ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው። #ኢትዮጵያ ያግኙን +251913134524
"ከ250 በላይ ሀይስኩሎች ላይ የዲጂታል ላይብረሪ አቋቁሚያለው" SRE
በኢትዮጵያ ‘Scientific Revolution Earth (SRE) በሚል የተመሰረተውየቴክኖሎጂ ኩባንያ የ10ኛ ዓመት በዓሉን አክብሯል።
ተቋሙ በስካሁኑ ጉዞው በገጠራማው ክፍል ሁሉ ያለ ኢንተርኔት አገልግሎት የዲጂታል ላይብረሪዎችን ማቋቋም፤ የትራፊክ ፍሰት የሚቆጣጠርና ሌሎች ከውጪ በውድ ዋጋ የሚገዙ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ማምረቱን ገልጿል።
የዲጂታል ላይብረሪውን በተመለከተ ለምሳሌ በትግራይ ክልል በራያ የኒቨርሲቲ ድጋፍ ከ20 በላይ አካባቢዎች ሃይስኩሎች ላይ መተግበሩን እና በቡልቲም ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ደግሞ በአካባቢው ባሉ በርካታ ተቋማት ላይ መተግበሩን አስረድቷል።
በአማራ ክልል በተመሳሳይ በአማራ ልማት ማኀበር አማካኝነት ከ110 በላይ ተግባሪዊ ሆኗል ያለው ድርጅቱ በአማራ ትምህርት ቢሮ አማካኝነት ደግሞ ደሴ፣ ወልዲያ፣ ሰቆጣ፣ ከሚሴ መምህራት ትምህርት ኮሌጆች ኢምፕልመንት ተደርጓል ሲል አስታውቋል።
በአጠቃላይ የድጅታል ላይብረሪው ከ250 በላይ ሀይስኩሎች፣ ከ16 በላይ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ መተግበሩን ገልጿል።
በተቋሙ የለሙ ቴክኖሎጂዎች በሀገር ውስጥ በመመረታቸው ከውጪ ከሚገዙበት ዋጋ 50 በመቶ ቅናሽ እንዳላቸውም ተገልጿል። በተጨማሪም የአንድ አመት ዋስትና እና በቀላሉ የጥገና አገልግሎት ማመቻቸት ይቻላል ተብሏል።
ተቋሙ 10ኛ ዓመቱን አስመልክቶ ባዘጋጀው የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የማስተዋወቅ ዝግጅት እስካሁን በሪሰርች ያሉ 32 ፕሮዳክቶችን ጨምሮ በዕለቱ ለዕይታ ያቀረባቸውን 10 የሚሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን አስተዋውቋል።
ተቋሙ አንዳንዶቹ ቴክኖሎጂዎች የመንግስትን አብሮነት የሚጠይቀ ናቸው ብሏል። "ለምሳሌ እንደ ትራፊክ ራዳር፣ የትራፊክ መብራቶች፣ ከተማው ላይ ያሉ የስማርት ሲቲ ቴክኖሎጂዎች ከመንግስት ጋር መስራትን የሚፈልጉ ናቸው” ነው ያለው።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethmagazine
ሳዑዲ አረቢያ በ100 ቢሊዮን ዶላር በጀት አዲስ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ልትገነባ ነው።
ሳዑዲ አረቢያ ከጎረቤት አገሯ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ጋር ለመወዳደር የሚያስችላትን እስከ 100 ቢሊዮን ዶላር በጀት የተመደበለት አዲስ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ልትገነባ ነው ተብሏል።
"Project Transcendence" የተሰኘው ይህ ተነሳሽነት አዳዲስ ባለተሰጥኦዎችን ወደ ሀገሪቱ የመመልመል፣ የቴክኖሎጂ ስነ-ምህዳሩን በማዳበር የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ወደ ሀገሪቱ እንዲገቡ በማበረታታት ላይ ያተኩራል ተብሏል።
ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘም ከቀናት በፊት የጎግል ኩባንያ በሳውዲ አረቢያ የአረብኛ ቋንቋ AI ሞዴሎችን እና ሳዑዲ-ተኮር AI መተግበሪያዎችን ለመስራት የሚያገለግል ማዕከል ለመገንባት ተስማምቷል።
ይህ የሳውዲ ፕሮጀክት አላማው ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ገበያ ጋር በመወዳደር የሰለጠነ የሰው ሀይል ማቅረብ ነው ተብሏል።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በ2017 የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሚኒስትር ዴኤታ በመሾም የመጀመሪያዋ ሀገር ስትሆን በ2031የ AI የስህበት ማዕከል ለመሆን ብሔራዊ ስትራቴጂ ነድፋ እየተንቀሳቀሰች ያለች ሀገር ናት።
@tikvahethmagazine
ወጋገን ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የአንድ አክሲዮን ትርፍ 36.89 በመቶ መድረሱን ገለጸ
ባንኩ እ.ኢ.አ በ2023/24 በጀት ዓመት በታሪኩ ከፍተኛውን ብር 9.8 ቢሊዮን ገቢ ማስመዝገቡን አስታውቋል።
ባንኩ ዛሬ በሒልተን ሆቴል 31ኛ መደበኛና 15ኛ አስቸኳይ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የጠራ ሲሆን፣ በዚህም ከታክስ በፊት 2.2 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን የባንኩ የዳይሬክቶሬት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲሹ ሁሴን ተናግረዋል።
በገለጻው መሠረት፦
- ባንኩ 9.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን፣ ተቀማጭ ገንዘቡ ደግሞ 22 በመቶ እድገት በማሳዬት 52.1 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ገልጿል።
- እ.ኤ.አ ሰኔ 30/2024 የባንኩ ባለአክሲዮኖች ብዛት 12 ሺሕ፣ የተከፈለ ካፒታሉ 27 በመቶ እድገት በማሳዬት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ 5.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል።
- የባንኩ ጠቅላላ ካፒታል 33 በመቶ እድገት በማሳዬት 9.2 ቢሊዮን ብር፣ የአንድ አክሲዮን ትርፍ 36.9 በመቶ ደርሷል።
- ባንኩ የሰጠው ብድር በዓመቱ መጨረሻ ሲሰላ 45.1 ቢሊዮን ብር፣ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት 65.7 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
"አርሷደሩ ተጠቃሚ ነው ማለት ይቻላል" የሲዳማ ክልል ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን
በሲዳማ ክልል ባለፈው ዓመት 25 ሺህ 572 ቶን ነው ወደ ማከላዊ ገበያ መቅረቡን እና በዘንድሮም ዓመትም በ15 ሺ በማሳደግ ወደ አርባ ሺ ቶን ለማዕከላዊ ገቢያ ለማቅረብ እቅድ መያዙን የክልሉ ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መስፍን ቃሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ቡና በክልሉ በምን መንገድ ነው ለማዕከላዊ ገቢያ የሚቀርበው?
ዋና ዳይሬክተሩ ቡና አሁን ላይ በሦስት ዋና ዋና መንገዶች እየተሰበሰበ ይገኛል ብለዋል። በዚህም የመጀመሪያው በማኅበራት በኩል የሚሰበሰብ እንደሆነ ገልጸዋል።
በክልሉ ከ77 በላይ የቡና ምርት የሚሰበስቡ መሰረታዊ የህብረት ስራ ማኅበራት እንደሚገኙ አስቀምጠዋል። "እነዚህ [ማኅበራቱ] ከአርሷደሩ ምርቱን ተቀብለው ለዩኒየኑ [የሲዳማ ቡና አብቃይ ዩኒየን] አቅርበው ዩኒየኑ ደግሞ እስከውጪ ኤክስፖርት ያደርጋል" ሲሉ ያስረዳሉ።
ሁለተኛው መንገድ ደግሞ አቅራቢ ነጋዴዎች አማካኝነት የሚሰበሰብ እንደሆነ ነው የገለጹት። " ከ205 በላይ በግል ኢንዱስትሪ ያላቸው አቅራቢ ነጋዴዎች እና 129 በአክሲዮን የሚሰሩ አሉ በእነዚህ እየተሰበሰበ ለላኪዎች ቀርቦ ላኪዎች ደግሞ ቡናውን ኤክስፖርት የሚያደርጉበት አሰራር አለ።" ብለዋል።
አቶ መስፍን ሦስተኛውን መንገድ ሲገልጹ፥ "ሶስተኛው ደግሞ ሁለት ሄክታር እና ከዛ በላይ ቡና ማሳ ያላቸው አርሷደሮች አሉ 262 ናቸው እነዚህ የራሳቸውን ቡና ብቻ ሰብስበው አድርቀው ለውጭ ገበያ ያቀርባሉ።" ሲሉ ተናግረዋል።
በዚህም፥ "ላኪ የሆኑ አርሷደሮች ቡናቸውን ተደራድረው፤ ጥራት ያለው ቡና አዘጋጅተው እስከ ውጪ ድረስ የሚልኩበት አሰራር አለ" ብለዋል።
አክለውም፥ "ለማኅበራት የሚያስረክቡ ደግሞ ሲያስረክቡ ቅድመ ክፍያ ያገኛሉ፤ ማኅበራቱ ካተረፉ ደግሞ ሁለተኛ ክፍያ ያገኛሉ፤ ዩኒየን ካተረፈው ደግሞ ሶስተኛ ክፍያ የሚያገኙበት አሰራር አለ" ሲሉ ያስረዳሉ።
የመሸጫ ዋጋው ጉዳይስ ?
