ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
ለልጆቻችን ምን እንመግብ ?
በሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ዩኒሴፍ ዘገባ 38.6% ከ5 አመት በታች ያሉ ልጆች የቀነጨሩ ሲሆኑ 21% የሚሆኑ 5 አመት በታች ያሉ ልጆች ከሚጠበቅባቸዉ ክብደት በታች ያሉ ሲሆን ከ15-49 ያሉ ሴቶች በምግብ እጥረት የተጎዱ ናቸው።
ስለተመጣጠነ ምግብ ማውራት ብዙ ሰው ቅንጦት ይመስለዋል፤ ነገር ግን ቅንጦት ሳይሆን እጅግ በጣም ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።
ምክኒያቱም የምግብ ጉዳይ ከጽንስ ጅምሮ እስከ 2 አመት ለልጆች የምናበላዉ እስከ ህይወት ፍጻሜያቸዉ ድረስ ተጽኖ ስለሚያመጣ ትኩረት ልናደርግ ይገባል።
ለልጆች መመገብ ካለብን ውስጥ
1፡ ጥሩ ቅባት (smart fat)፡
ህጻናት ትክክለኛ ቅባት/ fat /ያስፈልጋቸዋል። ይህ ማለት ዝቅተኛ ቅባት ሳይሆን ምርጥ ቅባት ያለዉ ምግብ ያስፈልጋቸዋል ማለት ነው።
-:ለህጻናት ጥሩ ቅባት ምንጭ ከሆኑ ምግቦች መካከል የባህር ምግብ(salmon)፣ ተልባ(flax oil)፣ አቮካዶ ፣ የአትክልት ዘይት ፣ ለውዝ (አላርጂክ ሊያስከትል ስለሚችል ከ2 አመት በኋላ)
- ለህጻናት ጥሩ ያልሆኑ ቅባቶች፡ ዘይት የበዛባቸውና የተጠበሱ ምግቦች፣ ብስኩት (crackers)
2: ጤናማ ስኳር (Best Carbs)
ህጻናት በተፈጥሮአቸዉ ስኳርና ጣፋጭ ነገሮችን ይወዳሉ፣ ሰዉነታቸዉም ይፈልጋል። ስኳር የሰዉነታቸዉ ዋናዉ ነዳጅ እና ሀይል ሰጪ ነዉ።
ጤናማ ስኳር የያዙ ምግቦች፦
አፕል ፣ ሙዝና ፍራፍሬ ፣ የጡት ወተት ፣ የወተት ተዋዖዎች (በተለይ ባዶ እርጎ) ፣ ትኩስ ፍራፍሬ፣ ፓስታ፣ ድንች ፣ አኩሪ አተር። ስኳር ድንች ፣ አትክልት እና አዝእርቶች።
3፡ ፕሮቲን
ፕሮቲን ገንቢ ምግብ በመባል ይታወቃል። ፕሮቲን ለእድገት፣ ለሰዉነትን ግንባታ ትልቁ ድርሻ ይወስዳል።
በፕሮቲን የበለጸጉ ምግቦች፦
የባህር ምግብ ፣ የወተት ተዋዕዖ (እርጎ፣ቺዝ እና ወተት) ፣ ጥራጥሬ (አኩሪ አተር፣ ምስር፣ ቦሎቄ)፣ ስጋና የዶሮ ስጋ፣ እንቁላል የለዉዝ ቅቤ ፣ያልተፈተጉ እህሎች (ስንዴ፣ ሩዝ፣ አጃ፣ በቆሎ እና ማሽላ)
4፡ በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን ማዘውተር
ፋይበር/ቃጫ/ የምንለዉ የማይፈጨው የአትክልት እና የፍራፍሬ አካል ነው። በተፈጥሮ አንሸራታችነት ባህሪ ስላለዉ ከሰውነታችን አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎችን ለማሶገድ ይረዳል። ለህጻናት በፋይበር የበለጸገ ምግብ ሰገራቸዉ እንዲለሰልስና አላስፈላጊ ቆሻሻ ቶሎ እንዲወገድ ከመርዳቱም ባሻገር ድርቀትን ይከላከላል።
በፋይበር የበለጸጉ ምግቦች፦
አትክልት( ድንች ከነልጣጩ)፤ ያልተፈተጉ እህል፤ ቡኒ ሩዝ፤ ቦለቄ የመሳሰሉት፤ ካልተፈተገ እህል የተዘጋጀ ፓስታ፣ መኮረኒ፣ አጃ፣ ጥራጥሬ።
5፡ ቪታሚን
ከሶስቱ ዋና የምግብ ክፍሎች ( ቅባት፣ ፕሮቲን፣ ሃይል ሰጪ ምግቦች) በተጨማሪ ቪታሚን ለህጻናት እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል። እንደ ዋና ምግቦች( Macro nutrients) እኚህ ቪታሚንና ሚኒራለስ (micro nutrients) በቀጥታ ለሰዉነታችን ሃይል አይሰጡንም። ነገር ግን ለህጻናት የበሉት ምግብ በአግባቡ እንዲጠቅማቸውና የሰውነት ክፍላቸው በአግባቡ እንዲሰራ ያደርጋል።
ሰውነታችን እነዚህን ንጥረነገሮች ካላገኘ በአግባቡ መስራት አይችልም። ሰውነታችን 13 ቪታሚኖች ያስፈልጉታል። ቪታሚን A, C, D, E, K, እና 8 የ B ቤተሰቦች ማለትም thiamine, niacin riboflavin, pantothenic acid, biotin, folacin, B6 and B12.
6: ሚኒራልስ
እንደ ቪታሚንስ ሚኒራልስ (micro nutrients) የሚካተት ሲሆን ለህጻናት እድገት አስፈላጊ ንጥረነገር ነው። ሚኒራል የምንላቸው ካልሽየም፣ ፎስፈረስ፣ ማግኒዝየም እነዚህ ሶስቱ ጠንካራ አጥንትን ለመገንባት ይጠቅማሉ።
አይረን እና ኩፐር (copper) ደምን ይገነባሉ። ዚንክ( zinc) በሽታ የመከላከል አቅምን ይገነባል፣ሶዲየምና ፖታሺየም( sodium and potassium) ኤሌክትሮ ላይት የምንለዉ በሰውነታችን ውስጥ ያለውን የውሃ መጠን ይቆጣጠራል።
7፡ የአይረን መጠንን መጨመር
እያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል( organs) በአግባቡ እንዲሰራ ብረት በጣም አስፈላጊ ንጥረነገር ነው። ዋናው ስራውም ሂሞግሎቢንን (hemoglobin) መገንባት እና በቀይ የደም ሴል ውስጥ ያለውን ኦክስጅን የሚሸከም ነው።
አንድ ህጻን ልጅ ከ9_10 ወራት ውስጥ ሂሞግሎቢኑ መለካት አለበት፣ ይህም የሚሆንበት ምክኒያት ህጻኑ የደም ማነስ እጥረት ይኑርበት አይኑርበት ለማጣራት ነው።
በአይረን የበለጸጉ ምግቦች፦
የጡት ወተት፣ በብረት የበለጸጉ የህጻናት ወተቶች፣ የቲማቲም ጁስ፣ምስር፣ አኩሪ አተር፣አሳ፣ የዶሮ ስጋ፤ ቦለቄ እና የመሳሰሉት።
[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]
@TikvahethMagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ሀይል ሽያጭ ልትጀምር ነው
ኢትዮጵያ በኬንያ በኩል 100 ሜጋ ዋት ያህል የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ታንዛኒያ ለመሸጥ ማቀዷን ብሉምበርግ ዘግቧል፡፡
ሽያጩ የሚጀመረው ሁለቱ አገራት የድንበር ተሻጋሪ የኤሌክትሪክ ሀይል ንግድን ለማካሄድ የሚያስችለውን ስምምነት ከጨረሱ በኋላ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
የሃይል ሽያጭ መጠኑ ሁለቱ አገራት ከተነጋገሩ በኃላ ሊከለስ እንደሚችል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ሞገስ መኮነን መናገራቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡
ኬንያ እና ታንዛኒያ ኃይል ለማስተላለፍ ከፍተኛ የቮልቴጅ መስመሮችን መጠቀም የሚያስችል ስምምነት መፈራረማቸው ሲገለጽ ስምምነቱ በኬንያ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን እንዲጸድቅ እየተጠበቀ ነው፡፡
ስምምነቱ ከተጠናቀቀ በኃላ ኢትዮጵያ በወላይታ ሶዶ አቅጣጫ በተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር፤ በኬንያ ሱስዋ በኩል ወደ ሰሜን ታንዛኒያ የኃይል ሽያጭ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡
@TikvahethMagazine
#ጥቆማ
የ2017/2024 ዓለምአቀፍ የንግድ ስራ ፈጠራ ሳምንት ህዳር 9 – 17, 2017 ዓ.ም ‹ኢንተርፕሪነርሽፕ ለሁሉም › በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡
የዘንድሮው ዓለም አቀፉን የአንተርፕሪነርሺፕ ሳምንት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር በህዳር ወር የግንዛቤ ማስጨበጫና መረጃ ሰጭ በሆኑ የተለያዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡበት ሆኖ የሚከበር ይሆናል፡፡
ቅዳሜ ህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሰት የሥራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም በርካታ አለም አቀፍ ተቋማት በተገኙበት የሙሉ ቀን የፓናል ውይይትና የመክክር መድረክ ይካሄዳል፡፡
