ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
2023 SY20 የተሰኘው አስትሮይድ በ18 ኢትዮጵያዊያን ተማሪዎች ግኝትነት ተመዘገበ።
በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ የማኅበረሰብ አቀፍ ሳይንስ ፕሮጀክት ሥር የሚገኘው የኢትዮ-አስቴሮይድ አዳኞች ክለብ አዲስ 2023 SY20 የተባለ የምልምል አስቴሮይድ ግኝት ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።
ይኸው ግኝት 18 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የአስትሮይዱን እንቅስቃሴ ከዓመት በፊት በማስተዋል ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከቀናት በፊት የዓለም አቀፉ የሥነ-ፈለካዊ ፍለጋ ትብብር ( IASC ) ግኝቱን አጽድቋል።
ይህም በኢትዮጵያውያን ዜጋ ሳይንቲስቶች የተገኘ የመጀመሪያው የአስትሮይድ ግኝት ያደርገዋል ተብሏል።
ምልምል አስቴሮይዱ ሊገኝ የቻለው በPan-STARRS የሕዋ ምልከታ ጣቢያ በተነሱ ምስሎች ሲሆን ፤ ተማሪዎቹ እነዚህን ምስሎች በመጠቀም እና ልየታ በማካሄድ ይህን ምልምል ምልምል አስቴሮይድ ሊያገኙ ችለዋል ሲል የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ለቲክቫህ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
ይህ ፕሮግራም በዓለም አቀፉ የሥነፈለካዊ ፍለጋ ትብብር ( IASC ) የፓን-አፍሪካን የአስቴሮይድ ፍለጋ ንቅናቄ አማካኝነት የሚተገበር ነው።
በሌሎች አፍሪካ ሀገራት የሚገኙ ወጣቶችም በግልም ይሁን በጋራ ተመሳሳይ የአስትሮይድ ፍለጋ ፕሮጀክቱ ላይ ተሳታፊ ሲሆኑ ከአንድ በላይ ያስመዘገቡም እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።
@TikvahethMagazine
በኦላይን መድረክ 50 የሚጠጉ ህጻናት ላይ ጾታዊ ጥቃት የፈጸመው አየርላዳዊ በእስራት ተቀጣ።
በሰሜናዊ አየርላንድ የሚኖረው የ55 ዓመቱ ዴቪድ ጆን አንድሪውስ በ130 የወሲብ ጥቃቶች ተከሶ የ27 ዓመት እስራት ተፈርዶበታል።
ከዚህ ውስጥ 46ቱ ህፃናት ናቸው ተብሏል። ጥቃት ካደረሰባቸው ህፃናትም ውስጥ በዕድሜ ትንሿ የ8 ዓመት ህፃን ናት።
ወንጀለኛው ጥቃቱን የፈጸመው እንዴት ነው ?
ጥቃት አድራሹ እራሱን በ አስራዎቹ እንደሚገኝ ታዳጊ አስመስሎ በ snapchat እና በ instagram ገፅ ላይ ለጥፎ 50 የሚደርሱ ህፃናት ላይ ጥቃት በማድረስ ነው ጥቃቱን ሲያደርስ የነበረው።
በተደረገው ምርመራም መርማሪዎቹ 10,000 የሚጠጉ ህገ-ወጥ የህፃናት ምስሎችን በአንድሪውስ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያው ላይ ያገኙ ሲሆን በአስራዎቹ እንዳለ ታዳጊ መስሎ ለመለጠፍ የተጠቀመባቸውን 40 የሚሆኑ የመለያ ስሞችም (user names) ተገኝቷል።
አብዛኛዎቹ ወንጀሎች "ካትፊሺንግ" ማለትም አንድ ሰው የሌላን ሰውን ምስል እንደራሱ አድርጎ ማቅረብ ጋር የሚያያዝ ነው።
ወንጀሎቹ በፍርድ ቤቱ ሲቀርቡ የአስገድዶ መድፈር ሙከራ ፣ከ13 ዓመት በታች የሆነን ልጅ ወሲባዊ ተግባር እንዲፈፅም ማድረግ ወይም መገፋፋት፣ ወሲብ ነክ የሆኑ መልዕክቶችን ወይም ንግግሮችን ማድረግ፣ ማስፈራራት ይገኙበታል።
በተጨማሪም ህፃናት የወሲብ አገልግሎቶችን እንዲፈፅሙ ገንዘብ ለመክፈል ሙከራ ማድረግ፣ የህፃናትን የወሲብ ንግድ ወይም ፖርኖግራፌን ማዘጋጀት ወይም ማመቻቸት፣ ተገቢ ያልሆኑ ምስሎችን መያዝ ይገኙበታል።
በዳውንፓትሪክ ክራውን ፍርድ ቤት የተሰየሙት ዳኛ ጂኦፍሪ ሚለር "እሱ ራሱ ልጅ ነው በሚል የተሳሳተ እምነት ልጆቹን አታሏቸዋል ... ይህን ካደረገ በኋላ በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ከሱ ጋር በማህበራዊ ሚዲያ ምስል እንዲያጋሩት የተለያዮ ማስፈራሪያዎችንና ማሳመኛ መንገዶችን ይጠቀም ነበር" ሲሉ ይገልጻሉ።
"ከእያንዳንዱ ልጅ ጋር የተለዋወጠው መልዕክት የይዘቱ አፀያፊነት የተከሳሹን መጥፎና አስፈሪ የሆነ አስተሳሰቡን ያሳያል" ያሉት ዳኛዋ አንድሪውስ ተበዳዮቹ የሰጡትን ምስል በማሰራጨት ለእሱ ደስታ የሚሆኑ ተጨማሪ ነገሮችንም እንዲልኩለት እነሱንና ጓደኞቻቸውንም ያስፈራራ እንደነበር ተናግረዋል።
የተጠቂዎቹ ቁጥር እየጨመረ በሄደ ቁጥር እሱም የወንጀል ዱካዉን ለመሸፈን ጥረት ሲያደርግ እየሞከረ መቆየቱን አክለዋል።
የሚፈጸምበት መንገድ ይለያይ እንጂ በእኛም ሀገር ተመሳሳይ ጥቃቶች ይፈጸማሉ። ቤተሰብ ከልጆቹ ጋር ያለውን ቅርበት በማጠናከር ከተመሳሳይ ጥቃት ልጆችን መጠበቅ፤ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ ልጆችን ከዚህ ሂደት እንዲወጡ ከባለሞያ ጋር ማገዝ ከምንም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው።
Source : Sky News
@TikvahethMagazine
መኖሪያዎን በፍጥነት እና በጥራት እየገነባን እንገኛለን!
እርሶም በካሬ 99,000 ብር በ15% ቅድመ ክፍያ
📌ቦሌ ደንበል (ከ71 ካሬ ጀምሮ)
📌 ገርጂ መብራት ሀይል
(ከ 169 ካሬ ጀምሮ)
📌ብስራተ ገብርዔል ከሚገኙ አፓርትመንቶች መኖሪያዎን ይምረጡ !
