National lottery
የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ስለወጣልኝ በድንገት--- ብድሩን ተውኩት!
ሙሉ ስሙ ወጣት ክብር ሰው ገብሬ ይባላል ነዋሪነቱ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ነው፡፡ የሚተዳደረውም አሮጌ ልብሶችን በመስፋት ሲሆን ከስራውም በተጓዳኝ አድማስ ዲጂታል ሎተሪን በስልኩ በተደጋጋሚ ይሞክራል ሎተሪም ዘወትር ለሚሞክራት አታሳፍርምና በ5ኛው ዙር በላከው Text 605A የ2ኛው ዕጣ ብር 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) እድለኛ ሆኗል፡፡
እኛም በገንዘቡ ምን አሰብክ ብለን ላነሳንለት ጥያቄ በፈገግታ እየታጀበ አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ከመሞከሬ በፊት ከአማራ ማይክሮ ፋይናንስ ብድር ለመበደር አስፈላጊውን መረጃ ሞልቼ ገንዘቡን ለመቀበል ሂደት ላይ ነበርኩ፤ ነገር ግን አሁን እድሜ ለብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የ800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) እድለኛ ስለሆንኩ የብድሩን ውሌን አቋርጫለሁ፡፡ ምክንያቱም ያለ ወለድ 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ ብር) እግዚአብሔር ሰጥቶኛልና ብሔራዊ ሎተሪን አመሰግናለሁ፡፡ በማለት ደስታውን ገልጾልናል፡፡
ውድ ደንበኞቻችን በማሕበራዊ የትስስር ገፃችን ከቀረቡ ገንቢ አስተያየቶች መካከል ለዛሬው ማብራሪያ እና መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች ከዚህ እንደሚከለተው ቀርቧል፡፡ ለአስተያየታችሁ ምስጋናችን ይድረስ እንላለን፡፡
የመጀመሪያው ጥያቄ 9695 ነፃ የስልክ መስመር ያለመነሳቱን የተመለከተ እና የመረጥነውን ፊደል ልከን(ቴክስት አድርገን) የእጣ ቁጥር አይደርሰንም የሚሉት ጥያቄዎች መካከል ናቸው
1. ውድ ደንበኞቻቸን በሰጣችሁን አስተያየት መሰረት 9695 ነፃ የስልክ መስመራችን ዘወትር በስራ ሰአት እንዲነሱና ለጥያቄዎቻችሁ ምላሽ እንዲሰጡ፤ እንዲሁም አስተያየታችሁን እንዲቀበሉ በተደራጀ መልኩ በማስተካከል ላይ እንገኛለን፡፡
2. የመረጥነውን ፊደል ወደ 605 ልከን(ቴክስት አድርገን) የእጣ ቁጥር አይደርሰን ለሚለው ጥያቄያችሁ
መልስ፡-የመረጣችሁት ፊደል ልካችሁ(ቴክስት አድርጋችሁ) የእጣ ቁጥር ወዲያዉኑ ሊደርሳችሁ ይገባል ይሁንና በሰርቨር መጨናነቅ ምክንያት ሊዘገይ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም እንኳን ከቆይታ በኋላ የእድል ቁጥራችሁ እንደሚደርሳችሁ እንገልፃለን፡፡
የእድል ቁጥር ፈፅሞ የማይደርሳችሁ ወይም ያልደረሳችሁ ከሆነ በነፃ የስልክ መስመራችን 9695 ላይ በመደወል ማሳወቅ የምትችሉ ሲሆን የእድል ቁጥራችሁ እንዲደርሳችሁ ይደረጋል፡፡በተጨማሪም በ605 ቴክስት በምንልክበት ወቅት ከጥቅል ዳታ የማይወስድ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡
እናመሰግናለን፡፡
በልዩ ዕድል ሎተሪ ከ1ኛ ዕጣ የ6ሚልየን ብር እድለኛ ወጣት ተመስገን ዘካሪያስ ቼኩን ተረከበ፡፡
በ2015ዓ.ም የተዘጋጀው የልዩ ዕድል ሎተሪ የ1ኛ ዕጣ ዕድለኛ የሆነውና በጀብሎ ስራ የሚተዳደረው ወጣት ተመስገን ዘካሪያስ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ሲሆን በደረሰው ገንዘብ ቤት ለመስራት ማቀዱን ገልፆልናል፡፡
ታህሳስ 25 ቀን 2015 የወጣው የአድማስ ድጅታል ሎተሪ ዕድለኞች ሽልማታቸውን ከ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እጅ ተረከበዋል ፡፡
Читать полностью…በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2015 በሕዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡ የአሸናፊ ቁጥሮችም እንደሚከተለው ሆነዋል ፡፡
በተጨማሪም የዕጣ አወጣጡ ሂደት ዛሬ ምሽት / ታህሳስ 25 2015/ 3፡00 ላይ በዋልታ ቴሌቪዥን መመልከታ ይችላሉ ፡፡
አድማስ ዲጂታል ሎተሪ !
