yimulu | Unsorted

Telegram-канал yimulu - TelePort (ቴሌፖርት)

5047

Subscribe to a channel

TelePort (ቴሌፖርት)

ውድ የቴሌብር ወኪሎቻችን፤

አሁናዊ (Real-time) የኮሚሽን አከፋፈል ስርዓት
=============================
ለወኪሎች የኮሚሽን ክፍያ ወዲያውኑ (Real-time) የሚያስገኙ የአገልግሎት አይነቶች የትኞቹ ናቸው?

• የአየር ሰዓት ሽያጭ - 12℅

• የጥቅል (Package) ሽያጭ - 5℅

• የቴሌብር የደንበኝነት ምዝገባ - 15 ብር

• የደንበኝነት ደረጃን ማሳደግ - 10 ብር

• የኢትዮ ቴሌኮም ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን መክፈል (ከ4 - 30 ብር እና ከ5ሺህ ብር በላይ ለሆኑ ክፍያዎች 1%) እና

• ሌሎች ወርሃዊ የአገልግሎት ክፍያዎችን መክፈል ናቸው።
የቴሌብር ኤጀንትና መርቻት አካውንት በመክፈት
ቢዝነሳችሁን ማቀላጠፍ እና ተጨማሪ ገቢ  ማግኝት የምትፈልጉ በሙሉ
በያላችሁበት እናስጀምራችኋለን!
አስፈላጊ መረጃወችን እንደ
-ንግድ ፍቃድ

- መታወቂያ

-ስልክ ቁጥር

-የባንክ አካውንት  በዚህ ቴሌግራም ይላኩልን
👉 @John_Mkt
ለበለጠ መረጃ:-0912972394 ይደውሎልን

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ
የቴሌብር ኤጀንትና መርቻት አካውንት በመክፈት
ቢዝነሳችሁን ማቀላጠፍ እና ተጨማሪ ገቢ  ማግኝት የምትፈልጉ በሙሉ
በያላችሁበት እናስጀምራችኋለን!
አስፈላጊ መረጃወችን እንደ
-ንግድ ፍቃድ

- መታወቂያ

-ስልክ ቁጥር

-የባንክ አካውንት  በዚህ ቴሌግራም ይላኩልን

👉 @John_Mkt

ለበለጠ መረጃ:-0988206077 ይደውሎልን

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

Telebirr ቴሌብር

ኢትዮቴሌኮም አዲስ በጀመረው የሞባይል መኒ አገልግሎት ከኛ ጋር ወኪል ሆነው በመስራት የኮሚሽን ተጠቃሚ ይሁኑ። ቀዳሚ መሆን የተለየ ጥቅም ያስገኝልዎታል።

የቴሌብር ወኪል ለመሆን
የንግድ ፍቃድ እና መታወቂያ ካልዎት ዛሬውኑ ይመዝገቡ

ለበለጠ መረጃ: 0988206077 ይደውሉ

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

አዲሱ ኢትዮ ቴሌኮም የጀመረው ፍሌክሲ ጥቅል ምንድን ነው?


በቅርብ በኢትዮ ቴሌኮም የተጀመረው ፍሌክሲ ጥቅል እንደ ነጥብ መቁጠር እንችላለን ማለትም ፍሌክሲ ጥቅል ስንግዛ ነጥቦችን እንደምንገዛ ይህም ማለት ለምሳሌ 100 ፍሌክሲ ቢኖረን ሲዘረዘር 6 ፍሌክሲ ተጠቅመን 1 ደቂቃ ስልክ ብናወራ ፣ በ 2 ፍሌክሲ 1 MB ኢንተርኔት ብንጠቀም ፣ በ 2 ፍሌክሲ 1 መልእክት ብንልክ ፣ 90 ፍሌክሲ ይቀረናል ማለት ነው::

Join @teleport_tech

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

✳️ የባትሪ እድሜ (Battery life)

◽️ በዚህ ዘመን በርካቶች የዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ይታመናል። ዘመናዊ ስልኮች ከስሪታቸው አንጻር ባትሪያቸው ቶሎ የሚያልቅና አጭር ጊዜን የሚያስጠቅሙ ናቸው። ከዚህ አንጻርም ተጠቃሚዎች ባትሪውን ቶሎ ቶሎ ሃይል ለመሙላት (ቻርጅ ለማድረግ) ሲሞክሩ ይስተዋላል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ምናልባትም የባትሪን እድሜ ሊያሳጥር እና ሙሉ በሙሉ ሊያበላሸውም ይችላል።

