atronosee | Unsorted

Telegram-канал atronosee - አትሮኖስ

246307

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩ ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል። Contact. @atronosebot please dont touch the leave button.😔😳😳

Subscribe to a channel

አትሮኖስ

#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አለማየሁና አስካለ ግንኙነት ከጀመሩ ከሰባት  ወር በኃላ
ግንኙነታቸውን ድንገት የሚያከስም  ችግር ተከሰተ፡፡በሁለቱም አእምሮ ያልታሰበበት ቅድመጥንቃቄ ያልተደረገበት አስደንጋጭ ችግር ነው፡፡
ደግሞ ወቅቱ የማትሪክ  ውጤት ከዛሬ ነገ ይለቀቃል ተብሎ እየተናፈሰ ስለሆነ አራቱም  ጓደኛሞች በጉጉት  በምጠበቅበት ወቅት ነበር፡፡ አስካለ ለአላዛር ደወለችለትና በአስቸኳይ እንዲገናኙ እንደምትፈልግ ነገረችው፡፡ከሰፈሯ ብዙም የማይርቅ ካፌ ተቀምጣ ትጠብቀው ጀመር፡፡ብዙም ሳያስጠብቃት እያለከለከ ተገኘ፡፡ እውነተኛ ስሜቱን የሚገልፅ መሸበር ፊቱ ላይ እየታየበት‹‹የእኔ ቆንጆ እንደደወልሽልኝ እየሮጥኩ ነው የመጣሁት.. በአስቸኳይ ፈልግሀለው ስትይኝ ደንግጬ ነበር፡፡››አላት፡፡፡

አስካለ ለእሱ ስሜት እና መሸበር ብዙም ሳትጨነቅ‹‹አዎ …ችግር ተፈጥሯል››አለችው ኩስትርትር እንዳለች፡፡

‹‹የምን ችግር …?ጋሼ ግንኙነታችንን አወቀ እንዴ?››ከፊቷ መኮሳተር እና መገርጣት ከበድ ያለ ነገር እንደተፈጠረ የሚያሳብቅ ነው፡፡ለዛ ነው እንደዛአይነት ጥያቄ የጠየቃት፡፡

‹‹አይ አስከአሁን አላወቀም…››ቅዝዝ እንዳለች መለሰችለት፡፡

‹‹እስከአሁን አላወቀም ስትይ..?ምን ለማለት ነው?››

‹‹ሰሞኑን ሲያዞረኝና ሲያቅለሸልሸኝ ነበር ስልህ ሰምተሀል  አይደል?››

‹‹አዎ !!ምነው ባሰብሽ እንዴ?››

‹‹አይ ..ጤና ጣቢያ ሄጄ ነበር…››

‹‹እና ምን አሉሽ..?መድሀኒት አዘዙልሽ?››

‹‹አይ..አርግዤለሁ››

‹‹ምን ..?አርግዤለሁ››

‹‹አዎ አርግዤለሁ››

‹‹‹ወይኔ ጉዳችን..ከእኔ ነው አይደል?››ሲል እራሱን ይዞ በድንጋጤ አይኖቹን እንዳጉረጠረጠ ጠየቃት፡፡‹‹አዎ ካንተ ነው ያረገዝኩት…››ብትለው ምን እንደሚያደርግ አያውቅም፡፡ይሄ በህይወቱ የጋጠመው እውነተኛው ሰበር ዜና ነው፡፡

እሷ ግን እንደዛ አላለችውም፡፡‹‹እሱ ምን ያደርግልሀል…? የጠራሁህ ልጁ ያንተነው ወይም አይደለም ልልህ አይደለም ››

‹‹እና ለምንድነው?››

‹‹ከዛሬ ጀምሮ  ግንኙነታችን መቀጠል እንደማንችል እንድታውቅ ነው፡፡››ያላሰበውን ሁለተኛ መርዶ ነገረችው፡፡

‹‹ማለት …ምን አጠፋው?አቅጄና ፈልጌ አይደለም እኮ እንድታርዢ ያደረኩሽ››

‹‹እኔም እንደዛ አልልኩም…አንተ ምንም አላጠፋህም..ግን አሁን እንደምታየው ብቻዬን አይደለሁም …በማህፀኔ ልጅ ይዣለሁ…ለራሴ ሳይሆን ለልጄም ደህንነት መጨነቅ አለብኝ፡፡

እስከዛሬ ካንተ ጋር  የቆየሁት ስለማፈቅርህ ነው…ምንም ነገር ቢፈጠር እወጣዋለሁ ብዬ አስቤ ነው…አሁን ግን ነገሮች ተቀይረዋል፡፡በልጄ ላይ እንደዛ ማድረግ አልችልም፡››

አለማየሁ ይሄ ቀን ለዛውም እንደዚህ በቅርብ ይመጣል ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር፡፡ይህቺን ሴት በጣም አፍቅሯት ነበር፡፡ከሰሎሜ ቀጥሎ ልቡ የደነገጠባት ሁለተኛዋ ሴት ነች፡፡

ወንድነትን ያጎናፀፈችው  ብቸኛዋ ሴት ነች፡፡በህይወቱ አይቶት የማያውቀውን ፍቅር አስኮምኩመዋለች፡፡ብዙ የደስታ ቀናትን እንዲያሳልፍ አድርገዋለች፡፡ በአለም ተወዳጁና ተፈቃሪው ሰው እንደሆነ እንዲሰማው አድርገዋለች..ይህቺን ልጅ እንዲህ በቀላሉ ‹‹በቃ እሺ እንዳልሺው ግንኙነታችንን እናቁም›› ሊላት አልፈለገም፡፡አዎ እሷ የተናገረቻቸው እያንዶንዷቹ ቃላት ከበሳል ሴት የተሰነዘሩና የፀነሰችውን ልጅ ደህንነት ብቻ ሳይሆን የእሱንም የወደፊት ህይወት አደጋ ላይ ላለመጣል አስባበት ያደረገችው ነው፡፡ለዛም እግሯ ስር ተንበርክኮ ሊያመሰግናት ይገባ ነበር፡፡ግን እንደዛ ማድረግ አልቻለም፡፡እንደውም በተቃራኒው ‹‹እባክሽ…ተረጋግተሸ አስቢበት…እኛ መለያየት የለብንም…ከፈለግሽም ተያይዘን መጥፋት እንችላለን፡፡››ሲል በአይኖቹ ጭምር እየተለማመጠ ተማፀናት፡፡
እሷ ግን የተናገረችውን ሁሉ ለቀናት አስባበት..አውርዳና አውጥታ  የወሰነችው ስለነበር ከአቋሟ ሽብርክ ልትል አልቻለችም‹‹እባክህ የምታፈቅረኝ ከሆነ ያልኩህን አድርግ….ሁለተኛ ቤት እንዳትማጣ… እንዳትደውልልኝ..መንገድ ላይ እንኳን ብታየኝ ልታናግረኝ እንዳትሞክር፡፡››ብላው እንባዋን እያንጠባጠበች…ለጠጡት ማኪያቶ ክፍያ የሚሆን ድፍን መቶ ብር ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ በተቀመጠበት ጥላው ሄደች፡፡

አለማየሁም ጓደኞቹ ግራ እስኪገባቸው ድረስ ለአንድ ወር ነበር ያዘነው፡፡ለሌላ የማይነግሩት የብቻ ሀዘን ደግሞ ውስጥን እንዴት እንደሚበላ የደረሰበት ነው የሚያውቀው፡፡በጣም ነበር የተጎዳው፡፡የሀዘኑ ምንጭ ከእሷ ጋር ያለው ግንኙነት ስለተቋረተ ብቻ አይደለም..እሱንማ ትክክለኛ ቀኑን አይወቅ እንጂ አንድ ቀን እንደሚሆን ከበፊቱ ያውቅ ነበር፡፡በጣም የጎዳው የተፈጠረው ሁኔታ ነው፡፡በመሀከላቸው ልጅ መፈጠሩ….ልጁ በተሳሳተ አባት እጅ ማደጉ….
በጣም የሚገርመው ደግሞ ከገባበት ደባሪ ሀዘን ሳይወጣ በተጨማሪ ሌላ ህይወት መንሸራተት ገጠመው ፡፡ የማትሪክ ውጤት ተነግሮ ከሁሴን በስተቀር እሱን ጨምሮ ሁሉም ጓደኞቹ ዝቅተኛ ውጤት ማምጣታቸው ታወቀ፡፡እርግጥ ከአራቱ ጓደኛሞች ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት  ሁሴን ብቻ ማምጣቱ  ከበፊቱም የሚጠበቅና ሚገመት ነበር፡፡ቢሆንም የቁርጡ ቀን መጥቶ ሁሉም በግልፅ ሲታወቅ ቅሬታ መፍጠሩ አይቀርም፤ቢሆንም ለዚህኛው ሀዘን አብረውት የሚያዝኑ ጓደኞች አሉት፡፡የእሱ  መከፋትን እነሱም ሚከፉት ስለሆነ እርስ በርስ ለመፅናናት ቀላል ነው፡፡እና እንደመጀመሪያው ችግር አልከበደውም፡፡
ሁሴን ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ደርሶት ደግሰውና መርቀው ከላኩት በኋላ እነሱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው መማከር ጀመሩ..እርግጥ ከበፊቱም ጀምሮ  አላዛር የራሱ ሱቅ ያለውና በንግድ የሚተዳደር ስለሆነ ከእነሱ በተለይ የሚፅናናበት እና ሚመካበት ነገር ስላለው ነገሮች ብዙም አላስጨነቁትም….አንድ ቤት እንደእህትና ወንድም የሚኖሩት አለማየውና ሰሎሜ ግን ምንም አማራጭ የላቸውም..በተለይ አለማየሁ ከገጠመው የፍቅር ስብራት ጋር አንድ ላይ ተጨማምሮ ተራራ የተሸከመ አይነት ስሜት ነበር እየተሰማው ያለው፡፡ ቢሆንም እንደምንም በጓደኞቹ ጎትጓችነት እንደምንም ከቁዘማ ወጥቶ ለገጠሙት ችግሮች መፍትሄ መፈለግ እንዳለበት በማመን መንቀሳቀስ ጀመረ….፡፡

በድንገት ወደህይወቱ ገብታ የፍቅር  አልኮል ስትግተው የሰነበተችው የጓደኛው የአላዛር የእንጀራ እናት ‹‹አርግዤለሁ እና ከአሁን ወዲህ አልፈልግህም ››ማለቷ ከፈጠረበት  ድባቴ መች ሙሉ ለሙሉ ማገገም እንደሚችል አያውቅም ፡፡ፈጽሞ ከአእምሮው ሊፍቀው የሚችል ሁኔታ አልሆነለትም፡፡በ19 አመቱ የልጅ አባት ከመሆኑም በላይ ከባለትዳር ሴት  መወስለቱ  በአሳዳጊው እቴቴ ዘንድ እንዲሁም በሚያፈቅራት በልጇ  ሰሎሜ ዘንድ  ምን አይነት ስሜት እንዲሚፈጥር እያሰበ እየተሳቀቀ ነው፡፡ደግነቱ ልጅቷ ለራሷ ደህንነት ስትል ሚስጥሩን ላለመናገር ወስናለች…በዛም የተወሰነ እፎይታ ተስምቷታል ፡፡ከአስካለ ጋር የነበረው አጭር ግን ደግሞ ጣፋጭ ፍቅር ግንኙነት በአጭሩ እና ባልሆነ መንገድ መቀጨቱ አሳዛኝ ቢሆንም አሁንም ዋናው የህይወት ህልሙ ሰሎሜ ስላለች ለእሷ በቂ ሰው ሆኖ መገኘት እንዳለበት አሰበ….ለዚህም ይረዳው ዘንድ እንደምንም ብሎ ትምህርቱን በመጠኑም ቢሆን ወደፊት መግፋት እንዳለበት ስለወሰነ...ከአላዛርና ከራሷ ከሰሎሜ ጋር በመመካከር ሶስቱም የሞያ ትምህርት ለመማር ተግባረእድ ኮሌጅ ተመዘገቡ…በዚህም የተወሰነ የመንፈስ  መነቃቃት አሳየ ….ትምህርቱ ከዛሬ ነገ ይጀመራል በሚል  ተስፋ መጠባበቅ ጀመሩ፡፡ ግን ደግሞ አንዳንዴ ሕይወት ከፊት ለፊታችን እንቅፋት መደርደር ከጀመረች

Читать полностью…

አትሮኖስ

ለወንዶች ብቻ ሴቶች እንዳትነኩት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
ለሴቶች ብቻ ወንዶች እንዳትነኩት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

ለወንዶች ብቻ ሴቶች እንዳትነኩት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
_
ለሴቶች ብቻ ወንዶች እንዳትነኩት
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️ play▶️ ⬜️⬜️⬜️
⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️⬜️

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================
አለማየሁ ልቡ ላይ አዲስ እና ያልተጠበቀ ፍቅር በቅሏል…የአስካለ ምስልም በተለይ ወሬዋና ሳቋ  ከምናቡ ለደቂቃም ሊሰወር አልቻለም፡፡ለዘላለም ከሰሎሜ ውጭ ሌላ ሰው ሊያፍቀር ሚችል አይመስለውም ነበር…ግን ሆነ፡፡እርግጥ ለሁለቱ ያለው ፍቅር ፍፅም ተመሳሳይ አይደለም….ይሄኛው አዲሱ ፍቅሩ የሚያንቀዠቅዝ አይነት ነው፡፡የወሲብ ርሀብ ያለበት የተክለፈለፈ ፍቅር፡፡የሰሎሜ ግን የተረጋጋና ጥልቅ ነው፡፡ስስትና እና ተስፋ ያቆሙት  ዘላለማዊ መሳይ ነው፡፡
ከአስካለ ጋር ባሳለፈ በሁለተኛው ቀን ወደአላዛር ሄደና‹‹አባትህ እንዴት ናቸው?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ያው ድኖ አይደል ወደቤት የገባው…ምን ይሆናል?››ሲል ድርቅ ያለ መልስ መለሰለት፡፡
‹‹አሁን እንዴት እንደሆኑ ደውለህ ጠየቅክ?››
‹‹ለምን ብዬ ጠይቃለሁ?››
‹‹በትክክል መጠየቅ ይገባሀል…›››
‹‹የትናንቱንም እንዴት እንዳደረኩት ግራ እየገባኝ ነው››
‹‹እንደውም ተነስ እንሂድና አይተናቸው እንምጣ፡፡››
አላዛር ግራ በመጋባት አፍጥጦ ሲያየው ከቆየ በኃላ፡፡‹‹ሰላም ነህ ግን?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ምነው…ምኔ ነው ሰላም አልመስል ያለህ ?››ሲል መልሶ ጠየቀው፡፡
‹‹ የምናገረው አይገባህም እንዴ? ትናንት በዛ ለሊት ለእሱ ስል ራሴም ተንከራትቼ እናንተንም ሳንከራተት ማደሬ እራሱ እየቆጨኝ ነው ..ጭራሽ ዛሬም ደግሜ ቤት ሄጄ እንድጠይቀው ትፈልጋለህ?፡፡››
‹‹ተወው በኃላ እንዳትፀፀት …ላንተው ብዬ ነው፡፡እኔ አባቴ ጠጪም ሌባም ፤ቁማርተኛም ..ምንም ሆኖ ምንም በህይወት ቢኖርልኝ እንዴት እንደምደሰት ልትገምት አትችልም፡፡በዚህ አለም ላይ እንደቤተሰብ ወሳኝ ነገር የለም፡፡ከፋም ለማም በጨለማ ቀናቶችህ አብረውህ የሚንከራተቱት እነሱ ናቸው፡፡..ቤተሰብ በህይወት መንገድ ወሳኙ አጋር እንደሆነ አውቃለው፡፡የገንዘብ ችግር ቢኖርብህ ቤተሰብ ካለህ ታልፈዋለ…ክፉኛ ብትታመም ቤተሰብ ካለህ ህመምህን ቻል አድርገህ በቀላሉ ማገገም ትችላለህ …ሀገርህ ፈርሳ ስደት ላይ ብትሆን እራሱ ቤተሰብህ ከጎንህ ካለ እንደምንም እየተደጋገፍክ ያንን ክፉ ቀን ታልፈዋለህ፡፡››
‹‹ገባኝ…የእኔ ቤተሰብ እናቴና እህቶቼ ናቸው፡፡በተጨማሪ ደግሞ እናንተ ወንድሞቼ አላችሁልኝ…እርግጥ እናቴ የለችም….ሁለት እህቶቼ ግን አሁንም አሉልኝ..እነሱ በቂዬ ናቸው፡፡ለእኔ አባቴ ከእናቴ ቀድሞ ነው የሞተው…አሁን እሱን ሳይ በድን አካሉ ብቻ ነው ሲንቀሳቀስ የማየው..ነፍሱ ውስጡ የለችም፡፡››
አለማየሁ ሊያሳምነው ስላልቻለ ተበሳጨ‹‹በቃ ቸው..ድሮም አንተ ከጠመምክ  መመለሻ የለህም››አለውና ፊቱን አዙሮ መራመድ ጀመረ፡፡
‹‹ቆይ አትሂድ..ና እንካ››አለና እጁን ወደባንኮኒው በመስደድ ብር በእጁ አስጨበጠው፡፡
‹‹ምንድነው?››
‹‹ማኪያቶ ልጋብዝህ ነበር …መውጣት አልቻልኩም..ስለዚህ ብቻህን ጠጣ››አለው፡፡
አለማየሁም‹‹አመሰግናለሁ፡፡››ብሎት የሰጠውን ብር በእጁ እያሻሸ አካባቢውን ለቆ ሄደ ..የእሱ ሀሳብ አላዛርን አሳምኖ አባቱ ቤት አብሮት መሄድ ነበር፡፡፡ያንን የፈለገው ያችን ውብ የጓደኛውን አባት ሚስት ዳግመኛ ለማየት ነው፡፡ከትናንትናው ምሽት ጀምሮ ፈፅሞ ከምናቡ ሊያሸሻት አልተቻለውም፡፡የአላዛር መገገም ግን እቅዱን ሁሉ ገደል ከተተበት፡፡
ከአላዛር ሱቅ ከራቀ በኃላ መዳፉን ፈልቅቆ ሲያየው ድፍን መቶ ብር ነው፡፡ስልኩን አወጣ ..ሰሎሜ ጋር ለመደወል ነው የፈለገው፡፡መቶ ብር ካለው ወይ ይዟት ሲኒማ ቤት ይገባል ወይ ደግሞ አንድ ካፌ ቁጭ ብለው ማኪያቶ እየተጎነጩ  ዘና ይላሉ፡፡እቅዱ እንደዛ ነው፡፡
‹‹ሄሎ ››
‹‹ምነው? አሁን ተለይተሀኝ ሄደህ አሁን ናፈቅኩህ እንዴ?››
‹‹ውይ ሰው ጠፍቶ አንቺ ትናፍቂኛለሽ…..?ጉረኛ ነሽ››
‹‹እመን …..››
‹‹ለምን ብዬ ነው የማምነው?››
‹‹እሺ ለምን ፈለከኝ?››
‹‹ምን እየሰራሽ ነው…?አመድ በኪሴ ስላለ ዘና ላድርግሽ ብዬ ነው…››
‹‹አንድ ጥብስ የማይገዛ ብር ይዘህ..ዘና ላድርግሽ ብዬ ነው ስትል ትንሽ አይሸምምህም?››
‹‹አንቺ ምስጋና ቢስ…ይሄኔ በኪስሽ አምስት ብር የለም…አሁን ትወጪያለሽ ወይስ አትወጪም?››
‹‹አዝናለሁ እቴቴ...ዘመዶቾ ጋር እንሂድ ብላኝ ለመሄድ እየተዘጋጀን ነው፡፡››
‹‹የት ?ሰንዳፋ?››
‹‹አዎ…ምነው መሄድ ትፈልጋለህ እንዴ?››
‹‹አይ ይለፈኝ…ግን ታድራላችሁ እንዴ?››
‹‹አዎ… ነገ ነው ምንመጣው፡፡››
‹‹እሺ መልካም መንገድ፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ በጊዜ ወደቤት ግባ …እቴቴ እንዳታዘርፈኝ እያለች ነው ፡፡››
‹‹እሺ …አታስቢ በያት፡፡››ብሎ ስልኩን ዘጋውና ተቀያሪ ሀሳብ ማብላላት ጀመረ…ወዲያው ነው መሳጭ የሆነ ሀሳብ ብልጭ ያለለት‹‹ መንገድ ተሻገረና ወደአትክልት መሸጫ ሱቅ ሄደ ..አንድ ኪሎ ሙዝ ገዛ፡፡ ታክሲ ውስጥ ገባ ፡፡ቀጥታ ወደአላዛር አባት ሰፈር ነው የሄደው፡፡ደረሰና የውጪውን በራፍ አንኳኳ…፡፡
ከተወሰነ ጥበቃ በኃላ ተከፈተለት…
ይህቺን ሴት ለሁለተኛ ጊዜ ሲያያት ይበልጥ አምራና ውብ ሆና ነው የታየችው፡፡አስካለ ፈፅሞ አየዋለሁ ብላ ያልጠበቀችው ስለሆነ በጣም ነው የደነገጠችው፡፡
በዝምታ አፍጥጣ ስታየው ግራ ተጋባና ‹‹ምነው አላወቅሺኝም እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡
በራፉን ጋርዳ እንደቆመች‹‹ይቅርታ እንዲህ በቅርቡ ደግሜ አይሀለው ብዬ ስላልገመትኩ ነው…እንጂማ አንተን እንዴት እረሳሀለው፡››አለችው ፡፡
በጥቁር ፔስታል የያዘውን ሙዝ እንድታይ እያወዛወዘ፡፡‹‹ጋሼን ለመጠየቅ ነው የመጣሁት››አላት፡፡
‹‹ግባ…ና ግባ››አለችና በራፉን ለቀቀችለትና ቀድማው ወደውስጥ መራመድ ጀመረች ፡፡ከኃላዋ ተከተላት፡፡ገቡ፡፡
‹‹ቁጭ በል፡፡››ሙዙን አቀበላትና ፈራ ተባ እያለ ቁጭ አለ፡፡
‹‹አሁን የእውነት ሰውዬው እሷቸውን ልጠይቅ እንደመጣው ያምኑኛል?››ሲል ከዚህ በፊት ያላሰበውን ነገር አሰበ‹‹አይ አላዛር ነው የላከኝ ..ስራ ላይ ስለሆንኩ ሰላም መሆኑን እይልኝ ሳለለኝ ነው የመጣሁት፡፡››እለዋለው ሲል ወሰና ተረጋጋ፡፡ሙዙን ተቀበለችውና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ..ከፊት ለፊቱ ሄዳ ተቀመጠች፡፡
‹‹ጋሼ ተኝተዋል እንዴ?››ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡
‹‹‹የሉም ስራ ገብተዋል››
በረጅሙ ተነፈሰ‹‹እንደዛ ነው…በደንብ ተሻሏቸዋል ማለት ነው?››
‹‹አዎ በደንብ ተሽሏቸዋል፡፡አተነፋፈስህ ግን ባለመኖራቸው ደስ ያለህ ይመስላል››አለችው፡፡ የውስጡን ስላነበበችበት አፈረ፡፡
‹‹አይ..ያው አለ አይደለ..ከድሮም ጀምሮ እፈራቸዋለው…ለዛ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ ይሄን ያህል የሚያጨናንቅህ ከሆነ ለምን መጣህ?››ብላ ሲፈራው የቆየውን ከባድ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ያው አላዛር ስራ ላይ ስለሆነ መጥቶ ሊጠይቃቸው አልቻለም…እይልኝ ብሎ ስላስቸገረኝ ነው››ከደቂቃ በፊት ያቀናበረውን ምክንያት ነገራት፡፡
ፈገግ አለች….
‹‹ምነው?››
‹‹አይ …እኔ ደግሞ እኔን ለማየት የመጣህ መስሎኝ ደስ ብሎኝ ነበር?››ስትል ያልጠበቀውን አማላይ አይነት መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹እሱማ ..ያው እግረመንገዴን አንቺንም ማየትና እንዴት እንደሆንሽ ማወቅ ስለፈለኩ ነው የመጣሁት፡፡››ሲል በከፊል  አመነላት፡፡
‹‹ስለመጣህ ደስ ብሎኛል…መጣው ተጫወት›› ብላ ወደውስጥ ገባችና ..ሻይ ጥዳ….ተመለሰች፡፡
ሞባይሉን አወጣና ሰዓቱን ተመለከተ..5፡20 ይላል፡፡‹‹ምሳ ሰዓት እየቀረበ ነው….››አላት፡፡
‹‹አዎ ..ምነው እርቦሀል ላቅርብ እንዴ?››
‹‹አይ!! ማለቴ ጋሼ  አሁን ለምሳ ይመጣሉ ለማለት ነው፡፡››

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

የማን ይሁን ?