እሁድ ህዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽት ከ12 ፡ 00 (ስዓት) ጀምሮ ወሰን አካባቢ የእሳት ዳር ጨዋታ (ስቶሪ ቴሊንግ) ልምድ የማካፋል ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡
በህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም በአፍሪካ ህብርት አዳራሽ ከጠዋቱ ሶስት ስዓት ጀምሮ ለግማሽን ቀን የአፍሪካ ተወካዩች በተገኙበት ስለኢንተርፕረነርሽፕ እና ተያያዥ የቴክኒክና ሙያ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ይደረጋል፡፡
በመጨረሻም የፕሮግራሙ ማጠቃለያ በኢንተርፕሪነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና መስሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ማክሰኞ ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ከስዓት በኃላ 8፡00 ጀምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና ጥሪ የተደረገላቸው የስነምህዳሩ ተዋንያን በተገኙበት የእውቅና ፕሮግራም እና ማጠቃለያ ይካሂዳል፡፡
በዘርፉ ያሉ ተዋንያን በዝግጅቶቹ እንድትሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።
@tikvahethmagazine
እንኳን ወደ ደህንነቱ የተጠበቀ ልዩ የጥርስ ህክምና በደህና መጡ! 🎊🎊🎉🎉
በሴፍ ስፔሻሊቲ የጥርስ ክሊኒክ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
1. Scaling (ጥርስ እጥበት)
2. Bleaching(ጥርስ ማንጣት)
3. Brace(ብሬስ)
4. Tooth Extraction (ጥርስ መንቀል)
5. Filling(ሙሌት)
6. Diastema closure(ፍንጭት መዝጋት)
7. Root canal treatment(የጥርስ ስር ህክምና)
8. ጥርስ መትከል ( ኢምፕላንት፣ ዚርኮኒያ ጥርስ፣ ሴራሚክ ጥርስ፣ ክሮሞኮባልት፣ አክሪሊክ )
ክሊኒካችን በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉ ታካሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያለውን የጥርስ ህክምና እና እንክብካቤ ይሰጣል።
📣ልብ ይበሉ!
ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እስከ 40% በሚደርስ ቅናሽ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነን ይጎብኙን።
🫵የዋጋ ዝርዝር ለማየት ቴሌግራም እና ቲክቶክ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ለተጨማሪ መረጃ
📞0907341414
📞0924143495
Telegram: /channel/Safedentalcare
Tiktok: safe.dental.care" rel="nofollow">https://tiktok.com/@safe.dental.care
"የቅድመ ክፍያ (Pre-Paid) ቆጣሪዎች ቅያሪ አደርጋለሁ" - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በያዝነው አመት ከጥር ወር ጀምሮ አውቶሜትድ የሆኑ የቅድመ ክፍያ (Pre-Paid) ቆጣሪዎች ቅያሪ እንደሚያደርግ ገልጿል።
አዲሶቹ ቆጣሪዎች ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ሲውሉ የነበሩ በካርድ የሚሰሩ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን የሚያስቀር ነው ተብሏል።
በዚህም ደንበኞች በስልካቸው በኦላይን በሚፈጽሙት (በቴሌብር ወይም በሞባይል ባንኪንግ) የኤሌክትሪክ ግዢ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው እንደሆነ ነው የተገለጸው።
ቆጣሪዎቹን የመቀየር ፕሮጀክት የሚካሄደው ዝቅተኛ የሃይል ተጠቃሚ በሆኑ እና ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ የሲንግል ፌዝ(Single Phase) ቆጣሪዎች ላይ እና በአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት ላይ በሚውሉ የስሪ ፌዝ (Three Phase) ቆጣሪዎች ላይ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሃላፊ አቶ ዘሪሁን አበበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በሲንግል ፌዝ ቆጣሪዎች ቅየራ የመጀመሪያ ዙር ትግበራ 10ሺ በሁለተኛ ዙር ትግበራ 15 ሺ በአጠቃላይ 25 ሺ ቆጣሪዎች ላይ ቅያሪ ይከናወናል ተብሏል።
የሙከራ ትግበራው ባልደራስ አካባቢ በመቶ ቆጣሪዎች ላይ መሞከሩን የገለጹት አቶ ዘሪሁን ውጤታማ ሆኖ በመገኘቱ ወደሙሉ ትግበራ ለመግባት በዝግጅት ላይ ነን ብለዋል።
የሲንግል ፌዝ ቆጣሪ ቅያሪው በተመረጡ አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ቀጣይነት ይኖረዋል ተብሏል።
በፕሮጀክቱ 125ሺ ለሚሆኑ የስሪ ፌዝ ቆጣሪዎች ቅያሪ የሚከናወን ሲሆን ይህም መሬት ላይ የሚገኙትን የስሪ ፌዝ ቆጣሪዎችን ሙሉ በሙሉ የሚተካ ይሆናል ብለውናል።
በፕሮጀክቱ 600ሺ ተጨማሪ ቆጣሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት በእቅድ መያዙን ሃላፊው ተናግረዋል።
ከጥር ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የሚጠበቀው የቆጣሪ ቅየራው የሚያስፈልጉ እቃዎችን ወደሃገር ውስጥ የማስገባት፣ አስፈላጊ የሆኑ የኔትወርክ እና የመገናኛ ገመዶችን የመዘርጋት እና ዳታ ቤዝ የመትከል ሥራዎች እየተጠናቀቁ ነው ብለዋል።
አቶ ዘሪሁን የቆጣሪ ቅየራው የሚከናወነው ሙሉ በሙሉ በነጻ መሆኑን አጽንኦት የሰጡ ሲሆን በቅየራው ሂደት ላይ ገንዘብ የሚጠይቁ ሰራተኞች ቢኖሩ ጥቆማ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በተጨማሪም ከሚያዚያ 2015 ዓም ጀምሮ በሁለት ዙር ተጀምሮ የነበረው ከፍተኛ ሃይል ተጠቃሚ ወይም የሃይል ፍጆታቸው ከ 25 ኪሎ ዋት(KW) በላይ በሚጠቀሙ የማሕበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚገኙ ቆጣሪዎችን በዲጂታል ቆጣሪዎችን የመቀየር ሂደት መጠናቀቁን ተገልጿል።
በመጀመሪያው ዙር ትግበራ 5ሺ በሁለተኛው ዙር ትግበራ 39 ሺ ቆጣሪዎችን ዲጂታላይዝ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
ይህ ዲጂታል ቆጣሪ የቅያሪ ሂደቱ በመጠናቀቁ ከአሁን በኋላ አዳዲስ ደንበኞች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሰረት ብቻ ቅያሪ የሚደረግ ይሆናል ተብሏል።
ዲጂታል ቆጣሪው በየቤቱ በሰው አማካኝነት የሚከናወኑ ቆጠራዎችን የሚያስቀር ሲሆን በተጨማሪም ደንበኞች የሃይል ፍጆታቸውን ለማወቅ ያስችላቸዋል የተባለ ሲሆን ይህንን የሚያሳውቅ አፕሊኬሽን በመጠናቀቅ ላይ ነው ብለዋል።
ዲጂታል ቆጣሪው ሃይል በሚቋረጥበት ጊዜ የሚጠቁሙ ጠቋሚዎች ያሉት ሲሆን አዲስ ደንበኞች ሲጠይቁ ለማቅረብ እንዲቻል ተጨማሪ 7 ሺ ዲጂታል ቆጣሪዎችን ለማስገባት በእቅድ መያዙን አቶ ዘሪሁን አበበ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba
@tikvahethmagazine
"የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ /ማሻሻያ/ ቁጥር 188/2017" ምን አዲስ ነገር ይዟል?