አቶ መስፍን ዋጋውን ሲያስረዱ፥ አሁን ላይ በክልሉ ሁለት አይነት ቡና እንደሚዘጋጅ ይጠቅሳሉ። "በምዕራብ ዞኖች እና ወረዳዎች አካባቢ ማለትም ከሀዋሳ ጀምሮ እስከ ዲላ በንቴ ያሉ ወረዳዎች ከ47-49 ብር ነው በኪሎ እየሸጡ ያሉት፤ በምስራቅ በኩል ያሉ ወረዳዎች ደግሞ ከ50-70 ብር እየሸጡ ነው ያሉት፤ በየወረዳው ዋጋው የሚለዋወጥበት ሁኔታ ነው ያለው ይህ ማለት የቡናው ጥራትም በዛው ልክ ይለያያል ዋጋው ሚለያየውም ለዛ ነው።" የሚል ምላሻቸውን ሰጥተዋል።
አክለውም፥ "አሁን ያነሳነው ዋጋ [ከ47 - 70 ብር በኪሎ ብለው ከላይ የጠቀሱት] የእሸት ቡና ዋጋ ነው። ከ100 ኪሎ እሸት ቡና ከ 19-20 ኪሎ ደረቅ ቡና ይወጣል። [ይኽም] 5.5 ኪሎ እሸት ቡና አንድ ኪሎ ንጹህ ቡና ይወጣዋል የሚለውን ካሰላን በዛ ማግኘት ይቻላል።" ሲሉ ያስረዳሉ።
አርሶአደሩ ተጠቃሚ ነው ማለት ይቻላል?
ይህንን ጥያቄ ያቀረብንላቸው ዋና ዳይሬክተሩ፥ "አዎ አርሷደሩ ተጠቃሚ ነው ማለት ይቻላል" የሚል ምላሽ ሰጥተውናል። አክለውም "ዝቅተኛ መሬት ያለው አርሷደር ብዙም ተጠቃሚ ላይሆን ይችላል፤ ግን አማካይ እና ደህና መሬት ያለው ተጠቃሚ የሚሆንበት አግባብ አለ" ነው ያሉት።
ይኽን ሲያስረዱም፥ "ምርትና ምርታማነቱን የሚያሳድግ አርሷደር ተጠቃሚ ነው የሚሆነው ዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ምርት ሚያገኝ አለ ያ ከፍተኛ ምርት የሚያገኘው የባለሙያ ምክር እና ሳይንሳዊ ፓኬጁን በአግባቡ ተግባራዊ ያደረገ አርሷደር ነው። የተሰጠውን ምክር ቶሎ ተቀብሎ ተግባራዊ የሚያደርግ አርሷደር የተሻለ ተጠቃሚ ነው የሚሆነው።" ሲሉ ይገልጻሉ።
"ቡናን ተክለው ቡናን አምርተው እስከ ኢንዱስትሪ የደረሱ አርሷደሮች አሉ፤ ሁለት እና ከዛ በላይ ሄክታር ያላቸው አርሷደሮች ምርታቸውን እስከ ውጭ ሀገር ድረስ ልከው ሀብታም የሆኑ አሉ፤ በ2016 ዓ.ም እራሱ "Cup of Excellency" ላይ ተወዳድሮ ያሸነፈ አለ፤ ይሄ አርሶአደር ምርቱን አዘጋጅቶ ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ነው የሸጠው ይህ ቀላል ነገር አይደለም። ስለዚህ ተጠቃሚነታቸው በሰሩት እና በለፉት ልክ ነው ሚሆነው ማለት ነው።" ሲሉ ያነሳሉ።
አክለውም "የተሻለ መሬት ያለው አርሷደር በቡና ምርት ላይ የሚሳተፍ ከሆነ የተሰጠውን የባለሙያ ምክር በአግባቡ የሚጠቀም ከሆነ እና ፓኬጁን ተግባራዊ የሚያደርግ ከሆነ ቡና ላይ ተጠቃሚ የሚሆንበት አግባብ ነው ያለው።" ሲሉ ተናግረዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
የአበባ ሥጦታ ለሚወዱት የተገባ ነው!
አበባ እርሶ ቃል ሳይናገሩ ብዙ መልዕክቶችን የማስተላለፍ አቅም አለው። ለዚህ ነው የፍቅር ዋና መገለጫ የሆነው።
ፍቅር ያጠነክራል፤ ለሰዎች ያለንን ክብር ያሳያል፤ መልካም ምኞት መግለጫ ነው፤ እንክብካቤንና ቅርበትንም ለማሳየት አበባ ቋንቋ ነው።
እኛ ደግሞ ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ሰው አበባ መላክ እንዲችሉ እድሉን አመቻችተናል። ለሚወዱት ሰው መልዕክቶን እናደርሳለን።
ያማክሩን በብዙ አማራጭ በተመጣጣኝ ዋጋ በምናዘጋጃቸው አበቦቻችን ብዙ ፍቅር ይሸምታሉ።
ይደውሉ 0911359234 ወይም 0954882764
ተጨማሪ መረጃዎችንና ፎቶዎችን የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ይመልከቱ /channel/bluebellgiftstore
" 17 በሽታ አምጪ ተህዋሲያን አዲስ ክትባት ሊፈለግላቸው እንደሚገባ በጥናት ለይቻው " - የዓለም ጤና ድርጅት
በአለም አቀፍ ደረጃ 17 ባክቴሪያ፣ ቫይረሶች እና አዘውትረው በሽታን የሚያስከትሉ ጥገኛ ተህዋሲያን አዲስ ክትባት ሊፈለግላቸው እንደሚገባ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባካሄደው አዲስ ጥናት ለይቷል።
ጥናቱ የተካሄደው በአህጉራዊ እና አለም አቀፋዊ የጤና ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ ነው። በዚህም ይህ እርምጃ ሥር የሰደደ በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ስልታዊ በሆነ መንገድ ለመከላከል የሚያስችል ነው ተብሏል።
ጥናቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በአመት ወደ 2.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን በሞት የሚነጥቁትን የኤች አይቪን፣ ወባን እና ሳንባ ነቀርሳን ጨምሮ ሌሎች ተዋህሲያን ለክትባት ምርምር እና ማልማት ቅድሚያ እንዲሰጣቸው አመልክቷል።
በዝቅተኛ ገቢ ባላቸው አገራት ከባድ ኢንፌክሽኖችን የሚያስከትለው እና እስከ 280ሺ የሚገድለው እንደ ግሩፕ A ስትሬፕቶኮከስ ለመሳሰሉት በሽታ አምጪ ተህዋሲያንም ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥናቱ ለይቷል።
የክትባት ምርምር የሚያስፈልጋቸው በሽታ አምጪ ተህዋሲያን፦ ግሩፕ A streptococcus፤ ሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ፤ ኤችአይቪ-1 Klebsiella pneumoniae ናቸው።
ክትባቶቻቸው የበለጠ እንዲበለፅጉ ከሚጠበቅባቸው መካከል ደግሞ ሳይቲሜጋሎ ቫይረስ፤ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ፤ ኖሮቫይረስ፤ ፕላዝሞዲየም ፋልሲፓረም ይገኙበታል።
ይህ ጥናት በአሁኑ ጊዜ የአለማቀፉን ማህበረሰብ በእጅጉ የሚጎዱ በሽታዎችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንሱ ብቻ ሳይሆን ታካሚዎች በጤና ተቋም ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ከፍተኛ የህክምና ወጪዎችን የሚቀንሱ ክትባቶችን ለማበልፀግ እንደሚረዳ ተነግሯል።
የዓለም ጤና ድርጅት ይህንን ትናት የሰራው ዓለም የአለምቀፍ እና አህጉራዊ ኤክስፐርቶች የሚሰጡትን ግምገማ መሰረት በማድረግ ሲሆን፤ በዚህ ግምገማ መሰረትም 17 በሽታ አምጪ ተዋህሲያንን አዳዲስ ክትባት እንዲሚያስፈልጋቸው መለየቱ ነው የተነገረው።
@tikvahethmagazine
የአበባ ሥጦታ ለሚወዱት የተገባ ነው!