የባሰ! እሾክና መርፌ ተነቅሎ የማይጣል፤ በቅርብ ሳይገፋ ያልተደረሰበት ፤ ከላይኛው የወረደ ዱብዳ ፤ የፈጣሪ የቁጣ ስጦታ፡፡ ለማን ታድርገው? ለማን ትስጠው? ለማንስ አቤት ትበል? ተቆርጦ የማይጣል የጣት ቁስል ሆነባት፡፡

ቀኑ ወደ ጨለማ ተቀየረ፡፡ እንደ ተዳፈነ እሳት ውስጧን አቃጠለው፡፡ እንደ ሰኔ ደመና አረምሞ ገፍቷል፡፡ በአንድ ቀን ስህተት የእግዚአብሔር ስራ እንኳን ባይባልም በመቅሰፍቱ በዲያቢሎስ ቅንብር ሆዷ ውፍረትን መከታ እና ከለላ ተጠቅሞ ሳይታወቃት እየገፋ መጥቷል፡፡

እድላዊት ከወንድሟ ከተመስገን ፀንሳለች፡፡ በአንድ እንዴት ላረግዝ እችላለሁ?፡፡ ስታዝን ስትጨነቅ ዘጠኝ ወር ተቆጥሮ ቦርጩ ወደ ልጅ ተቀየረ፡፡ ወንድ ልጅ ከነ ቃጭሉ ተገላገለች፡፡ ግን ከፊቷ አሁንም የማይገፋ ከዳቢሎስ የተገነባ የጨለማ ተራራ ተጋርዶባታል፡፡

ምንጃር ሸንኮራ አውራጃ ውስጥ ነው፡፡ ጉራንባ ማርያም አካባቢ ያለ ማህበረሰብ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡ በእምነታቸው አክራሪና ከእምነት ውጭ ለሚከሰቱ ማንኛውም የክርስትና ጥፋት የፈፀመ ከማህበረሰቡ ይገለላል፡፡ እንደ እድር ፣ ባልትና እና ማህበር የመሳሰሉትን መካፈል አይችልም፡፡ በማህበረሱቡ የተጠላ ፤የማይወደድ ፣ ከሰው እንዳልተፈጠረ ከሰው ውጭ ተደርጎ ይቆጠራል።

እድላዊት እያወቀች ሳይሆን ሳታውቅ ከወንድሟ ከተመስገን መውለዷን ከያሬድ ውጭ ማንም አያውቅም፡፡

የወለደችውን ልጅ ክርስትና የሚነሳው የወላጅ አባት ስም ካልታወቀ መነሳት ፤ መጠመቅ የተወገዘና የተከለከለ ነው፡፡ የእድላዊት ልጅ ባለማወቅ አባት ታዲያ ማን ይሁን ? የማንስ ተብሎ ክርስትና ይጠመቅ ? አክ ተብሎ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥ፡፡ የተመስገን ብትለው ለእሷ አንዴ ሞት ቢሆንም ለዘመዶቿና ለቤተሰቦቿ አስሬ ሞት ብቻ
ሳይሆን ከሰው እንዳልተፈጠሩና ወግ አጥባቂ የክርስትና አገልጋይ እንዳልሆኑ ከሰው ውጭ ተደርገው እንደሚገለሉ የሚታወቅ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡

ታዲያ እድላዊት ይህ ሁሉ የታዘለባትን የጭንቀት እሳት ማማከር ያለባት ለወንድሟ ለተመስገን እንጅ ለማንም ማማከር እንደ ማይቻል ግልፅ ነው፡፡ ግን አሁንም ሌሊቱ ጨልሞባታል፡፡

"ምን እናድርግ ? የልጁ የክርስትና ቀን እየደረሰ ነው፡፡ እኔ ጨንቆኛል፡፡ የማደርገው ጠፍቶኛል፡፡ ከእንግዴህ ያለኝ አማራጭ መርዝ ጠጥቸ ወይም ታንቄ መሞት ነው፡፡ የወንድሜ ነው ብየ ክርስትና አላስነሳም፡፡ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡

ተመስገን የእህቱ ጭንቀት በሱም ላይ ካደረበት እና ከሰነበተበት ቆይቷል፡፡ ጥሎ እንዳይጠፋ እድላዊትን ተመልሶ ዳግመኛ የማያገኛት መሰለው፡፡

እድላዊት እያለቀሰች መልስ እንኳን ሳይሰጣት ከያሬድ ጋር ደርሸ መጣሁ ብሏት ተነስቶ ወደ ያሬድ ቤት ሄደ፡፡

ተመስገን እንደደረሰ ከያሬድ ጋር የእግዚአብሔር ሰላምታ ተለዋወጡ፡፡ ያሬድ ወደ እርሻ ሊሄድ ሞፈርና ቀንበር እያዘጋጀ ነው፡፡

"ወደ እርሻ ልትሄድ ነው እንዴ ሞፈርና ቀንበር የምታሰናዳው?" አለ ፤ ተመስገን፡፡

"አዎ፤ እንዴው ትንሽ የፋልማ መሬት ከሰም ነበረኝ፡፡ ቧጠጥ አድርጌያት ልምጣ ብዬ ነበር አነሳሴ፡፡ ስተረካከም እዚሁ እረፈደ ብሎ ወደ ቤት ግባ እንጅ አለው፡፡

"ኧረ አልገባም፡፡ አንተ ጋር ነበር የመጣሁት"፡፡

"ምነው በደህና ነው"? አለ ፤ ያሬድ፡፡

"ምን ደህንነት አለ ፤ ገና ስፈጠር የአርባ ቀን እድሌ በእሳት ተሞልቶ የእሳት እረመጡ ወደ ጭስነት ተቀይሮ የመውጭያ በር አጥቶ በቁሜ እያቃጠለኝ፡፡

"ምነው እድላዊት ሰላም አይደለችም እንዴ?፡፡

"አይ! ተወኝ ፤ አሁን የእድላዊት ነገር አስጨንቆኛል፡፡ የልጁ ክርስትና እየደረሰ ነው፡፡ የአባቱ ስም ካልታወቀ ክርስትና እንደ ማይጠመቅ አንተም ታውቃለህ፡፡

የማደርገው ሁሉ ግራ ገብቶኛል፡፡ ወንድሜ እባክህ ከዚህ ጨለማ አውጣኝ፡፡ ያላንተ ማንም የማዋየውና የማማክረው የለኝም አለው፡፡በሃዘን ተሞልቶ ፡፡

"በምን ልርዳህ የማደርገው ጠፍቶኝ እኮ ነው፡፡ እስከ አሁንም ዝም ያልኩህ እንጅ እኔ እንኳን ወደ አዲስ አበባ ይዘናት እንድንሄድ አስቤ ነበር፡፡ ግን ክርስትና ሳታስነሳ ከቤት መውጣት አይቻልም ብየ ነው፡፡ አሁን በምን ላግዛችሁ ? ንገረኝና በተቻለኝ አቅም ልሞክር አለ፡፡

በፊቱ ላይ ወርዶ ቡሃቃ ያስመሰለውን እንባ በለበሰው ፎጣ እየጠራረገ እኔማ ለመጥፋትም አስቤ ነበር፡፡ ግን እድላዊት ጥሎ የሚሄድ አንጄት አጣሁ፡፡ አሁን አንተን የማስቸግርህ ልጁ ክርስትና እስከሚነሳ ድረስ የአባቱን ስም በአንተ እናድርግና ክርስትና ከተጠመቀ በኋላ ፤ የተፈጠረውንና የተደረገውን ባለመተዋወቅ እንደ ሆነ ለቤተሰብ እንነግራለን አለ፤ ተመስገን ፡፡ ደፍሮ በመናገሩ አይኑን ላለማየት አቀርቅሮ መሬት መሬት እያየ፡፡

የልጁ አባት ሆኘ ክርስትና ቢጠመቅ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ ግን የአካባቢያችንን ባህል እንደምታውቀው በሚስቱ ላይ ዲቃላ ወልዷል ተብየ እኔ ከማህበረሰብ እንደምገለል፡፡ ደግሞም ባለቤቴ ይህንን ስሰማ በእኔ ላይ ዲቃላህን ታንጠባጥባለህ ብላ ባዶቤት ዘግታብኝ ትሄዳለች አለ ፤ ያሬድ፡፡

"ያልከው ሁሉም ይገባኛል፡፡ ግን ከወንድሟ ወለደች ቢባል ምን ያህል እንደሚከብድ መገመት አያቅትህም፡፡ ደግሞ አባታችን በዚህ ቦታ ወግ አጥባቂ እንደ ሆነ ታውቃለህ፡፡

እባክህ! ያሬድ ስለፈጠረህ አምላክ! ተለመነኝ ሳላውቅ እንደ ሆነ እሳት ውስጥ የገባሁት አንተም ታውቃለህ፡፡ ሚስጥሩን ለባለቤትህ እንነግራታለን፡፡ መጀመሪያ አንተ ብቻ እሽ በለኝ፡፡ እያለቀሰ ተማፀነው፡፡

ያሬድ የሚለው ሁሉ ጨነቀው፡፡ የእድላዊትና የተመስገን ስቃና መከራ የሱም ሆነ፡፡ ክርስትናው እስከሚያልፍ የልጁ አባት ለመሆን ብቻውን መወሰን አልቻለም፡፡

"ለማንኛውም አበበችን አብረን ሚስጥሩን እናካፍላትና እሷ እሽ ካለች የእኔ አያስቸግርም፡፡ አይቻልም ካለች ግን ምንም ላደርግ አልችልም" አለው

"እሽ አንተ እንዳልክ" ብሎት ወደ ቤት ገቡ፡፡

"ደህና አደርሽ አበበች" ? አለ ፤ ተመስገን፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደርክ ተመስገን" ? አለች ፤ አበበች፡፡

ጉንጮቹ አብጠው ገና በጥዋቱ አይኖቹ ቀልተዋል፡፡

ምነው ደህና አይደል ይሆን ? ያለቀሰ ይመስላል፡፡ የሞተ ሰው ይኖር ይሆን ? ያሬድም ደስተኛ አይመስልም፡፡ ዛሬ ምን ተፈጥሮ ይሆን ? አበበች ከውስጧ ሳታወጣና ሳታሰማ የተናገረችው ነበር፡፡

ምን ብሎ እንደሚነግራት ግራ ተጋብቷል፡፡ የቤቱን ጣራ ጣራ እየተመለከተ እንባው በጉንጩ ላይ ይወርዳሉ፡፡ አንገቱን ዞር አድርጎ ለመጥረግ ሞክረ፡፡

አበበች ግን ገና ሲገባ አንስታ እየተመለከተችው ነበር፡፡

"ምነው ደህና አይደለህም እንዴ? የምታለቅሰው" አለች ፤ ለተመስገን፡፡ የተፈጠረውን ለመስማት እየተጨናነቀች፡፡
ተመስገን ከተቀመጠበት ብርጩማ ላይ ተነስቶ ምንም በማታውቀው እና ምንም ባልሰማችው አበበች እግር ላይ ተደፋ፡፡ እባክሽን ከጉድ አውጭኝ ፤ በምትወጅው ልጅሽ ፤ በምትኩ ስም እለምንሻለሁ እያለ ያለቅስ ጀመር፡፡

አበበች ተመስገን ስለምን እንደሆነ የሚያወራው ግራ ተጋብታለች፡፡ ሲለምናትና ሲማፀናት ገና ባልሰማችውና ባላወቀችው ቀላል ነገር መስሏት እሽ፡፡አሁን ተነስ ብላ ካስነሳችው በኋላ፤ ምንድ ነው እሱ የቸገረህ"? አለችው፡፡ ተነስቶ ወደ ነበረበት የብሩጩማ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ አሁንም ከየት መጀመር እንዳለበት ግራ ቢገባውም መንፈሱ ብትጨነቅም ሚስጥሩን ለአበበች ካላካፈለ መፍትሄ ስለማያገኝ ደፍሮ መናገርና መተንፈስ አለበት፡፡ ራሱን አፅናንቶ ለመናገር ወሰነ፡፡

Читать полностью…

አትሮኖስ

❓የየትኛው ክለብ ደጋፊ ናችሁ ❓ የክለባቹሁን ቻናል በመምረጥ ተቀላቀሉ ⁉️

Читать полностью…

አትሮኖስ

‹‹በቃ ደህና እደሪ››አላት፡፡
ባለችበት ቆመችና ፊቷን ወደእሱ መልሳ..‹‹አይ ልተኛ እኮ አይደለም… መኝታውን ላስተካክልልህ ነው፡››

ደነገጠ‹‹አረ ችግር የለውም፡፡ እዚሁ ሶፋ ላይ ተኛለው፡፡››ሲል ፈጠን ብሎ መለሰላት፡፡

‹‹ምን በወጣህ….ውስጥ አልጋ ላይ ነው የምትተኛው››ብላው ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ  ፊቷን አዛረችና ወደውስጥ ገባች፡፡በቆመበት አሰበ ፡፡.እሷን እዚህ የከረከሰ አሮጌ ሶፋ ላይ አስተኝቶ እሱ ውስጥ ገብቶ አልጋ ላይ ለመተኛት ህሊናው አልፈቀደለትም..በዛ ላይ ‹‹የባለትዳር አልጋ ላይ ለዛውም አባወራው በሌለበት መተኛት ነውር ነው››አላና ከመምጣቷ በፊት ሶፋው ላይ በመውጣት ትራሱና አስተካክሎ ጋቢውን ነጥሎ ሙሉ በሙሉ ለብሶ ተኛ፡፡
አልጋውን አዘጋጃጅታ ተመልሳ ስትመጣ..ተዘረጋግቶና ተሸፋፍኖ ስታየው ተገረመችና‹‹እንዴ መነው ፈጠንክ..?አረ ተነስ ግባና ተኛ››አለችው፡፡

‹‹አረ የማይሆነውን፡፡››

‹‹ለምንድነው የማይሆነው?››
‹‹እኔ ባልና ሚስት አልጋ ላይ መተኛት ያስፈራኛል››ሲል እውነቱን ነገራት፡፡

‹‹ምነው እንደአባቴ ናቸው አላልከኝም ነበር…አባትህ አልጋ ላይ መተኛት ምኑ ነው የሚያስፈራህ?››

‹‹አባቴ አልጋ ላይ መተኛት ሳይሆን ሚያስፈራኝ  እናቴን ከአላጋዋ አስወርጄ ሶፋ ላይ ማስተኛቱ ነው?›› ሲል ተረቧን በተረብ መለሰላት፡

ከተገናኙ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምፅ አውጥታ ሳቀች‹‹አንተ ለካ ጥሩ አጽናኝ ብቻ ሳትሆን  አሽሙረኛም ጭምር ነህ፡፡በል ተነስ አትስጋ … አልጋው ሁለት ነው ››አለችው፡፡

‹‹እውነትሽን ነው?››

‹‹አዎ …ምን ያስወሸኛል.?.››
ጋቢውን እንደተከናነበ ተነሳ፡፡ሲሊፐር  አቀበለችው.፡፡አጠለቀና ተከተላት፡፡ እውነትም ውስጥ ሲገባ መጠናቸው የሚለያ ሁለት አልጋዎች ነበሩ..የአልጋው አቀማመጥ አንደኛው አልጋ አንድን ግድግዳ ተጠግቶ የተቀመጠ ሲሆን ሌለኛው ደግሞ ቀጥሎ ያለውን ግድግዳ የተጠጋ ነው….ሁለቱ አልጋዎች የግድግዳው ኮርነር ላይ ተጋጥመው እርስ በርሳቸው ተሳስመው የ ኤል ቅርፅ ይዘዋል፡፡
በቆመበት ሆኖ ሁለቱንም አልጋ በማፈራረቅ ከተመለከተ
በኃላ‹‹የቱ ላይ ልተኛ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ደስ ያለህ ላይ?››

‹‹ይሄ ትልቁ የአባወራ መሰለኝ ››አለና የለበሰውን ጋቢ ከላዩ ላይ ገፎ በቅርብ ያገኘው ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠና ከእነለበሰው ልብስ አነስተኛው አልጋ ላይ ወጥቶ የተገለጠው ብርድልብስ ስር ገብቶ ተኛ….፡፡

‹‹ቢጃማ ልስጥህ አላልኩህም››

‹‹ግድ ለም….ሶስት ሰዓት ለመተኛት የምን ቢጃማ ነው››

‹‹ጥሩ›› አለችና እሷም እንደእሱ ከነለበሰችው ልብስ ትልቁ አልጋ ላይ ወጥታ ተኛች፡፡በተለያየ አቅጣጫ ላይ ቢሆኑም ጭንቅላታቸው ግን እርስ በርስ ተጠጋግቶ በመሀከል ያለው የሁለቱ አልጋ ጠርዞች ብቻ ነበሩ የለያዮቸው፡፡

‹‹መብራቱን ላጥፋው?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹እንደፈለግሽ››

ከጭንቅላቷ ብድግ አለችና ተንጠራርታ ማብሪያ ማጥፊያውን ተጫነችው…ድርግም ብሎ ሲጠፋ እቤቱ በጭለማ ተዋጠ፡፡

‹‹ደህና እደሪ››አላት፡፡

‹‹ደህና እደር››በለስላሳና በተንቀረፈፈ ድምፅ መለሰችለት፡፡
እንቅልፍ እንዲወስደው በመመኘት አይኖቹን ጨፈነ፡፡.ከአንድ ጀምሮ ወደላይ እስከ መቶ በጸጥታ ውስጥ ሆኖ ቆጠረ….እንቅልፉ ሊወስደው አልቻለም፡፡ከመቶ ጀመር ቁልቁል ወደታች እየወረደ መቁጠር ጀመረ…አርባ ላይ ሲደርስ ተሰላቸና ተወው፡፡ጆሮውን ቀስሮ ማዳመጥ ጀመረ፡፡ትንፋሿ ይሰማዋል…፡፡እንደእሱ ሁሉ እሷም አድፍጣ ይሁን ወይም ተኝታ እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡ተገላበጠና ፊቱን ወደእሷ አቅጣጫ አዞረ….ከደቂቃዎች በኋላ እሷም እንደእሱ ስትገላበጥ ሰማ፡፡ከዛ ተመሳሳይ ዝምታ ሰፈነ፡፡የልብ ምቱ ዷዷዷዷ ሲል የምትሰማው ሁሉ መስሎት ተሳቀቀ…፡፡ሰውነቱ እንደጋለ ነው ፡፡….ሁለ ነገሩ ተወጣጥሯል፡፡ እንደዚህ አይነት ውጥረት ውስጥ የሚገባው በሆነ አጋጣሚ ከሰሎሜ ጋር ተቀራርቦ በሚተኛበት ወይም ብቻውንም ተኝቶ እሷን ስሩ እንዳለችና አንዳቀፈችው ወይም እንዳቀፋት አድርጎ በሚያስብበት ጊዜ ነበር፡፡…ለሌላ ሴት እንዲህ አይነት መጨናነቅ ውስጥ ሲገባ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኙ ነው፡፡በዚህም እንደሚያፈቅራት እራሱ በቅጡ የማታውቀውን ሰሎሜን እንደከዳ አይነት ስሜት ተሰማውና ውስጡ በፀፀት ተሸማቀቀ፡፡ ግን ደግሞ መፀፀት እና  የተፀፀቱበትን ነገር ከማድረግ መቆጠብ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ስለሆነ ስሜቱ ባለበት ነው የቀጠለው፡፡
ለ20 ደቂቃ ያህል ከሁለቱም ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሆነ ድምጽ አልተሰማም ነበር.፡፡ግን ድንገት ሳያስበው ከእሷ መጀመሪያ የማንኮራፋት አይነት ድምፅ ሰማ፡፡‹‹ታድላ…እሷስ ተገላገለች እንቅልፍ ወሰዳት›› ብሎ በእሷ ቀንቶ ሳይጨርስ.. ተገላበጠችና እጇን ወደኃላ ዘረጋች፡፡ እጆ ፊቱ ላይ አረፈ፡፡ማንኮራፋቷን እንደቀጠለች ነው…፡፡እጇ ፊቱ ላይ ሲያርፍ የበለጠ ውጥረት… የበለጠ ግለት ውስጥ ገባ፡፡እጇን ቀስ ብሎ ወደታች አንሸራተተ እና ከንፈሩ አካባቢ አደረሰው..፡፡በስሱ እጣቶቾን ሳማቸው፡፡…ምንም ምላሽ የለም….፡፡ደመቅ አድርጎ ሳማት፡፡ማንኮራፋቷን እንደቀጠለች ነው፡፡እሱም እጁን አሸግሮ ሊያቅፋት ወይም ሊያሻሻት አሰበ፡፡‹‹ይሄ እኮ የአንድ አገር ሰራዊት ሌላ ሀገር ድንበር ጥሶ እንደመግባት አይነት አስጨናቂና መዘዙ የማይታወቅ ድርጊት ነው›› ሲል አሰበና ፈራ፡፡የሆነ ነገር ለማድረግ ከመንቀሳቀሱ በፊት እሷ ቀድማው ተንቀሳቀሰች፡፡ ድንበር ያሻገረችውን ቀኝ እጇን መልሳ ስባ ወደራሷ ወሰደችና ተገላበጠች፡፡አሁን ጭንቅላቷን ከጭነቅላቱ አርቃ ግድግዳውን ተለጥፋ ነው የተኛችው፡፡እንደዛ ያደረገችው አውቃ ይሁን ወይንስ በአጋጣሚ በእንቅልፍ ውስጥ ሆነ አልገባውም፡፡እሱም እንደእሷው በተቃራኒው ተገላበጠና ፊቱን አዙሮ ግድግዳው ላይ ተለጥፎ ነገ የሚፀፀትበትንና  መዘዝ የሚያስከትልበትን ስህተት ሳይሰራ በፊት እንቅልፍ ይወስደው ዘንድ ለፈጣሪው መፀለይ ጀመረ፡፡
ከምንም በላይ ያልሆነ ነገር ቢሰራ  ሁለት ነገር ይከሰታል ብሎ ያፈራል..አንደኛ የሚወዳው የልጅነት ጓደኛውና አሁንም በቸገረው ቁጥር 50 ሆነ መቶም ብር የሚሸጉጥለትን ጓደኛውን አላዛርን ማስቀየም አይፈልግም፡፡ ከዛም አልፎ እስከወዲያኛው ማጣትን ሊያስከትልበት  ይችላል፡፡ከዛም በላይ አስፈሪው ነገር ግን እደዚህ አይነት የተልከሰከሰ ነገር እንዳደረገ ሰሎሜ ጆሮ ከገባ በቃ እንደሞተ ነው የሚቆጥረው…ምክንያቱም ለእሱ ያላት አመለካከት መቀመቅ እንደሚገባና አንድ ቀን‹‹ አፈቅርሻለው ለእኔ የህይወቴ አጋር እንድትሆኚ ፈልጋለሁ›› ቢላት እንደአንተ አይነት ልክስክስ በአፍንጫዬ ይውጣ እንደምትለው እርግጠኛ ነው፡፡እናም ሌላም ከነዚህ ያነሱ ብዙ ውብስብ መዘዞችን አግተልትሎበት እንደሚመጣ አሰበ…ይሄን ሁሉ የሚያደርገው..ስሜቱን ለመግራት ሰውነቱን ለማቀዝቀዝ ይረዳኛል በሚል ግምት ነው..ሙሉ በሙሉም ባይሆንም በተወሰነ መልኩ ተሳካለትና ወደእንቅልፍ አለም ገባ …፡፡
ጥዋት ከእንቅልፉ ሲባንን እሷ አልጋዋ ላይ አልነበረችም፡፡ሰዓቱን ተመለከተ….12፡35 ይላል፡፡ከአልጋው ወረደና ሲሊፐሩን አጠለቀ፡፡ተንጠራርቶ ሰውነቱን ካፍታታ በኃላ ወደ ሳሎን ሲወጣ በስቶፍ ላይ ብረት ድስት ጥዳ….በመክተፊያ ላይ ቲማቲም ትቀጠቅጠለች›፡፡
ተንከባላይ አይኖቾን  ወደእሱ ወረወረችና