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በወረቀት ሎተሪዎች ከሚያካይደው የሎተሪ ጨዋታ በተጨማሪ አድማስ የተሰኘ ዘመናዊ የድጅታል ሎተሪ በመጀመር እና ለህብረተሰቡ አማራጭ የዕድል ሙከራ ማቅረብና መሸለም ከጀመረ እነሆ አራት ወራትን አስቆጥሯል፡፡
የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ ስርዓት ማስጀመር ቀልጣፋና በአጭር ጊዜ ለሁሉም ሰው በሞባይል ስልክ አማካኝነት ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑ እሙን ነው፡፡
ሀምሌ 8/2014ዓ.ም ጅማሬው የተበሰረው የዲጅታል ሎተሪ የአስተዳደሩ ደንበኞችን በሰፊውና በቀላሉ ለመድረስ ያስቻለ ሲሆን በየወሩ የሚወጣው አድማስ ዲጂታል ሎተሪ የመጀመሪያው ዕጣው ነሐሴ 13 /2014ዓ.ም በማውጣት እስካሁን ለ4 ተከታታይ ወራት ዕጣውን በማውጣት በአንደኛው ዕጣ 1.5ሚልዮን ብር እና ሌሎች በርካታ ሽልማቶ ከተንበሸበሹ እድለኞች መካከል ፡-
ነሐሴ 13 /2014ዓ.ም በወጣው ፡-
1.አቶ ዳንኤል ሰለሞን አድማስ ዲጅታል ሎተሪ በ1 ኛ እጣ የ1.5ሚልየን ብር እድለኛ/ጌድዮ ዞን ወናጎ /
2.ወ/ሮ ፋጡማ አባተማም አድማስ ዲጅታል ሎተሪ በ2ኛ እጣ የ800 ሺህ ብር እድለኛ /ወለቴ/
3. አቶ ዮናስ ወ/ዮሀንስ በ3ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ350 ሺህ ብር እድለኛ/አርሲ ነገሌ/
መስከረም 11 የወጣው አድማስ ዲጅታል ሎተሪ እድለኞች ፡-
1.አቶ አገኘው አምባቸው በ1 ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ1.5ሚልየን ብር እድለኛ /ባህርዳር/
2.አቶ ወርቅነህ መንክር በ2ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ800 ሺህ ብር እድለኛ /ዝዋይ/
3.አቶ አበበ ግዛው በ3ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ350 ሺህ ብር እድለኛ/ሂርና/
2.ጥቅምት 22/2015ዓ.ም በወጣው፡-
1.እምሻው ሙሉጌ ታ በ1 ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ1.5ሚልየን ብር እድለኛ /አሰላ/
3. .ኮ/ልአሰፋ አያሌው በ2ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ800 ሺህ ብር እድለኛ /አ.አ/
3.ወ/ሮ ግዛው በ3ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ350 ሺህ ብር እድለኛ/ሆሳህና/
ውድ የቴሌግራም ተከታታዮቻችን ለ4ኛ ጊዜ 1.5 ሚልየን ብር እና ሌሎች በርከታ ሽልማቶች የሚያንበሸብሸው የአድማስ ዲግታል ሎተሪ እጣ የሚወጣው ታህሳስ 25/2015ዓ.ም በመሆኑ ደጋግማችሁ እድላችሁን እንድትሞክሩ ስንል እናስታውቃለን፡፡
ህዳር 23 የወጣው የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ እድለኞች
1. አቶ ዮሴፍ ተርፋሳ የበ1 ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ1.5ሚልየን ብር እድለኛ/ ነቀምት/
2. መምህርት ፋንቱ ሀይሉ በ2ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ800 ሺህ ብር እድለኛ/ ሸኖ/
3. ወጣት ናርዶስ በድሉ በ3ኛ እጣ አድማስ ዲጅታል ሎተሪ የ350 ሺህ ብር እድለኛ/አዲስ አበባ/ ናቸው ፡፡
የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕጣ ቀጣይነት ያለው ሲሆን የዚህ ወር ዕጣ ታህሳስ25 ቀን 2015 የሚወጣ መሆኑን እየገለጽን በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌብር ወደ *127# በመደወል በ3ብር ከወዲሁ በመቁረጥ ዕድልዎ ይሞክሩ ፡፡
ይቁረጡ ይሸለሙ !