📌 የንግድ ሱቆች ከ 20 ካሬ ጀምሮ በገርጂ ሳይት
📞 0931333432 ወይም 0909340800
ማን እንደ ቤት🏘
ፓልም ሪል እስቴት 🌴
#AddisAbaba
"የትራፊክ ደንብ መተላለፍ የፈጸሙ ከ10ሺህ የሚበልጡ አሽከርካሪዎች የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል" - ት/ማ/ባ
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከሐምሌ 2016 እስከ ጥቅምት 30/2017 ባሉት 4 ወራት የትራፊክ ደንብ ተላልፈዋል ባላቸው ከ10ሺህ የሚበልጡ አሽከርካሪዎች ላይ የገንዘብ ቅጣት መጣሉን ገልጿል።
ከፍተኛ ቁጥር የሚይዘው ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ሲሆን ባለሥልጣኑ በተመረጡ 33 መንገዶች ላይ አካሄድኩት ባለው በቴክኖሎጂ በተደገፈ የፍጥነት ቁጥጥር ከ3,513 በላይ አሽከርካሪዎች በገንዘብ ቅጣት ተቀጥተዋል ብሏል።
እንዲሁም በከተማዋ 5 መስመሮች ላይ ለአውቶቡስ ብቻ በተፈቀደው መስመር 288 ጊዜ ቁጥጥር ተደርጎ 2,687 አሽከርካሪዎች ደንቡነ ተላልፈው የገንዘብ ቅጣት አንደተጣለባቸው በባለስልጣን መ/ቤቱ የትራፊክ ቁጥጥርና ኩነት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያሌው ኢቲሳ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም፦
- የትራፊክ መብራት ላይ ወይም በመስቀለኛ መንገድ ላይ ምጽዋት የሰጡ 56 ደንብ ተላላፊዎች፤
- ስልክ እያነጋገሩ የነበሩ 735 አሽከርካሪዎች፤
- የደህንነት ቀበቶ ባላደረጉ 651 አሽከርካሪዎች፤
- የጭንቅላት መከላከያ ቆብ ሳያደርጉ ያሽከረከሩ 60 የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች፤
- በህዝብ ትራንስፖርት መቆሚያ ስፍራ (Bus stop) ላይ ያሽከረከሩና የቆሙ 2,972 አሽከርካሪዎች የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል ተብሏል።
@TikvahethMagazine
መኖሪያዎን በፍጥነት እና በጥራት እየገነባን እንገኛለን!
እርሶም በካሬ 99,000 ብር በ15% ቅድመ ክፍያ
📌ቦሌ ደንበል (ከ71 ካሬ ጀምሮ)
📌 ገርጂ መብራት ሀይል
(ከ 169 ካሬ ጀምሮ)
📌ብስራተ ገብርዔል ከሚገኙ አፓርትመንቶች መኖሪያዎን ይምረጡ !
📌 የንግድ ሱቆች ከ 20 ካሬ ጀምሮ በገርጂ ሳይት
📞 0931333432 ወይም 0909340800
ማን እንደ ቤት🏘
ፓልም ሪል እስቴት 🌴
#DireDawa
"ከ130 ሚሊየን ብር በላይ በታክስ ስወራ እና ማጭበርበር የተጠረጠሩ 3 ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል" - የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን
የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ከ132 ሚሊየን ብር በላይ በታክስ መሰወር እና ማጭበርበር ተግባር ላይ የተሰማሩ ሶስት ግለሰቦች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።
ከሶስቱ ግለሰቦች ሁለቱ ያለ ግብይት ደረሰኝ በመቁረጥ ፤ በሀሰት ግብይት የሚያከናውኑ እና የባንክ ስሊፕ ማቅረብ ያልቻሉ ናቸው ተብሏል።
ሶስተኛው ግለሰብም ሀሰተኛ የንግድ ፍቃድ በመያዝ ለአምስት አመታት በስራ ላይ መቆየቱን የባለስልጣን መ/ቤቱ የኦዲት እና ህግ ማስከበር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አክሊለ ታጠቅ ገልጸዋል።
በተደረገው ምርመራም፦
- አንደኛው ተጠርጣሪ 88 ሚሊየን 713 ሺ ብር፤
- ሁለተኛው ተጠርጣሪ 28 ሚሊየን 292ሺ ብር፤
- ሦስተኛው ተጠርጣሪ 15 ሚሊየን 336ሺ ብር ግብርን በመሰወር እና በማጭበርበር ተግባር ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ውለዋል ብለዋል።
ሶስቱ ተጠርጣሪዎች እያንዳንዳቸው 153 ሚሊየን 266ሺ ፣ 56 ሚሊየን 311 ሺ እንዲሁም 22 ሚሊየን 45ሺ በድምሩ ከ231 ሚሊየን ብር በላይ አመታዊ ገቢ እንዳላቸውም ተጠቅሷል።
በመግለጫው ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ለቀረበባቸውን ክስ በ21 ቀናት ቅሬታቸውን እንዲያስገቡ እድሉ ተሰጥቷቸው እንደነበር ሆኖም ከቅርንጫፍ መስሪያ ቤቱ ጋር ለመነጋገር ፍቃደኛ እንዳልነበሩ ነው የተነገረው።
የግለሰቦቹን ማንነት እንዲሁም የፍትህ ሂደቱን በተመለከተ ተቋሙ በቀጣይ የህግ አግባብን በመከተል ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በድሬደዋ ከተማ መስተዳድር በ2016 በጀት አመት 27 ግለሰቦች ደረሰኝ ባለመቁረጥ የተያዙ ሲሆን በዘንድሮ በጀት አመት ደግሞ 14 ግብር ከፋዮች በተደረገ ክትትል እስከ ተመጣጣኝ ቅጣት ማስተላለፍ እርምጃ መወሰዱን አቶ አክሊለ ተናግረዋል።
#DireTv
@TikvahethMagazine
"የባለሙያውን ሚና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ እና እንደ ስጋት የጠቀስናቸውን ጉዳዮች ተመልሰውልናል " -የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኢትዮጵያ ሕንፃዎች አዋጅን፤ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁ ይታወሳል።
አዋጁ የወጣው በነባሩ የኢትዮዽያ ህንፃ ሕግ ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት የህዝብ መገልገያ ህንፃዎች ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽነትንና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ለማስቻል ነው ተብሏል።
አዋጁ ከመጽደቁ በፊት ረቂቁ ለከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበበት ወቅት ረቂቁ ከዚህ ቀደም የነበረውን "ባለሞያ ተኮር " ሂደት በአዲሱ ረቂቅ "ድርጅት" ተኮር እንዲሆን መደረጉ አግባብ አይደለም በሚል ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር እና ከሌሎችም ትችት ሲቀርብበት ነበር።
ከዚህ ቀደም በነበረው አዋጅ ባለሞያ ተኮር የሆኑ እና የባለሞያውንም የሞያ ክብር የሚያረጋግጡ አንቀጾች በአዲሱ ረቂቅም እንዲካተቱ እና ወደ ድርጅት ተኮር ወደ ሆነ አሰራር እንዳይቀየሩ የኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር ጠንከር ያለ ክርክር ሲያደርግ ቆይቷል።
ክርክር ሲያደርግ ከቆየባቸው ነጥቦች ውስጥ አዋጁ ማተኮር ያለበት እያንዳንዱ ባለሞያ ማለትም አርክቴክት፣ ስትራክቸራል ኢንጂነር፣ የኤሌክትሪክ ባለሞያ የሚመለከተውን ስራ ብቻ እንዲሰራ አዋጁ ማረጋገጥ አለበት የሚለው አንዱ ነው።
ይህ ካልሆነ ድርጅቱ እነዚህን ባለሞያዎች ቀጥሮ ሲያሰራ ሃላፊነታቸውን በትክክል መወጣታቸውን በማያረጋግጥ መንገድ ከመሆኑም በላይ ጥቅሙ ወደ ድርጅት ሲሄድ ጥፋት ሲኖር ግን የጥፋት ተጠያቂነትን ወደ ባለሞያው የሚያመጣ አሰራር መሆኑን ሲገልጽ ቆይቷል።