አበባ እርሶ ቃል ሳይናገሩ ብዙ መልዕክቶችን የማስተላለፍ አቅም አለው። ለዚህ ነው የፍቅር ዋና መገለጫ የሆነው።
ፍቅር ያጠነክራል፤ ለሰዎች ያለንን ክብር ያሳያል፤ መልካም ምኞት መግለጫ ነው፤ እንክብካቤንና ቅርበትንም ለማሳየት አበባ ቋንቋ ነው።
እኛ ደግሞ ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ሰው አበባ መላክ እንዲችሉ እድሉን አመቻችተናል። ለሚወዱት ሰው መልዕክቶን እናደርሳለን።
ያማክሩን በብዙ አማራጭ በተመጣጣኝ ዋጋ በምናዘጋጃቸው አበቦቻችን ብዙ ፍቅር ይሸምታሉ።
ይደውሉ 0911359234 ወይም 0954882764
ተጨማሪ መረጃዎችንና ፎቶዎችን የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ይመልከቱ /channel/bluebellgiftstore
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በገበያ ሞሎች ላይ የቁጥጥር ሥራ በዘመቻ መልክ እየሰራው ነኝ ብሏል።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በከተማዋ በርካታ ነጋዴዎች በግብር ከፋይነት ተመዝግበው ደረሰኝ የማይሰጡ በመሆናቸው እና ችግሩም በጣም እየሰፋ በመሆኑ ወጥነት ባለው መንገድ ህጉን እንዲያከብሩ እና ወደስርዓት እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።
ቢሮው የታክስ ኢንተለጀንስ እና ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ነጋሽ የቁጥጥር ስራው ከዚህ ቀደምም የነበረ ቢሆንም በዘመቻ መልክ ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ዘመቻ ሲባል ወደ ቫት ስርዓት ውስጥ ያልገቡትን ማስገባት ፣ፈቃድ የሌላቸው ፈቃድ እንዲያወጡ ማድርግ፣ ደረጃቸው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ የማይሰጡትን ደረሰኝ አስፈቅደው እና አሳትመው መጠቀም እንዲጀምሩ ለማስቻል ያለመ ነው።
ዘመቻው በልዩነት እየተሰራ ያለው የገበያ ሞሎች ላይ ነው ያሉት አቶ ተስፋዬ በዚህ ስፍራ የሚነግዱ ሰዎች የግብር ደረጃቸው ዝቅ ያለ በመሆኑ ወይም ደረጃቸው ትልቅ ሆኖ ሳለ እንደትልቅነታቸው ተመዝግበው ደረሰኝ መስጠት የሚገባቸው ሆኖ ሳለ ሳይሰጡ የሚነግዱ በመኖራቸው ትኩረት መደረጉን ጠቁመዋል።
በአሁኑ ሰዓት በከተማ አስተዳደሩ በግብር ከፋይነት የተመዘገቡ ነጋዴዎች ቁጥር ነጋዴ ያልሆኑ ግብር ከፋዮችን ጨምሮ 490 ሺ አካባቢ እንደሚሆኑ ተናግሯል።
ይህ ቁጥር አዲስ አበባ ላይ ያሉ ነጋዴዎችን በሙሉ አያካትትም።
በክልል ንግድ ፈቃድ ሳያስጠቅሱ ማለትም ክልል ላይ ፈቃድ ሲያወጡ ሌላ ክልል ላይ ቅርንጫፍ እንደሚኖረው ሳያስጠቅሱ የሚነግዱ በአንድ ክፍለ ከተማ ከ 100 በላይ ነጋዴዎች እየተገኙ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
ጥያቄ :-መርካቶ አካባቢ በሞሎች ላይ ያለደረሰኝ እየሰራችሁ ነው በሚል ለሁሉም ማስጠንቀቂያ እንዲሰጥ እየተደረገ መሆኑን ሰምተናል መረጃው አላችሁ ወይ ስንል የጠየቅናቸው ዳይሬክተሩ በምላሻቸው :-
"መርካቶ በባህሪው ብዙ የክልል ግብር ከፋዮች የሚያለቅሱበት ቦታ ነው የሌሎች ክፍለ ከተሞች ግብር ከፋዮችም ቅሬታ ያቀርባሉ ደረሰኝ አይሰጡም በሚል ትልቅ ችግር ስላለበት ትኩረት ተደርጎበት ያለ ነው እንጂ አዲስ አይደለም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ቦታው በልዩ ሁኔታ (በግብር አሰባሰብ) በመንግስት ትኩረት ተደርጎበት ሊሰራበት የሚፈለግ አካባቢ ነው ነገር ግን ከአሰራር አንጻር በሚፈለገው ልክ ማሳካት አልተቻለም ነው ያሉት።
ማስጠንቀቂያው በሁሉም ክፍለ ከተማ ለሚገኙ ገበያ ማዕከላት እና ሞሎች እንዲደርስ አድርገናል ያሉት አቶ ተስፋዬ ለእነዚህ እየተሰጠ ያለው ባደረግነው ክትትል በብዛት ያለደረሰኝ እንደሚሰሩ የተለዩ በመሆናችው ነው ብለዋል።
ማስጠንቀቂያውን በመቀበላቸው የሚደርስባቸው ነገር የለም ያሉ ሲሆን ነገር ግን " ያለ ደረሰኝ እየሰራችሁ መሆኑ ታውቋል አንታወቅም የሚል ድብብቆሽ አቁሙ እና በግልጽ በደረሰኝ ስሩ" ለማለት መሆኑን ተናግረዋል።
#በአዲሱ የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ መሰረት ያለደረሰኝ ሲነግድ የተገኘ ነጋዴ እስከ 100 ሺ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል።
@tikvahethmagazine
በኢኳቶሪያል ጊኒ ከታዋቂ ሴቶች ጋር ሲፈፅም የነበረውን ወሲብ፤ በቪዲዮ ካሴቶች ያከማቸው ባለስልጣን
የኢኳቶሪያል ጊኒ የፋይናንስ ምርመራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ባልታሳር ኢንጎንጋ ከታዋቂ ሴቶች እና የባለስልጣናት ዘመዶች ጋር ከቢሮ እና በተለያዩ ቦታዎች ወሲብ ሲፈፅም የሚያሳዩ ቪዲዎች አከማችቶ ተገኝቷል።
ቪዲዮው የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት እህት ጨምሮ የታዋቂ ሰዎችን የወሲብ ህይወት የሚያሳይ ነው የተባለ ሲሆን ከ400 በላይ የወሲብ ካሴቶችን በባለስልጣኑ ቢሮ እና መኖሪያ ተገኝቷል ተብሏል።
ድርጊቱ የተጋለጠው የ54 አመቱ ኢንጎንጋ በተጠረጠረበት የማጭበርበር ወንጀሎች ላይ ተመስርቶ በተደረገ ፍተሻ ነው።
በዚህም ባለስልጣኑ በቤቱ እና በቢሮው ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነቶችን በቢሮው እና በተለያዩ ቦታዎች ሲፈፅም የሚያሳዩ ቪዲዮዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተሰራጭተዋል።
በቪዲዮ ቅጂው ከታዩት ውስጥ የፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉማ ምባሶጎ እህት፤ የከፍተኛ ባለስልጣናት የትዳር አጋሮች ጨምሮ የቅርብ የቤተሰብ አባላት እና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ዘመዶች እንደሚገኙ አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።
ሮይተርስ በበኩሉ በቪዲዎቹ ላይ የሚታዩትን ባለስልጣናት እና ትክክልኝነት ማረጋገጥ እንዳልቻለ ገልጿል።
የቪዲዮ ቅጂዎቹ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ከወጡ በኃላ ከፍተኛ የህዝብ ቁጣ በመቀስቀስ የብዙሃን መገናኛዎችን ቀልብ ስቧል።
የአገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ማንጉ ማንኛውም ሰራተኛ በስራ ቦታ የወሲብ ድርጊት ሲፈጽም ከተገኙ “የሥነ ምግባር ደንቡን በመጣስ” እንደሚታገድ ገልፀዋል።
እኚህን መሰል ድርጊቶች ለመከላከልም የክትትል ካሜራዎችን በፍርድ ቤት እና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እንዲገጠሙ አዘዋል።
ይህንን መሰል ድርጊቶች "የአገሪቷን ገጽታ የሚያቆሽሹ" መሆኑን የገለፁት ምክትል ፕሬዝዳንቱ በቢሮ ውስጥ ወሲብ ሲፈጽሙ የተያዙ ሰራተኞች "ከባድ እርምጃዎችን እንደሚወሰድባቸው" አስጠንቅቀዋል።
@tikvahethmagazine
የአበባ ሥጦታ ለሚወዱት የተገባ ነው!