መልካም ዕድል !
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር
ይጠንቀቁ !!!
ብሔራዊ ሎተሪ ያዘጋጀው ሎተሪ አይደለም
ቤት ከነሙሉ እቃ እንሸልማለን በማለት ግለሰቦች በቴሌግራም እያሰራጩት ያለው ማስታወቂያ በብሔራዊ ሎተሪ የማይታወቅ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ብሔራዊ ሎተሪ ለባለዕድለኞች አስደሳች ዜና ይዞ መጥቷል በሚል ዕጣው ጥር 30 እንደሚወጣና ቤት ከነሙሉ ዕቃ እንደሚሸልም የሚገልጸውን ይህንን ሐሰተኛ የማጭበርበሪያ ማስታወቂያ ሕብረተሰቡ የብሔራዊ ሎተሪ ያሰራጨው ማስታወቂያ አለመሆኑን ተረድቶ በዕጣው ከመሳተፍ እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡
በቴሌግራም ገፃቸው የሚሳተፈውን ህብረተሰብ ቁጥር ለማሳደግ በተቋም ስም ህብረተሰቡን የሚያጭበርበር ማስታወቂያ የሚያሰራጩትን ግለሰቦች ለህግ እንደምናቀርብ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
የብሔራዊ ሎተሪ ትክክለኛው
የፌስቡክ ገጽ ፡- Ethiopian lottery/ የኢትዮጵያ ሎተሪ/
የቴሌግራም ከ149ሺ ተከታዮች ያሉበት ሆኖ፡- National lottery administration/ ብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር/ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በልዩ ዕድል ሎተሪ 3ኛ እጣ እድለኛ ወጣት ወንድምአገኝ ዋቆ የ3ሚልየን ብር ቼክ ተረክበዋል፡፡የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪው ወጣት ወንድምአገኝ ዋቆ የባንክ ሰራተኛ ሲሆን በደረሰው ገንዘብ በንግድ ስራ ተሰማርቶ ለመስራት አቅደዋል፡፡
Читать полностью…የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕድለኞች ተሸለሙ !
1ኛ ዕጣ
የመንግስት ሰራተኛው አቶ ዮሴፍ ተርፋሳ
ከነቀምት
1,500,000 ብር
2ኛ ዕጣ
መምህርት ፋንቱ ሀይሉ
ከሸኖ
800,000 ብር
3ኛ ዕጣ
የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪ ባለሙያው
ወጣት ናርዶስ በድሉ
ከ አዲስ አበባ
350,000 ብር
4ኛ ዕጣ
የቀለም ቀቢ ባለሙያው አቶ አብዮት ዱባለ
ከአዲስ አበባ
200,000 ብር
5ኛ ዕጣ
መምህር አድባሩ ፈንታ
ከወልቂጤ
160,000 ብር
ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ/ም
ጥብቅ ማሳሰቢያ
የቨርቹዋል ጌም /Virtual Game/ የሚባለው ጨዋታ ራሱን ችሎ ፈቃድ የሚሰጥበት ሳይሆን የስፖርት ውርርድ ህጋዊ ፈቃድ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር የተሰጣቸው ድርጅቶች ከተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ጋር በማጣመር በህግ የተፈቀዱ የተወሰኑ ስፖርት ነክ ጌሞችን ብቻ የሚያካሄዱት ጨዋታ ነው፡፡
ሆኖም አንዳንድ ድርጅቶች በህግ ያልተፈቀዱትን የቨርቹዋል ጨዋታዎችን ከአስተዳደሩ የተሰጠ ፈቃድ ሳይኖራቸው፣ ደረጃውን ባልጠበቀ ሱቅ ውስጥ፣ ባልተፈቀዱ አካባቢዎች ላይ እንዲሁም በህግ ላልተፈቀደላቸው ሰዎች ሁሉ በህገጥ መንገድ እያጫወቱ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡
በመሆኑም የቨርቹዋል ጨዋታም ሆነ ሌሎች ውርርዶች/ጌሞችን ከአስተዳደሩ ህጋዊ ፈቃድ ሳያገኙ ማጫወት፣ የሚሰሩበትን ቅርንጫፍ ለአስተዳደሩ አስቀድመው ሳያሳውቁና ደረጃውን የጠበቀ መሆኑ ሳይረጋገጥ መስራት፣ በህግ በተከለከሉ አካባቢዎች ላይ ቅርንጫፍ መክፈት፣ በህግ ያልተፈቀዱ ጨዋታዎችን ማካሄድ፣ ዕድሜያቸው ከ21 ዓመት በታች የሆኑ ወጣቶችን ማጫወት፣ ለተወራራጆች ህጋዊ ደረሰኝ ሳይቆርጡ ገንዘብ መቀበል፣ ለውርርዱ አሸናፊዎች ያለምንም ውጣ ውረድ በህጉ መሠረት ክፍያ ያለመፈፀም ህገወጥ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ድርጊት ላይ የተሰማራችሁ ግለሰቦች በአስቸኳይ ቅርንጫፉን እንዲትዘጉ እና ሥራውን እንዲታቆሙ በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
ይህንን ማስጠንቀቂያ በመተላለፍ በህገወጥ መንገድ የሚሰሩ ግለሰቦች ጉዳዩ በሚመለከተው የህግ አካላት አማካይነት ተይዘው በህግ የሚጠየቁ ከመሆኑም ሌላ ለዚህ ህገወጥ ተግባር የዋለ ንብረት በሙሉ በህግ የሚወረስ መሆኑን አውቃችሁ ከዚህ ህገወጥ ተግባር እንዲትታቀቡ እያሳሰብን ህብረተሰቡም ከላይ በተጠቀሰ መልኩ ከሚሰሩ ግለሰቦች በመጠንቀቅ ህገወጥ ጨዋታው የሚካሄድበትን ቦታና ሰዓት በመጠቆም ለህግ እንዲቀርቡ ለማድረግ እንዲቻል እንዲተባበረን እንጠይቃለን፡፡
ህገወጥ ጨዋታዎችን በጋራ በመከላከል ኃላፊነታችንን እንወጣ!!
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአድማስ ድጅታል ሎተሪ የ5ኛ ዙር በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ህዳር 23 ቀን 2015ዓ፣ም በይፋ ወጥቷል ፡፡ የወጡ ዕድለኛ የሚያደርጉ ቁጥሮች ፡-
Читать полностью…የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 006 ከህዳር 21 ቀን 2015 እኩለ ለሊት ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 22 ቀን 2015 ድረስ ገበያ ላይ ይውላል፡፡ "605" ላይ ማንኛውንም ምልክት ተጭነው ይላኩ ወይም *127# በመደወል እንዲሁም የቴሌብር መተግበርያን በመጠቀም በ3 ብር የ1.5 ሚሊዮን ብር አሸናፊ ይሁኑ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር
Читать полностью…የባህዳር ነዋሪ የሆኑት
አቶ መኮንን ሞላ በእንቁጣጣሽ ሎተሪ
ከ2ኛ ዕጣ የ4 ሚሊዮን ብር ሽልማታቸውን ተረክበዋል
/channel/national_lottery/743
Читать полностью…ጥብቅ ማሳሰቢያ
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በማህበራዊ ሚዲያዎች በተለይም በቲክቶክ የተለያዮ ግለሰቦች የሎተሪ ጨዋታ እያካሄዱ መሆኑን ደርሶበታል፡
በማህበራዊ ሚዲያዎቹ የሚካሄደው ሎተሪ ግለሰቦች እንዲያካሂዱት ፈቃድ ያልተሰጠው ህገ-ወጥ ጨዋታ ነው፡፡
በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ማቋቋሚያ ደንብ በቁጥር 160/2001 በአንቀጽ 20 በተደነገገው መሰረት ህገ-ወጥ ሎተሪ የሚያካሂድ ማንኛውም ሰው ከብር 50ሺህ እስከ 100ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮና ከ3 እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡
በማቋቋሚያ ደንቡ አንቀጽ 12 መሰረት አስተዳደሩ የገንዘብ ሎተሪዎችን ጨዋታ ማካሄድ ብቸኛ መብት አለው፡፡