በተጨማሪም የህንጻ ዲዛይን ስራን ማንኛውም ሰርተፍኬት ያለው ባለሞያ ወይም ሌላ ሰው ማስተባበር እንዲችል በመጀመሪያው ረቂቅ ላይ መቅረቡ አግባብ አለመሆኑን እና ሁሉም ሙያውን አክብሮ እንዲሰራ መደረግ እንዳለበትም ሲገልጽ ቆይቷል።
የማህበር ፕሬዝዳንት አርክቴክት ሐብታሙ ጌታቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት "ረቂቁ ላይ ሃሳባችንን ከሰጠን በኋላ የመጨረሻ ረቂቁን የማየት እድል አልነበረንም አሳዩን ስንል እናንተ የምትሰጡትን ግብአት ስለጨረሳችሁ ተሳትፏቹ አልቋል ስንባል ከተጠያቂነት ለመዳን በሚል ረቂቁ በሙያ እና በሙያ ባለሙያ ላይ ስጋት የሚያሳድር በመሆኑ ስጋቶች አሉን በሚል አቋማችንን አሳውቀናል" ብለዋል።
ማህበሩ በወቅቱ በአቋም መግለጫው ያሳወቃቸው እና በረቂቁ ላይ መካተት አለባቸው በማለት አጽንኦት የሰጠባቸው ነጥቦች
1) አዋጁ ድርጅት ተኮር ሳይሆን ባለሙያ ተኮር ተደርጎ መዘጋጀት እንዳለበት።
2 ) የሙያ ጥሰት ተጠያቂነት የሚመጣው በገለልተኛ የባለሙያ ቦርድ ተገምግሞ እንጂ ሚዛናዊነትን ባልጠበቀ መልኩ አንድ ተቋም ራሱ ከሳሽ ራሱ መርማሪ እና ራሱ ፈራጅ መሆን እንደሌለበት።
3 ) የሕንፃ ዲዛይን ስራ የአርክቴክቱ የፈጠራ ውጤት እንደመሆኑ በብቸኝነት የዲዛይን ስራን ማስተባበር ያለበት አርክቴክቱ መሆን አለበት የሚሉ ነበሩ።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አርክቴክት ሐብታሙ በአቋም መግለጫው የተካተቱት ነጥቦች በትክክል መመለሳቸውን እና በአዋጁ ተካተው እንዲጸድቁ መደረጉን ነግረውናል።
"በተለይ የባለሙያውን ሚና ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ እና እንደ ስጋት የጠቀስናቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች በሙሉ ምላሽ በማግኘታቸው ይህንን ድምፃችንን ሰምተው ተገቢውን ማስተካከያ ያደረጉ አካላትን በሙሉ ማህበሩ ማመስገን ይፈልጋል" ብለዋል።
"በብዛት እኛ ሃገር ያለው ልምምድ እንደሚያሳየው የህንጻውን ዲዛይን የሰራው ባለሞያ ሳይሆን ሌሎች ገብተው ህንጻውን ሲያምሱት ይታያል መጨረሻ ላይ ተጠያቂ የሚሆነው ግን ዲዛይነሩ ነው የአሁኑ አዋጅ ግን በግልጽ ህንጻውን ዲዛይን ያደረጉት ሰዎች ገብተው ሥራውን ሰርተው ተቆጣጥረው የማስረከብ ሃላፊነትን ከተጠያቂነት ጋር ሰጥቷል ለዚህም ምስጋና አለን" ብለዋል።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት "ገለልተኛ የሞያ አጣሪ ቦርድ የሚለው ወይም በአቋም መግለጫው ላይ በሁለተኛነት የተቀመጠው ይቀራል በደንብ እና በመመሪያ ጸንቶ ይወጣል ብለን እናስባለን ተጠሪነቱ ለተቋሙ መሆን የለበትም ነው የምንለው የፍትህ መዛባት እንዳያስከትል ይህን መለየት አለብን የሚል አቋም አለን "ሲሉ አክለዋል።
#TikvahEthiopia
@TikvahethMagazine
መኖሪያዎን በፍጥነት እና በጥራት እየገነባን እንገኛለን!
እርሶም በካሬ 99,000 ብር በ15% ቅድመ ክፍያ
📌ቦሌ ደንበል (ከ71 ካሬ ጀምሮ)
📌 ገርጂ መብራት ሀይል
(ከ 169 ካሬ ጀምሮ)
📌ብስራተ ገብርዔል ከሚገኙ አፓርትመንቶች መኖሪያዎን ይምረጡ !
📌 የንግድ ሱቆች ከ 20 ካሬ ጀምሮ በገርጂ ሳይት
📞 0931333432 ወይም 0909340800
ማን እንደ ቤት🏘
ፓልም ሪል እስቴት 🌴
የባንኮች ተቆጣጣሪ ነኝ ሥራ አስቀጥራለሁ በሚል ያጭበረበረው ግለሰብ በ13 ዓመት እስራት ተቀጣ
በተለያዩ ባንኮች ተቆጣጣሪ ነኝ በማለት ለስራ ማስቀጠሪያ በሚል ከ11 ግለሰቦች ገንዘብ የተቀበለው ተከሳሽ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የቢሾፍቱ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ወስኖበታል።
የድለላ ስራ የሚሰራው ፀጋ ስዩም የተባለው ተከሳሽ በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ወራቶችና ቀናቶች በቢሾፍቱ ከተማ በማዘጋጃ ቤት አካባቢና በሌሎችም የተለያዩ ስፍራዎች የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ፣ የአቢሲኒያ፣ የአባይና የፀሀይ ባንኮች “ተቆጣጣሪ ነኝ" በማለት 11 ግለሰቦችን ማጭበርበሩ ነው የተገለጸው።
በዚህም በተጠቀሱት ባንኮች በተለያየ ደረጃ ማስቀጠር እንደሚችል በማሳመን በተለያየ መጠን ከግል ተበዳዮቹ ጉዳይ ማስፈጸሚያ በሚል አጠቃላይ 381 ሺህ ብር በስሙ በተከፈተ የባንክ ሂሳብ ሲቀበል እንደነበር የዐቃቤ ሕግ ክስ ያሳያል።
የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ ቢሾፍቱ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሹ ላይ የሙስና ወንጀልን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 28 ንዑስ ቁጥር 3ን ጠቅሶ ስድስት ክሶች አቅርቦበታል።
ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሹ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከል በሰጠው ብይን ተከሳሹ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን ማስተባበል ባለመቻሉ የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል።
በዚህም ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየቶችን መርምሮ ተከሳሹን በ13 ዓመት ጽኑ እስራትና በ9 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኗል።
Via: FBC
@tikvahethmagazine
#𝐗𝐞𝐞𝐫𝐂𝐢𝐢𝐬𝐞: በኢትዮጵያ፣ በጅቡቲ እና በሶማሊያ በጋራ ያቀረቡት የሶማሌ - ኢሳ ማኅበረሰቦች የቃል ልማዳዊ ህግ (𝐗𝐞𝐞𝐫 𝐂𝐢𝐢𝐬𝐞) በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርሶች መዝገብ ተመዝግቧል።
@tikvahethmagazine
የዘረፉትን መኪና ሰሌዳና ስፖንዳ ቀለም ቢቀይሩም ከመያዝ አላመለጡም
ንብረትነቱ የአቶ ሸዋረጋ ዉቤ ደምሴ የሆነና ነባር የሰሌዳ ቁጥሩ B-78113 አአ ኦባማ አይሱዙ የጭነት መኪና መነሻዉን ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ወረዳ አረሪቲ ከተማ በማድረግ 56 ኩንታል ጤፍ ጭኖ ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ጉዞ በማድረግ ላይ ሳለ ነው ዝርፊያው የተፈጸመው።
ተሽከርካሪው ሀላባ ዙሪያ ወረዳ አለም ጤና ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ከምሽቱ 6 ሰዓት ገደማ ሲደርስ የታጠቁ ሃይሎች መኪናዉን በማስቆምና ሹፌሩንና ረዳቱን ግንድ ላይ አስረዉ ተሽከሪካሪዉን ይዘዉ ይሰወራሉ።
በወቅቱ መኪናውን እያሽከረከረ የነበረው ሹፌር "አለም ጤና ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ የፀጥታ አካላትን የደንብ ልብስ የለበሱና መሳሪያ የታጠቁ፤*ስድስት የሚሆኑ ሰዎች ለፍተሻ በሚመስል መልኩ ያስቆሙን" ሲል ሁነቱን ያስረዳል።
አክሎም "ልክ መኪናዉ መረጋጋቱን ሲያረጋግጡ ወደ ገቢናዉ ተጠግተዉ መሳሪያ ደቀኑብንና በግድ ከመኪናዉ አስወርደዉን በመሳሪያ በማስፈራራት ገንዘብና የእጅ ስልካችንን ከወሰዱ በኋላ እጅና እግራችንን ከግንድ ጋር በማሰር ጫካ ዉስጥ ጥለዉን መኪናዉን ከነጭነቱ ይዘዉ ተሰወሩ።
