ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
ፎቶ: ማስተርካርድ ፋውንዴሽን በዛሬው ዕለት አመታዊ የአጋር አካላት መማማሪያ ጉባኤውን አድርጓል።
#TikvahEthiopia
@TikvahethMagazine
መድኃኒት የተላመደ የወባ ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ተከስቷል?
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትላንትናው ዕለት ባካሄደው 7ኛ መደበኛ ስብሰባ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህ ወቅት ካነሱት ጉዳዮች አንዱ መመድኃኒት የተላመዱ የወባ ትንኞችን ይመለከታል። ዶ/ር መቅደስ ይህን አስመልክቶ በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ስር ባሉ ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም በዩኒቨርስቲዎችና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ጥናት እየተከናወነ ሆኑን አንስተዋል።
በዚህም "መድኃኒት መለማመድ የሚባለው ሙሉ ለሙሉ አለ አለ የምንልበት ደረጃ ላይ አይደለም።" ሲሉ አንስተዋል። ለዚህም አመላካች ያሉትን ጉዳይ ሲያነሱ፦
ከዚህ ቀደም ባሉ ዓመታተ ያለው የበሽታ ተጋላጭነት ቁጥር እንዲሁም ሆስፒታል ገብቶ የመተኛት ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ሆስፒታል ተኝቶ የመታከም ቁጥሩ ዝቅ ማለቱን አንስተዋል።
ይህም ዜጎች በበሽታው ተይዘው ወደ ሆስፒታል በሚሄዱበት ወቅት መድኃኒት ሲያገኙ የመሻል ነማገገም አዝማሚያው ከፍተኛ መሆኑን ነው የጠቀሱት።
ዶ/ር መቅደስ አክለውም፥ ጥናቶች ግን አሁንም መካሄዳቸውን እንደሚቀጥሉ ነው የገለጹት።
ከዚህ በተጨማሪም፥ በ2017 በጀት ዓመት በተሰራው የንቅናቄ ሥራ ጋር ተያይዞ 8 ሚሊዮን የሚሆን የመድኃኒት እንዲሁም 6 ሚሊዮን የሚሆኑ የፈጣን መመርመሪያ ኪቶች ሥርጭት መደረጉን ጠቁመዋል።
ከአጎበር ሥርጭት ጋር ተያይዞም ባለፉት ሁለት ዓመታት ከነበረው 19.7 ሚሊዮን የሚሆን የአጎበር ሥርጭት ተጨማሪ በዚህ በጀት ዓመት 2.2 ሚሊዮን የሚሆን አጎበር መሰራጨቱን ጠቅሰዋል።
ከ 2 ሚሊዮን በሚሆን ቤቶች ላይ ቀድሞ በተሰራ የቅኝት ሥራ የአጎበር የመጠቀም ልምዱ ከ50 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም ባለፉት ወራት በተሰራ ሥራ ይህን ወደ 70 በመቶ ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት።
ከህገወጥ የመድኃኒት ቁጥጥር ጋር ተያይዞም 450 ኩንታል መድኃኒት በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ በሚደረግበት ወቅት 9 ኩንታል የሚሆነው ከመንግሥት ቤት የወጣ መድኃኒት መሆኑን ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ 75 በመቶ የሚሆነው አከባቢ ለወባ ምቹ ነው የተባለ ሲሆን 70 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍልም በእነዚሁ አከባቢ የሚኖር ነው።
@TikvahethMagazine
ለፈገግታዎ ጥሩ እንክብካቤ ይገባዋል!
ከፍተኛ ሽልማት የሚያስገኘውን የ "The Earthshot Prize 2025" ኢትዮጵያውያን እንዲወዳደሩ ጥሪ ቀረበ
በእንግሊዝ ልዑል ዊሊያምና ሮያል ፋውንዴሽን በፈረንጆቹ 2020የተቋቋመውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከአካባቢና አየር ብክለት የፀዳ፣ ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ የሚያበረክትና ለተፈጥሮ ተስማሚ የሆነ ስራ የሚሰራ እየሰሩ ያሉ ተቋማትን፣ የቢዝነስ ፈጠራ ባለሙያዎችን ( ኢንተርፕረነሮችን) ወይም ግለሰቦችን የሚሸልመው "The Earthshot Prize 2025" የዘንድሮ እጩ ተወዳዳሪዎችን መቀበል ጀምሯል።
በአፍሪካ የውድድሩ ዋና አጋር መልቲቾይስ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እንዲወዳደሩ ጥሪ አቅርቧል። በአምስት የተለያዩ ምድቦች የሚካሄደውን ይህንን ዓመታዊ ሽልማት በተለይ ለአካባቢ ስምሙ የሆኑና ተፈጥሮን የማይበክሉ ቢዝነሶችን የሚያንቀሳቅሱ ኢትዮጵያውያን ይህን ታላቅ ሽልማት ሊያመልጣቸው እንደማይገባ ተገልጿል።
ውድድሩ እስከ አንድ ሚሊዮን ፓውንድ ሽልማት የሚያስገኝ በመሆኑ ፕሮጀክቶቻቸውን ለማስፋፋትና እየተባባሰ ለመጣው የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ እንዲያበረክቱ ያግዛል ተብሏል።
መልቲቾይስ አፍሪካ እንዳሳወቀው በደቡብ አፍሪካ በተከናወነው የ2024 ውድድር ከ ጋና እና ከኬንያ ሲሆኑ የ "ግሪን አፍሪካ ዩዝ ኦርጋናዜሽን" ከ ጋና እንዲሁም "ኪፕ ኢት ኩል" የተሰኙት የአረንጓዴ ጉዳይ አቀንቃኞችና የሥራ ፈጣሪዎች አሸናፊ እንደሆኑ አስታውሷል።
ለዚህ ዓመቱ ሽልማት ማመልከት የሚቻለው እስከ ፈረንጆቹ ዲሴምበር 04 / 2024 ሲሆን ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎች እና ተቋማት በ https://www.multichoice.com/earthshot-nomination.php#prId=324466 እንዲያመለክቱ ጥሪ አቅርቧል።
@TikvahethMagazine
"ለሴቶች ከባዱ የጥቃት ስፍራ ቤታቸው ነው" - ሪፖርት