አዲሱ መመሪያ ከህዳር 3 ቀን 2017 ዓም ጀምሮ በፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቦ እና ጸድቆ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
- በመመሪያው መሰረት እያንዳንዱ የደረሰኝ ቅጠል ሲታተም ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) እንዲኖረው የሚያዝ ሲሆን ተካቶ ካልታተም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ማንኛውም አታሚ ደረሰኝ ሲያትም በታክስ ባለስልጣኑ የተዘጋጀውን ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) በመውሰድ በእያንዳንዱ የደረሰኝ ቅጠል ላይ አካቶ ሊያትም የሚገባው ሲሆን፤ ሲያትም የልዩ መለያ ኮዱ ወርድና ቁመት ቢያንስ 2 ሴንቲ ሜትር ሆኖ በደረሰኙ የቀኝ ራስጌ ላይ መታተም እንዳለበት ያዛል፡፡
- ማተሚያ ቤቱ ምንም አይነት ስህተት ወይም ልዩነት ሳይኖር ደረሰኞችን ልዩ መለያ ኮድ (unique QR code) በማካተት ለማተም በማንዋል ደረሰኝ QR- code (Manual Receipt QR-code Web Portal) የተጋራውን ዳታ በትክክል ተቀብሎ የመተግበር ግዴታ እንዳለበት አስቀምጧል።
- ማተሚያ ቤቱ በማንዋል ደረሰኝ QR-code አስተዳደር ፖርታል (Manual Receipt QR-code Web Portal) በኩል ዳታ ሲጋራ ተገቢነት ያላቸውን ሁሉንም የዳታ ጥበቃ ደንቦችና መመሪያዎችን የማክበር ግዴታ አለበት ይላል፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት ልዩ መለያ ኮድ ያለው ማንዋል ደረሰኝ ሲያትም በወረቀቱ ላይ ሊሰርግ የሚችል ኢንክ ጀት (Ink jet) የሚባል ቀለም የመጠቀም ግዴታ አለበት፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት እንዲታተም የተፈቀደውን እና የታተመውን ደረሰኝ በተመለከተ በተዘጋጀው ሲስተም በወቅቱ ሪፖርት የመላክ ኃላፊነት እንዳለበት አስቀምጧል፡፡
- ማንኛውም ማተሚያ ቤት በታክስ ከፋዩ ደረሰኝ እንዲያትም ሲጠየቅ፤ በታክስ ባለስልጣኑ ለታክስ ከፋዩ የተሰጠ የደረሰኝ ህትመት ፈቃድ ደብዳቤ ሳይቀበል ደረሰኝ ማተም የለበትም፡፡
- በዚህ መመሪያ መሰረት የደረሰኝ ህትመት አገልግሎት የሚሰጥ ማተሚያ ቤት ከሚኒስቴሩ ጋር የቅንጅት አሰራር ስምምነት የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡
በአዲሱ መመሪያ የመሸጋገሪያ ድንጋጌ መሰረትም:-
ማንኛውም ታክስ ከፋይ ይህ የማሻሻያ መመሪያ ተፈጻሚ ከመሆኑ በፊት አሳትሞ ያልተጠቀመባቸው ደረሰኞች መጠቀም የሚችለው የማሻሻያ መመሪያው ተፈጻሚ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባለው ለሶስት ወር ጊዜ ብቻ እንደሆነ አስቀምጧል፡፡
@tikvahethmagazine
እንኳን ወደ ደህንነቱ የተጠበቀ ልዩ የጥርስ ህክምና በደህና መጡ! 🎊🎊🎉🎉
በሴፍ ስፔሻሊቲ የጥርስ ክሊኒክ የእርስዎ ጤናማ ፈገግታ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው!
እኛ ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ውስጥ አጠቃላይ የጥርስ ህክምና አገልግሎቶችን እናቀርባለን።
ክሊኒካችን በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉ ታካሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያለውን የጥርስ ህክምና እና እንክብካቤ ይሰጣል።
📣ልብ ይበሉ!
በስፔሻሊስት ሀኪሞች እና በላቀ ቴክኖሎጂ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እስከ 40% በሚደርስ ቅናሽ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነን ይጎብኙን።
ለተጨማሪ መረጃ
0907341414
0924143495
Telegram: /channel/Safedentalcare
Tiktok: safe.dental.care" rel="nofollow">https://tiktok.com/@safe.dental.care
የሎተሪ ዕድለኛው የደረሰውን መኪና መሸጥ ይፈልጋል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲወጣ ባዘጋጀው የቶምቦላ ሎተሪ ዕጣ የሁለተኛ ዕጣ ዕድለኛ በመሆን የ1500 ሲ.ሲ የቤት አውቶሞቢል መኪና እድለኛ እንደሆኑ ተነግሯቸው ነበር።
ታዲያ የቤት ኦቶሞቢል ቁልፍ በእጃቸው ይዘው ፎቶ ቢነሱም፥ ተሽከርካሪው ግን በእጃቸው እንዳልገባ በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።
በጌዴኦ ዞን ወናጎ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ሸምሱ በቶቶቦላ ሎተሪ እጣ እድለኛ የሆነበትን ኦቶሞቢል ጥቅምት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ተረክበዋል።
ታዲያ አሁን ላይ እድለኛው መኪናውን መሸጥ እንደሚፈልግ ገልጿል። መኪናውን መሸጥ የፈለገበት ምክንያትም ወደ ገንዘብ ተቀይረው ጥሩ ቢዝነስ ለመጀመር መሆኑን ገልጿል።
መረጃውን ቅሬታውን ተከታትሎ ሲዘግብ ከነበረው ዳራሮ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽንን ማግኘታችንን እንገልጻለን።
@tikvahethmagazine
በታማኝነት ተቀብለን በሃላፊነት ገንብተን እናስረክቦታለን!
ሰላም እንዴት ናችሁ፡፡ ኤስቴቲክ ኢንቲሪየሮች ነን የቤት፣ የቢሮ፣ የሆቴልም ሆነ ማንኛውም የስራ ቦታዎችን የኢንቲሪየር ስራ ከዲዛይን ጀምሮ ፈርኒቸርን ጨምሮ እስከ ፊኒሺንግ ድረስ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት እንታወቃለን፡፡ እርሶስ በዚህ ዓመት ቤቶን፣ ቢሮዎን ወይስ የትኛውን የስራ ቦታዎን ለማሰራት አስበዋል? እንግዲያውስ ምርጫዎን ኤስቴቲክ ኢንቲሪየርን ያድርጉ፡፡ ያማረ ዲዛይን፣ ፈጣን ግንባታ፣ ጥንካሬና ውበት ያላቸው የቤትና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ጥራት ካለው ስራ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክቦታለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በ0916441444 ደውለው ያናግሩን
Crafting your dreams into reality!
አድራሻ:- ደንበል ሲቲ ሞል ሁለተኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን፡፡
ስልክ:- 0916441444
#WolitaSodo
13 የሚጠጉ ማደያዎች ባሉባት ዎላይታ ሶዶ ከተማ አሁን ላይ በሁሉም ማደያዎች የቤንዚን አቅርቦት እንደሌለ ተገልጿል።
የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ከሰሞኑ በዚሁ ጉዳይ ውይይት ማድረጉን ገልጿል።
በመድረኩ ምን ተባለ ?