‹‹ውይ…ሳንኳኳ ቀሰቀስኩህ እንዴ?››አለችው፡፡

‹‹አረ በራሴ ጊዜ ነው የነቃሁት….››

‹‹ጥሩ እንቅልፍ ተኛህ?››

‹‹በጣም››

‹‹ተቀመጥ…ቁርስ እየሰራሁ ነው …የራሳችንን ፋንታ በልተን ለእነሱ ሆስፒታል ይዘንላቸው እንሄዳለን፡፡››አለችው፡፡

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የድንግሊቷየ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_ዘሪሁን_ገመቹ
===============

ላዳዋ ይዛቸው ትንሽ እንደተጓዘች

‹‹እሺ ምን ገጠመህ?››ሲል አለማየሁ  የመጀመሪያውን ጥያቄ ጠየቀ፡

አላዛርም‹‹ሰውዬው እየሞተ ነው መሰለኝ….፡፡››ሲል በደፈናው መለሰ፡፡

ሁሉም የአላዛር መልስ አልገባቸውም‹‹የትኛዬው ሰውዬ?››ሲል ሁሴን ጠየቀ፡፡

‹‹አባት ተብዬው፡፡››

‹‹በስመአብ..?ማን ነገረህ?››ሰሎሜ በድንጋጤ ጠየቀች፡፡

‹‹አንድ ሴትዬ ነች..ሚስቱ ነኝ አለችኝ..አላውቃትም፡፡››

‹‹ጋሽ ተሰማ አግብተዋል እንዴ?››ሁሉም በመገረም ጠየቁት..፡፡

‹‹እኔም ዛሬ ነው የሰማሁት፡፡››

‹‹አይዞህ አትደንግጥ ምንም አይሆኑም››ሰሎሜ ልታፅናናው ሞከረች፡፡

በንዴት በሚርገበገብ ድምፅ ‹‹ለምንድነው የምደነግጠው…? ቢሞት እንደውም ግልግል ነው፡፡››ሲል መለሰላቸው፡፡

‹‹ባክህ አታስመስል..ባትደነግጥ በዚህ ምሽት እኛንም ቀስቅሰህ ልታያቸው  ትሄድ ነበር?፡፡››
ሰሎሜ  ነች ተናጋሪው፡፡

‹‹አንቺን  አልቀሰቀስኩም..ብቻዬን  ከምሆን አሌክስን ብቻ ነው አካሂደኝ ያልኩት..አንቺና ሁሴንን አልጠየቅኳችሁም፡፡››

‹‹እና እናንተ ጓደኞቼ አይደላችሁም እያልከን ነው?››አለው ሁሴን በንዴት፡፡

‹‹አንተ ደግሞ ሁሌ ነገር ማጣመም ትወዳለህ፡፡››አላዛር ተበሳጨ፡፡

ሰሎሜ በድጋሜ‹‹ዝም ብለህ ስታስመስል ነው..ምንም ቢሆን አባትህ ናቸው፡፡››አለችው  ፡፡

‹‹ዝም በሉኝ በቃ… ሌላ ወሬ አውሩ››ተቆጣ ፀጥ አሉ…

አላዛር ሰፈሩን እንጂ ቤቱን እርግጠኛ አይደለም..ከአመት በፊት ነው አንድ ጓደኛው ጋር በዛ ሰፍር ሲያልፉ ‹‹የአባትህ ቤት ይሄ ነው›› ብሎ ያሳየው….በወቅቱ እቤቱን በጨረፋታ ተመልክቶ ከመገርም ውጭ  ለነገረው ልጅ  እንኳን መልስ አልመለሰለትም ነበር፡፡ግን እቤቱ እንደፈራው አልጠፋውም፡፡ሲደርሱ ከላዳዋ ወርደው ወደአጥሩ በራፍ እየሄዱ በተደወለለት ስልክ መልሶ ደወለ፡፡

‹‹ሄሎ አላዛር››ቀጭንና ልስልስ ድምፅ፡፡

‹‹መጥተናል በራፉን ክፈቺልን፡፡ ››

‹‹ክፍትነው ግፋውና ግባ፡፡››
እንዳለችው ገፋ ሲያደርገው ተከፈተ፡፡ሶስት ጓደኞቹን አስከትሎ አልፎ ወደውስጥ ሲገባ የሳሎኑ በራፍ ሲከፈት ተመለከተ.. በፍጥነት ተጠጉ..አንድ በእሱ እድሜ ያለች ገጠር ቀመስ ግን ደግሞ ውብ  ሴት እየተንቀጠቀጠች ትታያለች፡፡የአራቱም ዓይኖች በመላ አካሎ ላይ ተንከባለሉባት፡፡

‹‹የደወልሽልኝ አንቺ ነሽ?››

‹‹የአባቴ ሚስት አንቺ ነሽ ?››ብሎ መጠየቅ ነበር የፈለገው…..ምክንያቱም ይሄቺን የመሰለ ትንቡክቡክ ያለች ውብ ገራገር ወጣት ያንን ያበቃለትን የሰው አውሬ ብሎ የሚያስበውን  አባቱን እንዴት ታገባለች ብሎ ይገምት?››

‹‹አዎ ግቡ ግቡ ››በማለት ይዛቸው ወደውስጥ ገባች….እቤቱ ሳሎንና አንድ መኝታ ክፍል ያለው ባለሁለት ክፍል ነው፡፡አባትዬው ሳሎን ባለ አንድ አሮጌ ሶፋ ላይ ዝርግትግት ብሎ ትኝቷል፡፡ተጠጋውና በመጠየፍ አንገቱን ይዞ አወዛወዛው.. ለበድንነት የቀረበ ሁኔታ ላይ ነው ያለው፡፡
አለማየሁ‹‹ቶሎ ብለን ሀኪም ቤት እንውሰዳቸው››ብሎ ቀድሞ ሄደና ሰቅስቆ አቀፋቸው…ሁሴን የተንንዘላዘለ እግራቸውን በመደገፍ ሊያግዘው ሞከረ፡፡ሰሎሜ ተከተለችው…፡፡አላዛር ወደኃላ ቀረና

‹‹..አንቺ እዚሁ ጠብቂን…አይዞሽ ሰውዬው በቀላሉ የሚሞት አይነት ሰው አይደለም…አትጨናነቂ››አላት፡፡

የንግግሩ ይዘት አልገባትም፡፡ግራ በመጋባት አይኖቾን አቁለጨለጨችበት፡፡ ትከሻዋን በእጆቹ ቸብ..ቸብ እያደረገ‹‹አይዞሽ አትጨነቂ አልኩሽ እኮ…ያለውን ነገር እየደወልኩ አሳውቅሻለሁ፡፡ የሚያስተኙት ከሆነ  ጥዋት መጥቼ ወደተኛበት ሆስፒታል ወስድሻለው››ሲል ቃል ገባለት፡፡

ምርጫ ስላልነበራት
‹‹እሺ..አመሰግናለሁ..እግዜር ይስጥልኝ› ›ስትል መለሰችለት፡፡

አላዛር ፊቱን አዞረና ወጥቶ ሄደ..ጓደኞቹ አባትዬውን ላዳ ውስጥ አስገብተውት ነበር የጠበቁት….፡፡
አለማሁ ቀልቡ እዛ ቤት የቀረችው ወይዞሮ ላይ ተጣብቆ ስለቀረ ዝም ብሎ ላዳዋ ውስጥ ሊገባ አልቻለም፡፡

‹‹ እሷ አትመጣም እንዴ?››ሲል አላዛርን ጠየቀው…፡፡

‹‹ምን ትሰራላች ላዳዋ ለእኛም እኮ አትበቃንም፡፡››

‹‹አይ ድንጋጤ ላይ ስላለች ብቻዋን ትፈራለች ብዬ ነው፡፡››ለእሷ ይሄን ያህል ምን እንዳሳሰበው አያውቅም፡፡ግን ድንገት በጨረፍታ እንዳያት በዛው እስከወዲያኛው ሊረሳት አልፈለገም፡፡

አላዛርም ስጋቱ ተጋባበትና‹‹ለምን ከሶስታችሁ አንዳችሁ አብራችኋት አትሆኑም?››የሚል ሀሳብ አስከተለ፡፡ ሰሎሜን፤ ሁሴንንና አሌክስ እርስ በርስ ተያዩ…‹‹አንተ አብረሀት ሁን..ሁለት ሴት አብረን ከመፍራት ውጭ ምን እረዳታለው?ሁሴንም ቢሆን ወረቀት የሌለበት ቤት ያቃዠዋል››ስትል  ሰሎሜ  የራሷን ሀሳብ አቀረበች ፡፡

አለማየሁ በቀረበው ሀሳብ በመደሰት‹‹በቃ እሺ… እኔ አብሬት ሆናለው…ግን ያለውን ነገር በስልክ አሳውቁኝ፡፡››በማለት መስማማቱን አሳወቀ፡፡

አላዛርም‹‹አመሰግናለው አሌክሶ›› አለና ገቢና ገባ ፡፡ሰሎሜ ና ሁሴን ከኃላ  አባትዬውን ከግራና ቀኝ ደግፈው  ተቀመጡ… አሌክስ መልሶ ወደ ጊቢው ሲገባ ላዳዋ ተነቀሳቀሰች፡፡

አለማየሁ ወደጊቢ ገብቶ የሳሎኑን በር ሲቆረቁር…ወዲያው ብርግድ ተደርጎ ተከፈተ..ከበራፉ ጋር.. ያልጠና የወጣትነት ልቡም ነበር አብሮ የተበረገደው፡፡እሷ በራፉን ስትከፍት አላዛርን ነበር የጠበቀችው…ጓደኛው ሆኖ ስታገኘው ግን ግራተጋብታ

‹‹ምነው…ምን እረሳችሁ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ ምንም አረሳንም…ብቻሽን እንዳትሆኚ አብረሀት ሁን ብለውኝ ነው››

ነበር?››አለችው ከግራ መጋባቶ ሳትላቀቅ‹‹ውይ እኔ ምን ሆናለው ?እነሱን ብትረዳቸው አይሻልም፡፡

‹‹ሶስት እኮ ናቸው..እንደውም ከባለላዳው ጋር አራት ናቸው..እሱም  የሰፈር ልጅ ስሆነ ያግዛቸዋል፡፡››

‹‹ጥሩ እሺ ግባ››ብላ በራፉን ለቀቀችለት፡፡በዝግታ እርምጃ ገባና ፊት ለፊት ያለ አሮጌ ሶፋ ላይ ተቀመጠ፡፡እሷም በራፉን ዛጋችና ከእሱ በአምስት ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ኩርሲ ላይ ጭብጥብጥ ብላ ተቀመጠች፡፡ለተወሰነ ደቂቃዎች ዝም ተባባሉ፡፡
ከገባችበት ሀሳብ እንደመባነን ብላ‹‹ወይኔ በእግዚያብሄር ዝም አልኩህ አይደል…?ሻይ ላፍላ ብና?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አረ ችግር የለውም….ከቻልሽ ውሀ ስጪኝ››አላት

‹‹ እሺ››ብላ ወደውስጥ ገባችና ውሀ በብርጭቆ አምጥታ ሰጠችው….ተመልሳ ወደ ጓዲያ ገባችና የተጣጠፈ ጋቢ እየዘራጋች መጥታ ‹‹ብርድ ነው ትከሻህ ላይ ጣል አድርገው›› አለችውና አቀበለችው… ተቀበላትና ለበሰው፡፡

‹‹የአላዛር ጓደኛው ነህ?››

‹‹አዎ ጎረቤት ነን..አብረን ነው ያደግነው..ወንድም በይኝ››

‹‹እሳቸውንም ታቃቸዋለህ ማለት ነዋ?››

‹‹ጋሽ ተሰማን…አዎ ለእኔም አባቴ በያቸው፤ግን መቼ ነው የተጋባችሁት…?›ሲል የገረመውን ጥያቄ ጠየቃት፡

‹‹ብዙም አልቆየን… አንድ ሰባት ወር ቢሆነን ነው…፡፡››

‹‹ትዳር ታዲያ እንዴት ነው?፡፡››

እንደማፈር አለችና ተሸኮረመመች‹‹ችግር የማያደርግህ ነገር የለም፡፡የምደገፍበት ቤተሰብ የማኮርፍበት ዘመድ ስላልነበረኝ እሷቸው ላግባሽ ሲሉኝ እምቢ ማለት አልቻልኩም፡፡..ምንም እንኳን በእድሜ ከአባቴ ሚበልጡ ሰውዬ እንደሆኑ ባውቅም….አምላክ ከፈቀደው ምንም አይደል እንደአባት ይንከባከቡኛል እንደባል ያስደስቱኛል ብዬ እሺኝ አልኩና ገባሁበት፡፡የተደበቀ አመላቸው አፈትልኮ ለመውጣት ግን አንድ ወር እንኳን አልፈጀበትም…፡፡በቃ ትንሽ መጠጥ ከቀመሱ ሙሉ በሙሉ ሌላ ሰው ሳይሆን ሌላ አውሬ ነው የሚሆኑት፡፡ከዛሬ ነገ ይሻሻላሉ በማለት

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ


ጭንቅ

ደጅ ፣ ደጁን አስሬ እየወጣች ትመለከታለች፡፡ የጣደችውን ቡና እየተንተከተከ ሳታነሳው አራት ሰዓት ሆነው፡፡

በህሊናዋ የተለያየ ሃሳብ እየተመላለሰ ረብሿታል፡፡ ምን ገጥሟቸው ይሆን ? እንዴው መኪና ተገልብጦ ይሆን? ከሰው ተጣልተው ይሆን? ነጋዴው አልመጣላቸው ይሆን ? ጥሩውንም መጥፎውንም ልቧ የገመተውንም ሁሉ እያወጣች እያወረደች ከራሷ ሃሳቧ ትሟገታለች፡፡

ኮሽ ባለቁጥር እየወጣች እየገባች እንቅልፍ የሚባል በአይኗ ሳይዞር ከአሁን አሁን ይመጣሉ እያለች ሌሊቱን ሳታምነው ቁጭ ብላ የማደር ያህል አነጋች፡፡ ጭንቀቱ ውሎም አድሮም አልተፋታትም፡፡

ተመስገንና ያሬድ ወሬያቸው እና ብቅታቸውም ሳይታይ ቀናት ተቆጠሩ፡፡

ተመስገንና ያሬድ ወሬያቸው እና ብቅታቸውም ሳይታይ ቀናት ተቆጠሩ፡፡

አበበች ሃሳብና ጭንቀቷ እየባሰባት ቢሄድም መፍትሄ አላገኘችም፡፡ ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡

የቻለው አባት አለች፡፡ አቶ ጎሹን በበራቸው ላይ ከብቶች ይዘው ሲያልፉ ድንገት አይታ፡፡ ታዲያ አቶ ጎሹን የቻለው አባት ብላ መጣራቷ በልጃቸው ስም ስለምጠራቸው ነበር፡፡

አቶ ጎሹ የቻለው አባት ወደ አለው ድምፅ መለስ አሉ፡፡ "ጠራሽኝ ልበል" ? አሉ ፤ ለአበበች፡፡

አዎ ፤ እኔ ነኝ የጠራዎት፡፡ ብላ ቀኑም እረፍዶ ስለነበር ሰላም አረፈዱ የቻለው አባት" አለች፡፡

"ሰላም አረፈድሽ አበበች፡፡ ምነው ደህና አይደለሽም ኖሯል? አሏት፡፡ አይን አይኗን እየተመለከቱ፡፡

"አይ! እኔ እንኳን ደህናነኝ፡፡ ባለቤቴ ከተመስገን ጋር ውሎ ገባ እንመለሳለን ብለው ወደ ድሬደዋ ሄደው ነበር፡፡ ይኸው ውሎ ገባ ሳይመለሱ ሰነበቱ፡፡ አሁንም ብቅታቸውም ጠፋ፡፡ እንዴው የማደርገው ሲጠፋኝ ነው፡፡ እርሶዎን የጠራዎት" አለች፡፡ መሬት መሬት እየተመለከተች፡፡

አቶ ጎሹ ታዲያ ምን ይሆናሉ ብለሽ ነው፡፡ መኪና አጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም የሄዱበት ሳይሳካላቸው ቀርቶ አድረው ለመምጣት አስበው ይሆናል፡፡ ለማንኛውም ምንም ማሰብ ፣ መጨነቅ የለብሽም፡፡ ደግሞ ወንድ ልጆች ናቸው፡፡ አድረው ይገኛሉ፡፡ ሴት ልጆች ቢሆኑ እንኳን አድረው አይገኙም ይባላል፡፡ ማታ ሊመጡ ይችላሉ ብለው አፅናንተዋት ወደ ከብቶቻቸው ተመለሱ፡፡

አበበች የመለሱላትን የማፅናኛ መልስ በትንሹም ቢሆን ለመረጋጋት ሞክራ መኪና አጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም ነጋዴው ሳይመጣ ቀርቶ ሰንብተው ይሆናል፡፡ ብላ በማሰብ ተመልሳ ወደ ቤቷ ገባች ፡፡

አበበች ማታ ይመጣሉ እያለች ስትጠብቅ የሷ ማታ ሳያልቅ ማታና ማታ ተደምሮ አምስት ማታ ቢሆንም እንኳን ያሬድና ተመስገን ሊመጡ አይደለም አየናቸው የሚል ሳታገኝ..ቆየች

ህልምነው ቅዠት ;

"አዎ ፤ ነግቷል ወፍ እየተንጫጫ ነው፡፡ ምነው ሰላም አላደርሽም እንዴ? አሉ፡፡ ቄስ መልካሙ ለባለቤታቸው፡፡ በሌሊት ተነስተው ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ እየተነሳሱ፡፡

"እንዴው ዛሬ ደግሞ ሲያቃዠኝ ነው ያደረው" አሉ ፤ ቄስ

"ኧረ ! እኔንም ሲያቃዠኝ ነው ያደረው፡፡ ያ ተመስገን ደህና አይደል ይሆን? ከያሬድ ጋር የምንሄድበት አለ ብሎኝ ነበር የሄደው፡፡ ማታ ይመጣል ብዬ ጠብቄው ነበር፡፡ ይሄው ሳይመጣ ዛሬ አምስት ቀኑን ያዘ" አሉ፡፡ አይናቸውን በሸማቸው እየጠራረጉ፡፡

"ከያሬድ ጋር ከሄደ ምን ይሆናል ፤ ብለሽ ነው?፡፡ ያሬድ ነጋዴም አይደል ፤ ምን አልባት አብሮት ይዞት ሄዶ ሊሆን ይችላል፡፡ ለማንኛውም እመቤቴ እንደፍቃዷ፡፡ እንግዴህ ቼር ነገር ታሰማን ፡፡ ዛሬ ደግሞ ተረኛ ገቢ ነኝ፡፡ ለቅዳሴ ሳይረፍድብኝ ልሂድ ፤ አንችም ተመስገን ካልመጣ ለከብቶቹ የሚበላ ፤ የታሰሩበት ስጫቸው፡፡ ስመለስ ውሃ አጠጣቸዋለሁ፡፡ ብለው ነጠላቸውን ለባብሰው ፤ ዘንጋቸውን ይዘው ፣ ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሄዱ፡፡

"እንዴው ዛሬ ደግሞ ምን ልታሰማኝ ይሆን ? ውስጤ የሚረበሸው ፣ እንግዴህ እመብርሃን አንች ታውቂያለሽ ፡፡ ያለዐንች ማን አለኝ እያሉ የጥዋት ፀሎታቸውን በቤታቸው የእንጨት ምሰሶ ስር በፊታቸው ተደፍተው የሚወዷትን የአገራቸውን ታቦት ጥሩ ነገር እንድ ታሰማቸው ተማፀኑዋት፡፡

ከተንበረከኩበት የእንጨት ምሰሶ ስር ተነሱ፡፡ ቤታቸውን በዶዶሆ ቅጠል ጠረግ ፣ ጠረግ አደረጉ፡፡ የሳር ድርቆሽ ከዓውድማ አምጥተው ለከብቶቻቸው ሰጡ፡፡ ሲያቃዣቸው ያደረውን ህልም ይሁን ቅዠት በሃሳባቸው እያወጡ እያወረዱ ለመፍታት ይግተረተራሉ፡፡ አንዴ በጥሩ ፣ አንዳንዴ በመጥፎ ፣ እየፈቱ እንደገና ደግሞ ህልም እንደፈችው ነው እያሉ ከራሳቸው ሃሳብ ጋር ይከራከራሉ፡፡

ታዲያ ወ/ሮ አሰገደች ሳይታወቃቸው ሰዓቱ እረፍዷል፡፡ ቁርስ እንኳን ሳይቀምሱ ባለቤታቸው ከቤተክርስቲያን የመምጫቸው ሰዓት ተቃርቧል፡፡

ቄስ መልካሙ ከቅዳሴ እንደ ወጡ ዛቲ ቀምሰው ለምዕመናኑ አሳርገው ፣ ከብቶቻቸውን ውሃ የሚያጠጣላቸው ስለሌለ ፣ እንዳይረፍድባቸው ሰንበቴያቸውን ቀምሰው ገበታ እንደተነሳ ተነስተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

ከብቶቻቸው ከማሰሪያቸው ሳይፈቱ ደረሱ፡፡ የተሰጣቸውን የሳር ድርቆሽ መብላታቸውን ትተው ቆመዋል፡፡ ያ! ተመስገን አልመጣም ማለት ነው፡፡ ቢመጣ ከብቶቹን ውሃ ያጠጣቸው ነበር እያሉ ወደ ቤት ገቡ፡፡

"ዛሬ ደግሞ ሰንበቴ ሳትገባ ነው እንዴ የመጣኸው"? አሉ ፤ ወ/ሮ አሰገደች፡፡

"አልቆየሁም ፤ እንጅ ደረስ ብያለሁ፡፡ ከቅዳሴም ስንወጣ አረፈድን ፤ ዝክርና ክርስትና ስለነበር ፤ሰንበቴ ቶሎ አልገባንም፡፡ ብለው ተመስገን አልመጣም እንዴ"? አሉ፡፡

