጠቀም ስህተት - ገጽ 90
12. ዲሲፕሊንን አንድ ወጥ ያለማድረግ ስህተት - ገጽ 93
13. ሁል ጊዜ ችግራቸውን የመጋፈጥ ስህተት - ገጽ 96
14. ከልጆች ፍጽምናን የመጠበቅ ስህተት - ገጽ 99

ክፍል ስድስት - የልጆችን ብልህነት መለየትና መደገፍ - ገጽ 102
1. የብልህነት ዝንባሌህን መለየት - ገጽ 104
2. የግል ብልህነትን የማወቅ ወሳኝነት - ገጽ 109
3. ብልህነትና ማሕበራዊ ሃላፊነት - ገጽ 114
4. ብልህነትና የልጆች አስተዳደግ - ገጽ 118

ክፍል ሰባት - ልጆችን ከመገፋት መጠበቅ - ገጽ 123
1. “ካልተፈለገ” ጽንስ የሚነሳ መገፋት - ገጽ 125
2. በእናት ላይ ከሚደርስ ጉዳት የሚመጣ መገፋት - ገጽ 128
3. በልጅነት መገፋት - ገጽ 131
4. በአቻዎች መገፋት - ገጽ 136
5. ለመገፋት ተጋላጭ የሆኑ ልጆች - ገጽ 140

ማጠቃለያ - የልጆችን ለውጥ መከታተል! - ገጽ - 143

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ሕይወትን ማጣጣም!

“የትምህርታችሁን፣ የስራችሁን፣ የንግዳችሁን፣ ሰዎችን የማስደሰታችሁን . . . ሁኔታ ለማሳካት ስትሯሯጡ ሕይወትን መኖርና ማጣጣምን እንዳትዘነጉ!” (Life Principles)


ሕይወትን ማጣጣም ማለት ከራስ ጋር ማሳለፍ፣ አልፎ አልፎ አረፍ ማለት፣ የሚያዝናኑንን ነገሮች ለማድረግ ጊዜን መውሰድ፣ ከቤተሰብ ጋር በቂ ጊዜን ማሳለፍ . . . እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡ በተጨማሪም ለሌሎች ሰዎች መፍትሄ ሰጪ የሆነን አንድ ራእይ መከተል አጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡

ይህንን ሂደት በሚገባ ለመገንዝብ የሚረዳ ስልጠኛ ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ስላዘጋጀሁ፣ ቀደም ሲል የተለጠፈው ፖስተር ላይ ያለውን መረጃ ይመልከቱ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ትርጉም የለሽ ጸጸት

አንዳንዶቹ በጸጸት ጊዜአችንን የምናባክንባቸው ሁኔታዎች ምንም ትርጉም የማይሰጡ ጸጸቶች ናቸው፡፡ ምናልባት የተከሰተው ሁኔታ ያመጣብንን ተጽእኖ ለማረም አንዳንድ እርምጃዎች የመውሰድ እድሉ ቢኖረንም የተከናወነውን ነገር እንዳይከናወን ለማድረግ በወቅቱ ምንም አቅም ስላልነበረን ጸጸቱን ትርጉም የለሽ ያደርገዋል፡፡

ራስህን በእንደዚህ መሰሉ የጸጸት ሁኔታ ስታገኘው ልትወስዳቸው የምትችላቸው እርምጃዎች በርካታ ሲሆኑ ለመንደርደሪያ ያህል የሚከተሉትን መጠቀም ትችላለህ፡፡

1. የጉዳት ስሌት ስራ

የሆነው ነገር አንዴ ሆኗል፤ እንደገና ተመልሰህ እንዳይሆን ማድረግ አትችልም፡፡ የሆነውም ነገር የሆነው ከአንተ ቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ ነው፡፡ አሁን ማተኮር ያለብህ በሆነው ነገር ምክንያት የመጣው ውጤት ላይ ነው፡፡ ከመጸጸት ይልቅ በመጀመሪያ መለየት ያለብህ በሆነው ሁኔታ ምክንያት በአንተ ላይም ሆነ በሌላ ሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ካለ ያንን መለየት ነው፡፡ አየህ፣ በዚህ ትርጉም የለሽ ጸጸቶች ብለን በሰየምነው ክፍል ውስጥ የሚጠቃለሉ ለጸጸት የሚዳርጉ ሁኔታዎች በሙሉ የሚመደቡት ከአንተ ቁጥጥር ውጪ ከሆኑት ክፍል ነው፡፡ እነዚህን ከቁጥጥር ውጪ የሆኑትን ያለፉ ሁኔታዎችን ወደኋላ ተመልሰህ ልትደርስባቸው አትችልም፡፡ ያመጡትን ጉዳት ግን ልትደርስበትና መፍትሄ ልትፈልግለት ትችላለህ፡፡