በመድረኩ የተገኙት የወላይታ ዞን የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል ህገ ከሚፈቅደው ውጪ የሚሰሩ #የማዳያ_ባለቤቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።
በህገወጥ መንገድ ነዳጅ #ማታ ተቀድቶ እንዲያልቅ የሚተባበሩ አካላት ላይም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል።
የወላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኃይሌ ስላስ ከተፈቀደው አሠራር ውጪ በሚሰሩ ማደያዎች ላይ ጠንከር ያለ የህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
እንደ ሀገር #የነዳጅ_እጥረት መኖሩን የገለጹት ኃላፊው የመጣውን የነዳጅ ምርት በፍታሃዊነት መንገድ መሰራጨት ይገባል ብለዋል።
ከማዳያ ተቀጣሪ ሠራተኛ ውጪ ያሉ ህገ ወጥ #ደላላዎችን ከማደያ የማስወጣት ስራ መሰራት እንደሚገባም አሳስበዋል።
ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ይህን የተመለከተ ዘገባ ከቀናት በፊት አውጥቶ ነበር። በዘገባውም በከተማ አስተዳደሩ ያለው የገበያ አቅርቦት የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን ለከፍተኛ ምሬት መዳረጉን ይጠቅሳል።
አንድ ሊትር ቤንዚን በዎላይታ ሶዶ የሚሸጥበት ዋጋ 92 ብር ከ45 ሳንቲም እንዲሆን ታሪፍ ቢወጣለትም አሽከርካሪዎች በሊትር በ200 ብር ሂሳብ እንደሚገዙ ጠቁሟል።
ቤንዚን የሚቸረችሩ ቸርቻሪዎች አንድ ሊትር ቤንዚን ከ130 እስከ 150 ብር እንደሚረከቡ እና ይህንኑ ለተጠቃሚዎች የሚሸጡት ከ180 እስከ 200 ብር ባለው ዋጋ እንደሆነ መግለጻቸውን አስቀምጧል።
ቃላቸውን የሰጡ የነዳጅ ማደያ ሥራ አስኪያጆች ግን በወላይታ ሶዶ ከተማ ያለው የቤንዚን እጥረት ዋነኛው ምክንያት፤ ከተማይቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ እና የርዕሰ መስተዳድር መቀመጫ መሆኑዋን ተከትሎ የመጣው የቤንዚን ፍላጎት መጨመር እንደሆነ ይገልጻሉ ሲል ዘገባው ይጠቅሳል።
🧂 አሁን ላይ በከተማዋ አንድ ሊትር ቤንዚን እስከ 300 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።
@tikvahethmagazine
'' የነዳጅ ማደያዎች ቤንዚን በአግባቡ እየሰጡን አይደለም ፣ በህገ ወጥ እየገዛን ለመሥራት ተገደናል '' - አሽከርካሪዎች
'' በህገ ወጥ ተሳታፊዎች ላይ እርምጃ እንወስዳለን '' - ከተማ አስተዳደሩ
በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር ከባለሶስት እግር / ባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር በወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ ውይይት አድርጎ ነበር።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ካነሷቸው ጉዳዬች መካከል አንዱ የቤንዚን ህገ ወጥ ንግድን የተመለከተ ነው።
''ቤንዚን ጊዜውን ጠብቆ አይመጣም፤ ቢመጣም የነዳጅ ማደያዎች በፍትሃዊ መንገድ እያከፋፈሉን አይደለም፤ ተሰልፈን ውለን አለቀ ይሉናል፤ በጀሪካና በሃይላንድ እየቀዱ ለህገ ወጥ አካፋፋዬች እየሰጡ ሁለት ሊትር እስከ 350 ብር እየገዛን ለመሥራት ተገደናል፤ ማደያዎች መንግስት ካስቀመጠው የመሸጫ ታሪፍ በላይ በራሳቸው ዋጋ እየጨመሩ ተቸግረናል፤ መብራት ሳይኖር የጀኔሬተር ጭምር ክፈሉ እየተባልን ነው '' ሲሉ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
አሽከርካሪዎች ሥራ ሠርተን ለመኖርና የሚጠብቅብንን ግብር ለመክፈል መንግስት ችግሩን ሊያስተካክልና ህገ ወጥ ድርጊቱን ሊያስቆምልን ይገባል ሲሉም ጠይቀዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት የሸማች ክትትል ባለሙያ አቶ ማንደርሶ ገበየሁ ከቤንዚን ጋር ተያይዞ የተነሳው ችግር መኖሩን አምነው ችግሩ እንዲፈታ እየሠራን ነው ብለዋል።
''ማደያዎች በህገ ወጥ መልኩ በጀሪካ ሲቀዱ እየያዝን እንዲያስተካክሉ #መክረናል፤ እርምጃ የተወሰደባቸውም አሉ። በተደጋጋሚ ውይይት ብናደርግም መንግስት ያወጣው ታሪፍ አያዋጣንም በሚል የራሳቸውን ዋጋ አውጥተው የሚሸጡ አሉ'' ሲሉ ባለሙያው ገልጸዋል።
የባጃጅ አሽከርካሪዎችም የቀዱትን ቤንዚን እየሸጡ በድጋሚ ዙረው በመቅዳት ህገ ወጥ ሥራ የሚሰሩ በመኖራቸው #ሊስተካከሉ_እንደሚገባ አቶ ማንደርሶ አሳስበዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ተወካይ ከንቲባ አቶ ማማሩ ሽመልስ ህግን አክብረው በማይሠሩ የነዳጅ ማደያዎችና አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ለማስተካከል #እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል ሲል የፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
በርካታ ከተሞች አሁን ላይ በተመሳሳይ መልኩ የቤንዚን አቅርቦትና የገቢያ ችግር ቢኖርም ከየአካባቢው ኃላፊዎች የሚሰጠው ምላሽ ተመሳሳይ እና የተደጋገመ መሆን "ችግሩ ምኑ ጋር ነው ? " ያሰኛል!
አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞች የቤንዚን ዋጋ ከ150 -350 ድረስ ከማደያ ውጪ እየተሸጠ ይገኛል። በአብዛኞቹ ማደያዎች ቤንዚን ማግኘት የህልም እንጀራ ሆኗል።
የቤንዚን አቅርቦት ችግር ያለባቸውን ከተሞች በአስተያየት መስጫው ይጻፉልን
@tikvahethmagazine
#DireDawa
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ3 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ መኪኖችን በትራንስፖርት ዘርፍ ለማሰማራት የሚያስችል ስምምነት ከተማ አስተዳደሩ ከስዊፍት ቴክኖሎጂ እና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር ተፈራርሟል።
የስዊፍት ቴክኖሎጂ ተወካይ አቶ ብሩክ አሸብር በሚቀጥሉት ሶስት አመታት የባጃጅ ተሽከርካሪዎችን በኤሌትሪክ መኪኖች ለመተካት መታቀዱን ገልጸዋል።
በዛሬው ዕለትም 21 የኤሌትሪክ መኪኖች መመረቃቸውን የገለጹት አቶ ብሩክ፥ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እነዚህን ዘመናዊ የኤሌትሪክ የትራንስፖርት መኪኖች በፍጥነት ስራ ለማስጀመር የብድር ምችችት እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።
ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪኖቹ ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት የሀይል አቅርቦት ችግር እንዳይከሰት በተለያዩ ቦታዎች ቻርች ማድረጊያ ጣቢያዎች እንደሚዘጋጁም ተገልጿል።
@tikvahethmagazine
የሰውነት አካል ልገሳ ጉዳይ በኢትዮጵያ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ʺሰዎች ኩላሊታችንን ግዙን እያሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እንደሚመጡ ተገለጸʺ በሚል የሚሰራጨው ዜና ሀሰት እና ኮሌጃችንን የማይመለክት ነው ብሏል፡፡
ኮሌጁ ʺሰዎች ኩላሊት ግዙን ብለው ወደ ማእከሉ ይመጣሉʺ የሚለው አባባል ፍጹም ከእውነት የራቀ መሆኑ መታወቅ አለበት ሲል አሳውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ህግ የሰውነት ክፍልን በፈቃደኝነት ስለመለገስ ምን ይላል?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠበቃ እና የህግ አማካሪ የሆኑትን አቶ ዳንኤል ፈቃዱን አነጋግሯል።
ጥያቄ:-የሰውነት ክፍልን በፈቃደኝነት ስለመለገስ የኢትዮጵያ ህግ ምን ይላል?
አቶ ዳንኤል:- "የኢትዮጵያ ህግ እንደሚደነግገው እና የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያም እንደሚያመላክተው የሰውነት አካልን በፈቃደኝነት መለገስ በዘመዳሞች መካከል ብቻ ይፈቀዳል" ብለዋል።
ነገር ግን በህጉ መሰረት በዘመዳሞች መካከል የሚደረግን የሰውነት አካል ልገሳ ምንም አይነት የገንዘብ ውል እንዳይኖረው ክልከላ የሚያስቀምጥ ሲሆን ገንዘብን እንደ ውል በማስቀመጥ የሚደረግ ልገሳን ህገ ወጥ መሆኑን ተናግረዋል ።
ጥያቄ:- የሰውነት አካልን በፈቃደኝነት ለመለገስ መሟላት ያለባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው።
አቶ ዳንኤል:- ህጉ አስገዳጅ ነገሮች ብሎ ካስቀመጣቸው በዘመዳሞች መካከል ብቻ ፣ያለ ምንም ክፍያ እና በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት ገልጸው ከሦስቱ አንዱ ከጎደለ ልገሳው ተቀባይነት እንደማይኖረው ተናግረዋል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የምግብ፣ መድኃኒት እና የጤና እንክብካቤ አስተዳደር እና ቁጥጥር ደንብ 299/2006 እንደሚያስቀምጠው የሰውነት አካልን በፈቃደኝነት ዝምድና ለሌለው አካል ለመለገስ በመሀከል ምንም አይነት የጥቅም ግንኙነት አለመኖሩን መረጋገጥ እንዳለበት እንደሚያስቀምጥ ተናግረዋል ።
ይህንን የሚያረጋግጥ ራሱን የቻለ ተቋም መኖሩን ጠቁመዋል ።
ጥያቄ :- ከላይ ከተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ውጪ የሰውነት ክፍሉን በሽያጭ ያቀረበን አካል ህጉ ምን አይነት ቅጣት ያስቀምጣል?