በአዋጁ መሰረት አስተዳደሩ ፈቃድ ሰጥቷቸው መካሄድ የሚችሉት የዕድል ጨዋታዎች የፕሮሞሽን ሎተሪ፣ የቶምቦላ ሎተሪ፣ የኮንቪንሽናል ቢንጎ ሎተሪ እና የስፖርት ውርርድ ሎተሪዎች ናቸው፡፡
በመሆኑም የተለያዩ ግለሰቦች በተለይም በቲክቶክ የሚያካሂዷቸው ሎተሪዎች ህገ-ወጥ በመሆናቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰብን ከዚህ ድርጊታቸው የማይቆጠቡ ከሆኑ ለህግ የምናቀርባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ብሔራዊ ሎተሪ
‹‹ብሔራዊ ሎተሪ ለእኔ ለችግረኛው የደረሰና የጀመርኩትንም ስራ እንዳጠናቅቅ የረዳኝ ነው››!
**********************
የአንዳንድ ሰው ዕድል ያስገርማል እጅግም ያስደምማል አቶ ከድር ሀሰን ይባላሉ የሁለት ልጆች አባት ሲሆኑ ነዋሪነታቸው በፊቼ ከተማ ውስጥ ነው፡፡አቶ ከድር ከባለቤታቸው ጋር በመሆን በሸቀጣሸቀጥ ንግድ የሚተዳደሩ አባት ናቸው፡፡
የሎተሪ የረጅም ጊዜ ደንበኛ የሆኑት አቶ ከድር ዕድላቸውን ደጋግመው እንዲሞክሩ ባለቤታቸው በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያበረታቷቸው ገልጸውልናል፡፡
አቶ ከድር እድላቸውን በመሞከር ከአንዴም 3 ጊዜ የሎተሪ ባለ ዕድለኛ ለመሆን በቅተዋል ከዚህ በፊት በቢንጎ ሎተሪ ሁለት ጊዜ በ125,000 ብር እንዲሁም ታህሳስ 25/2015ዓ.ም በወጣው የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ 5ኛ ዕጣ የ160,000 ሺህ ብር ዕድለኛ ሆነዋል፡፡
የብሔራዊ ሎተሪ ለችግረኛ የደረሰና የጀመርኩትን ስራ እንዳጠናቅቅ የረዳኝ ነው በማለት በደረሳቸው ገንዘብ የጀመሩት የቤት ግንባታ ስራ ለማጠናቀቅ ማቀዳቸውን ገልጸውልናል፡፡
ውድ ደንበኞቻችን በማሕበራዊ የትስስር ገፃችን ከቀረቡ ገንቢ አስተያየቶች መካከል ለዛሬው ማብራሪያ እና መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች ከዚህ እንደሚከለተው ቀርቧል፡፡ ለአስተያየታችሁ ምስጋናችን ይድረስ እንላለን፡፡
የመጀመሪያው ጥያቄ 9695 ነፃ የስልክ መስመር ያለመነሳቱን የተመለከተ እና የመረጥነውን ፊደል ልከን(ቴክስት አድርገን) የእጣ ቁጥር አይደርሰንም የሚሉት ጥያቄዎች መካከል ናቸው
1. ውድ ደንበኞቻቸን በሰጣችሁን አስተያየት መሰረት 9695 ነፃ የስልክ መስመራችን ዘወትር በስራ ሰአት እንዲነሱና ለጥያቄዎቻችሁ ምላሽ እንዲሰጡ፤ እንዲሁም አስተያየታችሁን እንዲቀበሉ በተደራጀ መልኩ በማስተካከል ላይ እንገኛለን፡፡
2. የመረጥነውን ፊደል ወደ 605 ልከን(ቴክስት አድርገን) የእጣ ቁጥር አይደርሰን ለሚለው ጥያቄያችሁ
መልስ፡-የመረጣችሁት ፊደል ልካችሁ(ቴክስት አድርጋችሁ) የእጣ ቁጥር ወዲያዉኑ ሊደርሳችሁ ይገባል ይሁንና በሰርቨር መጨናነቅ ምክንያት ሊዘገይ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች ቢኖሩም እንኳን ከቆይታ በኋላ የእድል ቁጥራችሁ እንደሚደርሳችሁ እንገልፃለን፡፡
የእድል ቁጥር ፈፅሞ የማይደርሳችሁ ወይም ያልደረሳችሁ ከሆነ በነፃ የስልክ መስመራችን 9695 ላይ በመደወል ማሳወቅ የምትችሉ ሲሆን የላካችሁት ብር የሚመለስ ይሆናል፡፡
እናመሰግናለን፡፡
አድማስ ዲጂታል ሎተሪ 1.5 ሚሊዮን ብር እና ሌሎች አጓጊ ሽልማቶችን ይዞ በገበያ ላይ ዋለ! እስከ ጥር 23/2015 በቴሌብር መተግበሪያ፣ በ*127# ወይም 605 ላይ A ብለው በመላክ በ3 ብር ሚሊየነር የመሆን እድልዎን ይሞክሩ!
ኢትዮ ቴሌኮም እና የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በአጋርነት