2. የጥቅም ስሌት ስራ

ከላይ ከተጠቀሰው “የጉዳት ስሌት” ከተሰኘው ሃሳብ ሌላ ገጽታ ያለው የስሌት ሁኔታ ከተከሰተው “ትርጉም የለሽ” የጸጸት ሁኔታ የተገኘ ማንኛውም አይነት ጥቅም ካለ ያንን ለማግኘት የመሞከር ሂደት ነው፡፡ ምንም እንኳን ከአቅምህ በላይ በሆኑ ክስተቶች ምክንያት ብትጸጸትባቸው ምንም ለውጥ የማታመጣላቸው ሁኔታዎች ቢከሰቱም ከእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የምታገኘው ጥቅም ካለ እንዳያልፍህ በሚገባ ልታስብበት ይገባል፡፡ ብልህ ሰዎች በሕይወታቸው ከሚያልፉባቸው ከማናቸውም አይነት ልምምዶች ውስጥ ለወደፊት ኑሯቸው ጥበብን በመቅሰም የታወቁ ናቸው፡፡ በእንደዚህ አይነት ብልህ ሰዎች ሕይወት አንድም የሚወድቅ ልምምድ የለም፡፡ ከሁሉም ነገር ውስጥ ለትምህርታቸው የሚሆንን ነገር ፈልፍሎ የማውጣት ብቃቱ አላቸውና፡፡

3. የወደፊት እቅድ አውጣ

ያለፈው ታሪክህ ምንም ይሁን፤ እዚህ የደረስከው በየትም አልፈህ ይሁን፣ ዋናው ቁም ነገር ዛሬ የምትወስነው ውሳኔ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ሆነህ የትናንትናውን አስመልክቶ ትክክለኛ ቆጠራ አድርገህ በውጤቱ ሳትደናገጥ በምን መልኩ ወደፊት ለመሄድ እንደምትችል ማቀድ ትችላለህ፡፡ ከላይ በተጠቀሱት ነጥቦች እንደተገለጠው ካለፉት የሕይወት ምእራፎችህ የደረሱብህን ጉዳቶችና ያገኘሃቸውን ጥቅሞች በሚገባ ካሰላህ በኋላ ለነገ የሚሆኑ አዳዲስ ምእራፎች መጻፍ መጀመር ትችላለህ፡፡ በዚህ መልኩ ራስህን “ቢዚ” ማድረግ ስትጀምር ከአንተ አቅም በላይ በሆኑ መንስኤዎች ምክንያት ስለተከሰቱ ነገሮች መጸጸት በማቆም ወደፊት መገስገስ ትጀምራለህ፡፡

“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ሰላማችሁ ይብዛ የማሕራዊ ገጾቼ ተከታታዮች!

ወደ አዲሱ ዓመት ስንገባ ራዕያችንን ጥርት ባለ መልኩ በማየት መውሰድ የምንችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በማወቅ እንድንሻገር ይህንን የአንድ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

ለዚህ ስልጠና መመዝገብ ከፈለጋችሁ ተጨማሪ የምዝገባ መመሪያ በግላችሁ እንዲላክላችሁ በTelegram እና በFacebook የግል መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን መግለጽ ትችላላችሁ፡፡

Telegram፡
@DrEyobmamo

Facebook፡
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

ለመረጃ ስልክ፡
0947 33 95 55

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የእናንተ የሆነውና ያልሆነው

“የእናንተ ያልሆነውን ነገር ተቀብላችሁ አያስተናገዳችሁ በቆያችሁ ቁጥር የእናንተ የሆነው ነገር ወደ እናንተ እንዳይመጣ ታዘገዩታላችሁ” (Daily Life)


የያዛችሁት ዓላማ፣ የሰው ለሰው ግንኙነትም ሆነ ሌላ ነገር፣ የእናንተ እንዳልሆነ እያወቃችሁት መልቀቅ ወይም መላቀቅ ካልቻላችሁ ወይም ካልፈለጋችሁ፣ የእናንተ የሆነው ዘላቂ ነገር እየዘገየ፣ ምናልባትም አንደኛውንም እየቀረ እንደሚሄድ አስታወሱ፡፡