◽️ ስልክን ከመጠቀም ባለፈ ግን የባትሪ እድሜን ማራዘምና በአግባቡ ቻርጅ በማድረግ መጠቀም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው። እርስዎ ከእነዚህ ተጠቃሚዎች አንዱ ከሆኑ ስልክዎን ቻርጅ በሚያደርጉበት ጊዜ ምናልባት ያላስተዋሏቸው ነገሮች ይኖራሉና እነዚህን የባለሙያ ሃሳቦች እናካፍልዎ፡

🔺 ቻርጅ እያደረጉ ስልክን በጭራሽ አለመጠቀም፦

◽️ አንዳንድ ጊዜ አስቸኳይ ጉዳይ ቢያጋጥም እንኳን ስልክን ቻርጅ እያደረጉ ባይጠቀሙ ይመረጣል። ምናልባት የግድ ከሆነ ደግሞ ስልኩ ከተሰራበት ኩባንያ አብሮ የተዘጋጀን ቻርጀር እየተጠቀሙ ቢሆን ይመረጣል ይላሉ ባለሙያዎች።

🔺ጥራት ያላቸውን ባለማራዘሚያ ቻርጀሮች መጠቀም፦

◽️ ባለማራዘሚያና በአብዛኛው በነጭ መደብ የተሰሩ እውነተኛ ቻርጀሮችን መጠቀም የባትሪን እድሜ ለማራዘም ይረዳልና ይጠቀሙበት።

🔺ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ከማድረግ መቆጠብ፦

◽️ ወደ መኝታ ሲያመሩ ስልክዎን ቻርጀር ላይ ሰክቶ መተው አደጋ አለው። ይህም ባትሪው ከመጠን በላይ ቻርጅ በማድረግ ማዳከም ይጀምራል፥ በአብዛኛው ስልክን በ40 እና በ80 ፐርሰንት መካከል ቻርጅ ማድረግ መልካም መሆኑንም ይመክራሉ። ምክንያታቸው ደግሞ 40 ፐርሰንት ከደረሰ ቻርጅ ማድረጉ ግዴታ ሲሆን 80 ከሆነ በኋላ ነቅለው ቢገለገሉበት ችግር የለውም የሚል ነው።

🔺ስልክን ለተወሰነ ጊዜ ማጥፋት፦

◽️ ሰው ሰርቶ ማረፍ እንደሚፈልገው ሁሉ ስልክን ማጥፋትም ለባትሪው መልካም እንደሆነ ነው ባለሙያዎች የሚገልጹት። ለዚህ ደግሞ ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በተለይም ወደ መኝታ ሲያመሩ በማጥፋት እረፍት መስጠት። ይህ ሲሆን ደግሞ የስልኩ ባትሪ እድሜ እንዳያጥርና ረዘም ላለ ጊዜ እንዲያገለግልዎ ይረዳል።

🔺ባትሪው እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ አለማድረግ፦

◽️ ሌላውና በብዙ ሰዎች የተለመደው ጉዳይ ደግሞ የስልክ ባትሪ እስከሚያልቅ ጠብቆ ቻርጅ ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ ለባትሪ እድሜ የመጀመሪያውና ዋናው ጠር ነውና ባትሪው 40 ፐርሰንት ላይ ሲደርስ ቻርጅ ማድረጉን ይመክራሉ። ይህ ባይሆን እና በጣም ከወረደ በኋላ ቻርጅ ለማድረግ መሞከሩ ግን ባትሪን በመግደል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላልና ይህን ልማድ ያስወግዱም ይላሉ።

◽️ ከዚህ ባለፈም ቻርጀሩን ከቀጥተኛው ሶኬት ላይ አለመሰካት እና ከፍተኛ ሙቀት ባላቸው ቻርጀሮች አለመጠቀም መልካም ነው። እርስዎም ከላይ የተጠቀሱትን የባለሙያ ምክረ ሃሳቦች በመተግበር የስልክዎን ባትሪ እድሜ ያራዝሙ።

ለሚወዱት ያጋሩ✅
@teleport_tech

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

✳️ ስቲቭ ጆብስ ፡ Steve Jobs

◽️ Steve Jobs በ1955 በአሜሪካዋ San Francisco ወደዚህች ምድር ተቀላቀለ። ከሶርያ ለትምህርት ብሎ ከመጣው ወላጅ አባቱ እና የካቶሊክ እምነት ተከታይ ከሆነች እናት የተገኘው Steve ገና በጨቅላነቱ ነበር ለማደጎ ልጅነት የተሰጠው። የዚህም ምክንያት ጥንዶቹ ገና የዩንቨርሲቲ ተማሪ ስለነበሩ እና በሁለቱ መካከል በነበረው የባህል እና የእምነት ልዩነት ቤተሰብ ደስተኛ ሊሆን ባለመቻሉ ነበር።