አቶ ዳንኤል:- ህጉ በሦስት መንገድ የሚያየው መሆኑን ተናግረዋል።
- አስተዳደራዊ እርምጃ
-የወንጀል ተጠያቂነት
-የፍትሃብሔር ተጠያቂነት
በ 1997 በወጣው በኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 573 ላይ እንደተቀመጠው በህጉ ከተቀመጠው ውጪ ይህንን ድርጊት የፈጸመ ከሆነ:-
በተቋሙ ላይ አስተዳደራዊ ቅጣት እንደሚጣል የሚያስቀምጥ ሲሆን ይህም ፈቃድን መንጠቅ ሊሆን ይችላል።
ለጋሹ በህይወት ያለ ከሆነ ከ 3-5 ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት እና የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ይላል።
ወሳጁ ሐኪም የአካል ክፍሉን ከሞተ አካል የወሰደ ከሆነ ከ 5 ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ ያስቀምጣል ።
ወሳጁ ሐኪም የአካል ክፍሉን በህይወት ካለ ሰው በህጉ ከተቀመጠው ውጪ ከወሰደ ከ 5-10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ አስቀምጧል።
በማጭበርበር ፣በማስገደድ ወይም በማታለል ጉዳዩ የሚመለከተው ሰው ሳይፈቅድ አካል ክፍል የወሰደ ከሆነ ከ 10-25 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንደሚቀጣ አስረድተዋል።
የፍትሀብሔር ተጠያቂነትን በሚመለከት የሰውነት አካል ልገሳ ያደረገ ሰው ልገሳውን በማከናወኑ የደረሰበት ጉዳት ካለ ለፍርድ ቤት በሚያቀርበው ክስ መሰረት ጉዳቱ በሚመለከተው አካል ተረጋግጦ የሚገባውን ካሳ የሚያገኝበት አሰራር መሆኑን የህግ ባለሞያው ተናግረዋል።
#ምስል: ከዚህ ዜና ጋር የተያያዘው ምስል በሰው ሰራሽ አስተውሎት (Generative AI) አማካኝነት የተሰራ ነው።
@tikvahethmagazine
ባሳለፍነው ሩብ ዓመት በአዲስ አበባ 107 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል ተብሏል።
ሁሉም የደንብ ጥሰቶች የትራፊክ አደጋን የሚያስከትሉ ቢሆኑም ዋና ዋና በሚባሉ የትራፊክ አደጋ መንስኤዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየተሰራ መሆኑን በአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ የትራፊክ ሞያ እና ህዝብ ግንዛቤ ዲቪዥን ሃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ሃላፊው በ2017 ሩብ ዓመት 612 ሺ 445 ግለሰቦች በትራፊክ ደንብ ጥሰት ምክንያት ለቅጣት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ ውስጥ:-
° መንጃ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲያሽከረክሩ የተገኙ 306
° ሐሰተኛ መንጃ ፈቃድ ይዘው ሲያሽከረክሩ የተገኙ 213
° ቀይ የትራፊክ መብራት የጣሱ 45 ሺ
° የደህንነት ቀበቶ ሳያስሩ ያሽከረከሩ 24 ሺ
° የእጅ ስልክ እያዋሩ ሲያሽከረክሩ የተገኙ 28 ሺ
° አመታዊ የቴክኒክ ምርመራ ሳያከናውኑ ሲያሽከረክሩ የተገኙ 6,671
° ከፍጥነት ወሰን በላይ ሲያሽከረከሩ የተገኙ 7,316 ሰዎች ይገኙበታል።
ጠጥቶ ማሽከርከርን በሚመለከት ለ28 ሺ አሽከርካሪዎች ምርመራ ተደርጎ 871 ዱ በህግ ከተቀመጠው በላይ ጠጥተው የተገኙ በመሆናቸው ምክንያት እንዲቀጡ መደረጋቸውን ተናግረዋል።
በሩብ አመቱ 107 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በ 2016 ሩብ ዓመት ተመሳሳይ ወቅት 106 ሰዎች ህይወታቸው አልፎ ነበር።
ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር 379 ሲሆን በ 2016 ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 385 ሰዎች ጋር ሲነጻጸር መቀነስ ታይቶበታል።
በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት በአንጻሩ ከፍተኛ ጭማሪን ያሳየ ሲሆን በሩብ ዓመቱ 8,953 ንብረቶች ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን ባሳለፍነው ሩብ ዓመት ካጋጠመው 8,253 የንብረት ጉዳት ጋር ሲነጻጸር በ 700 ብልጫ ያለው ነው።
በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት በገንዘብ አልተተመነም።
የተሽከርካሪ መለያ፣ መመርመሪያ እና መመዝገቢያ አዋጅ 681/2002 መሰረት ማንኛውም ተሽከርካሪ በዓመት አንድ ጊዜ የተሽከርካሪ የምርመራ ሂደትን አልፎ በመንገድ ላይ መንቀሳቀስ እንዳለበት ቢደነግግም በሩብ ዓመቱ ከ 6 ሺ በላይ ተሽከርካሪዎች ይህንን ሳይፈጽሙ በመንገድ ላይ መገኘታቸውን ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።
@tikvahethmagazine
መምህራንን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ላይ ያላቸውን እውቀት እንዲያሳድጉ የቀረበው ስልጠና
የሰውሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ውጤቶችን በማበልጸግ የሚታወቀው OpenAI ከኮመን ሴንስ ሚዲያ ጋር በመሆን መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ጄኔሬቲቭ AI እና ChatGPT ላይ መሰረታዊ እና ሥነ-ምግባራዊ እንድምታዎችን የሚማሩበት ሞጁል አዘጋጅቷል።
ይህ ስልጠናም መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የትምህርት ዕቅዶችን እና ለተማሪዎች ተጨማሪ አጋዥ ትምህርቶችን እንዲሰጡ የሚያስችላቸዋል ሲል ነው የገለጸው።
በዚህም ከኬጂ እስከ -12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ መምህራን የኩባንያውን AI chatbot በመጠቀም እንዴት በክፍል ውስጥ መጠቀም እንደሚችሉ የሚያግዙ የኦንላይን የትምህርቶች ተዘጋጅተውላቸዋል።
AI በቅድመ መደበኛ እንዲሁም በመደበኛ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተግባራዊ የሚድረጉ ሂደት ገና በጅምር ላይ ያለ ቢመስልም OpenAI ጨምሮ ሌሎች ኩባንያዎች እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው።
ምንም እንኳን መምህራን አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን መጠቀማቸው እየጨመረ ቢሆንም በአብዛኛዎቹ አስተማሪዎች ዘንድ ቴክኖሎጂውን በመማሪያ ክፍል ውስጥ እንዲተገበር መታሰቡን አልወደዱትም።
ኮመን ሴንስ ሚዲያ በቅርብ ጊዜ በታዳጊ ወጣቶች ላን በሰራው አንድ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው 70 በመቶዎቹ የቤት ሥራቸውን ለማገዝ ወይም አሰልቺ የሚሏቸውን ሂደቶች ላለመከተል Generative AI ይጠቀማሉ። ነገር ግን ከዚህ ውስጥ አንድ ሶስተኛው ብቻ ናቸው ይህን ቴክኖሎጂ እየተጠቀሙ መሆናቸውን ለወላጆቻቸው ያሳወቁት።
@TikvahethMagazine
እንኳን ወደ ደህንነቱ የተጠበቀ ልዩ የጥርስ ህክምና በደህና መጡ! 🎊🎊🎉🎉
በሴፍ ስፔሻሊቲ የጥርስ ክሊኒክ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
1. Scaling (ጥርስ እጥበት)
2. Bleaching(ጥርስ ማንጣት)
3. Brace(ብሬስ)
4. Tooth Extraction (ጥርስ መንቀል)
5. Filling(ሙሌት)
6. Diastema closure(ፍንጭት መዝጋት)
7. Root canal treatment(የጥርስ ስር ህክምና)
8. ጥርስ መትከል ( ኢምፕላንት፣ ዚርኮኒያ ጥርስ፣ ሴራሚክ ጥርስ፣ ክሮሞኮባልት፣ አክሪሊክ )
ክሊኒካችን በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉ ታካሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያለውን የጥርስ ህክምና እና እንክብካቤ ይሰጣል።
📣ልብ ይበሉ!
ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እስከ 40% በሚደርስ ቅናሽ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነን ይጎብኙን።
🫵የዋጋ ዝርዝር ለማየት ቴሌግራም እና ቲክቶክ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ለተጨማሪ መረጃ
📞0907341414
📞0924143495
Telegram: /channel/Safedentalcare
Tiktok: safe.dental.care" rel="nofollow">https://tiktok.com/@safe.dental.care
#Update: በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙ 270 ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ ተሰጠ
የናይጄሪያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአሁኑ ጊዜ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ያሉ ከ270 ያላነሱ ናይጄሪያውያን ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ትእዛዝ አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ ይህንን ትእዛዝ እንዲስፈፅሙ ትእዛዝ የሰጠው ለአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የናይጄሪያ ዲያስፖራ ኮሚሽን እንደሆነ የናይጄሪያ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል።
ፍርድ ቤቱ ትእዛዙን ያስተላለፈው ኢትዮጵያ ለእስረኞቹ የሚሆን ምግብ፣ መድኃኒት እና ሌሎች ግብአቶችን ለመሸፈን የሚያስችል በጀት እንደሌላት በመግለጿ መሆኑ ተነግሯል።
የናይጄሪያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከዚህ ቀደም በአደገኛ እፅ ዝውውርና ሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ ናይጀሪያዊያን በቃሊቲ እስር ቤት እንደሚገኙ ገልጾ ነበር።
ከ250 በላይ ናይጀሪያዊያን እስረኞች ኢትዮጵያ ውስጥ አግባብ ባለሆነ መንገድ መያዛቸውን የሀገሪቱ የመብት ተከራካሪዎች ገልፀው የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ያሉ ናይጄራዊያን እስረኞችን ሁኔታ የሚያጣራ ኮሚቴ መዋቀሩም አይዘነጋም።
👋 @TikvahethMagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
#Hawassa
በሲዳማ ክልል ያለውን የነዳጅ ግብይት ሁኔታ ገምግሞ መፍትሔ ለመስጠት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የሚመለከታቸው የቢሮ ሃላፊዎችን በማወያየት አቅጣጫ አስቀምጠዋል ተብሏል።
በክልሉ በተለይ በሀዋሳ ከተማ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የነዳጅ እጥረት መከሠቱን በመግለጽም ችግሩ የአቅርቦትና የግብይት ስርዓቱ ላይ መሆኑ ተነስቷል።
የአቅርቦት እጥረት ለመቅረፍ አቅራቢ ድርጅት ጋር እንደሚሰራ እና የግብይት ችግሩን ለመፍታት ደግሞ ጠንካራ ግብረሀይል ተቋቁሞ ወደ ስራ እንዲገባ ርዕሰ መስተዳድሩ አቅጣጫ አስቀምጠው ግብረሀይሉ ወደ ስራ ገብቷል ተብሏል።
በትላንትናው ዕለት በከተማው ሁሉም ማደያ የቤንዚን ስርጭት እንዳልነበር የቲክቫህ ቤተሰቦች ጥቆማ ሰጥተው ነበር።
@tikvahethmagazine
ሦስት አዳዲስ ክትባቶች በያዝነው ዓመት መጨረሻ እንደሚሰጡ ተገለጸ።
በትላንትናው ዕለት በሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች የማህጸን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት በዘመቻ መልክ መሰጠት ተጀምሯል።
ለ 5 ቀናት የሚቆየው የክትባት ዘመቻው ከ 9-14 አመት የእድሜ ክልል ላይ ለሚገኙ ልጃገረዶች የሚሰጥ ሲሆን በዘመቻው 7.5 ሚሊየን ልጃገረዶችን ለመከተብ በእቅድ ተይዟል።
ተጨማሪ የዝግጅት ጊዜ በመፈለጋቸው በአዲስ አበባ እና በሶማሊ ክልል የክትባት ዘመቻው ያልተጀመረ ሲሆን ከ5 ቀናት በኋላ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የማህጸን ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት በኢትዮጵያ መስጠት የተጀመረው ከስድስት ዓመት በፊት ቢሆንም በነበረው የክትባት እጥረት ምክንያት 14 ዓመት ለሆናቸው ልጃገረዶች ብቻ ክትባቱ ሲሰጥ ቆይቷል።
በአሁኑ ዘመቻ በቂ ክምችት በመኖሩ ክትባቱ ሊሰጣቸው የሚገባቸውን ከ 9 -14 አመት የእድሜ ክልል ያሉ ልጃገረዶችን የሚያካትት ይሆናል ተብሏል።
"በአሁኑ ዘመቻ አንድ ጊዜ በዘመቻ መልክ ተሰጥቶ ከዚህ በኋላ ግን እድሜያቸው 9 ዓመት ሲደርስ እንደማንኛውም ክትባት መጥተው የሚከተቡበትን መንገድ ለማመቻቸት እንዲቻል የክትባት ዘመቻው ተጀምሯል" ሲሉ በጤና ሚኒስቴር የክትባት አገልግሎት ዴስክ ሃላፊ አቶ መልካሙ አያሌው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ በማህጸን ጫፍ ካንሰር በየአመቱ ከ 8ሺ በላይ ሴቶች ሲያዙ ከ 5 ሺ በላይ ሴቶች ደግሞ ለሞት እንደሚዳረጉ ተናግረዋል።
በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ኮቪድን ጨምሮ 13 ክትባቶች በመደበኛው የክትባት መርሃ ግብር እየተሰጡ የሚገኙ ሲሆን በ 2017 መጨረሻ ላይ ሦስት ተጨማሪ አዳዲስ ክትባቶችን በመጨመር ቁጥሩን ወደ 16 ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል።
የሚጀመሩት አዳዲስ ክትባቶች
°ለህጻናት የሚሰጥ የወባ መከላከያ ክትባት
°ህጻናት እንደተወለዱ በ 24 ሰዓት ውስጥ የሚወስዱት የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት እና
° የቢጫ ወባ መከላከያ ክትባት ናቸው።
@tikvahethmagazine
#Ethio_Istanbul
የዲቦራ ፋውንዴሽን መሥራች አቶ አባዱላ ገመዳ የሆስፒታላችንን የኢትዮ ኢስታንቡል አጠቃላይ ሆስፒታል የሥራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።
ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል፤ ሥራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ለ 32 ሕፃናት የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና በነፃ ማከናወኑን እንዲሁም በተጨማሪም 4 ሺ ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ የቀዶ ጥገና ሕክምና ማከናወኑን በዋና ሥራ አስፈፃሚያችን አቶ ብርሃን ተድላ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ሆስፒታላችን በቴክኖሎጂ በታገዙ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችና ከፍተኛ ልምድ ባካበቱ ከ73 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ስፔሻሊስትና ሰብ-ስፔሻሊስት ባለሙያዎች በመታገዝ ዜጎቻችንን ለህክምና ወደ ውጭ አገር በመሄድ የሚያወጡትን ከፍተኛ ወጪና እንግልት ለማስቀረት እና ውጭ አገር የሚያስኬዱ ሕክምናዎችን በሀገር ውስጥ ለመስጠት አላማው አድርጎ የተመሰረተ ነው።
አቶ አባዱላ ገመዳ ሆስፒታሉ ንፁህ፣ በሚገባ የተደራጀና በውጭ ሀገር በምንኼድበት ጊዜ የምናየው ዓይነት መሆኑን በመግለፅ ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልፀዋል።
አቶ ብርሃን ተድላ የዲቦራ ፋውንዴሽንን ለማገዝ በውጭ ሀገር ከፍተኛ ሕክምና ከሚያስፈልጋቸው መካከል ለሁለት ሰዎች ሙሉ ወጪ በመሸፈን ሕክምና ለመስጠት ቃል ገብተዋል። በተጨማሪም ወደፊት በምናደርገው ትብብር አቅም በፈቀደ ሁሉ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።
(ኢትዮ-ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል)
የ11 ዓመት ህፃንን አሰገድዶ የደፈረ ግለሰብ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ
በሰላምበር ከተማ አስተዳዳር ዳንባዬ ቀበሌ የ11 ዓመት ህፃንን አሰገድዶ የደፈረ ግለሰብ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የሰላምበር ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
አቶ ካስትሮ ካባሎ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይ የሆነችውን ህፃን ሐሴት አዲማሱን በቀን 06/10/2016 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 3:30 አካባቢ በግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት ጉሮሮዋን አንቆ በመያዝ በማስገድድ የግብረ ሥጋ ድፈረት ወንጀል መፈፀሙ ተገልጿል።
በዚህም ግለሰቡ የኢፌዴሪ የወንጀለኛ መቅጫ አንቀፅ 627 ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ጥፋተኛ መባሉን የጋሞ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ተከሳሹ ጥፋተኛ የተባለው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 627/1/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ሲሆን ወንጀሉ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 21/2006 መሰረት ደረጃ 1 እርከን 31 ነዉ።
ይህም የወንጀል እርከን ከ15 ዓመት እስከ 18 ዓመት ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ መሆኑን ህጉ የሚደነግግ ሲሆን ወንጀለኛው ከዚህ በፊት ምንም የወንጀል ሪከርድ የሌለው መሆኑ በማቅለያነት ተይዟል ተብሏል።
@tikvahethmagazine
እንኳን ወደ ደህንነቱ የተጠበቀ ልዩ የጥርስ ህክምና በደህና መጡ! 🎊🎊🎉🎉
በሴፍ ስፔሻሊቲ የጥርስ ክሊኒክ የእርስዎ ጤናማ ፈገግታ ቅድሚያ የምንሰጠው ጉዳይ ነው!
እኛ ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ውስጥ አጠቃላይ የጥርስ ህክምና አገልግሎቶችን እናቀርባለን።
ክሊኒካችን በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉ ታካሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያለውን የጥርስ ህክምና እና እንክብካቤ ይሰጣል።
📣ልብ ይበሉ!