በዚህ ምክንያት ነው በርካታ ሰዎች የእነሱ ያሆነውን ሕይወት ኖረውና ከእነሱ ያነሰን ነገር ተቀብለው የሚያልፉት፡፡

በሕይወታችሁ የምትፈልጉትን ነገር እወቁ! ዓላማችሁን በማወቅ ተንቀሳቀሱ! ራእያችሁን ንደፉ፣ ጻፉና በእሱ ተመሩ!

እግረ መንገዴን ራእያችሁን በማወቅ መኖር እንድትጀምሩ ወደሚያግዛችሁ ስልጠኛ ጋብዣችኋለሁ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ሲፈልጓችሁና ሳይፈልጓችሁ

ሰዎች ደግመውና ደጋግመው እንደሚፈልጓችሁ ከነገሯችሁ፣ በተቻላችሁ መጠን ለመስማት እድል ስጧቸውና ከዚያም ፍጎታችሁንና ውሳኔያችሁን ንገሯቸው፡፡ ይህ ተግባር፣ “ለሰዎች ተገቢውን ዋጋ መስጠት” ተብሎ ይጠራል፡፡

ሰዎች ደግመውና ደጋግመው እንደማይፈልጓችሁ ከነገሯችሁ፣ ዛሬ ነገ ሳትሉ ከሕይወታቸው ውጡላቸው፡፡ ይህ ተግባር፣ “የራስን ዋጋ ማወቅ” ተብሎ ይጠራል፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የወላዋይነት ዋጋው

“መወላወልና አለመወሰን የሚያስከፍላችሁ ውዱ ዋጋ፣ ብትወስኑ ኖሮ ልታጣጥሙት የምትችሉትን አስገራሚ ሕይወት ነው” (Growing Higher)

አንድ ነገር ትክክለኛ፣ ጠቃሚና ወቅቱ እንደሆኑን ካረጋገጣችሁ በኋላ ለነገ አታስተላልፉ፡፡ አድርጉት!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

መጥፎ ልማድ እንደምቹ አልጋ!

“አጉል ልማዶች ልክ እንደሚመች አልጋ ናቸው፤ ለመግባት ቀላል፣ ለመውጣት ግን እጅግ ከባድ ናቸው” (Quote Of The Day
)

ምንም አይነት ዋጋ ከፍላችሁም ቢሆን ማስወገድ የሚገባችሁ አጉል ልማድ ቢኖር፣ በየቀኑ ያገኛችሁትንና ያጋጠማችሁን ነገር እያስተናገዳችሁ የመኖር ሕይወትን የማስወገድ ልምምድ ዋነኛው ነው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ምንም አይነት ዋጋ ከፍላችሁም ቢሆን ማዳበር የሚገባቸሁ ልማድ ቢኖር፣ ራእይና ማወቅ፣ እቅድን ማውጣት፣ የመተግባር ዲሲፕሊንን ማዳበርና የጀመሩትን ከግብ ሳያደርሱ ያለማቆም ሁኔታ ነው፡፡

ይህንን አስገራሚ ልማድ የሕይወታችሁ ዘይቤ ለማድረግ ከፈለጋችሁ ጳጉሜ 2 ቀን የተዘጋጀው ስልጠና አያምልጣችሁ!

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ወደፊት!

“ዛሬ የደረሳችሁበት ከልምድ የመጣ የጥበብ ደረጃችሁ ያለፈው ስህተታችሁን እያሰባችሁ ራሳችሁን እንድትኮንኑ አያድርጋችሁ፡፡ ያን ጊዜ እኮ በነበራችሁ እውቀትና አቅም የምትችሉትን አድርጋችኋል” (Great Quotes)

በጸጸት ወደኋላ መመለስ የለም! ወደፊት!!!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የሚነገረውና የማይነገረው

“አፉን ዘግቶ የሚንቀሳቀስ አሳ ማጥመጃ አይዘውም” (Life Quotes)


ያረጋችሁትን፣ የምታደርጉትንና ለማድረግ ያሰባችሁትን ሁሉ ለሁሉም ሰው ከመናገር ተቆጠቡ፡፡

የትኛውን ነገር ለማንና መቼ እንደምትናገሩ ለይታችሁ እወቁ፡፡

የአብዛኛዎቹ ችግሮቻችን ምንጭ ካልተናገርነው ነገር የተነሳ ሳይሆን ከተናገርነው ነገር የተነሳ ነው፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ወስኑ!