◽️ ነገር ግን ከብዙ የመከራ አመታት በሃላ ትዳር መስርተው Lisa የተባለች ሌላኛው እህቱን አፍርተዋል። Steve ለማደጎ ከተሰጠ በሃላ አሳዳጊ ከነበረው አባቱ ጋር በትርፍ ጊዜያቸው ኤሌክትሮኒክስ እየጎረጎረ ያሳልፉ ነበር።

◽️ ከአመታት በኻላ ወደ ዩኒቨርስቲ የመግባት ዕድል የነበረው Steve ለስድስት ወራት ብቻ ተምሮ ለማቃረጥ በቅታል ይሄም የሆነው በትምህርት ሰርአቱ ላይ ተቃውሞ ስለነበረው ነው።

◽️ በ1974 ወደ ህንድ አቅንቶም ስለ Enlightenment እና ስለ Zen Buddhism እውቀት ለመቃረም ሞክሮራል። እንግዲ ከዚህ በኻላ ነበር ኮሌጅ እያለ ከተዋወቀው ጋደኛው Steve Wozniak ጋር በመሆን በቤታቸው ጋራጅ ውስጥ ቀን ከሌት ኤሌክትሮኒክስ በመጎርጎር ማሳለፍ የጀመሩት።

◽️ ለመጀመሪያ ጊዜም ህልማቸው ፍሬ አፍርቶ በ1976 Apple 1 ኮምፒውተርን ለገበያ ለማብቃት ችለው ሰፊ ተቀባይነትን በማግኘት ወደ 80000 የአሜሪካ Dollar ሊያስግቡ ችለዋል።

◽️ በቀጣይ አመትም Apple 2 ለገበያ አቅርበው ስኬታማ ሆነዋል። ነግርግን በ1984 በብዙ ወጪ የተሰራውን Apple Lisa ገበያ ላይ ቢያቀርቡም ከዋጋው መወደድ የተነሳ ለኪሳራ ተዳርገዋል። በዚህም የተነሳ Steve የመባረር እጣ ገጥሞታል። ይሄን አስመልክቶ በ2005 የዩኒቨርሲቲ ምርቃት ላይ ተጋብዞ እንዲህ ብሎ ነበር።

"...እናም እኔ 30ኛ ዓመቴን እንደያዝኩ - ተባረርኩ!...እንዴት ነው ራሳችሁ ካቋቋማችሁት ኩባንያ የምትባረሩት? ነገሩ እንዲህ ነው። አፕል እያደገ ሲመጣ በጣም ክህሎት አለው ብዬ ያመንኩበት ሰው አብሮኝ ኩባንያውን እንዲመራ ቀጠርነው፡፡ በመጀመሪያ ዓመት አካባቢ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበሩ። ቀስ በቀስ ግን የድርጅቱን መፃኢ ዕድል በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ራዕያችን እየተራራቀ መጣና በስተመጨረሻ ጭርሱኑ ተለያየን፡፡ ስንለያይ ፣ የዳይሬክተሮቹ ቦርድም ለእሱ ወገኑና ፣ በ30 ዓመቴ ተባረርኩ። ሀገር ባወቀው አሳፋሪ ሽንፈት-ተባረርኩ! ህይወቴን የሰጠሁለት ነገር በአንዴ ከእጄ በንኖ ጠፋ፡፡ ይጎዳል - ተጎዳሁ..."

◽️ Appleን ከተሰናበተ በኻላም ተስፋ ያልቆረጠው ስትቭ Next የተሰኘ አዲስ ድርጅት በመክፈት እንዲሁም Pixarን በመግዛት በሌላ ስኬት ብቅ ሊል ችላል። ከስቲቭ መሰናበት በሃላ Apple የውድቀት መንገዱን ተያይዞት ነበር። ከ10 አመታት በሃላ Apple የስቲቭ የነበረውን Nextን ሲገዛው ስቲቭም ወደ ስራ በመመለስ CEO ለመሆን በቅተዋል። ስለዚህ ሁኔታም በዛው የምርቃት ፕሮግራም ላይ እንዲህ ብሎ ነበር።

"...ከአፕል ባልባረር ኖሮ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ላገኝ እንደማልችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ በዕርግጥ በጣም መራር መድኃኒት ነበር። ግን እንደምገምተው ለበሽተኛው የግድ አስፈላጊ ነበረ፡፡ አንዳንዴ ህይወት አናታችሁን ትቀውራችኋለች፡፡ እምነት ግን አትጡ፡፡ በሽንፈቴ ውስጥ ሁሉ እንዳላቆም ፣ እንድቀጥል የረዳኝ የምሰራውን መውደዴ ለመሆኑ ጨርሶ ጥርጥር የለኝም፡፡