አበባ እርሶ ቃል ሳይናገሩ ብዙ መልዕክቶችን የማስተላለፍ አቅም አለው። ለዚህ ነው የፍቅር ዋና መገለጫ የሆነው።
ፍቅር ያጠነክራል፤ ለሰዎች ያለንን ክብር ያሳያል፤ መልካም ምኞት መግለጫ ነው፤ እንክብካቤንና ቅርበትንም ለማሳየት አበባ ቋንቋ ነው።
እኛ ደግሞ ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ሰው አበባ መላክ እንዲችሉ እድሉን አመቻችተናል። ለሚወዱት ሰው መልዕክቶን እናደርሳለን።
ያማክሩን በብዙ አማራጭ በተመጣጣኝ ዋጋ በምናዘጋጃቸው አበቦቻችን ብዙ ፍቅር ይሸምታሉ።
ይደውሉ 0911359234 ወይም 0954882764
ተጨማሪ መረጃዎችንና ፎቶዎችን የቴሌግራም ቻናላችንን ተቀላቅለው ይመልከቱ /channel/bluebellgiftstore
"ሁላችንንም የሚያስተባብር የሰላም ፍኖተ ካርታ የለንም" -ዶ/ር ዮናስ አሽኔ
በሃገራዊ ምክክሩ ስራዎች እና በኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታን የውይይት አጅንዳው ያደረገው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን አራተኛ ዓመት ጉባኤ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና የውጭ ግንኙነት መምህር እና ተመራማሪ ዶ/ር ዮናስ አሽኔ ጠንከር ያሉ ሃሳቦችን ሰንዝረዋል።
ካነሷቸው ሃሳቦች መካከል
ሃገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ምክክር የሚል ሃሳብ ይዞ ነው የገባው በኢትዮጵያ ባለው ነባራዉ ሁኔታ ምክክር ምን ያህል ሰላም ሊያመጣ ይችላል ብለን ስንጠይቅ ከግጭቶች ስፋት እና ጥልቀት አንጻር በምክክር ብቻ ሊቆም የሚችል አይደለም ብለዋል።
የምክክር ኮሚሽኑ ከተሰጡት እንደ የፖለቲካ ባህል ማሳደግ እና ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ መሰረት መጣል ያሉ ተግባር እና ሃላፊነቶችን ወደ ጎን በመተው ሃገራዊ ምክክሩ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ነውን ሲሉ ተችተዋል።
በታሪካችን ተቋማት በኢትዮጵያ የሚገነቡት ምን ዓይነት ባህሪ ይዘው ነው ብለን ስንጠይቅ በአብዛኛው ስልጣን የያዘው አካል ማስፈጸሚያ ሆነው ነው የሚሰሩት ያሉ ሲሆን የምንሰራቸው ተቋማት ሃገራዊ ምክክርን ጨምሮ ነጻ ይሆናሉ ብለን መጠበቅ የለብንም ብለዋል።
በተጨማሪም
°ቀውስ ያለው የፖለቲካ ሽግግር ውስጥ የምንገኝ በመሆናችን በእርስ በእርስ ጦርነት እና ዋልታ ረገጥ በሆኑ አቋሞች ባሉበት የታጠቁ ሃይሎች ተጨምረውበት የፖለቲካ አለመረጋጋት ውስጥ የሚደረግ ሃገራዊ ምክክር ነው።
°"የእዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ምክክር እንዴት ይሆናል ብለን ስናስብ ፈተናቸው የእነሱ(የምክክር ኮሚሽኑ) ፈተና ከባድ ይሆናል።
°በጣም ብዙ ሰው ሞቷል እየሞተ ነው ይሄ ሁሉ ቀውስ ሲመጣ ሁላችንም ለሳምንት ለቅሶ መቀመጥ ነበረብን ወደ ምክክር ከመግባት በፊት ሃዘን መቀመጥ ድንኳን መጣልና ጥቁር መልበስ ነበረብን ብለዋል።
ሁላችንንም የሚያስተባብር የሰላም ፍኖተ ካርታ የለንም ሁሉም ሰላምን ለማምጣት ይጥራል ግን ሰላምን እያሰፈንን አይደለም ያሉት ተመራማሪው
"መንግስት በአስተዳደር (Governance)እፈታቸዋለሁ የሚላቸው ብዙ ችግሮች አሉ ለምሳሌ ክልል ማዋቀር እና ሃገራዊ ምክክር እያለ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ ይሞክራል ነገር ግን በ አስተዳደር ስርዓቱ (Governance system) መንግስት የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሰላምን ያጸናሉ ? ወይስ ጦርነትን ነው Enable የሚያደርጉት? " ሲሉ ጠይቀዋል።
አክለውም "መንግስት በሚሰራቸው ስራዎች ያኮረፉ ወጣቶች የሚፈጠሩ ይመስለኛል ለምሳሌ የማትሪክ ፈተና እኔ በማስተምርበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ ሳይንስ ዲፓርትመንት ውስጥ ካሉ ዘጠኙ የትምህርት ክፍሎች በሦስቱ ብቻ ነው ተማሪ የገባው " ሲሉ ተናግረዋል።
"እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ወጣት ተስፋ በቆረጠበት ሁኔታ ውስጥ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን ሰው ብንጨምር ለሰላም አውድ አስተዋጽኦ አደረግን ማለት አይደል?" ብለዋል ።
ተስፋን የምንፈጥርባቸው አውዶች በGovernance (አስተዳደር) ውስጥ በሰራን ቁጥር ለእነዚህ ለምንላቸው የሰላም ልምምዶች (ሃገራዊ ምክክር)አስተዋጽኦ ያደርጉ ነበር ሲሉ አክለዋል።
ምሁራን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ችግር ፈጣሪዎች እየሆኑ ነው ተብሎ ከታዳሚ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ዶ/ር ዮናስ
"ጸረ ምሁራዊ የሆኑ ትችቶች አሁን አሁን በተለይ ከፖለቲካ መሪዎች አብዝተው ይሰማሉ። እንደ ማህበረሰብ ምሁር መወቀስ ይኖርበታል ነገር ግን ምንም እንኳን ዋና ተዋንያን ቢሆኑም የኢትዮጵያ ችግር የፓለቲካ ፓርቲዎች ፣ምሁሩ እና ማህበረሰቡ ብቻ ሳይሆን የተማረው፣ ያልተማረው፣ ሲቪል ማህበራት፣ አመራሩ ሁሉም የራሱ የሆነ ችግር ይኖርበታል" ብለዋል።
በተጨማሪም "መዋቅራዊ ችግሮች አሉብን ሁላችንንም ጠፍንጎ የያዘን አንዱ ጠመንጃ ነው የጠመንጃ እስረኛ የሆንነው ተቋም ስለሌለን ነው" ብለዋል።
ለምንድነው ጠመንጃ ይዘው ጫካ የገበት ሲሉ የጠየቁት ዶ/ር ዮናስ እነሱን የሚያሳትፍ ሰፊ የሆነ የፓለቲካ ተቋማት ስለሌለን ነው ብለዋል።
የሰላም ስራ ስንሰራ የጋራ የሆነ Framework/ፍኖተ ካርታ ያስፈልገናል የመንግስት አካላት የሚወስኑት ውሳኔ ሰላምን የሚያሰለጥን ወይም የሚያሰፋ ነው ? ወይስ ብዙ ተስፋ የቆረጡ ሰዎችን የሚያወጣ ነው? በማለት አስተዳደሩ የሰላም ፍኖተ ካርታ ቢኖረው ጥሩ እንደሆነ የፓለቲካ ምሁሩ ዶ/ር ዮናስ ምክረ ሃሳባቸውን አስቀምጠዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
"ጭብጨባ ውስጥ ባይገቡ ኖሮ የተሻለ ሚዛናዊ የፖለቲካ አውድ ይኖረን ነበር " - አቶ ደስታ ዲንቃ
በትላንትናው ዕለት የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን አራተኛ ዓመት ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ሃገራዊ የምክክር ሂደቱን ያለበትን ሁኔታ እና ያጋጠሙት ችግሮች አስመልክቶ መነሻ የውይይት ሃሳብ ቀርቧል።
ለውይይቱ መነሻ ሃሳብ ካቀረቡት መካከል የሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ስለሃገራዊ ምክክሩ እንደ ፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አብረን እየሰራን ነው ብለዋል።
ከመመስረቱ በፊት የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ቀርቦ ነበር ያሉት አቶ ደስታ "ከጅምሩ፣ ከሂደቱ እና ከሃሳቡ ወዴት እንደሚሄድ ብዙ ተስፋ የሚሰጠን አይደለም ሃሳቡ ከመጣ እና መንግሥትም ከተቀበለው ግን እናበረታታው አብረነው እንስራ"የሚል አቋም ከጥቂት የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀር ስምምነት መኖሩን ተናግረዋል።
ነገር ግን ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሰላምን ማምጣት በሚችል አኳኋን እየነዱት ነው ወይስ አይደለም? የሚል ጥያቄ ካነሳን ግን ከመገነኘት ያለፈ ሚና እየተጫወተ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።
በሃገር አቀፍ ደረጃ ያለ ግባቸው እና በየክልሉ እና ከተማ መስተዳዳደሩ ያሉ ቢሮዎቻቸው ጋር እየተናበቡ እየሰሩ እንዳልሆነ በተንቀሳቀስኩባቸው ቦታዎች ተረድቻለው ብለዋል።
አቶ ደስታ የውይይት ሃሳባቸውን ካቀረቡ በኋላ በርካታ ጥያቄዎች ከታዳሚያን ተነስቶላቸዋል።
ከተነሱላቸው ጥያቄዎች መካከልም
° የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ምሁራን ችግር ፈጣሪዎች እየሆኑ አይደለም ወይ?
° የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሃገር የጋራ አጀንዳ አላችሁ ወይ? የሚል ነበር።
የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ምሁራን ችግር ፈጣሪዎች እየሆኑ አይደለም ወይ ተብሎ ለተነሳው ጥያቄ ምላሻቸውን የሰጡት የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ "ልክ ነው (ችግር ፈጣሪዎች)ነን ከለውጡ ወዲህ አብዛኛው ፖለቲካ ፓርቲ የየራሳቸውን አጀንዳ ትተው ጭብጨባ ውስጥ ባይገቡ ኖሮ የተሻለ ሚዛናዊ የፖለቲካ አውድ ይኖረን ነበር። ነገር ግን ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲ እና መሪ አንድ ቦታ ዋለ እና ማጨብጨብ ገባ" ብለዋል።
ይህም የተሻለ የፖለቲካ ምህዳር እንዳይፈጠር እንቅፋት መሆኑን አስረድተዋል።
"የፓለቲካ ፓርቲዎች ተጠያቂነት አለባቸው ምሁራንም ህዝቡም እንደዚሁ በዋነኛነት ግን የፓለቲካ ፓርቲዎች እና ምሁራን መጫወት ያለባቸውን ሚና በእውቀት፣ በጥናት እና መርህ ላይ ተመስርተው መጫወት ሲገባቸው አልተወጡም" ብለዋል
አክለውም " የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ ስርዓት ባለፈ ቁጥር ጥያቄያቸው ባይመለስም በዛኛው ስርዓት ተጎድቻለሁ እና በዚህኛው ማካካስ አለብኝ ይላሉ ብዙ ሰዎች ወደድንም ጠላንም በተለይም በሽግግሩ አካባቢ ተፈትነው ወድቀዋል" ነው ያለት።
የጋራ አጀንዳ አላችሁ ወይ ለሚለው ጥያቄም የጋራ አጀንዳችን ሰላም ነው ብለዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
"ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይመስላል" - ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መታሰቢያ ፋውንዴሽን አራተኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ዛሬ ጥቅምት 24/2017 ዓም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።
ጉባኤው ትኩረቱን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት እና ስራ ከጀመረነት ጌዜ አንስቶ ምን ምን አብይ ጉዳዮችን አከናወነ ? ምን እንቅፋቶች ገጠሙት? ለእንቅፋቶቹስ ምን መፍትሄ ሰጠ የሚለውን ዋና የመወያያ አንጀዳ አድርጓል።
በጉባኤው ላይ የኮሚሽኑ ተወካይ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ እና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህር እና ተመራማሪ ዶ/ር ዮናስ አሽኔ ለውይይቱ መነሻ ሃሳብ አቅርበዋል።
ከውይይቱ አስቀድሞ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት ሰላም እንዴት ይምጣ የሚለው ነው ብለዋል።
"መንግስትም ሲጠየቅ ሰላም እፈልጋለሁ፣ ሽማግሌ ልክያለሁ ሞክሬያለሁ፣ ሰላም አጥተናል ሰላም እንዲሆን እመኛለሁ ይላል"
"ታጣቂ ቡድኖችም ሲጠየቁ እኛም ሰላም እንፈልጋለን ተገደን ነው ወደዚህ ነገር ውስጥ የገባነው " ይላሉ።
ስለዚህ ሁለቱም ሰላምን እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ናቸው ሰላምን እንዴት እናጸናለን የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኖብናል ኢትዮጵያ ውስጥ ብለዋል።
ይሄ የሰላም ጥያቄ ለመንግሥት እና ለተፋላሚ ወገኖች ብቻ የሚተው መሆን የለበትም ያሉ ሲሆን ተመሳሳይ የሆነ የግጭት ዓውድ ውስጥ ባለፉ ሃገሮች ልምድ መሰረት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚከተሏቸው ስልታዊ እና ተቋማዊ ሂደቶች አሉ እነዚህም የሃገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትህ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
እነዚህ ሁለት መፍትሄዎች ቀደም ብለው ተጀምረው ተግባራዊ እየሆኑ መሆኑን ተናግረው የተዓማኒነት ጥያቄ ግን እየተነሳባቸው መሆኑን አንስተዋል።
"ሂደቱ በተቻለ መጠን ሁሉን አሳታፊና ተዓማኒ እንዲሆን ይፈለጋል፤ ነገር ግን በተዓማኒነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት ተነስቶባቸዋል። ይህ አይነቱ የተዓማኒነት ጥያቄ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተነሳ ጥያቄ አይደለም ተመሳሳይ ሂደት በተከተሉ ሃገሮች በሙሉ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል" ብለዋል።
የተዓማኒነት ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ችግር ባይሆንም በቀላሉ የሚታይ ግን አይደለም ነው ያሉት።
አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ነው ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ ከችግሩ ክብደት አንጻር ላይገርም ይችላል ነገር ግን ብዙ ነገሮች እየመጡ ሲያልፉ አይተናል አሁን ያለውም ችግር ከኢትዮጵያውያኖች አቅም በላይ ነው ብዬ አላስብም ብለዋል።
@tikvahethmagazine
ምሽት 3:55 ላይ አዋሽ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።
" የዛሬውስ ያስፈራ ነበር ፤ ... በጣም ነው ያስደነገጠን ፤ ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው " የሚሉ መልዕክቶች በውስጥ የመጡ ናቸው።
ንዝረቱ አዲስ አበባም ነበር።
@tikvahethiopia
#FireAlert
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ማርያም ማዞሪያ አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ እሳት አደጋ አጋጥሟል።
ዛሬ ከቀኑ 6:38 ላይ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ከሆኑ መኖሪያ ቤቶች የተነሳው እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ የእሳት እና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋውን ለመቆጣጠር 11 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ተሰማርተዋል ተብሏል።
እሳቱ ከዚህ በኋላ ሊስፋፋ የሚችልበት እድል አለመኖሩን የጠቆሙት አቶ ንጋቱ እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ት/ቤት እንዳለ እና ወደዛ የመስፋፋት እድሉ ዜሮ መሆኑን ነግረውናል።
እሳቱ ምክንያት እስካሁን በሰው ላይ ያጋጠመ ጉዳት የለም።
ተጨማሪ ይኖረናል።
📹 AbenezerMat / #TikvahFamily
@tikvahethmagazine
ኢትዮጵያ ለዲጂታል ማጭበርበር ከተጋለጡ ሃገራት መካከል መሆኗን ጥናት አሳይቷል።
Sumsub የተሰኘ መረጃ ጠቋሚ የ103 ሀገራትን ለዲጂታል ማጭበርበር ያላቸውን ተጋላጭነት የሚያሳይ የመጀመሪያውን አለም አቀፍ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።
ጥናቱ የዲጂታል ማጭበርበር ስጋትን የሚያሳይ በ103 አገሮች ላይ የተደረገ የመጀመሪያው ጥልቅ ጥናት ነው ተብሏል።
ኢትዮጵያ ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋላጭ ተብለው ከተለዩ ሃገራት መካከል የተቀመጠች ሲሆን በሰንጠረዡ ላይም ከ 113 ሃገራት በ 99 ላይ ተቀምጣለች።
ከዲጂታል ማጭበርበር ደህንነታቸው የተጠበቁ 10 አገሮች መካከል ሲንጋፖር፣ ሉክሰምበርግ፣ ስዊዘርላንድ፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፊንላንድ፣ ስዊድን፣ አየርላንድ እና ሊቱዌኒያ ይጠቀሳሉ።
ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋላጭ የሆኑ ወይም ደህንነታቸው ውስን የሆኑ ሃገራት መካከል ኢትዮጵያ ፣ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዥያ፣ አርጀንቲና፣ ዩክሬን፣ ብራዚል፣ አልጄሪያ እና ሲሪላንካ ተጠቃሽ ናቸው ይላል ሪፖርቱ።
ጥናቱ ከቁጥሮች ይልቅ ለዲጂታል ማጭበርበር የሚያጋልጡ መንስኤዎችን በመለየት የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ በማለም የተደረገ ነው።
እስካሁን ድረስ፣ ዲጂታል ማጭበርበር በፋይናንስ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ስጋት ቢፈጥርም ስለ ማጭበርበር መጠን የሚያሳይ አጠቃላይ የሆነ ዓለም አቀፍ ትንታኔ አልነበረም።
ትንበያዎች እንደሚያሳዩት በአለም በኦንላይን የክፍያ ማጭበርበር ሳቢያ የሚደርሰው ኪሳራ ከ2023 እስከ 2028 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ362 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል ይላል።
የጥናቱ ዓላማ በዓለም ዙሪያ የኦንላይን ማጭበርበርን የሚያነሳሱትን ዋና ዋና ምክንያቶች እና ሁኔታዎች በጥልቀት በመመርመር ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ግንዛቤዎችን ለመስጠት፣ መንግስታት እና ተቆጣጣሪዎች ማጭበርበርን የሚገቱ የታለሙ እርምጃዎችን እንዲተገብሩ ለማስቻል ያለመ ነው ።
ለዲጂታል ማጭበርበር ተጋልጠው ያቃሉ? እንዴት ?ያካፍሉን!
@tikvahethmagazine
🌺ውብ የሆኑ አበባዎች ወብ ለሆናችሁ ደንበኞቻችን
🌺ለሚወዱት ፍቅረኛዎ በስጦታ ለመስጠት
🌺ለፍቅርዓመታዊ በዓሎ(Anniversary
🌺ለቀለበት ኘሮግራሞ(Engagement)
🌺 ለአራስ ጥየቃ
🌺ለሰርግ (Full package ) በተጨማሪ ለተለያየ ፕሮግራሞ አስቀድመው ደውለ ይዘዙን ያሉበት እናደርሳለን ።
🌺 ለሽያጭ ምትፈልጉ በብዛት ለመውሰድ እታች ባለው ቁጥር ይደውሉ
Contact us on -0911359234
-0954882764
/channel/bluebellgiftstore
አሐዱ ባንክ ከታክስ በፊት ብር 119.96 ሚሊዮን ብር ማትረፉን ገለፀ
አሐዱ ባንክ 3ተኛ መደበኛ የባለአክስዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን ዛሬ አከናውኗል።
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አንተነህ ሰብስቤ የባንኩን የሥራ እንቅስቃሴና የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክስዮኖች አቅርበዋል፡፡
የባንኩ ሪፖርት ምን ይመስላል ?