"እስከ አሁን አልመጣም፡፡ እኔም አበበች ጋር ሄጀ እጠይቃለሁ ብዬ ነበር፡፡ ከቤትም ሳልወጣ እየተንደፋደፍኩ ምንም የረባ ስራ እንኳን ሳልሰራ አንተም መጣህ"፡፡

ከብቶቹን ላጠጣና እስከምመለስ ካልመጣ አይተን እኔ አበበች ጋር ሄጄ እጠይቃታለሁ፡፡ ብለው ከብቶቻቸውን ከታሰሩበት ፈትተው ውሃ ለማጠጣት ወደ ወንዝ ወረዱ ፤ ቄስ መልካሙ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች ባለቤታቸው ከወንዝ እስኪመለሱ ቡና አፍልተው ጠበቋቸው፡፡

ከብቶቻቸውን አጠጥተው ተመለሱ፡፡ የጤፍ ጭድ የሚበላ ሰተው ፈልቶ የጠበቃቸውን ቡና ከባለቤታቸው ጋር እየጠጡ ነው፡፡

እንዴው ያ! ማንደፍሮ የሚሸጥ ባህርዛፍ አለ ብሎኝ ነበር፡፡ ጠዋት ቤተ ክርስቲያን አግኝቸው እጠይቀዋለሁ ብዬ ሳልጠይቀው እረሳሁት፡፡ አሁን ደረስ ብዬ ልምጣ መሰለኝ ፡፡

"እንዴ! ቅድም አበበች ጋር ሄጀ እመጣለሁ አላልከኝም?፡፡ እማንደፍሮ ጋር በሌላ ቀን አይደርስም"? አሉ ፤ ወ/ሮ አሰገደች፡፡

"ምን ያህል እቆያለሁ፡፡ በቁሜ ደረስ ብዬ የሚሸጠውን ባህርዛፍ አይቼ ቶሎ ስመለስ እሄዳለሁ፡፡

ታዲያ ቄስ መልካሙ ባለቤታቸው ያሉትን ለጊዜው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ተነስተው ወደ ማንደፍሮ ቤት አቀኑ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች ከአዳራቸው አንስተው ቀኑን ሁሉ ውስጣቸው ሲረበሽ መዋሉ እረብሿቸዋል፡፡ ልጀ ምን ሆኖ ይሆን ? እንዴው ከቤት እንኳን ወጥቶ አያውቅ፡፡ ከያሬድ ጋር ከተማ መሃል ተጠፋፍተው ይሆን ? ክልብ ክልብ ሲል መኪና ባልገጨብኝ ብቻ፡፡

ለአስር ዓመታት የተለየቻቸውን ብርቅየ የአንጀታቸው ክፋይ የሆነችው ልጃቸውን እድላዊትን ወደ ኋላ፤ ተመልሰው አስታወሱ፡፡ እንባቸው በሁለቱም አይኖቻቸው ግጥም አለ፡፡ ለመመለስ በውስጥ
ቀሚሳቸው ጠራርጉት፡፡ ከአንጀታቸው የመጣ እንባ መመለስ ግን አቃታቸው፡፡ በተቀመጡበት እንደ እንኳይ ኮለል እያለ እንባቸው ይዘረገፍ ጀመር፡፡

ቄስ መልካሙ ቆይተው ለአይን ያዝ ሲያደርግ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

Читать полностью…

አትሮኖስ

ሶስቱም ለእሷ የተለየ እይታ አላቸው…ከመቼ ጀምሮ እሷን መውድድ እንደጀመሩ ማንኛቸውም አያውቁም፡፡ምን አልባት እናቷዋ እቅፍ ላይ ሆና ጡት ስትጠባ ጀምሮ ሊሆን ይችላል፡፡ምን አልባት እናቷ  ህፃን ሆና እርቃኗን እያገላበጠች ፀሀይ ስታሞቃት ካዩበት ቀን ጀምሮ ሊሆን ይችላል…ምን አልባት ዕቃ እቃ ሲጫወቱ ባልና ሚስት ተባብለው ከእሷዋ ጋር ከተጣመሩበት ጊዜ አንስቶ ሊሆን ይችላል…ማንኛቸውም በእርግጠኝነት መነሻ ቀኗን አያውቁም፡፡ግን  በእሷ ሲፎካከሩና ሲጣሉባት የልጅነት ጊዜያቸውን ጨርሰው የጉርምስና ጊዜቸውን እንዳገባደዱ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡አዎ…እሷን መሀል አስገብተው ማስካካትና መጫወት የሁል ጊዜ ስራቸው ነበር፡፡እሷም ያንን ትወደዋለች…እንደውም አንዳንዴ ሌሎች ተጨማሪ ወንዶች እሷን በማድነቅ ቢቀላለቀሉና እርስ በርስ ሽኩቻችውን የበለጠ ቢያደምቁላት ደስተኛ ሳትሆን አትቀርም…በሆነ ምክንያት ከመሀከላቸው አንዳችው  ሲጎድሉ  እንኳን ንጭንጯ     በግልጽ ያስታውቅ ነበር፡፡
እንግዲህ ሁሉም በተናጠል ግንኙነታቸውም  ሆነ በህብረት  ጥምረታችው በጣም ብዙና ተነግሮ የማያልቁ አስቂኝ እና አሳዛኝ ገጠመኞችና ትዝታዎች አሏቸው፡
ከወንዶቹ መካከል አላዛር  ከአይን ሞልቶ የሚፈስ ውበትና የተለየ ባህሪ ያለው ልጅ ነበር፡፡እሱ ሲናገር ለመስማት ሰዓታትን መጠበቅ የግድ ይላል…አምጦ አምጦ የሚናገራቸው ነገሮችም እርባን የሌላቸው አይነት ናቸው፡፡በአጠቃላይ አላዛር በጣም ጭምተኛና ድንጉጥ የሚባል ልጅ ነው፡፡አለማየሁ እና ሁሴን ደግሞ በጣም ረባሽና ጮሂዎች ነበሩ…አላዛር ሁል ጊዜ  እንደከፋውና እንዳለቀሰ ነው፡፡እርግጥ ከሁሉም የተሻለ ኑሮ ያላቸውና በቀን ሶስቴ ምግብ የሚቀርብበትና በአመት ሁለት ሶስቴ ቅያሬ ልብስ የሚገዛበት ቤተሰብ ነበር ያለው፡፡አባቱ በሆነ መንግስት መስሪያ ቤት ኦዲተር ነገር ነበር፡፡እና በወር ከሚከፈለው ደሞዝ በተጨማሪ የሆነ ቁርጥራጭ ገቢ ስላማያጣ  የተሻለ ኑሮ ነበራቸው፡፡አላዛር ሁለት እህቶች  ሲኖሩት ..ከሁሉም የተሻለ የሚያምር ልብስ እየለበሰ ከሁሉም  በተሻለ የሚጣፍጥ ምግብ እየበላ ለምንድነው ሁሌ አልቃሻና ሀዘንተኛ የሆነው?የሚለው ጥያቄ  ሁሉንም ነበር የሚያስገርመው፡፡.አደግ ብለው ክፉና ደጉን ማገናዘብ ሲጀምሩ ግን ሁሉም ጓደኞቹ በቀላሉ ነበር ችግሩን ያወቁለት፡፡የአላዛር ሀዘን ምንጭ የገዛ አባቱ ነበሩ፡፡.የአባትዬው እና የእናትዬው ዘወትር የማያባራ ጥል እና ግርግር በሰፈሩ ሁሉ የታወቀ ነበር፡፡አባትዬው ሁልጊዜ ጠጥተውና ሰከረው እየተወላገዱ እኩለለሊት ወደቤት በመምጣት እናቱን ይደበድባሉ፡፡ይሄ የዘወትር ቋሚ ስራቸው ነበር…ለጭምተኝነቱና ለፈሪነቱ ዋናው ሰበበ ምክንያት ያ እንደሆነ የሁሉም ሰው ግምት ነው፡፡አሁን በጉርምስና ጊዜውም ምንም እንኳን አባቱ ከእሱ ሆነ ከቤተሰቡ ተለይተው የራሳቸውን ህይወት መኖር ከጀመሩ አመታት ቢያልፉም በዛ ምክንያት እናትዬውን በሞት ቢነጠቅም…ፀባዩ ግን ብዙም ተቀየረ የሚባል ነገር የለውም…አሁንም መተከዝና መጨመት ያበዛል…አንድ የተቀየረ ነገር ቢኖር ከእድሜው በላይ ኃላፊነት የሚሸከም ጫንቃ ያለው ሰው ሆኖ ድንገት ብቅ ማለቱ ነው፡፡
ሁሴን ከአራቱም የተለየ የትምህርት ፍቅር ያለውና ጂኒዬስ የሚባል ተማሪ ነው፡፡ከክፍላቸው እሱ ሁል ጊዜ አንደኛ ሆኖ ሲሸለም ሶስቱም ጓደኞቹ ግን ደረጃቸው ከሰላሳ  በታች ነበር፡፡ሶስተኛ ክፍል እያሉ ከክፍል  ሁለተኛ ደረጃ ስለወጣ በደረሰበት ብስጭት  ሳምንት ሙሉ  ከቤት ሳይወጣ  ሲያለቅስና ሲነፈርቅ  እንደነበረ ትዝ ባላቸው ቁጥር ሆዳቸውን እስኪያማቸው ድረስ  የሚስቁበት መዝናኛቸው ነው፡፡
የአለማየው ታርክ ይለያል፡፡ከህፃንነቱ ጀምሮ ደፋርና ውሳኔ ለመወሰን የማያወላውል ነው፡፡ለመወሰን ከመቸኮሉ የተነሳ ሁል ጊዜ የማይጠበቁ ነገሮችን እንዳደረገ ነው፡፡አራቱም በጥብቅ የተሳሰሩ ጓደኛሞች ቢሆኑም የሰሎሜና የአለማየሁ ግን የተለየ የሚያደርገው ነገር አለ፡፡
ከህፃንነታቸው ጀምሮ በፊት አለማየሁ እና ሰሎሜ  አንድ የጋራ ግድግዳ በነበረው ሁለት የቀበሌ ቤት ውስጥ ነበር የሚኖሩት ፡፡በሂደት ግን የአለማየሁ ወላጆችን ሞት ተከትሎ በመሀክል የሚለያችው ግድግዳ በመሀከል ተቀዶ በራፍ ወጥቶለት አንድ ላይ አንድ ቤት ውስጥ መኖር ከጀመሩ አራት አመት አልፏቸዋል፡፡ ያ ማለት ሰሎሜና አለማየሁ የአንድ ቤት ልጆች ሲሆኑ ሁሴንና አላዛር ሲጨመሩበት ደግሞ የአንድ ሰፈር ልጆች ይሆናሉ ማለት ነው፡፡ምክንያቱም…የሁሴን ቤት ደግሞ ከእነሱ ቤት ፊት ለፊት መንገድ ተሻግሮ የሚገኝ ደሳሳና የበለዘ ቆርቆሮ ቤት ሲሆን የአላዛር ደግሞ ከእነሁሴን ቤት ሁለት መቶ ሜትር ፈንጠር ብሎ የሚገኝ ከሌሎቹ በመጠኑ ሻል ያለ የግል መኖሪያ ቤት ነው፡፡
እንግዲህ እነዚህ አራት ጓደኛሞች እንዲሁ እንደተጣበቁ የጉርምስና አፍላ  ጊዜያቸው ላይ  ደርሰዋል፡፡


💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 19 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

Читать полностью…

አትሮኖስ

ሽንት ሄዶ የነበረው ተመስገን ድንገት በሩን ከፍቶ ገባ፡፡ ባየው ነገር ግራ ተጋባ፡፡ ሰውነቱ ተርበተበተ፡፡

ልቡ መዓበል እንዳናወጣት መርከብ ተናወጠ፡፡ ገና የተፈጠረውን ሳይሰማ አይኖቹ ተጎልጉለው ሊወጡ ደረሱ፡፡ ለመናገር አልቻሉም፡፡ ምላሱ ተያያዘበት ለማንቀሳቀስ ሞከረ፡፡

ምምምምምምምምምምን ተፈጠረ አለ፡፡ የሞት ሞቱን የተናገረበትን አፍ ሳይዘጋ፡፡

"ይቺን ልጅ ታውቃታለህ ? አለ ፤ ያሬድ፡፡

ተመስገን የሚለው ጠፋ፡፡ አይኖቹ ከየሽሃረግ ላይ ድርቅ እንዳሉ ሰኮንዶች ተቆጠሩ፡፡ ምግብ እንደያዘ ሰው ለመናገር አፉን

አንቀሳቀሰ፡፡"እእእእእእእእእእእእእእእድላዊትን ትመ ..ብሎ ሳይጨርስ..

የሽሃረግ ራሷን ስታ ተዘረረች፡፡ ተመስገን አንዴ ብቻ ሁለተኛም ሳይደግም አንደበቱ ተቆላለፈ፡፡

አንዴ ሜዳ ላይ የፈሰሰ ውሃ አይታፈስ ነገር ሆኖበት፡፡ ያሬድ ግራ ተጋብቶ ይወድቃል ይነሳል፡፡

የሆቴሉ ዘበኛ ጫጫታና ጩኸት ሰምቶ እየሮጠ መጣ፡፡ የሽሃረግ በሁለት ልጆች መሃል ተከባ ተዘርራ አያት፡፡ ከመደንገጥ ውጭ ምንም አልተናገረም፡፡ ተመልሶ እየሮጠ ሄደ፡፡

ፖሊስ ይዞ መጣ፡፡ ተመስገንና ያሬድ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወሰዱ፡፡ የሽሃረግም ወደ ሆስፒታል ወሰዷት፡፡

ከሶስት ቀን በኋላ፤ እድላዊት ራሷን ከሳተችበት ነቃች፡፡ ያለችበት ቦታ ሆስፒታል ነው፡፡ ጉልኮስ በተኛችበት ክፍል ውስጥ በአይኖቿ አማተረች፡፡ አንድ የሃኪም ጋወን የለበሰች ወጣት መልከ መልካም ሴት ጋር አይኖቿ ተጋጩ፡፡

"ምን ሆኘ ነው እዚህ የመጣሁት? አለች፡፡

"አመም አድርጎሽ ነው፡፡ እዚህ የመጣሽው ፤ ለጊዜው እራሽን አታውቂም ነበር፡፡ አሁን ተሸሎሻል አይደል"? አለቻት፡፡ እንድትከታተላት ከስሯ የተቀመጠችው ሃኪም፡፡ በደንብ መንቃቷን እየተመለከተች፡፡

እድላዊት የሆነውንና የተፈጠረውን ለማስታወስ እየሞከረች ነው፡፡

"አሁን መነሳት አልችልም"

"ስለተሻለሽ ትችያለሽ፡፡ ብላ የተተከለላትን ግሉኮስ ነቀለችላት፡፡ ከተኛችበት መኝታ ላይ ከአንገቷ ቀና አድርጋ አስቀመጠቻት፡፡ ልታዋራት አይን አይኗን እያየች ልጠይቃት ያሰበችውን ሳጠይቅ በር ተንኳኳ፡፡ ሃኪሟ ተነስታ ከፈተች፡፡

ተመስገንና ያሬድ በሁለት ፖሊሶች ታጅበው እበር ላይ ግጥም አሉ፡፡ እድላዊት ከተቀመጠችበት ተነሳች፡፡ ከወንድሟ ከተመስገን ላይ ተጠመጠመችበት ፡፡ ሁለቱም በእንባ ጎርፍ ተጠመቁ፡፡

ፖሊስ ተመስገንና ያሬድ እድላዊትን አስገድገው ደፍረዋታል፡፡ በሚል ወንጀል ተከሰው ነበር ለፍርድ የቀረቡት፡፡

ታዲያ ቃለ መጠየቅ የተደረገለት ያሬድ ነበር፡፡ ያሬድ አልደፈርናትም ፤ ልጅቷ ከቤተሰቦቿ ከጠፋች አስር ዓመት አድርጋ ነበር፡፡ አሁን በአጋጣሚ ከወንድሟ ስትገናኝ ማመን አቅቷት ነው፡፡ እራሷን ስታ የወደቀችው፡፡ እንጅ እኛ ምንም አላደረግናትም ነበር ያለው፡፡ ፖሊስ ያሬድ በሰጠው ቃል መሰረት እድላዊትን ወደ ተኛችበት ሆስፒታል ሄዶ አጣራ፡፡ ያሬድ የሰጠው ቃል ትክክል መሆኑን ባየው ነገር አምኖ ተመስገንና ያሬድ ከስርቤት ተለቀው..

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 18 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

Читать полностью…

አትሮኖስ

Free ተለቋል።✅✅✅✅
ቤቲንግ ለጠመመባቹ ብቻ።

ከኛ ጋር የማይቻል ይቻላል
ድንቅ አዲስ ቻናል፣ ምን ትጠብቃላቹ፣ ተቀላቀሉ እና የድሉ ተካፋይ ሁኑ

Читать полностью…

አትሮኖስ

ጎራቤቶችን በመስደብ አቀያይሞታል… .ውበቷን አርግፎታል..አቅሞን አክስሟታል…እና ይሄን ሁሉ ስለሚያውቅ እንደውም በራሱ ጊዜ እቤቱን ለቆ ባይወጣ አንድ ቀን በተኛበት አንቃ ሁሉ ልትገድለው ትችላለች የሚል ተስፋ ነበረው፡፡እናትዬው ግን በዛ ሁሉ መከራ ውስጥም ሆና ከእሱ ጋር መኖር መቀጠሉን  እንዲህ አምርራ መፈለጎን ሲያይ ‹‹አባቴ ብቻ ሳይሆን እናቴም በሽተኛ ነች ››የሚል እምነት አደረበት፡፡‹‹አባቴ ሰውን በማሰቃየት የህይወት እርካታ የሚያገኝ ሲሆን እናቴ ደግሞ በገዛ ባለቤቷ በመሰቃየት የምትደሰት ነች ›› የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰ፡፡

የአባትዬውን ቤቱን ለቆ ከወጣ በኃላ የተፈጠረው ሁለተኛው ችግር የኢኮኖሚ ነው፡፡አባቱ ከሚያገኘው ደሞዝ ቢያንስ ግማሹን ለቤት ወጪ ይሰጥ ስለነበርና ከቤት ከወጣ በኃላ ያ ስለተቆረጠ በቤት ውስጥ የኢኮኖሚ ችግር ተከሰተ… ምክንያቱም እናቱ ምንም ስራ ያልነበራት የቤት እመቤት ስትሆን ልጆቹም ገና ትምህርት ላይ የሚገኙ ነበሩ፡፡
አላዛር ግን ወዲያው አሰበና የእናቱ እናት አያቱ ጋር በመሄድ ሁኔታውን በማስረዳት የተወሰነ የመነገጃ ብር በመቀበል እቤታቸው ፊት ለፊት አንድ አነስተኛ ሱቅ ሰርቶ ሸቀጣ ሸቀጥ መነገድ እና ቤተሰቡን በገቢ መደጎም ጀመረ..ግማሽ ቀን ይማራል ግማሽ ቀን ደግሞ ይሰራል፡፡እሱ ትምህርት ቤት በሚሆንበት ጊዜ እህቶቹ ወይም እናቱ ይሸጡለታል…እና ቤተሰቡን በመደጎም እራሱንም ማሳደግ ጀመረ፡፡

አባትዬው ለቀው ከወጡ በኋላ ግን እናትዬ ሁለት አመት ሳይቆዩ ሞቱ፡፡የሀያ አምስት አመት ዱላ..ስድብና ስቃይ ያልገደላቸው.. የሁለት አመት የባላቸው ናፍቆት ነፍሳቸውን አሳጣቸው፡፡ይሄ አላዛርን ይበልጥ አባቱን እንዲጠየፍና እንዲጠላ ልክ አንደእናቱ ገዳይም እንዲያያቸው ዋና ምክንያት ሆነው ፡፡ከዛ በኋላ ትልቅ ሰው ለመሆን ወሰነ..ካለጊዜው አድጎ የራሱንም ሆነ እህቶቹን ኃላፊነት ወሰደ፡፡ንግዱ ላይ ጠንክሮ መስራት ቀጠለ..ተሳካለትም፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 19 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

Читать полностью…

አትሮኖስ

"እኔ እኮ ስምሽን ሲጠሩሽ የት ተዋውቃችሁ ብዬ ነበር፡፡ ደሞም ያዘዙልሽ ቢራ ነበር፡፡ ቢራ እንደማትጠጭ ስለማውቅ አትጠታም ብዬ ነው፡፡ ለስላሳ የታዘዘልሽ ፡፡
የሽሃረግ ቢራ ምን ምን እንደሚል ቀምሳ አታውቅም፡፡ ሁሌም ያሰክረኛል እያለች ትፈራለች፡፡ በደረሰበት አትደርስም ፡፡ ጓደኛዋ የታዘዘልሽ ቢራ ነበር ስትላት ለመቅመስ ጓጓች፡፡ ግን አንድ ብጠጣ ምን እሆናለሁ? ያሰክረኝ ይሆን እንዴ? አለቻት ለመቅደስ፡፡

"አንድ ቢራ እኮ አያሰክርሽም፡፡ ቀምሰሽ ስለማታቂው ነው እንጅ ከለስላሳ ምንም አይለያይም ፡፡

"ለመቅመስ ፈልጌ ነበር ይቅርብኝ፡፡ ይሄው የለመድኩት ለስላሳየ ይሻለኛል" አለች፡፡

ተመስገን የውስጥ ፍላጎቱን ደፍሮ ለመናገር አልፈለገም፡፡ ግን ፍላጎቱን ያሬድ ተረድቶታል፡፡

"የሽሃረግን ጥሪልን አለ ፤ ያሬድ ለመቅደስ፡፡

"ኧረ ! እሽ አትለኝም ፡፡

የከተማ ልጅ ሆና ቢራ ለምን አትጠጣም ? አንች እየጠጣሽ አይደለ እንዴ ፡፡

"እኔማ እየጠጣሁ ነው፡፡ እሷ ግን ጠጥታ ስለማታውቅ ነው ፡፡

"ለአንችም ጠጭ፡፡ ለእሷም ምንም አይልሽም በያትና አንድ ስጫት ፡፡

"አሁንም ቢራ ጠጭ ተብለሽ ታዞልሻል፡፡ ደግሞም ለአንችም ለወደፊት መልመድሽ ስለማይቀር አንድ ቅመሽ ብላ ሐረር ቢራ ከፍታ ሰጠቻት፡፡

የሽሃረግ በጓደኛዋ ተገፋፍታ ቢራ መጠጣት ጀመረች፡፡ እንደ ለስላሳ መስሏት ጭልጥ ጭልጥ አድርጋ ጠጣችው፡፡ አይኖቿ ድፍረት አገኙ፡፡

ተመስገንን በስርቆት ማየቱ ቀርቶ አትኩራ ማየቱን ተያያዘችው፡
እነ ተመስገን ከገቡ አንስቶ ውስጧ ሰላም አላገኘም፡፡ ለጓደኛዋ ግን የተናገረችው ነገር አልነበረም የሽሃረግ፡፡

በመልኳም ይሁን በፀባይዋም ጨርቁን ጥሎ ያላበደላት ፣ ያልሻፈደላት የመንግስት ሰራተኛ ይሁን ባለ ሃብት አልነበርም፡፡ የሽሃረግ ግን ትዳርም ይሁን ጓደኛ ለመያዝ ፍላጎት አልነበራትም፡፡ እስከ አሁን ድረስም ከአይኗ የገባና ልቧን ያማለለው ወንድ አልገጠማትም ነበር፡፡

ዛሬ ግን ተመስገን በጉንጮቹ ላይ መስመር ሰርተው የወረዱት አሪዝ ፂሙና አይናፋርነቱ ልቧን የወሰደባት ይመስላል፡፡ ባንኮኒ ውስጥ ሆና በአይኖቿ ሰረቅ እያደረገች ትመለከተዋለች፡፡ አንዳንዴ ዲምላይቱ ፈገግ ሲል አይን ለአይን ሲጋጩ እንደ ማፈር እያለች ፊቷን ታዞራለች፡፡

የቀመሰችው አንድ ሃረር ቢራ ድፍረትን ያላበሳት ይመስላል፡፡ አይኗ ብዥ ብዥ አለባት፡፡

"አንች ጠጭ ጠጭ ምንም አይልሽም ብለሽኝ አሁን እኮ አዞረኝ" አለች፡፡ ለጓደኛዋ መቅደስ፡፡

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 19 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

Читать полностью…

አትሮኖስ

◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

ቀነ ጎደሎ

ጨለማ በተቀላቀለበት ሌሊት ተነሱ፡፡ ወደ አዳማ ለመሄድ ተቻኩለዋል፡፡ ከቡቲካቸው አልባሳት እና ሌሎች እቃዎችንም ጫኑ፡፡ እንዳይረፍድባቸው ሹፌሩን ፍጥነት ጨምሮ እንዲነዳ አዘዙት፡፡ ከወትሮው በተለየ መልኩ ደብሯቸዋል፡፡ ሰውነታቸውን ከብዷቸዋል፡፡ ፊታቸውን ጨፍጓቸዋል፡፡ አፋቸውን እሬት እሬት ብሏቸዋል፡፡ ደጋግመው አፋቸውን በባዶው አላመጡት፡፡ ለውጥ ግን  አላመጣላቸውም

ለሹፌሩ "ዛሬ ደግሞ ምን እንደሆንኩ እንጃ አፌን እሬት እሬት እያለኝ ነው" አሉት፡፡

"ምነው ቁርስ አልበሉም እንዴ?" ደግሞ ደስተኛ አይመስሉም፡፡ ደህና አይደሉም"? አለ፡፡ ሹፌራቸው ሰለሞን፡፡
"ኧረ ! ደህናነኝ፡፡ ብቻ ውስጤ እርብሽብሽ ብሏል፡፡ ሌሊትም ደግሞ ሲያቃዥኝ ነው ያደረው፡፡ ጥዋትም ቁርስ ወደ አፌ ስል አልዋጥ አለኝ፡፡ ምን እንደሆንኩ ለራሴም ሊገባኝ አልቻለም አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡

"አስበውት ያላሳኩት ነገር አለ እንዴ"?