አንዳንድ ጊዜ እኮ ለጊዜው ስሜታችሁን በጣም የሚጎዳውም ቢሆን ለውስጣችሁ ግን ዘላቂ ሰላም የሚሰጣችሁን ውሳኔ መወሰን የሚኖርባችሁ ጊዜ አለ፡፡ ወስኑት!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ራእይና ማወቅና መከተል . . .

• በሰው ነገር ጣለቃ ከመግባት ይጠብቃችኋል!

• ትክክለኛ ጓደኛና አጋር እንድትመርጡ መስፈርቱን ያስቀምጥላችኋል!

• ገንዘባችሁን ምን ላይ እንደምታውሉት መስመር ያስይዛችኋል!

• ስራ ስለሚበዛባችሁ ጊዜ አጠቃቀማችሁን ስኬታማ ያደርግላችኋል!

• ለማደግ ፍላጎት ስለሚድርባችሁ የማንበብ ዲሲፕሊንን ይፈጥርላችኋል!

• ሰዎች በእናንተ ላይ ስላላቸው አመለካከት መጨነቅ እንድታቆሙ ብርታት ይሆናችኋል!

ይህንን አስገራሚ ልማድ የሕይወታችሁ ዘይቤ ለማድረግ ከፈለጋችሁ ጳጉሜ 2 ቀን የተዘጋጀው ስልጠና አያምልጣችሁ!

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ሰላማችሁ ይብዛ የማሕራዊ ገጾቼ ተከታታዮች!

ወደ አዲሱ ዓመት ስንገባ ራዕያችንን ጥርት ባለ መልኩ በማየት መውሰድ የምንችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በማወቅ እንድንሻገር ይህንን የአንድ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ስልጠና አዘጋጅቼላችኋለሁ፡፡

ለዚህ ስልጠና መመዝገብ ከፈለጋችሁ ተጨማሪ የምዝገባ መመሪያ በግላችሁ እንዲላክላችሁ በTelegram እና በFacebook የግል መልእክት በመላክ ፍላጎታችሁን መግለጽ ትችላላችሁ፡፡

Telegram፡
@DrEyobmamo

Facebook፡
https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

ለመረጃ ስልክ፡
0947 33 95 55

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የራእይ ድንቅነት!

ራእይ ከእድሜ በላይ ያደርጋችኋል
ራእያችሁን ስታገኙት “እድሜዬ ገና ነው” ወይም “እድሜዬ አልፏል” ከሚለው የተዛባ አመለካከት አልፋችሁ ትሄዳላችሁ፡፡ ራእይ ያለንን ጊዜ እንድንጠቀም ያደርገናል እንጂ ወጣት ወይም አዋቂ መሆን ራእይን ሊሰጠን አይችለም፡፡

ራእይ ከእውቀት በላይ ያደርጋችኋል
ራእያችሁን ስታገኙት “በቂ እውቀት የለኝም” የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት ትታችሁት ትሄዳላችሁ፡፡ ራእይ ለበለጠ እውቀት እንድንጓጓ ያደርገናል እንጂ፣ እውቀት ብቻውን ባለራእይ አያደርግም፡፡

ራእይ ከገንዘብ አቅም በላይ ያደርጋችኋል
ራእያችሁን ስታገኙት “በቂ ገንዘብ የለኝም” የሚለውን የተዛባ ግንዛቤ ጥላችሁት ትሄዳላችሁ፡፡ ራእይ ገንዘብን ለማግኘት መንገድ ይጠርጋል እንጂ፣ ገንዘብ ብቻውን ራእይን አይሰጥም፡፡

ራእይ ካለፈው ታሪካችሁ በላይ ያደርጋችኋል ራእያችሁን ስታገኙት “ታሪኬ የተበላሸ ነው” የሚለውን የተጣመመ እሳቤ ገፍታችሁት ትሄዳላችሁ፡፡ ራእይ መልካም ታሪክ ይሰጣል እንጂ፣ መልካም ታሪክ ራእይን አይሰጥም፡፡

ይህንን አስገራሚ የሕይወት ዘይቤ ለመለማመድ የሚያስችላችሁና እንደ ማስፈንጠሪያ የሚያለግላችሁ ስልጠና ቅዳሜ፣ ጳጉሜ 2 ቀን ተዘጋጅቶላችኋልና ዛሬውኑ በመመዝገብ ቀድመው የተመዘገቡትን በርካታ ሰልጣኞች ተቀላቀሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

“ንቁ አቃጆቹ” ናችሁ ወይስ “ምላሽ ሰጪዎች”?