በስፔሻሊስት ሀኪሞች እና በላቀ ቴክኖሎጂ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እስከ 40% በሚደርስ ቅናሽ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነን ይጎብኙን።
ለተጨማሪ መረጃ
0907341414
0924143495
Telegram: /channel/Safedentalcare
Tiktok: safe.dental.care" rel="nofollow">https://tiktok.com/@safe.dental.care
#Hawassa
በሀዋሳ ከተማ የተጀመረዉ ተሽከሪካዎችን በአይነትና በታርጋ ለይቶ በተወሰኑ ማደያዎች የመደለደሉ ስራ መፍትሔ ከመሆን ይልቅ ለጥቁር ገበያ ወይንም ለሕገወጥ ግብይት ዳርጎናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ተናግረዋል።
የሞተር ሳይክል እና የሚንባስ ታክሲ አሽከሪካሪ ቅሬታ አቅራቢዎች የተሽከርካሪ ምደባ ሥርዓቱ ችግር ፈቺ አለመሆኑን አስረድተዋል።
"ከማለዳ ጀምሮ ተሰልፈን ዉለን በተለያዩ ምክንቶች ሳንቀዳ የምንመለስበት አጋጣሚ ስላለ ተሰልፎ ከመዋል ይልቅ አዝማሚያዎችን አይተን በየመንገድ ዳሩ በዉሃ ሃይላዶች በ70እና 80ብር ልዩነት ለመግዛት እንገደዳለን" ሲሉ ነው የገለጹት።
አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎችና በየዕለቱ ከንግድና ገበያ ልማት መስሪ ቤቶች የሚመደቡ ባለመያዎች ጭምር የዚሁ ችግር ተባባሪዎች ናቸዉ ሲሉ አሽከሪካሪዎቹ ይናገራሉ።
በተጨማሪም ተራ ጠብቀዉ ከሚሰለፉት ባልተናነሰ በሰበብ አስባቡ ያለተራቸዉ እየገቡ የሚቀዱ ተሽከሪካሪዎች በህወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ለሚሸጡ ቤንዚኖች አቀባዮች ናቸዉ ብለዉ እንደሚያምኑም ተናግረዋል።
ስምንትና ሰባት ሊትር ለመቅዳት ብዙ ጊዜ ተሰልፈን እናድራለን የሚሉት የባጃጅ አሽከሪካሪዎች ይህ በመሸሽና ስራ ፈቶ ከመዋል አብዛኛው የባጃጅና ኪዩት አሽከርካሪ ከጥቁር ገበያ ከመደበኛው እጥፍ በሚባል ዋጋ በመገዛት በታሪፍ ላይ ያልተገባ ጭማሪ ለማድረግ እንደሚገደዱ ተናግረዋል።
በመንግስት ሞተር ሣይክልና መኪኖች ጭምር ለጥቁር ገበያዉ አሳላፊ ሆነዉ የሚሰሩ አካላት እንዳሉ በግልፅ እናያለን የሚሉት አሽከርካሪዎቹ በየማደያዉ አከባቢ የሚስተዋሉ መረባበሾችን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም ሄደዉ የሚቀዱባቸዉን ቦታዎች ጭምር እንደሚጠቁሙ ገልፀዋል።
በከተማዋ ረጃጅም የቤንዝን ሰልፎች እንዲስተዋሉና የጥቁር ገበያዉ እንዲስፋፋ #የአቅርቦት_እጥረት ዋነኛ ምክንያት ነዉ ሲል የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ይገልጻል።
አክሎም ለመፍትሔ ተብለው በየጊዜዉ የሚወሰዱ እርምጃዎች እየተለመዱ ሲመጡ ሌላ ችግር ይዘዉ መምጣታቸዉን በማጠን በየጊዜው አዳዲስ እርምጃዎች እየተወሰዱ ነዉ ሲል ገልጿል።
የምደባ ስርዓቱ በየማደያዉ የቀረበዉን ቤንዚን በአግባቡ ለመጠቀም እንጂ ለጥቁር ገበያው ምክንያት ሆኗል የሚል ቅሬታ ግን እስካሁን ቀርቦላቸዉ እንደማያውቅ መምሪያው ገልጿል።
በቀጣይ በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ በማሰባሰብ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት እንደሚጥርም አስታውቋል።
📌 ይህ ዘገባ ከመጠናቀሩ ሁለት ቀናት አስቀድሞ ህዳር የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት መመሪያ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተመስገን ችሎት ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።
#TikvahEthiopiaFamilyHW
@tikvahethmagazine
በታማኝነት ተቀብለን በሃላፊነት ገንብተን እናስረክቦታለን!
ሰላም እንዴት ናችሁ፡፡ ኤስቴቲክ ኢንቲሪየሮች ነን የቤት፣ የቢሮ፣ የሆቴልም ሆነ ማንኛውም የስራ ቦታዎችን የኢንቲሪየር ስራ ከዲዛይን ጀምሮ ፈርኒቸርን ጨምሮ እስከ ፊኒሺንግ ድረስ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት እንታወቃለን፡፡ እርሶስ በዚህ ዓመት ቤቶን፣ ቢሮዎን ወይስ የትኛውን የስራ ቦታዎን ለማሰራት አስበዋል? እንግዲያውስ ምርጫዎን ኤስቴቲክ ኢንቲሪየርን ያድርጉ፡፡ ያማረ ዲዛይን፣ ፈጣን ግንባታ፣ ጥንካሬና ውበት ያላቸው የቤትና የቢሮ ፈርኒቸሮች፣ ጥራት ካለው ስራ ጋር በተመጣጣኝ ዋጋ ሰርተን እናስረክቦታለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በ0916441444 ደውለው ያናግሩን
Crafting your dreams into reality!
አድራሻ:- ደንበል ሲቲ ሞል ሁለተኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን፡፡
ስልክ:- 0916441444
" በዓለም አቀፍ ደረጃ ከስኳር በሽታ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ከ800 ሚሊዮን በልጠዋል " - ጥናት
° " አገራት ጤናማ አመጋገብን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን ማውጣት አለባቸው " ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
ከ1990 ጀምሮ የስኳር ታማሚዎች ቁጥር በአራት እጥፍ በመጨመር በአለም ከ800 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በስኳር በሽታ መያዛቸውን የአለም ጤና ድርጅት ያወጣው አዲስ ጥናት አመለከተ።
ጥናቱ ይፋ የተደረገው የዓለም የስኳር በሽታ ቀን በትላንትናው እለት በተከበረ ቀን ነው።
ጥናቱ የተሰራው የአለም ጤና ድርጅት ከ NCD Risk Factor Collaboration (NCD-RisC) ጋር በመተባበር ሲሆን ከ1,500 ተመራማሪዎች እና ባለሙያዎችን አሳትፏል።
ከ18 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ 140 ሚሊዮን ሰዎችን መረጃ በመተንተን የተሰራው ይህ ጥናት የስኳር በሽታ የስርጭት መጠን እና የህክምና ሽፋን ላይ ትኩረቱን በማድረግ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።
በዚህም በ1990 እና 2022 መካከል ባለው ጊዜ የስኳር ህመም ከ7 ወደ 14 በመቶ መጨመሩን ያመለከተው ጥናቱ የስኳር ህመም መጠኑ እየጨመረ፤ የህክምና ተደራሽነቱም ዝቅተኛ እየሆነ መምጣቱን አሳይቷል።
አፍሪካ ደቡብ-ምስራቅ እስያ እና ምስራቅ ሜዲትራኒያን ዝቅተኛው የስኳር በሽታ ህክምና ሽፋን ያላቸው አህጉራት እንደሆኑ ተመላክቷል።
በ2022፣ ዕድሜያቸው 30 እና ከዚያ በላይ የሆኑ 450 ሚሊዮን የሚጠጉ አዋቂ የስኳር ህመምተኞች ውስጥ 59 በመቶው የስኳር በሽታ ህክምና እንደማያገኙ ጥናቱ አመላክቷል።
ይህ ቁጥር በ1990 ከነበሩት በስኳር ተይዘው የማይታከሙ ታማሚዎች ጋር ሲተያይ በ3.5 ጭማሪ ያሳየ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ከስኳር በሽታ ተማሚዎች ውስጥ ዘጠና በመቶው ያልታከሙ አዋቂዎች የሚገኙት ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ነው ተብሏል።
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም " ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ውስጥ የስኳር በሽታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አይተናል " ብለዋል።
በሽታው የተስፋፋው ከመጠን ባለፈ ውፍረት፣ ጤናማ ባልሆነ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባለማድረግ እንደሆነ ሲገልፁ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ደግሞ የበሽታውን ሁኔታ እንዳባባሱት ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።