"አስቤ ያላሳካሁት ነገር እንኳን ያለ አይመስለኝም፡፡ ምንአልባት ዛሬ ማርፈዴ ብቻ ነው ትንሽ ያበሳጨኝ፡፡ ለምን እንደረፈደብኝም ሳላውቅ ከሩቅ የሚመጣ ደንበኛ ነበረኝ ያሬድ የሚባል፡፡ እንዴው ጠብቆኝ ሲያጣኝ ባልተመለሰ ብቻ እንጅ ቢያድግልኝ እንኳን ከሱቅ የትም ስለማይሄድ አምሽተንም ብንደርስ እናገኘዋለን፡፡ ለማንኛውም ነዳጅ ሰጠት አድርገህ ቶሎ ቶሎ ንዳው ፡፡

"እሽ አሁንም እኮ ፈጥነናል፡፡ ግን እኔም እኮ እጄ ሁሉ ተሳሰረብኝ" አለ ሰለሞን፡፡

"ምነው አንተ ደግሞ ምን ሆነህ ነው ? ስትጨፍር እና ስትጠጣ አድረህ ፤ ምን አልባት እንቅልፍ መጥቶብህ እንዳይሆን"?

"እንኳን ስጠጣ ፣ ስጨፍር ላድር ፤ የጨብስም አጥቼ የዘጠኝ ብር አህያ መስየ ነው፡፡ ያደርኩት ፡፡

.አቶ ላንቻ የሰለሞን ፈሊጣዊ ንግግር አሳቃቸው፡፡ የዘጠኝ ብር አህያ ማለት ደግሞ ምን ማለት ነው? መቼም የዛሬ ልጆች የማታመጡት ጉድ የለም ፡፡

በመስኮት አይናቸውን ወርወር አደረጉ፡፡ ከበስተቀኝ በኩል የጋኔል ቁራጭ የሚመስል ጥቁር ውሻ ሊያቋርጣቸው ይሮጣል፡፡ ሰለሞን አፍጥነው ፣ አፍጥነው መኪናውን ፤ ይሔ ውሻ ሳያቋርጠን ፤ እንቅደመው አሉ፡፡ ሆዳቸው ተርፏ ተርፏ እያለ፡፡

ማርሽ ቀየረም ፤ ነዳጅ እረገጠም ፤ ውሻውን ግን ሊቀድመው አልቻለም፡፡ ውሻው አቋርጧቸው አለፈ፡፡

"ጭራሽ መንዳትም አቃተህ ፤ ውሻ መቅደም ያቅትህ አሉ፡፡ በፊታቸው ላይ የደም ስራቸው በንዴት እየተወጣጠረ፡፡

"መኪናው ሰርቪስ ከገባ ቆይቷል፡፡ ፍጥነት ጨምሬ ስነዳ እንዳይቆም ስለፈራሁ ነው፡፡ እንጅ ውሻ መቅደም አቅቶኝ አይደለም" ፡፡

የባሰ በጭንቀት ላይ ጭንቀት ሆነባቸው፡፡ መኪናው ከመንገድ ላይ እንዳይቆም ስጋቻ አደረባቸው፡፡ብቻ እንዳያዋርደን የባሰ ለማርፈዱ ሲቆጨን ከመንገድ ላይ ቆሞ፡፡ "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" እንደ ሚባለው ከሁለት አጉል እንዳንሆን፡፡ እያሉ ከአፋቸው ተናግረው ሳይጨርሱ መኪናው ማዞሪያ ላይ መሪው አልዞር አለ፡፡ መስመር ሳተ፡፡ ሰለሞን ላብ በላብ ሆነ፡፡ ጎትቶ የማስገባት ያህል መልሶ ወደ መስመር አሰገባው፡፡

አቶ ላንቻ ከአሁን አሁን ተገለበጠ እያሉ ሰለሞን መሪው ሲያዞር ያገዙት ይመስል አንገታቸውን አብረው ያዞሩ ነበር፡፡

ከመስመር ሲገባ ትንሽ ትንፏሻቸው መለስ አለ፡፡ በል አሁን ቀስ ብለህ ንዳ የትም ጫካ እንዳታስቀረኝ አሉ ፤ እየፈሩም ቢሆን፡፡

"አሁን እግዚአብሔር ነው ያተረፈን ፡፡ ተገልብጦብኝ ነበር፡፡ እንጃ ብቻ ዛሬ በሰላም የምንገባ አልመስለኝም፡፡ ሆዴ ሁሉ በጣም ፈርቷል ፡፡

በስ መዓብ በል፡፡ ደግሞ ታሟርታለህ እንዴ ? አንዳንዴ ማሟረት ጥሩ አደለም፡፡ አፍ ሊከተል ይችላል አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡

"አሁን ደግሞ ጭሱ መሽተት ጀምሯል፡፡

"እስኪ አቁመህ ውረድና እየው፡፡ የጭስ መውጫው ታፍኖ ይሆናል፡፡

ሰለሞን ወርዶ አየው፡፡ መኪናው ከመሽተት ውጭ የሚታይ ነገር አላገኘም፡፡ ተመልሶ ከሁለተኛ ማርሽ ወደ ሶስተኛ ማርሽ ቀይሮ ነዳ፡፡

የባሰ የመኪናው ድምፅ ተቀይሮ የመኪና ድምፅ መሆኑ ቀርቶ እንደ ወፍጮ መንኮራኮር ጀመረ፡፡ በስጋቻ አይኖቹ ተርገበገቡ፡፡ ቀኑ ወደ ጨለማ ተቀየረበት፡፡ አንዳንዴ የመኪና መብራት ያበራል፡፡

የመኪና መብራት የምታበራው መንገዱ አልታይ አለህ"? እንዴ አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡

አንዳንዴ ጨለማ እየመሰለኝ ነው እኮ፡፡ አሁንማ እጄ ሁሉ እየተንቀጠቀጠብኝ ነው፡፡ እስኪ ከእኔ ይሻሉ እንደሆን ይሞክሩት ፡፡

"እኔ ከአንተ እሻላለሁ ብለህ ነው፡፡ ምን አይነት ቀነ ጎደሎ ነው ፤ የገጠመን ዛሬ፡፡ እያሉ የሰለሞን ቦታ ቀይረው መኪናውን ለመንዳት መሪውን ጨበጡ፡፡ የባሰ እጃቸው ተሳሰረ፡፡ ግራና ቀኝ ዋዥቁ፡፡

"ፍሬን ይያዙ ፣ ፍሬን ይያዙ ፣ መስመር ስቷል፡፡ እያለ ጮኸ ሰለሞን፡፡ መኪናው ግን አልቆመም፡፡ እስከ አሁን ታግሸ አገለገልኳችሁ፡፡ የዚህ አለም ኑሮ ይበቃኛል፡፡ ብሎ አራት እግሩን ወደ ላይ ሰቅሎ ከመስመር በታች ወርዶ ተከረበተ፡፡

የፈሩት አልቀረም፡፡ ሰለሞን በደረሰው አደጋ ወዲያውኑ ህይወቱ ሲያልፍ አቶ ላንቻ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው ህይወታቸው ቢተርፍም ወደ ህክምና ሲሄዱ ጭንቅላታቸው በጣም ተጎድቶ ስለነበር ህክምናም ሳይደርሱ ህይወታቸው በመንገድ ላይ አለፈ፡፡

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 19 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

Читать полностью…

አትሮኖስ

ጅንጀና style part 1
😘😘😘😘😘😘😘
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

Читать полностью…

አትሮኖስ

‹‹እ..አይዞህ ዘና በል ፡፡አይመጡም..፡፡ምሳ ይዘው ነው የሚሄዱት…፡፡በጣም ፈጠኑ ከተባለ..ማታ 12 ሰዓት ላይ ነው የሚመጡት፡፡››
በረጅሙ አየር ወደውስጡ ሳበና‹‹እሰከዛ ሰዓት  ታዲያ ብቻሽን ነው የምትሆኚው?››
‹‹ለምን ብቻዬን ሆናለው…?አንተ አለህ አይደል?››
‹‹አይ ዛሬማ አለሁ…ለሌላው ቀን ነው ያልኩሽ፡፡››
‹‹አዎ…ብቻዬን ነው ምሆነው....ግን እንደምታስበው አይከብድም.. ቤት ሳፀዳ ፣እቃ ሳጥብ…ምግብ ሳዘጋጅ…ሳላስበው ነው መሽቶ የሚነጋው፡፡ እኔ የሚከባደኝ ቀን ብቻዬን መዋሉ ሳይሆን ማታ እሳቸው ሰክረው መጥተው ሚረብሹኝ ነገር ነው፡፡ደግሞ እኮ ሁሌም ቤት አልሆንም.. አልፎ አልፎ አስቤዛ ለመግዛት ዋጣ እላለሁ…እህል ላስፈጭ ወፍጮ ቤት ሄዳለሁ….መብራት ልሞላ መብራት ሀይል ሄዳለው……››
ይሁን ..ካሁን በኃላ ግን ብቸኝነት ሲሰማሽ እኔጋር ደውይልኝ›››
‹‹እና ሁሌ ስደውልልህ ትመጣልኛለህ››
‹‹አዎ..ትምህርት ቤት ካልሆንኩ በደቂቃ ውስጥ ነው የምመጣልሽ››
ከተቀመጠችበት ተነሳችና ወደእሱ ጠጋ ብላ ጎንበስ አለችና ጉንጩን በስሱ ሰማው.‹‹ታድዬ››ብላው ወደጓዲያ ገባች፡፡
እሱ በቀኝ እጁ መዳፍ  የሳመችውን ጉንጭ እየዳበሰ እንደፈዘዘ ቀረ፡፡ከደቂቃዎች በኃላ ለሁለቱም ሻይ ይዛ መጣችና አጠገባቸው የነበረች አነስተኛ  ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ ቁጭ አለች፡፡
ስድስት ሰዓት ተኩል አካባቢ ምሳ አቀረበችና ልክ እንደአዲስ ጎጆ ወጪ ሙሽሮች አይን ለአይን በስስት እየተያዩና እየተጎራረሱ ምሳቸውን በሉ፡፡
‹‹አየሩ ትንሽ ይሞቃል አይደል››አለችው የበሉበትን እቃዎች አነሳስታ እና ጠረጴዛውን አፀዳድታ ፊት ለፊቱ እየተቀመጠች፡፡
‹‹አዎ…እኔን ብቻ ነው እንዴ ሚመቀኝ እያልኩ በውስጤ እያሰብኩ ነበር፡፡››አለና የለበሰውን ጃኬት አውልቆ ከጎኑ ያለው ሶፋ ላይ ጣል አደረገው፡፡እጅጌው ጉርድ በሆነ ጃፖኒ ቀረ፡፡፡ሰውነቱ ፈርጣማ ስለሆነ አይን ይገባል፡፡
‹‹ታዲያ እኔስ ምን ላድርግ ቀሚሴን አላወልቅ?››
ሳቀ….ተሳሳቁ….
‹‹እንደውም አንድ ሀሳብ አለኝ …ከሳሎኑ ይልቅ መኝታ ቤቱ ቀዝቀዝ ይላል…..ና እዛ እንሁን ›› ብላ ቀድማ ተነሳችና እጁን ይዛ ወደመኝታ ቤት ይዛው ገባች፡፡ ለመስዋዕትነት እንደተመረጠ የዋህ በግ ዝም ብሎ ተጎተተላት፡፡አልጋው ጠርዝ ላይ ስትደርስ እጁን ለቀቀችና…የተጫማችውን ነጠላ ጫማ አውልቃ አልጋ ላይ ወጣችና ተጋደመች፡፡
ግራ በመጋባት አፍጥጦ እያያት ነው፡፡በህይወቱ እንደዚህ አይነት ነገር ገጥሞት አያውቅም….እና አሁን ምን ማድረግ እንዳለበት አላወቀም..‹‹ና ጋደም በል እንጂ…ምነው ፈራህ እንዴ?››አለችው፡፡
‹‹አረ ምን ያስፈራኛል?››አለና እሱም እንደ እሷ ጫማዋን አወልቆ አልጋ ላይ ወጣና አንድን ትራስ ለብቻው ተንተርሶ ከእሷ ሰውነት 20 ሳ.ሜትር ያህል ክፍትት ትቶ ተኛ፡፡ምን ልታወራ ነው ብሎ ሲጠብቅ፡፡
‹‹ይቅርታ …በዚህ ሰዓት ትንሽ ማሸለብ ለምጄለሁ…አንድ አስር ደቂቃ ብተኛ ቅር ይልሀል?››ስትል ጠየቀችው፡፡
‹‹አረ ችግር የለውም…ተኚ››አላት
‹‹እሺ..አለችና ወደእሱ ተጠግታ ደረቱ ላይ ተንተራሰችና አይኖቾን ጨፈነች፡፡››
ሳሎኑን ለቆ ወደመኝታ ቤት የመጣው ሙቀቱ እንዲቀንስለት ነበር፤አሁን ግን ይበልጥ ሰውነቱ እየነደደበት ነው፡፡ወደጎን የተዘረጋ እጁን ቀስ ብሎ አነሳና አቀፋት ፡፡ቀስ ብሎ አይኖቹን አጣሞ ሲያያት ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ የገባች ትመስላለች፡፡ትንፋሿ በአንገቱ አካባቢ ሲበተንበት ልክ ግንቡ እንደተደረመሰ የውሀ ማቆሪያ ግድብ ደሟ እንዳለ ወደታችኛው የሰውነቱ ክፍል ሿሿ እያለ ሲፈስና ብልቱን ሲወጣጥረው እየተሰማው ነው፡፡እንዳቀፋት ገልበጥ አለና ሙሉ በሙሉ ወደእሷ ዞረ፡፡እንደተቃቀፉ ተጣባቁ፡፡አንደኛውን እግሯን አነሳችና ታፋው ላይ ጫነችበት፡፡በዚህ ጊዜ የለበሰችው ቀሚስ ወደላይ ተሰበሰበ…ወደታች ሲያይ የሚያጓጓው ጭኗ ለእይታ ተጋልጦል፡፡የሚንተከተክ የወጣትነት ስሜቱን ይህን አይነት ፈተና ተቋቁሞ እንዲያልፍ አላደረገው፡፡በወቅቱ ስለምንም ነገር የሚያስብበት ሁኔታ ላይ አልነበረም..ቀስ አለና ከንፈሩን ወደከንፈሯ  በማስጠጋት ልክ ውብ ፅጌረዳ አበባ እንደምትቀስም ሰራተኛ ንብ ተጣበቀባት…ቀስ አድርጎ በስሱ ሳማት፡፡መልሳ ሳመችው….ከዛ በኃላ ያለው ነገር ከአእምሮ ስሌት ውጭ ስለሆነ ለመግለፅ እራሱ ከባድ ነበር፡፡መኝታ ቤት አልጋ ላይ  የተጀመረው ፊልሚያ ከ40 ደቂቃ በኃላ  ሳሎን ሶፋ ላይ እርቃን ሆነው ነበር የተገባደደው፡፡ከዛ በኃል ይሄ ድርጊት ማንም ጆሮ ሳይደርስ ለስድስት ወር ለበለጠ ጊዜ ሲደጋገም ነበር፡፡

💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 16 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014

Читать полностью…

አትሮኖስ

"አሁን የለመንኩሽና በልጅሽ ስም የተማፀንኩሽ ነገር ብሎ.. የነበረውን ድርጊት ሲያነሳ ውስጡ እንደገና ተረበሸ፡፡ እንባ ሲተናነቀው መናገሩን ትቶ አለቀሰ፡፡

ምን እንደምትረዳው ከአሁን አሁን ሊነግረኝ ነው እያለች ገና ምን እንደሆነ ሳታቅ እሽ በማለቷ ፍራት ፍራት ብሏታል፡፡

"እባክህ ማልቀሱን ተውና ንገረኝ?፡፡ እኔንም እኮ አስጨነከኝ አለች፡፡

ተመስገን ከማልቀሱ መለስ አለ፡፡ በባለፈው ከያሬድ ጋር ድሬ የሄድን እለት እድላዊትን ያገኘናት የሆቴል ሰራተኛ ሆና ነበር፡፡ እኛም በአጋጣሚ እድላዊት የነበረችበት ሆቴል አልጋ ይዘን ስናድር ሳንተዋወቅ ከእድላዊት ጋር አብሬያት አድሬ የተዋወቅነው ጠዋት ነበር፡፡ እና አሁን የወለደችው ልጅ ከእኔ ነው፡፡ የልጁ ክርስትና ስለደረሰ የማን ተብሎ ይነሳ አገሩ ደግሞ የአባት ስም ካልታወቀ ክርስትና መጠመቅ አይችልም፡፡ አሁን የምለምንሽ የልጁ ክርስትና እስከሚያልፍ ድረስ የአባቱ ስም በያሬድ አድርገን ክርስትናው ካለፈ በኋላ ፤ የተፈጠረውንና የተደረገውን እውነቱን አውጥተን የሚሰጠንን የሃጢያት ፍርድ እንቀበላለን ብሎ አይኖቹን የቤቱ ወለል ላይ ተከላቸው፡፡

አበበች የሰማችው ነገር ግራ የሚያጋባ ፤ ለማመን የማይከጀል ፤ በትዳሯ ላይና በሂወቷ ላይ ሰማይ የተደፋባት መስሎ ታያት፡፡ ታዲያ በምትወደው ልጇ በምትኩ ስም ሲማፀናት እሽ ብትልም ባለማወቅ ስለሆነ እሽ ያለችው ነገሩን ስትሰማ ግን ቸኩላ እሽ በማለቷ ተደበላለቀባት፡፡ ደግማ እሽ ሳትለው የባለቤቷ የያሬድን አይን ተመለከተች፡፡

"አንተስ ምን አስበሃል? የምሰማው እውነት ነው?፡፡ የምታቀውስ ነገር አለ? አለች፡፡

"ድርጊቱ የተፈፀመው ባለመተዋወቅ እንደሆነ እኔም አውቃለሁ፡፡ አሁን ተመስገን የጠየቀሽ ግን ለትዳራችንም ይሁን ለሂወታችን ጋሬጣ እንደሚሆን ጥርጥ የለውም፡፡ ነገር ግን ከተመስገንና ከእድላዊት ስቃይና መከራ አይበልጥብንም፡፡ እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር የለምና ለእግዚአብሔር ብለን እንርዳቸው፡፡ ባይሆን ተመስገን እንዳለው ልጁ ክራስትና ከተጠመቀ በኋላ፤ እውነቱን ተናግሮ በስህተት እንደ ሆነ ቤተሰቦቻቸውን አሳምነን ተመስገንና እድላዊት ንሰሃ እንዲገቡ ማድረግ ነው አላት፡፡

አበበች በትዳሯ ላይ ትንሽ የማይባል ነገር ወደ ፊት እንደሚገጥማት ብታስብም የተደበቀው ሚስጥር በቅርብ ቀን ስለሚወጣና ባለቤቷ ያሬድ እንርዳቸው ስላላት ለወደፊት የሚደርስባትን ስቃይና መከራ ወደ ጎን ትታ በባለቤቷ ሃሳብ ተስማምታ አንተ ከተስማማህ እኔ ከአንተ ውጭ አይደለሁም፡፡ ብላ ለተመስገን የሚያስደስት መልስ ሰጡት፡፡

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 16 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

Читать полностью…

አትሮኖስ

💰💵 በቤቲንግ መበላት ሰልችቷችኋል❓

እንግዲያውስ ይሄን ቻናል ተቀላቅላችሁ ትርፋማ ሁኑ ✅ ማየት ማመን ነው 🏆

Читать полностью…

አትሮኖስ

‹‹እንዴ!! ጥዋት ይወጣሉ ብለዋል እኮ፡፡ ይዞ መሄዱ አስፈላጊ ነው?፡፡

‹‹ቢወጡ እኮ ሶስት አራት ሰዓት ነው….እስከዛን ሰዓት ድረስ ዝም ብለን እዚህ ከምንጠብቅ …ብንሄድ ይሻላል፡፡››

‹‹ካልሽ ጥሩ….እሺ ምን ላግዝሽ?››

‹‹ምንም… ይልቅ ቁጭ በልና አውራኝ››

‹‹ማውራትማ ቀላል ነው.. አወራሸላሁ›› ብሎ ከፊት ለፊቷ ካለ  ሶፋ ላይ ተቀመጠ…..፡፡
ቀላልና ቀልድ አዘል ወሬ እያዋራት ቁርሱን ስርታ ጨረሰች..፡፡አቀረበችና አብረው በሉ…፡፡ወደሆስፒታል የሚሄደውን በሳህን ቆጥራ ዝግጁ ሆነች..፡፡ወደውስጥ ገባችና ልብሷን ቀየረች፡፡ተመለሳ መጣችና‹‹አሁን መሄድ እንችላለን››አለችው
ከተቀመጠበት ተነሳ