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው እ.አ.አ በ2023 በአለም ዙሪያ ከተገደሉ 85,000 ሴቶች እና ልጃገረዶች መካከል 60 በመቶው የሚሆኑት በቅርብ አጋራቸው ወይም የቤተሰብ አባል እጅ የሞቱ ናቸው።
ሪፖርቱ እንደጠቀሰው "ለሴቶች ከባዱ የጥቃት ስፍራ ቤታቸው ነው" ሲል ያስቀምጣል። 51ሺ ገደማ ሴቶችና ልጃገረዶች በቤታቸውና ቅርብ በሚሉት ሰው ጥቃት ሲፈጸምባቸው አፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል።
በአፍሪካ 21,700 ሴቶችና ልጃገረዶች በቤታቸውና ቅርብ በሚሉት ሰው ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። ይህም አኅጉሪቱ ካላት የህዝብ ቁጥር ጋር ሲነጻጸርም ከ100 ሺ ሰዎች 2.9 የሚሆኑት ተጠቂዎች መሆናቸውን ይጠቅሳል።
ከአፍሪካ በመቀጠል አሜሪካ ከላይ በተጠቀሰው ዓመት 8,300 የሚሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች በቤታቸውና ቅርብ በሚሉት ሰው ጥቃት ሲፈጸምባቸው ይህም ካላት የህዝብ ቁጥር ጋር ሲነጻጸር ከ100 ሺ ሰዎች 1.6 የሚሆኑት ተጠቂዎች መሆናቸውን ይጠቅሳል።
ለቤት ውስጥ ጥቃት የሚጋለጡት ሴቶች ብቻ አይደሉም እንደውም ሪፖርቱ እንደሚያስቀምጠው 80% የሚሆኑት የጥቃቱ ሰለባዎች ወንዶች ናቸው።
ነገር ግን በ2023 ከተገደሉት ሴቶች በቤተሰብ ወይም የቅርብ ሰው በሚያደርሰው ጥቃት የሞቱት 60% የሚሆኑት ሲሆኑ በዚህ ረገድ ሪፖርቱ ለወንዶች ያስቀመጠው ቁጥር 11.8 በመቶ የሚል ነው።
@TikvahethMagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
'ከረሜላ ልስጥሽ' በማለት አታሎ የ9 ዓመት ህጻን የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት እስራት ተቀጣ
በይርጋጨፌ ከተማ የ9 ዓመት ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል።
ግለሰቡ ድርጊቱን የፈጸመው በቀን 10/9/2016ዓ.ም በግምት ከጥዋቱ 4 ሰዓት በይ/ጨፌ ከተማ ካራ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተብሎ በሚጠራበት አከባቢ ነው።
የግል ተበዳይ 9 ዓመት ህጻን ተማሪ ስትሆን ሜክ አፕ ተጠርታ ተምራ እየመጣች ባለችበት ቅ/ኪዳነምህረት ት/ቤት ፊት ለፊት ባለው የመጠጥ ማከፋፈያ ውስጥ ሆኖ እማ ነይ ከረሜላ ልስጥሽ በማለት ደስታ ከረሜላ የመሰለ ነገር እንደበላች እራሷን እንደሳተች የክስ መዝገቡ ያስረዳል።
በመቀጠልም ወደ ውስጥ በማስገባት በፒላስቲክ ጅባ ላይ አስተኝቶ አሰገድዶ የደፈረ መሆኑንና ተከሳሽ ሆን ብሎ አስቦ በማድረጉ ተገልጿል።
ተከሳሹ፥ 1997 ዓ.ም በሥራ ላይ የዋለውን የኢፌዲሪ የወንጀል ዕግ አንቀፅ 627/1 የተደነገገውን በመተላለፍ በፈፀመው በሕፃናት ልጆች ላይ በሚፈፀም በግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።
በዚህም ተከሳሹ 14 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ማስተላለፉን የይርጋጨፌ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።
@TikvahethMagazine
በአማራ ክልል 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምሕርት ቤት አልሄዱም።
በአማራ ክልል አንድም ትምህርት ቤት ያልተከፈተባቸው 17 ወረዳዎች መኖራቸውን እና እንደ ክልልም 40 በመቶ ምዝገባ ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶች መኖራቸው ተገልጿል።
ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ 7 ሚሊዮን 71 ሺህ 933 ተማሪ ለመመዝገብ ታቅዶ የተመዘገበው 2 ሚሊየን 543 ሺህ 128 መኾኑን በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ይህም ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ኾነዋል ማለት እንደሆነ የገለጹት ኃላፊዋ፥ ትምህርት ቤቶች በታጠቁ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና የመምህራን ግድያ መኖሩ በትምህርት ላይ ጫና አሳድሯል ብለዋል።
ከትምህርት ሚኒስቴር በተመደበ በጀት 6 ሚሊየን 793 ሺህ መጻሕፍት ታትሞ መሰራጨቱን እና 5 ነጥብ 3 ሚሊዮን የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መጽሐፍ ወደ ደሴ እና ጎንደር የክዘና ማዕከል መግባቱን ጠቅሰዋል።
የተማሪዎች ምገባን በተመለከተ ከታቀደው አንድ ሚሊዮን ተማሪ ውስጥ 10 ሺህ ተማሪ ብቻ በመርሐ ግብሩ ተጠቃሚ መኾኑ በእጥረት ከተጠቀሱት መካከል ናቸው።
ምንጭ: አሚኮ
@TikvahethMagazine
እንኳን ወደ ደህንነቱ የተጠበቀ ልዩ የጥርስ ህክምና በደህና መጡ! 🎊🎊🎉🎉
በሴፍ ስፔሻሊቲ የጥርስ ክሊኒክ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
1. Scaling (ጥርስ እጥበት)
2. Bleaching(ጥርስ ማንጣት)
3. Brace(ብሬስ)
4. Tooth Extraction (ጥርስ መንቀል)
5. Filling(ሙሌት)
6. Diastema closure(ፍንጭት መዝጋት)
7. Root canal treatment(የጥርስ ስር ህክምና)
8. ጥርስ መትከል ( ኢምፕላንት፣ ዚርኮኒያ ጥርስ፣ ሴራሚክ ጥርስ፣ ክሮሞኮባልት፣ አክሪሊክ )
ክሊኒካችን በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉ ታካሚዎች ከፍተኛ ጥራት ያለውን የጥርስ ህክምና እና እንክብካቤ ይሰጣል።
📣ልብ ይበሉ!
ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እስከ 40% በሚደርስ ቅናሽ አገልግሎት በመስጠት ላይ ነን ይጎብኙን።
🫵የዋጋ ዝርዝር ለማየት ቴሌግራም እና ቲክቶክ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
ለተጨማሪ መረጃ
📞0907341414
📞0924143495
Telegram: /channel/Safedentalcare
Tiktok: safe.dental.care" rel="nofollow">https://tiktok.com/@safe.dental.care
በአራት ወራት ውስጥ ከ312 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ ባለፉት አራት ወራት ብር 311.56 ቢሊዮን ጥቅል ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 312.56 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 100.3 በመቶ ማሳካት ተችሏል ሲሉ ገልጸዋል።
አፈጻጸሙም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ118.58 ቢሊዮን ብር ብልጫ እና የ61 በመቶ እድገት ማሳየቱን ነው ያነሱት።
ሚኒስትሯ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በምስራቅ አፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ እንደሆነ አመልክተው ሆኖም ግን የሀገራችን ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው ገቢ አኳያ አሁንም እጅግ አነስተኛ የታክስ ገቢ እየተሰበሰበ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸምን በመሻሻል እና ህገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠር በህግ የተሰጡትን ስልጣንና ኃላፊነቶች በአግባቡ መወጣት የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን በመከተል ተግባራዊ እያደረገ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
@TikvahethMagazine
Universal Electronics
የፀሀይ ሀይል (ሶላር ፓወር ሲስተም)
- ድምፅ አልባ
- ቦታ የማይዝ
- ከ 10 ዓመት በላይ የአገልግሎት ጊዜ
- በሰልካች በቀላስሉ ከየትም ቦታ መቆጣጠር የምንችለዉ
- ነፃ የምክር፥ የገጠማ እና የአምስት አመት የዋስትና አገልግሎት
አድራሻ: አዲስ አበባ - ሀ/ጊዮርጊስ ድልድይ ተፈራ የንግድ ማዕከል
ይደውሉልን: 0911102251 , 0909539797, 0911917583 , 0905617070
ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በቅርቡ በቤርሙዳ ቲያትር ስራ እንደሚጀምር ተገለጸ
በኮሪደር ልማቱ ምክንያት ቲያትር ማሳየት ካቆመ ወራቶችን ያስቆጠረው ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት በቅርቡ ወደ አገልግሎት እንደሚመለስ ተገልጿል።
ቲያትር ቤቱ በቀዳሚነት ቤርሙዳ ቲያትርን ለተመልካቾች የሚያቀርብ ሲሆን የደፈረሱ አይኖች፣ ነገሩ አይቆምምና ሌሎችም ትዉፊታዊ ቲያትሮችንም ለተመልካቾች ሊያቀርብ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታዉቋል፡፡
የቲያትር እና ፊልም ባለሙያው ዩሐንስ አፈወርቅ የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ ቲያትር ሳይታይ መቆየቱና በአካባቢዉ ያሉ ማኅበረሰቦች መነሳታቸዉን ተከትሎ እንደ በፊቱ በቂ ሰዉ ላይመጣ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለዉ ገልጿል፡፡
ቲያትሮቹን ለእይታ ለማቅረብ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን እና የሚቀሩና የሚሟሉ ሥራዎች መኖራቸዉን ገልጾ፤ እነርሱን የማሟላት ሥራ እየተሰራ እንዳለና በቀዳሚነት በቤርሙዳ ቲያትር የተቋረጠዉ የቲያትር ቤቱ ስራ እንደሚጀመር ተናግሯል፡፡
ከዚህ ቀደም የቲያትር ቤቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ በነበረዉ አርቲስት አብዱልከሪም ጀማል ምትክ በጊዜያዊነት ቦታዉ ላይ አቶ ዩሐንስ ስለሺ እንደተቀመጡ ከመናኸሪያ ኤፍ ኤም ዘግቧል።
@TikvahethMagazine
🗞ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለንግድም ሆነ ለመኖሪያ እጅግ ተፈላጊ እየሆነ በመጣው አየር ጤና
📎መኖርያዎንም ሆነ የንግድ ሥራዎን በ አንድ ቦታ ያድርጉ
💸በማይታመን ዋጋ
✨ከ 144 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ የ ሱቅ እና የቤት ባለቤት ይሁኑ
📐የንግድ ሱቆች ከ 14 ካሬ ጀምሮ