◽️ የምታፈቅሩትን ልታገኙ ይገባል ይህ ደግሞ ለስራችሁም ሆነ ለፍቅራችሁ ወሳኝ ነው፡፡ ስራችሁ የህይወታችሁን ትልቁን ክፍል የሚይዝ ነው። እናም በስራችሁ ልትረኩ ዘንድ የምትሰሩት ነገር ታላቅ መሆኑን ልታምኑበት ይገባል፡፡

◽️ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ የምትወዱትን ስትሰሩ ነው! የምትወዱትን ሥራ እስካሁን ካላገኛችሁት ለመፈለግ አትቦዝኑ። ፈልጉ - አትርጉ፡፡ እናም ፣ እንደሁሉም ከልብ የሆነ ነገር ሁሉ ፣ ስታገኙት ታውቁታላችሁ። እንደሁሉም ታላላቅ ግንኙነቶች ሁሉ ፣ ዓመታት በነጎዱ ቁጥር፣ ይበልጡን እያማረና እየሰመረ ሂያጅ ነው፡፡ ስለዚህ ፈልጉ፤ አትርጉ!"

◽️ ከዛ በሃላ Apple አለማችን ላይ በጣም ዝነኛ ካምፓኒ ሊሆን በቅታል። ለመጀመሪያ ጊዜም Full Touch Screen ስልኮችን ለአለም አስተዋውቃል።

◽️ ስቲቭ በ1991 ትዳር የመሰረተ ሲሆን የ3 ልጆች አባት ነበር። በ2003 ጀምሮ በጣፊያ ካንሰር ሲሰቃይ የኖረው Steve ህመሙ ጸንቶበት በ2011 ለህልፈተ ህይወት ሊያበቃው ችላል። በአለም ላይ ሞቱ ብዙሀንን ያስደነገጠ ነበር።
ለሚወዱት ያጋሩ✅
@teleport_tech

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ብሉቱዝ በአጭር ርቀት ውስጥ ምንም አይነት ገመድ ሳይጠቀም ዝቅተኛ ፓወር ራዲዮ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ስልኮች፤ ኮምፒውተሮች እና የተለያዩ ኔትወርክ ዲቫይሶች እንዲገናኙ( ኮሚኒኬሽን እንዲያደርጉ) ያስችላል፡፡ ብሉቱዝ ስታንደርድ IEEE 802.15.1 ሲሆን ስሙን የወሰደው 1000 ዓመት በፊት ከነበረ Harald Bluetooth ከተባለ ዴንማርክ ንጉስ ነው፡፡

ብሉቱዝ ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ዲዛይን የተደረገው ቀላል ዋየርለስ ኔትወርክ ዲቫይሶችን፤ ስልኮችን እና ዋየርለስ ሄድሴት ሰፖርት ለማድረግ ሲሆን ዋየርለስ ሲግናል ትራንስሚትድ(የሚተላለፈው) በብሉቱዝ በአጭር ርቀት 10 ሜትር ውስጥ ነው እንዲሁም ብሉቱዝ ዲቫይሶች በአጠቃላይ ግንኙነት የሚያደርጉት 1 Mbps ያነሰ ነው፡፡

የብሉቱዝ ኔትወርክ ፒኮኔት(piconet) ወይም ፐርሰናል ኤርያ ኔትወርክ(PAN) ሲሆን ፒኮኔት ቢያንስ ቢያንስ 2 እና ከ8 ያልበለጡ ብሉቱዝ ዲቫይሶች የተገናኙበት የብሉቱዝ ኔትወርክ አይነት ነው፡፡ዲቫይሶች ግንኙነት ሲያደርጉ ፕሮቶኮል(ቐንቐ) ይጠቀማሉ ብሉቱዝ የተለያዩ ቨርዥን ሲኖሩት እነሱም 1.1, 1.2 and 2.0 ናቸው፡፡

ብሉቱዝ በተለያዩ ዲቫይሶች ላይ የምናገኘው ሲሆን ለምሳሌ፡- በኮምፒውተር፤ በስልክ፤ በጌም መጫወቻዎች፤ ሄድሴት፤ ወዘተ
ብሉቱዝ ዲቫይሶች ለማገናኘት ምንም አይነት ኢንስታሌሽን ወይም ኮንፊገሬሽን (ኔትወርክ ዝርጋታ) አያስፈልግም በቀላሉ ዲቫይሱን ብሉቱዝ ኢኔብል(መክፈት) ብቻ ነው የሚያስፈልገው፡፡
ለሚወዱት ያጋሩ✅
@teleport_tech