‹‹ግን ከመሄዳችን በፊት ስልክ ቁጥርሽን አትሰጪኝም ?››አላት፡፡

‹‹ምን ሊያደርግልህ..?አብረን አይደል የምንሄደው?››አለችው በመገረም፡፡

‹‹አይ ለዛሬ አይደለም…ሌላ ቀን እንዴት እንደሆንሽ መጠየቅ ብፈልግ እንዴት አገኝሻለው…?ደግሞ የሆነ ችግር ደርሶብሽ እርዳታ ብትፈልጊ እንዴት ደውለሽ ታገኚኛለሽ?››አላት፡፡ ልክ ለብዙ ጊዜ አብረው ኖረው ብዙ ታሪክ አሳልፈው ሊለያዩ እንደተቃረቡ ወዳጆች አይነት ስሜት ነው እየተሰማው ያለው፡፡

ለደቂቃዎች በቆመችበት ፈዛ ስታየው ከቆየች በኃላ‹‹እና የሆነ ነገር ቸግሮኝ ብደውልልህ..መጥተህ ታግዘኛለህ ማለት ነው?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ….?በደንብ ነዋ፡፡››

ከአይኗቾ እንባዋ ረገፈ፡፡አለማየሁ ያንን ሲያይ ደነገጠ‹‹ምነው ምን አጠፋው…?ምን ክፉ ነገር ተናገርኩ?››ሲል በመርበትበት ጠየቃት፡፡

‹‹አይ ..ደስ ብሎኝ ነው…የሆነ ችግር ሲያጋጥመኝ ደውዬ ድረስልኝ የምለው ሰው መኖሩን በማወቄ የሆነ የማላውቀው አይነት የደስታ ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡››ብላ ትክክለኛ የውስጧን ስሜት ነገረችው፡፡
‹‹አይዞሽ በእኔ ተማመኚ…አሁን ቁጥርሽን ስጪኝ፡፡››

‹‹የለኝም …ሞባይል የለኝም..እንደምታየው የቤት ስልክም የለንም››

‹‹ሲያበሳጭ…ታዲያ ምን ይሻላል?፡፡››

‹‹ለምን ያንተን ቁጥር አትሰጠኝም..፡፡እኔ ሲመቸኝ ከሱቅ ወይም የሚያስደውለኝ ሰው ሳገኝ ደውልልሀለው…ቆይ ወረቀትና እስኪሪፕቶ ላምጣ››

‹‹ወረቀት ብቻ አምጪ እስኪሪፕቶ አለኝ›› አላት፡፡፡

ወደውስጥ ገባችና አንድ አሮጌ አጀናዳ ይዛ መጣች፡፡ተቀበለና በመጨረሻው ገጽ ላይ ስሙንና ሞባይል ቁጥሩን ፃፈላት፡፡ከዛ ተያይዘው ወጡ፡፡

አለማየሁ ሆስፒታል ካደረሳት በኃላ ብዙም ሳይቆይ ነበር  እሷንም ሆነ አላዛርን ተሰናብቶ ወደቤት የተመለሰው…፡፡


💫ይቀጥላል💫

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 18 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref630645014

Читать полностью…

አትሮኖስ

ለወራት ታገስኳቸው...ሲያቅተኝ ብን ብዬ ወጣሁና ወደአገናኘችን ሴትዬ ሄጄ በቃኝ አልፈልግም…ሰው ቤት ተቀጥሬ በጉልበቴ ብኖር ይሻለኛል፤አፋቺኝ አልኳት፡፡….በማግስቱ የነፍስ አባታቸውን አስከትለው መጥተው እግሬ ላይ ተደፉ፡፡ሁለተኛ አይደገመኝም፤የመጀመሬያ ቤቴን አፍርሼ ልጆቼንና ባለቤቴንም ያጣሁት በዚህ አመሌ ነው፡፡እባክሽ አንቺንም ማጣት አልፈልግም ፡፡.አንድ እድል ብቻ ስጪኝ ብለው በምስክሮች ፊት ምለው ሲገዘቱ …እምቢኝ ብል ጡር ይሆንብኛል ብዬ እሺኝ አልኳቸውና ተመለስኩ፡፡››

‹‹ከዛ ታዲያ ውጤቱ ምን ሆነ?››ሲል በጉጉት ጠየቃት፡፡

‹‹ይሄው ተሻሻሉ ተመስገን ብዬ ለፈጣሪ ስለቴን ካስገባሁ በኃላ እንደምታየው ጥንብዝ ብለው ሰክረው መጡ፡፡የገቡት ቃልና የማሉት መሀላ ደረሰባቸው መሰለኝ…እንደበፊቱ ልደባደብ ብለው ከመወራጨት ይልቅ አረፋ እየደፈቁ ፀጥ አሉ…እይይ …ምን አይነት እድል ነው ያለኝ?፡፡››
የምትወደውን ባለቤቷን የሞት መርዶ እንደተነገራት ሚስኪን ሴት ስቅስቅ ብላ በማልቀስ እንባዋን ትዘረግፈው ጀመር፡፡አለማየሁ ደነገጠ፡፡.ከመቀመጫው ተነሳና ወደእሷ ተንቀሳቀሰ ፡፡እጇን ያዛትና ከተቀመጠችበት ኩርሲ አስነስቶ አሮጌው ሶፋ ላይ አጠገቡ አስቀመጣት፡፡ ከእሷ ተለጥፎ ተቀመጠ፡፡.ምን እያደረገ እንዳለ ለራሱም አልገባውም.፡፡እንዲህ የማድረግ ድፍረቱን ከየት እንዳመጣው አያውቅም፡፡

ልጅቷ ለቅሶዋን አስፋፍታ ቀጠለች፡፡እጁን አነሳና በትከሻዋ አዙሮ አቀፋት…ልጥፍ ብላበት ፊቷን አንገቱ ስር ቀበረችና መነፍረቋን ቀጠለች፡፡.እንባዋ እየተንጠባጠበ በአንገቱ በመንኳለል ወደታች ወደጀርባው ሲዘልቅ እየተሰማው ነው…እምባዋ ሀዘን ብቻ ሳይሆን ንዴትም እና ቁጣም የተቀላቀለበት ሳይሆን አይቀርም በጣም ያቃጥላል..ወይም ሚያቃጥል አይነት ስሜት ነው የተሰማው፡፡
‹‹አይዞሽ፡፡አንቺ ወጣትና ቆንጆ ልጅ ነሽ፡፡ብዙ ምርጫ አለሽ……››ልክ በህይወት ውጣ ውረድ ተፈትኖ ብዙ ተራራ ወጥቶ ብዙ ዳገት ወጥቶ ህይወትን አብጠርጥሮ እንደተረደ ጎልማሳ ሰው አይነት ነው በልበሙሉነት እየመከራት ያለው፡፡እርግጥ አለማየሁ በእድሜው ገና 18 ዓመቱ ይሁን እንጂ በችግር ከማደጉ በልጅነቱ እናትና አባቱን በማጣቱ ምክንያት በሀዘንን ውስጥ በማለፉ ከሰው ተጠግቶ ከእጅ  ወደአፍ በሆነ ኑሮ እያደገ እንዳለ ወጣት ቀላል የማይባል የህይወት ግንዛቤና ያለው እና  የኑሮ ውጣ ውረድ ያጣጣመ ልጅ ነው፡፡ ስለሆነ  አሁን የሚናገረው ንግግር  ከእሱ የሚጠበቅ አይደለም ሊባል የሚችል አይደለም፡፡

‹‹አይ ተወኝ ባክህ..አሁን አሁንማ ተስፋ እየቆረጥኩ ነው…እኔም እንደወላጆቼ ምናለ ቢገድለኝ››ሰትል አሳዘነችው…

እሷም እንደእሱ ወላጅ አልባ መሆኗን ማወቁ ስሜቷን በጥልቀት እንዲረዳት ያድርገው ወይስ በውበቷ ተጠልፎ ስለወደቀ ታሳዝነው አያውቅም፡፡..ይበልጠ ጨምቆ ከደረቱ ለጠፋትና ቀኝ እጁን የተንጀረገገ ሉጫ ፀጉሯ ውስጥ ከቶ ያሻሽላት ጀመር፡፡ቀስ በቀስ ለቅሷዋን እየቀነሰች….በተወሰነ መንገድም እየተረጋጋች መጣች፡፡የስልክ መንጫረር ነበር ሁለቱንም ካሉበት ስሜት ባነው እንዲነቁ እና ከተቃቀፉበት እንዲላቀቁ ያደረጋቸው፡፡ስልኩን ከኪሱ አወጣና ከተቀመጠበት ተነስቶ ቆመ..አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ አላዛር…ጋሼ እንዴት ነው?››

‹‹እኛ እንሰቃይ እንጂ እሱ ምን ይሆናል…?››በመነጫነጫ መለሰ፡፡

‹‹ህክምና አገኙ?››

‹‹አዎ ታክሟል… አሁን  ነቅቷል››

‹‹እና እየመጣችሁ ነው?››አለማየው ከገመተው ጊዜ  ፈጥነው  ጨርሰው እየመጡ እንዳለ ገመተና ቅር ተሰኘ..ይህቺን ሚስኪን ሴት የበለጠ ሊያወራትና የበለጠ ሊፅናናት ፈልጎ ነበር፡፡ታመው ሆስፒታል ከተወሰዱት የጓደኛው አባት ይልቅ ይህቺ አጠገቡ ያለች ሚስኪን ሴት ነች የበለጠ የታመመችው….ቀድሞውኑ የዛ ሰውዬ መታመም ምንም አላስቸነቀውምም. አላሳዘነውምም.. በውድቅት ለሊት ከእንቅልፉ ተነስተቶ የመጣው ለጓደኛው ሲል ነበር፡፡ግን እንኳን መጡ ..ባልመጣ ይህቺን ከመሰለች ውብ ጋር አልገናኝም ነበር››ሲል ተፅናና፡፡‹‹እሷ ነች የበለጠም ተንከባካቢና አስታማሚ ሚያስፈልጋት፡፡››ሲል ስልኩን ጆሮው ላይ እንደለጠፈ አሰበ፡፡.ለዛ ደግሞ ከእሱ የተሻለ ሰው እንዳማታገኝ አምኗል..እና ለዛነው ቅር የተሰኘው፡፡
አላዛር ግን የሚያስደስተውን ነገር ነው የነገረው፡፡‹‹ሀኪሞቹ ዛሬን እዚህ ማደር አለበት ብለዋል..አልጋ ይዞል››

‹‹እንደዛ ነው ..ታዲያ ምን ይሻላል?››ሲል የጓደኛውን ሀሳብ ለማወቅ ጠየቀ፡፡

‹‹አሌክሶ..እዛው ብታድር ቅር ይልሀል?››ሲል በጣም የሚፈልገውን ነገር ፈራ ተባ እያለ በልምምጥ ቃና ጠየቀው፡፡
አለማየሁም ፈጠን ብሎ ‹‹አይ ቅር አይለኝም››ማለት አልፈለገም ….ስሜቱን ላለማጋለጥ ዙሪያ ጥምዝዝ መሄድ ፈለገ‹‹ችግር የለውም..ግን ሰሎሜስ እንዴት ትሆናለች?››ሲል ያላሳሰበውን ነገር እንዳሳሰበው አድርጎ ጠየቀ፡፡

‹‹እሷን ሁሴንን በላዳው ልካቸዋለው…ሁሴን እቤት ያስገባታል?..ያው ያንተን ያህል ስለሚወዳት ክፉ ነገር እንዲያገኛት አያደርግም››አለው ፡፡

‹‹ሽሙጥ መሆኑ ነው…እንደዛ ከሆነ እሺ… ››ሲል ተስማማ፡፡

‹‹በል ደህና እደር ››
‹‹ደህና እደር… ችግር ካለ ደውልልኝ››ብሎ ስልኩን ዘጋውና በተቀመጠችበት ኩርምት እንዳለች ወደላይ አንጋጣ ወደምታየው ሴት አዘቅዝቆ ማየት ጀመረ፡፡

‹‹ምን አለህ?››

‹‹ጋሼ ነቅተዋል..መድሀኒት ስለተሰጣቸው እስከጥዋት እዛው ሀኪም ቤት መቆየት አለባቸው ተብሏል››

በረጅሙ ተንፍሳ‹‹ይሁን… ተመስገን ነው፡፡››አለች፡፡

‹‹ነግሬሻለሁ እኮ ..አንቺ ብዙም አትጨናነቂ ..ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል››

‹‹ለዛሬ ሰላም ቢሆን ምን ዋጋ አለው…?.ነገም ሰላም መሆኑን ማረጋገጫ ከሌለኝ ምኑን እረጋጋለሁ፡፡››
‹‹ቢሆንም …እራስሽን በሀዘን መጉዳት የለብሽም….ሁላችንም ብንሆን እኮ ነገ ምን እንደሚፈጠር እርግጠኛ ሳንሆን ነው ዛሬን ተደስተን እና አጣጥመን ለመኖር  እየመኮርን ያለነው፡፡››
‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ..ግን ብዙ ሰው  እንዳልከው ስለነገ በእርግጠኝነት መናገር ባይችልም መገመት ግን  ይችላል..ቢያንስ ወደየት እየተጓዘ እንዳለ የመንገዱ ጫፍ ላይ ያለው ጭላንጭል አምፑል ይታየዋል….የእኔን ግን ድፍን እና ጨለማ ቤት ውስጥ  ያለች ነፍስ በለኝ፡፡በራፍም መስኮትም ያሌለበት ድፍን ጨለማ ቤት…የእኔ ህይወት በእንደዛ አይነት ወጥመድ ውስጥ ነች››

‹‹አረ በፈጣሪ አሁን ሁሉን ነገር እርሺው…እስቲ ዘና ብለሽ ተቀመጪ››
አቀማመጧን በመሳተካከል ሰውነቷን ለቀቀ ለማድረግ ሞከረች፡፡

‹‹አሁን ቀስ ብለሽ በጥልቀት ወደውስጥ አየር ሳቢ..››ሌላ ትዕዛዝ አዘዛት፡፡

‹‹ምን?››

‹‹እመኚን ያልኩሽን አድርጊ…››
እሱን ለማስደሰት እንዳላት አደረገች…‹‹አሁን ደግሞ በረጅሙ ወደውጭ ተንፍሺ….ከዛ ድገሚው…..አሁንም ድገሚው…..አሁንም….በቃ…..እንዴት ነው?››
በቆረጣ አይን አይኑን እያየች‹‹አመሰግናለው..አሁን ትንሽ ቀለል ያለኝ መሰለኝ ...አንተንም አስቸገርኩህ አይደል…?አመሰግናለሁ በጣም ጥሩ ልጅ ነህ››አለችው…፡፡

‹‹አንቺም በጣም ቆንጆ ልጅ ነሽ..ማለቴ ይቅርታ በጣም ጥሩ ልጅ ነሽ ለማለት ነው፡፡››

በንግግሩ እና በመርበትበቱ ተገርማ በመጠኑ ፈገግ አለችና..‹‹ችግር የለውም..እንደማስበው ማደርህ መሰለኝ››

‹‹አዎ..አንቺን በዚህ ሁኔታ ጥዬሽ ብሔድ እንቅልፍም አይወሰደኝም..ለዛውም እኮ 8 ሰዓት አልፏል …እየነጋ ነው..››

‹‹ጥሩ ››ብላ ከመቀመጫው ተነሳችና ወደውስጠኛው ክፍል መራመድ ጀመረች

Читать полностью…

አትሮኖስ

"ደግሞ የእሱ ማምሸት ምን ይሉታል ? ልጆቻችንን በትነን ጧሪ ቀባሪ እንኳን እንጣ"፡፡ እያሉ ወገባቸውን ይዘው ግቢ ግቢውን እንደ ፎካሪ ይንቆራጠጣሉ ፡፡ ወ/ሮ አሰገደች፡፡

"ምነው ደህና አይደለሽም ? ብቻሽን እንደ እብድ የምትለፈልፊው አሉ ፤ ቄስ መልካሙ፡፡

"እኔ እማ አላበድኩም ደህና ነኝ፡፡ አንተ ደግሞ ቶሎ እመጣለሁ ብለህ ሄደህ ትተኛለህ ? እኔ እንኳን ሄጄ እንዳልመጣ፡፡ እኔ ሄጄ እጠይቃለሁ ብለህ ሳትጠይቅ ይሄው መሸ፡፡ ተመስገንም ብቅታውም ጠፋ፡፡

"እኔማ ቶሎ እመለሳለሁ ብዬ ነበር አካሄዴ ፤ ግን ከማንደፍሮ ጋር እየተከራከርን አንድ ፣ ሁለት ስንል ፣ ተቀምጠን ፣ ሳይታወቀን ለአይን ያዘ ፡፡ እኔ እንኳን ተመስገን ይመጣል ብዬ ነበር፡፡ አሁን ታዲያ
ቢመሽም ደረሼ ልምጣ"፡፡ ብለው ጋቢያቸውን ለመልበስ ወደ ቤት ገቡ፡፡

ቄስ መልካሙ ጋቢያቸውን እየለባበሱ የሚነጋገር የሰው ድምፅ ከውጭ በኩል ሰሙ፡፡

"እንዴውም መጣ መሰለኝ፡፡ የሚነጋገር ሰው በውጭ በኩል ይሰማል" አሉ፡፡

"የሚነጋገረው መንገደኛ ይሆናል፡፡ ተመስገን ከመጣ ብቻውን ነው የሚመጣው፡፡ ከማን ጋር ይነጋገራል ፡፡

የሚነጋገረውን የሰው ድምፅ ለመለየት ከቤት እየወጡ፡፡ "ደህና አመሻችሁ መምሬ? አለ፡፡ አንድ ጎርነን ያለ የወንድ ድምፅ መሳይ፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ማን ልበል" ? አሉ ወ/ሮ አሰገደች፡፡

"የመሸበት እንግዳ ነው፡፡ ማሳደር አይቻልም እንዴ?" አለ፡፡

ማን ይሆን ደግሞ ከመሸ የመጣው፡፡ እንዴው አምላኬ ምን ልታሰማኝ ይሆን"? ደግሞ ሲናገር ንግግሩ እንደቀልድ ሆነባቸው፡፡ የቤተሰብ ሰው መሆኑን ተጠራጠሩ፡፡ ድምፁን ግን መለየት አልቻሉም፡፡ ማንነቱን ለማወቅ ወደ ውጭ በር ተጠጉ፡፡

ይግቡ ፤ ቤት የእግዚአብሔር ነው፡፡ ባይሆን አድረው ያደሩበትን የሞያተኛ ሰርተው ይሔዳሉ አሉ፡፡ ወ/ሮ አሰገደች ፤ ተራቸውን እንደመቀለድ ብለው፡፡

የሚቀላልድባቸውና የሚያሾፍባቸው ያሬድ ነበር፡፡ ልባቸው ለሁለት ተሰነጠቀ፡፡ ትንፋሻቸው ቁርጥ ፣ ቁርጥ አለ፡፡

"አንተው ነህ እንዴ የምታሾፍብኝ፡፡ ልጄ የታለ? ወዴት ቀርቶ ነው? ካንተ ጋር አልመጣም እንዴ? አሉት፡፡ ጥድፍ ጥድፍ እያሉ፡፡

"ኧረ ! ከእኔ ጋር ነው ለሽንት ወደ ኋላ፤ ቀረት ብሎ ነው፡፡ እኔ ቀደም ብዬ ነው አለ፤ ያሬድ፡፡

"ምነው ታዲያ በሰላም ነው የሰነበታችሁት ለመሆኑ፡፡ በል ና ግባ ፤ ለሽንት ከሆነ የቀረው ይመጣል፡፡ እንኳን በሰላም መጣችሁ እንጅ እያሉ ያሬድን ይዘውት ወደ ቤት ገቡ፡፡

ቄስ መልካሙ "ከማን ጋር ነው የምታወራው ብለው ከዘራቸውን ከመኝታቸው ስር አንስተው ቀና ሲሉ "ደህና አመሻችሁ መምሬ? አለ ፤ ያሬድ፡፡

"ደህና አመሸህ ያሬድ፡፡ ተመስገን የለም እንዴ ? አሉ ፤ በተራቸው ፡፡

ተመስገንና እድላዊት የውጭ በር ከፍተው ገቡ፡፡ ያሬድ መልስ ሳይመልስላቸው፡፡

"ደግሞ ከማን ሴት ጋር ነው የሚመጣው? ነው የሰው ልጅ ጠልፋችሁ መጣችሁ"? አሉ ፤ ወ/ሮ አሰገደች፡፡ ተመስገን ሁለት ሆኖ በጨለማ ውስጥ ሲመጣ አይተውት፡፡

እድላዊት በእናቷ እግሮች ላይ ተደፋች፡፡ እማዬ ማሪኝ አለች፡፡ አለቀሰች፡፡

የጠረጠሩት ሌላ ፤ ያዩት ሌላ ሆነባቸው፡፡ በድንጋጤ ተብረክርከው ቤቱ ወለል ላይ ወደቁ፡፡ ማመን አቃታቸው፡፡

እድላዊት እግራቸው ላይ ተደፍታ ስታለቅስ፡፡ የቤት ወለል ላይ አነሳቸው፡፡ ተመስገን እናቱን
ልጄ.. ልጄ....እድል…..እድል አንች ነሽ አቤት ልጄ! አቤት ልጄ! እድል አንች ነሽ? ተነሽ፡፡ ልጄ አንች አይደለሽም ጥፋተኛ እኔ ነኝ፡፡ የበደልኩሽ እኔው ነኝ፡፡

ልጃቸውን ተደፍታ ከምታለቅሰው እግራቸው ላይ አነሷት፡፡ በእቅፋቸው አቀፏት፡፡ ሁለቱም እንባቸውን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡

ቄስ መልካሙ በተቀመጡበት የድንጋጤ መንፈስ አስክሯቸዋል፡፡ ያዩትን ማመን ተስኗቸዋል፡፡ ልጃቸውን አዩዋት፡፡

እድላዊት ከእናቷ እቅፍ ተላቃ አባቷ በተቀመጡበት ተጠመጠመችባቸው ፡፡ በጉልበቷ ተንበርክካ አባየ ማረኝ አለች፡፡ የባሰ ሆድ ባሳት፡፡

ታዲያ የእድላዊት የአይኖቿ እንባ በአባቷ እግር ላይ ሲወርድ ላየ ሰው እንባ ሳይሆን የእግር መታጠቢያ ውሃ ይመስል ነበር፡፡

✨ይቀጥላል✨

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
atronose" rel="nofollow">https://www.youtube.com/@atronose

ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 17 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

Читать полностью…

አትሮኖስ

Wallpaper ወይስ Profile ይፈልጋሉ? 😍

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አላዛር አስራሁለተኛ ክፍል ተማሪና ነጋዴ እያለ ነው፡፡ በቀኑ በድካም የዛለ ሰውነቱን ለማሳረፍ ወደአልጋው የሚሄድበት ሰዓት ነው፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት  ሆኗል፡፡ቢሆንም ግን ከመተኛቱ በፊት የእለቱን ሂሳብ ቆጥሮና ወጪና ገቢውን መዝግቦ ማጠናቀቅ አለበት..ይሄ ሁል ጊዜ ወደአልጋው ከመሄዱ በፊት  መስራት ያለበት የግዴታ  ስራው ነው..ግን መዝግቦ ከመጨረሱ በፊት ስልኩ ጠራ፡፡የማያውቀው ቁጥር ቢሆንም ከስራ ጋር የተገናኘ ይሆናል በሚል ግምት አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ›

‹‹ሄሎ …አላዛርን ፈልጌ ነበር››ሳግ የተናነቀው የሴት ድምፅ ነው፡፡ግራ ገባው…፡፡በዛ ሰዓት እያለቀሰች እሱ ጋር የምትደውል  ሴት ማን ነች..ለመገመት አንኳን አልቻለም፡፡