🏘የመኖሪያ ቤቶች ከ96 ካሬ ጀምሮ
🛌ባለ 1 ባለ 2 እንዲሁም ባለ 3 መኝታ አማራጭ
📍 አየር ጤና አደባባይ ወደ አለም ባንክ በሚወስደው መንገድ አየር ጤና ትምርት ቤት ፊት ለፊት
☎️ 0906138437 ፈጥነው ይደውሉልን
"RELIEF የሚባል ሕገወጥ መድኃኒት እንዳትጠቀሙ" - የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን
የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን RELIEF የሚባለው መድኃኒት ህገወጥ እና በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያልተመዘገበ፤ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ የማይታወቅ ነው ሲል ገልጿል።
መድኃኒቱ በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው ይገመታል ያለው ባለሥልጣን መስሪያቤቱ በኢትዮጵያ ገበያ እየተዘዋወሩ መሆኑን ተደርሶበታል ብሏል።
አክሎም "ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህንን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።" ሲል ህብረተሰቡ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስቧል።
አክሎም RELIEF የተሰኘው መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ተቅማጥ ፣ የሆድ ህመም ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ ድካም፤ የእይታ መዛባት፤ መፍዘዝ ፣ ራስ ምታት ፣ የቆዳ ሽፍታ ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመርና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የኩላሊት ጉዳትን ያጠቃልላል ሲል ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
@TikvahethMagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
#ወባ
በኢትዮጵያ ካለፉት ዓመታት በተለየ የወባ ወረርሽኝ በዚህ አመት ከፍተኛ ቁጥር ማስመዝገቡን የአለም ጤና ድርጅት ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ።
ሊገባደድ ባለው የፈረንጆቹ ዓመት 7.3 ሚሊዮን የሚሆኑ የወባ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል ተብሏል። ይህም ካለፈው ዓመት 2023 ጋር ሲነጻጸር የ4.1 ሚሊዮን ጭማሪ አለው።
ከዚህ ውስጥ ከሀገር አቀፉ አጠቃላይ ቁጥር የኦሮሚያ ክልል 48.5 በመቶ የሚሆነውን እንደሚወስድ ተገልጿል።
ድንበር የለሽ የኃኪሞች ቡድን (MSF) ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በምሥራቅ ወለጋ ነቀምቴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ነጆ አጠቃላይ ሆስፒታል ባቋቋመው የወባ ህክምና መስጫ ክፍል (Ward) በሳምንት ብቻ 750 የሚጠጉ ሰዎችን እያከመ መሆኑን ገልጿል።
በኦሮሚያ ክልል ለዓመታት በዘለቀው የጸጥታ ችግር እና የጤና አገልግሎት አቅርቦት ውስንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ለወባ የሚጋለጡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንም ነው የተገለጸው።
ድንበር የለሽ የኃኪሞች ቡድን (MSF) በሚንቀሳቀስበት ሌላው ክልል ጋምቤላ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት የወባ ሥርጭቱ 150 % ጭማሪ ሲያሳይ በኩሌ ጤና ጣቢያ ብቻ ከ36 ሺ በላይ ሰዎች የወባ በሽታ ህክምና ማግኘታቸው ነው የተነገረው።
ክልሉ ከ500 ሺ በላይ ተፈናቃዮችን የሚያስተናግድ በመሆኑ ወባ እና መሰል በሽታዎች ይበልጥ ተጋላጭነቱ ይሰፋል።
MSF በ2025 እንዲሁም በ2030 የተያዙ እቅዶች ተፈጻሚ እንዲሆኑ በኢትዮጵያ እየተከሰተ ያለው የወባ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋል።
@TikvahethMagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
ለህጻናት ጠጣር ምግብን መቼ እና እንዴት እናስተዋውቃቸው?
የእናት ጡት ለህጻኑ የሚያስፈልገውን ንጥረ ነገር በሙሉ የያዘ ሲሆን በመጀመሪያዎቹ 6 ወራት የእናት ጡት ወተት ብቻ በቂው ነው።
6 ወር ከሞላው ቦኃላ ከጠጣር ምግብ ጋር ልጁን ማስተዋወቅ መጀመር የሚኖርብን ሲሆን ጡትም ለማስጣል ህጻኑን ጠጣር ምግብ ቀስበቀስ ማስለመድ ይኖርብናል።
ጠጣር ምግብ የጡት ወተትን ሙሉ በሙሉ ስለማይተካ ጡት ማጥባት እስከ 2 አመት ማቆም አይኖርባትም።
1፡ መቼ እንጀምር ?