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

በኢፕይ አፕ የሞባይል ካርድ በችርቻሮ ለመሸጥ አፑን ለማውረድና ለመመዝገብ የሚከተሉትን ወኪሎቻችን በመደወል መስተናገድ ይችላሉ።

አዲስ አበባ እና አከባቢው

ዮሃንስ ጌቱ - 0988206077
ሙስጠፋ ተማም - 0921093031
ሙስጠፋ ሙደሲር - 0911265565
ቢኛም ይርዳው - 0936830998
ዮሐንስ ጌቱ - 0912972394



> አላሚን - 0923576554


ደሴ እና አከባቢው
አብዱልራሂም ያሲን - 0900236410

ጎንደር እና አከባቢው
ሶሎሞን አለሙ -0921576852

መቐለ እና አከባቢው
ያሬድ ካሳሁን - 0912736449
ሰናይ አለማየሁ - 0979402782

በቦረና እና አከባቢው
ሙሉቀን አሰፋ +251911880016

በሚቀጥለው ሌሎች ወኪሎቻችን እናስተዋውቃለን

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ሰላም የቴሌፖርት ቤተሰቦች!

ከነገ ጀምሮ ከ ኢትዮ ቴሌኮም በመጣ ትእዛዝ መሰረት የኢቪዲ(የወረቀት ካርዶች) 5% ማበረታቻ የነበረው በ 2.5% እንዲቀነስ ተደረጉአል:: ይህም ማለት ከ (ባለሱቆች) ላይ ከተፈቀደው 10% ወደ 7.5% ይቀንሳል ማለት ነው፥፥ ይህን ተገንዝባቹ ለ ደንበኞቻችሁ እንድታሳውቁ እንመክራለን!

ነገር ግን *922# ይሙሉ ቸርቻሪዎች 5% ማበረታቻው ይቀጥላል!

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ለኢቪዲ ሞባይል ካርድ አከፋፋዮች መልካም ዜና!

ከድርጅታችን ቴሌፖርት ጋር ሲሰሩ የስቶክ እጥረት እንደማያጋጥሞ ያውቃሉ?
በ 0923576554 እና 0943877302 አሁኑኑ ደውለው ይመዝገቡ!

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ሰላም ውድ የቴሌፖርት አባሎች፣

ከስር በሚገኘው አጭር ቪዲዮ የድርጅታችንን "ePay"መተግበሪያ ሙሉ አጠቃቀም ታገኛላችሁ!
ይመልከቱት

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

የሞባይል ካርድ በሚያቱምበት ግዜ አንድ አንድ ግዜ ጽሁፉ በጣም አንሶ ወይም ተልቆ ካስቸገራቹ
የብሉቱዝ ፕሪንተር ፎንት መጠን ለማስተካከል በሚቀጥለው የአንድ ደቂቃ ከሰላሳ ሰኮንድ ቱቶርያል እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል ይመልከቱ

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ
የቴሌብር ኤጀንትና መርቻት አካውንት በመክፈት
ቢዝነሳችሁን ማቀላጠፍ እና ተጨማሪ ገቢ  ማግኝት የምትፈልጉ በሙሉ
በያላችሁበት እናስጀምራችኋለን!
አስፈላጊ መረጃወችን እንደ
-ንግድ ፍቃድ

- መታወቂያ

-ስልክ ቁጥር

-የባንክ አካውንት  በዚህ ቴሌግራም ይላኩልን

👉 @John_Mkt

ለበለጠ መረጃ:-0988206077 ይደውሎልን

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

Telebirr ቴሌብር

ኢትዮቴሌኮም አዲስ በጀመረው የሞባይል መኒ አገልግሎት ከኛ ጋር ወኪል ሆነው በመስራት የኮሚሽን ተጠቃሚ ይሁኑ። ቀዳሚ መሆን የተለየ ጥቅም ያስገኝልዎታል።
የቴሌብር ወኪል ለመሆን
የንግድ ፍቃድ እና መታወቂያ ካልዎት ዛሬውኑ ይመዝገቡ

ለመመዝገብ: https://mobilemoney.et/

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

Daldaltonii Jimma Fi naanoo isheti kan argamtan. Oduu gamachisaa!