‹‹አዎ አላዛር ነኝ፡፡ ማን ልበል?››

‹‹በዚህ ምሽት ስለደወልኩልህ ይቅርታ፡፡አስካለ እባላለሁ፡፡››

አስካለ የሚባል ስም ያላት ሴት ቢያስብ ሊመጣለት አልቻለም፡‹‹ይቅርታ አስካለ… አላወቅኩሽም፡፡››

‹‹አታውቀኝም..የአባትህ  ባለቤት ነኝ፡፡ ›

‹‹የአባትህ ባለቤት?››

‹‹አዎ ››

ሊገባው አልቻለም፡፡በመጀመሪያ ስለአባቱ ምንም ነገር መስማት አይፈልግም፡፡.ከዛም አልፎ አባቱ ባለቤት እንዳለው አሁን ገና መስማቱ ነው፡፡ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህቺ የአባትህ ባለቤት ነኝ የምትል ሴት ለምን እንደደወለችለት መገመት አለመቻሉ ነው፡፡

‹‹እና በሰላም ነው?››

‹‹እኔ እንጃ፣አባት ምን ጠጥተው እንደመጡ አልውቅም…. እራሳቸውን ስተው                         አረፋ እየደፈቁ ነው፡፡እኔ ለአካባቢውም ለሀገሩም እንግዳ ነኝ፡፡ምን እንደማደርጋቸው አላወቅኩም፡፡ እጄ ላይ እንዳይሞቱ ፈርቼለሁ፡፡እባክህ አንድ ነገር አድርግ››አለችው፡፡

‹‹ለመሆኑ ቁጥሬን እንዴት አገኘሽው?››

‹‹ከአባትህ ማስታወሻ ደብተር ላይ ነው ፡፡ልጄ አላዛር ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ ከዛ ላይ ነው ያገኘሁት፡፡››

ግርም አለው…አንደኛ አባቱ አላዛር የሚባል ልጅ እንዳለው የሚያውቅ አይመስለውም ነበር…ቢያውቅ እንኳን በቁም ነገር የእሱን ስልክ ቁጥር በማፈላለግ  በማሳታወሻው መዝግቦ ያስቀምጣል የሚል ቅንጣት ጥርጠሬ እንኳን አልነበረውም፡፡

‹‹እሺ ምን አልከኝ…?በፈጣሪ..ቢያንስ ለእኔ ስትል እርዳኝ፡፡›› ልስልስ እና እንስፍስፍ በሆነ የድምፅ ቃና ተማጸነችው፡፡
አረፋ እየደፈቁ ነው ከተባሉት አባቱ በላይ በሲቃ የምትንሰቀሰቀው የማያውቃት እንጀራ እናቱ  አሳዘነችው፡፡ ‹‹እሺ በቃ መጣሁ….እቤቱ ከጠፋኝ ደውልልሻለው… ወጥተሸ ትቀበይኛለሽ፡፡››

‹‹እሺ አመሰግናለው..እባክህ ቶሎ በል፡፡››

ስልኩን ዘጋና ጃኬት ደርቦ ከመሳቢያ ውስጥ ብር አንስቶ ወደኪሱ ጨምሮ ወጣ….መጀመሪያ ጓደኞቹ  ጋር ደወለ፡፡

‹‹አሌክስ ተኝተሀል እንዴ?››
በሻከረና በተዳከመ ድምፅ‹‹አዎ!! ምነው በሰላም ነው?››ሲል መለሰለት፡፡

‹የሆነ ችግር አጋጥሞኛል…አንድ ቦታ አብረኸኝ እንድትሄድ ነበር..፡፡››

አለማየሁ ከመኝታ ተነስቶ  ልብሱን እየለበሰ‹‹ምነው በሰላም?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹ፍጠን …ስትመጣ ነግርሀለው…››ብሎ ስልኩን ዘጋና የሚያውቀው ባለ ላዳ ጋር ደወለ..፡፡ላዳው መጥቶ ውስጥ ገብቶ ሲጠብቅ አለማየሁ ሰሎሜን አስከትሎ መጣ፡፡

‹‹እንዴ !!አንተን  ና አልኩህ እንጂ እሷን ይዘህ ና ብየሀለው?››
‹‹ምንድነው ችግርችሁ? የሴት ጉዳይ ነው እንዴ…? ልመለስላችሁ?››አለች ሰሎሜ… በኩርፊያ፡፡
‹‹አረ አይደለም..በዚህ ለሊት  በመንገላታትሽ አሳዝነሺኝ ነው››አላት፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ እሱም ጓደኛህ እኔም ጓደኛህ…..እሱ ካስፈለገህ እኔም አስፈልግሀለው ማለት ነው፡፡››

‹‹እሺ ግቡ››

ከኃላ ከፍተው ገቡ..ላዳዋ ልትንቀሳቀስ ስትል አለማየሁ‹‹ቆይ ሁሴንም ደውዬለት መጣሁ ብሏል.. ትንሽ እንጠብቀው››
አላዛር በሰማው ነገር ተበሳጨ‹‹እንዴ ማን ንገረው አለህ…?አሁን ሳምንቱን ሙሉ እንዳላጠና አዘናጋችሁኝ እያለ ሲነጫነች ነው የሚከርመው፡፡››

‹‹ባንነገርው ደግሞ‹እኔስ ጓደኛችሁ አይደለሁም ወይ?› ብሎ ሳምንት ያኮርፈናል››ሲል አለማየሁ መለሰለት፡፡

ሰሎሜ ‹‹እሱ እኮ….››ብላ ሀሳቧን ልትናገር ስትል ሁሴን ደርሶ የኃላዋን የላዳ በራፍ ከፍቶ ተቀላቀላቸው….ላዳዋ ተንቀሳቀሰች፡፡

እነዚህ አራት ጓደኛሞች ከአንድ መሀፀን እንደወጡ መንታ ልጆች ናቸው፡፡በክፉውም ቀን ሆነ በደጉ አብረው ናቸው፡፡
የአራቱ ጓደኝነት መነሻ ምክንያቱ አንድ ሰፈር ውስጥ ተፋፍጎ ከተሰራ ቤት ስለተወለዱ ብቻ አልነበረም፡፡የአራቱም እናቶች  ቡና የሚጠራሩ የአንድ ክለብ ተጫዋች አይነት ስለሆኑ ነበር…አንዳችው ቤት ቡና ተፈልቶ ሁሉም እናቶች ሲጠሩ ሁሉም የየራሳቸውን ልጆች ይዘው ይመጣሉ…ከዛ ሁሉም  ከእናታቸው  እቅፍ ውስጥ እየሾለኩ እርስ በርስ የመጫወት  ሙከራ ያደርጋሉ…ያ ደግሞ በተለየ መልኩ ከጮርቃነታችው ጀምሮ በተለየ ሁኔታ እንዲቀራረብ አደረጋቸው፡፡ የእናቶቻቸውን ጡት ሳይጥሉ የጀመረ ጓደኝነት …የእናቶቻችውን መሰባሰብ ሳይጠብቁ በራሳቸው ተጠራርተው በአንዳቸው ቤት በረንዳ ወይም  በሆነ ብጣቂ ሜደ መጫወት ተጀመረ…፡፡
ከዛ ትምህርት ቤት የገቡትም አንድ ላይ በአንድ ወቅት ነበር፡፡ሌላው ይቅር አንዳንድ የማይዳረሱ መፅሀፎች አንድ ለሶስት ወይም ለአራት ሲሰጥ ሳይነናጋገሩ ነው የሚቧደኑት፡፡ከመሀከላችን አንድ ሰው ሲጠቃም አንድ ላይ ድንገት አጥቂውን ይወሩታል፡፡ማንም ቢሆን በቁመትም ሆነ በውፍረት ከእነሱ  ቢበልጥ እንኳን አራት ሆነው አንደአንድ ለመፋለም ሲከቡት  ይፈራል፡፡በዚህም ምክንያት  ማንም እነሱን ለመጋፈጥ ድፈረቱ አይኖረውም፡፡
እንዳዛም ሆኖ  በህብረት ከሌላው ሰው ጋር ከሚጣሉበት  ይልቅ እርስ በርሳችው የሚጣሉበት ጊዜ በብዙ እጥፍ ይበልጥ እንደነበረ ትዝ ይለዋል፡፡የጥላችው  90 ፐርሰንት ምክንያት ግን ሰሎሜ ነች፡፡በመሀከላቸው ያላችው አንድ ብቸኛ ሴት ሁላችውም በሆነ መንገድ ከሌላቸው የተሻሉ  ሆነው  በሆነ መጠን ወደእራሳቸው የበለጠ እንድታጋድል ስለሚፈልጉ ሁሉ ጊዜ የጥቅም ግጭት በመሀከላችው  ይፈጠር ነበር፤እና ሁሉንም እኩል በመቆጣት ጥላችውን  አቁመው  በስምምነት እንዲከቧት  የምታስገድዳቸው እሷው ነች፡፡ሰሎሜ በዛ የጓደኝነት ክበብ ውስጥ ልክ እንደንግስት ንብ አይነት ነበረች፡፡
ንግስት ንብ ትውልድ ከማስቀጠል በተጨማሪ ፌርሞን የተባለ ኬሚካል ታመነጫለች፡፡ፌርሞን ሚስጥራዊ ኃይል ያለው ንጥረ ነገር ሲሆን  በአንድ ቀፎ ውስጥ በጋራ የሚኖሩ ንቦችን የውል እና የጋራ ባህሪን  በበላይነት ለመቆጣጠር የሚረዳ ረቂቅ ኬሚካል ነው፡በዛ ኬሚካል አማካይነት ንግስቲቱ በዙሪያዋ ያሉትን እሰከ60 ሺ የሚቆጠሩ የንብ መንጋዎችን ሰጥ ለጥ አድርጋ  ትመራለች ፤ ትቆጣጠራለች፡፡ፌርሞን ለንግስቲቱ የአገዘዛ እና  የኃይል ምንጭ ከመሆኑም በተጨማሪ  በመስክ ስራ ላይ ካሉ ንቦች ጋር መልዕክት የምትለዋወጥበት የመገናኛ አውታር ጭምርም ነው፡፡በተጨማሪ ፌርሞን በአንድ ቀፎ ውስጥ  በህብረት ለሚኖሩ  ንቦች እንደመታወቂያ ወረቀት ሆኖም ያገለግላል፡፡በአንዷ ንግስት የሚተዳደረው የንብ መንጋ ከሌላው ጋር ይለያል..ያ ማለት አንድ ንብ ከሌላ ቀፎ መጥቶ የተሳሳተ ቀፎ ውስትጥ ገብቶ ከሌሎች 60 ሺ   ንቦች ጋር ቢቀላቀል  ሰርጎ ገብ መሆኑን በቀላሉ ይለያል ማለት ነው፡፡
እንግዴህ ሰሎሜም ልክ እንደንግስቲቱ ንብ ሶስቱንም የምትቆጣጠርበት እና እንደፈለገች የምታዝበት የራሷ የሆነ ሚስጥራዊ መንገድ ነበራት፡፡

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስራ_አንድ


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

"አንች ጠጭ ጠጭ ምንም አይልሽም ብለሽኝ አሁን እኮ አዞረኝ" አለች፡፡ ለጓደኛዋ መቅደስ፡፡

"አንዱን ቢራ ጨረሽው እንዴ? ትገርሚያለሽ እንደለስላሳ ነው ስልሽ እንደለስላሳ ጨለጥሽው፡፡ በይ አሁን ቀስ ብለሽ አንድ ድገሚና ከዚያ በኋላ ይበቃሻል፡፡ ለነገሩ ቢራ አንድ ስለማይጠጣ ነው እንጅ በአንድ ቢበቃሽ ጥሩ ነበር፡፡

"አሁን አመመኝ እያልኩሽ ድገሚና ጠጭ ትይኛለሽ ? ብላ ብትኮሳተርም መድገሟ አልቀረም ሁለተኛ ቢራዋን አስከፈተች፡፡

በስካር መንፈስ ምሽቱ ወደ ቀን ተቀይሮበታል፡፡ አይመሽም እንዴ? ሆቴሉ አይዘጋም? ይላል ፤ ተመስን በውስጡ ፡፡

"ከአሁን በፊት ከሴት ጋር ተኝተህ ታውቃለህ"? እንዴ አለው ያሬድ፡፡

"ከሴት ጋር መተኛት አይደለም ለመተኛትም አውርቼ አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን ብተኛ ምን እሆናለሁ፡፡

"እና የትኛዋ ትሻልሃለች"?፡፡

"የሽሃረግ ትሻለኛለች ፤ እሽ ካለች፡፡

"እሽ ፤ እንጠይቃታለን ግን እንደ ገጠር ሴት ዝም ብለው እሽ አይሉም፡፡ ገንዘብ ይጠይቃሉ፡፡

"ለብር ችግር የለም፡፡ ብቻ እሽ አሰኝልኝ ፡፡

ያሬድ መቅደስን ለብቻዋ ጠርቶ ለማነጋገር ፈልጓል፡፡ ከመቀመጫው ተነሳ፡፡ መቅደስን ጠራት፡፡ ከሰው ጋር እንዴ? ብሎ ጠየቃት፡፡

"እኔ ከሰው ጋር ነኝ፡፡ የሽሃረግ ደግሞ እንደዚ አይነት ስራ ሰርታ ስለማታቅ አትወጣም አለችው፡፡

ደግሞ የከተማ ሴት እንደ ገጠር ነው እንዴ? በገንዘብ እሽ አትልም? ፡፡

"እሱማ ልክ ነህ ፤ እሷ ግን ስለማትሰራ ነው፡፡

ጓደኛየ ከአሁን በፊት ከሴት ጋር ተኝቶ አያውቅም፡፡ ዛሬ ምን እንደነካው እንጃ በየሽሃረግ አብዷል አላት፡፡

ብቻ ከእሷ ለመስማት እሽ ካለች እጠይቃታለሁ፡፡ ብላ ልጠይቃት እየፈራች ቢሆንም ተጠጋቻት፡፡ የሽሃረግ የጠጣችው የሐረር ቢራ አስክሯታል፡፡ ወደ ኋላ ያሰረችውን ሐር የሚመስለውን ፀጉሯን ለቃዋለች፡፡

ታዲያ አይኗን ሸፍኖት ትንሽ ትንሽ ነበር ፊቷ የሚታየው፡፡

መቅደስ የጠጣችው ቢራ እሷንም ሞቅ አድርጓት ስለነበር የሽሃረግን ሳትፈራ ስሟን አቆላምጣ የሺዬ ያሰውዬ ፎንቅቄያለሁ እያለ ነው አለቻት፡፡

"የቱ ነው"? አለች፡፡ ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ገለጥ እያደረገች፡፡

ቢራ ከጋበዙሽ አንደኛው ፡፡ ያ የፂሙ አሪዝ የሚያምረው ሰውዬ፡፡ ደግሞ ሴት የሚባል አውጥቶ አያውቅም፡፡ ቢራ እራሱ የተማከራችሁ ይመስል እንደ አንችው ዛሬ ነው ፤ የጀመረው አለቻት፡፡

"አንች በምን አወቅሽ ዛሬ ቢራ መጀመሩን ?፡፡

አብሮት ያለው ጓደኛው ነው የነገረኝ፡፡

"እኔ እንደዚህ አይነት ስራ እንደማልሰራ እያወቅሽ ፤ ለምን ትጠይቂኛለሽ"? አለች፡፡ ውስጧ ፍራት ፍራት እየተሰማት፡፡

እሱንማ አውቃለሁ፡፡ ግን አንች እስከመቼ ድረስ ነው? ወንድ የማትፈልጊው ፤ የጠየቀሽን ሁሉ አልፈልግም እያልሽ፡፡ ላይፍሽን በአሁን ሰዓት ካልተጠቀምሽበት መቼ ልትጠቀሚበት ነው?፡፡ ደግሞ ጊዜሽ ካለፈ ወዲያ ማንም ሊጠይቅሽ አይደለም ዞር ብሎ የሚያይሽ አታገኝም፡፡ ይልቁንም ዛሬ እትዬም ስለሌለች አብረሽው እደሪ አለቻት፡፡

እሳትን በእሳት እንደ ሚባለው ሴትን በሴት አሳምኖ በቁጥጥር ስር ማድረግ በሴቶች የተለመደ መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡

ጊዜሽ ካለፈ ዞር ብሎ የሚያይሽ አታገኝም፡፡ ያለቻት ህሊናዋን በመርፌ የተወጋች ያህል ተሰማት፡፡ በትካዜ ተዋጠች፡፡ መጀመሪያም ልቧን በአይን አፋርነቱና በጉንጩ ላይ መስመር ሰርቶ በወረደው አሪዛም ፂሙ አሸፍቶ የወሰደባት ተመስገን እንኳን ለሴት ልጅ ለወንድ ልጅ ያማልል ነበር፡፡

"እትየ ስትመጣ ካልነገርሽብኝ እኔም ወድጀዋለሁ"፡፡ አለቻት የልብ ትርታዋ ከመጠን አልፎ ቁና ቁና እያስተነፈሳት፡፡

አልነግርብሽም፡፡ ደግሞ እኔ የምናግረው ጣቱን የሚጠባ ህፃን አደረግሽኝ እንዴ ብላት "በይ አሁን
ሰውም ስለሌለ እንዘጋጋና እኔም ሰው እየጠበቀኝ ነው እንተኛ አለቻት፡፡

"እምቢ ሳትል አትቀርም አለ ፤ ያሬድ፡፡

የከተማ ሴት ገንዘብ ነው የሚፈልጉት አላልከኝም" እንዴ አለ ፤ ተመስገን፡፡

የዚች የተለየ ነው እባክህ ብሎ ሌላም ደግሞ ሳይናገር መቅደስ ጠጡና ተነሱ ልንዘጋ ነው አለች፡፡

ተመስገን መሸ እንዴ? አለ፡፡

አልታወቀህም እንዴ? ከመምሸቱም ሊነጋ ተቃርቧል፡፡ እንዴውም የእኛ ብቻ ነው፡፡

ያልተዘጋው እንጅ የሁሉም ሆቴሎች ተዘግተዋል አለች ፤ መቅደስ፡፡

"እሽ ፤ እንነሳለን ግን የሽሃረግ ምን አለችሽ"? አለ

መቅደስ በስንት ልመና እሽ አስብያታለሁ፡፡ አሁንም እየፈራች ስለሆነ እናንተ ተነሱና አልጋ ቤት ጠብቁኝ፡፡ እኔ ይዣት እመጣለሁ አለች፡፡

ተንገዳገደ፡፡ ደግፎት ወደ መኝታ ቤት ገቡ፡፡

መቅደስ ሆቴሉን ዘጋግታ ከጨረሰች በኋላ፤ የሽሃረግን የሆቴሉ ዘበኛ እንዳያያት ወደ ሽንት ቤት የሚሄዱ አስመስላ ወደ እነ ያሬድ አልጋ ቤት አስገባቻት፡፡ ያሬድ ለሚተኛበት ሌላ አልጋ ከፍታለት አብሯት ወደ ሚያድረው ሰው ጋር ተመለሰች ፡፡

ለተመስገን ችግር የሚያጋጥምህ ከሆነ እዚህኛው አልጋ ቤት ነው የምተኛው፡፡ ነገ በጥዋት ወደ አቶ ላንቻ ቤት እንሄዳለን ብሎት ሁለተኛ ወደ ያዘው አልጋ ሄዶ ተኛ፡፡

የመኝታው በር ተዘጋ፡፡ ልብሳቸውን አወላለቁ፡፡ ከአሁን በፊት እንደሚተዋወቁ ፍቅረኛ ተቃቀፉ፡፡ ታምሪያለሽ ፤ አንተም ታምራለህ፡፡ ብቻ የሚል ቃል ተነጋግረው በለበሱት ብርድልብስ ውስጥ ከንፈር ለከንፈር ተፈላልገው ተገናኙ፡፡

የሁለቱም የሰውነት ሙቀት ጨመረ፡፡ ሳይታወቃቸው የተመስገን እግሮች በየሻረግ እግሮች ውስጥ ተጠላለፉ፡፡ በስካር መንፈስ ጉዳያቸውን ከፈፀሙ በኋላ ሁለቱም እራሳቸውን ሳቱ፡፡ መተቃቀፉና መሳሳሙ ቀረ፡፡ ድጋሜም አልተገናኙም፡፡ የለሊቱ ጨለማ ለቆ የቀኑ ብርሃን ተተካ፡፡

ያሬድ እሱም በስካር መንፈስ የመኝታ በሩን ከፍቶ እንደ ገባ ጫማውን እንኳን አላወለቀም፡፡ የወደቀበትን አያውቀም፡፡ ስካርና እንቅልፉን አሳልፎ ከተኛበት መኝታ ላይ ባነነ፡፡ ጫማውን ሳያወልቅ በመተኛቱ ተገረመ፡፡እንደዚህ እራሴን እስከምስት ድረስ ሰክሬ ኖሯል፡፡ ወይ ነዶ የሰውዬው ልጅ እያለ ተነሳ፡፡ በሩን ከፈተ፡፡ ሌሊቱ ነግቶ ቀን ቀን እየሸተተ ነው፡፡

የስካር ፊቱን ታጠበ፡፡ ልቡ አቶ ላንቻ ጋር ለመሄድ ተቻኩሏል፡፡ የአልጋው በር አልተዘጋም፡፡ ገርበብ ብሏል፡፡ ሳይዘጉት ይሆን እንዴ? የተኙት እያለ ገርበብ ያለውን በር ከፈት አድርጎ ገባ፡፡

የሽሃረግ ከተኛችበት ስትነሳ ከማታውቀው ሰው ጋር ተኝታ የንፅህና ክብሯን በመስጠቷ የሞት ያህል ተሰምቷታል፡፡ በሁለት እጆቿ እራሷን ደግፋ ከአንገቷ ወደ መሬት አቀርቅራ ከመኝታው ላይ ተቀምጣለች፡፡ የተፈጠረውንና ያደረገችውን ሁሉ ለማስታወስ እየሞከረች ከህሊናዋ ጋር እየተሟገተች ሳለ ያሬድ በር ከፍቶ ገባ፡፡ ካቀረቀረችበት ቀና አለች፡፡ ከያሬድ ጋር አይን ለአይን ተጋጩ፡፡ ያሬድ ሰውነቱ ተንቀጠቀጠ፡፡ ድንጋጤ ተሰማው፡፡

የሽሃረግን ደጋግሞ አትኩሮ ተመለከታት፡፡ ማታ በዲም ላይትና በፌር ቅባት ህንዳዊ መስላ የታየችው የፊት ላይ ቅባት ተወግዶ የኢትዮጵያዊነት ደም ግባቷ ተመልሷል፡፡ የጠይም ለግላጋ ቆንጆ መሆኗን በደንብ ይታያል፡፡ የሚያውቃት የሚያውቃት መሰለው፡፡

ተመስገን የት እንደ ሄደ እንኳን አልጠየቃትም፡፡ ወደ ተቀመጠችበት መኝታ ተጠጋ፡፡

ምነው? የማውቅሽ መሰለኝ፡፡ ግን ስምሽ ትክክለኛ የሽሃረግ ነው? አላት፡፡

የሽሃረግ ጭንቅላቷን በመጥረቢያ እንደተመታች ያህል ባለችበት ክው ብላ ቀረች፡፡ ያሬድን አፍጣ ፣ ደግማ ፣ ደጋግማ አየችው፡፡

"የየየየየየየየየየየየየ..ታ...ውቀኛለህ"?  አለች፡፡ አፏ እየተንተባተበ፡፡

Читать полностью…

አትሮኖስ

ሴት ልጅ አንተን እንዳፈቀረችክ የምታቅበት 10 ምልክቶች ከታች #JOIN ብለክ ተተቀምበት እና ህዝቤ ሆይ ምን ትተብቂያለሽ ገብተህ አንበዋ😋😋😋😋
👇👇👇👇👇👇👇