እንዳንጮህ ዘራፊዎቹ የለበስነዉን ልብስ ቀደዉ አፋችንንም አስረዉበት ስለነበር ጮኸን ሰዉ እንዲደርስልን ማድረግ አልቻልንም፤በስቃ ዉስጥ አድረን በማግስቱ የአከባቢው ነዋሪዎች ደርሰዉ ፈቱንና የደረሰብንን ለሀላባ ፖሊስ አመለከትን" ሲል ገልጿል።
በማግስቱ ዘራፊዎቹ ተሽከሪካሪዉን ሊያሹት ይችላሉ ተብሎ ወደሚታሰቡ አጎራባች ከተሞች መረጃ እንዲሰራጭ የተደረገ ሲሆን መረጃዉ የደረሰዉ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ባገኛቸዉ ፍንጮች መነሻ በ24 ሰዓታት ዉስጥ ተሽከሪካሪዉን ከነ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪ አዛዥ ኮማንደር መልካሙ አየለ ዘራፊዎቹ የተሽከርካሪዉን ሰሌዳና ስፖንዳ ቀለም በመቀየር በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቱላ ክፍለ ከተማ ገመጦ ቀበሌ ዉስጥ አንድ እርሻ ማሳ ዉስጥ ደብቀዉት እያለ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል።
ባለንብረቱና የሹፌሩ እንዲሁም የረዳቱ ቤተሰቦች በተገኙበት ተገቢዉ ማጣራት ከተደረገ በኋላ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ተጠርጣሪዎችና አስፈላጊ መረጃዎች ተጠናክረዉ ጉዳዩ ወደ ተመዘገበበት የማዕላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ፖሊስ መላኩን አክለው ገልጸዋል።
@tikvahethmagazine
በአዲስ አበባ ጤና መድህን የአባልነት የምዝገባ ህዳር 30 ያበቃል።
በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች የሚካሄደውን የ2017 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባልነት የምዝገባ ህዳር 30 እንደሚያበቃ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
በዘንድሮው ዓመት አዳዲስ አባላቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል።
በከተማ አስተዳደሩ በጸደቀው መዋጮ መጠን መሠረት መደበኛ መዋጮ መጠን አንድ ሺህ 500 ብር ሲሆን የድሀ ድሃ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን ተነግሯል።
ይህ ማለት - ነባር አባል መዋጮ 1,500 ብር፣ አዲስ አባል መዋጮ 1,500 ብር እና የመመዝገቢያ 200 ብር በአጠቃላይ 1,700 ብር አመታዊ መዋጮ ይክፍላሉ ማለት ነው።
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆነ ልጆች እና በአባሉ ጥላ ስር ለሚኖሩ ተጨማሪ ቤተሰብ 750 ብር በመክፈል አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ።
በኢ-መደበኛ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተቀመጠውን መዋጮ በመክፈል ዓመቱን ሙሉ በሁሉም ውል በተገባባቸው የጤና ተቋማቶች አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ብሏል ቢሮው።
በ2016 ዓ.ም ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች በላይ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል የሆኑ ሲሆን ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ እስከ ፌደራል ሆስፒታሎች ባሉት የጤና ተቋሞች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸው መገለጹ ይታወሳል
@tikvahethmagazine
𝐍𝐞𝐰 𝐓𝐫𝐚𝐢𝐧𝐢𝐧𝐠 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐀𝐧𝐧𝐨𝐮𝐧𝐜𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭 📣📣📣
"National Customs Procedure" Second Round Training
For More Information join our channel @EFFSAAtrainingcenter
and Registration,
📱 +251 903 182525
📞 +251 115 589045
📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ1ሚሊዮን በላይ ፍልሰተኞችን እያስተናገደች ትገኛለች።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ1ሚሊዮን ሰባ አንድ ሺ በላይ ፍልሰተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እያስተናገደች ያለች መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNCHR) ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ።
ከዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው ሲገለጽ 54 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ እድሜያቸው 0- 17 የሚሆኑ ናቸው።
ከደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የፍልሰተኞች ቁጥር ያለ ሲሆን ይህም 40 በመቶ ይሆናል ነው የተባለው። በቀጣይነት ከሶማሊያ (34 በመቶ)፤ ከኤርትራ (17 በመቶ) ፤ ከሱዳን (8 በመቶ) የሚሆነውን ደረጃ ይይዛሉ።
በ2024 ብቻ 23,513 ፍልሰኞች በስደት የወጡ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል ያለው ተቋሙ ከ2023 ጀምሮ ከሱዳን የተሰደዱ እና ድጋፍ የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥርም 64,669 አድርሶታል።
የጋምቤላ ክልል ከፍተኛውን የፍልሰተኞች ቁጥር የሚያስተናግድ ክልል ነው ተብሏል። በክልሉ 389,200 ፍልሰተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሲገኙ በመቀጠል የሶማሊ ክልል መልከዲዳ 220,185 ፍልሰተኞችን በማስተናገድ ይከተላል።
መዲናችን አዲስ አበባ 79,571 ፍልሰተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ይገኙበታል ተብሏል።
19,400 የሚሆኑ ፍልሰተኞች ደግሞ 'ፋይዳ' የዲጂታል መታወቂያ ወስደዋል።
UNCHR በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ትግራይና አፋር ክልል በኩል ከኤርትራ የሚገቡ ስደተኞች ጥበቃ እና ከለላ ያስፈልጋቸዋል ሲል በሪፖርቱ አስቀምጧል።
ካለፈው ዓመት ጥር ወር ወዲህ ከ20,000 በላይ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደገቡ ይገመታል ሲል ነው የገለጸው።
የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራዊያን እነፈለሱ ላሉ ጥገኝነት ጠያቂዎች ምዝገባ አንዲካሄድ መንግስትን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም አስታውቋል።
ኤርትራዊያን ስደተኞችን አስመልክቶ UNCHR ያለው ስጋት ከምን የመጣ ነው?