- ባንኩ ከታክስ በፊት ብር 119.96 ሚሊዮን ትርፍ ማስመዝገቡን ገልጿል።
- ባንኩን የቅርንጫፍ ተደራሽነት ወደ 104 ከፍ ማድረግ ችያለው ያለ ሲሆን የደንበኞች ቁጥርን 704,000 በማድረስ የተቀማጭ ሃብት መጠኑ ብር 4.6 ቢሊዮን መድረሱን አሳውቋል።
- በውጭ ምንዛሪ ረገድ 80.1 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማሰባሰብ መቻሉን ሲጠቀስ በዚህ በጀት ዓመት በባንኩ የተሰጠ የብድር መጠን ብር 1.7 ቢሊዮን ደርሷል።
- የባንኩ አጠቃላይ ሃብት ብር 6.26 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ የባንኩ የተፈረመ የካፒታል መጠን ብር 1.4 ቢሊዮን ነው። አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታል መጠን ደግሞ ወደ ብር 1.03 ቢሊዮን ማድረስ መቻሉ ተነግሯል።
አቶ አንተነህ እንደገለፁት የባንኩ ዘርፍ ተለዋዋጭና ጥብቅ በሆኑ መመሪያዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ ለማሳያነት በነሐሴ 2016 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የናረውን የዋጋ ግሽበት ለመቆጣጠር በማለም፣ የንግድ ባንኮች በሚያበድሩት ብድር ላይ ጣርያ ማስቀመጡን አስታውሰዋል፡፡
ይህ ፓሊሲ የንግድ ባንኮች በሚያበድሩት ብድር ላይ ጣርያ ማስቀመጡን እና ፓሊሲው አዳዲስ ባንኮችን በከፍተኛ ሁኔታ ገቢ ከሚያስገኝላቸው የብድር አገልግሎት ስለሚገድብ፣ በባንኮቹ አፈጻጸም እና በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንዲሁም በሀብት ማንቀሳቀስ አቅም ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ እንደነበር ጠቅሰዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
"እኛ ተጠቃሚ ነን አንልም ሚጠቀመው ሌላ አካል ነው" ቡና አምራች አርሶአደሮች
በሲዳማ ክልል 170 ሺህ ሄክታር በቡና የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 143 ሺህ ሄክታሩ ምርት የሚሰጥ ነው ከዛ 159 ሺህ ቶን ይጠበቃል። አጠቃላይ 401 ሺህ ቡና አምራች የሆነ አርሶ አደርም በክልሉ በዚሁ ዘርፍ ተሰማርቶ ይገኛል።
ሆኖም ቡና አምራች አርሶአደሮች ከተጠቃሚነት አንጻር ቅሬታ ሲያቀርቡ ይደመጣል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ቡናን የሚያመርቱ አርሷደሮችን ጠይቋል።
ቡና አምራች አርሷደሮች ምን አሉ?
የቡና ተክል ተክለን ፍሬ ለማግኘት ከ3-5 ዓመት እንደሚፈጅባቸው የነገሩን አንድ አርሶአደር፥ ቡና በማምረት ውስጥ ያለው ድካም ቀላል እንዳልሆነና ነገር ግን ፍሬው ሲታይ ድካሙ ሁሉ እንደሚጠፋ ይገልጻሉ።
"ሆኖም ለገቢያ ሲወጣ የሚቀርብበት የሽያጭ ዋጋ ልብ ሰባሪ ነው" ሲሉ ነው የተናገሩት። "ልክ ካመረትን በኋላ ለነጋዴዎች ነው ምናስረክበው ለመሀበራት ሚያስረክቡም አሉ። አምና መጨረሻው 30 ብር ነበር ዘንድሮ 35 ብር ነበር የጀመረው አሁን 45 ብር ደርሷል በኪሎ ይህ ደሞ ከልፋታችን አንጻር በጣም የወረደ ሂሳብ ነው" ሲሉ ያስረዳሉ።
"እኛ ተጠቃሚ ነን አንልም ሚጠቀመው ሌላ አካል ነው (በስም ያልገለጿቸው) እንደውም አንዳንዴ መሬቱን ሽጠን ወደሌላ ዘርፍ እንግባ ብለንም እናስባለን፣ በዚህ ሰዓት ቡና ብቻ አምርቼ ኖራለው ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።" ሲሉም ጉዳቱን ያነሳሉ።
"በአሁን ገበያ አንድ ሰራተኛ ቡና ሊለቅም እንኳን ሚገባ በ120 ብር ነው ሚሰራው አሁን ላይ የሚሸጠው በ 45 ብር ነው ምናልባት 10 ሰው ሊለቅም ከገባ ገንዘቡ ለዛ ብቻ ነው ሚውለው ማለት ነው። እንደውም አምና ለሰራተኛ ብቻ ሰጥተን ነው የገባነው ዘንድሮም ያው ነው።" በማለት ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።
ለመሆኑ ዋጋውን የሚወስነው ማነው ?
"ዋጋውን እራሳቸው ይወስናሉ እኛ ማን እንደሚወስን የምናውቀው ነገር የለም በዚህ ያህል ተከፈተ ሲባል ነው የምናውቀው ህብረቱም በዚህ ዋጋ ከፈተ ሲባል ነው ምንሰማው፣ ምናልባት ባለሀብቱ አንድ ብር እንኳን አሳልፎ ከገዛ እንኳን ያንን ባለሀብት ተረባርበው እንዴት እንዲህ አደረክ ብለው ወዲያው ይጣሉታል የትኛው አካል እንደዚህ እንደሚያደርግ ግን አናውቅም።" ሲሉ ይናገራሉ።
አክለውም፥ "እነሱ እኮ (ቡናውን የሚረከቡት ለማለት ነው) ስራውን በጀመሩ ሦስት እና አራት ዓመት ነው በብልጽግና ማማ ላይ የሚወጡት በጣም አልፈው ነው ሚሄዱት፤ አርሷደሩ እንደለፋ አላገኘም ባለስልጣናቱም ጭምር በእኛ ዘንድ ይታማሉም" ብለውናል።
"የሚመለከተው አካል ቢደርስልን እየተንገዳገድን ነው ወደ መውደቅ እየደረስን ነው ታች ተወርዶ ምን እየተካሄደ ነው ሚለውን አይቶ የቡናን ነገር ቢያይልን የዋጋውን ነገር ቢመለከትልን" ሲሉም ጠይቀዋል።
"ቡናችን ለአርሷደሩ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚጠቅም ነገር ነው ህብረተሰቡ በዋጋ ማነስ ምክንያት ወደሌላ ምርት ፊቱን ካዞረ ጉዳቱ እንደ ሀገር ስለሆነ የገቢ ምንጭም ስለሚቀንስ መንግስት አርሷደሩን ወርዶ ቢመለከት ቢያወያዩ አርሷደሩ እንዳይጎዳ ቢያደርግ መልካም ነው" ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በጉዳዩ ላይ የክልሉ ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣንን ጠይቀናል ምላሹን የምናቀርብ ይሆናል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
ሮያል ሆምስ ሪል እስቴት
በሴራሚክ አቅርቦት የሚታወቀው አንጋፋው ሮያል ሴራሚክስ ሮያል ሆምስ ሪል አስቴትን ይዞሎት ቀርቧል ።
በመካኒሳ ጀርመን አደባባይ ግንባታ ደረጃቸው 70% የደረሱ አፓርትመንቶች በጥራት ገንብቶ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በካሬ 70,000 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ ይሎታል!