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የገና ሎተሪ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዛሬ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም በህዝብ ፊት በይፋ የወጣ ሲሆን አሸናፊ የሚያደርጉ የወጡ የዕድል ቁጥሮችም ፡-
የ1ኛ ዕጣ የ10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0470132
2ኛ ዕጣ የ5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0914609
3ኛ ዕጣ የ 2.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0059544
4ኛዕጣ የ1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0600123
5ኛዕጣ የ1 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0430545
6ኛ ዕጣ የ500 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ ቁጥር -0057083
እና በርካታ ዕጣዎቸ የወጡ ሲሆን የማስተዛዘኛ ዕጣ ቁጥር 5 በመሆን ወጥተዋል ፡፡
እድለኞችን ሚሊየነር ሊያደረግ አምስተኛው አድማስ ዲጂታል ሎተሪ መውጫው ቀን ደረሰ!
እስከ ታህሳስ 22 በቴሌብር መተግበሪያ፣ በ*127# ወይም 605 ላይ A ብለው በመላክ በ3 ብር እድልዎን ይሞክሩ!
ኢትዮ ቴሌኮም እና የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በአጋርነት
የሀረር ከተማ ነዋሪ አቶ ጥላሁን ሀይሌ የ600,000ብር ቼክ ተረክበዋል።
አቶ ጥላሁን ሀይሌ ባለትዳርና የ5 ልጆች አባት ሲሆኑ ህዳር 1 /2015ዓ.ም በወጣው 1972ኛ መደበኛ ሎተሪ በአንደኛ እጣ የስድስት መቶ ሺህ ብር እድለኛ ሆነዋል።
አቶ ጥላሁን በጡረታ ገቢ የሚተዳደሩ ሲሆን በደረሳቸው ገንዘብ ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር ማቀዳቸውን ተናግረዋል።
ታህሳስ 13 ቀን 2015 የወጣው የመደበኛ ሎተሪ የወጡ የዕጣ ቁጥሮች
Читать полностью…በብሔራዊ ሎተሪ ታሪክ ሎተሪ ደግሞ ደጋግሞ ከደረሳቸው ባለእድለኞች መካከል የ13 ጊዜ እድለኛ የጎንደር ከተማ ነዋሪ አቶ መሃመድ አብደላ ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በቅርቡም ደግሞ ከአንዴም ሶስት ጊዜ እድለኛ የሆኑት በአዲስ አበባ ከተማ ላፍቶ ክፍለከተማ ነዋሪ አቶ መሃመድ ሰይድ ህዳር 07 በወጣው የልዩ እድል ሎተሪ የ5 ሚልየን ብር እድለኛ ሆነዋል፡፡
አቶ መሃመድ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ሲሆኑ በወጋገን ባንክ አክሲዮን ማህበር በሹፍርና ሞያ ያገለግላሉ፡፡
አቶ መሃመድ በደረሳቸው ገንዘብ ቤት ለመግዛት ማቀዳቸውን ገልፀው ሁሉም ሰው ሎተሪን ደጋግሞ በመቁረጥ እድሉን ሊሞክር ይገባል ብለዋል፡፡
ህዳር 23 ቀን 2015 ዓ.ም የወጣው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕድለኞች ሽልማታቸው ተረክበዋል ፡፡
Читать полностью…የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዓለምአቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ‹‹ሙስናን መታገል በተግባር››