ቢቢሲ በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች መጠነ ሰፊ እስራት እየተፈጸመባው ይገኛል በመቶዎች የሚቆጠሩት ላይ ደግሞ ፖሊስ የሚወስደው ርምጃ እየተጠናከረ መምጣቱን ዘግቧል።
በርካቶች ኤርትራን የሸሹት ከግዳጅ ወታደራዊ ግዳጅ እና ጭቆና ለማምለጥ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የእስር እና የመባረር ዛቻ ገጥሟቸዋል ሲል ነው ዘገባው የጠቀሰው።
ዘገባው UNHCR እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ጉዳዩን እየመረመሩ መሆኑን ገልጸውልኛል ብሏል። በዚህ ዘገባ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምላሽ ለማካተት እንዳልተቻለ ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት አሁንም አለመረጋጋት የስደተኞቹን ችግር የበለጠ አወሳስቦታል ነው ያለው ዘገባው።
@TikvahethMagazine
ተፈጥሮን የማይጎዳ ቢዝነስ እየሰሩ ነው? ማሳደግስ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ አሁኑኑ ለሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት ይወዳደሩ!
ከአካባቢና አየር ብክለት የፀዳ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያበረክትና ለተፈጥሮ ተስማሚ የሆነ ስራ የሚሰራ ተቋም ፣ የቢዝነስ ፈጠራ እያንቀሳቀሱ ያሉ የኢንተርፕረነር ድርጅት ወይም ግለሰብ ከሆኑ ይህ ታላቅ ሽልማት አያምልጥዎ!!
በ " The Earthshot Prize 2025" ይወዳደሩና ስራዎን የሚያጠናክሩበት እስከ 1 ሚሊዮን ፓውንድ ይሸለማሉ።
በዚህ ቀላልና ጊዜ በማይፈጅ ማስፈንጠሪያ ገብተው አሁኑኑ ያመልክቱ። https://apo-opa.co/3ZfDXdG
የማብቂያ ጊዜ December 04,2024
For more information please visit: https://www.multichoice.com/nominations-25.php
በኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች የኤች አይ ቪ ኤድስ ሥርጭት ከ2 -3 % እንደሚደርስ ተገለጸ።
በኦሮሚያ ክልል ያለውን የኤች አይ ቪ ኤድስ ሥርጭትን በተመለከተ በዛሬው ዕለት የክልሉ ጤና ቢሮ በሰጠው መግለጫ ላይ ተነስቷል።
መግለጫውን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ጉሻ ባላኮ የሰጡ ሲሆን በክልሉ 157,226 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር አብረው እንደሚኖሩና 131,278 የሚሆኑ ዜጎች መድኃኒት መጠቀም መጀመራቸውን ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም፦
- በ2016 ሦስት ሚሊዮን ሰዎች የኤች አይ ቪ ምርመራ አድርገው 10,267 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ማወቃቸውን፤
- ባለፉት አምስት አመታት 44,993 የሚሆኑ ዜጎች አዲስ ቫይረሱ እንዳለባቸው አውቀው መድኃኒት መጀመራቸውን፤
- 7,703 የሚሆኑ ዜጎች ባለፉት 5 ዓመታት በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን ገልጸዋል።
ዶ/ር ጉሻ አክለውም፥ በክልሉ ያለው አጠቃላይ የቫይረሱ የሥርጭት መጠን 0.6% መሆኑን አንስተው፥ ይህ ቁጥር በከተሞች ሲሆን ወደ 2-3% ከፍ እንደሚል ነው የተናገሩት።
የኤችአይቪ ስርጭት በጣም የከፋው ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ጉጂ፣ ሆሮሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ ጉጂ፣ ምስራቅ ሸዋ እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ አከባቢዎች መሆኑንም ተናግረዋል።
በክልሉ የትኞቹ ከተሞች የኤችአይቪ ሥርጭት በስፋት ታይቶባቸዋል?
እንደ ምክትል ኃላፊው ገለጻ የሥርጭት መጠኑ ከፍተኛ ብለው ያስቀመጧቸው፦
- ሞጆ
- አሰላ
- አዳማ
- ቢሾፍቱ
- አምቦ
- መቱ
- ነቃምቴ
- ሻኪሶ
- ሮቤ
- ሸገር
- ጅማ ናቸው።
ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፍበት መጠን በሀገር አቀፍ ደረጃ 8.64% ሲሆን በክልሉ ደግሞ 7.48% መሆኑን ዶ/ር ጉሾ ባላኮ በመግለጫው ወቅት የተናገሩት።
መረጃው የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።
@TikvahethMagazine
𝐍𝐞𝐰 𝐓𝐫𝐚𝐢𝐧𝐢𝐧𝐠 𝐏𝐫𝐨𝐠𝐫𝐚𝐦 𝐀𝐧𝐧𝐨𝐮𝐧𝐜𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭 📣📣📣
"National Customs Procedure" Second Round Training
For More Information join our channel @EFFSAAtrainingcenter
and Registration,
📱 +251 903 182525
📞 +251 115 589045
📍 Kazanchis, Nigist Towers Hotel and Apartments, 4th floor (In front of Elilly Hotel)
#ጥቆማ
በወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታህሳስ 13 እና 14 ለሁለት ተከታታይ ቀናት ነጻ የዐይን ህክምና አገልግሎት ይሰጣል።
ህክምናው የሚሰጠው ወራቤ ኮምፕሬሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከሀበሺስታን ዴቬሎፕመንት ኤንድ ኮኦፕሬሽን አሶሴሽን /Habeshistan development and cooperation Association/ ጋር በመተባበር ነው።
ህክምናው ነፃ የአይን ምርመራ እና የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎትን ያካትታል።
በመሆኑም የአይን ችግር ያለባችሁ በሙሉ በተጠቀሰው ቀን ወራቤ ሆስፔታል በመገኘት ነፃ የአይን ምርመራ እና የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ማግኘት እንደምትችሉ ሆስፒታሉ ገልጿል።
@TikvahethMagazine
የጾታዊ ጥቃት አድራሾችን የሚመዘግበው የዲጂታል የመረጃ ሥርዓት በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ተባለ።
ከእለት ተእለት እጨመረ ለመጣው የሴቶችና የሕፃናት ጥቃት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተማሪ ሕግ እየተረቀቀ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰአት ቀደም ሲል የነበረውን ሕግ ለማሻሻል፤ ሕጉን የመፈተሽ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ ማሻሻያው በቀደመው ሕግ ላይ የነበሩበትን ክፍተቶች በመለየት የመከላከሉን ሥራ ውጤታማ ማድረግ የሚያስችሉ ተጨማሪ ጠንካራ ሕጎች እና አሠራሮች ተግባራዊ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል፡፡
የሕጉ መሻሻል ያስፈለገው በሴቶችና በሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸው ፣ጥቃቶቹ በምስክር ፊት የሚደረጉ አለመሆናቸው፣ ከዛም ባለፈ ጥቃቶች እየረቀቁ በመምጣታቸው እንደሆነም ነው የገለጹት።
ከሕግ ማሻሻያ ሥራው ጎን ለጎን ጥቃት አድራሾችን መመዝገብ የሚያስችል ዲጂታል የመረጃ ሥርዓት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን እየጎለበተ እንደሚገኝም አስታውሰዋል፡፡
ይህ የመረጃ ሥርዓት ጥቃት አድራሾች ጥቃቱን ሲፈጽሙ መረጃቸው ተመዝግቦ ከዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ ጋር እንዲያያዝ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡
የሚለማው የዲጂታል ሥርዓት ጥቃት አድርሶ እንደተፈለገ መኖር እንደማይቻል እና ቀድሞ ማሰብ እንደሚገባ የሚያደርግ መተግበሪያ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፤ የማልማት ሥራውም በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ሲሉ ገልጸዋል።
መረጃው የኢፕድ ነው።
@TikvahethMagazine
የማንዋል ደረሰኝ ህትመት አገልግሎትን አንድ ማተሚያ ድርጅት ብቻ እንዲያሳትም ተወሰነ።
የገቢዎች ሚኒስቴር ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ጋር በደረሰኞች ላይ ልዩ መለያ ኮድ (QR-Code) አካቶ ማተም በሚያስችል አሠራር ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ስምምነቱ የህትመት ጥያቄ መቀበል፣ ከታተመ በኋላ የስርጭትና የቁጥጥር ሥርዓትን ማስፈን የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ደረሰኝ እንዲታተም ፍቃድ ከመስጠት ጀምሮ ያሉ አገልግሎቶችን ማስተናገድ እንዲቻል የራሱ የሆነ ዲጂታል ፕላትፎርም የተዘጋጀ ሲሆን ማንኛውም ግብር ከፋይ በዚሁ መንገድ መስተናገድ ይችላል ተብሏል።
ከታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ በዚሁ ፕላትፎርም የማንዋል ደረሰኝ የማሳተም ጥያቄ ማቅረብ ይቻላልም ተብሏል።
በአንጻሩ ከየካቲት 01/2017 ዓ.ም ጀምሮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ ጥቅም ላይ የሚውለው የማንዋል ደረሰኝ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ብቻ የታተመ መሆን ይጠበቅበታል።
የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) የተካተተበት እና አስመስሎ መስራት የማይቻል የህትመት ሥራ ለማከናወን መዘጋጀቱን በስምምነቱ ወቅት ገልጿል።
@TikvahethMagazine
መኖሪያዎን በፍጥነት እና በጥራት እየገነባን እንገኛለን!