ኮምፓዉንዳችን ያካተተው ጂም፣ስፓ፣ ሱፐርማርኬት፣የህፃናት ማቆያ፣አረንጓዴ ስፍራ፣የህፃናት መጫወቻ ስፍራ፣ሰገነት አና በቂ የሆነ የመኪና መቆምያ።
ለበለጠ መረጃ በ 0930627256 ወይም 0911005545 ይደውሉልን ።
አውስትራሊያ ከ16 አመት በታች የሆኑ ህጻናትን ከማህበራዊ ሚዲያ የሚያግድ ህግ አወጣች።
የአውስትራሊያ መንግስት በአለም ለመጀመሪያ ጊዜ ከ16 አመት በታች የሆኑ ህጻናትን ከማህበራዊ ሚዲያ የሚያግድ ረቂቅ ህግ አውጥቻለሁ አለ።
የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኔዝ ረቂቁ በሚቀጥለው ሳምንት ለፓርላማ እንደሚቀርብ የገለፁ ሲሆን፤ ህጉ በአውስትራሊያ ህጻናት ላይ የማህበራዊ ሚዲያ እያደረሰ ያለውን "ጉዳት" ለመከላከል ያለመ ነው ብለዋል።
ረቂቅ ህጉ ለፓርላማ ቀርቦ ተገምግሞ ከፀደቀ፤ ከ12 ወራት በኋላ ተግባራዊ ይሆናል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውስትራሊያ እናቶች እና አባቶች ለልጆቻቸው ደህንነት እየተጨነቁ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የአውስትራሊያ መንግስት የወላጆች ጭንቀት በመረዳት ይህንን ህግ ማውጣቱን ተናግረዋል።
በአተገባበር ላይ ዝርዝር ጉዳዮች ገና ለክርክር የሚቀርቡ ቢሆንም እገዳው አሁን ላይ ማህበራዊ ሚዲያ እየተጠቀሙ ባሉ ወጣቶች ላይ አይተገበርም።
ከወላጆቻቸው ፈቃድ ያገኙ ልጆች የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ለመሆን የእድሜ ገደብ አይኖርባቸውም ተብሏል።
ህጉን ተላልፈው በሚገኙ በተጠቃሚዎች ላይ ምንም አይነት ቅጣት እንደማይኖር ሲገለፅ የህጉ አስፈፃሚ አካል የአውስትራሊያ የኦንላይን ደህንነት ተቆጣጣሪ ኮሚሽነር ይሆናል ተብሏል።
የወጣውን ህግ ተከትሎ የአገሪቱ ባለሙያዎች የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች የታዳጊዎችን አእምሮአዊ ጤንነት ሊጎዱ እንደሚችሉ ቢስማሙም፣ በሌላ ወገን ያሉ ተከራካሪዎች " ህጉ ሁሉንም የትስስር ገጾችን በአንድ ላይ ህገ ወጥ ማድረጉ ልክ አይደለም" በማለት አልደገፉትም።
የአገሪቱ የህጻናት መብት ተሟጋቾች ህጉ ላይ ትችት ስንዝረዋል። ህጉ ታዳጊዎችን እንደ ቲክ ቶክ፣ ኢንስታግራም እና ፌስቡክ ላሉ የትስስር ገጾች ያላቸውን ተጋላጭነት የሚቀንስ ቢሆንም፤ እገዳው ታዳጊዎች ውስብስብና አስቸጋሪ የዲጂታል አማራጮችን እንዴት ስልታዊ በሆነ መንገድ መጠቀም እንደሚችሉ አያስተምርም ተብሏል።
ሌሎች የዚህ ህግ ደጋፊዎች ህጻናትን ከዲጂታል ጥቃቶች፤ ከጎጂ እና የተሳሳቱ መረጃዎች፣ እንዲሁም ሌሎች ማህበራዊ ጫናዎች ለመጠበቅ ክልከላዎች ያስፈልጋሉ በማለት ለአውስትራሊያ መንግስት ተማፅኖ አቅርበዋል።
ቀደም ሲል በአውሮፓ ህብረት አባል አገራትን ጨምሮ የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ለመገደብ የተደረጉ ሙከራዎች በአብዛኛው አልተሳኩም። በተቃራኒው ከቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ትችትን አስተናግደዋል።
ባለፈው ወር ከ100 በላይ ምሁራን እና በ20 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተፈርሞ ለመንግስት በተላከው ደብዳቤ የአውስትራሊያ መንግስት በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የደህንነት መለኪያ መስፈርቶችን (safty standard) እንዲያወጡ ጠይቀው ነበር።
በተጨማሪም የኦንላይን መድረኮችን ለመቆጣጠር የተነደፉት ፖሊሲዎች ህጻናት የማህበራዊ ሚዲያን ቢጠቀሙም ደህንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀመ እንዲኖራቸው ሊያደርግ እንደሚገባ ባላሙያዎች ምክር ለግሰዋል።
Source : BBC
@tikvahethmagazine
ሮያል ሆምስ ሪል እስቴት
በሴራሚክ አቅርቦት የሚታወቀው አንጋፋው ሮያል ሴራሚክስ ሮያል ሆምስ ሪል አስቴትን ይዞሎት ቀርቧል ።
በመካኒሳ ጀርመን አደባባይ ግንባታ ደረጃቸው 70% የደረሱ አፓርትመንቶች በጥራት ገንብቶ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በካሬ 70,000 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ ይሎታል!
ኮምፓዉንዳችን ያካተተው ጂም፣ስፓ፣ ሱፐርማርኬት፣የህፃናት ማቆያ፣አረንጓዴ ስፍራ፣የህፃናት መጫወቻ ስፍራ፣ሰገነት አና በቂ የሆነ የመኪና መቆምያ።
ለበለጠ መረጃ በ 0930627256 ወይም 0911005545 ይደውሉልን ።
" በመጪዎቹ ወራት በቆላማው የሶማሌ፣ የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ድርቅ ይከሰታል " - ዩኒሴፍ
በኢትዮጵያ በመጪዎቹ ወራት በቆላማው የሶማሌ፣ የኦሮሚያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች "ላ ኒና" በተሰኘው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ድርቅ እንደሚከሰት ዩኒሴፍ ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።
"ላኒ-ና" ከጥቅምት እስከ ታህሳስ ባለው የዝናብ ወቅት ድርቅ እንደሚያመጣ ይጠበቃል ያለው ሪፖርቱ በተጠቀሱት አካባቢዎች ከአማካይ በታች ዝናብ እንደሚዘንብ ተንብዪዋል።
ይህም ሁኔታ የውሃ እና የግጦሽ አቅርቦት ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር፣ የምግብ ዋስትናን እንደሚያባብስ እና እንደ ኮሌራ እና የኩፍኝ ወረርሽኝ ያሉ የህዝብ ጤና ስጋቶችን እንደሚባባሱ ሪፖርቱ አመልክቷል።
በተቃራኒው የመስከረም-ጥቅምት የመኸር ወቅት፣ በመላ ሀገሪቱ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች አጣዳፊ የምግብ ዋስትና እጦትን ቀስ በቀስ እያሻሻለ ነው ተብሏል።
ዩኒሴፍ በመላ ሀገሪቱ ከነሐሴ እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ከ94,000 በላይ በከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ለተቸገሩ ህጻናት ድጋፍ መስጠቱ ተመላክቷል።
ዩኒሴፍ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦትን ለመደገፍ 535 ሚሊዮን ዶላር እንደሚፈልግ ያመለከተው ሪፖርቱ እስከ መስከረም ባለው ጊዜ ያገኘው የገንዘብ ድጋፍ 116 ሚሊዮን ዶላር ነው። ይህም 78 በመቶ የገንዘብ ድጋፍ እጥረት እንዳለበት በሪፖርቱ ገልጿል።
@tikvahethmagazine
#Airbus_A350_1000
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን የኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን መረከቡ ይታወሳል።
አውሮፕላኑ በትላንትናው ዕለት ከሰዓት በኋላ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የስታር አሊያንስ አባላት ከሆኑ ሦስት (የግብጽ እና የደቡብ አፍሪካ)አየር መንገዶች አንዱ ነው።
በአፍሪካ በአይነቱ የመጀመሪያው የሆነው የኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ፣ ለንደን፣ ፓሪስ እና ፍራንክፈርትን ጨምሮ ወደ ሌሎችም ቁልፍ መዳረሻዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሳደግ ያስችለዋል ተብሏል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ሰዓት የ ኤ350 ቤተሰብ የሆኑ 21 አውሮፕላኖች ባለቤት ነው።
በሚቀጥሉት አመታት 11 A350-900 እና ሶስት ተጨማሪ A350-1000 አውሮፕላኖችን ጨምሮ 14 ተጨማሪ ኤ350 አውሮፕላኖችን የአየር መንገዱ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑን ለመግዛት ያዘዘው እ.ኤ.አ በ 2022 ሲሆን የ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን በአጠቃላይ 395 መንገደኞችን (46 ቢዝነስ እና 349 የኢኮኖሚ ደረጃ መቀመጫዎች) ማስተናገድ ይችላል።
አውሮፕላኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድን የመንገደኞችን የማጓጓዝ አቅም ያሳድጋል ተብሎለታል።
A350 በዓለም ላይ በጣም ዘመናዊ እና ቀልጣፋ የሆነ ባለ ግዙፍ አካል አውሮፕላን ሲሆን እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እና የኤሮዳይናሚክስን ውጤቶችን ያካተተ ነው።
ከቀድሞ የአውሮፕላን ስሪቶች ጋር ሲነጻጸር በበረራ ወቅት የሚፈጥረው ድምጽ 50 በመቶ ያነሰ መሆኑ ተገልጿል።
አውሮፕላኑ የአዲሱ ትውልድ ዘመናዊ የሮልስ ሮይስ ትሬንት XWB ሞተሮች የተገጠሙለት ሲሆን ቀላል ክብደት ካላቸው ቁሳቁሶች የተዋቀረ በመሆኑ ነዳጅ ቆጣቢ ከሆኑ አውሮፕላኖች አንዱ ያደርጉታል።
እ.ኤ.አ. 2024 መጨረሻ ወር ድረስ 1,340 ኤ350 ስሪት አውሮፕላኖች በአለም አቀፍ ደረጃ በ60 ደንበኞች የታዘዙ ሲሆን፣ይህም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ውጤታማ አውሮፕላን መሆኑን አመላካች ነው ተብሎለታል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ባሉት 147 አውሮፕላኖች 139 ዓለም አቀፍ እና 22 የሀገር ውስጥ የበረራ መዳረሻዎችን እየሸፈነ ይገኛል፡፡
አየር መንገዱ በትላንትናው ዕለት የተቀበለው አውሮፕላን መቼ ሥራ እንደሚጀምር እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር የለም።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
ሮያል ሆምስ ሪል እስቴት
በሴራሚክ አቅርቦት የሚታወቀው አንጋፋው ሮያል ሴራሚክስ ሮያል ሆምስ ሪል አስቴትን ይዞሎት ቀርቧል ።
በመካኒሳ ጀርመን አደባባይ ግንባታ ደረጃቸው 70% የደረሱ አፓርትመንቶች በጥራት ገንብቶ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በካሬ 70,000 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ ይሎታል!
ኮምፓዉንዳችን ያካተተው ጂም፣ስፓ፣ ሱፐርማርኬት፣የህፃናት ማቆያ፣አረንጓዴ ስፍራ፣የህፃናት መጫወቻ ስፍራ፣ሰገነት አና በቂ የሆነ የመኪና መቆምያ።
ለበለጠ መረጃ በ 0930627256 ወይም 0911005545 ይደውሉልን ።
"የሽግግር ፍትህ የሀገራዊ ምክክሩ ውጤት ነው ብለን ነው የምናምነው አሁን ከሃገራዊ ምክክሩ ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም።" - ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወ/ማርያም
የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን አራተኛ ዓመት ጉባኤውን ባካሄደበት በተካሄደው ውይይት ላይ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ መላኩ ወ/ማርያም ተሳትፈው ነበር።
ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም በዕለቱ ምን ሀሳብ አነሱ?