የራእይ ሰዎች “ንቁ አቃጆች” (proactive) ሲሆኑ ራእይ የሌላቸው ደግሞ “ምላሽ ሰጪው” (reactive) ናቸው፡፡

“ንቁ አቃጆች” (proactive) ሰዎች ራእያቸውንና ዓላማቸውን አጣርተው ያውቃሉ፣ በጥቃቄ እቅድ ያወጣሉ ከዚያም በእዚያ እቅድ መሰረት ስኬታማነታቸውን እየገመገሙ ከእድገት ወደ እድገት ይሸጋገራሉ፡፡

“ምላሽ ሰጪ” (reactive) ሰዎች ካለምንም የሕይወት ራእይና ዓላማ ዝም ብለው አየኖሩ፣ ለሚመጣው እድል፣ ገጠመኝና እንቅፋት ስሜታዊ ምላሽ እየሰጡ እንዲሁ ባሉበት ይረግጣሉ፡፡

ራእያችሁን በሚገባ በመለየት “ንቁ አቃጆች” ወደመሆን ለመሸጋገር ከፈለጋችሁ የቅዳሜ ጳጉሜ 2 ስልጠናዬ አያምልጣችሁ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

አቅርቦት ወይስ አብሮነት?

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

በማደግ ውስጥ ያለ ስኬት

“በኑሮ ደረጃ ስኬታማ ለመሆን መሯሯጣችሁን አረጋጉትና ራሳችሁን ማሳደግና ዋጋችሁን መጨመር ላይ ተግታችሁ ስሩ፡፡ ራሳችሁን ስታሳድጉ ሁሉም ነገር አብሮ ስለሚያድግ ስኬት ተከትሎ ይመጣል” (Growing Daily)

ራሱን በማወቅና ራእዩን በመለየት ራስን ማሳደግ ላይ ያተኮ ሰው፣ ራስን ከማሳደግ ወደሚመጣ የኑሮ ደረጃ እድገት ውስጥ መግባቱ አይቀርም፡፡

ራእያችሁን የመለየትንና የመከተልን ጉዞ ዛሬውኑ እንድትጀምሩ ላነሳሳችሁ፡፡

ይህንን ለማድረግ ወደሚያግዛችሁ ስልጠና ጋብዣችኋለሁ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ልምምጡን ለጊዜው ተወት!

የጠየቁትን ነገር ሁሉ ሰጥታችኋቸውና አድርጋችሁላቸው ምስጋና-ቢስ ለሆኑና ለእናንተ ግድ ለማይሰጣቸው ሰዎች ያንኑ ነገር ጨማምራችሁ ብትሰጧቸውና ብታደርጉላቸው የሚወዷችሁ እየመሰላችሁ የበለጠ የምትጦዙ ከሆነ በጣም ተሳስታችኋል፡፡

ሶስት የማይለወጡ እውነታዎች . . .

1. በእውነት የሚወዳችሁ ሰው ምንም ነገር ብትሰጡትም ባትሰጡትም ይወዳችኋል!

2. በእውነት የሚወዳችሁ ሰው ትንሽም ሰጣችሁት ብዙ ይወዳችኋል፣ ያመሰግናችኋል!

3. በእውነት የሚወዳችሁ ሰው በመጀመሪያም ሆነ በመጨረሻ የሚፈልገው እናንተን እንጂ የእናንተ የሆነውን ነገር አይደለም!

ልምምጡን ለጊዜው ተወት አድርጉና ያመናችሁበትን ትክክለኛውን ነገር አድረጉ!

መልካም እንቅልፍ!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ደረጃውን አንድ በአንድ!