▪️ቤተሰብ ምግብ በሚመግብበት ጊዜ ህጻኑን ምግብ ጠረጵዛ ዙሪያ አብሮ በማቅረብ እና የህጻኑን የምግብ ፍላጎት መመልከት ይቻላል።
▪️ምግብ በምንመገብ ጊዜ ህጻኑ የሚያሳየዉ ምልክቶች ለምሳሌ ፦ሳህን አካባቢ ለመድረስ እና ለመያዝ፣ ስንጎርስ የመጓጓት አፍ የመክፈት፣ ማንኪያችንን መያዝ፣ የመሳሰሉት ምልክቶች ልጆች ጠንካራ ምግብ ለመብላት ፍላጎት የማሳየት ምልክቶች ናቸዉ።
2፡ የመጀመሪያ ጉርሻ
የመጀመሪያ ጠጣር ምግብ ስንጀምር አላርጂክ ሊያስከትሉ የሚችሉ ምግቦችን ለይተን ማወቅና ማስወገድ ይኖርብናል፣ የመጀመሪያው ጉርሻ ለጡት ወተት የቀረበ ጣዕም ያላቸዉ ቢሆኑ ይመረጣሉ።
አላርጂክ ሊያስከትሉ የሚችሉ ምግቦች
▪️የወተት ተዋዖዎች ፣ እንቁላል፣ ለዉዝ፣ የአሳማ ስጋ፣ስንዴ፣አኩሩ አተር ወዘተ
አላርጂክ በብዛት የሌላቸዉ ምግቦች
▪️አፕል ፣ አቮካዶ ፣ ቀይ ስር ፣ ብሮክሊ ፣ ካሮት፣አበባ ጎመን፣አጃ ፣ ማንጎ ፣ ፓፓዬ ፣ ሩዝ ፣ የሱፍ ዘይት ፣ የስኳር ድንች ፣ የዶሮ ስጋ
▪️መጀመሪያ ጉርሻ ለምሳሌ የተፈጨ ሙዝ፣ የተፈጨ ስኳር ድንች በጡት ወተት ወይም በፎርሙላ ወተት የተቀላቀለ ሊሆን ይችላል።
የመጀመሪያ ጉርሻ መሆን ያለበት በእጃችን ማቅመስ ቢሆን ይመከራል። በመጀመሪያ በጣታችን የተፈጨዉን ሙዝ በማንሳት ለህጻኑ ከንፈር ላይ በማድረግ በቀስታ እንዲቀምስ መተዉ።
ከቀመሰው ቦኋላ ጣታቸንን እንዲጠባ በማድረግ ከጠጣር ምግብ ጋር ማለማመድ፣ አንዴ ከቀመሰ ቦኋላ መጠኑን በመጨመር ወደ ህጻኑ ምላስ በማድረግ ማብላት፣ ህጻኑ እየበል ከሆነ ካልተፋ ወዶታል ማለት ነዉ፣ በተደጋጋሚ የሚተፋ ከሆነ ግን ለመመገብ ዝግጁ አይደለም ማለት ነዉ።
በመጀመሪያው ሙከራ ህጻኑ አልተመገበም ብለን ተስፋ መቁረጥ የለብንም፣ በመደጋገም ሙከራ ማድረግ ይኖርብናል።
3፡ በምን ያህል መጠን እንጀምር?
በሙዝ የጀመርነውን የመጀመሪያውን ጠጣር ምግብ ህጻኑ ከወደደው ለጅማሮ ከሙሉ ጣት ወደ ግማሽ ማንኪያ ከዚያም ወደ አንድ ማንኪያ፣ ከዚያም ወደ አንድ ሙሉ የሾርባ ማንኪያ፣ ከዚያም ወደ ግማሽ ብርጭቆ ማሳደግ ይቻላል።
የምንመግበዉ ጠጣር ምግብ በሾርባና በጁስ መልክ መሆን አለበት። ማስታወስ ያለብን እስካሁን ከጠጣር ምግብ ጋር ህጻኑን እያስተዋወቅን መሆናችንን ነዉ።
ከመጀመሪያው ጉርሻ በኋላ ህጻኑ ጠጣሩን ምግብ ከወደደውና መብላት ከጀመረ ቀስ እያልን መጠኑን እየጨመርን እንሄዳለን ፣ማስታወስ ያለብን የህጻኑ ሆድ ትንሽ የእጅ ጭብጥ መጠን መሆኑና ብዙ እንዲበላ ማስገደድ እንደሌለብን ነዉ። ምናልባት ህጻኑ 2 ወይ 3 ማንኪያ ብቻ በቀን ውስጥ ቢበላልን በቂ ነው።
4፡ መቼ እናብላዉ?
▪️በመጀመሪያ ጠጣር ምግብ ባስተዋወቅንበት ቀናት ህጻኑ ተናዳጅ፣ ያለመፈለግን ምልክት ሊያሳይና ይችላል፣ በዚህ ጊዜ ሁለታችሁም አካሄድዱን መቀየር ሊኖርባቹ ይችላል።
▪️በመጀመሪያ በጣም ምቹ ሰአትን መምረጥና የአመጋገብ ሁኔታም ከተለመደዉ ወጣ ያለና ጫወታን የቀላቀለ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል።
ጠዋት የህጻናት የጣሳ ወተት (formula) ለሚጠጡ ልጆች ጠጣር ምግብ ለማብላት ወደ ማታ ጊዜ ምቹ ነው። የጡት ወተት በሚቀንስበት ሰአት ጠጣር ምግብ ለማብላት መዘጋጅት ምቹ ሰአት ነው። ለህጻኑ ጠጣር ምግብ ማብላት ያለብን ጡት በማጥባት በመሀል ነው።
ጠጣር ምግብ ምናልባት በጡት ወተት ውስጥ ያለውን ጠቃሚ ንጥረ ነገር ሊወስድ ስለሚችል (ለምሳሌ አይረንን) በአንድ ላይ ጠጣር ምግብና ጡት ማጥባት አይመከርም።
▪️በምንመግባቸው ጊዜ በፍጥነት አብልተን ለማስነሳት መቸኮል አይገባንም። ህጻናት በጣም ቀስ እያሉ እየተጫወቱ ስለሚበሉ ትዕግስት ያስፈልገናል።
[ @BikuZega ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የቀረበ ]
@TikvahethMagazine
"የወባ ወረርሽኝ የህብረተሰብ ጤናን ከመጉዳት ባለፈ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ትልቅ እንቅፋት እየሆነ ነው" ፕ/ር ነጻነት ወርቅነህ
የኦሮሚያ ጤና ቢሮ የወባ በሽታን አስመልክቶ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው የቢሮው ኃላፊ ፕሮፌሰር ነጻነት ወርቅነህ የወባ በሽታ በክልሉ 18 ወረዳዎች እና 10 ከተሞች መስተዋሉን ጠቅሰዋል።
በዚህም 39 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለወባ በሽታ ሥርጭት ተጋላጭ መሆናቸውን የገለፁት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊዋ፤ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን የሚሆኑት በሽታው ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።
ባለፉት አምስት ወራት በተሰሩ የመከላከል እና የመቆጣጠር ሥራዎች በበሽታው ከተያዙት ውስጥ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት በቂ የሕክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን ገልጸዋል።
በተጨማሪን የወረርሽኙን ስርጭት ለመከላከል በክልሉ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት 500 ሺሕ በሚጠጉ ቤቶች ላይ የፀረ-ወባ ኬሚካል መረጨቱንና ከ8 ሚሊዮን በላይ የአጎበር ስርጭት መደረጉንም አንስተዋል።
@TikvahethMagazine
"በመሰረተ ልማቶች ላይ በሚደርስ ስርቆት በህዳርና ጥቅምት ወር ብቻ ከ1.6 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሶብኛል" - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
በጥቅምትና ህዳር ወር ብቻ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ በተፈፀመ ስርቆት ከ1.6 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት ደርሷል ተብሏል።
ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት የደረሰውም በደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ቡልቡላ አካባቢ፣ ገላን ኮንዶሚኒየም፣ ለቡ ሙዚቃ ቤት እንዲሁም ጀርመን አደባባይ አካባቢ በተፈፀመ የመሰረተ ልማትና የኃይል ስርቆት ነው።
በአሁኑ ወቅት በመዲናዋ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
በ2017 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ በተፈፀመ ስርቆት ከ2.7 ሚሊየን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን አገልግሎቱ አስታውሷል።
@TikvahethMagazine
ለፈገግታዎ ጥሩ እንክብካቤ ይገባዋል!
ለሁለተኛ ዙር አልባሳት (ቦንዳ ልብሶች) ከየት ይመጣሉ? ምን ያህልስ ዋጋ ያወጣሉ?
አፍሪካ ለሁለተኛ ዙር አልባሳት (ቦንዳ ልብሶች) ዋነኛ መዳረሻ ነች። እንደ Observatory of Economic Complexity (OEC) መረጃ እነዚህ ልብሶች በብዛት ከአሜሪካ፣ ቻይና፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ጀርመን እና ከደቡብ ኮሪያ የሚመጡ ናቸው።
በአንጻሩ ያገለገሉ ጨርቆችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስመጡ ሀገራት ተርታ ፓኪስታን፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች፣ ቺሊ፣ ኬንያ እና ጓቲማላ ይጠቀሳሉ።
በ2022 የወጣው የዚህ ጥናት ቡድን ሪፖርት እንደሚያሳየው አፍሪካ ለቦንዳ ልብሶች 1.75 ቢሊየን ዶላር ወጪ እንዳወጣች ያስቀምጣል።
ከአፍሪካ ከፍተኛ ገንዘብ ለቦንዳ ልብስ የሚያወጡ ሀገራት መካከል ኬኒያ ቀዳሚውን ስፍራ ስትይዝ በተጠቀሰው ዓ.ም 202 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ወጪ ለዚሁ አውላለች ይላል።
ኬንያን በመከተልም ጋና (164 ሚ.) ፤ ታንዛኒያ (148 ሚ.) ፤ አንጎላ (127 ሚ.) ፤ ናይጄሪያ (94.7 ሚ.) ዶላር የሚገመት ወጪ ለዚሁ ለቦንዳ ልብሶች ማውጣታቸው ጠቅሷል።
ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓና ከሌሎች ገበያዎች ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የቦንዳ አልባሳት ንግድ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ሕጋዊ ቢሆንም፣ በሌሎች ደግሞ በድብቅ እንዲሁም እስከ ማገድ የደረሱ ሀገራት አሉ።
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ ከተሰራጨው ጨርቃ ጨርቅ 53 በመቶ የሚሆነው በሕገወጥ መንገድ ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባ ተጠቅሶ ነበር።
እ.ኤ.አ. በ2016፣ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (East African Community) የሀገር ውስጥ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪን ለመደገፍ በ2019 የቦንዳ አልባሳትን ለማገድ አቅዶ የነበር ቢሆንም የዘርፉ ቀንደኛ ተዋናይ የሆነችው አሜሪካ ውሳኔውን በመቃወም ማዕቀብ እስከመጣል የሚደርስ ማስፈራሪያ አቅርባ ነበር።
አሜሪካ በ2022 ከዚሁ የቦንዳ ልብስ ሽያጭ ገቢያ 1.01 ቢሊዮን ዶላር የሚጠቃ የኤክስፖርት ገቢ እንደምታገኝ ሪፖርቱ የሚጠቅሰው ነው።
Credit : Business Insider Africa
@TikvahethMagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
መንግሥት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የያዘውን ዕቅድ ቀውስ ይፈጥራል በሚል ሥጋት አዘገየ
መንግሥት በመላ አገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን ለመወሰን ቢያስብም፣ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የበለጠ ይሆናል በሚል ሥጋት ከመወሰን መቆጠቡን ሪፖርተር አስነብቧል።
ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው የተባሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ‹‹ዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን በሕግ ማስቀመጥ ሥራ አጥነትን፣ እንዲሁም ማኅበራዊ ቀውስን ሊያስከትል ይችላልና ይህንን ሁኔታ ማገናዘብ ይጠይቃል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሶ እንዲዘገይ ተደርጓል፤›› ብለዋል።
በተጨማሪም፣ መንግሥት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለልን በሕግ ቢወሰን አሠሪዎች የሠለጠኑና ክህሎት ያላቸው ሠራተኞችን ምርጫቸው ያደርጋሉ፤ ይህ ደግሞ አብዛኛውን ዝቅተኛ ተከፋይ ሠራተኛ ከሥራ ውጪ በማድረግ ማኅበራዊ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ በበኩላቸው፥ ኮንፌዴሬሽኑ የዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን በመንግሥት በኩል ሥራ ስለመጀመሩም ሆነ ጥናት ስለመደረጉ የሚያውቀው ጉዳይ እንደሌለ ገልጸዋል።
ሙሉ ዜናውን ያንብቡ https://www.ethiopianreporter.com/135747/
@TikvahethMagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
3ኪሎ ግራም ወርቅ የሰወረው የፖሊስ አመራር እየተፈለገ ነው!