በሚል መሪ ቃል በጅማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አከበረ፡፡ በባዓሉ የአስተዳደሩ የተለያዩ የስራ ኃላፊዎችና የማስተባበሪያው ሰራተኞች በተገኙበት ህዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተከብረዋል ፡፡
በርካታ ደንበኞች የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 005 ዕጣ መውጫን በተመለከተ ጥያቄዎች አቅርበዋል በመሆኑም የ አድማስ ዲጂታል ሎተሪ መደብ 005 ዓርብ ህዳር 23 / 2015 በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር በህዝብ ፊት የሚወጣ ሲሆን የወጡ የዕጣው ቁጥሮችም ወዲያው በቴሌግራምና ፌስቡክ አካውንታችን የምንለቅ መሆኑን እናሳውቃለን ፡፡ ለጥያቄዎቻችሁና አስታየቶቻችሁ እናመሰግናለን ፡፡
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር
ወ/ሮ ይልፋሸዋ ገ/ህይወት ይባላሉ በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ ለረጅም ዓመታት የሎተሪ ደምበኛ ናቸው ፡፡
በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም የቆረጧት የሎተሪ ቲኬት ግን ከተለመደው የሎተሪ ደምበኝነታቸው ለየት የምታደርግና በእንቁጣጣሽ ሎተሪ 4ኛ ዕጣ የ 3 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ የምታደርግ ነበረች ፡፡ ወ/ሮ ይልፋሸዋ ገ/ህይወትም የ3 ሚሊዮን ብር ቼካቸው ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ኃላፊዎች ህዳር 19 ቀን 2015 ዓ.ም ተረክበዋል ፡፡
የ3ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዕድለኞች
Читать полностью…በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ልዩ-ዕድል ሎተሪ ህዳር 7/ 2015 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሲሆን ለወዳጆቻችሁ በማጋራት ማውጫው እንዲደርስ አድርጉ፡፡ እናመሰግናለን!
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር!
ለጥንቃቄ !
አንዳንድ ህገ-ወጥ ግለሰዎች እና ድርጅቶች በዓይነትም ሆነ በገንዘብ ሽልማቶች እንደሚሸልሙ በማሰመሰል የሀሰት የቴሌግራም አካዉንቶች በመክፈት መረጃዎች እያሰራጩ መሆናቸውን ደርሰንበታል ፡፡ በመሆኑም ውድ የሎተሪ ደንበኞች ማንኛውም የሎተሪም ሆነ የእድል ሙከራዎች መረጃ ከብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ኦፊሻላዊ የቴልግራም እና ፌስቡክ አካውንቶች ብቻ እንድትጠቀሙ እየገለጽን የተሳሳተ መረጃዎች በማሰራጨት ህዝቡን የሚያጭበረብሩ ግለሰቦችም ሆነ ድርጅቶች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እያሳሰብን በዚህ ህገወጥ ስራ ለይ የተሰማሩ ህጋዊ እርምጃዎችን የምንወስድ መሆኑንም እንገልጻለን ፡፡
ትክክለኛ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አካውንቶች፡-
ፋስቡክ ፡- Ethiopian lottery / የኢትዮጵያ ሎተሪ/
ቴሌግራም/ ከ140 ሺ በላይ ተከታዮች ያሉበት/ ፡- National lottery administration/ ብሔረራዊ ሎተሪ አስተዳደር/
የብሔረራዊ ሎተሪ አስተዳደር