Telebirr inba tatannii jirtuu?
Bay'een isanii telebirr inba ta'uudhan fayyadama ta'aani jiru. Isinis Waraqaa eyyama kan daldalaa Fi tin numberii yoo Qabatan inba ta'uudhan guyyaa kana qabdanii hojii egaluu ni dandesu!
Online galma'uudhaaf sarara website kenyaa fayyadama
Https://mobilemoney.et/

Ayyana garii 🌻

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ሰላም የቴሌፖርት ኤጀንቶች!

ማንኛውም በ ኢፔይ አፕ ላይ ለሚገጥማችሁ ችግሮች በ 0923576554 በመደወል | @epayethio1 መልእክት በማስቀመጥ መፍትሄ ማግኘት ትችላላችሁ! በተረፈም በ ኢፔይ የተመዘገባችሁ ኤጀንቶች ብቻ ይሄን ቻናል ጆይን ያድርጉ https://t.me/joinchat/R3EBgHtQ8KJQIZA8

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

✳️ ውድ የቴሌፖርት ቤተሰቦቻችን ዛሬ የዘመናችን አስደናቂ ፈጠራዎች ከሆኑት መሀል ዛሬ ስለ ሜሞሪ ካርድ ወይም SD CARD በጥቂቱ መረጃ ልንሰጣችሁ አስበናል።

◽️ ይህች SD Card የምንላት መሳሪያ ኤሌክትሮኒክ የመረጃ ማከማቻ ስትሆን ዲጅታል ኢንፎርሜሽኖችን ለማስቀመጥ ወይም Store ለማድረግ ያገለግላል፡፡ ይቺ ዳታ ማከማቻ በዲጅታል ካሜራዎች፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ በላፕቶፖችና በኮንፒውተሮች፣ በታብሌቶች ፣በmp3 ማጫዋቻዎችና በቪድዮ ጌም ኮንስሎች ትገኛለች፡፡

◽️ የሚሞሪ ካርድ በመጀመሪያ ወደ አለም ብቅ ያለው በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995 ሲሆን ይሄውም PC Card (PCMAIA) የሚል ስያሜ ነበራቸው፡፡ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪዎች አሁን በስፋት ተሰራጭተው ከሚገኙ ሚሞሪዎች በመጠን ከፍ ያሉ ሲሆን መረጃ የመያዝ አቅማቸውም በጣም አነስተኛ ነበር፡፡

◽️ በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቀደምት ሚሞሪዎች በስፋት እያገለገሉ ያሉት በእንዱስትሪያል አፕልኬሽኖችና እንደ ሞደም ያሉ ኤሌክትሪካል ዲቫይሶችን ለማገናኘት ብቻ ነው፡፡ አብዛሃኞቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃዎችን እንደገና መላልሶ ማጥፋትና መጫን የሚያስችሉ ሲሆን መረጃዎችንም የሚይዙት ያለምንም ፓዎር ነው፡፡

◽️ ከአመታት በኋላ መሻሻሎችን በማሳየት የተላየዩ ሚሞሪዎች ገበያውን መቀላቀል ጀመሩ በተለይ ከመጀመሪያዎቹ PC Card በመጠን አነስ ያሉና መረጃ የመያዝ አቀማቸው ከፍ ያሉ በመሆናቸው ተቀባይነት ለማገኘት ብዙ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ከነዚህም ውስጥም Compact Flash, Smart Media, እና Miniature Card ይገኝበታል፡፡

◽️ በ2001 (እ.ኤ.አ) Smart Media ሚሞሪ ካርድ 50% የዲጅታል ካሜራ ገበያውን ተቆጣጥሮ ነበር፡፡ Compact Flash, የተባለው የሚሞሪ ካርድ አይነት ደግሞ በአብዛኛው የፕሮፌሽናል ዲጅታል ካሜራዎች ላይ ነግሶ ነበር፡፡ እነዚህ የሚሞሪ ካርድ አይነቶች ተፈላጊነታቸው ጥያቄ ውስጥ የገባው በ2010 (እ.ኤ.አ) Micro SD ሚሞሪ ካርዶች መምጣታቸውን ተከትሎ ሲሆን በብዙ የሞባይል ብራንዶች ላይ እና ታብሌቶች ላይ በመገጠም ተፈላጊነታቸው በጣም ሊንር ችሏል፡፡

◽️ እስከ 2010 (እ.ኤ.አ) የሶኒ ካምፓኒ ለምርቶቹ ሚሞሪ እስቲክን ብቻ ይጠቀም ነበር በተመሳሳይ ታዋቂው የዲጅታል ካሜራዎች አምራች Olympus ኩባንያ sd CARD ብቻ የሚጠቀሙ ካሜራዎችን ያመርት የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሶኒም ሆነ ኦሎምፐስ በምርቶቻቸው ላይ SD MEMORY CARD እንደተጨማሪ የሚያስገቡ ካሜራዎችን ማምረት ግድ ብሏቸዋል፡፡