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዲኦ ዞን ጮርሶ ወረዳ ህዳር 7/2017ዓ/ም በአንድ አፖች ሞተር ሳይክል ተጭኖ ወደ መሀል ሀገር ሲገባ የነበረ 7 ኪሎ ግራም ወርቅ በፖሊስ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ይዉላል።
ከጉሙሩክ ባጣራነዉ መሰረት ወርቁ ባለ 24 ካራት የወጪ ሀገር ወርቅ ነዉ።
በማግስቱ ህዳር 8/2017ዓ/ም የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የሆነው ኢ/ር መስፍን ሽፈራዉ ለዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ በደፈናዉ ማዕድን ስለመያዙ እያጣሩ ስለመሆናቸዉ በመግለፅ መረጃ ይሰጣቸዋል።
በማግስቱም ነገሩ ወርቅ መሆኑንና መጠኑም አራት ኪሎ ግራም መሆኑን ያስረዳቸዋል።
ይህን ተከትሎም ከዞኑ ፖሊስና ሠላምና ፀጥታ መምሪያ የተዉጣጣ ግብረ ሃይል ወደ ጮርሶ በማቅናትና መረጃ በማሰባሰብና ቃለ ጉባኤ በመፈራረም የተያዘውን 4 ኪሎ ግራም ወርቅና ተጠርጣሪዎቹን ወደ ዲላ ከተማ ይዞ ይጓለዛል።
ወዲያው ወርቁና ተጠሪጣሪዎቹ ወደ ጉሙሩክ ባለስልጣን ሀዋሳ ቅርጫፍ ይላካሉ። በዚህ መሀል የተያዘዉ ወርቅ 4 ኪሎ ግራም ብቻ እንዳልነበር መረጃዎች ይወጣሉ።
የማጣራት ስራ ሲጀመርም የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኢ/ር መስፍን ሽፈራዉ ለጊዜው ከአከባቢው ይሰወራሉ።
የዞኑ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ባለሥልጣን ሀዋሳ ቅርንጫፍ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የማጣራትና ክትትል በመጀመር በወቅቱ ወርቁን የያዙት ፖሊሶችን በቁጥጥር ስር በማዋልና ቃል በመቀበል መነሻ ፍለጋዉ ይቀጥላል።
ከዚህ በኋላም የዞኑ ፖሊስ የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ባለቤት በቁጥጥር ስር በማዋል በቤታቸው በተደረገ ፍተሻ 3ኪሎ ግራም ወርቅ ሊገኝ ችሏል።
የዞኑ ፖሊስም ከትላንት በሲቲያ ወርቁን ለኢትዮጵያ ጉሙሩክ ባለሥልጣን ሀዋሳ ቅርንጫፍ ማስረከቡን የጌዲኦ ዞን ፖሊስ አዛዥ ኮ/ር ግርማ በየኔ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጉሙሩክ ባለሥልጣን ሀዋሳ ቅርንጫፍ በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቅን ሲሆን የተያዘው 7ቱ ኪሎ ግራም ወርቅ ሙሉ ገቢ መደረጉን አረጋግጦልናል።
በመጀመሪያው ዙር 4ኪሎ ግራም ገቢ ከተደረገ በኋላ በተሰሩ የኦፕሬሽን ስራዎች ህዳር 12/2017ዓ/ም ከጮርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ቤት ተገኘ የተባለው 3 ኪሎ ግራም ገቢ መደረጉንም ነው የገለጸልን።
ይህን ባለ 24ካራት የዉጪ ሀገር ጥፍጥፍ ወርቅ ሲያጓጉዙ የነበሩ ተጠራጣሪዎች ከነሞቴርሣይክላቸው ጭምር በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገባቸው ነዉ መሆኑንም ነው የተገለጸው።
መንግስት በወርቅ ጥቁር ገበያ ላይ የወሰደዉን እርምጃ ተከትሎ ከዉጪ ሀገራት የወርቅ ምርት ወደ ሀገር ዉስጥ የመግባት አዝማሚያዎች ተበርከተዋል ተብሏል።
#TikvahEthiopia
@TikvahethMagazine
😍For ladies and gentlemen 😍
- ብራንድ የሴት ቦርሳዎች👜
- ኦርጅናል ሰአቶች ⌚️
-ቀሚሶች 💃
- Orginal duty free prefumes
-አድራሻ ቦሌ መድሀንያለም ሞል
-free delivery 🚚
ሱቃችንን ለመጎብኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ 👇👇👇
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
/channel/+NuL9kONj3Mw1YzM0
የሳይበር ደህንነት ንቃተ ህሊናን ያጎለብታሉ ተብለው የተመረጡ ፊልሞች ተሸላሚ ሆነዋል።
በየአመቱ ጥቅምት ወር ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሚያካሄደው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር ዘንድሮም “ የቁልፍ መሰረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዓላዊነት ” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1- 30/2017 ዓ.ም በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተከብሯል።
የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳንኤል ጉታ " የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ እንደ ሀገር በልዩ ትኩረት እየተሰራ ይገኛል " ብለዋል።
በጥቅምት ወር በተካሄደው የሳይበር ደህንነት ወር ከሳይበር ደህንነት ጋር የተያያዙ የአጭር ፊልም ውድድር መካሄዱ ተገልጿል።
በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ላጠናቀቁ እንደየ ደረጃቸው ከ50 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር ሽልማት በዛሬው ዕለት ተበረክቶላቸዋል።
በሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወሩ በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ ጸድቆ ተግባራዊ በሆነው “ሀገራዊ የሳይበር ደህንነት ፖሊሲ” ከተለያዩ ቁልፍ ተቋማትና ሚኒስቴር መ/ቤቶች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር ምክክር መደረጉን ተገልጿል።
በወሩ በተካሄዱ ኮንፈረንሶችና የአዉደ ርዕይ መርሃ ግብሮች ላይም ከሁለት መቶ ሦስት (203) ተቋማት የተዉጣጡ ከአራት ሺ አምስት መቶ በላይ (4,500) ሰዎች ተሳታፊ መሆናቸውን በተቋሙ የኮምዩኒኬሽን እና የሳይበር ደህንነት ባህል ግንባታ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ሃይሉ ገልጸዋል፡፡
@tikvahmagazine
ልጆቻችን ምን ይመልከቱ?