“የደረጃው ከፍታ የሚወስዳችሁ ድረስ የመሄድን ጉዞ መጀመር ከፈለጋችሁ፣ ከፊት ለፊት ባለው ደረጃ ላይ አተኩሩ እንጂ የፎቁ ጫፍ ድረስ የሚያደርሳችሁ አጠቃላይ የደረጃዎች ብዛት ላይ አታተኩሩ” (Life Hacks)


የራእያችሁ እና የሕልሞቻችሁ ጉዞ ሩቅና ከባድ መሆኑ ላይ አታተኩሩ፡፡ የዛሬን ዛሬ መጀመርና መራመድን ተማሩ፡፡ ሌላው ቀስ እያለ ጊዜውን ጠብቆ ይመጣል፣ እንደ አመጣጡም ይሰራበታል፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

በአንተና በድህነት መካከል ያለው የእርምጃ ርቀት!

“ያለህ ገቢ ወርሃዊ ደሞዝህ ብቻ ከሆነ፣ በአንተና በድህነት መካከል አንድ እርምጃ ብቻ ነው የሚቀረው” – Warren Buffett

በአንድ መስሪያ ቤት ተቀጥረህ በታማኝነት የመስራትህ ጉዳይ ለአንተ፣ ለመስሪያ ቤቱም ሆነ ለሃገር ጠቃሚ የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የገቢህን ምንጭ ግን ከአንድ በላይ እንድታደርግ ትመከራለህ፡፡ የገቢህ ምንጭ ወርሃዊ ደሞዝህ ብቻ ሲሆን በርካታ ጉዳቶች አሉት፡፡

• ብቸኛው ገቢህ አንድ ቀን የቆመ እንደሆነ ሊደርስብህ የሚችለውን የኑሮ ቀውስ በማሰብ ትሰጋለህ፡፡

• የዘመኑ ተለዋዋጭ ሁኔታ ብቸኛው ገቢህ አንድ ቀን ሊቋረጥ እንደሚችል ጠቋሚ ስለሆነ አንድ ቀን ከተቋረጠ ድንገተኛ ችግር ውስጥ ራስህን ታገኘዋለህ፡፡

• ሌሎች የገቢ ምንጮችን ለመፍጠር በሚደረግ ጥረት ውስጥ የሚያድገው የፈጠራ ብቃትህ ይታመቃል፡፡

• የገቢህን መጠን ባለበት ይቁም፣ ይጨምር ወይም ይቀንስ የሚሉትን ወሳኝ ጉዳዮች የሚወስንልህ ቀጣሪህና ቀጣሪህ ብቻ ይሆናል፡፡

• ገቢህ ውስንና የተቆለፈ ስለሚሆን ከሚያስፈልግ ነገር (Needs) አልፈህ ለምትፈልገው ነገር (Wants) የምታወጣው የገንዘብ ነጻነት አይኖርህም፡፡

• ተጨማሪ ገቢን ስትፈጥር በምታገኘው ተጨማሪ ገቢ የተነሳ ሊመጣ የሚችለውን የገንዘብ መባዛት ታጣዋለህ፡፡

በሚገባ ካሰብክበት፣ ተገቢውን ስልጠና ከወሰድክ፣ ለሰዎች ተሞክሮ ልቦናህን ከከፈትክ፣ ባለህ በመጀመር ተስፋ ሳትቆርጥ ከተንቀሳቀስክ በአንተና በብልጽግና መካከል አንድ እርምጃ ብቻ ነው የሚቀረው፡፡

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

የራእይ ጉዞ

ራእይ ሲኖራችሁ ራእዩን ለማሳካት የምትሰሩትን ስራ ይሰጣችኋል፡፡ ይህንን ስራ ተልእኮ (ተግባር) እንለዋለን፡፡

ተልእኮ (ተግባር) ሲኖራችሁ ተግባሩ መከናወን ያለበትን የጊዜ ገደብ እንድታስቀምጡ ይጠይቃችኋል፡፡ ይህንን የጊዜ ገደብ ግብ እንለዋለን፡

ግብ ሲኖራችሁ ለተግባሮቻችሁ የጊዜ ገደብ አስቀምጣችሁላቸው የቀን ገደቡ ሳያልፍ ምን ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ማቀድ ትጀምራላችሁ፡፡ ይህንን ሂደት ደግሞ የአሰራር ስልት እንለዋለን፡፡

የአሰራር ስልት ሲኖራችሁ እንቅስቃሴ ውስጥ ገባችሁ ማለት ነው፡፡

እንደዚህ ነው ራእይ የሚወለደው፣ የሚጀመረው፣ የሚሰራውና ስኬታማ ሕይወት እንዲኖረን መንገዱን የሚጠርግልን፡፡

ይህንን አስገራሚ የራእይ ሂደት በሚገባና በጥልቀት ለመገንዘብ ከፈለጋችሁ ጳጉሜ 2 ቀን የተዘጋጀው ስልጠና አያምልጣችሁ!