◽️ አሁን ላይ በብዛት የምንጠቀምባቸው Micro SD ሚሞሪ ካርድ 1.4 mm ቲክነስ ያላቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት እስከ 1 TB ወይም 1000 GB መረጃን የመሸከም አቅም እንዲኖራቸው ተደርጎ ለመስራት ተችሏል፡፡ ልብ በሉ የመጀመሪያዎቹ ሚሞሪ ካርዶች መረጃ የመሸከም አቅም 32 MB ነበረ ይህ ማለት ከ30 ፎቶዎች በላይ የመያዝ አቅሙ ያልነበረው ነው፡፡ ለ25 አመታት የፍላሽ ስቶሬጅ (Flash Storage) ገበያውን እየመራ ያለው San የተባለው እውቅ ካንፓኒ አሁን ላይ ባለው ቴክኖሎጂ 128 GB SDXC Memory Card (1.4 mm) ማምረቱን ያስታወቀ ሲሆን መረጃን በስሌት ለማስርዳት ያህል አዲሱ ሜሞሪ፡-
🔺16 ሰዓት HD ቪድዮዎች
🔺7500 ሙዚቃዎችን
🔺3200 ፎቶዎችን
🔺ከ125 በላይ አፕልኬሽኖችንም በዛች ጉደኛ SDXC ሚሞሪ ካርድ (1.4mm) ከላይ የተጠቀሱትን ሚዲያ ፋይሎች በሙሉ በአንድ ላይ ማስቀመጥ ተችሏል ይለናል፡፡
ለሚወዱት ያጋሩ✅
@teleport_tech

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

🌟 Merry Christmas 🌟
🎄 መልካም የገና በዓል 🎄

Teleport™ @teleport_tech

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

👉"Wi-fi" የተፈጠረው በድንገት ነው ። የአውስታሊያ ሳይንቲስቶች ከ"Black Hole" ውስጥ የሚውጣውን Radiowave ለመሰብሰብ የሚያስችል እቃ በመስራት ላይ እያሉ ነው የተፈጠረው ።
@teleport_tech

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ሲም ካርድ ምንድን ነው?

🔷 ሲም ማለት ነው የተመዝጋቢ ማንነት ሞዱል. SIM stands for Subscriber Identity Module ከማንኛውም የሞባይል ስልክ በጣም አስፈላጊ አካል ነው ፡፡ በአንዳንድ አገሮች ICC (Integrated Circuit Card ) and UICC ( Universal Integrated Circuit Card ) በመባልም ይታወቃል ፡፡ በቀላል አነጋገር ሲም ካርድ በመሠረቱ SIM Card is a or ማይክሮ መቆጣጠሪያን መሠረት ያደረገ የመዳረሻ ሞዱል (microcontroller-based access module) ወይም የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚ መረጃን የሚያከማች (a small portable memory chip) ፣ የ 16 አኃዝ ወይም የ 17 አኃዝ ኮድ ያለው ሲሆን ግን እንደየሀገሩ ይለያያል የኔትወርክ አጓጓዥ መረጃን እና የሚያከማች አነስተኛ ተንቀሳቃሽ የማስታወሻ ቺፕ ነው ፡፡ ልዩ የተጠቃሚ መታወቂያ / የሞባይል ስልክ ቁጥር ነው።

✅ የሲም ካርድ ሲም ካርዶች በ 3 መሠረታዊ መጠኖች ይገኛሉ መደበኛ ፣ ማይክሮ እና ናኖ ፡፡ ከነዚህ ሶስት መጠኖች ውስጥ መደበኛ መጠኑ የመጀመሪያው ነው ፡፡ ማይክሮ እና ናኖ ሲም ካርዶች ከመደበኛው ሲም ካርድ ዙሪያ ያለውን ተጨማሪ ፕላስቲክን በመቁረጥ አነስተኛ እንዲሆኑ ተደርገዋል ፡፡ ለተሻለ ግንዛቤ የሚከተለውን ምስል ይመልከቱ ፡፡