እርሶም በካሬ 99,000 ብር በ15% ቅድመ ክፍያ
📌ቦሌ ደንበል (ከ71 ካሬ ጀምሮ)
📌 ገርጂ መብራት ሀይል
(ከ 169 ካሬ ጀምሮ)
📌ብስራተ ገብርዔል ከሚገኙ አፓርትመንቶች መኖሪያዎን ይምረጡ !
📌 የንግድ ሱቆች ከ 20 ካሬ ጀምሮ በገርጂ ሳይት
📞 0931333432 ወይም 0909340800
ማን እንደ ቤት🏘
ፓልም ሪል እስቴት 🌴
#Ethio_Istanbul
ኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር የአፍሪካ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ቀንን አከበረ
ሆስፒታሉ ህዳር 27/2017 ዓ.ም የተከበረውን 'የአፍሪካ ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ቀን' ከአፍሪካ ህብረት ጋር አንድ ላይ በመሆን ነፃ የጤና ምርመራ እና ምክር አገልግሎት በመስጠት አክብሮ ውሏል።
በተጨማሪም ሆስፒታሉ ከአፍሪካ ኀብረት ጋር የሕክምና አገልግሎት ስምምነት ፈፅሟል። በዚህ ስምምነት የድርጅቱ ሰራተኞች በሆስፒታሉ ሕክምና አገልግሎት ያገኛሉ።
ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል በቴክኖሎጂ በታገዘ የአገልግሎት አሰጣጡ፣ ማኀበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየተጋ የሚገኝ ተቋም ነው።
( ኢትዮ-ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል )
ምግብ ለመመገብ የሚያስቸግሩ ልጆችን በምን ዘዴዎች እናብላቸው?
ብዙ ወላጆች ልጆቻቸው አንበላም አሉን ምን ይሻላል? የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄን ሲያነሱ ይስተዋላል። በእርግጥ ልጆችን ማብላት ትዕግስት እና ጥበብ የሚጠይቅ ሂደት ነው። ለዛሬ ልናበላቸው ስንል ማድረግ ከሚገባን ነገሮች ዉስጥ በጥቂቱ ለመዳሰስ እንሞክራለን።
1፡ ለመመገብ በተቀመጥን ወቅት ማውራትና ማጫወት
መመገብ ህጻኑ እንደ አንድ ማኅበራዊ ግንኙነት እንዲመለከተው ማድረግ እንዲሁም ለህጻኑ ጠጣር ምግብ ስናቀርብለት አንድ አዲስ ነገር ከሚወደው ሰው እንደተሰጠው እንዲሰማው ማስቻል።
ስለምግቡ በማውራት ለምሳሌ “ቤቢ ካሮት እየበላ ነው፤ ካሮት ይወዳል" በማለት ማብላት የምንችል ሲሆን በዚያውም አዲስ ቃልም እንዲያውቅ እንረዳዋለን። በተጨማሪም አብረን አፋችንን በመክፈት ህጻኑም በማጉረስ የመመገቢያውን ሰአት ወደ መዝንኛ መቀየር አንዱ መንገድ ነው።
2፡ እንደምንበላ ማስመሰል
በምናበላው ጊዜ እራሳችን እንደምንበላ በማስመሰል ለምሳሌ ማንኪያ ሙሉ የህጻኑን ምግብ በመዉሰድ እንደምንበላ አፋችንን ከፍተን እንደ በላን በማስመሰል እንዲጓጓ በማድረግ ማብላት።
3፡ አለማስገደድ
በምናበላቸው ጊዜ አለመፈለግ፣ ጭንቅላታቸውን ማዞር እና አፋቸውን አለመክፈት ያለመፈለግ ምልክት ስለሚሆኑ ባለማስግደድ እስኪርባቸዉ መጠበቅና ፈልገው እንዲበሉ ማድረግ ይኖርብናል። የምናስገድጋቸዉ ከሆነ ሊጠሉ ስለሚችሉ ባናስገድዳቸው ይመከራል።
4፡ ማታ ጠጣር ምግብ አለመመገብ
ህጽኑ ወደ አልጋ በመሄጃዉ ሰዓት ጠጣር ምግብ ማታ እንዳይነሳ ብሎ መመገብ ህጻኑን የሚረብሸው እና በቂ እንቅልፍ እንዳያገኝ ያደርገዋል። ጠጣር ምግብ ላይፈጭና ድርቀት ሊያመጣ ስለሚችል ማታ ወይም ከመተኛቱ በፊት የጡት ወተት ወይም ፎርሙላ ማጥባት ይመከራል።
5፡ እራሳቸዉ እንዲበሉ ማበረታታት
ህጻኑ 6 ወር ሲሞላው ሁለት ችሎታዎችን ያዳብራል። እነርሱም #መቀመጥ እና #መያዝ ናቸው። በዚህ ጊዜ ልጆች ለመያዝ በሚያመቻቸው መጠን ፍራፍሬዎችን በመቆራረጥ እራሳቸው አንስተው እንዲበሉ ማበረታታት ያስፈልጋል።
6፡ ምግብ መቀያየር
አንድ አይነት ምግብ ሁሌ መመገብ ህጻኑ እንዲሰላቸውና እንዲጠላው ስለሚያደርግ የተለያ ምግብ በመቀያየር ማብላት ይገባል።
7፡ የተቀላቀለ ምግብ አለመመገብ
አንድ ምግብ ብቻ ለህጻኑ ማስተዋወቅ አላርጂ የሆነውን መለየት እንድንችል ያደርገናል። ስለዚህ በመጀመሪያ ጠጣር ምግብ ስናስተዋውቀው ብዙ ምግቦችን በመቀላቀል ከሚሆን አንድ ብቻ በማብላት መጀመር ይመከራል።
8፡ ጨውና ስኳር አለመጠቀም
በመጀመሪያ ጠጣር ምግብ በምናስተዋውቅበት ጊዜ ስኳር እና ጨው አለመጠቀም የሚመከር ሲሆን ጣፋጭና ጨዋማ ምግብ ለልጆች በህጻንነታቸው ጊዜ አይመከርም።
[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]
@TikvahethMagazine
የአካል ጉዳተኞች ቁጥር እየጨመረ ስለሆመሆኑ ቢገለጽም ምን ያህል ለሚለው ግን በቂ ምላሽ የለም።
የአለም ጤና ድርጅትና አለም ባንክ በጋራ በ2011 እ.ኤ.አ በወጣ ጥናት በኢትዮጵያ 15 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከአካል ጉዳት ጋር ይኖራሉ ይህም በወቅቱ ከነበረው የህዝብ ቁጥር ከ17.6% የሚሸፍን ነበር።
በቅርብ በተደረጉ ጥናቶች ቁጥራዊ ዳታዎችን ማቅረብ ባይቻልም አሁናዊዉ የሀገራችን አሃዝ ደግሞ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ሕዝቦች ዉስጥ ከ20 በመቶ በላይ የሚሆነዉ ከልዩ ልዩ አይነት አካል ጉዳቶች ጋር አብሮ እንደሚኖር አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተለይም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የቅርቡን ጨምሮ ቀደም ብለው የነበሩ ጦርነቶች ጥለዉት ባለፉት አሻራ ምክንያት የአካል ጉዳተኞች ቁጥር በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ቁጥሩ ከፍ ያለ ነው።
ሆኖም ይህ ነው የሚባል ቁጥራዊ መረጃዎች ተመዝግበው አይገኙም። የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚንስትር ደኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊ፥ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰቱ ግጭቶች አዳዲስ አካል ጉዳተኞች መመዝገባቸው እንደማያጠያይቅ ይገልጻሉ።
ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ በትግራይና አማራ ክልሎች ግጭቶችን ተከትሎ ትክክለኛ ቁጥራዊ መረጃ ባይኖርም የአካል ጉዳተኞች ቁጥር እየጨመረ ስለሆመሆኑ ከማኅራት ጥምረት መረጃዎች እየደረሱ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።
የትግራይ ክልል የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ሕብረት ሊቀመንበር አቶ ዮሐንስ አበበ በቅርቡ በሰሜኑ የሀገራች ክፍል ተከስቶ የነበረዉ ጦርነት ተጨማሪ አዳዲስ አካል ጉዳተኞች ማስከተሉን ገልጸው የሚደረገው ድጋፍ ግን ከቁጥሩ አንጻር አነስተኛ መሆኑን ነግረውናል።
ሚንስቴር ደኤታ ወ/ሮ ሁሪያ አሊም በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በኋላ ድጋፍ አድርገናል ሲሉ ገልጸው፥ ከተደራሽነት አንፃር ግን በቂ አለመሆኑን አንስተዋል።
የአማራ ክልል አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ጥምረት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ማህቶት በለጠ በበኩላቸዉ አሁን ላይ በአማራ ክልል በተለያዩ አከባቢዎች ባሉ ግጭቶች ምክንያት አዳዲስ አካል ጉዳተኞች እየተመዘገቡ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ማኅቶት አክለውም፥ በክልሉ ግጭቶች ባሉባቸዉ አከባቢዎች ላሉ ነባር አካል ጉዳተኞች ከቤት እንዳይወጡ በስልክና በአጭር የፅሑፍ መልዕክት የጥንቃቄ መልዕክቶችን እንደሚያደርሱ መሆኑንም ነው የገለጹት።
ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ለ33ኛ፤ ሀገራችን ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ በሀዋሳ ከተማ መከበሩ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethmagazine
በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋት አይደለም የሚሉ ሰዎች ከሚበዙባቸው ሀገራት ተርታ ነች - ጥናት
በሎይድ ሬጅስተር ፋውንዴሽን በተካሄደ የዓለም ስጋት ደሰሳ ጥናት መሠረት 39% ኢትዮጵያውያን የአየር ንብረት ለውጥን እንደ ስጋት አይቆጥሩትም ሲል ያስቀምጣል።
ይህም ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ሥጋት አይደለም ብለው የሚያስቡ ሰዎች በብዛት ካሉበት ሀገራት መካከል በሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።
በጥናቱ እንደተቀመጠው በኢትዮጵያ ውስጥ 40 በመቶ የሚሆኑ አዋቂዎች የአየር ንብረት ለውጥን እንደ ደኅንነት ሥጋት አድርገው ሲመለከቱት ከዚህ ውስጥ 16 በመቶዎቹ ‘በጣም ከባድ’ ስጋት እንደሆነ አስቀምጠዋል። 21 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ስጋት መሆኑን እና አለመሆኑን እንደማያውቁ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ስላለው የአየር ንብረት ለውጥ ሰዎች ያላቸው አመለካከት እና ሀገሪቱ እየተጋፈጠችው ባለው አደጋ መካከል ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ ጥናቱ የሚጠቁም ሲሆን በዚህ ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሥራ የበለጠ መስራት ያስፈልጋልም ተብሏል።
ይህ መረጃ የተሰበሰበው በዓለም ዙሪያ ባሉ 142 ሀገራት በተደረገ 147,000 ቃለ መጠይቅ ነው።
በጥናቱ መሰረት የአየር ንብረት ለውጥ ምንም አይነት ስጋት አይደለም የሚሉ ሰዎች የሚበዙባቸው 10 ሀገራት፦
🇸🇦 ሳውዲ አረቢያ (46%)
🇪🇹 ኢትዮጵያ (39%)
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (38%)
🇮🇱 እስራኤል (36%)
🇮🇶 ኢራቅ (33%)
🇲🇱 ማሊ (31%)
🇧🇭 ባህሬን (30%)
🇯🇴 ጆርዳን (28%)
🇪🇪 ኢስቶኒያ (27%)
🇮🇳 ህንድ (25%)
@tikvahethmagazine
በ "Alive" የጋራ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና የቤተሰብ ቬስቲቫል ላይ ይሳተፉ!
እሁድ ህዳር 29/2017 ዓ.ም አስደሳች የቤተሰብ ጨዋታዎች፣ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች፣ ጤናማ ምግቦች ከጤና ምክር ጋር ለእርስዎ እና ለልጆችዎ ተዘጋጅቶሎታል።
ይምጡ ከነቤተሰብዎ የደስታ ጊዜን ያሳልፉ!
📍ቦታ :- ወሎ ሰፈር በሚገኘው ቃና ስቱዲዮ
🕑 ሰዓት :- ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ
የመግቢያ ቲሸርቱ ዋጋ:
ለአዋቂዎች 500 ብር
ለህፃናት (ከ8 ዓመት በታች) 300 ብር
ቲሸርቱን :- በቴሌ ብር: Alive
በአዋሽ ብር መርቻንት ኮድ Alive01
በሳንቲም ፔይ ALIVE Payment https://santim.io/?eid=1383
በሁሉም አማራጭ የገዙትን ቲሸርት ከሚከተሉት የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፎች ይውሰዱ :-
- ሳር ቤት አፍሪካ አንድነት ቅርንጫፍ
- አድዋ ሙዚየም ሸገር ቅርንጫፍ
- ጉርድ ሾላ ቅርንጫፍ
- ፍፌንድ ሺፕ ህንፃ ቦሌ ቅርንጫፍ
ለተጨማሪ መረጃ 0974108244 ይደውሉ
ገቢው ሙሉ በሙሉ ለተቀናጀ የህፃናት እድገት ማዕከል ግንባታ ይውላል።
#AddisAbaba
በመዲናችን የሚገኝ አንድ በርበሬ ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ የሚመረትበት መጋዘን ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ የሚገኘው ይኸው መጋዘን በህገወጥ መልኩ በርበሬን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ምርት ሲመረት በቁጥጥር ስር መዋሉን ወረዳው አስታውቋል።
@tikvahethmagazine
ሐሳብ አለኝ ዲጂታል መጽሔት በቅርብ ቀን!