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

መፍራት አቁሙና መኖር ጀምሩ!

“ፍርሃት ሞትን አያስቀረውም፣ ሕይወትን እንዳንኖራት ግን ይከለክለናል” (Naguib)


ፍርሃት ያስራችኋል፡፡ ቆልፎ ያስቀምጣችኋል፡፡ ወደፊት እንዳታዩ አይናችሁን ይጋርደዋል፡፡

ልክ መፍራት ስንጀመር መኖርን እናቆማለን፡፡

ራእያችንንና ዓላማችንን አውቀን መኖር ስንጀምር ደግሞ መፍራት እናቆማለን!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ራእይን ፍለጋ!!!

“ራእይ”
ማለት ምን ማለት ነው?

“ተልእኮ” ማለትስ ምን ማለት ነው?

“ግብ” በራእያችን ውስጥ ያለው ተሳትፎ ምንድን ነው?

“እሴት” በራእያችን ውስጥ ያለው ስፍራ ምንድን ነው?

“ሕልም” ከራእይ የሚለየው በምንድን ነው?

ቅዳሜ ጳጉሜ 2 ቀን በሚኖረን ስልጠና ላይ ከምንማራቸው ትምህርቶች በተጨማሪ ለእነዚህና ለመሰል ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን፡፡

ዛሬውኑ ይመዝገቡ!

ስለምዝገባው ሂደት መረጃ ለማግኘት በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ራስን የማድመጥ ግዴታ!

“ራሳችሁን ከማድመጥ ውጪ መኖር ስለማትችሉ፣ ለራሳችሁ የምትናገሩትን ነገር ተጠንቀቁ”
(Life Quotes)

ማሕበራዊ ሚዲያውን ላለመስማት መዝጋት ትችላላችሁ፡፡

ሰዎችን ላለመስማት ከሰዎቹ መራቅ ትችላላችሁ፡፡

ራሳችሁን ላለመስማት ግን የትም መሄድ አትችሉም፡፡

ስለዚህ፣ ያላችሁ ብቸኛ አማራጭ የራስ-በራስ ቋንቋችሁን ማስተካከል ነው፡፡

ለራሳችሁ . . .

• “እችላለሁ” በሉት!
• “ሙሉ ሰው ነኝ” በሉት!
• “ጎበዝ ሰራተኛ ነኝ” በሉት!
• “ከስህተቴ ተምሬ እለወጣለሁ” በሉት!


/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

“በተጠንቀቅ” በመቆምና “በዝግጅት” በመቆም መካል ያለው ልዩነት

በተጠንቀቅ መቆም (Being Ready) ማለት ሊመጣ ለሚችለው ነገር በንቃት መጠባበቅ ማለት ነው፡፡

በዝግጅት መቆም (Being Prepared) ማለት ግን ሊመጣ ለሚችለው ነገር ተገቢውንና በቂ ዝግጅት አድርቆ መጠባበቅ ማለት ነው፡፡

በዚህ ትርጉም መሰረት አብዛኛው ሰው ለሚመጣው ነገር በተጠንቀቅ ስለቆመ ብቻ ዝግጁ እንደሆነ እየመሰለው ነው የሚታለለው፡፡ ለዚህም ነው የመጣው ነገር ሁሉ ግራ የሚያጋባው፡፡ በንቃትና በተጠንቀቅ መጠበቅ ችግር የለበትም፣ ከበቂ ዝግጅት ውጪ ግን ውጤቱ ላያምር ይችላል፡፡

ቀላል ምሳሌ ብንወስድ፣ አንዳንድ ሰዎች የፍቅር ግንኙነትን ለመጀመር በተጠንቀቅና በንቃት ይጠብቃሉ፣ ግንኙነቱ ሲከሰት ግን ትክክለኛው ዝግጅት ስለሌላቸው ከገቡበት በኋላ የሚያዘውና የሚጨበጠው ይጠፋባቸዋል፡፡

ሌላ ምሳሌ ለመጨመር ያህል፣ ሁሉም ተማሪ እኮ የፈተናውን ጊዜ በተጠንቀቅና በንቃት ይጠብቃል፣ በበቂ ዝግጅት የሚጠብቁት ብቻ ግን ነገሩ የገባቸው ብቻ ናቸው፡፡

በተጠንቀቅ መጠበቅ ፈተናን አያሳለፍም፣ በቂ ዝግጅት አድርጎ መጠበቅ እንጂ!