° በኢትዮጵያ እጅግ መሰረታዊ በሚባሉ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የለንም ካልተግባባን እና እንዴት እንግባባ ካልን ልንግባባ የምንችለው በምክክር ነው ኮሚሽኑም የተቋቋመው ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ነው።
° ምክክሩን የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ የሚሳተፍበት ነው የሚል አቋም ስላላለን የጀመርነው ከወረዳ ነው።
° በዙ ጊዜ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚታወቀው በቁጥር ነው እንጂ በተሳትፎ ብዙም አይደለም የኢትዮጵያ ባለቤትም ሆኖ አያውቅም ይህ ሂደት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሂደት ነው።
° ከትግራይ እና አማራ አካባቢዎች በስተቀር በተሳታፊ ልየታ በእኛ እይታ አጥጋቢ ሊባል በሚችል መልኩ ተከናውኗል።
° በተሳታፊ ልየታው 8,099 ተባባሪ አካላት እና 105 ሺ የሚሆኑ ተሳታፊዎች ተካፍለውበታል።
° ኦሮሚያ ላይ አጀንዳ ማሰባሰብ በቀጣይ ይጀመራል ደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የአጀንዳ ማሰባሰብ እየተካሄደ ነው።
° ቀጣዩ የሚሆነው ኦሮሚያ፣አማራ ፣ትግራይ እና ከዲያስፖራው ማህበረሰብ አጀንዳ የመሰብሰብ ሂደት ነው።
° ከመነሻው ጀምሮ በተቻለ መጠን ሁሉን ያሳተፈ እንዲሆን ጥረት አድርገናል።
° ስራችንን ጨርሰን ለማጠናቀቅ በያዝነው የሦስት ዓመት እቅድ እንዳንሰራ በተወሰነ መጠን ተጽዕኖ ያሳደረብን እዚህም እዚያም ያለው የጸጥታ ችግር ነው።
° እስካሁን ተጽዕኖ ያሳደረብን አካል የለም መንግስትንም የጠራነው እኛው ራሳችን ነን የመንግስት አቋም ምንድነው? የሚለውን ለመጠየቅ እና ተፋላሚ ወገኖች ፈቃደኛ ሆነው ለመደራደር ቢመጡ ደህንነታቸው የሚረጋገጠው እንዴት ነው? የሚለውን ለመጠየቅ ነበር በዚህም አወንታዊ ምላሽ አግኝተናል።
° የሽግግር ፍትህ የሀገራዊ ምክክሩ ውጤት ነው ብለን ነው የምናምነው አሁን ከሃገራዊ ምክክሩ ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም።
° ምክክሩ ተበዳዮችም ጭምር የሚሳተፉበት በመሆኑ ተጠያቂዎች (በዳዮች)ማን እንደሆኑ ከህዝብ ነው የምናገኘው ።
° የሽግግር ፍትህ መነሻ ሃሳብ በዳዮች፣ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ ሰዎች አሉ የሚል ነው። እነዚህ ሰዎች እንዴት ነጥረው ይወጣሉ የሚለው የሚመለሰው በምክክር ሂደቱ ነው ከዚያ በኋላ ምን ይሁኑ የሚለው ጥይቄ ለህዝብ መተው አለበት ብለዋል።
ምን ያህል ገለልተኛ ናችሁ ተብሎ ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ኮሚሽነር መላኩ "ምን ያህል ገለልተኛ ናቸው የሚለውን የሚያረጋግጥልን ህዝቡ ነው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
አክለውም "እስካሁን ገለልተኛ አይደላችሁም የሚሉ ወገኖች እንዳሉ እናውቃለን በምን መረጃ ላይ ተመስርተው ይህንን እንዳሉ የደረሰን መረጃ የለም እኛ እስከምናውቀው ነጻ እና ገለልተኛ ነን። ይህን በፍጹም ለድርድር የምናቀርበው አይደለም" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
"አንድም በማስረጃ የተደገፈ እንደዚህ አድርጋቹሃል የሚል ደርሶን አያውቅም ከአሉባልታ በቀር"
"ወቀሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አንድ መልካም የሆነ ባህል ተወስዷል ይሄ መሆን የለበትም"
"እኛ ስራችንን ክፍት አድርገናል በግልጽነት ነው የምንሰራው ማንም አያገባህም የምንለው አካል የለም" ያሉ ሲሆን ሃላፊነት የሚሰማው ሁሉ ሊያግዝ ይገባዋል ብለዋል።
"እስከዛሬ ድረስ የነበረው ሁሉንም ነገር በጠብመንጃ አፈሙዝ የመፍታት ባህል ነው ያለን " ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የምክክር ሂደቱ አዲስ የፖለቲካ ባህል የመገንባት አካል መሆኑን ተናግረዋል።
በምክክሩ ሂደት አንሳተፍም ያሉ ፓርቲዎችን በተመለከተ ዝምብለን አልተመለከትንም "በቻልነው መጠን በግልም በቡድንም ለማነጋገር እየሞከርን ነው። ከነሱ ዘንድ ይሁንታ ማጣት ነው እንጂ ኮሚሽኑ ጥረት ሳያደርግ ቀርቶ አይደለም " ብለዋል።
" ከዛ በተጨማሪም ሸኔንም ቢሆን፤ ፋኖንም ቢሆን በራሳችን ባለን መንገድ፤ በራሳችን ባለን አግባብ ኢንጌጅ እያደረግን ነው። ዝርዝሩን ነገር እዚህ ጋር መናገር አስፈላጊ አይደለም " ሲሉ ተናግረዋል።
ሁሉን በምክክር ሂደቱ ላይ እንዴት ማሳተፍ ይቻላል? ከዚህ ምክክር ሂደትስ ህዝቡ የበላይ ማድረግ ይቻላል ወይ? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱም።
"ህዝቡን ሁሉ ማሳተፍ የሚቻለው በውክልና ነው" ብለዋል።
"ይህ የሚቻለው ራሱ ህዝቡ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች በሚሰሩት ስራ ነው ይህንን ሂደት በመደገፍ እና በጋራ በመስራት ህዝቡ የበላይ እንዲሆን መጣር አለብን ይህ የግል እምነቴ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
#TikvahEthiopia
@tikvahethmagazine
ሮያል ሆምስ ሪል እስቴት
በሴራሚክ አቅርቦት የሚታወቀው አንጋፋው ሮያል ሴራሚክስ ሮያል ሆምስ ሪል አስቴትን ይዞሎት ቀርቧል ።
በመካኒሳ ጀርመን አደባባይ ግንባታ ደረጃቸው 70% የደረሱ አፓርትመንቶች በጥራት ገንብቶ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በካሬ 70,000 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ ይሎታል!
ኮምፓዉንዳችን ያካተተው ጂም፣ስፓ፣ ሱፐርማርኬት፣የህፃናት ማቆያ፣አረንጓዴ ስፍራ፣የህፃናት መጫወቻ ስፍራ፣ሰገነት አና በቂ የሆነ የመኪና መቆምያ።
ለበለጠ መረጃ በ 0930627256 ወይም 0911005545 ይደውሉልን ።
📸ፎቶ: የፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መታሰቢያ ፋውንዴሽን አራተኛ ዓመታዊ ጉባኤ ዛሬ ተካሂዷል።
የዚህ ዓመት ጉባኤ አቢይ መርሕ በኢትዮጵያ የሰላም ሁኔታና በሃገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ ያደረገ ነበር።
በኢትዮጵያ ሰላም እንዲሰፍን እና በሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማነት ምን መደረግ አለበት? የሚለው ጥያቄ የጉባኤው ዋና መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ ሆኖ ተነስቷል።
በዕለቱ የተነሱ ሀሳቦች ወደ እናንተ እናደርሳለን።
@tikvahethmagazine
#Update
በቦሌ ክፍለ ከተማ ማርያም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ አጋጥሞ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።
የአደጋው መንስኤ እና የውድመት መጠኑ እየተጣራ መሆኑን አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።
አደጋው በቆርቆሮ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ የሚባል ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል።
የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 12 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች እና ሁለት የውኃ ቦቴ ከ70 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጋር መሰማራታቸውንም ተነግሯል።
@tikvahethmagazine
ሮያል ሆምስ ሪል እስቴት
በሴራሚክ አቅርቦት የሚታወቀው አንጋፋው ሮያል ሴራሚክስ ሮያል ሆምስ ሪል አስቴትን ይዞሎት ቀርቧል ።
በመካኒሳ ጀርመን አደባባይ ግንባታ ደረጃቸው 70% የደረሱ አፓርትመንቶች በጥራት ገንብቶ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በካሬ 70,000 ብር ጀምሮ የቤት ባለቤት ይሁኑ ይሎታል!
ኮምፓዉንዳችን ያካተተው ጂም፣ስፓ፣ ሱፐርማርኬት፣የህፃናት ማቆያ፣አረንጓዴ ስፍራ፣የህፃናት መጫወቻ ስፍራ፣ሰገነት አና በቂ የሆነ የመኪና መቆምያ።
ለበለጠ መረጃ በ 0930627256 ወይም 0911005545 ይደውሉልን ።