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አላዛር አባቱን በጣም ይጠላል፡፡ለአባቱ ያለው ጥላቻ ለሰሎሜ ካለው ፍቅር ጋር በግራና  እና ቀኝ ጫፍ ላይ ካለው የሚዛኑ ዘንግ ላይ ቢንጠለጠሉ በእኩል ሌቭል ላይ ተንሳፈው ነው የሚታዩት፡፡ሰሎሜን መቼ ማፍቀር እንደጀመረ እንደማያውቀው ሁሉ አባቱንም መቼ መጥላት እንደጀመረ አያውቅም፡፡ብቻ ለአባቱ ያለው ጥላቻም ሆነ ለሰሎሜ ያለው ፍቅር በእድሜ ዘመኑ ሁሉ የነበረና ከእሱ የአካልና የአእምሮ እድገት ጋር ተያይዞ እያደገና እየጠነከረ የመጣ  ባለሁለት መልክ ስሜት  ነው፡፡

ሁል ጊዜ ስለአባቱ ሲያስብ አንድ የሚያስጨንቀው ነገር‹‹አሁን አባቴ ቢሞት አለቅሳለሁ?…››የሚለው ጥያቄ ነበር፡፡ ምክንያቱም በአባቱ መሞት ውስጡ እንደማያዝን ያውቃል…፡፡ካላዘነ ደግሞ እንዴት ብሎ እንባው  ሊመነጭለት ይችላል….?ለገዛ አባቱ ደግሞ ማልቀስ ካልቻለው  ቀሪው  ማህበረሰቡ ምን ይለዋል…?ይሄ ጉዳይ ሁል ጊዜ እንዳሳሰበው ነው፡፡ግን ደግሞ የሚፅናናው‹‹አረ እሱ አይሞትም….እንደእሱ አይነት ክፉና ፀያፍ ሰው እንኳን ሰው ሞት እራሱ ይሸሸዋል ››በሚለው እምነቱ ነው፡
አላዛር አባቱን ለመጥላት የቻለበት ዋናው ምክንያት ከህፃንነቱ ጀምሮ በሚወዳት እናቱ ላይ ያደርሰው የነበረውን ድብደባና በደል ጥርቅም ትውስታ በአእምሮው ስለታጨቀ  ነው፡፡አባትዬው በሳምንቱ ውስጥ ካሉ ሳባት ቀኖች ቢያንስ ስድስቱን እኩለ ለሊት ካለፈ በኃላ ሰክሮና ጥንብዝ ብሎ ነው ወደቤት የሚመጣው፡፡መስከሩና ውድቅት ለሊት በራፍን እያንኳንኳ የተኛውን የሰፈሩን  ሰው ሁሉ መቀስቀሱንና መረበሹ ብቻ አይደለም የሚያበሳጨው፡፡ተከፍቶለት ወደቤት ከገባ በኋላ ለአንድና ሁለት ሰዓት የሚያደርጋቸው ድርጊቶች ናቸው ይበልጥ አስፀያፈዎች፡፡ልክ እንደጀማሪ ሰባኪ ድምጽን ከጣሪያ በላይ ከፍ በማድረግ  በቀኝ ያለው ጎረቤቱን ወይም በግራ ያለውን ስም እየጠራ ጥንብርኩስን አውጥቶ ይሳደባል፡፡ስድቡን ከአባወራው ከጀመረ ወደሚስትዬው ይሸጋገርና ልጆቹ ላይ ያበቃል.፡፡በዚህ ጊዜ ታዲያ የአላዛር እናት ዙሪያውን እየተከተለች በመሳቀቅ ልታስቆመውና ዝም ልታስብለው ትጥራለች፡፡በዚህን ጊዜ በቡጢ ሲላት ከግድግዳ ጋር ትላተማለች፡፡.ትንሽ ትረጋጋና አሁንም ልታስተኛው ትጥራለች..በጠራባ ሊያነሳት ይልና እራሱ ተንሸራቶ ወለሉ ላይ ይዘረጋፋል…እንዳይጎዳባት ሮጣ ሄዳ ከወደቀበት ልታነሳው ስትሞክር በጥፊ አይነ-ስቧዋን ያቃጥልላታል … ያዞራትና ስሩ ሄዳ ዝርግት ትላለች፡፡

ይሄንን በየቀኑ መኝታው ላይ ሆኖ..ድብን ያለ እንቅልፍ ውስጥ ያለ ይመስል ዝርግትግት ብሎ..ትንፋሹን ለራሱ እንኳን እንዳይሰማ ወደውስጥ ውጦ.. በለበሰውን ብርድልብስ ቀዳዳ አይኖቹን አጨንቁሮ ይመለከታል…ተነስቶ እራስጌው ባለው የብረት ዘነዘና ሰካራም አባቱን  አናቱን መፈርከስና አናትዬውን ነፃ ማውጣት ይፈልጋል…ግን ምኞት ብቻ ነበር፡፡ያንን ለማድረግ ወኔ አልነበረውም፡፡አይደለም እንደዛ ለማድረግ ሞክሮ ይቅርና ድንገት እንቅስቃሴ ቢያሳይ እንኳን አባትዬው ትኩረቱን ከጎረቤት ወደእሱ ይመልስና ጎትቶ ከአልጋው ያስነሳዋል…በዛ ውድቅት ለሊት የሆነ ሰበብ ፈጥሮ ተንበርከክ ይለዋል…ሲንበረካክ በኩርኩም አናቱን ያነደዋል..እናትዬው እንዳይጎዳባት በመሀከላቸው ስትገባ ቡጢውናና ጥፊውን ያለስስት ይሸልማታል… መጮጮኸና ትርምሱ በእጥፍ ይበዛል፡፡
ያንን ስለሚያውቅ ገና የአባቱን ድምፅ ከውጭ ሲሰማ በድን ሆኖ እራሱን ይቀብራል…በምንም ነገር ጣልቃ ላለመግባት እስከመጨረሻ ከስሜቱ ጋር ይታገላል.. እናቱም እንደዛ እንዲያደርግ ነው የምትመክረው..ዘወትርም የምትለምነው፡፡
አላዛር….አባቱ በእውነታው አለም ተጫባጭ ሰው አይመስሉትም፡፡.የሆነ ንክ ደራሲ ለገፀ ባህሪነት ፈልጎ አጣሞና አወላጋግዶ  የሳላቸው ንክ ሰው ነው የሚመስሉት፡፡ ምክንያቱም ሲጠጡ ሰይጣን …መጠጥ ባልቀመሱበት ሰዓት  ደግሞ ፍጽም መልአክ መሰል ሰው ናቸው፡፡
ሲሰክሩ ለሊቱን ሙሉ ሲሰድብት ያደሩትን ጎረቤት ጥዋት ተነስተው ወደስራ ሲሄዱ በራፍ ላይ ካገኙት መሬት እስኪደርሱ ለጥ ብለው ሰላም ብለውት ፤አቅፈው ተከሻውን ወዝውዘውት …ቸገረኝ ካለ ኪሳቸው ገብተው ሸጎጥ አድርገውለት …የሚስቱን ደህንነት የልጆቹን ሰላም መሆን ጠይቀውት መንገዳቸውን ይቀጥላሉ፡፡
‹‹ማታ ምነው እንዳዛ የሰደብከኝ?››ብሎ ሚጠይቃቸው ካለ…‹‹አረ በፈጣሪ..ምን ይሁነኝ ብዬ አንተን የመሰለን ወዳጄን ሰድባለው…?.እማይሆነውን››ከማለት ውጭ አንድም ነገር አያስታውሱም፡፡ብዙውን ጊዜ እንደውም ጥዋት ሲነሱ የሚስታቸው ጉንጭ አብጦ ..ወይም አይኖቻቸው ቀልቶ….ወይንም ደግሞ እጆቾ ተስብረው…ሲያዩ ኡኡ አገር ይያዝልኝ..ሚስቴን ማነው እንዲህ ያደረጋት? ብለው እስከማልቀስ ይደርሳሉ፡፡ሁለተኛ መጠጥ ላለመቅመስ ምለው ይገዘታሉ፡፡ በከንፈራቸው መሬት ስመው የሚስታቸውን ይቅርታ ጠይቀው በፀፀት እያጉረመረሙ ወደስራ ይሄዳሉ…ማታ ሲመጡ ግን እንደተለመደው ጥንብዝ ብለው  ነበር ወደቤታቸው የሚመለሱት፡፡››
በዚህም የተነሳ የሰፈር ሰው ሆነ ወዳጅ ዘመድ ሁሉ‹‹ እሱ እኮ መጠጥ ሲጠጣ አብሾ ስላለበት ነው…››በሚል  የሽፋን ምክንያት ጥፋቱን ሁሉ ይቅር ይሉታል፡፡አላዛር ግን ይሄ የአባቱ የማጭበርበሪያ ዘዴ  እንደሆነ አድርጎ ነው የሚቆጥረው… ከለሊቱ ድርጊታቸው በላይ የጥዋት ማስመሰላቸውና እንደተፀፀቱ ጠብ እርግፍ የሚሉት የማስመሰያ ድራማ እና የማደናገሪያ ዘዴያቸው እንደሆነ ስለሚያምን  ይበልጥ ይበሽቅባቸዋል፡፡የት እንዳነበበው ባያውቅም ‹‹እንደምትቀየር እርግጠኛ ካልሆንክ ይቅርታ አትጠይቅ››የሚል አባባል እንዳለ  ያስታውሰዋል፡፡አባቱ ሁል ጊዜ ጥፋት እንደሰሩ… ቀጥሎ ይቅርታ እንደጠየቁ ነው፡፡.ግን አንድም ቀን ቅንጣት ያህል እንኳን የመለወጥ ተነሳሽነት አግኝቶባቸው አያውቅም፡፡

አላዛርና እህቶቹ እያደጉ ሲመጣ ግን አባትዬውን ለመታገስ ያላቸው ትዕግስት እየተመናመነ ሄደ…አባትዬውን መክሰስ እና  ማሳሰር ….እናትዬውን ሊያጠቃ ሲል መሀከል መግባት ሲጀምሩ የአባትዬውም ተስፋ እየተሞጠጠና ብስጭታቸውም ከእለት ወደእለት እየጨመረ ሄደ፡፡በስተመጨረሻ እቤቱን ለቆላቸው ወጣና  ሌላ ሰፈር ሌላ ቤት ተከራይቶ ገባ፡፡

በዛን ጊዜ የአላዛር እድሜ 14 ዓመት አካባቢ ነበር እህቶቹ ደግሞ 19 እና 24 ዓመታቸው ፡፡በቤቱ በዘመናቸው አይተው የማያውቁት ነፃነትና ሰላም ሰፈነ…ግን ደግሞ ሌላ ሁለት ችግር ተከሰተ ፡፡አንደኛ በአባትዬው እቤቱን ለቆ መውጣትና ትዳሩን ማፍረስ እናትዬው በጣም ሀዘንተኛ ሆነች፡፡ከአሁን አሁን ተመልሶ ይመጣል ብላ በተስፋና በናፍቆት መጠበቅ..ተስፋዋ አልሰምር ሲል አይኗ እስኪደክም ማልቀስ…የነፍስ አባታቸውንና ሌሎች ሽማግሌሎችና የአባቱን ጎደኞች በየተራ  እየለመነችና እየተማፀነች ባለቤተዋ ጋር ሽምግልና መላክ…ቆሚ ስራዋ ሆነ፡፡

ይሄ የእናትዬው ድርጊት ከአላዛር የማሳብ አቅም በላይ ነበር የሆነበት፡፡አባትዬው እቤቱን ለቆ መውጣቱን ሲያውቅ መጀመሪያ በአእምሮ የመጣለት እናቱ እንዴት ከመጠን በላይ  ደስታኛ ሴት እንደምትሆን ነበር፡፡ምክንያቱም ይሄ ሰው እናቱን ቢያንስ ከሀያ አመት በላይ አሰቃይቷታል..ከሚወዷትና በድሎት ሊያኖሯት ከሚችሉ ሀብታም ቤተሰቦቾ አቋራርጧታል… ደብድቧታል….. አቁስሏታል.. አስርቧታል… ልጆቾን በመደብደብ አሳቆታል..

Читать полностью…

አትሮኖስ

#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አስር


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

አንድ አይጠጣም

የወጣት ሰውነቱ ፣ ለግላጋ ቁመናው ፣ ተቀያይሯል፡፡ ከአሁን በፊት ያልነበረውን ፂም አውጥቷል፡፡ ታዲያ በጉንጮቹ ላይ ግራና ቀኝ የወረደው አሪዝ መሳይ ፂሙ ጳጳስ አስመስሎታል፡፡ እንኳን ለማያቀው ለሚያውቀውም ሰው ተመስገንን መለየት ያስቸግር ነበር፡፡

ምግብ አዝዘው እየበሉ ነው፡፡ መብላቱን ተወት አድርጎ በሆቴሉ ዲም ላይት ይገረማል፡፡

"ከተሜ ማለት እንደ ዚህ ነው እንዴ"? አለ ተመስን፡፡

የተለየ ነገር አየህ"? አለው ያሬድ፡፡

"እኛም አገር ነጫጭ ሰው አስተናጋጅ ሆኖ ሳይ ነው"፡፡

"ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ………...ትገርማለህ የአገርህን ሰው እንኳን መለየት አቃተህ፡፡ እነዚህ እኮ የእኛ አገር ሰዎች ናቸው፡፡ ቅባት ስለተቀባቡ ነው፡፡ ነጭ የመሰሉህ ብሎት ለምግብ ማወራረጃ ቢራ ለማዘዝ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ዞር አደረገ፡፡ ከአንድ መልከ መልካም ህንዳዊ ከምትመስል ቆንጆ ሴት ልጅ ጋር አይኖቹ ተጋጨ፡፡

"ማነሽ እህት ቢራ ታዘዥን" አላት፡፡

"እኔ እኮ ቢራ ጠጥቼ አላውቅም፡፡ ያሰክረኛል ፣ አልጠጣም፡፡ ለራስህ እዘዝ ፤ ለእኔ ጠጅ የለመድሁት ይሻለኛል፡፡ አለ ፤ ተመስገን፡፡

"አይ! ተመስገን ትገርማለህ ፤ እኔ እኮ ብዙ የምታቅ ትመስለኝ ነበር፡፡ ለካስ ምንም አታውቅም፡፡ ጠጅ እኮ እንደዚህ ያለ ሆቴል ውስጥ አይሸጥም፡፡ አለማወቅህ ነው እንጅ ከጠጁ ቢራው ነው የሚሻለው፡፡ ባይሆን አንድ ጠጥተህ ትተወዋለህ፡፡ ብሎት ቢራ እንዲጠጣ አሳመነው፡፡

"ምን አይነት ቢራ ልታዘዛችሁ አለች፡፡ የተጠራችው መልከ መልካም የህንድ ቆንጆ የምትመስል አስተናጋጅ፡፡

"በእናንተ አገር መጀመሪያ ሰላምታ አይፈቀድም እንዴ"? አላት ያሬድ፡፡

"ኧረ ! ይባላል፡፡ እሽ ይቅርታ ብላ የእጅ ሰላምታ ሰጠቻቸው፡፡ ለዛ ያለው ፈገግታዋ በታከለበት፡፡

"ስምሽ ማን ይባላል"? አላት ያሬድ፡፡ እጁን ከእጇ ሳያላቅቅ፡፡

"የሽሃረግ እባላለሁ" ፡፡

"እሽ አመሰግናለሁ ብሏት የራሱን ስም ሳይነግራት ሁለት ሐረር ቢራ አምጭልን አላት፡፡

የሽሃረግ አስተናጋጅ አይደለችም፡፡ አስተናጋጅዋ ወደ ሱቅ ወታለች፡፡ እስከ ምትመለስ ግን ወደ ሆቴሉ የሚገቡትን ተስተናጋጆች ታስተናግዳለች፡፡

ታዲያ የሆቴሉ አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይና ሐምራዊ የተቀላቀለ በሚመስለው ዲም ላይት ውስጥ ሽር ሽር እያለች ስታስተናግድ አትኩሮ ለተመለከታት ፤ የቀሚስ አለባበሷ ፤ ኢትዮጵያዊነቷን ያለቀቀ ሆኖ በሰው እጅ የተሰራ ሳይሆን ከለግላጋ ሰውነቷ ጋር አምላክ አብሮ የፈጠረው ይመስል ነበር፡፡

ተመስገን የሽሃረግ እጁን ከጨበጠችው በኋላ፤ ከባንኮኒው ስትወጣና ስትገባ አብሯት በአይኖቹ ይመላለሳል፡፡

"ሊያመኝ ነው መሰለኝ"? ፡፡

"ጠጣበት ይለቅሃል፡፡ ዘና በል ደግሞ እንደ ልጅ አገረድ አትሽኮርመም"፡፡ "ምነው ደግሞ አይንህን በልጅቷ ላይ የምታንጃብበው"? አለው ያሬድ፡፡

"ኧረ ! አላንጃበብኩም፡፡ ግን ጓደኛዋ የወንድ ሱሪ ነው ያጠለቀችው፡፡ እሷ ደግሞ እንዴው ሳያት አለባበሷ አገረኛውን አለቀቀም፡፡ ታምራለች" ፡፡

"የቤት ልጅ ሆና ይሆናል፡፡ አለ ፤ ያሬድ፡፡

ያሬድ የአልባሳት ንግድ ከጀመረ ብቻ ሳይሆን በፊትም ከእናት አባቱ ቤት እያለ ስለከተማ ሴቶች አንዳንድ ነገሮችን ያውቃል፡፡ ለከተማ አዲስ አይደለም፡፡

ተመስገን አንድ ቢራ ያሰክረኛል ብሎ እየፈራ ቢጠጣውም አንድ ቢራ ግን አላሰከረውም፡፡ ለመድገም ፈልጓል፡፡

"ለካ ቢራ እንደዚህ ይጣፍጣል እንዴ"? አለ፡፡ ከጠርሙሱ ውስጥ የቀረውን እየጨለጠ፡፡

ቢራ እንግዴህ አንድ አይጠጣም፡፡ ከሰከርክም ከአሁን በኋላ ፤ ስለማንቀሳቀስ መቼም መኝታችን ድረስ ገብተን መተኛት አያቅተንም፡፡ ብሎት ቢራ ሊደግሙ የሽሃረግን ጠራት፡፡

የሽሃረግ ደግሞ አስተናጋጇን መቅደስን ጠርታ እዛጋ እየጠሩሽ ነው፡፡ ታዘዣቸው አለች፡፡

መቅደስ "ቢራ ይደገም"? አለች፡፡

ድገሚን ሳይላት "የሽሃረግ አታስተናግድም እንዴ"? አላት ያሬድ፡፡

"እሷ ብዙም አታስተናግድም፡፡ ሂሳብ ነው የምትቀበለው፡፡ የማስተናግደው እኔ ነኝ ፡፡

"እሽ ሁለት ሐረር ድገሚን" ፡፡

ተመስገን የጥላሁን ገሰሰ "ያቺ ቆንጆ ጥርሰ በረዶናት ፤ ውብ አይናማ ናት፡፡ የሚለውን ቀዝቀዝ ያለ ዜማ ልቡን ወሰድ አድርጎታል፡፡ አይኖቹን በየሽሃረግ ላይ ማንከራተቱን አላቋረጠም፡፡








ድገሚን ሳይላት "የሽሃረግ አታስተናግድም እንዴ"? አላት ያሬድ፡፡

"አሁን ከቅድሙ ድብርቱ ለቀቅ አላደረገህም ?

ካለቀቀህ ቢራውን ደጋግምበት፡፡ አልያም ሐገረኛ ሙዚቃ አስከፍተን እንጨፍራለን" አለ ፤ ያሬድ፡፡ የያዘውን ቢራ ጎንጨት እያደረገ፡፡ አንዳንድ ቢራ አልበቃቸውም፡፡ አራት አራቱን ቆነደዱት፡፡ ተመስገን ሞቅ እያለው መጣ፡፡

ያሬድ አገረኛ ሙዚቃ የለም እንዴ? አለ ፤ ለመቅደስ፡፡

"ልቀይርላችሁ"? ፡፡

"አዎ፤ በዚያውም ቢራ ይዘሽልን ነይ" ፡፡

አገረኛው ሙዚቃ ተከፈተ፡፡ ተነስተው ግን አልጨፈሩም፡፡ በተቀመጡበት አንገታቸውን ያወዛውዛሉ፡፡ የጠጣው ሐረር ቢራ መንፈሱን ሰረቅ አድርጎታል፡፡"ያች ኮረዳ ዝምብላ ታየኛለች" አለ ተመስገን፡፡ የራሱ አትኩሮ ማየት ሳይታወቀው፡፡

"የቷ ኮረዳ"? ፡፡

"ያቺ እዛ ውስጥ ተቀምጣ አንገቷን ብቻ የምትታየው፡፡ ስሟ ማን ነበር ያለችው"?

"የሽሃረግን ነው የምትለው"?፡፡

"አዎ፤ ትክክል ነህ፡፡ ቅድም እኮ ስትጠራት ሰምቼ አሁን አፌ ላይ ጠፍቶብኝ ነው፡፡

"የፈለግሃት ትመስላለህ፡፡ ለማንኛውም የሽሃረግን ለማግኘት መቅደስን መጥራት አለብን፡፡ በእጁ አጨብጭቦ መቅደስን ጠራት፡፡

"ልድገማችሁ" ብላ ጠየቀች መቅደስ፡፡ ቢራ ፈልገው መስሏት፡፡

"ቢራ እንኳን አልጨረስንም፡፡ ለየሽሃረግ አንድ ቢራ

ስጫት" አለ ፤ ያሬድ፡፡

ቢራ ጠጥታ አታውቅም፡፡ ለስላሳ ከሆነ ነው እንጅ ፡፡

"እሽ ፤ ስጫት" ፡:

መቅደስ የታዘዘችውን ለስላሳ ከፊሪጅ አውጥታ ሰጠቻት፡፡

ማነው ያዘዘሽ ; አለቻት የሽሃረግ?፡፡

"እዛጋ የተቀመጡት ሁለት ሰዎች ናቸው የጋበዙሽ፡፡ ብላ እነ ያሬድን በእጇ አመለከተቻት፡፡ ደግሞ ስምሽን ያውቁታል፡፡ ከአሁን በፊት ትተዋወቃላችሁ እንዴ?

"ኧረ ! ካለ ዛሬ አላየኋቸውም፡፡ ቅድም ነው ሱቅ ሄደሽ ሳስተናግዳቸው ስምሽ ማነው ሲሉኝ የነገርኳቸው" አለች፡፡ በዲም ላይቱ ፈገግታ ተመስገንን በስርቆት እየተመለከተች፡፡

Читать полностью…

አትሮኖስ

🥰ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️ላ🀄️ሉን!👇

/channel/+UqU8zCoHqyw2NzQ0

Читать полностью…

አትሮኖስ

🔵 ቤቲንግ ለምትመድቡ ሁሉ ይህን ምርጥ ቻናል እናስተዋውቃቹ  🤑

🔥 ብዙ ዓመት ልምድ ባላቸው ቀማሪዎች የተከፈተ ብችኛ ታማኝ ቻናል ነው ከኛጋ በመሆን ከሳምንት እስከ ሳምንት አሸናፊ ለመሆን ቻናሉን JOIN ያድርጉ 👇

Читать полностью…
Subscribe to a channel