በአሁኑ ሰዓት በርካታ ልጆች ለዲጂታሉ አለም በቶሎ በሚኖራቸው ተጋላጭነት ሳቢያ ላልተመረጡ ፕሮግራሞች እና ኮንተንቶች ሲጋለጡ ይስተዋላል።
ከዚህም ባለፈ አንዳንድ የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ምድባቸው የመዝናኛ ይሁን እንጂ ይዘታቸው ለህጻናት የሚመጥን ሳይሆን ብዙ ሰዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ ይደመጣል።
እነዚህ ፕሮግራም እና ቪዲዮዎች የልጆች አስተዳደግ እና አስተሳሰብ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖዎች አላቸው።
በተለይ ደግሞ ልጆች የቋንቋ እና የአስተሳሰብ ችሎታቸው የሚዳብረው በመጀመሪያ ሰባት አመት በመሆኑ በዚህ እድሜ ላልተመረጡ ፕሮግራሞች የሚኖራቸው ተጋላጭነት ላልተፈለጉ ጫናዎች ይዳርጋቸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳን ላይ ጠቅላላ ሃኪም እና ሁለንተናዊ የህጻናት እድገት ባለሞያ የሆኑትን ዶ/ር ቱሚም ጌታቸውን አነጋግሯል።
ዋና ዋና ነጥቦች፦
- ልጆች በመጀመሪያው ሰባት አመት ከፍተኛ የአዕምሮ እድገታቸው የሚጀምርበት እድሜ ነው፤
- ከ ሰባት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት እንደ እድሜያቸው አስተማሪ የሆነ ፕሮግራሞችን ቢያዩ ይመከራል፤
- ትምህርታዊ ፕሮግራሞች ቢሆኑም እንኳን ከ ሰባት ዓመት በታች ያሉ ህጻናት በቀን ከ ሁለት ሰዓት በላይ ስክሪን እንዲመለከቱ አይመከርም።
- ሚዲያዎች በወላጅ ድጋፍ እንዲመለከቷቸው የሚያስታውሱ የጽሁፍ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉት ፕሮግራም ላይ ማስቀመጥ ቢችሉ መልካም ነው።
- ወላጆች ለልጆቻቸው እነሱ አስቀድመው ያዩትን እና የፈተሹትን ቢያሳዩ ያንን ባይችሉ እንኳን ልጆቻቸው ሲያዩት አበረው ቁጭ ብለው ቢያዩ እና የሚያዩትን ነገር ለልጆቻቸው ማስረዳት ቢችሉ ይመከራል።
- ልጆች በልጅነታቸው የተራዘመ የስክሪን ቆይታ ሲኖራቸው እድሜያቸው እየጨመረ በሚመጣበት ወቅት ለዲጂታል ጾታዊ ጥቃት ተጋላጭነታቸውን ያሰፋዋል።
- ወላጅ ልጆቼን እንዴት አድርጌ ልቆጣጠራቸው እችላለሁ የሚለውን ማወቅ ያለባቸው በመሆኑ በተቻለው መጠን ስለ ኤሌክትሮኒክስ ያላቸው እውቀት ሊያሳድጉ ይገባል።
ሙሉ ቃለመጠይቁን ያንብቡ https://telegra.ph/ETH-11-22-5
@TikvahethMagazine
🗞ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ለንግድም ሆነ ለመኖሪያ እጅግ ተፈላጊ እየሆነ በመጣው አየር ጤና
📎መኖርያዎንም ሆነ የንግድ ሥራዎን በ አንድ ቦታ ያድርጉ
💸በማይታመን ዋጋ
✨ከ 144 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ የ ሱቅ እና የቤት ባለቤት ይሁኑ
📐የንግድ ሱቆች ከ 14 ካሬ ጀምሮ
🏘የመኖሪያ ቤቶች ከ96 ካሬ ጀምሮ
🛌ባለ 1 ባለ 2 እንዲሁም ባለ 3 መኝታ አማራጭ
📍 አየር ጤና አደባባይ ወደ አለም ባንክ በሚወስደው መንገድ አየር ጤና ትምርት ቤት ፊት ለፊት
☎️ 0906138437 ፈጥነው ይደውሉልን