ተመሳሳይ ምሳሌዎችን ከማሕበራዊ ግንኙነት፣ ከስራው አለምና ከመሳሰሉት አንጻር ብንመለከት አብዛኛውን ጊዜ ከገባንባቸው በኋላ ግራ የምንጋባባቸው ሁኔታዎች በእነዚህ በሁለቱ ሃሳቦች መካከል የተምታታ ግንዛቤ የያዝንባቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡

በአሁኑ ሰዓትም ሆነ ለወደፊቱ ወደ አንድ ነገር ውስጥ ከመግባታችሁ በፊት፣ “ይህንን ሁኔታ ስጠብቅ በንቃትና በተጠንቀቅ ብቻ ነው የምጠብቀው ወይስ ትክክለኛውን ዝግጅት በማድረግም ጭምር ነው?” የሚለው ጥያቄ መመለሳችሁን አትዘንጉ፡፡

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/D

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

መታገል ወይስ መታገስ?

አንድ አንድ ችግሮችን ታግላችሁ ታሸንፏቸዋላችሁ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ ታግሳችሁ ታልፏቸዋላችሁ”

በመታገል ማሸነፍ ያለባችሁን በዝምታ ማለፍ ጊዜያችሁን ይበላባችኋል፡፡ ስለዚህ ታገሉ!

በመታገስ ማሳለፍ የሚገባችሁን ደግሞ በከንቱ መታገል ጉልበታችሁን ይጨርስባችኋል፡፡ ስለዚህ ታገሱ!

/channel/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Читать полностью…

Dr. Eyob Mamo

ራእይ! የስኬታማ ሕይወት መነሻና መዳረሻ!

በሕይወታች ፈጣሪን ከማመንና በእሱ ላይ ከመደገፍ ቀጥሎ ትልቁን ስፍራ የሚይዘው ራእያችንን የማወቃችንና የመከተላችን ጉዳይ ነው፡፡

ማንኛውም ሰው ከራእይ ውጪ መኖር ቢችልም የባከነ ሕይወት ነው የሚኖረው፡፡ አብዛኛዎቹ የሕይወታችን ችግሮች የሚፈቱት ራእያችንን ስናውቅና ያንን ያወቅነውን ራእይ መኖር ስንጀምር ነው፡፡

በማንኛውም የሕይወት ሁኔታም ሆነ ደረጃ ብንኖር ለዚያ ሕይወት ትርጉም የምናገኘው ራእይ ሲኖረንና ያንን ራእይ መከተል ስንጀምር ነው፡፡

የችግራችን ዋነኛ መፍትሄ!

• አንድ ሰው የሚሞተው ጤናው ሲጠፋ ብቻ አይደለም … ራእይ ሲጠፋም ጭምር ነው!

• አንድ ሰው የሚከስረው ስራ ሲበላሽ ብቻ አይደለም … የራእዩ ሁኔታ ሲበላሽም ጭምር ነው!

• አንድ ሰው ብቸኝነት የሚሰማው ሰው ሲርቀው ብቻ አይደለም … ራእይ ሲርቀውም ጭምር ነው!

• አንድ ሰው ተስፋ የሚቆርጠው ሁኔታዎች አልታይ ሲሉት ብቻ አይደለም … ራእይ አልታይ ሲለውም ጭምር ነው!

• አንድ ሰው ውዳቂ የሚሆነው ስለወደቀ ብቻ አይደለም … ራእዩን ሲጥል ጭምር ነው!

በራእይ ላይ ያላችሁን ትርጉም አስተካክሉ፡፡ ራእያችሁ አግኙና ግራና ቀኝ ሳትሉ ተከተሉ፡፡ የቀረው ሁሉ ቦታውን ይይዛል፡፡

ይህንን ጉዞ ለመጀመር ከፈለጋችሁ ጳጉሜ 2 ቀን የተዘጋጀው ስልጠና አያምልጣችሁ!

ለበለጠ መረጃ በ @DrEyobmamo ኢንቦክስ ያድርጉ!

Читать полностью…
Subscribe to a channel