✅ የሲም ካርድ ዓይነቶች ሲም ካርዶች በዋናነት 2 አይነቶች ናቸው - GSM (ጂ.ኤስ.ኤም) እና
CDMA (ሲዲኤምኤም) ናቸው።

✅ GSM ማለት (Global System for Mobiles) SIM ለሞባይል ዓለም አቀፍ ስርዓት ማለት ነው፡፡ በማንኛውም የሞባይል ስልክ ውስጥ ሊገባና ሊወጣ ይችላል፡፡
CDMA ማለት ሲተነተን Code Division Multiple Access ማለት ነው፡፡ አንዴ ከመጀመሪያው ስልክ ውስጥ ሊወገድ ወይም ሊወጣ አይችልም።

✅ eSIM ካርድ በአሁኑ ጊዜ eSIM Card ተብሎ የሚጠራ አዲስ የሞባይል ስልክ ግንኙነት ቴክኖሎጂ አለ ፡፡ eSIM ማለት Embedded ሲም ማለት ነው፡፡ እንደ GSMና CDMA SIM አይነት አይደለም ገና ስልኩ ሲሰራ አብሮ ከስልኩ ጋ ተጣብቆ የሚመረት ነው እንዲሁም በ eSIM ላይ ያለው መረጃ እንደገና ሊፃፍ ስለሚችል የኔትወርክ ኦፕሬተርዎን መለወጥ ይችላሉ ፡፡


✅ ሲም ካርድ ክፍሎች እና ተግባር በሲም ካርድ ላይ የተለያዩ የወረዳ ክፍሎች የተለያዩ ተግባራት አሏቸው ፡፡ የሚከተለው የአንድ ሲም ዋና ዋና ክፍሎች ናቸው ፡፡

🔷 1. VCC ( Power Supply )
የሲም የኃይል አቅርቦት ፒን ነው ፡፡ 5V DC ኃይልን ይደግፋል ፡፡ ሲም ካርዱ እንዲሰራ ይህ የቪ.ሲ ፒን ከ 5V DC ጋር መቅረብ አለበት ከዚያም በሲም ካርዱ ውስጥ የተካተተው IC(Integrated Circuit) ብቻ ነው የሚሰራው ፡፡

🔷 2. RST ( Reset )

የሲም ካርዱን Signal እና ግንኙነቶችን (Communication) እንደገና ለማስጀመር የሚያገለግል ፒን ነው ፡፡ ይህንን ፒን ሲጠቀሙ ሲም ሁሉንም የወቅቱን Signal ዳግም በሚያድስ ነባሪው ሞድ ያደርገዋል ፡፡ የ RESET ፒን በሞባይል መሳሪያዎች ወይም በሲም ካርዱ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይሠራል። በአጠቃላይ ሲም ተጠቃሚዎች ይህንን ተግባር እንዲጠቀሙ አነስተኛ ፈቃድ ይሰጣቸዋል፡፡

🔷 3. CLK ( Clock ) ሰዓት-ሲምውን ለprocessor የሰዓት Signal ይሰጣል፡፡

🔷 4. GND (Ground) ሲም የIntegrated Circuit ያለው አነስተኛ የኤሌክትሮኒክስ ሃርድዌር እንደመሆኑ Ground ተብሎ ተሰይሟል ፡፡ GND አሁን ለሲም ካርዱ ትክክለኛ ሥራ ወረዳውን ያጠናቅቃል ፡፡

🔷 5. VPP ( Voltage Programming Power )
ቀደም ሲል ይህ ፒን በሲም ካርዱ ማህደረ ትውስታ ውስጥ ያለውን ውሂብ ለመፃፍ ወይም ለመሰረዝ የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ቮልት ለመሸከም ያገለግላል ነገር ግን አሁን ይህ ስራ በVCC የሚሰራ ስለሆነ በጣም ጠቃሚ አይደለም፡፡

🔷 6. SIM Data I/O Pin

ግብዓት / ውጤት-በሞባይል ስልኮች በሲም ካርድ ውስጥ ያለውን data ለማንበብ እና ለመፃፍ ጥቅም ላይ ይውላል ፡፡ እንደ የdata ማስተላለፊያ ፒን የሚሰራ ግማሽ ባለ ሁለትዮሽ የግንኙነት ፒን ነው። ሲም ካርዱ እያነሰ እና እየቀነሰ ሲመጣ አፈፃፀሙ እና አቅሙ በየቀኑ እየጨመረ ሲሆን በአዲሱ ቴክኖሎጂ እና ምርምርም ምስጋና ይግባው ፡፡

Join : @teleport_tech

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

ትላልቅ ወረቀቶችን ሳናባክን እንዴት መጠቀም እንችላለን የሚለውን ይመልከቱ!

Читать полностью…

TelePort (ቴሌፖርት)

https://www.youtube.com/watch?v=I86v0-KmtRM&feature=youtu.be

Читать полностью…
Subscribe to a channel