ሐሳብ ላላቸውና ሐሳባቸው ማካፈል ለሚወዱ፤ ጥናትና ምርምር በማድረግ ለማኅበረሰብ ጠቃሚ መረጃዎችን ለሚሰጡ፤ በእውቀትና ሐቅ ላይ ቆመው ለሚሟገቱ ወጣቶች አዲስ መድረክ ተከፍቷል።
ይህ መድረክ፥ አዳዲስ ድምጾች የሚሰሙበት፤ ሐሳቦች የሚንሸራሸሩበት ወጣቶች በአከባቢያቸው ስላሉ ጉዳዮች ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ የሚያበረታታ እና ሥራቸውን የሚያቀርቡበት አዲስ መንገድ ነው።
እነሆ በቅርቡ አንድ እርምጃ እንራመዳለን፥ ለወራት በተለያየ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ጥናት በማድረግ የቆዩ ወጣቶች ሥራቸውን እነሆ ይላሉ። #ሐሳብ_አለኝ ቅጽ 1 ዲጂታል መጽሔት ዝግጅቷ ተጠናቆ በቅርቡ በዚሁ መድረክ ለአንባቢያን ትደርሳለች።
ዋና ዓላማችን ምን አይነት አቅም ያላቸው ወጣቶች እንዳሉ ማሳየት፤ ሙያዊ ክህሎትን ማሳደግ፤ የሥራ ላይ ልምምድን እንዲያዳብሩ ማስቻል እና የወጣቱ ሐሳብ የሚደመጥበት መድረክ መፍጠር ነው።
ከዚህም ባለፈ ጸሐፊያንን ለማበረታታት ለሥራቸው የሚመጥን ባይሆንም እንደ መጀመሪያ ለማበረታቻ የሚሆን ክፍያዎች ይኖሩታል።
ይህ ተነሳሽነት በመጽሔት ብቻ የሚገደብ ወንይም የተነሱት ሐሳቦች በጹሑፍ ብቻ የሚቀሩ ሳይሆኑ በሚነሱ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችና መድረኮች ይካሄዳሉ፤ አዳዲስ ድምጾች ፤ ልዩነት የሚፈጥሩ ሐሳቦች ወደ ማኅበረሰቡ የሚደርሱበት መድረክ ጭምር ይመቻቻል።
ከዚህም ባለፈ ሐሳብ እና አቅም ኖሯቸው የተደበቁ ወጣቶች የሚተዋወቁበት፤ ተጨማሪ የሥራ ዕድል የሚፈጠርበት፤ በሙያቸው ካሉ ሙያተኞች ጋር የመተዋወቅ እና ልምድ የማዳበር እድል የሚፈጠርበት፤ የተለያዩ ድጋፎች የሚያገኙበት አዲስ መድረክ ነው።
ሐሳብ ነበረኝ ግን እንዴት ለማኅበረሰቡ ላድርስ ብላችሁ ካሰባችሁ፤ በዚህ ጉዳይ ጥናት ማድረግ እወድ ነበር ግን ምን አደርገዋለሁ ብላችሁ ካቆያችሁት፤ የሚያሳስበኝ ነገር አለ ለዚያ ጉዳይ ለመሟገት ዝግጁ ነኝ ብለው ካሰቡ ይቀላቀሉን።
#አዳዲስድምጾች: የሐሳብ መሪነትና ሙያዊ ብቃት የሚንጸባረቅበት መድረክ
#EmergingVoice : A hub for thought leadership and professionalism
Produced by @Concepthubeth
published By @tikvahethmagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
"የገበያ ትስስር ስራ ፈጣሪዎችን ከሚያጋጥማቸው ችግር አንዱ ነው ዋነኛው ነው ብዬ ግን አልገልጸውም ዋነኛው ችግር የማይንድ ሴት እና የክህሎት ችግር ነው" - ዶ/ር ሃሰን ሁሴን
ማስተርካርድ ፋውንዴሽን በዛሬው ዕለት አመታዊ የአጋር አካላት መማማሪያ ጉባኤውን አካሂዷል።
በጉባኤው ወቅት እንደተገለጸው የማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በኢትዮጵያ በያንግ አፍሪካ ወርክስ ስትራቴጂ (Young Africa Works Strategy) እ.ኤ.አ ከ 2019 - 2024 ባለው የአምስት ዓመት ምዕራፍ 2.2 ሚሊየን ወጣት ወንዶች እና ሴቶች የስራ እድል እንዲያገኙ ማድረጉን ገልጿል።
ፋውንዴሽኑ እስከ 2030 ባለው የስትራቴጂ ትግበራ ወቅት 7 ሚሊየን ወጣት ሴቶችን እና 1 ሚሊየን የተጎዱ እና ተደራሽ ያልሆኑ ወጣቶችን ጨምሮ በጠቅላላው 10 ሚሊየን ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር በእቅድ ይዟል።
የስራ እድል ይፈጠርላቸዋል ከተባሉት ውስጥ 70 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
በአመታዊ ጉባኤው ላይ የክልል የስራ እና ክህሎት ቢሮ ሃላፊዎችን ጨምሮ የጉባኤው አጋር አካላት ታድመዋል።
በጉባኤው ላይ የተቋሙ የአምስት አመታት ጉዞን ጨምሮ ስላከናወናቸው ተግባራት ገለጻ ተደርጓል።
የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች የገበያ ትስስር እንዲያገኙ ምን እየተሰራ ነው ?
ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው ለሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆነው የኢትዮጵያ ኢንተርፕረነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሰን ሁሴን ናቸው።
ዳይሬክተሩ በምላሻቸው "የገበያ ትስስር ስራ ፈጣሪዎችን ከሚያጋጥማቸው ችግር አንዱ ነው ዋነኛው ነው ብዬ ግን አልገልጸውም ዋነኛው ችግር #የማይንድ_ሴት እና #የክህሎት ችግር ነው" ብለዋል።
አክለውም "ኢትዮጵያ ብዙ ችግር የሚፈራረቅባት ሃገር ናት ማህበራዊ እና እኮኖሚያዊ ችግሮች አሉ አንድ ሰው የስራ ፈጠራ ማይንድሴት ካለው ችግሮች ለእርሱ ሲሳይ ናቸው።
ነገር ግን ማይንድሴቱ የተዛባ ስለሆነ ብዙ ሰዎች ራሳቸውን ከመጠየቅ ይልቅ ሌላውን መጠየቅ ስለሚያስቀድሙ አጠገባቸው ያሉትን አያሌ እድሎች መመልከት አይችሉም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ሌላው ችግር ለሥራ ፈጠራ ገንዘብ የማግኘት ችግር እና ከመንግስት አሰራር ጋር ያሉ ችግሮች አሁንም ማነቆ ሆነው ቀጥለዋል ብለዋል።
ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን በካናዳ የተመዘገበ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በዓለም ትልቅ ከሚባሉ ፋውንዴሽኖች ውስጥ አንዱ ነው።
የፋውንዴሽኑ "ያንግ አፍሪካ ወርክስ ስትራቴጂ" ተግባራዊ መደረግ የጀመረው እ.ኤ.አ. በ2018 ሲሆን ዓላማውም በአፍሪካ 30 ሚሊዮን ወጣቶችን ከዚህም ውስጥ 21 ሚሊዮን ወጣት ሴቶችን እስከ 2030 ባለው ጊዜ ውስጥ ክብር ያለው እና አርኪ ሥራ እንዲያገኙ ማስቻል ነው።
ስትራቴጂው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ዘርፎች ውስጥ የግብርና ቢዝነስ፣ የግብርና ምርት ማቀነባበር/ማኑፋክቸሪንግ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ ይገኙበታል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@TikvahethMagazine