ዶ/ር ቴዎድሮስ " ዓለም አቀፉን የስኳር በሽታ ለመቆጣጠር አገራት አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ አለባቸው " ሲሉም አሳስበዋል።
አክለውም አገራት ጤናማ አመጋገብን እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን የሚደግፉ ፖሊሲዎችን በማውጣት እና በሽታን በመከላከል እና በመቆጣጠር የበቃ የጤና ስርዓት መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
@tikvahethmagazine
ቢጂአይ ኢትዮጵያ በባቱ ከተማ ያስገነባውን ትምህርት ቤት አስመርቆ ለማህብረሰቡ አስረከበ
ቢጂአይ ኢትዮጵያ በባቱ ከተማ ያስገነባውን አባ ገዳ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የምረቃ ስነ-ስርዓት በዛሬው እለት አስመርቋል።
ትምህርት ቤቱ ተገንብቶ ያለቀው በ 6ወራት ጊዜ ውስጥ ሲሆን ተማሪዎች በአዲሱ የትምህርት ዘመን ትምህርት መጀመራቸው ተነግሯል።
600 ህፃናት ተማሪዎችን በፈረቃ ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው ይህ ትምህርት ቤት 9 ሚሊዮን ብር እንደወጣበት የቢጂአይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሄርቬ ሚልሃድ ተናግረዋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ የተገኙት የከተማው እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ባለድርሻ አካላት ትምህርት ቤቱ እንደ አጥር ያሉ አስፈላጊ ግብዓቶች እንዲሟሉለት ጠይቀዋል።
ቢጂአይ በማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ በሰራው ስራ በዘንድሮው አመት ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ በትምህርት፣ ጤና፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ላይ ማውጣቱን የ
ዋና ስራ አስፈፃሚው ጠቅሰዋል።
ኩባንያው ዛሬ በባቱ ከተማ ያስመረቀውን ፕሮጀከት ጨምሮ በሐዋሳ፤ በጕራጌ ዞን ዘቢዳር እና በኮምቦልቻ ባሉ ከተሞች የትምህርት መሰረተ ልማትን በመገባት ለነዋሪዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።
በዘቢዳርና በኮምቦልቻ ያሉ ት/ቤት ግንባታዎች በቅርቡ ለማህበረሰቡ እንደሚያስረክብም ኩባንያው አሳውቋል።
@tikvahethmagazine
ሮያል ሆምስ ሪል እስቴት
በሴራሚክ አቅርቦት የሚታወቀው አንጋፋው ሮያል ሴራሚክስ ሮያል ሆምስ ሪል አስቴትን ይዞሎት ቀርቧል ።
በመካኒሳ ጀርመን አደባባይ ግንባታ ደረጃቸው 70% የደረሱ አፓርትመንቶች በጥራት ገንብቶ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በካሬ 70,000 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ ይሎታል!
ኮምፓዉንዳችን ያካተተው ጂም፣ስፓ፣ ሱፐርማርኬት፣የህፃናት ማቆያ፣አረንጓዴ ስፍራ፣የህፃናት መጫወቻ ስፍራ፣ሰገነት አና በቂ የሆነ የመኪና መቆምያ።
ለበለጠ መረጃ በ 0930627256 ወይም 0911005545 ይደውሉልን ።
"ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም" -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የቁጥጥር ስራው ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም በዘመቻ መልክ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ዘመቻ ሲባል ወደ ቫት ስርዓት ውስጥ ያልገቡትን ማስገባት ፣ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንዲያወጡ ማድረግ፣ ደረጃቸው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ የማይሰጡትን ደረሰኝ አስፈቅደው እና አሳትመው መጠቀም እንዲጀምሩ ማስቻልን ያካትታል።
የቁጥጥር ስራው በተለይም በገበያ ሞሎች ላይ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘም በዛሬው ዕለት በመርካቶ አካባቢ ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው የሚል የተለያዩ ውዥንብሮች መፈጠራቸው እና ይህም አንዳንድ ነጋዴዎችን ግርታ ውስጥ መክተቱ ተናግሯል።
ስለ ጉዳዩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽን አነጋግሯል።
ዳይሬክተሩ በምላሻቸው "ጠዋት ሱቆች ሁሉ ተዘግተዋል ተብሎ ተወርቶ በአካል ዞሬ አይቻለሁ የተወሰኑ ሱቆች የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተዘጉ የሚመስሉ አሉ ነገር ግን መደበኛ ሥራ ቀጥሏል" ብለዋል።
"በዚህ ደረጃ ተዘግቷል ለማለት እይቻልም ተዘጋ የሚባለው ምን ያህል ሱቅ ሲዘጋ ነው? አንድ ቤት ሁለት ቤት ተዘግቶ ይሆናል ነገር ግን አብዛኛው እየሰራ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ህገ ወጥነትን ማስቀጠል የሚፈልግ አካል አለ ያለት ዳይሬክተሩ " ሆን ብሎ የሆነ ነገር ተሰርቷል፣ ሊሰራ ነው የሚል ውዥንብር መፍጠር የሚፈልግ አካል እንዳለ ነው የተረዳሁት " ብለዋል።
"ቁጥጥር ሊደረግ ነው በተለይ አስመጪ እና አከፋፋይ ላይ ሲባል ቸርቻሪ ላይ ስጋት የሚፈጥሩ አሉ፣ በትላንትናው ዕለትም የሚሸሹ ነጋዴዎች ገጥመውናል ያለፍቃድ ይነግዱ የነበሩ ናቸው ብንጠየቅ መልስ የለንም በሚል ስጋት ነው። ሱቃቸውን ቢዘጉም እነሱ ናቸው የሚሆኑት" ሲሉ አክለዋል።
ተዘግቷል የሚለውንም እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል በእርግጥ የተዘጋ ነው ወይስ ነጋዴው በsocial ችግር ሱቃቸውን ዘግተው ስለሌሉ ነው የሚል ጥርጣሬ የሚያጭር ስለሆነ የተዘጉ አይደሉም ወደሚል ድምዳሜ ነው የደረስነው ብለዋል።
ይርጋ ሃይሌ የገበያ ሞል ላይ ከ 15 ቀን በፊት ኮንትሮባንድ ስለነበረ ጎምሩኮች በርብረዋል ደረሰኝ የሌለውን ወርሰዋል ደረሰኝ ያለውን ጥለው ወጥተዋል።
"የገበያ ሞሉ ላይ እቃዎችን መለየት አስቸጋሪ ስለነበር እና ሰዎቹም ተባባሪ ስላልነበሩ ለጊዜው ታሽጎ ነበር" ያሉ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ሀሉም መከፈታቸውን ጠቁመው የቀረ ካለ በንግድ ቢሮ በኩል ፈቃድ ያልነበረው በመሆኑ በተወሰደ እርምጃ መሆኑን ጠቁመዋል።
"ታሽገው የነበሩ አብዛኛው ሱቆች ተከፍተዋል እስካሁን ያልተከፈተ ካለ ፈቃድ ስላላወጣ ነው የሚሆነው በተረፈ እቃ የሚወረሰው ኮንትሮባንድ ሲሆን ብቻ ነው" ብለዋል።
በተጨማሪም ሁሉም ሰው ደረሰኝ ስለማይሰጥ የሚመለከተው ብቻ ነው ደረሰኝ እንዲሰጡ የሚጠበቀው መስጠት የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች ደረሰኝ እየሰጡ ግብይታቸውን ይቀጥሉ ብለዋል ።
"እቃችሁ እየተወረሰ ነው፣ ሊወረስብን ነው ፣የሚሉ አካላት እቃቸው ምን ስለሆነ ነው የሚወረሰው ? እንደዚህ የሚሉ አካላት ኮንትሮባንድ ስለሆነ ይመስላል።"
አክለውም "ያለደረሰኝ አትግዙ ፣የሚሸጥላችሁን ጠቀሙ እኛ ደግሞ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈጽምን አካል እንቆጣጠራለን ብለናል የምንከታተላቸውም ለዛ ነው።" ያሉ ሲሆን እቃ ለመውረስ የህግ መሰረት የሚያስፈልግ መሆኑን ተናግረው እቃ የሚወረሰው የታክስ እዳ ማካካሻነት ከተያዘ ብቻ ነው መሆኑን አስረድተዋል።
"ግብይት ላይ ያለ እቃን የታክስ ማካካሻ ብለን የምንወርስበት ምክንያት የለንም። ክፍተት ያለበትን ነጋዴ ለማወናበድ የሚሮጥ ሌላ ጥላ የሚፈልግ አካል የሚያወራው ወሬ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ዳይሬክተሩ " ያለደረሰኝ አትሽጡ አልን እንጂ እቃ እንወርሳለን ያለ አካል የለም" ብለው ይህም ለነጋዴዎች በደብዳቤ እንዲደርሳቸው መደረጉን ነግረውናል።
@tikvahethmagazine